Buna Tech ቡና ቴክ
284 subscribers
777 photos
51 videos
13 files
220 links
Welcome to our Buna Technology.
It's a channel where you find the amazing and new things about Computer and technology and get a variety of funny surprises and you get knowledge. Thanks 🙏
Download Telegram
Google Messages

ስልካችሁ ላይ Default messaging app የምትጠቀሙት Google messages ከሆነ አንዳንድ መልዕክቶች ወይም short codes አይገቡላችሁም። ይህ የሚሆነው spam ስለሚያደርገው ስለሆነ ይህን check ለማድረግ።

Profile ላይ ከገባችሁ በኋላ spam and blocked የሚል ምርጫ አለ። እሱን ስትከፍቱ spam ናቸው ያላቸውን ተዘርዝረው ታገኛላችሁ።

የምትፈልጉትን መርጣችሁ ከspam ማውጣት ትችላላችሁ።
👍1
Forwarded from NETRO TECH -AM (ⓃⒶⓇⒹⓄⓈ🇪🇹)
ስለ 'ኮምፒውቲንግ'፣ 'ቶን' እና 'ዌብ3'
የበለጠ ለመረዳት ።👇👇👇👇

1. ኮምፒውቲንግ (Computing)
● በቀላሉ: 'ኮምፒውቲንግ' ማለት መረጃን በኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች (እንደ ኮምፒውተር) ማስላት፣ መተንተን እና ማቀናበር ማለት ነው።
● ምሳሌ: ስልክዎ ወይም ኮምፒውተርዎ ሲደመር፣ ሲቀነስ፣ ቪዲዮ ሲያሳይ ወይም የፌስቡክ መልእክት ሲልክ... ያ ሁሉ 'ኮምፒውቲንግ' ነው። 'ኮኩን' የሚሠራውም የኤአይ ስሌቶችን የማስላት (Computing) ሥራ ነው።

2. ቶን (TON - The Open Network)
● በቀላሉ: 'ቶን' ማለት በቴሌግራም መስራች (ፓቬል ዱሮቭ) የተጀመረ ፈጣን እና ትልቅ አቅም ያለው የብሎክቼይን (Blockchain) አውታረ መረብ ነው።
● ዋናው ነገር: ልክ እንደ ቢትኮይን (Bitcoin) ወይም ኢቴሬም (Ethereum) 'ቶን' የራሱ ዲጂታል ገንዘብ (ቶከን) አለው። 'ቶን' በአብዛኛው ከቴሌግራም ጋር የተገናኙ አገልግሎቶችን ለመሥራት እና ገንዘብ ለመላክ የሚያገለግል ነው።
● በኮኩን ውስጥ ያለው ሚና: ቀደም ብለን እንዳየነው፣ የጂፒዩ አቅም የሚያዋጡ ሰዎች እንደ ሽልማት የሚቀበሉት ገንዘብ 'ቶን' ነው።

3. ዌብ3 (Web3)
● በቀላሉ: 'ዌብ3' ማለት የኢንተርኔት ቀጣይ ምዕራፍ ወይም ትውልድ ማለት ነው።
🤔 ምን ማለት መሰላችሁ:

● ዌብ1 (የቀድሞው ኢንተርኔት): መረጃን ብቻ ማንበብ የሚቻልበት (ለምሳሌ፡ ጋዜጣ ማንበብ)።
● ዌብ2 (አሁን ያለንበት): መረጃን መጻፍ እና ማጋራት የሚቻልበት (ለምሳሌ፡ ፌስቡክ፣ ዩቲዩብ፣ ትልልቅ ኩባንያዎች የሚቆጣጠሩት)።
● ዌብ3 (አዲስ የሚመጣው): ያልተማከለ (Decentralized) ኢንተርኔት ነው። ማለትም ትልልቅ ኩባንያዎች ብቻ ሳይሆን ተጠቃሚዎች ራሳቸው ኢንተርኔቱን የሚቆጣጠሩበት፣ ግላዊነት የተጠበቀበት እና በብሎክቼይን (እንደ ቶን ባሉ) ላይ የተመሠረተ አዲስ አሰራር ነው።
➽ ማጠቃለያ: 'ዌብ3' ማለት ግላዊነት ያለው፣ ያልተማከለ እና ለሁሉም ክፍት የሆነ አዲስ የበይነመረብ ዓለም ነው።
1
ዛሬ፣ ሕይወታችን ከሞባይል ስልኮቻችን፣ ከማኅበራዊ ሚዲያዎቻችን እና ከኮምፒውተሮቻችን ጋር ተቆራኝቷል። ስለዚህ የዲጂታል ደህንነታችን የህልውና ጉዳይ ሆኗል።
የደህንነት ኦዲት የሚጀምረው ከንቃተ-ህሊና ነው። ለምን? ምክንያቱም ጥናቶች እንደሚያሳዩት የሳይበር ጥቃቶች ከ80% በላይ የሚሆኑት የሚከሰቱት በሰው ስህተት (Human Error) ነው።
ጠላፊዎች ቴክኖሎጂውን ሳይሆን ሰውን ማጥቃት ይቀላቸዋል—የይለፍ ቃልዎን እንዲሰጡ በማግባባት ወይም አደገኛ ሊንክ እንዲጫኑ በማድረግ። የሳይበር ደህንነት ግድግዳችን የቱንም ያህል ጠንካራ ቢሆን፣ አንድ የማያውቁት ሊንክ ወይም ግድየለሽነት ሁሉንም ሊያፈርስ ይችላል።
ComingSoon
Forwarded from NETRO TECH -AM (ⓃⒶⓇⒹⓄⓈ🇪🇹)
#info

ስለ "ክሎድ" (Claude) እና የሆስፒታል ሂሳብ ቅነሳ ታሪክ
​አንድ ሰው 195,000 ዶላር የነበረበትን የሆስፒታል ሂሳብ በክሎድ (Claude) የተባለውን ሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) መሳሪያ ተጠቅሞ እስከ 33,000 ዶላር ድረስ እንዲቀንስ አደረገ።
● ​ጠበቃም ሆነ የሆስፒታል ሰራተኛ ሳይጠቀም

●​በወር 20 ዶላር ብቻ የሚያስከፍለውን የክሎድ ፕላስ አገልግሎት በመጠቀም።

እንዴት?
ሰውየው ዝርዝር የሆስፒታል ክፍያ ደረሰኙን ለክሎድ ሰጠው። ክሎድም፡

● ​ተደራራቢ ኮዶችን (duplicate codes)፣
●​ ህገ-ወጥ ድርብ አከፋፈልን (illegal double billing)፣እና

● ​በመንግስት የጤና መድህን ህጎች (Medicare rules) በግልጽ የተከለከሉ ክፍያዎችን ለየለት።

●​ ከዚያም ሞዴሉ ሁሉንም ጥሰቶች በህግ ቋንቋ በመጥቀስ መደበኛ የይግባኝ ደብዳቤ አዘጋጀለት።

➛​ውጤቱ: ሆስፒታሉ የክፍያ ጥያቄውን በ83% ቀንሷል።

​ይህ ምን ማለት ነው?
​ ይህ የሚያሳየው AI ምን ያህል ለውጥ ማምጣት እንደሚችል ነው። ለረጅም ጊዜ ሆስፒታሎች፣ መድን ሰጪዎች እና የህግ ድርጅቶች ከሂደቱ ውስብስብነት እና ከጥቃቅን ህጎች ተጠቅመው ቆይተዋል።
ክሎድ ግን ለአንድ ግለሰብ ልክ እንደ አንድ የክፍያ እና የህግ ክትትል ቡድን (compliance team) ተመሳሳይ የትንታኔ ኃይል ሰጠው።

​AI ሰራተኞችን ከመተካት ባለፈ፣ ስርአቶቹን እኩል እንዳይሆኑ ያደረገውን ግልጽነት ማጣት (opacity) እያጠፋው ነው።

ምን ትላችሁ ወገን👍

For more join channel ➛ @netrotech9
👍1
ነጻ የማማከር እና ኦዲት ለ12 ሰዎች ብቻ

ፈጥነው ይመዝገቡ ለመመዝገብ
1. በTiktok እና Facebook አካውንቴን Follow ማድረግ
2. Screenshot በማድረግ በቴሌግራም አድረሻ @bunasupport ላይ መለክ

ለማግኘት +251786675646 ላይ ብቻ ይደውሉልን ።
ነጻ የማማከር እና ኦዲት ለ12 ሰዎች ብቻ

ፈጥነው ይመዝገቡ ለመመዝገብ
1. በTiktok እና Facebook አካውንቴን Follow ማድረግ
2. Screenshot በማድረግ በቴሌግራም አድረሻ @bunasupport ላይ መለክ

ለማግኘት +251786675646 ላይ ብቻ ይደውሉልን ።
👍1
#እንድታውቁት

በኢትዮ ሳት የሚሰራጩ የሳተላይት ሥርጭቶች በሙሉ ከሰዓታት ጀምሮ እየሰሩ አይደለም።

በዚህ ጉዳይ አርትስ ቴሌቪዥን የሚከተለውን አስፍሯል ፦

"የሳተላይት አገልግሎት አጋራችን በእስራኤል ውስጥ ባጋጠመው ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት መቆራረጥ ምክንያት ሥርጭታችን ተቋርጧል።

በመሆኑም ችግሩን ለመፍታት ከቴክኒክ ባለሙያዎቻችን እና የሳተላይት አገልግሎት አቅራቢያችን ጋር በመሆን በሙሉ አቅማችን እየሠራን እንገኛለን።

ለተፈጠረው የሥርጭት መቋረጥ ይቅርታ እየጠየቅን በተቻለ ፍጥነት ወደ ሥርጭት የምንመለስ መሆኑን እንገልፃለን።"

Via TikvahethMagazine
Telegram update!!

Telegram የmessage input bar and bottom panel update ተደርጓል።

Better microphone/voice message UI
New chat bar design
New reactions or stickers
New formatting tools
New attachment layout (cleaner icons)
New emoji panel improvements
Faster keyboard opening

update አድርጉና ሞክሩት።
#telegram_update
የኬንያ መንግስት የሳይበር ጥቃት ተፈፀመበት።

በኬንያ በተፈጸመ የሳይበር ጥቃት የፕሬዚዳንቱን ፅህፈት ቤት ጨምሮ የበርካታ ሚኒስቴሮች ድረ-ገጽ ተጠልፎ የነበረ ሲሆን ከሰዓታት በኋላ ዳግም ተመልሷል።

በዚህ የተቀናጀ የሳይበር ጥቃት የፕሬዚዳንቱን ጽህፈት ቤት ጨምሮ የጤና፣ የትምህርት፣ የስራ፣ የአካባቢ፣ የሃገር ውስጥ፣ የቱሪዝምና የቴክኖሎጂ ሚኒስቴሮች ድህረገጽ መጠለፉ ተነግሯል።

ድረ-ገጾቹ መጠለፋቸውን ተከትሎ በድሀረገፆቹ ላይ "Access denied by PCP", "We will rise again", "White power worldwide", and "14:88 Heil Hitler" የሚል ፅሁፍ ታይቷል።

ድህረገፆቹ ከተጠለፉ በኋላም መንግስት በኦንላይን የሚሰጣቸው አገልግሎቶች አቋርጦ ቆይቷል።

የመከላከያ እና የገንዘብ ሚኒስቴር በጥቃቱ ሰለባ አልሆኑም ሲባል ለጥቃቱ ኃላፊነቱን የወሰደ ቡድን እስካሁን የለም።

በ2023 በኬንያ መንግስታዊ ተቋማት ላይ ተመሳሳይ ጥቃት ደርሶ የነበረ ሲሆን የሱዳን የመረጃ መዝባሪዎች ቡድን ኃላፊነቱን ወስዶ ነበር።

VIA #TikvahethMagazine
Forwarded from NETRO TECH -AM
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#info
💡 አዲስ የGoogle ፕሮጀክት: ብዙ ወኪሎች (Multi-Agents)
​Google ሃሳቦችን በጥብቅ በውድድር መልክ በማወዳደር የሚያጣሩ ብዙ ወኪሎች (multi-agent systems) ላይ እየሰራ ነው።
➛ ​እያንዳንዱ ሂደት 40 ደቂቃ የሚወስድ ሲሆን፣ በአንድ የምርምር ርዕስ ላይ 100 ዝርዝር ሃሳቦች ያስገኛል።
​ለGemini Enterprise ሁለት አዲስ ብዙ ወኪሎች እየተዘጋጁ ነው:
➊ ​የሃሳብ ማፍለቂያ (Idea Generation): "ብዙ ወኪል ያለው የፈጠራ ስብሰባ አካሂድ" ("Create a multi-agent innovation session")
➋ ​ተባባሪ ሳይንቲስት (Co-Scientist): "ከCo-Scientist ጋር አዲስ ሳይንሳዊ ግኝቶችን አምጣ" ("Drive novel scientific discovery with Co-Scientist")
🧪 የCo-Scientist የሥራ ሂደት (3 ደረጃዎች)
​ዝግጅት: Co-Scientist ምን መመርመር እንደሚፈልጉ ይንገሩት፣ ተዛማጅ መረጃዎችን ያሳዩት እና የግምገማ መስፈርቶችን ያዘጋጁ።
​ሃሳብ ማመንጨት: የወኪሎቹ ቡድን ያሉባቸውን መረጃዎች በመጠቀም በርስዎ ርዕስ ላይ ሃሳቦችን ያመነጫሉ።
🔦​ግምገማ እና ደረጃ መስጠት: ወኪሎቹ ሃሳቦቹን በመስፈርትዎ መሠረት ይገመግማሉ እና እንደ ውድድር (tournament-style) ደረጃ ያስቀምጧቸዋል።

​Google የምርምር ሥራን በራስ-ሰር ማከናወን ብቻ ሳይሆን፣ ሌሎችም ይህን እንዲያደርጉ የሚያስችል ምርት እያዘጋጀ ነው።

@netrotech9 | @netrotech9
1
#AAiT

Full Stack Software Developer Training Program

Registration: Sept 29 – Nov 28, 2025,
Class Start Date: Nov 29, 2025

Recognized & Accepted Training and Certificates in the USA, Canada, & Europe!

🎓 Earn 4 Professional Certificates:
✔️ Front-End Development
✔️ Back-End Development
✔️ Database Development
✔️ DevSecOps

💼 Career Support & Job Opportunities: Full-time, part-time & freelance opportunities in Ethiopia & worldwide. Portfolio Development and Resume & Interview Preparation

📞 Contact Us: 0902-340070 / 0945-039478 / 0935-602563 Office:011-1-260194

🔗 For more details, check our channel: @AAU_DEVELOPER
Forwarded from NETRO TECH -AM
#cybersecurityAwareness

🤖 ጎግል በኤ.አይ. ሞዴሎች በመጠቀም ጥቃቶችን የሚያሻሽሉ ማልዌሮችን አገኘ
​ጎግል የማልዌር (Malware) ጥቃት አድራጊዎች የጥቃታቸውን ስልት ለማሻሻል ትልልቅ የቋንቋ ኤ.አይ. ሞዴሎችን (LLMs) እየተጠቀሙ መሆኑን አግኝቷል።

1. Quietvault (ኳይትቮልት): ይህ ጥቃት የተሰራው ከዊንዶውስ ኮምፒዩተር ውስጥ የመግቢያ መረጃዎችን (login credentials) ለመስረቅ ነው። ይህ ማልዌር "በተጠለፈው ኮምፒውተር ውስጥ ያሉ ሌሎች ሚስጥራዊ መረጃዎችን ለመፈለግ የኤ.አይ. መጠየቂያ (AI prompt) እና በኮምፒውተሩ ላይ የተጫኑ የኤ.አይ. መመሪያ መስጫ መሳሪያዎችን (AI CLI tools) ይጠቀማል።"

2. Promptflux (ፕሮምትፍለክስ): ይህ ሌላኛው የማልዌር አይነት የጠላፊዎች የሙከራ ሥራ ይመስላል። ከሌላው ለየት የሚያደርገው ጎግል የሰራውን ጀሚኒ (Gemini) ቻትቦት በመጠቀም የራሱን የኮምፒውተር ኮድ በመቀየር በደህንነት መመርመሪያዎች እንዳይያዝ መሞከሩ ነው። ​"የPROMPTFLUX በጣም አዲስ እና አስገራሚ ክፍል 'አሳቢ ሮቦት' (Thinking Robot) የሚባል ሲሆን፣ ስራው የፀረ-ቫይረስ ሶፍትዌሮችን ለማምለጥ የሚያስችል አዲስ ኮድ ለማግኘት ጀሚኒን በተደጋጋሚ መጠየቅ ነው።"
​"የPROMPTFLUX በጣም አዲስ እና አስገራሚ ክፍል 'አሳቢ ሮቦት' (Thinking Robot) የሚባል ሲሆን፣ ስራው የፀረ-ቫይረስ ሶፍትዌሮችን ለማምለጥ የሚያስችል አዲስ ኮድ ለማግኘት ጀሚኒን በተደጋጋሚ መጠየቅ ነው።"


@netrotech9 @netrotech9
Google "the most intelligent" ሞዴል ነው ያለውን Gemini 3 ዛሬ ይፋ ያደርጋል።

Gemini 3 pro በGemini application እና በGoogle search እንደተካተተና በኮዲንግ እንዲሁም በreasoning ከሌሎች ሞዴሎች እጅግ የተሻለ ነው ተብሏል።

Google ለሁሉም Gemini application ተጠቃሚዎች ለመጀመሪያ ጊዜ Gemini 3 proን በነፃ እንደሚለቅ ተገልጿል።

ተጨማሪ ዝርዝር ፊቸሮቹን ይዘን እንመለሳለን።
Perplexity AI እዲሱን comet የተሰኘ AI browser ማስተዋወቁ አይዘነጋም።

አሁን ደግሞ የandroid አፕሊኬሽኑ ተለቋል።

You can download and test it👇
https://play.google.com/store/apps/details?id=ai.perplexity.comet