በክርስቶስ ( in christ)
866 subscribers
100 photos
34 videos
40 files
40 links
Who is ownership of kingdom
በዚህ ቻናል መንፈሳዊ አገልግሎት እና ጉዳዬች ላይ ይተኮራል @ownkin
Download Telegram
“በእግዚአብሔር ፈቃድ የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ የሆነ ጳውሎስ፥ በኤፌሶን ላሉት ቅዱሳን በክርስቶስ ኢየሱስም ላሉት ምእመናን፤”
  — ኤፌሶን 1፥1



  በኤፌሶን የሚገኘ ቅዱሳን
በክርስቶስ ኢየሱስ ያመኑ

አስገራሚ እውነት ነው ። ሁለት አድራሻ በዚህ ምድር ናቸው ደግሞ ሰማይ አሉ ። በኤፌሶን ናቸው ደግሞም በክርስቶስ ናቸው ።

በኤፌሶን ውስጥ ይኖራሉ በክርስቶስ ውስጥም ይኖራሉ ። በኤፌሶን እንደሚኖሩ ምድር መዝግባቸዋለች በክርስቶስ እንዳሉ ሰማይ መዝግቧቸዋል ።


   በክርስቶስ( inchrist ). in.ማለት ውስጥ ማለት ነው ።  in christ ክርስቶስ ውስጥ እንደማለት ነው ።

ምሳሌ እኛ በአብ ቀኝ አልተቀመጥንም ።ክርስቶስ በአብ ቀኝ ተቀምጧል እናም እኛ በክርስቶስ ወይም በክርስቶስ ውስጥ ስለሆን ተቀምጠናል ።እኛ ሳይሆን እሱ ስለተቀመጠ
በአዲስ ኪዳን መነቃቃት ሳይሆን መንቃት ነው ያለው ።

@ownkin
@cgfsd
በረከታችን በክርስቶስ ኢየሱስ ያገኘነው ማንነት ነው ።

@ownkin
@cgfsd
ኢየሱስ በእግዚአብሔር ዘንድ አንድያ ስለሆነ ውድ ልጁ ነው ። ልጁ በአባቱ ዘንድ ስለተከበረ እና ስለተወደደ የአባቱ ምርጥ ነው ።የሚደሰትበት እና የሚረካበት ውድ ልጁ ነው !!

@ownkin
@cgfsd
ብሩክ ትሁን ጌታን ያወኩበት ዕለት
ወንጌልን የተረዳሁበት
የክርስትና የጀርባ አጥንት የሚባሉ
 ፍቅር ፣እምነት ፣ተስፋ ነው ። እነዚህ ሶስቱ በምድር ያሉ በሰማይ የሚቀጥሉ ዘላለማዊ ናቸው ።

ጌታ እንድናምን ይፈልጋል ደግሞ በእምነት እንድናድግ እንድንጨምር ይፈልጋል ። በእኛ እና በጌታ መካከል የተደረገው ህብረት ኪዳናችን መያያዛች እምነት ነው ። እምነት እኔ እና እግዚአብሔር የተስማማንበት መስማሚያችን ነው ። እግዚአብሔር እና እኛ ሀ ብለን ህብረት እንድንጀምር ያያዘን ገመድ እምነት ነው። እግዚአብሔር ወደ እኛ ሊያደርሰው ያሰበውን ይቅርታ ፣ምህረት ፣በረከት የላከል በእምነት በኩል ነው  እኛም ከእግዚአብሔር የደረሱን ስጦታዎች በሙሉ በእምነት በኩል ነው ። እና እግዚአብሔር እምነት ያስደስተዋል ..በእምነት ደስ ይለዋል ። ለእርሱ ያለን እምነት እንዲበረታታ እንዳይቀዘቅዝ ይፈልጋል ። ከእምነት ወደ እምነት በእግዚአብሔር ላይ መደገፍ ፣መታመን እግዚአብሔር ላይ የሙጢኝ እንድንል ይፈልጋል ።


በቅዱሳን ዘንድ ያለ ፍቅር ..እግዚአብሔር ፍቅሩ ታላቅ ነው አካፍሎናል ። ያካፈልን ያጋራን ፍቅር እንድንለዋወጥ በሰጠን ፍቅር እንድንዋደድ ይወዳል ። ጌታ ኢየሱስ ከማረጉ በፊት ደቀመዛሙርቱን እየደጋገመ ሲናገር የነበረው አደራ አዘል ሀሳብ እርስ በእርሳችሁ ትዋደዱ ዘንድ ነው ። የቅዱሳን ቅዱሳን የሚያሰኘው ፍቅራቸው ነው ። ክርስቶስ ፍቅሩን ተቆርሶ አሳይቷል እኛም እርስ በእርስ ልንቆራረስ ይገባል ። ፍቅር horizontal እና vertical ነው ።  vertical  ከሰማይ ወደ ምድር የመጣ አጋፔ አምላክ እኛን የወደደበት ፍቅር ነው ። horizontal ደግሞ ቅዱሳን ከላይ የተቀበሉትን ፍቅር ወደ ጉን የሚያፈሱት ፍቅር ነው ።

ጳውሎስ ሁል ጊዜ ጌታን የሚያመሰግንበት ርዕሱ ለጌታ ያለ እምነት እና ለቅዱሳን ያለን ፍቅር ነው ።

@ownkin
@cgfsd
ኢየሱስ በአፅናፉ ታሪክ አንድ ጊዜ ብልጭ ብሎ የከሰመ ብርሃን ሳይሆን ብርሃናት ሳይፈጠሩ በፊት ያለ ብርሃን ከጠፉም በኋላ የሚቀጥል ዘላለማዊ ብርሃን ነው ።

Alex zetse'at

@ownkin
@cgfsd
በቅዱሳን ዘንድ ያለ ርስት ክብር ባለጠግነት !!!

ቅዱሳን በክርስቶስ አምነን የዳን እኛ ነን ። እርሱ ደግሞ ያለው በቅዱሳን ዘንድ ነው ።ማለት በእኛ ዘንድ ያለ ርስት ነው። የሚገርመው በቅዱሳን ዘንድ በእኛ መካከል ምን አይነት እርስ ይገኛል ።
እንግሊዘኛው በቅዱሳን ዘንድ ያለ his hesitance ይላል የእርሱ ርስት(ውርስ) እንደማለት ነው ።በቅዱሳን ዘንድ የእርሱ ርስት የእርሱ ውርስ ርስት አለ ማለት ነው ። የማን ርስት የእግዚአብሔር ነዋ ።እግዚአብሔር ርስት አለው የት በቅዱሳን ዘንድ አለ ። በቅዱሳን ዘንድ እግዚአብሔር ሊወሰርሰው ያዘጋጀው የእኔ ያለው ርስት አለው ያ ርስት በቅዱሳን ዘንድ ያለ ባለጠግነት ነው ። እግዚአብሔር ሊወርሰው ያዘጋጀው ርስት ቅዱሳን ናቸው ። የእግዚአብሔር ርስት ቅዱሳኑ ነው ።እግዘብሔርን ቅዱሳኑን ይወርሳል ። የቅዱሳኑ ርስት እግዚአብሔር የእግዚአብሔር ርስት ደግሞ ቅዱሳኑ ናቸው ።ስለዚህ በቅዱሳን ዘንድ ያለው ርስት እጅግ የከበረ ነው እሱ ርስት በቅዱሳን መካከል ያለ የእግዚአብሔር ርስት ነው ።ለዚህ ነው እግዚአብሔር ግድግዳ እና ቆርቆሮ ያልፈለገው ለግድግዳ ሳይሆን ለሰው የዋጋ የከፈለው ቅዱሳን ስለፈለገ ነው ። የቅዱሳኑ መኖሪያ እግዚአብሔር የእግዚአብሔር መኖሪያ ቅዱሳኑ ነው ።


በቅዱሳኑ ዘንድ ያለ ርስት ምን ያህል ባለጠግነት ነው !!(የእግዚአብሔር ርስት ነዋ)

@ownkin
@cgfsd
ኢየሱስ በአደባባይ አትስበኩ አትበሉ ። ኢየሱስ ክርስቶስ የሞተው ቤተክርስቲያን ሳይሆን አደባባይ ላይ ነው ።

ከገፅ የተወሰደ
ቃል ስጋ ሆኖ ድንኳን በመደኮኑ የተሻለ መቅደስ ተገኘ ። መቅደሱም ኢየሱስ ነው እግዘብሔር እና ሰው የሚገናኙበት ።

@ownkin
@cgfsd
ኢየሱስ ቤተመቅደስ እንዳንገባ የተከለከልነውን ቤተመቅደስ አደረገን ።

ከገፅ የተወሰደ

@ownkin
@cgfsd
በመዳኑ ደስ የሚሰኝ በእግዚአብሔር ልብ ውስጥ ያለው ብርቱ የማዳን ፍላጎት የተረዳ ነው ።

@ownkin
@cgfsd
በድሮ ዘመን መፀሀፍ ቅዱስ በተፃፈበት ጊዜ
ሁለት ሀገሮች ከከተማቸው ውጭ ወጥተው ጦርነት ያረጋሉ ።የተሸነፈ ወደኋላ የእግሬ አውጪኝ ይሸሻል ከተማው ገብቶ የከተማው በሮች ይጠረቅማል ። ያሸነፈው ደግሞ ሁለት ምርጫ አለው አሸንፊያለሁ ብሎ እየጨፈረ ወደ ሀገሩ መመለስ ወይም እየተከተሉ በሩን ሰብረው ገብተው መማረክ ብሎ መቆጣጠር ። የመጀመሪያው ድሉን ሙሉ አያረግም እንደው ጠላት የበለጠ እንዲጠናከሩ ጊዜ ይሰጣል ።ሁለተኛው ግን ድሉን ሙሉ ያረጋል ።

ቤተክርስቲያን የገሃነም ደጆች አይችሏትም ማለት እንዲህ ነው በክርስቶስ ድል አድርገናል ዲያቢሎስን ተሸንፏል እየዘመርን ሀሴት እያረግን መመለስ እንችላለን ነገር ግን ወደ ጠላት ወረዳ ሂደን ደጆች ሰብረን በጠላት ስር ያሉን ለክርስቶስ መማረከም ደግሞ እንችላለን ።ቤተክርስቲያን የገሃነም ደጆች አይችሏትም ስለዚልም ለክርስቶስ በጠላት ስር ያሉት ሰዎች ትማርካለች ።

@ownkin
@cgfsd