መጋቢት 12 ፦ ኢአማኒ የነበረውን ቂሶንን ወደ ክርስትና የመለሰበት ቀን ነው፡፡
ሚያዝያ 12 ፦ ነብዩ ኤርሚያስን በአመጸኛው ሴዴቅያስ ከተጣለበት የቆሻሻ ጉድጓድ ያወጣበት ቀን ነው፡፡
ግንቦት 12 ፦ ወደ ነብዩ ዕንባቆም ተልኮ ዕንባቆምን በባቢሎን ዳንኤልን በአንበሳ ጉድጓድ በተጣለበት ጊዜ ምግብ እንዲያደርስለት ከምድረ ፍልስጥኤም በተአምር ተሸክሞ ፋርስ አውርዶት ዳንኤልን የረዳበት ቀን ነው፡፡
ሰኔ 12 ፦ ቅድስት አፎሚያን ከሰይጣን የታደገበት ቀን ነው፡፡ ባሕራንንም የሞቱን ደብዳቤ አጥፍቶ፣በሠርግ ተክቶ ተአምር እንደሰራለት ድርሳኑ ይነግረናል፡፡
ሐምሌ 12 ፦ እግዚአብሔር የይሁዳ ንጉሥ የሕዝቅያስን ጸሎት ሰምቶ ቅዱስ ሚካኤልን ልኮለት ከሰናክሬም መቅሰፍት ኢየሩሳሌምንና የይሁዳ ሰዎችን ያዳነበት ቀን ነው፡፡
ነሐሴ 12 ፦ ንጉሡ ቆስጠንጢኖስን የረዳበት፤አርባ ዘመን ቤተ ክርስትያንን ሲያቃጥሉ ክርስትያኖችን በእሳት ሲማግዱ፣በሰይፍ ሲያርዱ የነበሩትን ዲዮቅልጥያኖስንና መክስምያኖስን ከምድረ ገጽ ያጠፋበት ቀን ነው፡፡
ሺህ በክንፉ ሺህ በአክናፉ ሊቀ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል በብርሃናዊ ክንፉ አቅፎ ደግፎ ከክፍ ነገር ይሰውረን፡፡ የቅድስት አፎሚያ፣የቅዱስ ላሊበላ ጸሎት በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን፡፡
ሼር በማድረግ ለወዳጆ በቅዱስ ሚካኤል ስም ይዘክሯቸው፡፡
ሰኔ 12/10/2017 ዓ.ም

🙏1
ሰኔ 12 ቀን ቅዱስ ሚካኤል ደገኛዋን ቅድስት አፎሚያን ከሰይጣን ተንኮል የታደገበት ዕለት እንደሆነ ድርሳኑ መዝግቦልናል፡፡
❤1🙏1