University
1.82K subscribers
912 photos
76 videos
18 files
203 links
እኛ ሁሉም ነገር መልካም ይሆናል ብለን እናምናለን!!
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#AddisAbaba

📍ቦሌ አትላስ አካባቢ የደረሰው አደጋ 9:20 አካባቢ በቁጥጥር ስር ማዋል ተችሏል።

ዛሬ ከሰዓት 8 ሰዓት አካባቢ ቦሌ አትላስ አካባቢ የሚገኙት የግንባታ ዕቃዎች መጋዘኖች ላይ ከፍተኛ የእሳት ቃጠሎ ተነስቶ በንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል።

የእሳት አደጋው በቅዱስ ዑራኤል ቤተ ክርስትያን እና በአትላስ እንዲሁም በፀጋ ሆስፒታል መሃል ላይ በሚገኙት የንግድ ሱቆች መጋዘኖች ላይ የደረሰው።

የአደጋው መነሻ እስካሁን አልታወቀም።

ቁጥራቸው 7 የሚደርስ የአዲስ አበባ ከተማ አደጋ ስጋትና አመራር ኮሚሽን እሳት አደጋ መከላከል ተሸከርካሪዎች የእሳት አደጋው ወደ ሌሎች አካባቢዎች አንዳይዛመት ከፍተኛ ጥረት አድርገዋል።

እሳቱ 9፡20 አካባቢ ማጥፋት ተችሏል።

የአካባቢው ነዋሪዎች በተለይም ወጣቶች እሳቱን ለማጥፋት ያደርጉት የነበረው ርብርብ የሚደነቅ እንደነበር ተገልጿል።

Credit : ETHIO FM 107.8
ቪድዮ : አቤል

@campus_life3
@campus_life3
ለቀጣይ ዙር የ2014 የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች;
።።።፡።።።።:::::
ፈተናው የሚሰጥበት ጊዜ እየተቃረበ መሆኑን አውቃችሁ በተዘጋጃችሁት ልክ ተረጋግታችሁ ለመስራት ጥረት እንድታደርጉ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

በተለይ በግጭት አካባቢ የነበራችሁ ተማሪዎች በብዙ ችግር ውስጥ ሁናችሁ ስትዘጋጁ እንደቆያችሁ ይታወቃል። ችግራችሁን በመገንዘብም ቀጣዩ ዙር ፈተና የተዘጋጀላችሁ መሆኑን በመገንዘብ ዕድላችሁን በአግባቡ እንድትጠቀሙበት ምክራችንን እንለግሳለን።

በአንደኛው ዙር ፈተና (በተለይ በማህበራዊ ሳይንስ ፈተና) ወቅት የተከሰቱት ችግሮች እናንተንም እንዳይገጥሟችሁ ማስታወስ ተገቢ ነው ብዬ ስላሰብሁ የሚከተሉትን ላጋራችሁ ወደድሁ:

1. በ2013 ተፈትነው ነገር ግን በድጋሚ በመደበኛው ኘሮግራም ለመፈተን እድል የነበራቸው የተወሰኑ ተማሪዎች(ሁሉንም ለማለት አይደለም) ሲያጠኑ ስላልከረሙ እና የተሻለ ውጤት ማምጣት የማይችሉ መሆናቸውን በመገመት የፈተና ስርዓቱን ለማወክ ባደረጉት ሙከራ እጅግ በርካታ ቁጥር ያላቸው እና ጥሩ ውጤት ለማስመዝገብ ተስፋ የነበራቸው ተማሪዎቻችን ከፈተና ተስተጓጉለውብናል። ይህ ድድርጊት እጅግ በጣም ስሜታችንን ጎድቶት አልፏል። በመሆኑም በቀጣይ እንዳይደገም ትምህርት መውሰድ ተገቢ ነው።

2. አንዳንድ ተማሪዎች ፈታኞችን ያልተገባ ንግግር በመናገር እና በማበሳጨት እንዲሁም የክፍል ፈተና ስርዓቱ እንዲረበሽ በማድረግ ፈታኞች ፈተናውን በችግር እንዲመዘግቡት የማድረግ ያልተገባ ግፊትም ተስተውሏል።

ይህ ድርጊት ምንጩ አስከአሁን ግልፅ ባይሆንም በተለይ ፈታኞች በሳል ሁነው ችግሩን በጥበብ ማለፍ ካልቻሉ ተፅዕኖው ቀላል እንደማይሆን ስጋት መፍጠሩ አልቀረም።

በጊዜው ሁሉም ቦታ ለመድረስ ባይቻልም መድረስ በቻልንባቸው የፈተና ጣቢያዎች ፈታኞችን ለማረጋጋት እና ድርጊቱ ውስን ቁጥር ያላቸው የተለዬ ፍላጎት ያላቸው ተማሪዎች ጉዳይ መሆኑን ተገንዝበው በትዕግስት የፈተና ስርዓቱን እንዲመሩት ለማግባባት ተሞክሯል። ሌሎች ያልደረስንባቸው ጣቢያዎች ሁኔታ ምንይመስል እንደነበር ግን እርግጠኛ መሆን አይቻልም። ፈታኞች ይህን ታሪካዊ ሀላፊነታቸውን በትዕግስት እና በጥበብ ተወጥተውት እና ለብዙሀኑ ተማሪዎች ሲባል የአንዳንድ ተማሪዎችን ያልተገባ ስነምግባር በትዕግስት አልፈውት እንደሚሆን እንጠብቃለን።

3. በተለይ ድብረታቦር ዩኒበርስቲ ላይ የተፈጠረው ያለመረጋጋት ተማሪዎች ተረጋግተው እንዲፈተኑ የሚያስችል ሁኔታ ነበር ብሎ ለማለት ያስቸግራል። የነበረው ሁኔታ ፈተና አቋርጠው በሄዱት ላይ ብቻም ሳይሆን በፈተና ሂደቱ ውስጥ በነበሩት ተማሪዎች ላይም ተፅዕኖው ከባድ እንደሚሆን ይገመታል።

በዚህም ሁከት እጅግ በርካታ ቁጥር ያላቸው ውጤታማ ተማሪዎቻችን ባላሰቡት መንገድ ተስተጓጉለውብናል።

በአጠቃላይ የመጀመሪያው ዙር ፈተና እንደሀገር የመጀመሪያ ከመሆኑም ጋር ተያይዞ ከትምህርት ሚኒስቴርም ሆነ ከት/ቢሮውም በኩል የነበሩ ከቅድመዝግጅት መጓደለም ጋር የተያያዙት መለስተኛ ችግሮች (በተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተና ወቅት ማስተካከያ የተደረገባቸው ችግሮች)ተጨምረውበት በርካታ ተማሪዎቻችን ከፈተና ስርዓቱ የተስተጓጎሉበት ሁኔታ መፈጠሩ የትምህርት ማህበረሰቡን እጅግ በጣም ያሳዘነ ክስተት ሆኗል።

የነበሩ የቅድመዝግጅት መጓደሎችን እና አጠቃላይ ሂደቱን በሚመለከት ለሚመለከተው አካል በጊዜው የግምገማ ሪፓርት ስላቀረብን እዚህ ላይ መዘርዘሩ አያስፈልግም።

በአጠቃላይ ከግምገማ ሪፓርታችንም ሆነ ከሌሎች ነባራዊ ሁኔታዎች በመነሳት ውሳኔ ሰጭው አካል የሚሰጠው ውሳኔ እንደተጠበቀ ሆኖ በቀጣዩ ዙር ፈተና የባለፋት ችግሮች በድጋሜ እናንተንም እንዳያጋጥሟችሁ ተገቢውን የጥንቃቄ ቅድመዝግጅት እንድታደርጉ ከወዲሁ እያሳሰብሁ መልካም የፈተና ጊዜ እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ!!

ማተብ ታፈረ(ዶ/ር)
የአብክመ ትምህርት ቢሮ ሃላፊ


የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@campus_life3
@campus_life3
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ውድ የCampus life channel ቤተሰቦች በዚህ ተወዳጅ channel ላይ ማንኛውን post ለመpost ፍላጎት ያለው 👉 @Ethio_send_bot በዚህ ያናግረን።

እኛ ሁሉም ነገር መልካም ይሆናል ብለን እናምናለን።
@campus_life3
@campus_life3
ለአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ መምህራን በሙሉ

በዩኒቨርሲቲው መምህራን ማኅበር ጥሪና ሰብሳቢነት በ24/3/2015 ዓ/ም በተካሄደው ስብሰባ በወጣው አቋም መግለጫ የተላለፈውን የመማር ማስተማር ሥራ የማቆምን ሃሳብ ዩኒቨርሲቲው የማያውቀው በመሆኑ ሁሉም መምህር እንደተለመደው በመደበኛ ክፍለ ጊዜው መሠረት መማር ማስተማር ሥራው ላይ እንዲገኝ ዩኒቨርሲቲው ይገልጻል፡፡

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት
@campus_life3
@campus_life3
ሀገር አቀፍ የምሁራን የምክክር መድረክ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል።

በመድረኩ የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)፣ ከመላ ሀገሪቷ የተውጣጡ ምሁራን እንዲሁም ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነት የምሁራን አበርክቶ እንዲሁም ለኢትዮጵያ ሰላምና መረጋጋት የምሁራን አስተዋፅኦ ላይ ውይይት እንደሚደረግ የወጣው መርሃ ግብር ያሳያል።

የምክክር መድረኩ በኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲና በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በጋራ የተዘጋጀ ነው።

@tikvahuniversity
@campus_life3
@campus_life3
የዩኒቨርሲቲው መምህራን እና ተማሪዎች ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሥራ ላይ መገኘታቸው ተገመገመ።
በዩኒቨርሲቲው የዕለቱ የመማር ማስተማር ሂደት ፍጹም ሠላማዊ ሆና ያለአንዳች የጸጥታ ስጋት መቀጠሉን ነው የዩኒቨርሲቲው ማኔጅመንት ከኮሌጅ/ትምህርት ቤት የሥራ ኃላፊዎች ጋር በመሆን የገመገመው።በዩኒቨርሲቲዎች መምህራን እና ቴክኒካል ረዳቶች ስም የተሰራጨውን የሥራ ማቆም አድማ አቋም የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር እንደማያውቀው ማሳወቁን በግምገማው ተጠቁሟል።
የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ለሰላማዊ መማር ማስተማር ሂደት መረጋገጥ ተገቢው ክትትል ሲያደግ መቆየቱ በግምገማው ተግልጿል።እንደ ሀገር በመምህራን እና በቴክኒካል ረዳቶች ሥም
የፖለቲካ አጀንዳ ያነገቡ ኢ-መደበኛ ኃይሎች የሚያራምዱት የሥራ ማቆም አድማ ፍጹም ተቀባይነት እንደሌለው ነው በመድረኩ የተገመገመው።

በመድረኩ ለሥልጣን ጥመኞች በር ከፍተን የትርምስ አጀንዳ አስፈያሚ መሆን የለብንም የተባለ ሲሆን፤ በአድማ፥ በአመጽ ፥በእምቢተኝነት እና ሀገር አፍራሽ ተልዕኮ በማንገብ ሳይሆን በትብብርና ተቀናጅቶ በመሥራት ነው ተቋምን ሆነ ሀገርን የሚያሻግረው ተብሏል።

በዛሬው ዕለትም የዩኒቨርሲቲው መምህራን እና ተማሪዎች ፍጹም ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሥራ ላይ መገኘታቸው በመድረኩ ተገመምግሟል።

ጥብቅ የቁጥጥር እና የክትትል ሥርዓትን በማጠናከር ለፍጽም ሰላማዊ መማር ማስተማር ሥራ መጎልበትና ተጠናክሮ መቀጠል በትብብር መስራት አለብን ተብሏል።

ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሥራ ለማረጋገጥና ለማዝለቅ የውስጥና የውጭ ተጋላጭነት መቀነስ፤ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት መሥራት፤ የህግ የበላይነት ማረጋገጥ እንዲሁም የተደራጀና ችግር ፈቺ ክትትልና ድጋፍ መስጠት የቅድሚያ ቅድምያ ተሰጥቶ እንደሚሠራ በግምገማው አቅጣጫ ተቀምጧል።
@campus_life3
@campus_life3
#ባንዲራ #አዲስአበባ

ዛሬ አዲስ አበባ ከተማ አዲስ ከተማ መሰናዶ ት/ቤት የሚገኙ ተማሪዎች የትምህርት ቤቱ አስተዳደር በአስገዳጅ ሁኔታ የክልል መዝሙር እንድንዘምር እና የክልል ባንዲራም እንድንሰቅል አያስገድደንም ከብሔራዊ የኢትዮጵያ ባንዲራ ውጪም የክልል ባንዲራ አንሰቅልም ሲሉ ተቃውሞ ያሰሙ ሲሆን ፖሊስ ተማሪዎችን እና ወላጆችን ሲደበድብ ተስተውሏል።

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@campus_life3
@campus_life3
ሰንደቅ አላማ ጋር በተያያዘ በተነሳ ግጭት የአንድ ተማሪ ህይወት አለፈ

በአዲስ አበባ ፈረንሳይ አካባቢ ልዩ ስሙ ጉራራ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ በሚገኘው፣ ከፍተኛ 12 ትምህርት ቤት ሰንደቅ አላማ ጋር በተያያዘ በተማሪዎች መካከል በተፈጠረ ግጭት የአንድ ተማሪ ህይወት ማለፉን አዲስ ማለዳ በወቅቱ በቦታው ከነበሩ ተማሪዎች ሰምታለች፡፡

ከትናንት በስተያ ኀዳር 27/2015 በኦሮሚያ ክልል ሰንደቅ አላማ ምክንያት በተማሪዎቸ መካከል በተከሰተው ግጭት፣ ከ10 በላይ የትምህርት ቤቱ ተማሪ የመቁሰል አደጋ ጋጥሟቸዋል ተብሏል፡፡ ከተማሪዎች በተጨማሪ አንድ የትምህርት ቤቱ መምህር መጎዳቱን አዲስ ማለዳ ምንጮች ጠቁመዋል፡፡

የግጭቱ መነሻ የኦሮሚያ ክልል ሰንደቅ አላማ በትምህርት ቤቱ በመሰቀሉ ቅሬታ ባደረባቸው ተማሪዎች፣ የሰንደቅ አላማውን መሰቀል በሚደግፉ ተማሪዎች መካከል በተፈጠረ ልዩነት ነው ተብሏል፡፡ በዚህም የሰንደቅ አላማውን መሰቀል የማይደግፉ ተማሪዎች እንዲወርድ ፍላጎት ሲያሳዩ፣ በአንጻሩ መሰቀሉን የሚደግፉት ደግሞ ሰንደቅ አላማው አይወርድም የሚል ውዝግ ውስጥ ገብተው እንደነበር ታውቋል፡፡

በግጭቱ ተሳታፊ ያልሆኑ ተማሪች ጭምር ከኹለቱም ወገን በሚወረወር ድንጋይ ቆስለዋል፡፡ በሰንደቅ አላማው ይሰቀላል አይሰቀልም ውዝግ በተነሳው ግጭት፣ ጉዳት ያስተናገዱ ተማሪችን ወደ ህክምና ተቋም ለመውስድ ኹለት አንቡላንሶች በትምህርት ቤቱ ተገኝተው ነበር፡፡

ሰንደቅ አላማውን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ት/ት ቤቶች እንዲሰቀል መንግሥት ከወሰነ በኋላ፣ የተለያዩ አካላት ውሳውን ሲቃወሙ ነበር፡፡ ከመቃወምም አልፈው ወደፊት ችግር ሊፈጥር ይችላል በማለት ስጋታቸውን ሲገልጹ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እስከ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የኦሮሚያ ክልል ሰንደቅ አላማውን በት/ት ቤቶች መሰቀሉን ይቀጥላል ከማለት ውጪ ያሉት ነገር የለም፡፡

(አዲስ ማለዳ)

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@campus_life3
@campus_life3
#Update

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በመላው ሀገሪቱ ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ከተውጣጡ ምሁራን ጋር ውይይት አድጥያቄዎችን

ተሳታፊዎች በመማር ማስተማር ሂደት ውስጥ እንዲሁም በሀገራዊ ልማት እንዲሁም በሰላምና ፀጥታ ጉዳዮች ላይ ጥያቄዎችን አቅርበዋል። ሰፊ ውይይትም ተደርጓል።

ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ምሁራኑ በተሻለ ደረጃ እንድትገኝ የሚመኟትን ሀገር ለመገንባት አስፈላጊውን ርብርብ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው አመላክተዋል።

ኢትዮጵያ እያጋጠሟት ያሉትን የተለያዩ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጫናዎችን በመገንዘብ ፍላጎቶቻቸውን ከነባራዊ ሁኔታዎች ጋር በማጣጣም እና የበሰሉ መፍትሄዎችን በማፍለቅ የበለጠ ሚና እንዲጫወቱ አሳስበዋል።

በተሳታፊዎች የተነሱ አንኳር ጉዳዮችን በተመለከተም የሚመለከታቸው አካላት ክትትል እንዲያደርጉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

ምንጭ፡- የጠ/ሚ/ር ጽ/ቤት
@campus_life3
@campus_life3
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ የ አራት ሀገራት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የ IPORA (interdisciplinary policy oriented research on Africa ) የሚባል ፕሮጀክት በጋራ ለመስራት በ ኮዲቯር አቢጃን የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ።

በዛሬው እለትም ይህንንውፕሮጀችት አስመልክቶ በ ኮትዲቫር ዋና ከተማ አቢጃን የ አራትዮሽ ሰምምነት ውይይት እየተካሃደ ሲሆን በዉይይቱ ላይ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሐናን ጨምሮ የፈረንሳይ ሃገር  ቦርዶ  ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት፣ የ Cote D'Ivoire ሀገር ፌሊክስ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት እና የ ሞሮኮ ራቫት ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ንግግር እና ማብራሪያ ሰተዋል።

የ IPORA ፕሮጀክት በፈረንሳይ ዩኒቨርሲቲ ቦርዶ የሚደገፍ እና ፖሊሲን ያማከለ አለማቀፍ እና ጥናታዊ የምርምር መድረኮችን የሚያዘጋጅ ፕሮግራም ነው።

ለ ፕሮጀችቱም ከ 8 ሚሊዮን ዩሮ በላይ ፈሰስ እንደሚደረግ ተገልጿል።

የአዲስ አበባ ዪንቨርስቲ የፈረንሳይኛ ቋንቋ ተናጋሪ አገራት ዪንቨርሲቲዎች ኔትዎርክ ጋር ሲሰራ ይህ የመጀመሪያው ጊዜ ነው።

@campus_life3
@campus_life3
#MoE

የትምህርት ሚኒስቴር ፤ የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና " ላልተገደበ ጊዜ " እንደሚሰጥ አሳውቋል።

የመውጫ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን የሚያገኙት ፈተናውን ወስደው ብቁ መሆናቸው ሲረጋገጥ ብቻ ነው ተብሏል።

ተማሪዎች ፈተናውን ደጋግመው መውሰድ የሚችሉበት ዕድል መመቻቸቱን በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ጥራትና ብቃት ማሻሻያ ዴስክ ኃላፊ ሰይድ መሀመድ ለኢፕድ ተናግረዋል።

የዩኒቨርሲቲ ቆይታቸውን ያጠናቀቁ ተማሪዎች በየስድስት ወሩ ፈተናውን የሚወስዱበት ዕድል እንዳለ ኃላፊው ጠቁመዋል።

የመንግስት ዩኒቨርሲቲ ተመራቂዎች ለአንድ ጊዜ ብቻ የፈተና ወጪያቸው እንደሚሸፈንላቸው ገልጸዋል።

በመንግሥትና በግል ተቋማት ላይ የሚሰጡ ከ300 በላይ የመጀመሪያ ዲግሪ የትምህርት ፕሮግራሞች እንዳሉ ያነሱት ኃላፊው፤ በየትምህርት መስኩ እየተደረገ በአስር ዙር ፈተናው ለመስጠት ታቅዷል።

@campus_life3
@campus_life3
የጓደኝነት ትክክለኛ ትርጉም ❤️

አልበርት የሮናልዶ ጓደኛ ነው። ሮናልዶ ስለ ጓደኛው እንዲህ ይላል፦

"ወዳጄን አልበርት ለስኬቴ ስላበረከተው አስተዋጽኦ ላመሰግነው እወዳለሁ። አብረን ለታዳጊዎች ቡድን ስንጫወት አንድ መልማይ ከስፖርቲንግ ሊዝበን ክለብ መጣ። ብዙ ጎል ያስቆጠረ ልጅ በአካዳሚው ተቀባይነት እንደሚያገኝ ነገረን።

ጨዋታውን 3-0 አሸነፍን። እኔ የመጀመሪያዋን ጎል ሳስቆጥር አልበርት ሁለተኛዋን አስቆጠረ። ሶስተኛዋ ጎል ሁሉንም ሰው አስገርማለች።

ጓደኛዬ አልበርት ከግብ ጠባቂው ጋር ፊት ለፊት ተገናኘ። እኔ ከጎኑ እየሮጥኩ ነበረ፣ አልበርትም ኳሷን በቀላሉ መረቡ ውስጥ መክተት እየቻለ ለእኔ አቀበለኝ እና ሶስተኛዋን ጎል አስቆጥሬ የሊዝበን አካዳሚ ተቀበለኝ።

ከጨዋታው በኋላ ለምን እንዲህ አደረክ፣ ለምን ራስህ ጎሏን አላስቆጠርክም?" ብዬ ስጠይቀው "አንተ ከኔ የተሻልክ ተጫዋች ነህ" ብሎ መለሰልኝ።"

ከብዙ አመታት በኋላ ጋዜጠኛው ሮናልዶ የልጅነት ጓደኛ አልበርት ቤት ሄዶ ታሪኩ እውነት እንደሆነ ሲጠየቀው የእግር ኳስ ህይወቱ በዚያ ጨዋታ እንዳበቃና እስከ አሁን ድረስ ያለ ሥራ እንደተቀመጠ ነገረው።

ጋዜጠኛው ፦ "ያለ ስራ እንዴት ቤት እና መኪና ልትገዛ እንዲሁም የተንደላቀቀ ሂወት ሊኖርህ ቻለ?" በማለት ጠየቀው።

አልበርት እንዲህ ብሎ መለሰ ፦

"ዕድሜ ለልጅነት ጓደኛዬ ክርስቲያኖ ሮናልዶ፣ የሱ ሥጦታ ነው፣ ዕድሜ ልኬን አመሰግነዋለሁ" ❤️🙏

@campus_life3
@campus_life3
ማስታወቂያ
ለ2014 ትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ (12ኛ ክፍል) ፈተና ተፈታኞች በሙሉ
የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት የተለቀቀ በመሆኑ ተፈታኞች ከዛሬ ጥር18 2015 ዓ.ም ከሌሊቱ 5፡30 ጀምሮ፡-
• በዌብ ሳይት https://eaes.edu.et/ ወይም
• በ6284 አጭር የጽሑፍ መልዕክት መላኪያ ላይ የምዝግባ ቁጥራቸውን (Registration Number) ብቻ በመላክ ወይም
• በቴሌግራም ላይ https://t.me/eaesbot
ማየት የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

ማሳሰቢያ፡-
• ማንኛውም ቅሬታ ያላቸው ተፈታኞች በአካል መምጣት ሳያስፈልግ እስከ ጥር 26/2015 ዓ.ም ድረስ በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዌብ ሳይት https://eaes.edu.et/ ላይ Compliant የሚለውን ማስፈንጠሪያ በመጫን ማቅረብ ይችላሉ፡፡
• የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አድራሻ ላይ ብቻ ይጠቀሙ፡፡ ከተመሳሳይ እና የተዛባ መረጃ ለማሰራጫት ከሚሞክሩ አካላት ራስዎን ይጠብቁ፡፡
የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት
ጥር 18/2015 ዓ.ም
አዲስ አባባ - ኢት
@campus_life3
@campus_life3
"ከፍተኛ የውጤት ማሽቆልቆል መከሰቱን ተከትሎ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ውይይት ላይ ይገኛሉ"

የ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ወደ ድኅረ ገጽ የመስቀል ሂደት የተጠናቀቀ ሲሆን ከዛሬ እኩለ ለሊት ጀምሮ ተማሪዎች ውጤታቸውን ማየት ይችላሉ ተብሏል።

አዲስ ማለዳ አረጋግጫለሁ ባለችው መረጃ መሰረት እጅግ ከፍተኛ የውጤት ማሽቆልቆል መከሰቱን እና ወደ 28 ሺህ የሚጠጉ ተማሪዎች ብቻ ከ300 በላይ ማምጣታቸውን ተከትሎ በልዩ ሁኔታ ዩኒቨርሲቲዎች መቀበል የሚችሉትን ያህል ተማሪዎች መቀበል እንዲችሉ እንዲደረግ እና ለማለፊያ ተቀራራቢ ውጤት ያላቸው ተማሪዎች ደግሞ የማጠናከሪያ ትምህርት ተሰጥቷቸው በእንዲገቡ የሚደረግበት መንገድ መተግበር የሚችል እንደሆነ ባለስልጣናቱ ውይይት ላይ መሆናቸውን አረጋግጫለሁ ስትል አዲስ ማለዳ ዘግባለች።

🛎 መረጃው ከአዲስ ማለዳ የተገኘ ነው 🛎

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@campus_life3
@campus_life3
ለመውጫ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎቻችን በሙሉ
#ሰኞ ሐምሌ 03/2015 ዓ.ም የሚኖር የፈተና መርሃግብር
#session One: ከጧት 2:30-5:30
#Session Two: ከቀኑ 6:30-9:00
#Session Three:  ከቀኑ 9:30-12:00 ድረስ መሆኑን አውቃችሁ ዝግጁ እንድትሆኑ እናሳውቃለን!

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉ።
@campus_life3
@campus_life3
ውድ የሪሜድያል ተማሪዎቻችን በሰላም ወደየቤታችሁ ግቡ !!
ለውጤታችሁ መልካም እድልን እየተመኘን
ቀጣን ምርጫችሁን ዩኒቨርሲቲያችንን እንደምታደርጉ ተስፍ እናደርጋለን።

ወ.ሶ.ዩ እውቀትን በተግባር!
የወ.ሶ.ዩ ተ/ህ ጽ/ቤት

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@campus_life3
@campus_life3
ማሳሰቢያ

ሐምሌ 3-7/2015 የሚሰጠውን የመውጪያ ፈተና የምትወስዱ ተመራቂ ተማሪዎች የሚከተሉትን ጉዳዮች ተፈጻሚ እንድታደርጉ እናሳስባለን።

1. በማስፈጸሚያ መመሪያ ላይ እንደተመለከተው ተፈታኞች ወደ መፈተኛ ላቦራቶሪ ስትመጡ ማንኛውም ስልክ-ስማርት ዋች(ሰዓት)፤ ታብሌት ላፕቶፕና ወዘተ ተመሳሳይ ቁስ መያዝ የተከለከለ ነው

2. ፈተና ከመጀመሩ ከሰላሳ ደቂቃ በፊት መፈተኛ ክፍል(ላቦራቶሪ) ላይ እንድትገኙ (ጧት ከ2፡00 በፊት ፤ ከሰዓት 8፡00 በፊት ) ቀድማችሁ እንድትገኙ እናሳስባለን

3. User name and Password lower-case and upper-case ፊደላትን
ለይታችሁ በጥንቃቄ እንድትይዙ እናሳስባለን

4. ከፈተና ቀን አንድ ቀን ቀደም ብሎ የእለቱ ፈተና እንዳለቀ መፈተኛ ላቦራቶሪ ላይ ስማችሁ ስለሚለጠፍ አስቀድማችሁ እንድትመለከቱ እናሳስባለን

5. ሁሉም ተፈታኝ መታወቂያ ይዞ መገኘት አለበት

6. የፈተና ድንብ አክብራችሁ እንድትፈተኑ እናሳስባለን።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@campus_life3
@campus_life3