የቦሌ ክ/ከተማ የሕግ ስርፀትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት
275 subscribers
366 photos
3 videos
137 files
97 links
ይህ የቦሌ ክ/ከተማ የሕግ ስርጸትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት ቻናል ስለኢትዮጵያ ሕጎች)ማብራሪያ የሚሰጥበት፣ አዳዲስ ሕጎች የሚጋሩበት፣ ሕግ ነክ ዜናዎችና መረጃዎች የሚተላለፉበት፣ በዳይሬክቶሬቱ የተሰጡ የንቃተ-ሕግ ስልጠናዎች፣ የሕግ መልዕክቶች፣ በራሪ ጽሑፎች እና መሰል ሰነዶች የሚለቀቁበት ነው።
መልካም ቆይታ!
Download Telegram
በ25/12/2013 ዓ.ም ቦሌ ክ/ከተማ አስተዳደር ዐቃቤ ሕግ ጽ/ቤት ባዘጋጀው የ2013 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት እንዲሁም የ2014 በጀት ዓመት ዕቅድ ውይይት 18 ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ ከፖሊስ መምሪያ፣ከሴት ማህበር እና ከሰላምና ፀጥታ ይገኙበታል። ውይይቱ ላይ በጽ/ቤቱ ስር የሚገኙትን 2 ዳይሬክቶሬቶች ጨምሮ የቁልፍ ተግባራት አፈጻጸምን እና አበይት ተግባራትን የጽ/ቤቱ ባለሙያ ወ/ሮ ፀሐይ ማራኪ በሆነ መልኩ ያቀረቡልን ሲሆን በጥንካሬ ከተጠቀሱት ውስጥ፡-
1.የመንግስትንና የሕዝብ ጥቅም ማስጠበቅን በተመለከተ በፍትሕብሔር ከ19 ሚሊዮን ብር በላይ ማስጠበቅ መቻሉ
2. አመራሩና ፈጻሚው ተቀናጅቶ መሥራት በመቻሉና ለባለሙያው የአቅም ግንባታ ሥልጠና በመሠጠቱ የጽ/ቤቱ አፈጻጸም ውጤት ከፍ ማለቱ
3. የወንጀል ክሶች በቅርበት ለተገልጋዩ ዐቃቤያን ሕግ በየፖሊስ ጣቢያው መመደባቸው ለሥራው ውጤት ማምጣቱ
4. የደንብ ጥሰት ክስ በወረዳ ማህበራዊ ፍ/ቤት ውሳኔ ማግኘቱ
5. የሕግ ጽሑፎች ለህብረተሰቡ በቴሌግራም ቻናል፣በብሮሸር፣በቲቪ ስክሪን፣በመድረክ፣በመጽሔት ተደራሽ መሆናቸው
6. ለሴቶች ተሳትፎ የተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና መሠጠቱ ጥቂቶቹ ሰሆኑ ጥሪ የተደረገላቸው ባለድርሻ አካላትም የቀረበውን ሰነድ መሠረት በማድረግ የተለያዩ ገንቢ የሆኑ አስተያየቶችና ምላሽ የሚፈልጉ ጥያቄዎችን አንሸራሽረዋል። ውሳኔ ማስፈፀም ላይ ከሳሽ አካላት ውሳኔውን ተቀብሎ ማስፈፀም አለመቻሉና የዋስ መብት በተገቢው መልኩ አለመተግበሩ ከተጠሩት ባለድርሻ አካላት ክፍተት ናቸው ተብለው የተነሱ ናቸው። በመድረኩ ከተንሸራሸሩ አስተያየቶች ለአከባቢ ፀጥታ ሁሉም በየአከባቢው በብሎክ አደረጃጀት ቢጠናከር እና ከፖሊስ ጋር በቅንጅት ብንሰራ ወንጀል ይቀንሳል የተባለው እንደ ግብዓት ከተወሰዱት ውስጥ...
…የቀጠለ
ሲሆን በይበልጥ ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገባቸውን ሥራዎች በ2014 በጀት ዓመት ጽ/ቤታቸው ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራበት ቃል ገብተዋል።
መልካም የሥራ ዘመን ይሁንልን!
ዛሬ ጳጉሜ 2 ቀን 2013 ዓ.ም በቦሌ ክ/ከተማ አስተዳደር ዐቃቤ ሕግ ጽ/ቤት ስር ያለን የሁለቱም ዳይሬክቶሬቶች ሰራተኞች፣የጽ/ቤቱ ሰራተኞች እንዲሁም ደግሞ ተጋባዥ እንግዶች ባሉበት የአገልጋይነት ክብር ቀንን በዚህ መልኩ ያከበርን ሲሆን የጽ/ቤቱ ኃላፊ ወ/ሮ አንቀጸ ከጽ/ቤቱ እና ከሁለቱም ዳይሬክቶሬቶች ለተውጣጡ 3 ሴት ሰራተኞች የእንቁላል ሽልማት አበርክተዋል፡፡
አዲሱ ዓመት የሰላም፣የፍቅርና የብልፅግና ይሁንላችሁ!
ጤና ይስጥልኝ
ክቡራትና ክቡራን እንኳን ለ2014 አዲስ አመት መዳረሻ አደረሳችሁ
በዓሉን ስታከብሩ የዴልታ ኮሮና ቫይረስ መግባቱንና ብዙ ዜጎቻችንን ታማሚ ሆነው የጤና ማዕከላት ማስተናገድ ከሚችሉት በላይ ሆኖባቸው እንዳለ በማስታወስ በመመሪያ ቁጥር 30/13 መሰረት ርቀታችሁን በመጠበቅ፤
የአፍ መሸፈኛ ሳታደርጉ ባለመንቀሳቀስ፤
መነፋፈቅ ቢኖርም መሳሳምንና መጨባበጥን በማስወገድ፤
ከወንጀል በመራቅ ጠጥቶ አለመንዳትን፤ የተፈጸመ ወንጀልን በመጠቆም ለፍትህ መስፈን አስተዋጽዖ በማድረግ ያዩትን ባለመመስከር ተጠያቂ ላለመሆንም ሆነ ከወንጀል የራቀ ማህበረሰብ ለመፍጠር ለሚደረገው ጥረት አስተዋጽኦ በማድረግ፤
ሲገዙም ሆነ ሲሸጡ ተገቢውን ጥራትና ዋጋ መሰረት ባደረገ መልኩ እንዲሆን፤
የበዓላቱንም ሆነ በዋዜማው ሲዝናኑ የድምጽም ሆነ የቆሻሻ አወጋገድዎ ህግንና የሌላውን ጤንነትና ምቾት ያልተጋፋ እንዲሆን ይህ ባይሆን ደግሞ በወንጀልም ሆነ በሌሎቹ ሕጎች የሚያስቀጣና በዓልዎን በቤትዎ ሳይሆን በሕግ ቁጥጥር ስር አድርጎወት የራስዎትን ብቻ ሳይሆን የወዳጆችዎን ደስታ እንዳያበላሹ የቦሌ ክፍለ ከተማ ዐቃቤ ሕግ ጽ/ቤት የሕግ ስርጸትና ምክር መስጠት ከልብ በመነጨ ወገንተኝነት ያስታውሰዎታል!!

መልካም አዲስ አመት
ሲሳይ ሰማኝ
ጳጉሜ 4/2013 ዓ.ም
ጤና ይስጥልኝ!!!
አዲሱን ዓመት ከጀመርን 13 ቀናት አልፈው መስከረምን አጋምሰነዋል፡፡ ይህ የሆነው በጤና በመኖራችን አይደል!
በዚህ ሳምንት የጤና ሚኒስትርዋ ለብዙሀን መገናኛዎች በሰጡት መግለጫ ኮቪድን ለመከላከል የሚደረገው ጥረት አካል የሆነውን ክትባት መውሰድ የቻሉት 2.6 ሚሊዮን ሰዎች ብቻ መሆናቸውንና ሌሎችን ለመከተብ በሀገሪቱ 1.5 ሚሊዮን ክትባቶች ቢሰራጩም ሕዝቡ ለመከተብ ያለው ፍላጎት ዝቅተኛ መሆኑን ይህ ደግሞ የመከላከል ጥረቱን አድካሚ አድርጎታል ሲሉ ገልጸዋል፡፡
ውድ የዚህ መልዕክት አንባቢ ከዚህ በፊት በ2013 መጀመሪያ የወጣውን መመሪያ ቁጥር 30/2013 በዚህ ቴሌግራምም ሆነ በሌሎቹ መገናኛ ብዙሃን በተደጋጋሚ የተወራና በዝርዝር የቀረበ ቢሆንም ምን ያህል ተግብረዋል?
የተከለከሉት ተግባራት፡-
ርቀትን ሳይጠብቁ መሄድም ሆነ ብዙ ሰው ባለበት መገኘት፤
የፊት መሸፈኛ ሳያደርጉ ከሰው ጋር አለመቀላቀል፤
በማንኛውም መልኩ አለመጨባበጥና አለመሳሳም፤
ከ50 ሰዎች በላይ በቀብር ጊዜ እንዳይገኙ ማድረግ፤
በቂ የኮቪድ መከላከያ ንጽህና መጠበቂያ ግብዓቶችን ሳያሟሉ የአገልግሎት መስጫ ተቋማትን ክፍት አለማድረግ፤
በስብሰባ፣ በስልጠና፣ በክብረበዓላትና በሰርግ አዳራሹ መያዝ ከሚችለው 1/4/ ብቻ መገኘት እንዳለበት የተደነገገው ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ተጥሶ ኮቪድ እንደመጣ በየአገልግሎት መስጫ ተቋማቱ በር ላይ ይደረግ የነበረው መታጠቢያ ውሃና ሳሙና የት አለ?
የእጅ ንጽህና መጠበቂያ አልኮል የትኛው ድርጅት ያቀርባል?
በጤና ሚንስትሯ ገለጻ እንደተገለጸው በአዲስ አበባ በፊት የፊት መሸፈኛ ያደርግ የነበረው ነዋሪ እስከ 83 ፐርሰንት ደርሶ የነበረ ቢሆንም አሁን ሶስተኛው ማዕበል እየተስፋፋ ባለበት ወቅት ከ52 ፐርሰንት በላይ የማያደርግ ሕዝብ ሲሆን ከአዲስ አበባ ሲወጣ የማያደርገው ሰው እስከ 100 ፐርሰንት ይደርሳል፡፡
እባካቹን ለራሳችን ባናስብ በኛ ቸልተኝነት የቅርቦቻችን፤ የለፉብንን ወላጆችና ሀገር ባናከስርና ለኛ ጤና ሲባሉ የወጡ ሕግጋትን እናክብር!!
ለሕግ አክባሪዎች ክብርና ጤንነት ይሁን!!
ሲሳይ ሰማኝ (መስከረም 13/2014 ዓ.ም