ብራና ሚዲያ BRANA MEDIA
355 subscribers
1.3K photos
11 videos
146 files
169 links
Download Telegram
ዛሬ የብርሃን እናት መጽሐፍ በስካይላይት ሆቴል ተመርቋል። እንኳን ደስ አለህ Deacon Henok Haile! 👏🏾

"የብርሃን እናትን እየመረቅን "በእንተ ስማ ለማርያም ስለ እመብርሃን" የሚለውን የአብነት ተማሪ የክረምት ስንቅ አብረን እንሰንቅ።" ብሎ ከቲኬቱ የሚገኘውን ሙሉ ገቢ ለጉባኤያቱ ድጋፍ ሰጥቷል። ከትኬት ሽያጩ ውጪ ለመደገፍ የምትፈልጉም የጉባኤ ቤቱ ፕሮጀክት የሒሳብ ቁጥር 1000391852058 ባሕር ዳር ሀገረ ስብከት የ፬ቱ ጉባኤያት ሕንጻ አሠሪ ኮሚቴ ቁጥር ላይ ማስገባት ትችላላችሁ ተብላችኋል።

ባለፈው ሳምንት "የግዮን ወንዝ - አዲስ መጽሐፍ - በቅርብ ቀን። ሙሉ ገቢው በአዲስ አበባ (መርካቶ) ለደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ሕንፃ እድሳት የሚውል" ብሎናል።
ከመጽሐፉቱ ሽያጭ ውጭ የእድሳት አገልግሎቱን መደገፍ፣ ከበረከቱ መሳተፍ ለምትፈልጉ
--*በሞባይል ባንኪግ*--
የሒሳብ ቁጥር የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000442101349
ገቢ በማድረግ ይቻላል።
ለበለጠ መረጃ 0911-117613 , 0913645364
https://t.me/Tekley24
***የተክልዬ ወዳጅ ነኝ!!!
ይህን መጽሐፍ ሳነበው የተሰማኝ እንዲህ ነው!
እኛ ሰዎች የፈጠርናቸው ነገሮች ያለኛ ትርጉም አልባ አይደሉምን? እንዲሁ ተፈጥሮም በዓላማ ከፈጣራትና ካስገኛት ውጪ ምን ናት? በጥቂት አሳቢዎች ፍልስፍና መነሻነት የምዕራቡ ዓለም ስልጣኔ አምክ የለሽ ሆኗል፡፡ ሕይወትና ዓለሙን ሁሉ ከፈጣሪያው ዓላማ ነጥሎ ትርጉም ሊሠጣቸው ይሞክራል፡፡ ሕይወት ግን ከተፈጥሮ ዓላማዋ በራቀችበት መጠን ይበልጥ ትርጉም እያጣች ሔዳለች፡፡ ከዚህ የተነሣ ሰዎች ደስታን ፍለጋ
የሚያደርጉት ጥረት ብዙው የበዛ መከራ ምንጭ ሆኖ ይታያል፡፡ ወንዝ ዳር የለመለመችውን ተክል ወስዶ አሸዋ ላይ እንደመትከል ነው፡፡

ሥዝማዊው ሥልጣኔ በሳይንስና ቴክኖሎጂ በመታገዝ ለሕይወት የሚያደርገው ጥረት ሁሉ ያለ ተፈጥሮ ዕሴቷ አለት ላይ ለተተከለችው ተክል ውኃ እንደማጠጣት፣ ጊዜያዊ እፎይታን
እንጂ ዘላቂ ሰላምና እርካታን ሲያስገኝላት አይታይም፡፡ ይህ ምዕራባዊ ቁሳዊ ዕሳቤ ዛሬ መደበኛው ቢሮክራሲ ነው፡፡

የመግሥት ፖሊሲና የትምሕርት ተቋሞቻችንም ይህንኑ ይግቱናል፡፡ ጥቂቶች ሀገራት በራሳቸው መንገድ ወንዝ ሆነው ሲፈሱ፣ የራሳቸው ቀለም ያለው ልህቀት ባለቤት በመሆን
ለዓለም አበርክቶ ኖሯቸዋል፡፡ ብርቱ አእምሮ ያጡ እንደኛ ያሉ ሀገራት የምዕራቡን ዓለም መንገድ ኩረጃ ላይ በማትኮር ከጅራትነት የማያሳልፍ ጉዞ ውስጥ ከቶናል፡፡

አንባቢያን እጅ እንዲደርስ ጸሎቴ የነበረው ይህ የመምህሬ ጋሽ ፈንታሁን መጽሐፍ እሳቤዎችን እንድንፈትንና ግለሰባዊ ንቃት ኖሮን ማኅበረሰባዊ ልዕልናን እንድናደርግ የሚያስችለን ነው፡፡ እንደ ግል አንዴ ብቻ የምንኖራትን የምድር ሕይወት እንደ ንስር ከፍ ባለ ዕይታ ከሐሳቦች ሁሉ መርጦ በላቀው መንገድ የመምራት አዕምሮን ያስታጥቃል፡፡ እንደ ማኅበረሰብ ወንዝ ሆነን በራሳችን ማኅቀፈ እሳቤ መፍሰስ እንድንችል የሚረዳን
መጽሐፍ ነው።

አንድ ክፍለ ዘመን የደፈነው ምዕራባዊው የትምሕርት ጉዟችን ችግሮቻችንን ይበልጥ እያወሳሰባቸው የመጣበትን መንስኤ ማሳየት ብቻ ሳይሆን መሠረታዊ የዕውቀት ሥሪቱን
ጉድለቶች ማከምም የሚያስችለን መጽሐፍ ነው፡፡
https://www.facebook.com/mikiyas24/
https://t.me/brana_Book

https://www.facebook.com/Mikiyas-danail-102145778357310/
መልካም ንባብ
ብራና ሚዲያ
፳፰/፲/፳፻፲፬ ዓ/ም
+ + +

የማይቀርበት!

ቅዳሜ ሐምሌ 9 ቀን፡ ኹላችሁም ተጠርታችኋል። "የፀሓይ ከተማ"ን እንመርቃለን! መንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል አዳራሽ፡ ከ7:30 ጀምሮ እንገናኝ!

የቅዳሜ ሰው ይበለን!

+ + +
በቅርብ ቀን
እኩት እግዚአብሔር እንተ ኢትተረጎም
#ኦርቶዶክስ_መልስ_ናት
በዲን ገብረኪዳን
#ብዝዎች_ልብ_ያላልነው_መጽሓፍ
ባለፈው መምህር ምሕረትአብ አሰፉ ከአርጋኖን ገዝቶት ሲሄድ አይቼ ማታውኑ ወሰድኳት አለፍ እያልኩ ማንበብ ጀመርኩኝ ዲን ገብረኪዳን በብዙ መረጃዎች አስደግፎ
#በአማርኛ_ኢንግሊዘኛ_አረብኛ ለ303 ጥያቄዎች መልስ ይሰጣል።በአጭሩ ግሩም ሁኖ አግኝቸዋለሁ አንብቡት።

#የገጽብዛት_351
#ዋጋ_200ብር
ለኅብረቱ አባላት 150ብር ብቻ።ለማዘዝ
@orthokiha

#አርጋኖን_መጻሕፍት_መደብር_5ኪሎ_ማርያም_ዋናውበር_ሽዋዳቦ_ፊትለፊት_ካሉት_መነጽር_ቤቶችውስጥ_ለበለጠ_መረጃ_0966214181_ይደውሉ
ትዳርና_ተላጽቆ_በቀሲስ_ኅብረት_የሽጥላ.pdf
27.4 MB
በብዝዎች ጥያቄ #ትዳርና_ተላጽቆ አቅርበናል።አንብቡት አስነብቡት!!!