ቴዎድሮስ አብ (የትዝታው ወጣት)
142 subscribers
2 photos
3 links
ሠላም ወዳጆቼ የትዝታዉ ወጣት ነኝ

#ሙዚቃዎቼን
#ግጥሞቼን
# የተለያዩ ፅሁፎቼን በዚህ ቻናል ይከታተሉ
ለማንኛዉም አስተያየት @meryjan65
@casting113
Download Telegram
ማን ነኝ ልበላቸው ማን ብልስ ያምኑኛል
አንተ ማን ነው ያልከው ንገረኝ ጨንቆኛል
የአክስቴ ልጅ ናት ዘመድ ናት ባባቴ
ወይስ የልጅነት አብሮ አደግ ናት ጓዴ
ንገረኝ ማን አልከኝ ምንህስ አረከኝ
ዛሬ ደሞ ምን አልክ ማን ብለክ ሰየምከኝ
ለአንተ ባለኝ ፍቅር ባሪያክ አደረከኝ
ከትብያ ቆሻሻ በታች አሳነስከኝ
አጥቼ መስሎክ ነው ካንተ የበለጡ
ክብር ለሴት ማለት ጠንቅቀው የሚያውቁ
አንተን የመረጠክ ምክንያት ነው ልቤ
ፍቅርህን አገዘፍኩ ክብሬን ወዲያ ጥዬ
ለሰጠው ፍቅር ምላሽ ቢኖር መልስህ
አይቆጨኝም ነበር ምንም ብሆንልህ
ግና ላፈቀረ ልቤ ለሰጠህ ክብር
ረግጠህ ጥለ ሄድክ የወደዋላህን
አሁን ቢል ቤተሰብ አምጣልኝ እጮኛ
ያከበረው ወስዷል ከናቀው ክብረኛ
በማለት መልስ ስጥ እባክህ አደራ
ባገኝሽ ብዬ ነው አንቺን መጠበቄ
ልብሽ ጠፍሮ ይዞኝ ባንቺ መወሰኔ
ሌላ ላያሳየኝ በጨለማ ጋርዶ
ልቤ አንቺን ይላል በሰመመን ነጉዶ
ካሰኘው በሀሳብ ውቅያኖስ ወርውሮኝ
ዘልቆ ከጥልቀቱ ከአፈር ቀላቅሎኝ
መንጥቆ ይወጣል ከትዝታ ፈረስ
እኔም ከቅዘቴ ከሀሳቤ ስመለስ
ልብህ ያነገሳት ፈፅሞ ላታይክ
ለምንስ ማሰብህ ጭንቀትን ማብዛትክ
ብዬ አስባለው ግራ ቢገባኝ
ልቤን ለማስመለስ ድፍረት ቢያጥረኝ
ባይተዋር አረኩት ልቤን ገለልተኛ
ከሰውም አርቄ አረኩት ብቸኛ
ሰዎች ንገሩልኝ በሏት ታሞልሻል
ልቡን ወስደሽበት ለሞት ጫፍ ተቃርቧል
ግነትም አይደለም ሀቅ አለው በውስጡ
አይኖርም ተንፍሶ ልብን አንዴ ካጡ
የህይወቴ ተስፋ ዛሬ ይኸው መክኗል
የድሮ ደስታዬ በሙሉ ጨልሟል
ከዛች ቀን በኋላ ማንባት ነው ስራዬ
ሀዘን በኔ ነግሶ በቤት በጓዳዬ
...
የድሮግዜዬን በትዝታ እያየው
በናፍቆትህ ብዛት እየተሰቃየው
ኑሮ በማይሉት ህይወት እኖራለው
....
ተስፋዬንአጥቼ ሞት እየናፈቀኝ
ያሳለፍኩት ሁሉ ህልም እየመሰለኝ
ደግሞም በትዝታ ስጓዝ ወደ ኋላ
በጎጇችን ውስጥ ስንጠጣ ስንበላ
ድቅን ይልብኛል የሚያምረው ፍቅራችን
እንደዛ ተዋደን አብረን መኖራችን
....
ግን....ማዘንብቻ ነው ከ ሀሳቤ ስነቃ
አጠገቤ የለህ ነፍሴ እንዲ ተጨንቃ
መቼም ላትመጣ ዘውትር ምትናፍቀኝ
በ ኦናው ቤቴ ውስጥ ባዶ ቅኔ የምቀኝ
.....
ግንእስከመቼ ነው እንደዚህ ምኖረው
ባልኖረው አካልህ አንተን የማልመው
እስከመች ድረስ ነው???
የቀረብሽኝ ጊዜ

የሞቴ ጥላ ሸሽቶ እንትንፋሴ ተመለሰ፣
የወደኩበት ዳገት ሜዳማ ሆኖ ታረሰ፣
የሚያዳልጠኝ ሁሉ ሆኖልኝ መደገፊያ፣
ሆንሽልኝ ውብ ድልድዬ ጥላቻዬን ማለፊያ!!
እናም ንግሰቴ ሆይ ነሽና የልቤ ወደብ፣
ካ'ለሽበት አልቀርም ቢያንገላተኝም ወጀብ!!

የጠላሁሽ 'ለት

ሐገር ሁሉ ይጥላኝ ይትፋኝ አሽቀንጥሮ፣
ሞት ቀድሞ ያግኘኝ በሕይወት ቀጠሮ፣
ምርኩዝ ያልኩት ሁሉ ይሁነኝ እንቅፋት፣
ስንገዳገድ እንድኖር ይብዛብኝ መገፋት።

"ለምን?" ያልሽኝ እንደኹ

እኔ አንችን ጠልቼ ወደ ሌላ ስሄድ፣
ቀድሞ ነው 'ሚጥለኝ ያቀናኹት መንገድ።

የኩለ ሌ'ት ጥሪ

በጽልመት ድንኳኔ ብርሐን ለኩሰሽ፣
ለማቅ ደበሎዬ ግማጃሽን አልብሰሽ፣
በደውልሽ ውግረት ነፍሴን አስነቅተሽ፣
በካሕንሽ መረግድ ጥሞናዬን ነስተሽ፣
''ተነስ!'' ብትይኝም መ'ተሽ በ'ኩለ ሌ'ት፣
ግና አላወኩሽም ቅድስት ትሆኝ ማኅሌት!!

የሆነ ዘመን ላይ...

አእዋፋት 'ረበው በደመና ጣሪያ፣
ፍስኃ ሲደመጥ በሠማያት ዙሪያ፣
የፍቅር ቄጤማ በም'ድር ሲነሰነስ፣
እርግቦች ሲንሩ በእባቦች ማነስ፣
አበቦች ለንቦች በሃሴት ሲያብቡ፣
ንድፊያውን የቻሉ ማሩን ሲመገቡ፣
ኩሬዎቹ ሰፍተው ሲሆኑ ውቅያኖስ፣
ለፀሐይ ስትታጭ የጎጆይቱ ፋኖስ፣
ግርምታ ፈጥሮብሽ እንዳትጨነቂ፣
ይህ በሆነ ጊዜ...
የትንሳኤሽ ዘመን መቅረቡን እወቂ።
የመጠበቅ ቅኔ

የጽኑ ጎጆዬ ግድግዳው ፈራርሶ ፤
ባ'ጥ አሳቃይ ጠፍቶ ጣራው ተደርምሶ ፤
ጨረቃና ፀሐይ እንደ ጤዛ ሟምተው ፤
ሕፃን የነበሩት ከዋክብት አርጅተው ፤
የምድር አለቶች ......
ከመቆየት ብዛት ሆነው ደቃቅ አፈር ፤
ነፋስ አቅም አጥቶ ቆሞ ሲንፈራፈር ፤
የሊባኖስ ዝግባ ከስቶ ሳር አክሎ ፤
ውቅያኖስ በሚራዥ በውኃ ጥማት ከስሎ ፤
መላእክቶች ጃጅተው አክናፋቸው ዝሎ ፤
ይህን ሁሉ ችዬ...
ያንችን መምጣት ዘመን ስጠባበቅ እኔ ፤
እግዜር በመደመም ዓይኑን ጥሎ ካይኔ ፤
<<ፍቅር>> ብሎ ጻፈው....
ያለመታከትን የጥበቃን ቅኔ፡፡
ሲበርደን ኡ ኡ ታ
ሲሞቀን ኡ ኡ ታ
ሲርበን ኡ ኡ ታ
ስንጠግብ ኡ ኡ ታ
ስንጠማ ጩኸት
ስንጠጣ ጩኸት
ስንፋቀር ጩኸት
ስንጣላ ጩኸት
በድለንም ለቅሶ
ሲበድሉን ለቅሶ
ግራ ግብት አለው
እግዜሩ ጨርሶ
ሠላም ወዳጆቼ 🙏🙏🙏
በልምምድ ወቅት.......🎤🎤

መልካሙ ተበጀ (ስትወደኝ ስወዳት)🎹🎹
Audio
አዲስ የሙዚቃ ቪዲዮ በቅርብ ቀን ይጠብቁን
ማነዉ?
ምን አይነት ጉድ ነዉ?
እንዴት ሰራዉ?
ሲያምር!!!!!!!
የሚያስብል እና የተበደሉን ጆሮዎች የሚክስ ምርጥ ስራ👏👏👏👏👏👏

COMING SOON 😊😊😊😊