ለውድ አባላት በሙሉ፣
የማህበራችን የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ሐምሌ 04 ቀን 2018 ዓ.ም በተሳካ ሁኔታ ተካሂዷል። በዕለቱ ጥሪያችንን አክብራችሁ የተገኛችሁ የልደታ ክፍለ ከተማ ኅብረት ሥራ ማህበር ተወካዮች፣ የንብ ባንክ አመራሮች እና ሰራተኞች፣ እንዲሁም ውድ አባላት በሙሉ የላቀ ምስጋናችንን እናቀርባለን።
በተለይም ይህ ስብሰባ እንዲሳካ ላደረጉልን የስብሰባ አዳራሽ አገልግሎት እና በእለቱ የሻይና ቡና ፕሮግራም ድጋፍ ላደረጉልን ለንብ ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ በማህበሩ ስም ልዩ ምስጋና እናቀርባለን።
በስብሰባው ላይ በተነሱት አጀንዳዎች ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጎ፦
1. የ2016 ዓ.ም እና የ2017 ዓ.ም. የኦዲት ሪፖርት ፀድቋል።
2. የ2016 ዓ.ም እና የ2017 ዓ.ም የትርፍ ትርፍ ክፍፍል ተሰልቶ ወደ እጣ እንዲዞር ተወስኗል።
3. የ2018 ዓ.ም. የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቧል።
4. የ2019 ዓ.ም. እቅድ ፀድቋል።
5. የ2018 ዓ.ም. ዓመታዊ የኢንስፔክሽን ሪፖርት ቀርቧል።
6. የማህበሩ ቁጥጥር ኮሚቴ ዓመታዊ ሪፖርት ቀርቧል።
7. በመተዳደሪያ ደንባችን ላይ አነስተኛ የብድር መድህን ህይወት ሽፋን (የሞት) 1.2% ከተበዳሪው ላይ እንዲቆረጥ ተወስኗል። ይሁን እንጂ፣ የሚከተሉት ሁኔታዎች ሲከሰቱ የመድህን ዋስትናው ተፈፃሚነት አይኖራቸውም፦
o ለሶስት ተከታታይ ወራት ክፍያ ሳይፈጸም ቢሞት (ወይም ሶስት ወራት ኃላፊነት የማይወጣ ከሆነ)፣
o አባሉ ስለመሞቱ በ15 ቀናት ውስጥ ወኪል ህጋዊ ማስረጃ ካላቀረበ።
ማሳሰቢያ፡ ይህ መዋጮ ብድር ሲወስዱ እየተቆረጠ አባላት ከወሰዱት ብድር ጋር ተነጻጽሮ፣ የማህበሩ የመክፈል አቅም ታይቶ ለቀጣይ ጠቅላላ ጉባኤ የሚቀርብ ይሆናል፤ የአነስተኛ የብድር መድህን ህይወት ሽፋን(ሞት)ተግባራዊ የሚደረግበት ጊዜም በቀጣይ ውይይት የሚወሰን ይሆናል።
8. አባላት የሂሳብ ደብተር ለማስሞላት የሚያባክኑትን ጊዜ ለመቀነስ እና የማህበሩን ሶፍትዌር ስራ ለማቀላጠፍ፣ የየራሳችሁን መረጃ በድጋሚ በዚህ ሊንክ https://docs.google.com/forms/d/1-2SFqqxEC8sKCN4_OIQmxNBYRf4Zy94UMawnW9nmiBQ/preview ተጠቅማችሁ እንድትመዘገቡ በጥብቅ እናሳስባለን። አባል የሆናችሁበትን ቀን፣ ወር እና ዓመተ ምህረት የማታውቁ አባላት "Today" የሚለውን በመጠቀም መሙላት የምትችሉ ሲሆን፣ ማህበሩ ማስተካከያውን የሚያደርግ ይሆናል።
9. የማህበሩ መስራችና ስራ አስኪያጅ ለሆኑት አቶ ሲሳይ ሁንዴ ለ10 ወራት ተከፍሎ የሚያልቅ በወር 30 ብር (በድምሩ 300 ብር) መዋጮ ተደርጓል። ይህም ገንዘብ ጉባኤው ለቦርዱ በሰጠው ኃላፊነት መሰረት አጠቃላይ የአፈፃፀም ሪፖርቱ በቀጣይ ጉባኤ የሚቀርብ ይሆናል።
10. ለቀድሞ የቦርድ አባላት፣ ለሰራተኞች፣ ለት/ቤቶች፣ ለማህበራት እንዲሁም ለንብ ኢንተርናሽናል ባንክ በእለቱ የሽልማትና የእውቅና መርሃ ግብር ተካሂዷል።
በስብሰባ ላይ አለመገኘት የሚወሰኑ ቅጣቶች፦
· ሀ. ለመጀመሪያ ጊዜ ቀርቶ ሳይገኝ ሲቀር፡ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) ይቀጣል።
· ለ. ለሁለተኛ ጊዜ ቀርቶ ሳይገኝ ሲቀር፡ ብር 150.00 (አንድ መቶ ሃምሳ ብር) ይቀጣል። (ይህ ደንብ ጥሪ ተደርጎላቸው ባልተገኙ አባላት ላይ ሁሉ ተፈፃሚ ይሆናል)
ጠቅላላ ጉባኤ
ሐምሌ 04/2018 ዓ.ም

Google Docs
Membership Data
ብሩህ ተስፋ መም/ሠ/የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃ/የተ/ህ/ሥራ ማህበር
❤34👍13👏2
እንኳን ለ2019 ዓ. ም የእንቁጣጣሽ በዓል በሠላም አደረሳችሁ!!
******
ከነሐሴ 12/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ነሐሴ 29/2018 ዓ.ም ድረስ የእንቁጣጣሽ ልዩ ብድር መስጫ ጊዜ ስለሆነ ውድ አባላት በዓካል በመቅረብ የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ሂሳብ ቁጥራችሁን በመያዝ መመዝገብ የምትችሉ ሲሆን የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ሂሳብ ቁጥር የሌላችሁ አባላት የፋይዳ መታወቂያ ወይም ቁጥራችሁን እና ሁለት ፎቶ ግራፍ ይዛችሁ በመገኘት የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ሂሳብ ቁጥር የሚሰጣችሁና ብድሩ መበደር የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
****

❤24👍3