Buna Tech ቡና ቴክ
282 subscribers
777 photos
51 videos
13 files
220 links
Welcome to our Buna Technology.
It's a channel where you find the amazing and new things about Computer and technology and get a variety of funny surprises and you get knowledge. Thanks 🙏
Download Telegram
🍎 ግዙፉ አፕል ድርጅት IPhone 17 ስልክን ይፋ አደረገ

🫧 የዓለማችን ግዙፉ የቴክኖሎጂ ኩባንያ አፕል፣ አዲሱን የIPhone 17 ስማርት ስልክ ተከታታይ ሞዴሎችን በይፋ ለገበያ ማቅረቡ ተገለጸ።

➡️ አዲሶቹ ስልኮች የቴክኖሎጂ ፍላጎትን በሚያሟላ መልኩ የተሰሩ ሲሆን፣ ዋጋቸውም በገበያ ላይ ከሌሎቹ ተለይቶ ቀርቧል።

🔌 የአዲሱ አይፎን ዋጋ በዝርዝር እንደሚከተለው ነው!

↪️ IPhone 17: ዋጋው 3,399 ድርሀም ሲሆን፣ በኢትዮጵያ ብር ሲሰላ ወደ 128,142.30 ብር ይሆናል።

↪️ IPhone 17 Air: ዋጋው 4,299 ድርሀም ሲሆን፣ ወደ ብር ሲመነዘር 162,072.30 ብር ይሆናል።

↪️ IPhone 17 Pro: ዋጋው 4,699 ድርሀም ሲሆን፣ ወደ ብር ሲመነዘር 177,152.30 ብር ይሆናል።

↪️ IPhone 17 Pro Max: ዋጋው 5,099 ድርሀም ሲሆን፣ ወደ ብር ሲመነዘር 192,232.30 ብር ይሆናል።

➡️ ይህ ዋጋ በባንክ የምንዛሬ ተመን ላይ የተመሰረተ ነው::
የዓለማችን እጅግ ባለፀጋ ሰው ማን ነው? 🤔

በቅርቡ በተደረገው የዓለማችን ሀብታሞች ደረጃ አሰጣጥ ላይ ያልተጠበቀ ለውጥ ተከስቷል። የኦራክል (Oracle) መስራች የሆኑት ላሪ ኤሊሰን በኩባንያቸው የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) እና የክላውድ አገልግሎቶች መሻሻል ምክንያት ሀብታቸው ወደ 393 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር በማሻቀቁ ለጥቂት ጊዜ ያህል የዓለማችን ቁጥር አንድ ባለፀጋ መሆን ችለው ነበር።

ይሁን እንጂ፣ የቴስላ እና ስፔስኤክስ መስራች የሆኑት ኢሎን መስክ የአክሲዮን ዋጋቸው በድጋሚ በመናር ከ 384-440 ቢሊዮን ዶላር ባለው ክልል ውስጥ በመንቀሳቀስ የቀድሞ ቦታቸውን መልሰው መያዝ ችለዋል።

በአጭሩ: የቴክኖሎጂ አክሲዮኖች በከፍተኛ ፍጥነት በመለዋወጣቸው ምክንያት የባለፀጎች ደረጃም በየጊዜው እየተቀያየረ ይገኛል። 📈
1
አልባኒያ የመጀመሪያውን በ Ai የተሰራ ሚኒስተር ሾማለች 😊😂

የመጀመሪያዋ የ Ai-minister ያላት ሃገርም ሆናለች!

Diella የሚሰኘው ይህ የ Ai-bot minister የ public Procurement ሃላፊነትን ወስዶ የ ሙስና የፀድ ስራ እንዲሰራ ተሽሟል።

የትኛው ሚኒስተር ይቀየርላችሁ ?
ዳዮ ይርጋጨፌ የቡና በልዩ የይርጋጨፌ ቡና ጥራቱ እና በሚያቀርበው ባህላዊ መስተንግዶ በጌዴኦ-ዞን እና በሌሎችም አከባቢዎችና የተለያዩ እንግዶችን ተቀብሎ በማስተናገድ ይታወቃል። ነገር ግን፣ በዛሬው ዲጂታል ዘመን ጠንካራ የበይነመረብ መገኘት ከሌለ፣ ብዙ ደንበኞችን የማግኘት እና  ስሙንና ስራውን  በሰፊው የማድረስ እድሉ የተወሰነ ይሆናል።
#DayyoCoffee.com Comming Soon
👍1
ሳም አልትማን እንኳን አድንቆታል! አፕል እጅግ ቀጭን አይፎን ሰራ 🤯

አፕል (Apple) ታሪክ የሰራ አዲስ አይፎን ይፋ አድርጓል — በ5.6mm ውፍረቱ የኩባንያው ታሪክ ውስጥ እጅግ ቀጭኑ ስልክ ሆኗል። ይህ ዲዛይን በቴክኖሎጂው ዓለም ትልቅ መነጋገሪያ ሆኗል።

የበለጠ አስገራሚ የሚያደርገው ግን በስልኩ የተደነቀው ሰው ነው። የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ግንባር ቀደም ድርጅት የሆነው የOpenAI ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሳም አልትማን፣ በግልጽ አድናቆቱን ገልጿል።

💬 አልትማን በX (የቀድሞው ትዊተር) ገጹ ላይ እንዲህ ሲል ጽፏል፡-

"ለረጅም ጊዜ ለመለወጥ የፈለኩት የመጀመሪያው አዲስ አይፎን! በጣም ምርጥ ይመስላል።"


ከአልትማን መሳሰሉ ከፍተኛ የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች የሚመጣው እንዲህ አይነቱ ምስጋና የአፕልን አዲስ የዲዛይን አቅጣጫ ምን ያህል አስደናቂ እንደሆነ ያሳያል። አይፎን ኤር (iPhone Air) ብዙዎች ተገመች ነው ብለው የገመቱትን የአፕል የምርት መስመር ወደ አስደሳች ደረጃ መልሶታል።

ለምን ትልቅ ለውጥ ያመጣል?

🎯እጅግ በጣም ቀጭን እና ቀላል ክብደት ያለው ዲዛይን
🎯ከአፕል የሚጠበቀውን የዲዛይን አቅጣጫ የቀየረ
🎯ከታላላቅ የቴክኖሎጂ መሪዎች ከፍተኛ ምስጋናን ያገኘ

የቴክኖሎጂ መሪዎች እንደ አልትማን ለአዲስ አይፎን ፍላጎት ማሳየታቸው፣ እጅግ ቀጫጭን ስልኮች የቴክኖሎጂው አዲስ ምዕራፍ መሆናቸውን ሊያመለክት ይችላል። 📱
#Buna_Tech
ውድ ቡና ቴክ ቤተሰቦቻችን መደበኛ የTelegram Chanel
@bunatech ላይ

Join 🙏🙏
Share 🙏🙏🙏

በማድረግ የተለመደ ድጋፋችሁን በፍቅር እንጠይቃለን ።

ከሰላምታ ጋር
Buna Tech Official Chanel

@bunatech
#tech_tip

Chatgpt የሚሰጠንን ምላሽ customize ማድረግ እንደምችል ታውቃላችሁ?

ለchatGPT ስለኛ የፈለግነውን ነገር share በማድረግ የሚመልስልንን መልስ በዛ መሰረት እንዲመልስልን ማድረግ እንችላለን።  ይህም በcustom instructions ይባላሉ። ይህንንም on/off እያደረግን መጠቀም እንችላለን።

ፕሮፋይላችን ውስጥ ከገባን በኋላ personalization ከዛ enable Customization የሚለውን  on በማድረግ custom instructions, Nickname, more about you የሚሉት ውስጥ ስለኛ ልዮ ልዩ መረጃዎችን በማስገባት chatGpt የሚሰጠንን ምላሽ ማስተካል እንችላለን።

ማሳሰቢያ፡ Enable personalization የሚለው on ማድረግ እና ካስተካከላችሁ በኋላ የright ምልክቱን መንካት አትርሱ። ከዚህ በኋላም በChatGpt ምላሾች ላይ ለውጥ ልታዩ ትችላላችሁ።
1
🤔 ይህን ያውቁ ኖሯል?

📱 የሞባይል ስልክ ግንኙነት: ሀገራችን ውስጥ ከ85 ሚሊዮን በላይ የሞባይል ስልክ ግንኙነቶች አሉ! ይህም ከጠቅላላው ህዝብ 63.8% ጋር እኩል ነው።

🌐 የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች: 28.6 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ናቸው። ይህ ማለት ግን አሁንም 78.7% የሚሆነው ህዝባችን ኢንተርኔት አይጠቀምም።

👥 የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች: 8.3 ሚሊዮን የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች አሉን። ከእነዚህም ውስጥ 67.7% ወንዶች ሲሆኑ 32.3% ሴቶች ናቸው።

👍 ፌስቡክ አሁንም ቀዳሚ ነው! በኢትዮጵያ 8.3 ሚሊዮን የፌስቡክ ተጠቃሚዎች አሉ።
ይህ መረጃ የሀገራችን የዲጂታል እድገት የት ላይ እንዳለ ያሳያል። ለንግድዎ ወይም ለስራዎ ይህንን መረጃ እንዴት ሊጠቀሙበት ይችላሉ?


ምንጭ
https://datareportal.com/reports/digital-2025-ethiopia?utm_source=chatgpt.com

#ዲጂታልኢትዮጵያ #ይህንያውቁኖሯል #ኢትዮጵያ #ማህበራዊሚዲያ #ኢንተርኔት #ቴክኖሎጂ #DigitalEthiopia #DidYouKnow #EthiopiaFacts #SocialMedia
Instagram 3 ቢልዮን Active user አፈራ።

የmeta CEO mark zukerberg እንደገለፀው ከሆነ Instagram 3 ቢልዮን ወርሀዊ ንቁ ተጠቃሚ ወይም Active users ማግኘት ችሏል።
Meta ኢንስታግራምን በ2012 በ1 ቢልዮን ዶላር መግዛቱ አይዘነጋም።

አንድዳንድ አስገራሚ የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ቁጥራዊ መረጃዎች
በ1997 እንደፈረንጆች አቆጣጠር ጅማሮውን ያደረገው ማህበራዊ ሚዲያ አኗኗራችንን እና የእርስበርስ መስተጋብርጅራችንን ሙሉ ለሙሉ ለውጦታል።
ዛሬ ላይ በአለም አቀፍ ደረጃ 5.41 ቢሊዮን የሚሆኑ ሰዎች ወይም 65.7% የሚሆነው የዓለም ህዝብ ማህበራዊ ሚዲያን ይጠቀማል።
አማካኝ ዕለታዊ የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም 2 ሰአት ከ40 ደቂቃ ነው።
አንድ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚ በአማካኝ 6.8 የsocial media አካውንቶች አሉት።
የማህበራዊ ሚዲያ የሚጠቀሙ ሰዎች ቁጥር በየአመቱ በአማካይ 4.7% ጭማሪ ያሳያል። በየሰከንዱ 7.6 አዳዲስ ሰዎች ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ይመዘገባሉ።
ማህበራዊ ሚዲያን ከሚጠቀሙት ውስጥ 75% የሚሆኑት ከ13 ዓመት በላይ ናቸው።
95.7% የሚሆኑት ኢንተርኔትን አዘውትረው የሚጠቀሙ ሰዎች የማህበራዊ ሚዲያም ተጠቃሚ ናቸው።
የአለም ህዝብ በየቀኑ 14.5 ቢሊዮን ሰአት ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ያሳልፋል። ያ ማለት 17 ሚሊዮን አመታት በየቀኑ ማህበራዊ ሚዲያ በመጠቀም ያልፋል። 

ምንጭ: datareportal.com

✍️እናንተ ስንት ማህበራዊ ሚዲያ አካውንት አላችሁ?
Hey! Introverts You’re invited to The Introvert Society. @TheIntrovertSociety a low-pressure space . No need to chat if you don’t feel like it, and feel free to leave anytime if it gets too noisy. Come hang out whenever you want, at your own pace. 😊

No pressure, just good chat for introverts like us.
@TheIntrovertSociety
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Introducing Early Decision.

For students who want to do a startup but also want to finish school first. Apply now, get funded the moment you're accepted, and do YC after you graduate.

More info
ycombinator.com/early-decision

Also, if you're not in your final year, you can still apply for Early Decision. You'll be able to finish the school year you're currently in, and then either join a later batch or decide to drop out and start sooner.

#YC
@DagmawiBabiJobs
🧥 እንደ ስቲቭ ጆብስ (iphone's Founder)፣ ቢል ጌትስ (Microsoft's Founder) እና ማርክ ዙከርበርግ (Facebook's Founder) ያሉ ሰዎች በየቀኑ ተመሳሳይ ልብስ የሚለብሱት ለምን እንደሆነ አስባችሁ ታውቃላችሁ!?

👕 የትኛውን ልብስ መልበስ እንዳለባቸው መወሰን አይፈልጉም።

👖 በቀን ውስጥ ብዙ ውሳኔዎችን የምትወስን ከሆነ አዕምሮህ እየደነዘዘ ይመጣል።

👟 አዕምሮህ በቀን ጥቂት ውሳኔዎችን ብቻ የማድረግ ሀይል አለው እናም ቀንህን በጥበብ አሳልፈው!!

🩴 "በየቀኑ የተለያዩ ልብሶችን የሚቀያይሩ እና ፋሽን ተከታይ የሆኑ ሰዎች የድህነት ብራንድ ናቸው!!" ኤለን መስክ (Tesla & X CEO)

#inspiration
2🥰1🤝1
#info
What is SOS(Save Our Souls)?
🔹 “እርዳታ ይፈልጋል” ወይም “ሕይወታችንን አድኑ” ማለት ነው።
🔹 መጀመሪያ በ ሞርስ ኮድ (· · · – – – · · ·) በመላው ዓለም የሚጠቀሙት የአደጋ ምልክት ነበር።
🔹 በተለይም መርከቦች ለከደጋ ግዜ የሚጠቀሙት ነበር።
🔹 አሁን ግን "SOS" ማለት በቀላሉ “እርዱኝ!” ወይም “አስቸኳይ እርዳታ” ብለው ይጠቀሙበታል።
የእንግሊዝ መንግስት ዜጎች Digital ID እንዲያወጡ የሚያስገድድ ህግ ሊያወጣ ነው።

ህገወጥ ስደትን ለመከላከል ይረዳል የተባለ ሀገር አቀፍ Digital ID ሁሉም የእንግሊዝ ዜጋና በህጋዊ መንገድ እንግሊዝ ውስጥ የሚሰሩ የሌላ ሀገር ዜጎች እንዲያወጡ ህገ ሊወጣ ነው።

የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር Keir Starmer "ዲጂታል መታወቂያ ለዩናይትድ ኪንግደም ትልቅ እድል ነው። በዚህ ሀገር ውስጥ በህገ-ወጥ መንገድ የሚሰሩትን ለመቆጣጠር ይረዳል፣ ይህም ድንበራችንን የበለጠ ደህንነቱ የተጠበቀ ያደርገዋል።" ብለዋል።

የእንግሊዝ መንግስት ይህን መግለጫ ካወጣ በኋላ ብዙ የሰብዐዊ መብት ተሟጋቾች ተቃውሞ እያሰሙ ነው።
እስካሁን ድረስም 830,000 የሚሆኑ ዜጎች ድርጊቱን በመቃወም የOnline ፊርማዎች ፈርመዋል።

ይህ ህግ ወደ ተግባር ከመግባቱ በፊት ለሀገሪቱ ፓርላማ ቀርቦ መፅደቅ ይጠበቅበታል።