@Book for all
4.81K subscribers
676 photos
4 videos
62 files
50 links
ማንበብ ማንበብ ማንበብ ‹‹ሰፊ ይለበሳል ጠባብ ይቀደዳል››
@መባ
ለማንኛውም አስተያየት
@Dasolo
Download Telegram
አንድ ሃያሲ ዶስቶቭስኪን ሲክበው ከእግዚአብሔር በታች የሰውን ልጅ ስነልቡና ጠልቆ የተረዳ ነው ይለዋል። ስነልቡናዊ ልብወለዶችን ከዶስቶቭስኪ በፊትም ሆነ በኋላ እንደሱ የተራቀቀበት የለም።

በዚህ አለም ላይ እንደ ሰው ልጅ አስደናቂ ፍጥረት የለም። ከሰው ልጅ ባህሪያት ደግሞ እንደ አእምሮው እፁብ ድንቅ አካል የለም። የዚህን አስገራሚ አካል ረቂቅ ባህሪ የሚያጠና ሳይንስ ደግሞ ስነልቡና ይባላል። በዘመናዊ አለም ታሪክ ደግሞ የፍሩይድን ያህል የስነልቦና አዋቂ የለም። አስደናቂው ነገር እዚህ ጋር ነው። ፍሩይድ ራሱ ጥይት የሆነው ዶስቶቭስኪን አንብቦ ነው። እዚህ ጋር ጋሽ ስብሐት ያቋርጠንና እንዲህ ይለናል፦

"ዶስቶቭስኪን አንብበህ ፐ! ይሄ ደራሲ ፍሩይድን አንብቦት ገብቶታል ልትል ትችላለህ። ነገሩ ወዲህ ነው። የሚቀድመው ዶስቶቭስኪ ነው"

አንዴ እንዲህ ማንበቤን አስታውሳለሁ፦

"የሰው ልጅ በሥልጣኔ እስከ ጥግ ሲራቀቅ የመጨረሻው የጥናት ዘርፍ ስነልቡና ነው"

ዛሬ በነጩ ሱሪ ፋንታ ቀዩን የለበስክበት ምክንያት ቢጠና ምንጩ ስነልቡና ነው። ሁለተኛው የአለም ጦርነት የተጀመረበት መሰረታዊ ምክንያት ቢጠና መነሻው ስነልቡና ነው። የሁሉም ግጭቶች መሰረት ቢተነተን ምንጩ ስነልቡና ነው። ስነልቡና የመሰረታዊ አስፈላጊነቱን ያህል ውስብስብ ነው። ሰዎች ምን ይወዳሉ? ለምን ይወዳሉ? ለምን ይጠላሉ? ከልጅነት ጀምሮ በሚገባ መጠናት የሚገባው ሰፊ ርእስ ነው። የህፃናት ስነልቡና! የአዋቂዎች ስነልቡና! የእንስሳት ስነልቡና! የወንጀለኞች ስነልቡና! የፍቅር ስነልቡና! የአሸናፊነት ስነልቡና!

የሰው ልጆች ስነልቡና በሚስጥር የተደበቀ ሃብት ቢሆን ዶስቶቭስኪ የዚያን ሃብት ሙሉ ካርታ የያዘ ጠቢብ ነው። ዶስቶቭስኪ በስነልቡና ያልነካው ርእስ የለም። ሁሉንም ጉዳዮቻችንን ይተነትንልናል። በግብረገብ፣ በስነመለኮት፣ በፍልስፍና፣ በፖለቲካ፣ በሂሳዊ ስነፅሁፍ ተፅዕኖ አሳርፏል። ብዙ መፅሀፍት ለማገላበጥ ግዜ ለሌላችሁ ስለ ሰው ልጅ ስነልቡና አብጠርጥሮ ለመረዳት ዶስቶቭስኪን መርጣችሁ አንብቡ። ታተርፋላችሁ! መልካም ንባብ! Dostoyevsky is a must read!
@Bookfor
@Bookfor
"አሁን" ሁሉም ነገር ይበርዳል ማለዳው ይበርዳል ቀትሩ ይበርዳል ምሽቱም ይበርዳል ሰዉ ይበርዳል ደስታ ይበርዳል ሳቅም ይበርዳል ክህደት ይበርዳል እምነትም ይበርዳል ስሜቶች ሁሉ በራድ ሆነዋል .....
አካልን አሳስቶ አጥንትን የሚያደቅ ስቃይ....... ህሊናና ልብ አንቀላፍተው አይኖች ሁሉ ስጋ ላይ ተጥለው ሳይ ያነዜ እጨነቃለሁ 😔 አከላቴን እየተጫንኩ የተጣበቁብኝ አይኖችን ወደ ልቤ ዘልቀው እንዲገቡ እሻለሁ ወደ ውስጤ ላሰጥማቸው ብዙ አለፋለሁ ግን ማየት እሚፈልገውን ብቻ እንደሚያይ ሰው የታወረ የለም ።
ስጋዬን ብቻ እየተመለከቱ ሰውነታቸውን ሸሽገው አውሬነታቸውን ያመላክቱኛል ......😔

በስጋዬ ላይ አይናቸውን እሚጥሉ እልፍ አይናማዎች በዙሪያዬ ሲተረማመሱ ልቤ ትጨነቃለች ነፍሴም ትለዝብብኛለች ስለምን ልበ-ስውራን አድርገህ አይናቸውን አበራህ እያልኩ እጠይቀዋለሁ ፈጣሪያቸውን ለምን ከሚያስፈልጋቸው በላይ ፈላጊ አደረካቸው ለዚህስ ተጠያቂው አንተ ነህ እነሱ እያልኩ ነዘንዘዋለሁ
በሞላው የስጋ ጥርቅሜ ውስጥ የከሳሁትን እኔን በውስጤ መኮሰሴን ማንም አያውቅልኝም እኮ ነፍሴ አቻዎቿ እንደዋዛ ሲወዳድቁ እያየች በፍርሀትና በሀዘን ነትባለች ንፋስ እንደሚያውለበልባት ከመንገድ የወደቀች ቅጠል ሆናብኛለች የት ይሆን መድረሻዋ ስል መልስ አልባ ጥያቄ ለራሴ አቀርባለሁ በዋዛ ወድቀው የቀሩ ነፍሳትን አስባለሁ ዘመኔን ፈራሁት ፤ ትውልዴን ሰጋሁት ፤ ታሪኬን ጠላሁት.....😥 ግን ........... ግን .......... ዘዉትር ፤

የሚደንቀኝ እና እምወደው ልቤን የሚረታብኝ የሆነ ነገር አለ ። ምን አትሉም? ....... " "!!!!!!!
እዚህ ሁሉ ስሜት ውስጥ ሆኜ እንኳ ይሄኛውን ስሜት እሚበልጠው ሌላውን ስሜቴን አደምጠዋለሁ !
ዘዉትር ከእኔ እማይነጥፍ "ተስፋ" እሚሉት ማገገሚያ አለ ........ አትገረሙም ወይ!!!!!! ተስፋ አታደርጉም ወይ?!

ነገ ደህና ይሆናል! 🙏🙏🙏
@Bookfor
@Bookfor
ለሰንበቲታችን!
💚
የኔ ሃገር ይች ናት!!!!!!
ሆሳእና በአርያም የሚዘመርባት፤
በዘንባባ መሃል፤
ህፃናት በእልልታ የሚጨፍሩባት፤
በዘንባባ አጊጠው፤
ነጠላ ታሽመው፤
ፍቅር ተሸክመው፤ የሚቦርቁባት፤
በዘንባባው መሃል፤የምራመድባት፤
አትጠራጠሩኝ፤
የኔ ሃገር የኔ ሃገር፤ የኔ ሃገር ይች ናት።
@Bookfor
#የእውነት #ስቅ #ላት
ትናንት ጥፋተኛን
በአደባባይ ሰቅለን ~ በገበያ መሐል
እስከዛሬ ድረስ
ፍትህ ችሎ ሳይቆም ~ ፍርዳችን ይድሀል
#የቀን #ባለተራ
ወደታች እንዳይወርድ ~ ከላይ ለመከልከል
ገበያን ይሰቅላል ~ በሌቦች መካከል
* * *
በመደብ ትግል ላይ ~ገደብ ጣይ ይወጣል
ለእለት ገበያው ~ ዘመኑን ይሸጣል
ፍርድ እየሸቀጠ ~ ፍትህ ያራክሳል
በአያቱ ችሎት ~ የልጅ ልጅ ይከሳል
* * *
ከገዢም ከሻጭም ~ ከሁለቱም ወገን
ባፍ እየደለሉ ~ የግፍ ዲናር መዝገን
ሁለቴ ለማትረፍ ~ ሁለት ጊዜ ማክሰር
በርባንን ለመፍታት ~ ንፁሀንን ማሰር
በደል መከመር ነው ~ ብሶት መደራረብ
ሌባም ዳኛም ሆኖ ~ ከሐገር ችሎት መቅረብ
#እኛም #ተከፋፍለን
ሕገ አቃቤ ሁነን ~ አንዳችን ጠበቃ
ክርክር ተጋጥመን ~ ሙግት ሳናበቃ
በመዶሻው ጩኸት ~ ባነን ስንነቃ
የመሀሏን እውነት ~ ለስቅላት ዳርጎ
ሌባ ያማክራል ~ ግራና ቀኞ አርጎ
#ድንገት #ስንባንን
ዳኛው ከሌባው ጋር ~ ቦታ ተቀያይሮ
በስላቅ ሹክሹክታ ~ ግራና ቀኝ መክሮ
ፍትህ የተጠማ ~ ሲቁለጨለጭ አይኑ
በነፃነት ሚዛን ~ ነፃ ነው ብይኑ
#አወይ #መገጣጠም
ያኔ ስትሰቀል ~ እውነት በጎልጎታ
ግራና ቀኝ ነበር ~ የሌቦቹ ቦታ
ዛሬ በወንበር ላይ ~ መስቀል ተጀምሮ
ሦስቱም ሌባ ሆኗል ~ መሀሉን ጨምሮ
===||===
ከሙሉቀን ሰ•
@Bookfor
@Bookfor
Forwarded from Meba
በግዜ ብዛት የማይናወጥ ፣ በመቆየት የማይረሳ ፣ ሁሌም ለሰው ልጅ እርምጃ መሪነት የሚፀናው ቅንነት ነው። ቅንነትን እንደያዝን ከፈተናዎች ጋር እየታገልን ቅንነት ድል ያደርጋል ብለን ተነስተን በማይዝለው ጉልበት ፣ በማይነጥፈው ብዕራችን ፣ በማይዝለው እጃችን የቅንድል ትሩፍታችን መፅሔት እንሆ በትንሳኤ ዋዜማ ወደ አንባቢያን ልትደርስ ነው።
በተለያዩ ጉዳዮች መፅሔታችን በቀኑዋ ባለመድረሷ አሳስቧችሁ የቅንነት ልባችሁ ሳይታክት ስትከታተሉን እና ስታበረታቱን ለነበራችሁ ሁሉ በመዘግየታችን ይቅርታ እየጠየቅን ቅንድል ዲጂታል መፅሔት ቅፅ 2 ቁጥር 8 እንድታመቡ እንጋብዛለን።
በቅንነት ብርሀን ፣ በምክንያታዊነት መርህ ፣ በሀገር ፍቅር ቱሩፍት እየተጓዝን በቅንነት ድል እናደርጋለን።

#ቅንድልዲጂታልመፅሔት
እፁብድንቅ ሀገር ኢ ት ዮ ጵ ያ 💚💛

#Ethiopia - በስሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ውስጥ የሚገኘው የጅንባር ፏፏቴ በአፍሪካም በኢትዮጵያም ረጅሙ ፏፏቴ ነው!!

ከመሬት ወለል 500 ሜትር ወደታች ጥልቀት ያለው በእውነቱ የሚያስደምም ውብ እይታ !!
.
#The_Real_One

መልካም ፍሲካ ለቻናላችን ቤተሰቦች ተመኘን!
@Bookfor
@Bookfor
🎖
ምሳሌ የሌለሽ መቅደስ ኢትዮጵያ ጠላት ኢጣሊያ ስላረከሰሽና፤መሰዊያሽን ስላጠፋ ከእንግዲህ ወዲህ ተቀደሺ ኃይልንም ገንዘብ አድርጊ፡፡" (አምባሳደር ብርሃኑ ድንቄ)
************
<<አገሬ ኢትዮጵያ ውዲቱ ውዲቱ፤
በሦስቱ ቀለማት የተሸልምሽቱ፤
ላንቺ የማይረዳ ካለ በሕይወቱ፤
በረከትሽን ይንሳው እስከለተ ሞቱ።>>
(ቀኝ ጌታ ዮፍታሄ ንጉሴ) እንዳሉት።

፨ዘልዓለማዊ ክብር ለአባት/እናት አርበኞች አገርን ከነሙሉ ክብሯ ላቆዪቱ።
#80ኛ_ዓመት_የአርበኞች_የድል_መታሰቢያ!
@Bookfor
@Bookfor
በተገኘበት ይነበብ
የተወዳጁ ሙዚቃ ባለሙያ ኤልያስ መልካን ህይወት የሚዳስሰው "የከተማው መናኝ" በሚል ርዕስ ለንባብ በቅቷል።

@Bookfor
@Bookfor
ለመላው ሙስሊም ወገኖቻችን ሁሉ፡-

እንኳን ለተከበረዉ ለታላቁ ለዒድ አልፊጥር አደረሳችሁ! በዓሉ የደስታ ይሆን ዘንድ ልባዊ ምኞታችንን እንገልጻለን!


💫💫 ኢድ ሙባረክ 💫💫


@Bookfor
የሱፊ ተረት እንዲህ ይላል፦

"ብዙ መጻሕፍት የተሸከመች አህያ ያው አህያ ናት!"

ይቺን አህያ ሁላችንም እናውቃታለን። ቀኑን ሙሉ ተዘፍዝፎ የሚያነብ ምሁር፣ ባዶ ቃላት የሚሰብክ ሰባኪ ወይም ምንም የማይሰራ አንባቢ ሊሆን ይችላል። እውነተኛ ጥበብ የሚገኘው ቁምነገሩን በማንበብ ሳይሆን ቁምነገሩን በመኖር ነው።

ቅዱሳን መጻሕፍትን አንብበናል፤ ግን ምሳሌውን ተከትለን በፍቅር አልኖርንም። የሳይንስ ሰነዶችንም አገላብጠናል። ለምስኪኑ ወገናችን ጠብ የሚል ነገር አልፈጠርልነትም።

በቤተክርስቲያን እና በመስጊድ እንመላለሳለን፤ ቅዱስ ቃሉን ከመጣፍም ከሊቅ አፍም እንሰማለን። ግን በልባችን ፍቅርና ርህራሄ የለንም። ያነበብነውን የማንኖር ግብዞች ሆነናል።
@Bookfor
@Bookfor
"በአብሮነትና በብቸኝነት መሀል መታደስ"

ጥያቄ ፦ "ከፍቅረኛዬ ጋር በቅርቡ ተለያይተናል። አዳዲስ ጓደኞች ለመያዝ ብሞክርም ከብቸኝነትና ሀዘን መላቀቅ አልቻልኩም"

ኦሾ ፦ ልነግርሽ የምችለው ነገር ቢኖር ብቸኝነትሽን ለማስወገድ እንዳትጣደፊ ነው። በራሱ ጊዜ እንዲሄድ ታገሺው። የአሁኑ ፍለጋሽ ጥሎሽ የሄደ ፍቅረኛሽን ለመተካት የምታደርጊው ድካም ነው። በመጀመሪያ ግን የተወሽ ፍቅረኛሽን ከውስጥሽ ማስወጣት አለብሽ። ያለፈ ህይወቱን በጥሩ ብርታት ማሰናበት የቻለ ሠው በድጋሚ ድንግል ይሆናል። ድንግልናን ከአካላዊ እድሳት ማያያዝ የዋህነት ነው። ድንግልና የመንፈስ ንፅህና ነው። በብቸኝነታችሁ ተደሰቱ ብቸኝነት መልካም አጋጣሚ ነው። ከሕይወታችሁ ታላላቅ ነገሮች አንዱ ግለ-ሰባዊነታችሁን ደጋግማችሁ ማግኘት ነው። በመቀጠል ቀስ በቀስ ወደ ታላቁ የሕይወት ጥበብ ትዘልቄላችሁ ፤ በድጋሚ ታፈቅራላችሁ ፤ በፍቅረኛችሁ ነጠላ ግለ-ሰባዊነት ውስጥም ልዩ ሥፍራ ትይዛላችሁ ። ይህ የሕይወት ትምህርት ነው። ፍቅር የደስታ ምንጭ እንጂ ህመም ሆኖ አያውቅም፤ ስቃይን አስከትሎም አያውቅም።

እኔም አልኩ፦ ተወዳጁ ኦሾ ሆይ በእነዚህ የፍቅርና የብቸኝነት መንገዶች መሀል ተመላልሻለሁ። ልክ በፍቅር ውስጥ ሆኜ እንደተፍለቀለኩት ሁሉ በብቸኝነቴ ውስጥም ብዙ መባረኮችን ኖሬያለሁ። ለዛም ነው ለዚህ ሀሳብና አስተምሮትህ እውነተኛ ምስክር የምሆነው። ከመለያየት በኋላ ያለውን ብቸኝነታችሁን ለማምለጥ ለመሸፈን አትሯሯጡ ይልቅ ኑሩት አጣጥሙት 🙏🙏
@Bookfor
@Bookfor
@Bookfor
🎼..ስሜ ተፅፎ አየሁት በክብር ቃል
ሰው ነህ ይላል
ቋንቋ በፊት ከዘር ቀድሞ ተፅፏል
🟩🟨🟥 Rophnan 👌👌
በአዲስ ስራ ብቅ ብሏል ትወዱታላችሁ።

@Bookfor
@Bookfor
ሮፍዮጵያ

ኢትዮጵያን ጎኗን ወጓት፡-
ኢትዮጵያ እና ሰውነት ተጠልተዋል በአገራችን፡፡ ኢትዮጵያን ና የሰው ልጅንም በመስቀል ላይ ሰቅለናቸዋል፡፡ ሞትን እንዲጎነጩ አድርገናቸው፡፡ ከፍጥረት ጀምሮ የነበረውን ሰውነት እና ኢትዮጵያዊነትን ምናምንቴ አድርገናቸዋል፡፡ (double reductionism)
ለዚህ ዓይነት አገራዊ ችጋር ላይ ያደረሰን አገር እና ትውልድ ልንሠራ የተነሳንበት የፓለቲካ እና የባህል ስሪት ትርክት ነው፡፡ ኢትዮጵያ እና ሰውን በዘረኝነት እና በጠባብ ብሔርተኝነት መንፈሥ መመዘናችን ዋናው በሽታችን ነው፡፡ (ethnic determine sociological character of thinking and monological dialogue) ሮፍናንም የዚህ ትውልድ መልክ ኾኖ ሰውነቱ ጥያቄ ውስጥ ሲገባ አርዶታል፡፡

አንተ ሰው ማነህ ብለው ጠየቁኝ
የማንን ልበል ካንቺ መፈጠር ብዙ አድርጎኝ

ሰው መኾን ተብሎ ስም በሚወጣበት የኢትዮጵያ ምድር÷ ቀኝህን የመታህን ግራህን ስጥ በተባለበት ቀዬ÷ ለእንግዳ አልጋ ለቆ በሚኖርበት ሰፈረ ሰላም÷ እንኳን በህይወት ያለውን ሰው ለሞተው ፀሎት በሚቆምበት ኢትዮጵያ በጎ ኅሊና እንደ ሰማይ ራቀን፡፡
የጓራ ህሊናችን ስንጥቅጥቁ ወጣ፡፡ የነፃነት እና የድል አምባ የኾነችው አገር በእኛ በልጆቻ አለመገረዝ ወደቅን፡፡ በልሒቃኑ ትርክት እና አገራዊ አረዳድ ብቻ በችግር ሸለቆ ውስጥ፤ በሐዘን እምቀ እምቃት ውስጥ ሰጠምን፡፡ አቅመ ቢስነት እና ትርጉም ማጣት አሸነፈን፡፡ ኢትዮጵያም ባቢሎን ኾነች፡፡ (powerlessness and meaninglessness)

ቃል እየተማዘዝን እኛው በእኛ አንሰን ከተራክሰን
በእነሱ አድዋ ድል አድርገናል ግን የእኛን አድዋን ተሸንፈናል

ሕዝብን ማዕከል ያላደረገ የእውቀት አመፃ እና የራስ ማንነት ጥላቻ ከትናንት ትውልድ ወደ ዛሬ ነፍሷል፡፡ አገራዊ የባህል የእውቀት እና የኑሮ ጥበብን ተፀይፈዋል፡፡ ኢትዮጵያንም ከዘር፤ ከብሔርተኝነት አንፃር ብቻ ቃኝተዋታል፡፡ በአገራቸውም ላይ ራሳቸው የፈጠሩትን ቅኝ ግዛትን አውጀዋል፡፡ (self contained metaphysical colonial consciousness)
አዋጃቸው ለአዲሱ ትውልድ መሥቀል ኾኖታል፡፡ የመኖር ጉዳይ ብርቅ እንዲሆንበት በቁስሉ ላይ ጨው ነስንሰውበታል፡፡ (self immolating) በባለ ተወርዋሪው ልሒቅ ዩሐንስ አድማሱ ገለፃ "ቢጥዱት አይበስል÷ ቢፈጩት አይቦካ÷ ቢያምሱት አይታመስ÷ ቢያቦኩት አይቦካ" ኾናል ዘመኑ፡፡ ሮፍናንም በእርሱ እና በትውልዱ የአዕምሮ ሰሌዳ ላይ የሰፈረውን "የቃል ዕዳን" ያስታውሰናል፡፡

የኔ ትውልድ ሰው እንዳይሆንበት
አጎንብሶ ሄደ ከአንገት እና ጀርባው ዘር ጭነውበት

እንዲህ አይነት "የዘመን ቅርቃር" ላይ ኢትዮጵያን እና ሕዝቦቻን ያደረሱት "አዋቂዎች እና ባለዙፋኖችንም" ፊት መልካቸውን÷ አረማመድ÷ አነጋገራቸውን በፍልሱፍ ዘፈኑ ውስጥ ይገልጣቸዋል፡፡ ስጋ ለብሰው፤ መንፈሳቸው በአደባባይ ተገልጦ ራቁታቸውን እንዲታዩ ያደርጋቸዋል፡፡ ጥፍራቸውን÷ ጭራቸውን ሳይደብቅ ይገልጣቸዋል፡፡ ለትውልዱም በእውቀት እና በጥበብ አሳልፎ ይሰጣቸዋል፡፡ (from crisis to brink of collapse)

ጠብቁኝ በደም ርሰው
የጥፋት ጉድጓድን ምሰው
በሰባራቸው አፍሰው
ሰባራ ሰንደቅ ይዘው

ኢትዮጵያ የጋራ ኅሊና፡-
ኢትዮጵያና እና የሰው ልጅ መንምነው ቢያያቸውም የነፀብራቁ ሮፍናን 'ምን እሆናለሁኝ ብቻዬን ብኖር፤ ከሰው ተለይቼ በጸጥታ አገር' ብሎ ሽሽትን አልመረጠም፡፡ (cultural relics and redemptive power)
ትውፊት÷ አገራዊ ብሔርተኝነት÷ አለምአቀፋዊ ሰውነት÷ የድል አለቃ የኾነውን አድዋ÷ አብርኸማዊነት÷ ፍትሐ ነገስትን÷ ሰናይ ባህርያትን ኢትዮጵያ ነው ስሜ ብሎ ለአዲሱ ትውልድ "የመዳን ነፀብራቁን" ከምሥራቅ በኩል ያደርሳል፡፡ ሰው ከኹሉ ሥራ ቀዳሚው ማንነታችን መኾኑን ይመሰክራል፡፡ ቀዳሚውን መስካሪ "አንድዬ፤ ባለቤቱን" አድርጎ ከርትዕ መድረክ ይጠራዋል፡፡ (mass emancipation under the law of God)

ስሜ ተፅፎ አየሁት
በክብር ቃል ሰው ነህ ይላል፡፡
(በፈጠረን ፊት ከበለጠ ሰው
እንደ አምላክ ባስብ ስህተቱ የት ነው)

The atomism of Ethiopia national philosophy contain central place in our memory for our common and inter subjective meaning of reconstruction of the state.
ለአስራ ስድስት ደቂቃ አንድ ሰከንድ ፈሪ በኾነው የዘፈን ፍልሱፍ ውስጥ አዝማሪው ከታሪካችን ዶሴ በንግስት ሳባ÷ በቀዳማይ ምንይልክ÷ በዮዲት ጉዲት÷ በግራኝ አህመድ÷ በኹለቱ ካሳዎች መስዋዕትነት ውስጥ እንደ አፄ ዮሐንስ ንግግር "ብሰዋም፤ ድል ባደርግም ዥግና ነው የምባል" የሚለውን ከመተማ መስዋዕትነት በፊት የተናገሩትን የንጉሱን ቃል ለትውልዱ ያበስራል፡፡ (responsible interdependence)
የኅሩይ ወልደ ሥላሴን የኢትዮጵያን ታሪክ እየመረመርን መልካሙን መያዝ ክፉውን መተው ይገባል ያሉትን በዋዜማ መጽሐፋቸውን ያሰፈሩትን አስታራቂ ወርቅ አፉቸውን ይናገርበታል፡፡ የዶ/ር ጠና ደዎን "የሰናይ ባህርያት በማስቀደም ከእኩይ ነገሮች ራስን እና አገርን እንዴት ማዳን" እንደሚቻል ይሸልልበታል፡፡ ( grand and delicate emancipator potentiality)

ጦቢያው ለይቅርታ ቅደም
ቀድመህ እንዳትተው ድገም
ደግሞ ቢያስቀይምህ ሰልስ
የአባትህን አደራ መልስ
ያኔ በላይ ይዘልቃል
ያን ጊዜም ቴዎድሮስ ይደገማል
ያን ጊዜ አሉላ ራስ ነው
ምንይልክ ዛሬም ንጉስ ነው፡፡

ሮፍናን የዘረኝነት ሶሻል ኢንጅነሪንግ ዘመንን ለማሸነፍ መንገዱን መጥረጉን ይቀጥላል፡፡ ትግሉ ቀላል አይደለምና፡፡ የደበዘዙ የመሰሉ ሰዋዊ ባህርያትን እና ሰውነትን አጥብቆ ይይዛል፡፡ የእጅግአየሁ የመንፈሥ ድባብ ከሚነበብበት የሰከላ የዘፈን ልቡና ውስጥም "አድዋ ዛሬ ናት፤ አድዋ ትናንትን" ለአዲሱ ትውልድ ይሠጠዋል፡፡ (tradition is the living faith of legacy)
ለአዲሱ አገራዊ ትግልም "ነጋሪቱን" ይመታል፡፡ ጦርን÷ ሚሳኤል÷ ጀትን ይዛችሁ ኑ ከማለት ይልቅ "አዲስ የአዕምሮ ስሪት" ለውጥን ይሠራል፡፡ አዲሲቷን ኢትዮጵያንም "በአድዋ ፍልፍል አብያተ ሰው" ላይ ያንፃታል፡፡ ለዘረኞቹ፤ ለክፋት አለቆቹም ምኅረት እና ኅብረትን ይጠራል፡፡ እንደ ኤልያስ መልካም ተጠላትን አንሞትም፤ ሰው ጠልተን አንሞትምን ለትውልዱ ያበሥራል፡፡ (common social reality myth)

እንግዲህማ እኔ ልሻል
መርዙን በይቅርታ ልሻር
ከአባቶቼ ባይኾንልኝ ከአያቶቼ አንድነት ልማር
እሯ በል የዛሬ ሰው
ፍቅር ፈሶብኝ ልፈሰው
ልንተባተብ ጀግንነቱን
ከልቤ ላግኝ ምኅረቱን

ማስታወሻ፡-
በፍልስፍናዊ ዘፈኑ ውስጥ ብዙ ሊያነጋግሩ፤ ሊያወያዩ የሚችሉ እሳቦቶች ሞልተውታል፡፡
©Habetu g.
@Bookfor
@Bookfor
ሰዓት እላፊ!
💚

የስፔን ላሊጋ የመጨረሻ ጨዋታዎች እጅግ አጓጊ ነበሩ ዛሬ ሁለቱ የከተማ ተቀናቃኞች አትሌቲኮ ማድሪድ እና ሪያል ማድሪድ ክለቦች ማን ዋንጫውን ያነሳዋል የሚለው ለማየት ከአንዱ ቤት ታድሜ ሁለቱንም ጨዋታዋች በግራ እና በቀኝ በኩል ባሉ የቴሌቪዥን መስኮት ስከታተል ነበር። የጨዋታዎቹ ውጤቶች የመጀመሪያው አጋማሽ ላይ በሁለቱም የጨዋታ ሜዳዎች ያልተገመቱ እና ያልተጠበቁ ነበሩ። ሁለተኛው አጋማሽ ላይ ግን ጨዋታዎቹ በሁለቱም ሜዳዎች መልካቸውን ቀይረው በመጨረሻዎቹ ሰዓታት ተመልካችን በስሜት ሰቅዘው እንደያዙ የዋንጫው ባለቤት አትሌቲኮ ማድሪድ መሆኑን የደረጃው ሰንጠረዥ አበሰሩ። የዛሬውን እና ከዛሬ ጨዋታ በፊት የነበረውን ጨዋታ ውጤት የቀየረው ሊዮስ ስዋሬዝ ነበር። ዛሬም አጭር ነገር ማለት የፈለኩት ከሱ ህይወት አንድ ነገር የምንማረው ነገር አለ ብዬ ነው ይኸውም.....


ባርሴሎና <<አርጅተሃልና ካሁን በኋላ አትጠቅመንም>> ብሎ ያባረረው ሉዊስ ሱዋሬዝ በseasoኑ 21 ጎል አስቆጥሮ አትሌቲኮ ማድሪድን ለአስራ አንደኛ ጊዜ የላሊጋ ሻምፒዮና አድርጓል።



መገፋት ለበጎ ነዉ። አንዳንድ ጊዜ መጋፋት የማትችለዉን ተራራ አሜን ብለህ መቀበል ብልህነት ነዉ። አሜን ብሎ መቀበል የመሸነፍ ምልክት አይደለም። ራስህን የምታሳይበት አንተነትህን አጉልተህ አሸናፊነትህን የምታረጋግጥበት ልዩ አጋጣሚ ነዉ።

መፅሀፉም እንዲህ ይላል.."ግንበኞች የናቁት ድንግይ አሱ የማዕዘን ራስ ሆነ"

<<አትችልም!>> የሚሉህን እርሳ፣ በእራስህና በአምላክህ ተማመን፣ ድልን ጨብጥ!!

ሰላም እደሩልኝ!

@Bookfor
@Bookfor
እንኳን አደረሳችሁ ለግንቦት 20!✌️💪 (ስለዘገየሁ በጣም ይቅርታ!)

🙏ክብር ስለሀገር ለቆሰሉ፣ ለደሙ እና ለሞቱ ይሁን!


አንድ አንበሳ፣
ያገር ፍቅር የሚያገሳ!!

አንድ ነብር፣
የሞት ጥላን የሚያስደነብር፣

አንድ ብርቱ፣
ልብ የሆነ መሰረቱ፣

አንድ ጀግና፣
የነፃነት ብርሃን ፋና!!

(( አፈር ጭረው ጭረው - ያወጡት ብረት፣
ሃየሎም አርአያ ጀግናው መሰረት!!
ተደርምሶ አይወድቅም ቢነቀንቁት!! ))

@Bookfor
@Bookfor
ህይወት ሁሌም ሁለትዮሽ ናት።
ክፍ ቀን ጥሩ ነው ;
ጥሩ ቀንን እየጮኸ ይጣራል፣
ክፍ ቀን እንደለሊት ጨለማ ነው; የለሊቱ ጨለማ ለእንቅልፍ እንደሚጠቅም ሀሉ
የቀኑ ብርሀንም ለስራ ይበጃል፣
ለህይወት እንቅልፍም ስራም በግድ አስፈላጊዎች ናቸው! ስለዚህም ይፈራረቃሉ።

መኖርን ምሉዕ የምናደርገው ሁለት ተቃራኒዎችን በሚዛን በመከወን ነው፡፡ እንባም ሳቅም፣ ደስታም ኀዘንም ፣ መስጠትም መቀበልም ፡፡ መሙላትም መጉደልም። ሲጠቃለል ፣ ሕይወት ኅብረ ቀለሟ ያማረ ቀስተ ደመና ነች፡፡

❤️ትግስት መከራን አርግዛ ደስታን ትወልዳለች። እንደሳቀ የሚቀረው
ስቀው የተነሱት ፎቶ ብቻ ነው።

ውብ ቅዳሜ❤️
@Bookfor
@Bookfor
. . . ሐሳብ ተራማጅ ነው። ከህይወት ጋር አብሮ ይጓዛል። የህይወት ምዕራፍ እስኪዘጋ ድረስ። ህይወት እጣፈንታ ነው። እንደፈለከው ሳይሆን እንደተፃፈልክ የመኖር ሚስጢር።መኖር ፈተና ነው።ካለመኖር የሚደረግ ትግል። የመሸነፍ እና ያለመሸነፍ ፍጥጫ። የመውረድ እና ያለመውረድ ፍትግያ። የመውደቅ እና የመነሳት ትንቅንቅ። ይህ ሁሉ በህይወት ውስጥ አለ። የመምጣት እና የመሄድ፡የማግኘት እና የማጣት፡ የማፍቀር እና የመፈቀር፡ ብርሀን የመሆን እና የመጨለም፡የመሆን እና ያለመሆን፡ ተስፋ የማድረግ እና ተስፋ የመቁረጥ ሩጫ፡ የማመንና ያለማመን ስሜት፡የሁለት አፅናፍ የማሸነፍ እና የመሸነፍ ጉዞ። ሁልጊዜም በህይወት ውስጥ አለ። ህይወት እንዲህ ናት።
#ashu madoenis
@Bookfor