@Book for all
4.81K subscribers
676 photos
4 videos
62 files
50 links
ማንበብ ማንበብ ማንበብ ‹‹ሰፊ ይለበሳል ጠባብ ይቀደዳል››
@መባ
ለማንኛውም አስተያየት
@Dasolo
Download Telegram
አውቃለሁ
የሆነ ወቅት ላይ ልቧ እንደቆሰለ
ታውቃለች
የሆነ ግዜ ላይ ልቤ እንደተጣለ፡፡
እና ዛሪያችን ላይ
የመውደዳችን ሀቅ ቢታይም ተገልጦ
ልንተጣጣ ነው
ከፍቅራችን በላይ ፍራታችን በልጦ፡፡
#meba
@Bookfor
@Bookfor
እቴ!❤️'ለነገ ብለሽ ፊት የምትነሺው ትላንት አለ'

ደባሪውን ትላንትን ካስተያየሺው ፤ፊት ከሰጠሺው ይጎትትሻል። ንፍጣም ነው ቀሚስሽን ይዞ አያራምድሽም ፤ላባብለው ካልሽ ዝርክርክ ነው አይፅናናም ።አይጠራም ያጨማልቅሻል ነገሽን ፤ህልምሽን ፤ሳቅሽን ያንገራግጨዋል ።

ዛሬሽን ይኮረሽምብሻል ። ውበት እና እድሜሽ ከሚኮረሸሙት ዋነኛቹ ናቸው።

እና የትላንት ጎታች ፊት ነስተሽ ነገ ላይ መንጠራራት ይበልጣል ትላንት ላይ ከማጎንበስ viva ነገ💪🏾💪🏾💪🏾✌️
@Bookfor
ሽንቁሩ በዝቶብሽ ሰላምሽ ቢጠፋ
አይዞሽ እናት አለም
ይነጋል በቅርቡ አትቁረጪ ተስፋ
@Bookfor
ውብ ቅዳሜ
ረመዳን
❤️
ረመዳን የተከበረው ወር ስያሜ መሆኑ ይታወቃል። ለመሆኑ ረመዳን ማለት ምን ማለት
ነው?

ረመዳን የሚለውን ስያሜ የቋንቋው ሊቃውንቶች በተለያየ መልኩ አብራርተውታል።
ከፊሎች ረመዳን (ረመደ ወይም ረምዳእ) ከሚለው ቃል የተወሰደ መሆኑን ይገልፃሉ።
ይህ ማለት ደግሞ ጥማትና ረሀብን የሚያመጣ እጅጉን የበረታ ሀሩር (ሙቀት) ማለት
እንደሆነ አያይዘው ይገልፃሉ።
ሌሎችም ከዚህ ጋር ተቀራራቢ ባለው መልኩ አብራርተውታል።


ለምሳሌ ታላቁ ሙፈሲር ኢማሙል ቁርጡብይ :—
"ረመዳን እኮ የተባለው ወንጀሎችን
በመልካም ስራዎች አቃጥሎ አመድ ስለሚያደርጋቸው ነው።" በማለት አብራርተውታል።
ቁም ነገሩ:—
ማነው በዚህ በተከበረ ወር መልካም ስራዎችን አብዝቶ በመስራት አመቱን ሙሉ
ያከማቸውን ወንጀል አቃጥሎ አመድ ለማድረግ ቆርጦ የተነሳ!?

❤️ረመዳን ቁርአን የወረደበት ወር
❤️ረመዳን የጀነት በሮች የሚከፈቱበት ️የጀሀነም በሮች የሚዘጉበት
❤️ረመዳን ሰይጣኖች የሚታሰሩበት ወር
❤️ረመዳን ከሺህ ወር የምትበልጥ አንድ ሌሊት የያዘ ወር
❤️ረመዳን ከምንጊዜውም በበለጠ ዒባዳ የሚደረግበት ወር
❤️ረመዳን ፈርድ ስራዎቻችን በ 70 የሚባዙበት ሱናዎቻችን የፈርድን ዋጋ የሚያገኙልን ትልቁ
የረመዳን ወር ነው።




ረመዳን መጣ!!!!!!


እንግዲህ ጓዴ ሆይ፤
ሾይጣን ሊታሰር ነው፤ ረመዳን መጣ፤
መቼስ ሰው ነኝና፤
የበደልኩህ ካለ፤
አኡፉ በሉኝና!!!!!
እኔም ሸክሜ ይቅለል፤ አንተም ነጃ ውጣ።
ለእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለታላቁ እና ተናፋቂው የረመዳን ወር በሰላም አደረሳቹ!❤️
((( መባ))) @Bookfor
#ታላቅ #እንግዳ
ከዲኑ እየሸሸ
ዱኒያን ሲከተል ~ አለም ሁሉ ታሞ
ታላቁ ሮመዳን
በርህን ያንኳኳል~ ከደጅህ ላይ ቆሞ

ክፈቺለት ይግባ ~ የልብሽን ዝግ በር
ከቁርአን ታረቂ ~ስጋሽ በዲን ይክበር

ከአላህ ትእዛዝ በቀር ~ ይውጣ ሌላ ደባል
እሱ ይቅር እንዳለን ~ ይቅር እንባባል
ዝቅ በል ከፊቱ
ቀን ከሌት ተንበርከክ ~ ለሶላት ተገዛ
በፈጥር ጊዜያቶች ~ ዱአ ማድረግ አብዛ
ከተሰጠን እንስጥ
ሰደቃሽን አብዢ ~ ሰደቃህን አውጣ
እንደ ምህረቱ ~ እዝነቱ እንዲመጣ
ይህ ክፉ ቀን አልፎ
የምትወደው ተርፎ
ዲንህ ተትረፍርፎ
የአሂራህ መንገድ ~ ቀንቶ እንድታገኘው
ታላቁ እንግዳህን
በፍቅር አገልግለህ
በዘካተል ፈጥር ~ ኢማን አርገህ ሸኘው
===||===
ከሙሉቀን ሰ•
@Bookfor
🌊እስከዚያው አልኖርም


💎“It is not uncommon for people to spend their whole life waiting to start living. ” ― Eckhart Tolle

ታላቁ ገጣሚ ጸጋዬ ገ/መድህን “አብረን ዝም እንበል” በተሰኘው ግጥሙ ውስጥ
“ተስፋ መቀነን ነው መቼም
የሰው ልጅ አይችለው የለም” ይለናል።

💧አንድም ህይወታችን ያለተስፋና እና ምኞት ነቅታ መጓዝ እንደማትችል ሲጠቁመን። በሌላ በኩል ደግሞ የሰውን ልጅ ማለቂያ የሌለውን ምኞት ሲያስዳስሰን ይመስለኛል። ህይወታችንን ብንቃኘው ደስታ ይሰጡናል ብለን ስንጠብቃቸው የነበሩት ነገሮች በእጃችን ሲገቡ እንዳሰብነው ደስተኛ ሳያደርጉን ይቀሩና ደግሞ ከፍ ወዳለ ሌላ ምኞት ያሻግሩናል።

💧“ይህንን ባገኝ ደስተኛ እሆን ነበር” የሁላችንም መፈክር አይደለም? ወይም የለመድነው የኑሮ ሂደት። ከላይ የሰፈረው የኤካርት ቶሌ አባባል ይህንን አኗኗራችን በደንብ ይገልጸዋል ብዬ አስባለው ። ሰዎች ኑሮን ለመጀመር እየጠበቁ ኑሮን ሀ ብለው ሳያጣጥሙ የእድሜያቸው ጀንበር ትጠልቃለች። ጥሩ ስራ ሲኖረኝ፤ ትዳር ስመሰርት፤ ይህንን ያህል ገንዘብ ሳገኝ፤ አላማዬን ሳሳካ ደስተኛ እሆናለው እያለን ለኑሮዋችን ቀጠሮ ስንሰጥ፤ ያሰብነው እስኪሳካ ደስተኛ ላለመሆን እየወሰንን ነው።

💧የሰው ልጅ ምኞት ማለቂያ የለውም። በጠየቅን ቁጥር ፈጣሪ ያልነውን ቢሰጠን እንኳን እንደሰው እረክቶ ለመኖር ይከብደናል። ለዚህ ነው ደስታችንን ነገ ከምናገኛቸው ነገሮች ጋር መቋጠር ዛሬን በሰመመን እንድንኖር የሚያደርገን። ያሰብኩት እስኪሳካ ደስተኛ መሆን አልችልም ማለት ነው “አስከዛው አልኖርም” ማለት ነው።
የነገው ህይወታችን ትልቅ ትርጉም አለው፤ ዋጋው ግን የዛሬን ያህል በፍጹም አይሆንም።

✍️ሚስጥረ አደራው

ሰላም!!🙏 @Bookfor @Bookfor
የተሰበረውን ጥንድ እግሯን እያሸሁ
በጀርባዬ አዝያት ሀገሬን ባሸሸሁ።
እስከ መቼ በፅልመት ውስጥ እንኖራለን? እስከመቼ ነው በንፁሀን ደም አበባ የምናሳድገው? እስከመቼ ህንፃ እያስመረቅን የድሀ ጎጆ በሳት ሲነድ እናያለን? ሀዘን ደጃችን ካልመጣ ማዘንና ለሌላው መጮህ ስለምን ተሳነን? ስለምን ከሰውነት በይ ቦታ ገደበን?
<<ልለምንህ ነበር?....>>

ልለምንህ ነበር?
ይታይሃል ሀገር?
ያ ደጉ ገበሬ፣ በክረምት አብቅሎ
ሸጨ እኖርበት ዘንድ፣ የሰጠኝን ቆሎ፤
በሰላም እንድሸጥ
አንተ እንድትጠብቀኝ፣ ከባለጊዜ ቆመጥ፤
ከአንገቴ ዝቅ ብዬ፣ በርከክ ከጉልበቴ
ልለምንህ ነበር፣ ወደ አንተ መምጣቴ?

ልለምንህ ነበር
ይታይሃል ሀገር?
አብቅሎ የሰጠኝ ይሄን እፍኝ ጥሬ
ነደደ ይሉኛል፣ ያ ደጉ ገበሬ?
ሰምተህ ይሆን እግዜር?
እባክህ ተናገር?
ሰው ለምን ይነዳል፣ የእጅ ፍሬ የሰጠው?
እንደያዝሁት ጥሬ፣ ቆሎ ሆኖ አልሸጠው?

ምነው ዝም አልህ አምላክ?
እባክህ ተናገር፣ ወይ ምህረትህን ላክ፤
ልለምንህ ነበር?
ይታይሃል ሀገር?
© Z T
@Bookfor
#ራእይ
**
#ድህነት_ምኞትን_የሚኮስስ_ህልምን_የሚገድል_መርዝ_ነው........

[Dr. ምህረት ደበበ]
................
ከካፌ በረንዳ ለይ ተቀምጬ ያላፊ አግዳሚውን ፊት በማየት መደነቅ ማደነቅ እወዳለሁ። ፊት የውስጥ ስሜት መገለጫ ሰሌዳና የሰፊው ሕይወታችን መታያ ሜዳ ነው።ለእንቦቀቅላ ሕጻናትም የሰው ፊት ከሁሉ የሚያዝናናቸውና የሚያስደምማቸው አሻንጉሊት ነው ይባላል። ፊት ባለ ብዙ ቀለም (ነጭ፣ ቀይ፣ ቡኒ፣ ጥቁር …)፣ ተንቀሳቃሽ ምስልና ድምፅ አፍላቂ መሆኑ ብቻ ሳይሆን በብዙ ስሜት የተሞላ መሆኑም ነው።

ታዲያ አንድ ቀን እንዲሁ ቁጭ ብዬ አላፊ አግዳሚውን ስቃኝ አንዲት ትንሽ ልጅ ቀረብ ብላ በሚቁለጨለጩ አይኖቿና ሀዘን በተሸከመ ድምጿ ገንዘብ እንድሰጣት ታግባባኝ ጀመር። የአፍታ ትውውቃችን ሲጨምር ታሪኳን በወፍ በረር አወጋችኝ … ምን ያህሉ እውነት ይሆን? እኔ እንጃ። ግና … ልጅ ናትና ያነገረችኝን ሁሉ ማመን መረጥኩ።ከወሬያችን ቅንጫቢው እንዲህ ነበረ።

“ሚሚዬ ስታድጊ ምን መሆን ነው የምትፈልጊው?” አልኩ እጅ እጄን የሚያዩ አይኖቿንና ቀልቧን ለመግዛት እየሞከርኩ።
ብዙም ሳታቅማማ “የቤት ሰራተኛ” አለች አንገቷን ሰበር አድርጋ። ምላሿ ከነበርኩበት ዝምብሎሽዮሽ ጨዋታ አወጣኝ። ከልቧ መሆኑን ስረዳ አቀማመጤን አስተካክዬ ነገረ-ነገሬን ወደርሷ ሙሉ ለሙሉ አዞርኩኝ። “ለምን?” አልኳት … ‘የቤት ሰራተኛ መሆን እንዴት ላንድ ህጻን ልጅ የህልም ጥግ ሊሆን ይችላል’ አልኩ በልቤ። ምክንያቱም … ‘ጥያቄው የምኞትና ስለምኞት ነው … ታዲያ ለምን መሃንዲስ፣ ጠበቃ፣ አስተማሪ ወይም ፓይለት …አላለችም? ብዬ አሰብኩ’። አሳዘነችኝ።

“የፈለኩትን ምግብ እስክጠግብ እንድበላ” ብላ፣ የሚንከራተቱ አይኖቿን በልጅነት የዋህነቷ በጎሬያቸው ውስጥ ስታንከባልላቸው ልቤ በደረቴ ውስጥ ተላወሰ። ባዶ እግሯን ናት። ፊቷና ልብሷ አቧራ ጠግቧል። ባንድ እጇ የተንጨበረረ ጸጉሯን እያከከች ዙሪያ ገባዋን ቃኘት ቃኘት አደረገች። ከኔ የተሻለ ሳያስለፈልፍ የሚሰጥ ሰው የፈለገች መሰለኝ። ትንሽ አወራሁዋት። የሰጠሁዋትን ተቀብላ ብን ብላ ካጠገቤ ስትጠፋ ምስሏና ምኞቷ ግን ከእኔ ህሊና ተጣብቆ ቀረ። ድህነት ምኞትን የሚኮስስ ህልምን የሚገድል መርዝ መሆኑን ተረዳሁ።

ልጅቱን ከዛ ወዲህ አላየሁዋትም። የዛሬ አምስት አመት ኤድና ሞል አካባቢ ነበር። ያኔ እድሜዋ ስምንት አመት ቢሆናት ነበር። ዛሬስ ህልሟ የት አድርሷት ይሆን? እርሷስ ህልሟን የት አድርሳው ይሆን?

********************************************
@Bookfor
@Bookfor
አንድ ሃያሲ ዶስቶቭስኪን ሲክበው ከእግዚአብሔር በታች የሰውን ልጅ ስነልቡና ጠልቆ የተረዳ ነው ይለዋል። ስነልቡናዊ ልብወለዶችን ከዶስቶቭስኪ በፊትም ሆነ በኋላ እንደሱ የተራቀቀበት የለም።

በዚህ አለም ላይ እንደ ሰው ልጅ አስደናቂ ፍጥረት የለም። ከሰው ልጅ ባህሪያት ደግሞ እንደ አእምሮው እፁብ ድንቅ አካል የለም። የዚህን አስገራሚ አካል ረቂቅ ባህሪ የሚያጠና ሳይንስ ደግሞ ስነልቡና ይባላል። በዘመናዊ አለም ታሪክ ደግሞ የፍሩይድን ያህል የስነልቦና አዋቂ የለም። አስደናቂው ነገር እዚህ ጋር ነው። ፍሩይድ ራሱ ጥይት የሆነው ዶስቶቭስኪን አንብቦ ነው። እዚህ ጋር ጋሽ ስብሐት ያቋርጠንና እንዲህ ይለናል፦

"ዶስቶቭስኪን አንብበህ ፐ! ይሄ ደራሲ ፍሩይድን አንብቦት ገብቶታል ልትል ትችላለህ። ነገሩ ወዲህ ነው። የሚቀድመው ዶስቶቭስኪ ነው"

አንዴ እንዲህ ማንበቤን አስታውሳለሁ፦

"የሰው ልጅ በሥልጣኔ እስከ ጥግ ሲራቀቅ የመጨረሻው የጥናት ዘርፍ ስነልቡና ነው"

ዛሬ በነጩ ሱሪ ፋንታ ቀዩን የለበስክበት ምክንያት ቢጠና ምንጩ ስነልቡና ነው። ሁለተኛው የአለም ጦርነት የተጀመረበት መሰረታዊ ምክንያት ቢጠና መነሻው ስነልቡና ነው። የሁሉም ግጭቶች መሰረት ቢተነተን ምንጩ ስነልቡና ነው። ስነልቡና የመሰረታዊ አስፈላጊነቱን ያህል ውስብስብ ነው። ሰዎች ምን ይወዳሉ? ለምን ይወዳሉ? ለምን ይጠላሉ? ከልጅነት ጀምሮ በሚገባ መጠናት የሚገባው ሰፊ ርእስ ነው። የህፃናት ስነልቡና! የአዋቂዎች ስነልቡና! የእንስሳት ስነልቡና! የወንጀለኞች ስነልቡና! የፍቅር ስነልቡና! የአሸናፊነት ስነልቡና!

የሰው ልጆች ስነልቡና በሚስጥር የተደበቀ ሃብት ቢሆን ዶስቶቭስኪ የዚያን ሃብት ሙሉ ካርታ የያዘ ጠቢብ ነው። ዶስቶቭስኪ በስነልቡና ያልነካው ርእስ የለም። ሁሉንም ጉዳዮቻችንን ይተነትንልናል። በግብረገብ፣ በስነመለኮት፣ በፍልስፍና፣ በፖለቲካ፣ በሂሳዊ ስነፅሁፍ ተፅዕኖ አሳርፏል። ብዙ መፅሀፍት ለማገላበጥ ግዜ ለሌላችሁ ስለ ሰው ልጅ ስነልቡና አብጠርጥሮ ለመረዳት ዶስቶቭስኪን መርጣችሁ አንብቡ። ታተርፋላችሁ! መልካም ንባብ! Dostoyevsky is a must read!
@Bookfor
@Bookfor
"አሁን" ሁሉም ነገር ይበርዳል ማለዳው ይበርዳል ቀትሩ ይበርዳል ምሽቱም ይበርዳል ሰዉ ይበርዳል ደስታ ይበርዳል ሳቅም ይበርዳል ክህደት ይበርዳል እምነትም ይበርዳል ስሜቶች ሁሉ በራድ ሆነዋል .....
አካልን አሳስቶ አጥንትን የሚያደቅ ስቃይ....... ህሊናና ልብ አንቀላፍተው አይኖች ሁሉ ስጋ ላይ ተጥለው ሳይ ያነዜ እጨነቃለሁ 😔 አከላቴን እየተጫንኩ የተጣበቁብኝ አይኖችን ወደ ልቤ ዘልቀው እንዲገቡ እሻለሁ ወደ ውስጤ ላሰጥማቸው ብዙ አለፋለሁ ግን ማየት እሚፈልገውን ብቻ እንደሚያይ ሰው የታወረ የለም ።
ስጋዬን ብቻ እየተመለከቱ ሰውነታቸውን ሸሽገው አውሬነታቸውን ያመላክቱኛል ......😔

በስጋዬ ላይ አይናቸውን እሚጥሉ እልፍ አይናማዎች በዙሪያዬ ሲተረማመሱ ልቤ ትጨነቃለች ነፍሴም ትለዝብብኛለች ስለምን ልበ-ስውራን አድርገህ አይናቸውን አበራህ እያልኩ እጠይቀዋለሁ ፈጣሪያቸውን ለምን ከሚያስፈልጋቸው በላይ ፈላጊ አደረካቸው ለዚህስ ተጠያቂው አንተ ነህ እነሱ እያልኩ ነዘንዘዋለሁ
በሞላው የስጋ ጥርቅሜ ውስጥ የከሳሁትን እኔን በውስጤ መኮሰሴን ማንም አያውቅልኝም እኮ ነፍሴ አቻዎቿ እንደዋዛ ሲወዳድቁ እያየች በፍርሀትና በሀዘን ነትባለች ንፋስ እንደሚያውለበልባት ከመንገድ የወደቀች ቅጠል ሆናብኛለች የት ይሆን መድረሻዋ ስል መልስ አልባ ጥያቄ ለራሴ አቀርባለሁ በዋዛ ወድቀው የቀሩ ነፍሳትን አስባለሁ ዘመኔን ፈራሁት ፤ ትውልዴን ሰጋሁት ፤ ታሪኬን ጠላሁት.....😥 ግን ........... ግን .......... ዘዉትር ፤

የሚደንቀኝ እና እምወደው ልቤን የሚረታብኝ የሆነ ነገር አለ ። ምን አትሉም? ....... " "!!!!!!!
እዚህ ሁሉ ስሜት ውስጥ ሆኜ እንኳ ይሄኛውን ስሜት እሚበልጠው ሌላውን ስሜቴን አደምጠዋለሁ !
ዘዉትር ከእኔ እማይነጥፍ "ተስፋ" እሚሉት ማገገሚያ አለ ........ አትገረሙም ወይ!!!!!! ተስፋ አታደርጉም ወይ?!

ነገ ደህና ይሆናል! 🙏🙏🙏
@Bookfor
@Bookfor
ለሰንበቲታችን!
💚
የኔ ሃገር ይች ናት!!!!!!
ሆሳእና በአርያም የሚዘመርባት፤
በዘንባባ መሃል፤
ህፃናት በእልልታ የሚጨፍሩባት፤
በዘንባባ አጊጠው፤
ነጠላ ታሽመው፤
ፍቅር ተሸክመው፤ የሚቦርቁባት፤
በዘንባባው መሃል፤የምራመድባት፤
አትጠራጠሩኝ፤
የኔ ሃገር የኔ ሃገር፤ የኔ ሃገር ይች ናት።
@Bookfor
#የእውነት #ስቅ #ላት
ትናንት ጥፋተኛን
በአደባባይ ሰቅለን ~ በገበያ መሐል
እስከዛሬ ድረስ
ፍትህ ችሎ ሳይቆም ~ ፍርዳችን ይድሀል
#የቀን #ባለተራ
ወደታች እንዳይወርድ ~ ከላይ ለመከልከል
ገበያን ይሰቅላል ~ በሌቦች መካከል
* * *
በመደብ ትግል ላይ ~ገደብ ጣይ ይወጣል
ለእለት ገበያው ~ ዘመኑን ይሸጣል
ፍርድ እየሸቀጠ ~ ፍትህ ያራክሳል
በአያቱ ችሎት ~ የልጅ ልጅ ይከሳል
* * *
ከገዢም ከሻጭም ~ ከሁለቱም ወገን
ባፍ እየደለሉ ~ የግፍ ዲናር መዝገን
ሁለቴ ለማትረፍ ~ ሁለት ጊዜ ማክሰር
በርባንን ለመፍታት ~ ንፁሀንን ማሰር
በደል መከመር ነው ~ ብሶት መደራረብ
ሌባም ዳኛም ሆኖ ~ ከሐገር ችሎት መቅረብ
#እኛም #ተከፋፍለን
ሕገ አቃቤ ሁነን ~ አንዳችን ጠበቃ
ክርክር ተጋጥመን ~ ሙግት ሳናበቃ
በመዶሻው ጩኸት ~ ባነን ስንነቃ
የመሀሏን እውነት ~ ለስቅላት ዳርጎ
ሌባ ያማክራል ~ ግራና ቀኞ አርጎ
#ድንገት #ስንባንን
ዳኛው ከሌባው ጋር ~ ቦታ ተቀያይሮ
በስላቅ ሹክሹክታ ~ ግራና ቀኝ መክሮ
ፍትህ የተጠማ ~ ሲቁለጨለጭ አይኑ
በነፃነት ሚዛን ~ ነፃ ነው ብይኑ
#አወይ #መገጣጠም
ያኔ ስትሰቀል ~ እውነት በጎልጎታ
ግራና ቀኝ ነበር ~ የሌቦቹ ቦታ
ዛሬ በወንበር ላይ ~ መስቀል ተጀምሮ
ሦስቱም ሌባ ሆኗል ~ መሀሉን ጨምሮ
===||===
ከሙሉቀን ሰ•
@Bookfor
@Bookfor
Forwarded from Meba
በግዜ ብዛት የማይናወጥ ፣ በመቆየት የማይረሳ ፣ ሁሌም ለሰው ልጅ እርምጃ መሪነት የሚፀናው ቅንነት ነው። ቅንነትን እንደያዝን ከፈተናዎች ጋር እየታገልን ቅንነት ድል ያደርጋል ብለን ተነስተን በማይዝለው ጉልበት ፣ በማይነጥፈው ብዕራችን ፣ በማይዝለው እጃችን የቅንድል ትሩፍታችን መፅሔት እንሆ በትንሳኤ ዋዜማ ወደ አንባቢያን ልትደርስ ነው።
በተለያዩ ጉዳዮች መፅሔታችን በቀኑዋ ባለመድረሷ አሳስቧችሁ የቅንነት ልባችሁ ሳይታክት ስትከታተሉን እና ስታበረታቱን ለነበራችሁ ሁሉ በመዘግየታችን ይቅርታ እየጠየቅን ቅንድል ዲጂታል መፅሔት ቅፅ 2 ቁጥር 8 እንድታመቡ እንጋብዛለን።
በቅንነት ብርሀን ፣ በምክንያታዊነት መርህ ፣ በሀገር ፍቅር ቱሩፍት እየተጓዝን በቅንነት ድል እናደርጋለን።

#ቅንድልዲጂታልመፅሔት