ADD - BRANA BOOK
++++++++++++++++++
ሌሎች የብራና መጽሐፍ ቤተሰብ አባል እንዲሆኑ፤ ዘመድ ወዳጆን አድ/add ያድርጉ!!!
ብራና መጽሐፍ BRANA BOOK✍
https://t.me/brana_Book
ከ 2,000 ወደ 5,000 እናሳድግ

♥ሠላም ሠላም የተከበራችሁ የብራና ቤተሰቦች እንዴት አደራችሁ?...👍
📚ሳምንቱ እንዴት አለፈ?...ምን ዓይነት መጽሐፍ አነበባችሁ በቀጣይስ የተኛውን መጸሐፍ ለማንበብ አቀዳችሁ?..ካነበባችሁት መጸሐፍ መካከል እስኪ ፍሬ ሀሳቦችን ጻፉልን....✍🏿

ብራና መጽሐፉ BRANA BOOK
+++++++++++++++++++++
በዚህ ግሩፕ ላይ ቢሳተፉ የምትሏቸውን ዘመድ ወዳጆቾን Add ያድርጉ....
***********************
Add ያድርጉ
Subscribe ያድርጉ
*************
እናመሰግናለን••••••••

የመ/ር ዳዊት ደስታ “ኦርቶዶክሳውያን እና ፖለቲካ” መጽሐፍ - ኦርቶዶክሳዊያን ፖለቲካ ላይ መሳተፍ እንደሚገባን የሚያወያይ
-ታላቅ ወንድማችን ዳዊት ደስታ ከሦስት በላይ መጽሐፍትን ያበረከተልን ኦርቶዶክሳዊ ነው፡፡ በስምዓ ጽድቅ ጋዜጣ የጽሑፍ አበርክቶውም እናውቀዋለን፡፡ በቅርቡ በ2013 ዓ.ም “ኦርቶዶክሳውያን እና ፖለቲካ” በሚል ርእስ ሊያወያይ የሚያስችል መጽሐፍ አበርክቶልናል፡፡ ለነዚህ ሁሉ ሥራዎችህ ምስጋናየ ድረስህ ወንድማለም፡፡
- “ኦርቶዶክሳውያን እና ፖለቲካ” መጽሐፍ በ217 ገጽ የተቀነበበ ሲሆን በሰባት ምዕራፎች የተከፈለና በያንዳንዱ ምዕራፍ በጣም ብዙ አወያይ ጉዳዮችን ይነሣሣል፡፡ ማንኛውም ኦርቶዶክሳዊ ገዝቶ ሊያነበውና ሊወያይበት ሊከራከርበት የሚገባ መጽሐፍ ነው፡፡ በመጽሐፉ የተጻፉትን ሐሳቦችም ለመሞገትም ሆነ ለመከራከር የልዩነት ሐሳብን ለማስቀመጥም መጽሐፉን ማንበብ ያስፈልጋል፡፡
- መ/ር ዳዊት ደስታ መጽሐፉን ስለጻፈበት ምክንያቱን ሲገልጽ “ውለታዋን አንስተን የማንጨርሰው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቀድሞ የነበራት ሚና ወደ ጎን በመደረጉ የተነሣ በተለይ በፖለቲካው ዓለም ተሳትፎ የሚያደርጉ የሌሎች ቤተ እምነት ተከታዮች ቤተክርስቲያኗ እና አማኞቿ ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ እያሳደሩባት ይገኛሉ፡፡” ይለናል፡፡(ገጽ 1) እውነቱን ነው፡፡ ኦርቶዶክሳዊ ቤተክርስቲያንን ጠላት አደርገው የተነሱ የፖለቲካ ድርጅቶችንና ፖለቲከኛ ነን ባይ ግለሰቦችን ፖለቲካ ላይ በመሳተፍ በቤተክርስቲያን ላይ የሚያደርጉባትን ሴራ መታገል ይቻላል እንጅ “ፖለቲካና ኮረንቲ በሩቁ ነው” በማለት ችግሩን መፍታት እንደማይቻል መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡
1.) የመጽሐፉ ጠቀሜታ
-ሌሎች ኦርቶዶክሳዊያን ስለ ቤተክርስቲያን ፖለቲካዊ ጉዳዮችን ለመጻፍ ቢፈልጉ መንደርደሪያ ይሆናቸዋል፡፡
-ኦርቶዶክሳዊያን ፖለቲካ ላይ መሳተፍ እንደሚገባቸው ያስገነዝባል ያወያያል፡፡
-በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ ቤተ እምነቶች ፖለቲካውን አስመልክቶ ሥልጣን በመቆጣጠር ረገድ እየሠሩ ያለውን ተግባር ያስገነዝባል፡፡ (ገጽ-8)
2.) የመጽሐፉ ምዕራፍ አንድ ግለሰብ እና ሕዝብ በኢትዮጵያ ፖለቲካ በሚል ርእስ የሚብራራበት ምዕራፍ ነው፡፡ በዚህ ምዕራፍ ውስጥ የፖለቲካ ምንነትን ሕዝብና ፖለቲካ በኢትዮጵያ ምን እንደሚመስሉ ግለሰብና ፖለቲካ ያለውን ተዛምዶ እንዲሁም ፖለቲካ ለሰው ልጅ ለምን እንዳስፈለገ የምናነብበት የመጽሐፉ ቀዳሚ ምዕራፍ ነው፡፡ ምዕራፍ ሁለት ስለ ፖለቲካና የምሁራን አስተሳሰብ፣ ፖለቲካውን አስመልክቶ ያሉ አስተሳሰቦች፣ የፖለቲካ አስተሳሰብ በቤተ እምነት ምን እንደሚመስል ያብራራልናል፡፡ በምዕራፍ ሦስት ቤተክርስቲያንና የፖለቲካ ርዕዮት፣ ቤተክርስቲያንና መንግሥት ሃማኖታዊ ፖለቲካ እንዲሁም ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችንም በመጽሐፉ ያነሳል ይሞግታል፡፡
-ምዕራፍ አራት የወጣቱ የፖለቲካ ተሳትፎ፣ ክርስቲያኖች ፖለቲካዊ ተሳትፏቸው ምን መሆን አለበት? እንዲሁም የፖለቲካዊ ተሳትፎ የምናደርገው ለምንድን ነው? በሚሉ ጥያቄዎች ተንደርድሮ በያንዳንዱ ንዑስ ርእስ አወያይ ሐሳቦችን ማስረጃ እየጠቀሰ ያስነብበናል፡፡ ምዕራፍ አምስት፣ ስድስት እና ሰባት በአጠቃላይ ስለ ፖለቲካ ፓርቲ ሚና እና የፖለቲከኛ አቋም፣ የኦርቶዶክሳዊያን ፖለቲካ መሸሽ፣ መሳተፍና አለመሳተፍ ያለው ጉዳት ምንድን ነው? እንዲሁም ስለ ፖለቲካ ንቃት በየምዕራፉ ቅደም ተከተል በመጽሐፉ በሰፊው ተብራርተውበታል፡፡ የተጋረጠብንን ችግሮች ብቻ ሳይሆን የሚያስረዳው መጽሐፉ ኦርቶዶክሳዊያን ምን ማድረግ እንደሚገባንም መፍትሔዎችንም ያስረዳል ይተነትናል፡፡
-ለማንኛውም ማንኛውም ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፉን ገዝተው ይወያዩበት ይመካከሩበት፡፡ ተግባራዊ እርምጃም እንውሰድ ሐላፊነታችንን እንወጣ፡፡
Fantahun Wakie

+መጻሕፍትንና አበውን ያናገረ መጽሐፍ+
#ጽንዐ_ተዋሕዶ
#መግቢያ
መፍቀሬ ሰብእ ክርስቶስ በኤማሁስ ሲያቀኑ የነበሩትን መንገደኞች መጻሕፍትን ተርጉሞ አእምሮ መንፈሳዊና እንደቸራቸው ሁሉ የራቀውን አቅርበው የረቀቀውን አጉልተው የሚያሳዩ በዘመን ሁሉ የተነሱ ሊቃውንትም መጸሐፍትን እየተረጎሙ የሳተውን እያረሙ የሰው ልጆች ጥራዝ ነጠቅ ፈቺ ሆነው እንዳይቀሩ ሲደርሱ ሲደጉሱ ኖረዋል።
ሃይማኖት እያቀኑ ብዙዎችን ስሁት ከሆነ ትምሕርት ነጥቀዋል በቃል የመጣውን በቃል በመጸሐፍ የመጣን በመጸሐፍ እያደረጉ ድል ነስተዋል። ዘመን የሚወልዳቸው ጸሐፍያን ደግሞ የሊቃውንቱን ትምህርት ማመሳከርያ እያደረጉ የቤተክርስቲያንን መሠረተ እምነት በጎልሕና በተረዳ አስቃኝተውናል። ከእነዚህም ውስጥ መምህር በዓማን ነጸር አንዱ ነው ብዬ አምናለው። የመስኮት ሰው ስላልሆን በመልክ ብዙዎቻችን ባናቀውም ቅሉ ባበጀው ክታበ ገጽ(fb) ላይ ጠንከር ያሉ ምን አልባትም ወተት ለለመድን ሰዎች እንደ አጥነት የጠነከሩ ጽሑፎችን ሲያጋረን እናቀዋለን። በጽሑፎቹ በጥበብ ሲገስጽ እና በብስለት ሲያስተምርም ተመልክተነዋል።
ስለ ደቂቀ እስጢፋኖስ ከአንጻሩ የሚያነጻጽር ጥንተ አብሶን ከነጓዙ የሚተነትን ቁንጸላዎችን የሚወድር ወለታ ጽድቅ በተሰኘው መጽሐፉ የተዋወቀን በአማን ነጸረ ተቀብዓ ተኮር መጽሐፋዊ ሐረጋት ጉባኤያት ታሪክና ዶግማ ከምክንያተ ጽሕፈት ከዘርዝር የነገረ ክርስቶስ ሐተታ ጋር የቀረበ ጽንዐ ተዋህዶ የተሰኘ መጽሐፍ በ2012 በገበያ ላይ አውሏል። ይሕን መጽሐፍ ባናነበው እንኳን ለብዙ ጥያቄዎች ምላሽ አንድም ማመሳከርያ ሊሆን የሚችል መጽሐፍ በመሆኑ ለትውልድ ቢሻገሩ ብዬ መምኛቸውው መጽሐፍት ውስጥ አንዱ ሆኗል።
#የምዕራፎቹ_ጭብጥ ሐሳቦች
1👉በመጀመርያው ምዕራፍ በዘመነ ሊቃውንት የተዘጋጁ ተቀብዐ ተኮር ምንባባትን ከምክንያት ጽሕፈት ጋር ያትታል። በዚህ ክፍሉ የሄሬኔዎስን÷ የባስልዮስ ዘቂሳርያን÷የጎርጎርዮስ ዘኑሲስን÷ የአርጌንስን÷የአውሳብዮስ ዘቂሳርያን÷የአርዮስን የጎርጎርዮስ ዘእንዚናንዙን÷የአትናቴዎስን የዩሐንስ አፈወርቅን÷የንስጥሮስን÷የቅዱስ ቄርሎስን የቴዎዶስዩስ ዘእስክንድርያን÷የሳዊሮስ ዘአንጾኪያን÷ ተቀብዐ ተኮር ጽሑፎችን ያብራራል አንድም "ተቀብዐ" የሚለውን ቃል በምን መልኩ ለማን እና ለምን እንደተጠቀሙበት በጥልቀት ያስረዳል። ተቀብዐን በሁለቱ ጉባኤ ቤቶች ውስጥም ያለውን ፍቺ ይገልጣል። በምንፍቅና የተወገዙትን እንዲሁም የቅዱሳን ሊቃውንት የአበው መጻሕፍት እንዲናገሩ እድል ሰጥቷል።
2👉በዘመነ ሊቃውንት ያሉትን ተቀብዕ ተኮር መጽሐፋዊ ሐረጋትና ካስቃኝ በኋላ "ተቀብዐ" በመካከለኛው ዘመን በኢትዮጵያ በተደረሱና የተተረጎሙ መጻሕፍተ ሊቃውንትን ከተጨባጭ ታሪኮች ጋር ያስቃኘናል። ሁለቱ ቤተ መነኮሳት ማለትም በቤተ ተክለሃይማኖት እና በቤተ ኤዎስጣቴዎስ የተደረገው የቅድምና ክርክርን ይተርካል። ተቀብዕ ከልሳነ ዐረብ ከተተረጎሙ ድርሰቶች ውስጥ በሃይማኖተ አበው ዘቄርሎስ÷ በሃይማኖተ አበው ዘሳዊሮስ ዘአንጾኪያ÷በሳዊሮስ ዘእስሙናይን ድርሳን÷ግብረ ሕማማት ዘሐሙስ ውስጥ ያሉትንም ሐረጋት ይመረምራል። "ተቀብዕ" ኢትዮጵያዊው ቄርሎስ በተሰኘው በአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ሥራዎች ላይም እንዴት እንደተገለጠ ያስነብባል የዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ መጽሐፈ ሚላድንም ይዳስሳል።
3👉በመቀጠል ድኅረ ምጽአተ ካቶሊክ የተደረጉ ጎባኤያትን ከሥር መሠረታቸው ይተርካል። ሱታፌ መንፈስ ቅዱስ በነገረ ሥጋዌ የተነሣበት ከካቶሊካውያን ጋር የተደረገውን የመጀመርያውን ጉባኤ÷በዐፄ ዘድንግል ዘመን የተደረገውን ጉባኤ÷ በዓፄ ሱሲንዮስ የተደረጉ ተጨማሪ ጉባኤያትን እና የነገረ ክርስቶስ አለመግባባት የወለዳቸው አመፃዎችና ምዕላዶች ከፎገራ ጉባኤ ማግሥት እስከ ፋሲለደስ ንግሥና ድረስ ያለውንም ይተርካል። በዚሁ ሳያበቃ የነገረ ክርስቶስ ምዕላዳት መጀመርና ውስጣዊ የነገረ ክርስቶስ ክፍፍሎችንም እያስቃኘ ይሔዳል። የአልፎዝ ሜንዴዝ ወደ ሐገር መምጣት÷ተቀብዐ ተኮር ትምሕርቱና የተሰጠው ምላሽ÷ከሀገር በምን መልኩ እንደለቀቀና÷በእርሱ ምክንያት ስለተደረገው ጉባኤ÷እንዲሁም የሜንዴዝ እሾሆች የተባሉትን ይገልጻል። "የቅብዓት አስተምህሮ የት መጣ" በሚለው ንዑስ ርዕስ ምዕራፍ ሦስትን ይዘጋል።
4👉በቀጣዩ ምዕራፍ ማለትም በምዕራፍ አራት ከ1624-1762 የነበረውን ዘመን ያስቃኛል በዘመነ ጎንደር በነገረ ክርስቶስ ጉዳይ የተደረጉ ክርክሮችን ይዟል። በዘመነ ፋሲል÷በዘመነ አእላፍ ሰገድ÷በዘመነ አድያም ሰገድ ኢያሱ÷ በዘመነ ንጉሥ ተክለሃይማኖት÷በዘመነ ዐፄ ቴዎፍሎስ÷በዘመነ ዐፄ ዳዊት ሣልሳይ ÷በዘመነ ዐፄ በካፋና ብርሃን ሰገድ ኢያሱ÷በዘመነ ኢዩአስ በነገረ ክርስቶስ የተደረጉ ጉባኤያትና ያለ ጉባኤ የተደረጉ አዋጆችን ይዞ እናገኘዋለን።
5👉ከዘመነ ጎንደር ወደ ዘመነ መሳፍንት ያቀናና የጸጋን አመጣጥ በአቡነ ዮሳብ ዘመነ ጵጵስና÷ጸጋ ከተዋህዶ ጋር÷የጸጋና የቅብዐት ዳግም ግንባር መፍጠር በዘመነ አቡነ ቄርሎስ÷ በስተመጨረሻም ከፕሮቴስታንታውያን ጋር የተካሄዱ የነገረ ክርስቶስ ንግግሮችን ይገልጻል።
6👉ጉባኤያት ድኀረ ዘመነ መሳፍንት እና መጽአተ አቡነ ሰላማ ሣልሳይ በምዕራፍ ስድስት ሠፍሯል። የአቡነ ሰላማ ምርጫበተመለከተ ወደ ሀገረ ኢትዮጵያ ሲመጡ ነበረውን ሃይማኖታዊና ፖለቲካዊ ነባራዊ ሁኔታ÷የአቡነ ሰላማና የዐፄ ቴዎድሮስ ጉዞ ከአምባ ጫራ እስከ መቅደላ ዘልቆ ካሳየ በኋላ ዐፄ ዮሐንስ መፍቀሬ ተዋህዶ አቋማቸውን እንዲሆም የቦሩ ጉባኤ እንዲሁም በተለምዶ ዘጠኝ መለኮት ስለሚባለው አስተምህሮ ይይዛል።
7👉ሰፊ ርዕሶችና በዛ ያሉ ንዑስ ርዕሶች የተካተቱበት ምዕራፍ ሰባት ሦስቶ የኢትዮጳውያን የነገረ ክርስቶስ ዘውጎች ካነሷቸው አርእስት ጋር ያብራራል። ተዋህዶ÷በተዋህዶ ከበር÷ሁለቱ የጸጋ አስተምህሮዎች÷ብሂለ ቅብዓት የተሰኙ ዐበይት ርዕሶች አሉት።
8 👉የመጸሐፉ የመጨረሻው ምዕራፍ ስምንት ከነገረ ክርስቶስ ጋር የተገናኙ ቅኔያትን ያስነብባል።
#ማጠቃለያ_{_የመጽሐፉ_አስፈላጊነት_}
፩👉መማርያ እና ማመሳከርያ
ይህ መጽሐፍ ጥናታዊ ስልትን የተጠቀመና ከሀገር ውጪ እንዲሁም ሀገር በቀል ድርሰቶች ተመርምረው የቀረቡበት ተቀብዐ ተኮር እና ነገረ ክርስቶስ የተዳሰሰበት በመሆኑ በቲዎሎጂ ላሉ መማርያ አልያም ማመሳከርያ ሊሆን የሚችል ክታብ ነው። በሀገራችን እንደነ አድማሱ ጀንበሬ አይነት ሊቃውንት የጻፏቸውን የመልስና የቤተክርስቲያንን አስተምህሮ የሸከፉ መጻሕፍትን ለትውልድ ከማስተላለፍ ባሻገር በመንፈሳዊ የትምሕርት ተቋማት ውስጥ እንደ ማመሳከርያ ሊቀርቡ ሲገባቸው ከግለሰቦች ውጪ ብዙ ምዕመናን እጅ ውስጥ መገኘት ተስኗቸዋል። እንዲህ ያሉ ችግር ፈቺ እና አንኳር ርዕሰ ጉዳዩች የያዙ መጽሐፎች ተመርጠው ለመማርያና ለማመሳከርያ ሊሆኑ ይገባል የሚል ቅናታዊ ሐሳብ አለኝ። ቢቻል ቢቻል የጥናትና የምርምር ማዕከል ተገንብቶ ዶግማቲክ ርዕሰ ጉዳዩች የሚዳሰሱበት መጽሐፋዊ ሐረጋትም ትንታኔ የሚሰጥባቸው ቢሆን እጅግ የተሻለ ይመስለኛል። በጥቅሉ ጽንዐ ተዋህዶ ከገበያ ሽያጭ ባለፈ ማጣቀሻ እና ማመሳከርያ ሆኖ ከቤተመዛግብት ሊቀመጥ የሚገባ ይመስለኛል።
፪👉የቤተክርስቲያንን አስተምህሮ የገለጠ
የቤተከርስቲያኒቱን አስተምህሮ ያበራል።
አንድ አንድ መጽሐፉች ላይ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማጣቀሻዎችን ከመስጠት ባሻገር የተለየ ድርሳናትነ እና ሐረጋትን እና ሐረጋትን አያትቱም። የሳተውን የሚመልሱ የመጸሐፍትን ምሥጢር እየመረመሩ እውነትን የሚገልጡ ጸሐፍት ባይኖሩ ኖሮ ለብዙ ዘመናት በተለይ በሐገራችን ሲያነታ

ርክ የቆየው የቅባት ትምሕርት እና አስተሳሰብ ርቱዓን አበው ያስተማሩትን የርትዕት ሃይማኖትን መሠረተ እምነት በቁንጽል እንዲቀር ሊያደርግ ይችሉ ነበር። "ተቀብዐ ተኮር እና ነገረ ክርስቶስን" ድርሳናትን በመመርመር መጸሐፋዊ ሐረጋትን በመተንተን በተለያዩ ጊዝያቶች የተደረጉ ጉባኤያትን በመቃኘት የቤተክርስቲያንን ተቀብዐ ተኮር አስተምህሮ ያሳያል። በዘመነ ሊቃውንት የነበሩ ደገኛ አባቶች በሚጽፏቸው ድርሰቶች በሚያስተምሯቸው ትምሕርቶች ውስጥ የቤተክርስቲያንን አስተምህሮ አጽንተው የማለፍ ልማድ አላቸው። ጽንዐ ተዋህዶም ተቀብዐ ተኮር አገላለጾችን በብስለት ከፈታ በኋላ ነገረ ተዋህዶን አጽንቶ መሥመር አስይዞ ያልፋል። የምርምርና የጥናት አካሔድን ቢጠቀምም ውጤቱ ግን የተዋህዶን ሐቅ ማስጨበጥ ነው።
፫👉ቁንጽል ሐሳቦችን ያቀናል
"ተቀብዐ ተኮር እና ነገረ ክርስቶስ ትምህርቶችን በአንድም በሌላም ማለትም በመጸሐፍም በቃልም ተምረነዋል። ነገር ግን ስለ ቅባት ሲነሳ ሊወሱ የሚገቡ የቅዱሳን ሊቃውንት ትምሕርት የተዘነጉ ነበር። ቅባት የአንድ ክህድት ትምሕርት ብቻ እንደሆነ የምናስብበት ቁንጽል ዕውቀት ነበረን። መጸሐፉ ግን ነገረ ቅባትን ለክህደት የተጠቀሙበትን ብቻ አያሳይም በዕውቀትም በሕይወትም የበረቱ ሊቃውንትን እንዴት እንደተጠቀሙበትም ያስረዳል እንጂ። ለአብነትም ባስልዮስ ዘቂሳርያ "ክርስቶስ ቅቡዕ የሚለውን የቅድሥት ሥላሴን አካላዊ ሦስትነት በነገረ ድኅነት ያላቸውን ድርሻ ከምሥጢረ ጥምቀት ጋር አያይዞ ለማሳየት ተጠቅሞበታል።" በቤተክርስቲያን ቅዱሳን ሊቃውንት መደብ ውስጥ የሚገኘው ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ "ተቀብዐን የመንፈስ ቅዱስ አምላክነትን ለማስረዳት ተጠቀሞበታል" ሊቁ ቅዱስ አትናቴዎስም "ተቀብዐ በጊዜ ሥጋዌ ሲነገር የነገረ ድኅነት ነው በዩርዳኖስ ሲሆንም የማዳን ሥራው አምሳል /ምልክት ነው/ ፍጻሜው ለእኛ ነው ቅብዓቱ ለእርሱ አልሆነም" ይላል። ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅም "ለሊሁ ቀባኢ ለሊሁ ተቀባዒ" በሚል አስተምሮበታል ከላይ ያነሳናቸው ደገኛ አባቶችን ትምሕርት በአማን ነጸር በመጽሐፉ በጥልቀት አብራርቶታል። ተቀብዓን በአርዩሳዊ አፈታት "ፍጡርነትን" የሚያሳይ ትምሕርት ብቻ አድርገን ምናስብ መጽሐፉ ተቀብዓ የሚለው ቃል ለተለያዩ መሠረታዊ አስተምህሮቸ ሊቃውንቱ እንደተጠቀሙበት በማስረዳት ቁንጽል ሐሳቦችን ያሰፋል።
፬👉አበውና መጻሕፍትን ያናገረ መጽሐፍ
በዚህ መጽሐፍ ላይ በተነሳበት ዐውድ መጻሕፍትን እና ገጸ ንባባትን ከነፍቺያቸውያስቀምጣል። ሀገር በቀል የሆኑና ከሀገር ውጪ የሆኑ ሊቃውንትን በተነሳው ርዕሰ ጉዳይ ላይ በዘመናችን መጥተው ሐሳባቸውን እንዲገልጡ አድርጓል። የሊቃውንቱን ትምሕርት ወደ እኛ እንዲቀርብ ከማድረግ አንጻርና መጻሕፍትን ከመርመር አንጻር የተዋጣለት ድንቅ መጽሐፍ ነው። ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አሥራው መጻሕፍትን ተንተርሰው የተዘጋጁ የአበው መጻሕፍትን ለነገረ ሃይማኖት ምርምር እንዴት ባለ መልኩ እንደምትጠቀምበት ያሳየና የአበው ትምሕርት ዛሬ በጥራዝ ነጠቅ ፍቺ ለተጠመዱ ሰዎች አእምሮ መንፈሳዊን የሚያደሉ መሆኑን ከዛም ባለፍ እይታቸውን እያደነቅን እንድናመሰግን እድል ሰጥቶናል። ከመጀመርያው እስከመጨረሻው መጻሕፍትን እያናገር የአበውን ትምሕርት ከማብራርያ ጋር እያደረገ በጉልህና በተረዳ ያስቀምጣል።
፭👉ታሪካዊ ማስረጃዎች
በጥልቀት መጻሕፍትን ያልመረመረ ምን አልባት እንደ እኔ ደካማ የሆነ ሰው ይህን መጽሐፍ ሲያነብ መደነቁ ማየቀር ነው በተለይ በሐገራችን የተደረጉ ጉባኤያት እና የተነሳባቸው ጠንከር ያሉ ርዕሰ ጉዳዩች "በኛ ዘመን ምን ደና መናፍቅ አለ" የሚያስብል ሽሙጥ ውስጥ የከተናል። በየጊዜው የተፈጸሙ ክስተቶችን አጥርቶ ከማሳየቱ በላይ ሲነሱ የነበሩ አስተምህሮዎችን ከታሪካዊ መነሻቸው ጋር ሰናስሎ ያቀርባል ነገረ ሃይማኖት ላይ ጠለቅ ባለ መንገድ ይመራመሩና ያጠኑ እንደነበር በታሪክ ዘውግ የቀረቡ አገላለጾች ያስረዱናል። ታሪካዊ ማስረጃዎች የተጠናከሩና ብዙ የተደከመበት መሆኑን ያሳያል።
(መጽሐፉ፡- ከትንተና ይልቅ አበውና መጻሕፍት እንዲናገሩ፣ እነርሱ ወደኛ እንዲመጡ ከመጣር ይልቅ እኛ ወደ እነርሱ እንድንቀርብ፣ በያሰኛል አመክንዮ እየተቀጣጣለ አበው ሊናገሩ ከፈለጉበት ዐውድና ንባብ እንዲሁም ንባቡ ከተነገረበት ታሪካዊ መነሻ በራቀ መልኩ ጥቅስና ሐሳቦች ርቀው እንዳይሄዱ እንዳቅሚቲ ጥረት የተደረገበት ነው፡፡ የተወገዘ አስተምህሮም ሆነ መናፍቅ ተከራካሪው ወገን በገለጠበት ሳይሆን ራሱ በተናገረው እንዲገለጥ በመመኘት ተጽፏል፡፡ በማስረጃ ምዘናና ትንተናዬም ሕሊናዬን የአንድ አካዳሚክ ጥናት መስፈርት እንዲጠቀም ተጭኜዋለሁ፡፡ (አዘጋጁ በአማን ነጸረ)
13 ያልታተሙ የግእዝና አማረኛ መጻሕፍት። 52 የታተሙ የግእዝና የአማረኛ መጻሕፈት። 84 በውጭ ሀገር ጸሐፊዎችና ቋንቋዎች የታተሙ መጻሕፍት በጠቅላላ 149 መጻሕፍትን በማጣቀሻነት የተዘጋጆ 415 ገጾችን የያዘ መጽሐፍ ነው። ባይነበብ እንኳን ለታሪክ ሊቀመጥ የሚገባ መጽሐፍ መሆኑን ልብ ይሉታል።
ይህን መጽሐፍ በ"ይከብዳል" ስም መሸሻችን ተገቢ አይደለም!
ዲ/ን ሞገስ አብረሃም

ይህ መጽሐፍ ከብዙ ሺህ ዓመታት በላይ ያልተቋረጠ የመንግሥትነት ታሪክ ያላት አገራችን ኢትዮጵያ ረጅም ዘመናትን በመጓዝ ነጻነቷን ጠብቃ ለዚህ ትውልድ እንድትደርስ በቀደምት አባቶቻችንና እናቶቻችን የተደረገውን ተጋድሎና የተከፈለውን መሥዋዕትነት የምንረዳበት ልዩ ዝክረ ሰነድ ነው። አገራችን በረጅም ጊዜ ታሪኳ ካስተናገደቻቸው አያሌ የመሥዋዕትነት ትግሎች መካከል በርካታ ኢትዮጵያውያን የደም ግብር የከፈሉበት ከ1928-1933 ዓ.ም ድረስ የዘለቀው የአምስቱ ዓመት የፋሽሽት ኢጣልያ ወረራ ተጠቃሽ ነው። በዚህ መጽሐፍ ከተዘረዘሩት ዐርበኞች ስም መረዳት እንደሚቻለው በዚያ የመከራ ዘመን ኢትዮጵያውያን የቋንቋ፣ የብሔር፣ የጎሳ፣ የሃይማኖት፣ የጾታ ወዘተ ልዩነት ሳይገድባቸው ለአገር አንድነት፣ ነጻነትና ክብር ያደረጉትን የሕይወት መሥዋዕትነት ነው። ይህ መጽሐፍ ኢትዮጵያዊነት በደም የተገነባ የመሥዋዕትነት ታሪካችን፤ በጽኑ መሠረት ላይ የተጣለ የአብሮነት ሐውልት መሆኑን የምንረዳበት የዕውቀት ዐምድ ነው። ጸሓፊው መዝገቡ ከፍያለው ይህ ትውልድ ቀደምት ኢትዮጵያውያን በአንድነት በከፈሉት የደም መሰዋዕትነት ያስረከቡትን አገር በድርሻው ጠብቆ ለመጭው ትውልድ ለማስተላለፍ ያለበትን አደራና ኀላፊነት የሚያስገነዝብ በመሆኑ ታላቅ ምስጋና ይገባዋል። የብዙ ጥረትና ድካም ውጤት የሆነውን ይህን የመጀመሪያውን ቅጽ ያበረከተልን ወንድማችን ቀጣዩን ደግሞ በቅርብ እንካችሁ እንደሚለን ባለሙሉ ተስፋ ነኝ።
ቀሲስ ዶ/ር መንግስቱ ጎበዜ
በአ.አ.ዩ የታሪክ፤አርኪዮሎጂና ቅርስ መ/ር
ቀሲስ ዶ/ር መንግስቱ ጎበዜ
በአ.አ.ዩ የታሪክ፤አርኪዮሎጂና ቅርስ መ/ር