Bank of Abyssinia
186K subscribers
2.13K photos
176 videos
51 files
630 links
Bank of Abyssinia – The Choice for All
Welcome to BoA’s official Telegram channel!

Use @BOA_ATM_bot to access:

ATM locators
Card services & support
Real-time updates
Download Telegram
ባንካችን አቢሲንያ እና ቪዛ የ2026 ፊፋ ዓለም ዋንጫን ለመታደም ዕጣ የወጣላቸዉን የ2ኛ ዙር 4 ዕድለኞች ይፋ አደረጉ

ባንካችን አቢሲንያ እና ቪዛ ደንበኞችን ለማበረታታት ብሎም ለመሸለም የ2026 ፊፋ ዓለም ዋንጫን በስፍራው በአካል ተገኝተው ለመከታተል የሚያስችል ዕጣ የወጣላቸዉን የሁለተኛ ዙር 4 ዕድለኞች በጋራ ይፋ አደረጉ።

መጋቢት 15 ቀን 2018 ዓ.ም በዋናው መ/ቤት የባንካችን የሥራ ሐላፊዎችና የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ታዛቢዎች በተገኙበት መርሐ ግብር ላይ የባንካችን ዴፒዩቲ ቺፍ ከስተመር ሪሌሽንሺፕና አኪዩዜሽን ኦፊሰር አቶ ወሰንየለህ አበራ የዕጣ ማውጣቱን ሥነ-ሥርዓት በይፋ አስጀምረዋል።

ግልጽነትን በተከተለ መንገድ በተካሄደው በዚህ የዕጣ አወጣጥ ሥነ-ሥርዓት መሠረትም የባንካችን የምስራቅ አዲስ ዲስትሪክት ሶስት ደንበኞች (የዕጣ ቁጥር 500003708፣900018878 እና 100022256)
ዕድለኛ የሆኑ ሲሆኑ፣ አራተኛው ዕድለኛ ደግሞ የማዕከላዊ አዲስ ደንበኛ (የዕጣ ቁጥር 400010191)ሆነዋል።

ከዕጣ አወጣጡ ሥነ-ሥርዓት በኋላ ዕድለኞቹን "እንኳን ደስ አላችሁ!" በማለት ንግግራቸውን የጀመሩት አቶ ወሰንየለህ "ከቪዛ ጋር ባለን ትብብር የዲጂታል ክፍያ ስርዓትን ቀልጣፋ ለማድረግ በምናደርገው ጥረት ውስጥ ለደንበኞቻችን የ2026 ዓለም ዋንጫን በስፍራው ተገኝተው እንዲከታተሉ ዕድል በመስጠታችን ደስታ ይሰማናል!" ብለዋል።

በቪዛ የምስራቅ አፍሪካ ክላስተር ኃላፊ አቶ ያሬድ እንዳለ በበኩላቸው "ከአቢሲንያ ባንክ ጋር እያካሄድን ያለነው የሽያጭ ዘመቻ ደንበኞች በዲጂታል መንገድ ለመክፈል መምረጣቸው ከምቾቱ እና ደህንነቱ ባሻገር፣ እንደ ፊፋ ዓለም ዋንጫ 2026 ባሉ አለም አቀፍ መድረኮች ላይ መታደም ያሉ ሌሎች ተጨማሪ ዕድሎችን እንደሚፈጠር ማሳያም ጭምር ነው" ብለዋል።

በዚህ የሽያጭ ዘመቻ ጠንካራ የደንበኞች ተሳትፎ የታየ ሲሆን፣ ባለፈው አንድ ሳምንት ብቻ ከ6,000 በላይ ኩፖኖች የአቢሲንያ ባንክ ቪዛ ካርዶችን በመጠቀም ከ1,000 ብር በላይ ግብይቶችን ለፈጸሙ ደንበኞች ተሰራጭተዋል።

ይህ የሽያጭ ዘመቻ የዲጂታል ክፍያዎችን ተደራሽ ማድረግ እና የፋይናንስ አካታችነትን መደገፍ ላይ ያተኮረ ሲሆን በባንካችን እና በቪዛ መካከል በመላው ኢትዮጵያ የክፍያ ስርዓቶችን ፍጥነት፣ ደህንነት እና ቅልጥፍና ለማሻሻል ያለመ ሰፊ ስትራቴጂካዊ ትብብር አካልም ነው።

ተጨማሪ ዕጣዎች በቀሪዎቹ ሳምንታት በሚኖሩ ቀጣይ ዙሮችም የሚወጡ ሲሆን፣ ይህም ለደንበኞች በየዕለቱ የቪዛ ካርድ ሲጠቀሙ የዓለም ዋንጫ ታዳሚ የመሆን ዕድል የሚሰጥ ይሆናል።
43👍9👏3🔥2😁2
2% ተጨማሪ ጉርሻ!

የውጭ ገንዘብ ምንዛሪ ተመን (መጋቢት 17፣ 2018 ዓ.ም)

ከውጪ ሃገር በደሃብሺል፣ በዌስተርን ዩኒየን፣ መኒግራም፣ ትራንስ ፋስት፣ ቴራፔይ፣ ኢትዮ ዳሽ፣ ፋስትፔይ፣ ሪያና ሌሎች ገንዘብ አስተላላፊዎች በኩል የተላከልዎትን ገንዘብ በባንካችን በኩል ሲቀበሉ ወይም ሲመነዝሩ፤ በሁሉም ቅርንጫፎቻችን ከቀልጣፋ መስተንግዶ ጋር ተጨማሪ ጉርሻ እናበረክትልዎታለን!
አቢሲንያ የሁሉም ምርጫ!

March 26, 2026 - Exchange rate at Bank of Abyssinia

Facebook
| Instagram | LinkedIn | Twitter | Website |TikTok | Telegram
27👍10🤔1👌1
ጊዜው የፍጥነት እና የጥራት ነው፡፡ መቻልሽን የሚያግዙ አማራጮችን ስታገኚ ደግሞ ቀልጠፍ በይ! በአቢሲንያ ባንክ ዲጂታል አማራጮች ስትከፍይም ሆነ ስትገበያዪ መኪና የሚያሸልም የዕጣ ቁጥር ይላክልሻል!

አቢሲንያ የሁሉም ምርጫ!

ለተጨማሪ መረጃ 👉 https://www.bankofabyssinia.com/i-can-campaign/

#BoA_I_Can_5 #እችላለሁ #WomenAndFinance #bankofabyssinia #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ.
35👍8🔥1
2% ተጨማሪ ጉርሻ!

የውጭ ገንዘብ ምንዛሪ ተመን (መጋቢት 18፣ 2018 ዓ.ም)

ከውጪ ሃገር በደሃብሺል፣ በዌስተርን ዩኒየን፣ መኒግራም፣ ትራንስ ፋስት፣ ቴራፔይ፣ ኢትዮ ዳሽ፣ ፋስትፔይ፣ ሪያና ሌሎች ገንዘብ አስተላላፊዎች በኩል የተላከልዎትን ገንዘብ በባንካችን በኩል ሲቀበሉ ወይም ሲመነዝሩ፤ በሁሉም ቅርንጫፎቻችን ከቀልጣፋ መስተንግዶ ጋር ተጨማሪ ጉርሻ እናበረክትልዎታለን!
አቢሲንያ የሁሉም ምርጫ!

March 27, 2026 - Exchange rate at Bank of Abyssinia

Facebook
| Instagram | LinkedIn | Twitter | Website |TikTok | Telegram
18👍10
የነዳጅ ክፍያዎን - በአቢሲንያ ባንክ የሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያ ይክፈሉ!
ባንካችን አቢሲንያ፣ የሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያውን በመጠቀም የነዳጅ ክፍያዎን በቀላሉ እንዲፈጽሙ ቀላል እና ፈጣን አማራጭ አመቻችቷል፡፡ አቢሲንያ የሁሉም ምርጫ! ለአንድሮይድ:https://play.google.com/store/apps/details?id=com.boa.boaMobileBanking
ለiOS: https://apps.apple.com/us/app/boamobile/id6463218765
17👍10😁3
ዣጥ-ክፍል እንዳደረጉ ነፃ የጨዋታ ቲኬትዎን ሊያሸንፉ ይችላሉ! በአቢሲንያ ቪዛ ካርድዎ 1000 ብር እና ከዚያ በላይ ክፍያ ይፈፅሙ፤ የፊፋ የዓለም ዋንጫ 26ን ጨዋታ የሚመለከቱበትን ነጻ ቲኬት ያሸንፉ! ዕድሜ ለቪዛ!
ደጋግመው ይክፈሉ፤ የበለጠ ዕድለኛ ይሁኑ!
#FIFAWorldCup26 #WeAre26 #Visa #BankofAbyssinia
18👍8🤔2
ንግድሽን አሳድጊ! መኪናሽን አሸንፊ!

በአቢሲንያ ባንክ POS/QR ገበያሽን አዘምነሽ በቀላሉ ከ500 ብር ጀምሮ ክፍያ ስትቀበይ ዘመናዊ የኤሌክትሪክ መኪና እንሸልምሻለን

በቀላሉ ሊንኩን ተጫኚ ፤ የአቢሲንያ ቤተሰበ ሁኚ፤ ወደ መኪናሽ ቅረቢ👉https://mcnpkmnf81rz7s-0mxl8ql8p6yz8.pub.sfmc-content.com/awgmdgdxin0?src=telegram&cmp=I_can_merchant
22👍10👌3
2% ተጨማሪ ጉርሻ!

የውጭ ገንዘብ ምንዛሪ ተመን (መጋቢት 19፣ 2018 ዓ.ም)

ከውጪ ሃገር በደሃብሺል፣ በዌስተርን ዩኒየን፣ መኒግራም፣ ትራንስ ፋስት፣ ቴራፔይ፣ ኢትዮ ዳሽ፣ ፋስትፔይ፣ ሪያና ሌሎች ገንዘብ አስተላላፊዎች በኩል የተላከልዎትን ገንዘብ በባንካችን በኩል ሲቀበሉ ወይም ሲመነዝሩ፤ በሁሉም ቅርንጫፎቻችን ከቀልጣፋ መስተንግዶ ጋር ተጨማሪ ጉርሻ እናበረክትልዎታለን!
አቢሲንያ የሁሉም ምርጫ!

March 28, 2026 - Exchange rate at Bank of Abyssinia

Facebook
| Instagram | LinkedIn | Twitter | Website |TikTok | Telegram
16👍2🤩1
ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ የባንካችንን የሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያ በመጠቀም፣ ብድር ይውሰዱ ፡፡

ለአንድሮይድ | ለiOS
36👍27🔥16👏9
ያንቺ ቢሆን ደስ ይለናል! ከአቢሲንያ አገልግሎት የሚመችሽን መርጠሽ ስትገለገይ እኛ በአገልግሎታችን ከምታገኝው እርካታ በተጨማሪ የመኪና ዕድለኛ የሚያደርግሽ ዕጣ አዘጋጅተናል።

ለተጨማሪ መረጃ 👉 https://www.bankofabyssinia.com/i-can-campaign/

#BoA_I_Can_5 #እችላለሁ #WomenAndFinance #bankofabyssinia #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ.
28👍11🤔1
እንደ አጥቂ ቪዛ ካርድዎን ደጋግመው ይጠቀሙ!

አንድ ሺ ብርና ከዛ በላይ በቪዛ ካርድዎ ግብይት በመፈፀም የዕጣ ቁጥር ይቀበሉ!ዕድለኛ ከሆኑም በ2026 ፊፋ ዓለም ዋንጫ ድንቅ ጊዜ ያሳልፋሉ ! ትኬቱን የማሸነፍ ዕድል በእጅዎ ነው ! ዕድሜ ለቪዛ ! !

ፎርሙን ይሙሉ፤ ደንበኛ ይሁኑ፤ እድሎን ይሞክሩ
https://mcnpkmnf81rz7s-0mxl8ql8p6yz8.pub.sfmc-content.com/hehzo3aayy2?src=telegram&cmp=fifa
43👍12
4% ተጨማሪ ጉርሻ!

የውጭ ገንዘብ ምንዛሪ ተመን (መጋቢት 21፣ 2018 ዓ.ም)

ከውጪ ሃገር በደሃብሺል፣ በዌስተርን ዩኒየን፣ መኒግራም፣ ትራንስ ፋስት፣ ቴራፔይ፣ ኢትዮ ዳሽ፣ ፋስትፔይ፣ ሪያና ሌሎች ገንዘብ አስተላላፊዎች በኩል የተላከልዎትን ገንዘብ በባንካችን በኩል ሲቀበሉ ወይም ሲመነዝሩ፤ በሁሉም ቅርንጫፎቻችን ከቀልጣፋ መስተንግዶ ጋር ተጨማሪ ጉርሻ እናበረክትልዎታለን!
አቢሲንያ የሁሉም ምርጫ!

March 30, 2026 - Exchange rate at Bank of Abyssinia

Facebook
| Instagram | LinkedIn | Twitter | Website |TikTok | Telegram
19👍12👏1
መጋቢት 30 እየደረሰ ነው !!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ኅዳር 25 ቀን 2018 ዓ.ም ባወጣው ጥብቅ መመሪያ መሠረት ሁሉም የባንካችን ደንበኞች ሂሳባቸውን ከብሔራዊ መታወቂያ (ፋይዳ) ጋር እስከ መጋቢት 30 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ እንዲያጣምሩ ማሳሰባችን ይታወቃል። በዚህ መመሪያ መሰረት፣ በተጠቀሰው ቀነ ገደብ በአቅራቢያዎ ወደሚገኝ የባንካችን ቅርንጫፍ በመሄድ ወይም ይህን ማስፈንጠሪያ በመጠቀም (https://cs.bankofabyssinia.com/fayda_connect) ሂሳብዎን ከብሔራዊ መታወቂያ (ፋይዳ) ጋር እንዲያጣምሩ በአክብሮት እንጠይቃለን።
37👍14😱4
4% ተጨማሪ ጉርሻ!

የውጭ ገንዘብ ምንዛሪ ተመን (መጋቢት 22፣ 2018 ዓ.ም)

ከውጪ ሃገር በደሃብሺል፣ በዌስተርን ዩኒየን፣ መኒግራም፣ ትራንስ ፋስት፣ ቴራፔይ፣ ኢትዮ ዳሽ፣ ፋስትፔይ፣ ሪያና ሌሎች ገንዘብ አስተላላፊዎች በኩል የተላከልዎትን ገንዘብ በባንካችን በኩል ሲቀበሉ ወይም ሲመነዝሩ፤ በሁሉም ቅርንጫፎቻችን ከቀልጣፋ መስተንግዶ ጋር ተጨማሪ ጉርሻ እናበረክትልዎታለን!
አቢሲንያ የሁሉም ምርጫ!

March 31, 2026 - Exchange rate at Bank of Abyssinia

Facebook
| Instagram | LinkedIn | Twitter | Website |TikTok | Telegram
19🔥5👍4👏2
ባንካችን አቢሲንያ በጅማ ከተማ በአብዱልከሪም አባገሮ (ፔሌ) ስም አዲስ ቅርንጫፍ ከፈተ

የባንካችን ጅማ ዲስትሪክት መጋቢት 19 ቀን 2018 ዓ.ም በአቶ አብዱልከሪም አባገሮ (ፔሌ) ስም በጅማ ከተማ በተለምዶ ፈረንጅ አራዳ አካባቢ እጅግ ዘመናዊ ቅርንጫፍ ከፈተ።

ቅርንጫፎቹን በሃገር ባለውለታዎች በመሰየም የሚታወቀው ባንካችን ከዚህ ቀደም የጅማ ከተማ ቆርቋሪ በሆኑት በንጉሥ አባጅፋር ስም ቅርንጫፍ የከፈተ ሲሆን፣ አሁን ደግሞ የሳቸዉ አራተኛ ትውልድ በሆኑት  አብዱልከሪም አባገሮ (ፔሌ) በከተማዋ 10ኛ ቅርንጫፉን ከፍቷል።

በ1952 ዓ.ም በጅማ ከተማ የተወለዱት አብዱልከሪም አባገሮ በኢትዮጵያ ተስፋ ብሔራዊ ቡድን ውስጥ በመጫወት ስማቸው በጉልህ የሚወሳ ሲሆን፣ “ፔሌ” የሚለውን የቅጽል ስም ያገኙትም በወቅቱ በነበራቸው ድንቅ የእግር ኳስ ብቃት ምክንያት ነበር። 

አቶ አብዱልከሪም የአምስቱ ጊቤ ታሪክ አባት በመባል ሲታወቁ፣ በተለይም የሰላም አምባሳደር ከመሆናቸዉ ጋር ተያይዞ ብዙዎች ''የጂማው ማህተመ ጋንዲ'' ሲሉ ይጠሯቸዋል።

አቶ አብዱልከሪም  በልማት፣ በጤና፣ በትምህርት፣ በታሪክና ባህል ዘርፎች በርካታ የበጎ አድራጎት ሥራዎችን በማከናወን ለጅማ ከተማ ብሎም ለሃገራቸው ጉልህ አስተዋጽኦ ያደረጉ ሲሆን በአሁኑ ወቅትም የጅማ ከተማ የሰላም አምባሳደር በመሆን በተለያዩ ተቋማት በማገልገል ላይ ይገኛሉ።

በመርሃ ግብሩ ላይም የጅማ ከተማ ከፍተኛ የመንግስት ሃላፊዎች፣ የባንካችን ከፍተኛ የሥራ ሐላፊዎች፣ የጅማ ከተማ ነዋሪዎች እና ጥሪ የተደረገላቸዉ እንግዶች ተገኝተዋል።
37👍11👏5🔥3🤔2😱2😁1