የ ቡቱ መጣጥፍ ✍️🌤📖📖📒📔📓
155 subscribers
50 photos
8 videos
10 files
10 links
Download Telegram
መልመድ ነው ሰው መሆን

በውሽክሽክ አለም ታስሮ በማይረጋ
ያንተን ቀለም ስታውቅ ባሳብ ስትወጋ
አጊንተህ ላትኖረው እራስህን ፍለጋ
ስትምስ ስትዳክር ብትኖር ስትፈጋ
ህይወት እንደምድር
በኖርክበት ሳይሆን ባዙሪቷ ድምር
ደርሳ ስትዘቀዝቅ ደሞ ደርሳ ስትንር
ሃይልህ ሁሉ አልቆ ወኔህ ደቆ ቦክቶ

የተስፋ ጥበቃህ ረግፎ ተንኮታኩቶ
ፀዳሉ ተገፎ ጨለማ በርክቶ
ስታይ ባዶው ጎልቶ
አለም ከንቱ ማለት የት ይቀራል ከቶ
ዳሩ ግ ን በመናወጥ አለም
ቀለምህን መርጠህ ቆመህ ብትፋለም
ብትረታም ብትወድቅ እጣህን ካልክ አሜን
ከዳዴ እስከ ሩጫ መልመድ ነው ሰው መሆን
ደሞ ሰው ስትሆን
መርጠህ እንዳልመጣህ መርጠህ አትኖርም
የመኖር ገፅታ ቢፈካ ቢጠቁርም
ሰው መሆን አይቀርም
ምን ቢቆይም ታሞ
ነግቶ እንዳልቀረ ከቶ አይቀር ጨልሞ
ተንገዛግዞ እንጂ አለም ደስታ አዝግሞ
መኖር አያውቅ ቆሞ


#Butu
👍31💅1
የወዳጁ መሞት እንዳስተከዘው ሰው
የዚ ሰሞን መልኬ ጭምት ኩርምት ነው
ስጓጓለት ማውቀው አንዱም ጣእም የለው
የኖርሁ ያለፍኩት ሁል ከሬትም ጎምዝዟል
ብቻ እንዲው ስስለው መኖር ይበቃኛል


#እድሜ አለም
😢21💅1
Ummon Hiyonat with English Lyrics
Hi girl 🙌 I have some tip for you. If you love someone and they love you back, keep spreading the love.ካልወደድሽው እና ልታፈቅሪው ካልቻልሽ tell them that you don't love them and apologize for not being able to accept their love. "Don't say anything else " , don't pretend to be close to them. የውነት እራቂው ስታፈቅሪውም የውነት አፍቅሪው እንዲ እንዲዘፍን አታድርጊው "

#melka
🥰4😁2💅1
#የተሰበረ ልብ

የተሰበረ ልብ የተበሳ ፊኛ
መንሳፈፍን አይቶ ከመሬት የተኛ
የተሰበረ ልብ . . . . . .
ንፋስ የማያምን ማይሞክር ዳግመኛ
ለፍርድም ለሸንጎ የማይሄድ ከዳኛ
አልቃሻ አኩራፊ ሲለው ቸልተኛ
ትግልን ያቆመ ዝምታው ሃይለኛ
ለተሰበረ ልብ ከእንባ እና ሳግ ወዲያ የለው አማረኛ ።

#Bitu
21/08/2017
👍4🔥2💅1
እንደመፍራት ተስፋ እንደማጨለም ቶሎ መፅናናት ቢቻል ምን ነበረበት 😟
😢4💅1
ከቲክቶክ መንደር
ትንሽ ቁም ነገር
🫶
🥰4💔3💅1
እንኳን ለበዓለ ልደታ ለማርያም አደረሰን አደረሳችሁ።
2💅1
ማንበብ መልኬ ነው 😌😊
💅2
ማንበብ መልኬ ነው
💅2
የስርቻው መጣጥፍ.pdf
6.4 MB
ተመችቶኛል ቅመሱት
💅1
ቀኑ የአባቶች ቀን ነው እናም አባት ማለት ጋሻ ፣ መከታ እና መሸሸጊያ ነው ፤ በምድር ላይ ከተሰጡን ልዩ ስጦታዎች ውስጥ አንዱ አባትነት ነው ፤ እና ዛሬ እነሱን የምናከብርበት ፣ የምናመሰግንበት ቀን ነው ።

ለአባቶች ቀን በሰላም አደረሳችሁ ፤ ለቻናላችን ቤተሰብ አባቶች በሙሉ እንኳን አደረሳችሁ።
1👍1🫡1
መጋቢት 12 ፦ ኢአማኒ የነበረውን ቂሶንን ወደ ክርስትና የመለሰበት ቀን ነው፡፡

ሚያዝያ 12 ፦ ነብዩ ኤርሚያስን በአመጸኛው ሴዴቅያስ ከተጣለበት የቆሻሻ ጉድጓድ ያወጣበት ቀን ነው፡፡

ግንቦት 12 ፦ ወደ ነብዩ ዕንባቆም ተልኮ ዕንባቆምን በባቢሎን ዳንኤልን በአንበሳ ጉድጓድ በተጣለበት ጊዜ ምግብ እንዲያደርስለት ከምድረ ፍልስጥኤም በተአምር ተሸክሞ ፋርስ አውርዶት ዳንኤልን የረዳበት ቀን ነው፡፡

ሰኔ 12 ፦ ቅድስት አፎሚያን ከሰይጣን የታደገበት ቀን ነው፡፡ ባሕራንንም የሞቱን ደብዳቤ አጥፍቶ፣በሠርግ ተክቶ ተአምር እንደሰራለት ድርሳኑ ይነግረናል፡፡

ሐምሌ 12 ፦ እግዚአብሔር የይሁዳ ንጉሥ የሕዝቅያስን ጸሎት ሰምቶ ቅዱስ ሚካኤልን ልኮለት ከሰናክሬም መቅሰፍት ኢየሩሳሌምንና የይሁዳ ሰዎችን ያዳነበት ቀን ነው፡፡

ነሐሴ 12 ፦ ንጉሡ ቆስጠንጢኖስን የረዳበት፤አርባ ዘመን ቤተ ክርስትያንን ሲያቃጥሉ ክርስትያኖችን በእሳት ሲማግዱ፣በሰይፍ ሲያርዱ የነበሩትን ዲዮቅልጥያኖስንና መክስምያኖስን ከምድረ ገጽ ያጠፋበት ቀን ነው፡፡

ሺህ በክንፉ ሺህ በአክናፉ ሊቀ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል በብርሃናዊ ክንፉ አቅፎ ደግፎ ከክፍ ነገር ይሰውረን፡፡ የቅድስት አፎሚያ፣የቅዱስ ላሊበላ ጸሎት በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን፡፡

ሼር በማድረግ ለወዳጆ በቅዱስ ሚካኤል ስም ይዘክሯቸው፡፡

ሰኔ 12/10/2017 ዓ.ም
🙏1
ሰኔ 12 ቀን ቅዱስ ሚካኤል ደገኛዋን ቅድስት አፎሚያን ከሰይጣን ተንኮል የታደገበት ዕለት እንደሆነ ድርሳኑ መዝግቦልናል፡፡
1🙏1