የቦሌ ክ/ከተማ የሕግ ስርፀትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት
276 subscribers
366 photos
3 videos
137 files
97 links
ይህ የቦሌ ክ/ከተማ የሕግ ስርጸትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት ቻናል ስለኢትዮጵያ ሕጎች)ማብራሪያ የሚሰጥበት፣ አዳዲስ ሕጎች የሚጋሩበት፣ ሕግ ነክ ዜናዎችና መረጃዎች የሚተላለፉበት፣ በዳይሬክቶሬቱ የተሰጡ የንቃተ-ሕግ ስልጠናዎች፣ የሕግ መልዕክቶች፣ በራሪ ጽሑፎች እና መሰል ሰነዶች የሚለቀቁበት ነው።
መልካም ቆይታ!
Download Telegram
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
በፎቶሾፕ ከሚቀናበሩ የምርጫ ውጤቶች ተጠንቀቁ !

የምርጫ ጣቢያዎች ውጤት እያሳወቁ ይገኛሉ።

በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች የተለያዩ የምርጫ ጣቢያዎች ውጤት ናቸው የተባሉ ወረቀቶች እየተለጠፉ ነው።

ነገር ግን ወረቀቶቹ ላይ ያሉትን ቁጥሮች በፎቶሾፕ የመነካካት፣ የማስተካከል ምልክቶችን ታዝበናል።

በተለይ የቲክቫህ አባላት በሙሉ ፦

1ኛ. ዘመኑ የረቀቀ ነውና የምርጫ ውጤትን በተመለከተ ትክክለኛው ሪፖርት እስኪላክላችሁ ታገሱ

2ኛ. ድምፅ የሰጣችሁበት የምርጫ ጣቢያ #በአካል ተገኝታችሁ የተለጠፈውን ውጤት እንድትመለከቱ እናበረታታለን።

የውጤት ጉዳይ በጥንቃቄ ካልተያዘ እስካሁን የተመጣበትን #ሰላማዊ ሂደትን ሊያበላሽ ስለሚችል ከሀሰተኛ መረጃዎች/በይፋ በምርጫ ቦርድ ካልተረጋገጡ ሪፖርቶች ሁሉ እንድትርቁ አደራ እንላለን።

@tikvahethiopia
እንደስም ማጥፋትና ስድብ ያሉ የወንጀል ጉዳዮች በፌዴራል ፍርድ ቤቶች መታየታቸው ቀረ

ሐምሌ 13 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ በግል አቤቱታ አቅራቢነት ክስ የሚመሠረትባቸው የወንጀል ጉዳዮች እና በግለሰቦች መካከል የሚደረጉ እስከ ብር 500 ሺ የገንዘብ፣ ውልና ብድር የፍትሐ ብሄር ጉዳዮች በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ እና በፌዴራል ፍርድ ቤት መታየታቸው ቀርቶ በአዲስ አበባ ከተማ እና በድሬደዋ ከተማ አስተዳደር ዐቃቤ ሕግ ቢሮ እና ፍርድ ቤቶች መታየት ይጀምራሉ፡፡

በዚህም ምክንያት ከተጠቀሰው እለት አንስቶ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ እነኚህን ጉዳዮች ተቀብሎ የማያስተናግድ በመሆኑ እንደ ስድብ፣ ስም ማጥፋት፣ ዛቻ እና ሌሎች ቀላል እና በተበዳዩ አቤቱታ መሰረት ክስ የሚያስመሰርቱ ጉዳዮች እንዲመረመሩለት የሚፈልግ ወይም የዋጋ ግምቱ ከ500 ሺ ብር በታች የሆነ የፍትሀብሄር ክስ ማቅረብ የሚፈልግ ማንኛውም ሰው አቤቱታውን ወንጀሉ የተፈጸመበት ቦታ ለሚገኘው ፖሊስ ጣቢያ ወይም ለከተማ አስተዳደሩ ዐቃቤ ሕግ ቢሮ እና ፍርድ ቤት እንዲያቀርብ አሳስቧል።
በየግልግል ዳኝነት እና የዕርቅ አሠራር ሥርዓት አዋጅ ቁጥር 1237/2013 አንቀጽ 8 ንዑስ 4 መሰረት የግልግል ዳኝነት ስምምነቱን መኖር በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ አለማንሳት የግልግግል ዳኝነት ስምምነቱን ቀሪ እንደሆነ ያስቆጥረዋል፡፡
ቸር ያሰማን! (14/11/2013 ዓ.ም) (ኦምኒኤል)
በየግልግል ዳኝነት እና የዕርቅ አሠራር ሥርዓት አዋጅ ቁጥር 1237/2013 አንቀጽ 7 መሰረት ከታች የተዘረዘሩት ጉዳዮች ለግልግል ዳኝነት አይቀርቡም፡-
የፍች፣የጉዲፊቻ፣የአሳዳሪነት፣የሞግዚትነት እና የውርስ ጉዳዮች፣
የወንጀል ጉዳዮች፣
የግብር ጉዳዮች፣
መክሰር ላይ የሚሰጥ ውሳኔ፣
የንግድ ማሕበራት መፍረስ ላይ የሚሰጥ ውሳኔ
የሊዝ ጉዳይን ጨምሮ አጠቃላይ የመሬት ጉዳዮች፣
አስተዳደራዊ ውሎች በልዩ ሁኔታ በሕግ ካልተፈቀደ በስተቀር፣
የንግድ ውድድርና የሸማቾች ጥበቃ፣
በሕግ ለሚመለከታቸው አስተዳደራዊ አካላት በተሰጠ ሥልጣን ሥር የሚሸፈኑ አስተዳደራዊ አለመግባባቶች፣
በግልግል እንዳይታዩ በሕግ የተከለከሉ ሌሎች ጉዳዮች፣
በዕርቅ ሂደት በአንደኛው ተዋዋይ ወገን የተሰጠ የእምነት ቃል፣
በአስታራቂው የቀረበ የዕርቅ ሀሳብ እና በአስታራቂው የቀረበውን የዕርቅ ሀሳብ ለመቀበል በአንደኛው ተዋዋይ ወገን የተሰጠ ፈቃደኝነት

ቸር ያሰማን! (14/11/2013 ዓ.ም) (ኦምኒኤል)
ከሀምሌ 13 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ በግል አቤቱታ አቅራቢነት ክስ የሚመሠረትባቸው የወንጀል ጉዳዮች እና በግለሰቦች መካከል የሚደረጉ እስከ ብር 500,000 የገንዘብ፣ ውልና ብድር የፍትሐ ብሄር ጉዳዮች በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ እና በፌዴራል ፍርድ ቤት መታየታቸው ቀርቶ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዐቃቤ ሕግ ቢሮ እና በአዲስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤቶች መታየት ይጀምራሉ፡፡

በዚህም ምክንያት ከተጠቀሰው እለት አንስቶ ቦሌ ክፍለ ከተማ ዐቃቤ ህግ ጽ/ቤት እነኚህን ጉዳዮች ተቀብሎ የሚያስተናግድ በመሆኑ በተበዳዩ አቤቱታ መሰረት ክስ የሚያስመሰርቱ ጉዳዮች እንዲመረመሩለት የሚፈልግ ወይም የዋጋ ግምቱ ከ500,000 ብር በታች የሆነ የፍትሀብሄር ክስ ማቅረብ የሚፈልግ ማንኛውም ሰው አቤቱታውን ወንጀሉ የተፈጸመበት ቦታ ለሚገኘው ፖሊስ ጣቢያ ወይም ለክ/ከተማ ዐቃቤ ሕግ ፅ/ቤት በመቅረብ መስተናገድ የምትችሉ ሲሆን ክሱ የሚታየውም (የዳኝነት ስልጣን) በአዲስ አበባ ፍ/ቤቶች መሆኑን ጨምረን እንገልጻለን ።
ከሐምሌ 13/2013 ጀምሮ የአዲስ አበባ እና ድሬዳዋ ፍርድ ቤቶች የወንጀል ጉዳዮች የዳኝነት ስልጣን
**************************************************************
በፌደራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ 1234/2013 ዓ.ም ጥር 13/2013ዓ.ም በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መፅደቁ የሚታወቅ ሲሆን የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ከሐምሌ 13/2013 ዓ.ም ጀምሮ ከዚህ በታች በተዘረዘሩ የወንጀል ጉዳዮች ላይ የዳኝነት ስልጣን አይኖረውም፡፡
 በሌሎች ሕጎች የተጠቀሱ ጉዳዮች እንደተጠበቁ ሆኖ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍርድ ቤቶች እና የድሬደዋ ከተማ ፍርድ ቤቶች በቻርተር አዋጆች ከተሰጣቸው የደንብ መተላለፍና በወ/መ/ስ/ስ/ሕጉ መሰረት ከሚቀርብላቸው ጉዳዮች በተጨማሪ በግል አቤቱታ አቅራቢነት የሚቀርቡ የወንጀል ጉዳዮ በከተማ መስተዳደር ፍርድ ቤቶች እንደሚስተናገዱ በአዋጁ አንቀጽ 4(16) የተደነገገ በመሆኑ የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ከሐምሌ 13 ጀምሮ በግል አቤቱታ አቅራቢነት የሚቀርቡ የወንጀል ጉዳዮችን ተቀብለው አያስተናግዱም፡፡
በዚሁ መሰረት በአዲስ አበባ እና ድሬዳዋ ከሐምሌ 13 ጀምሮ በወንጀል ሕጉ ላይ የተደነገጉ ከዚህ የሚከተሉት የወንጀል ጉዳዮች ማስተናገድ ይጀምራሉ ፡-
• አንቀፅ 261 በውጭ አገር መንግስት ላይ የሚደረግ የተቃዋሚ ድርጊት
o አንቀፅ 262 የውጭ አገር መንግስትን ግዛት መጣስ
o አንቀፅ 264 የውጭ አገር መንግስታትን ማዋረድ
o አንቀፅ 265 የታወቁ የውጭ አገር ምልክቶች ማዋረድ
o አንቀፅ 266 በመንግስታት መካከል የተቋሙ ድርጅቶችን ማዋረድ
o አንቀፅ 267 የውለታ መመለስ /principle of reciprocity/
o አንቀጽ 380 /2/ ሰነዶችን ማጥፋት
o ወንጀሉ የተፈፀመው በቤተሰብ አባል ፣ ቅርብ ዘመድ፣ በጥቅም ወይም በፍቅር በተሳሰረ ወይም አብሮነት በሚኖር ሰው ላይ ሲሆን
o አንቀጽ 399/1/ በሞያ ወይም በስራ ምክንያት የታወቀ ምስጢር መግለጽ
o አንቀጽ 556/1/ ቀላል አካል ጉዳት ማድረስ
o አንቀጽ 559 /3/ በቸልተኝነት የሚፈፀም ቀላል አካል ጉዳት ማድረስ
o አንቀጽ 560 እጅ እልፊት
o አንቀጽ 580 ዛቻ
o አንቀጽ 583/1/ የመወሰን ችሎታን ማሳጣት ተደራራቢ ሲሆን
o አንቀጽ 593 ወላጆች ልጆቻቸውን ሲጠልፉ
o አንቀጽ 603 የስራ ነፃነት መብትን መጣስ
o አንቀጽ 606 የመጻጻፍ ወይም የግንኙነት ግላዊት መብትን መድፈር
o አንቀጽ 613 /1-4/ ስም ማጥፋትና የሀሰት ሀሜት
o አንቀጽ 615 እና 618 ስድብና ማዋረድ
o አንቀጽ 625 አንድ ሴት ያለባትን ከፍ ያለችግር ወይም ጥገኝነትዋን ምክንያት በማድረግ የሚፈፀም ድርጊት
o አንቀጽ 643/2/ ለመልካም ጠባይ ተቃራኒ የሆኑ መግለጫዎችና ማስታወቂያዎች
o አንቀጽ 642/2/ ጋብቻን በተንኮል ወይም በማታለል መፈፀም
o አንቀጽ 652/1-2/ አመንዝራነት
o አንቀጽ 658 ቀለብ መስጠት ግዴታን አለመፈፀም
o አንቀጽ 667 የጋራ ንብረት መስረቅ
o አንቀጽ 679 አግኝቶ መደበቅ
o አንቀጽ 680 ወድቆ የተገኘውን ንብረት ለራስ ማድረግ
o አንቀጽ 685 በከብት መንጋ አማካኝነት በሌላ ሰው ንብረት ላይ ጉዳት ማድረስ
o አንቀጽ 686 /1/ በሰው ንብረት ላይ ሁከት ማድረግ
o አንቀጽ 689-691 በሌላ ሰው ንብረት ላይ ጉዳት ማድረስ
o አንቀጽ 700 በህዝብ እምነት በመጠቀም ማታለል
o አንቀጽ 704 ጥቅም ታገኛለህ በማለት ሌላውን ሰው በመደለል ማነሳሳት
o አንቀጽ 705 ችሎታ የሌላቸውን ሰዎች ንብረታቸውን የሚጎዳ ስራ እንዲፈጽሙ ማነሳሳት
o አንቀጽ 717 ግዙፍነት በሌላቸው በሌላ ሰው መልካም ስም ላይ ጉዳት ማድረስ
o አንቀጽ 718 ጉዳትን የሚያደርሱ ሀሰተኛ መግለጫዎች
o አንቀጽ 719 ተገቢ ያልሆነ የንግድ ውድድር
o አንቀጽ 725 በማጭበርበር እዳ መክፈል አለመቻል
👍1
አንድ ፍርድ እንደገና እንዲታይ በመጀመሪያ ፍርዱን በሰጠዉ ፍ/ቤት እንደገና ስለሚታይበት ሁኔታ
1. የስነ-ስርዓት ጉድለት
2. አዲስ መስረጃ ማግኘት
3. መቃወሚያ
የስነ-ስርዓት ጉድለት
ፍርዱን የሰጠዉ ፍ/ቤት የሕጉን ድንጋጌዎች ባለመከተሉ የሥነ-ሥርዓት ጉድለት የፈጸመ እደሆነና ይህም ጉድለት አንዱን ተከራካሪ ወገን በሚጎዳ ሁኔታ የጉዳዩን ዉሣኔ አሰጣጥ በእጅጉ ያዛባዉ እንደሆነ ፍርዱን ሊያነሣዉ ይችላል፡፡
የሥነ-ስርዓት ጉድለቱ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ከመቅረቡ በፊት ወይም በዚሁ የክርክር ሂደት የተፈጸመ እንደሆነ በሥነ-ሥርዓቱ ጉለት ምክንያት በደል ደረሰብኝ የሚለዉ ተከራካሪ ተቃዉሞዉን በዚያዉ ጊዜ ማቅረብ አለበት፡፡
ጉድለቱ የተፈጸመዉ የሥነ-ሥርዓት ደንቦችን ባለመከተል የሆነ እንደሆነ ፍ/ቤቱ በራሱ ወይም በአንዱ ተከራካሪ ጠያቂነት የክርክሩን ሂደት በሙሉ ወይም በከፊል በጉድለቱ ምክንያት ሊሰርዘዉ ሊያሻሽለዉ ወይም ተገቢ መስሎ የታየዉን ሌላ ትዕዛዝ ሊሰጥ ይችላል፡፡
ፍ/ቤቱ በተሰጠዉ መጥሪያ በወሰነዉ ፍርድ በሰጠዉ ዉሣኔና ትዕዛዝ ላይ የአጻጻፍ ሥህተት፤ የቁጥር አጻጻፍ ጉድለት ወይም ያልታሰበና ባለማስተዋል የተዘለለ ድንገተኛ የቃል ሥህተት መኖሩን ያረጋገጠ እንደሆነ ወይም ከባለጉዳዮቹ አንዱ ሲያመለክት በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 107 የተነገረዉን የስነ ሥርዓት ጉድለት ካልሆነ በቀር ፍ/ቤቱ ሊያርመዉ ይችላል፡፡
የተሰጠዉን ዉሣኔ በመሠረታዊነት ሊለዉጥ የሚችል ወይም በተከራካሪ ወገን ላይ ጉዳት ሊያደርስ የሚችል ከሆነ ፍ/ቤቱ የክርክሩን ሂደት መሰረዝ ቀጠሮ ሰጥቶ እንደ አዲስ ክርክር እንዲካሄድ ካደረገ በኋላ ዉሣኔ ይሰጣል፡፡ ዉሣኔዉ መሰረታዊ ጉድለት የማያደርስ ከሆነና ጉድለቱ ሊታረም የሚችል ከሆነ የክርክሩ ሂደት ላይሰረዝ ይችላል፡፡
የስነ-ስርዓት ጉድለቱ እንደ ይግባን ምክንያት ሊሆን የሚችለዉ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 209 መሰረት ማመልከቻ ካልቀረበና ጉድለቱ ከተሰጠዉ ፍርድ ወይም ዉሳኔ ጋር የተያያዘ ከሆነ ነዉ፡፡
የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 209(3)፤ 207፤ 209(1)፤ 208፤ 210(1)፤ 211
ሴድለር
ህድአት ሐምሌ/2013 ዓ.ም
አዲስ ማስረጃ ስለማግኘት
ይግባኝ ሊቀርብበት የሚችል ፍርድ፤ ዉሣኔ ወይም ትዕዛዝ ተሰጥቶ ግን ደግሞ ቅሬታ አቅርቦ ከማሰማቱ በፊት፤ ወይም
ይግባኝ ለማቅረብ ያልተፈቀደበት ፍርድ፤ ዉሣኔ ወይም ትዕዛዝ ቢሰጥ፤
1/ የመጨረሻዉ ፍርድ ከተሰጠ በኃላ ሀሰተኛ ሰነድ ወይም ሀሰተኛ የምስክርነት ቃል ወይም መደለያ እንዳልተደረገና አቤት ባዩም ፍርድ ከመስጠት በፊት አስፈላጊዉን ትጋት አድርጎ ለማወቅ ያለመቻሉን በሚገባ ለማስረዳት የሚችል ከሆነ፤
2/ እነዚህ ጉዮች መኖራቸዉ ወይ መፈጸማቸዉ ታዉቆና ተገልጾ ቢሆን ኖሮ ለፍርዱ መለወጥ ወይም መሻሻል በቂ ምክንያት ሊሆኑ ይችል እንደነበር ለማስረዳት የቻለ እንደሆነ፤
ፍርዱን፤ ትዕዛዙን ወይም ዉሣኔዉን ለሰጠዉ ፍ/ቤት አቤቱታዉን ለማቅረብ ይችላል፡፡
የተሰጠዉን ፍርድ ሊያስለዉጥ የሚችል አድስ ማስረጃ ማግኘቱ ብቻ ፍርዱ እንደገና እንዲታይ አያደርገዉም፡፡ የተገኘዉ ማስረጃ ፍርዱ በማሣሣት ያበላሸ ተገቢ ያልሆነ ድርጊትን የሚያሳይ መሆን አለበት፡፡ ይህ አይነት አቤቱታ ማስረጃዉ ከተገኘበት ቀን ጀምሮ በአንድ ዉር ጊዜ ዉስጥ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 6
ሴድለር
ህድአት ሐምሌ/2013 ዓ.ም
ጤና ይስጥልኝ ፡-
ስለኃላፊነቱ የተወሰነ የንግድ ማህበር ስራ አስኪያጅ ከንግድ ሕጉ አንጻር የሚከተለዉን እናቅርብ፡-
መልካም ምንባብ፤
የአክስዮን ማህበር ወይም የኩባንያ ስራ አስኪያጅ የሆነ ሰዉ ድርጅቱ የሚያዝበት ገንዘብ እንደሌለዉ እየወቀ በድርጅቱ ስም በሚያወጣዉ (በሚሰጠዉ )ቼክ በኃላፊነት ሊያስጠይቀዉ የሚችልና ስራ አስኪያጁ በንግድ ሕጉ የተመለከቱትን ድንጋጌዎች ወይም የኩባንያዉን መተዳደሪያ ደንብ በመጣስ መስራቱ የተረጋገጠ እንደሆነ ከድርጅቱ ጋር በአንድነት ወይም እንደነገሩ ሁኔታ በተናጠል ሊጠየቅ የሚችል መሆኑን ግብዛቤ እንያዝበት፡፡
ሐምሌ 2013ዓ.ም
ደረጀ ማርቆስ
ጤና ይስጥልኝ ፡-
ግለሰቦችም ይሁኑ አበዳሪ ተቋማት በብድር ዉላቸዉ ላይ ባመለከቱት ወለድ ብቻ እንደሚገደዱ የሚከተለዉን እናቅርብ
መልካም ምንባብ፤
ፍ/ቤት ተከራካሪ ወገኖች ወለድን አስመልክቶ በዉላቸዉ ካመለከቱት ሃሳብ ዉጪ የራሱን ስሌት መሰረት በሚደረግ ዉሳኔ መስጠት እንደማይችል በፍትሐ-ብሔር ሕጉ ላይ ተደንግጎ ይገኛል፡፡
ሐምሌ 2013ዓ.ም
ደረጀ ማርቆስ
ከጥር 13 ቀን 2013 ዓ.ም ከዚሀ በፊት የነበረውን የፌደራል ፍ/ቤቶች አዋጅ ቁጥር 25/1988 እና አዋጁን ለማሻሻል የወጡትን ማሻሻያዎችን በመሻር ተግባር ላይ የዋለው የፌደራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 የፍትሐብሔር የዳኝነት ሥልጣንን በተመለከተ የፌደራል ፍርድ ቤቶች በሚከተሉት የፍትሐ ብሔር ጉዳዮች ላይ የዳኝነት ሠልጣን ይኖራቸዋል፡-
1. የግለሰብ ዓለም አቀፍ ሕግን በሚመለከቱ ጉዳዮች፤
2. የውጭ ሀገርን ፍርድ ወይም ብይን ማስፀም በሚቀርብ አቤቱታ፤
3. ዜግነትን በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ በሚነሱ ክርክሮች፣
4. ከመክሰር ጋር በተያያዙ ጉዳዮች፤
5. ዓለም አቀፍ የዲኘሎማቲክ ሕጎችና ልምዶች እንዲሁም ኢትዮጵያ አባል የሆነችባቸው ሌሎች ዓለም አቀፍ ስምምነቶች እንደተጠበቁ ሆነው፤ የውጭ ሀገር አምባሳደሮች፣ ቆንስላዎች፣ የዓለም አቀፍ ድርጅቶች፣ የውጭ መንግሥታት ወኪሎች ተጠያቂ በሆኑባቸው ወይም/እና ልዩ መብትና ጥበቃ ያላቸው በኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖሩ የውጭ ሀገር ሰዎች ተከራካሪ በሆኑበት ጉዳዮች፣
6. የፌደራል መንግሥት አካል ተከራካሪ በሆነበት ጉዳይ
7. የፌደራል መንግሥቱን ንብረቶች በተመለከተ የሚነሱ ጉዳዮች፤
8. መደበኛ ነዋሪነታቸው በተለያዩ ክልሎች፣ በክልል እና በአዲስ አበባ ከተማ፣ በክልል እና በድሬዳዋ ከተማ፣ በአዲስ አበባ ወይም በድሬዳዋ ከተማ ውስጥ በሆኑ ሰዎች መካከል የሚነሱ ጉዳዮች፣
9. የፌደራል መንግሥቱ ባለሥልጣኖችና ሠራተኞች በስራቸዉ ወይም በሃላፊነታቸዉ ምክንያት ኃላፊ በሚሆኑባቸው ጉዳዮች፣
10. በፌደራል መንግሥቱ አካላት የተመዘገቡ ወይም የተቋቋሙ የንግድ ድርጅቶችና ማህበሮችን በሚመለከት የሚነሱ ክርክሮች፣
11. የሚተላፉየገንዘብ ሰነዶች በተመለከተ የሚነሱ ክርክሮች
12. በፈጠራ፣ በድርሰትና ሥነ ጥበብ፣ ቅጅ እና ተዛማጅ መብቶች ባለቤትነት በተመለከተ የሚነሱ ክርክሮች
13. የኢንሹራንስ ውልን በተመለከተ የሚነሱ ክርክሮች፣
14. ተገዶ የመያዝ ሕጋዊነትን ለማጣራት የሚቀርብ አቤቱታ፤
15. ለከተማ አስተዳደር ፍርድ ቤቶች በቻርተር አዋጅ የተሰጣቸው የፍትሀብሔር ዳኝነት ሥልጣን ማለትም በወሳኝ ኩነት ምዝገባ እና መታዎቂያ ወረቀት ህግ መሠረት በሚሰጥ ሰነድ ጋር በተያያዘ፣ ከስም ለውጥ፣ ከመጥፋት፣ የፍርድ ክልከላ፣ የባልነት ሚስትነት የአሳዳሪነት የሞግዚትነት ማስረጃ ይሰጠን ጉዳይ፣ የከተማው አስተዳደር ከሚያስተዳድረው ቤት ጋር በተያያዘ በሚነሳ የይዞታ ወይም የባለቤትነት ወይም ሌላ ማንኛውም ክርክር፣ በከተማው ውስጥ ከሚገኝ እዴድር ጋር በተያያዘ የመዲኘት ሥሌጣናቸው እንዯተጠበቀ ሆኖ በተጨማሪ በግሇሰቦች መካከሌ የሚደረጉ እስከ ብር 500,000 (አምስት መቶ ሺህ ብር) የገንዘብ፣ ውል፣ እና ብድር ክርክሮች የሚመለከቱ ሆኖ ቀሪ በአዲስ አበባ እና ድሬዳዋ ከተሞች የሚነሱ የፍትሀብሔር ክርክሮች በ,ፌደራል ፍርድ ቤቶች የሚዳኙ ይሆናሉ፤
16. በሌሎች ሕጎች የተጠቀሱ ጉዳዮች፡፡
የክልል ጉዳይ በክልሉ ፍርድ ቤት እየታየ እያለ ወይም ከተወሰነ በኋላ ከላይ በቁጥር 8 እና 13 ሥር የተጠቀሱት ተከራካሪ በማንኛወውም ሁኔታ ወደ ክርክሩ ቢገባ እንኳ ጉዳዩ በክልሉ ፍርድ ቤት መታየቱ ይቀጥላል፡፡
ቸር ያሰማን! (28/11/2013 ዓ.ም) (ኦምኒኤል)
የንግድ ዉድድርና የሸማቾች ጥበቃ አዋጅ ቁጥር 813/2006 ከሸማቹ ማህበረሰብ አንጻር የሚከተሉት አላማዎች ይኖሩታል
• ሸማቹን ከሚያስቱ የገበያ ሁኔታዎች ለመከላከል
• የሸማቾችን ጤንነትና ደህንነት አደጋ ላይ የሚጥሉ የንግድ እቃዎችንና አገልግሎቶችን መስፋፋት መግታት
• ደህንነታቸዉንና ሌጤና ተስማሚ መሆናቸዉን በዘላቂነት ማረጋገጥ
• ተጠቃሚዎች ላወጡት ዋጋ ተመጣጣኝ የሆኑ የንግድ ዕቃዎችና አገልግሎቶች ማግኘት የሚችሉበትን ሁኔታ ማመቻቸት ነዉ
ህድአት
ነሃሴ/2013 ዓ.ም
ጤና ይስጥልኝ ፡-
በኢትዮጵያ የፍትሐብሔር ሕግ የሟች ዉርስ በኑዛዜ ወይም ያለኑዛዜ ሊተላለፍ እንደሚችል የተደነገገ ሲሆን ሟቹ ንብረቱን ለተወላጆቹ ወይም ተወላጆቹ ላልሆኑ ሰዎች በኑዛዜ ማስተላለፍ የሚችል ሲሆን ስለዚሁ የኑዛዜ አንዳንድ ሁኔታዎች የሚከተለዉን እንበል፤
መልካም ምንባብ፡-
በሕጋችን ሦስት ዐይነት የኑዛዜ ፎርሞች ያሉና ተናዛዡ አለኝ የሚለዉን ንብረት ከሦስቱ ፎርማቶች በአንዱ ለኑዛዜ ተጠቃሚዉ ማስተላለፍ የሚችል ሲሆን ተናዛዡ የመጀመሪያ ደረጃ ወራሽ (ልጆች) የሆኑትን “በሕይወቴ ላይ ከፍተኛ ችግር ፈጥረዉብኛል “ በሚል በቂና ሕጋዊ ባልሆነ ምክንያት ወይም በዝምታ ከዉርሱ መንቀሉም ሆነ ሟቹ ካለዉ ሀብት ላይ እጅግ አነስተኛ የሆነ ንብረት ለተወላጁ በኑዛዜ የሰጠ እንደሆነ ተወላጁ ተነቅሏል ተብሎ ግንዛቤ ሲያዝበት የሚችል በመሆኑ ከዚህ በላይ የተገለጸዉ ከሆነ ተወላጁ ከሌሎች የጠቅላላ ኑዛዜ ተጠቃሚዎች ጋር እኩል መካፈል ያለበት መሆኑን ከፍ/ብ/ሕጉ ላይ ከተገለጹት ድንጋጌዎች በመነሳት በፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የሰበር ሰሚዉ ችሎት በሰ/መ/ቁ 58338 በሆነ የአስገዳጅነት ዉሣኔ ሰጥቶበታል ፡፡
ደረጀ ማርቆስ ነሐሴ 6/2013
ጤና ይስጥልኝ ፡-
ማንኛዉም ሰዉ በአንድ የወንጀል ደርጊት ተከሶ የመጨረሻ ዉሳኔ ባገኘበት በድጋሚ ሊቀጣ እንደማይገባ በኢፌዲሪ ሕገ-መንግስት አንቀጽ 23 ላይ የተደነገገዉን ስለአፈጻጸሙ በወንጀል ሕግ አንቀጽ 2/5 ላይ የተቀመጠዉን እንደሚከተለዉ እናቀርባለን፡፡
መልካም ምንባብ፡-
ማንም ሰዉ በሕግ መሠረት የመጨረሻ በሆነ ዉሣኔ ጥፋተኛነቱ ተረጋግጦ ከዚህ ቀደም በተቀጣበት ወይም ሌላ ሕጋዊ እርምጃ በተወሰደበት ወይም በነፃ በተለቀቀበት ወንጀል እንደገና አይከሰስም ወይም አይቀጣም በማለት በወንጀል ሕግ አንቀጽ 2/5 ላይ የተደነገገ ሲሆን በዚሁ ድንጋጌ ተጠቃሚ ነኝ በማለት በድጋሚ ልከሰስ አይገባም በሚል ክርክር ከቀረበ ከዚህ ቀደም ቀርቧል የተባለዉን በድጋሚ (ለሁለተኛ ጊዜ) ክስ ቀርቦበታል ከተባለዉ የወንጀል ድርጊት ጋር ተመሳሳይ መሆን አለመሆኑ ተገናዝቦ መሆን ያለበት ስለመሆኑ በፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የሰበር ሰሚዉ ችሎት በሰ/መ/ቁ/85237 በሆነ ዉሣኔም የሰጠበት መሆኑን ግንዛቤ ይያዝበት
ደረጀ ማርቆስ ነሐሴ 6/2013
የሸማች መብቶች
• ስለሚገዛዉ ዕቃ ወይም አገልግሎት ጥራትና አይነት በቂና ትክክለኛ መረጃ ወይም መግለጫ የማግኘት
• ዕቃዎችንና አገልግሎቶችን አማርጦ የመግዛት
• የዕቃዎችን ወይም አገልግሎቶችን ጥራት ወይም አማራጮችን በማየቱ ወይም የዋጋ ድርድር በማድረጉ ምክንያት እንዲገዛ ያለመገደድ
• በማንኛዉም ነጋዴ በትህትናና በአክብሮት የመስተናገድ እንዲሁም በነጋዴዉ ከሚደርስበት የስድብ፤ የዛቻ፤ የማስፈራራት እና የስም ማጥፋት ተግባር የመጠበቅ እና
• የንግድ ዕቃዎችን ወይም አገልግሎቶችን በመግዛቱ ወይም በመጠቀሙ ምክንያት ለሰረሰበት ጉዳት የንግድ ዕቃዎቹን ወይም አገልግሎቶቹን ከማቅረብ ጋር ተያይዞ በአምራችነት፤ በአስመጪነት፤ በጅምላ ሻጭነት፤ በችርቻሮ ሻጭነት ወይም በሌላ ማንኛዉም ሁኔታ በአቅርቦቱ የተሳተፉ ሰዎች በተናጠል ወይም በአንድነት ካሣ እንዲከፍሉት ወይም ከዚህ ጋር ተያያዥ መብቶችን የመጠየቅ መብት አለዉ
አዋጅ ቁጥር 813/2006 አንቀጽ 14
ህድአት
ነሃሴ/2013 ዓ.ም
ከተ.መ.ድ የስደተኞች ኮንቬንሽን እና ከአፍሪካን ኮንቬንሽን ጥምርት ምንባብ እንደምንገነዘበው አንድ ሰው ስደተኛ የሚባለው፡-
በዘሩ፤ በሃይማኖቱ፤ በዜግነቱ፤ በአንድ የህብረተሰብ ቡድን አባል በመሆኑ፤ ወይንም
በፖለቲካ እምነቱ ምክንያት፡ ተጨባጭ ማሳደድ. ወይንም አደጋ ወይንም እንግልት ወይንም ስቃይ ይደርስብኛል ብሎ በመስጋት ምክንያት ከአገሩ የተሰደደና፤ በነዚህ ክስተቶች ምክንያት የዜግነት አገሩን ጥበቃ ማግኘት ያልቻለ ወይም በዚሁ ስጋት
የተነሳ የዜግነት አገሩን ጥበቃ ያልፈለገ፤ ወይንም ዜግነት የሌለው ሆኖ ከላይ በተጠቀሱት ምክንያቶች ተጨባጭ ማሳደድ፤ አደጋ፤
እንግልት ወይም ስቃይ ይደርስብኛል ብሎ በመስጋት ከዜግነት አገሩ የተሰደደና
ወደቀድሞ መደበኛ መኖሪያው መመለስ ያልቻለ ወይም ያልፈለገ እንደሆነ እንዲሁም ደግሞ
ከላይ ከተቀመጡት ምክንያቶቸ በአማራጭ፤
ከአፍሪካ የመጣ ስደተኛ ከሆነ በውጭ ወረራ ምክንያት፤ በግዛት መያዝ፤ በውጭ አገዛዝ፤
የትውልድ ወይም የዜግነት አገሩን ህዝባዊ ስርአት በከፊልም ሆነ በሙሉ በሚያናጋ ከባድ
ክስተት ምክንያት፤ከትውልድ ወይንም ከዜግነት አገሩ ውጭ ጥገኝነት ለመጠየቅ ሲል መደበኛ መኖሪያ ስፍራውን ለመልቀቅ የተገደደ እንደሆነ ነው፡፡

ሰብአዊ መብት ባህል የሆነባት ኢትዮጵያን እንፍጠር!
ኦምኒኤል (14/12/2013 ዓ.ም)
የስደተኛ መብቶችን በተመለከተ በተ.መ.ድ የስደተኞች ኮንቬንሽንና በስደተኞች ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1110/2011 መሠረት:-
እንደ ስደተኛ የመቆጠር መብት
ተገዶ ያመመለስ መብት (non-refoulment)
ከአገር ያለመውጣት መብት
የጥገኝነት ማመልከቻ ያቀረበ እንደሆነ የይግባኝ መብት እስኪያበቃ ድረስ ኢትዮጵያ
ውስጥ የመቆየት መብት
ኢትዮጵያ ውስጥ የመኖር መብት
በፈቃደኝነት ወደ አገር የመመለስ መብት
የቤተሰብ አንድነት መብት
ስደተኝነትን የሚገልፅ መታወቂያ ወረቀት የማግኘት መብት
የጉዞ ሰነድ የማግኘት መብት
የትምህርት እድል የማግኘት መብት
የጤና አገልግሎት የማግኘት መብት
የመስራት መብት
የመደራጀት መብት
የመዘዋወር ነፃነት
ንብረት የማፍራትና የማስተላለፍ መብት
ፍትህ የማግኘት መብት
የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ የማግኘት መብት
የባንክ እና ፋይናንስ አገልግሎት የማግኘት መብት
የቴሌኮምዩኒኬሽን አገልግሎት የማግኘት መብት እንዲሁም ደግሞ
የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ የማግኘት መብት አለው።

ሰብአዊ መብት ባህል የሆነባት ኢትዮጵያን እንፍጠር!
ኦምኒኤል (14/12/2013 ዓ.ም)
በስደተኞች ጉዳይ አዋጃችን መሠረት
የኢትዮጵያ ዜግነት ማግኘት የሚፈልግ ስደተኛ/የውጭ አገር ዜጋ ሊያሟላቸው የሚገቡ ሁኔታዎች የሚከተሉት ናቸው፡-
ለአካለ-መጠን የደረሰና በህግ ችሎታ ያለው መሆን፤
መደበኛ መኖሪያን በኢትዮጵያ መመስረትና እስከ ማመልከቻው ቀን ድረስ ባሉት
አምስት አመታት ቢያንስ ለአራት አመት ኢትዮጵያ ውስጥ መኖር፤
ካገሪቱ ቋንቋዎች ቢያንስ ባንዱ መግባባት መቻል፤
ራስንና ቤተሰብን ማስተዳደር የሚያስችል ህጋዊ የገቢ ምንጭ ያለው መሆን፤
መልካም ስነ-ምግባር ያለው መሆን፤
በወንጀል ተከሶ ያልተቀጣ መሆን፤
የቀድሞ ዜግነቱን የተወ/የሚተው መሆኑን ማስረዳት የሚችል፤
የዜግነት ቃለ-መሃላ ለመፈፀም ፈቃደኛ መሆን፤

ሰብአዊ መብት ባህል የሆነባት ኢትዮጵያን እንፍጠር!
ኦምኒኤል (14/12/2013 ዓ.መ)
ቸር ይግጠመን
በቦሌ ክ/ከ/ዐ/ጽ/ቤት የህ/ም/መ/ዳይሬክቶሬት የቴልግራምመልክት የተዘጋጀ ነሐሴ 7/12/2013
በሰላም ይገላገሉ
ውድ የቴሌግራም ተከታታዮቻችን ማንም ሰው ለአቅመ አዳም /ሄዋን/ ደርሶ ስራ ከያዘ፣ ቀጥሎ ማሳካት ከሚፈልጋቸው ነገሮች አንዱ መውለድ ወይም ዘሩን መተካት ነው፡፡
መውለድ ደግሞ የግል ብቻ ሳይሆን ለሀገር ቀጣይ ተረካቢ ትውልድ የማፍራት ጉዳይ ስላለበት መንግስታትም ለሰራተኞቻቸው ከሚሰጧቸው መብቶች አንዱ የወሊድ ፈቃድ በመሆኑ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ሰራተኞች አዋጅ ቁጥር 56/2010የወሊድ ፈቃድ በሚል የሚከተለውን ደንግጓል እንደሚከተለው አቅርበነዋልና ለመውለድ ከምታደርጉት ዝግጅት አንዱ ይህንን ማንበብ ይሆን ዘንድ እጋብዛለሁ፡፡
አንቀጽ 42 የወሊድ ፈቃድ
1.ነፍሰጡር የሆነች የመንግስት ሰራተኛ፣
ሀ. ከእርግዝናዋ ጋር የተያያዘ ምርመራ ለማድረግ ሐኪም በሚያዘው መሰረት ደመወዝ የሚከፈልበት ፈቃድ ይሰጣታል፣
ለ. ከመውለዷ በፊት እረፍት እንድታደርግ ሐኪም ካዘዘ ደመወዝ የሚከፈልበት እረፍት ይሰጣታል
2.በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ (1)የተመለከተው ፈቃድ እንደ ህምም ፈቃድ አይቆጠርም
3.ነፍሰጡር የሆነች የመንግስት ሰራተኛ መውለጃዋ ሲደርስ እወልዳለሁ ብላ ከገመተችበት ቀን በፊት 30 ተከታታይ ቀናት የቅድመ ወሊድ ፈቃድ፣ እንዲሁም ስትወልድ ከወለደችበት ቀን ጀምሮ 90 ተከታታይ ቀናት፣ በአጠቃላይ 120 ተከታታይ ቀናት ደመወዝ የሚከፈልበት የወሊድ ፈቃድ ይሰጣታል
4.በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ (3) መሰረት ሰራተኛዋ የተሰጣት የቅድመ ወሊድ ፈቃድ ከማለቁ በፊት ከወለደች ያልተጠቀመችበትን ቀሪ የቅድመ ወሊድ ፈቃድ ከወለደች በኋላ እንድትጠቀምበት ይደረጋል
5.ሰራተኛዋ የወሰደችው የቅድመ ወሊድ ፈቃድ ሲያልቅ ያልወሰደችው የቅድመ ወሊድ ፈቃድ ሲያልቅ ያልወለደች እንደሆነ እስከምትወልድበት ቀን ድረስ ባሉት የስራ ቀናት የምትቆይበት እረፍት በበጀት ዓመቱ ካላት የዓመት ፈቃድ የሌላት እንደሆነ ከሚቀጥለው የበጀት ዓመት የእረፍት ፈቃዷ ይተካል
6.ሰራተኛዋ በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ (3) የተወሰነውን የወሊድ ፈቃድ ከጨረሰች በኋላ ብትታመምና ተጨማሪ ፈቃድ የሚያስፈልጋት መሆኑ በሐኪም ከተረጋገጠ በዚህ አዋጅ አንቀጽ 43(1) በተደነገገው መሰረት የሕመም ፈቃድ መውሰድ ትችላለች
7.ማንኛውም ስድስት ወር የሞላት ነፍሰጡር የሆነች የመንግስት ሰራተኛ የቅድመ ወሊድ ፈቃድ ከመውሰዷ በፊት ጽንሱ የተቋረጠባት ከሆነ ይህንኑ የሚያረጋግጥ የህክምና ማስረጃ ስታቀርብ የ60 ቀን የድህረ ወሊድ ፈቃድ ይሰጣታል
8.የቅድመ ወሊድ ፈቃድ ከወሰደች በኋላ የጽንስ መቋረጥ ካጋጠማት የወሰደችው የቅድመ ወሊድ ፈቃዷ ተቋርጦ በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ (3) የተመለከተው የ90 ቀን የድህረ ወሊድ ፈቃድ ይሰጣታል
9.ከሶስት እስከ ስድስት ወር ባለው የእርግዝና ጊዜ ውስጥ የፅንስ መቋረጥ ያጋጠማት የመንግስት ሰራተኛ ደመወዝ የሚከፈልበት 30 ተከታታይ ቀን ፈቃድ ይሰጣታል
10.ማንኛውም የመንግስት ሰራተኛ የትዳር ጓደኛው ስትወልድ ደመወዝ የሚከፈልበት 10 የስራ ቀን ፈቃድ ይሰጠዋል፡፡
በነገራችን ላይ ከዚህ በፊት የነበረውን አዋጅ ስድስትን በአዋጅ ሀምሳስድስት መቀየር ካስፈለገባቸው ምክንያቶች መካከል፡-
የጽንስ መቋረጥ ላጋጠማቸው ሴቶች የሚሰጠው ፈቃድ፤
የወሊድ ፈቃድን ከ90 ቅድመ ወሊዱን ጨምሮ ወደ 120 ቀናት ያሳደገው፤
እንዲሁም በክፍል 5 አንቀጽ 48/6 የተደነገገው ማንኛውም መስሪያቤት ህጻናት ማቆያ ማቋቋም እንዳለበት የሚደነግጉት ናቸው፡፡

አዘጋጅ ሲሳይ ሰማኝ