Bank of Abyssinia
187K subscribers
2.19K photos
177 videos
51 files
647 links
Bank of Abyssinia – The Choice for All
Welcome to BoA’s official Telegram channel!

Use @BOA_ATM_bot to access:

ATM locators
Card services & support
Real-time updates
Download Telegram
"አሚን ለበጎነት" በሚል መሪ ሐሳብ በተለያዩ ከተሞችና ተቋማት እየተደረገ የሚገኘው የአቢሲንያ አሚን ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት የረመዳን አስቤዛ የማድረስ ተግባር ዛሬም ቀጥሎ ውሏል። በዚህም በዛሬው ዕለት በአብደላህ ኢብኑ ኡሚ መክቱም የዓይነ ሥውራን አዳሪ የቁርኣን ት/ቤት የአቢሲንያ አሚን ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት የሸሪዓ አማካሪ ቦርድ ሰብሳቢ ሸይኽ ኑረዲን ደሊል፣ የባንኩ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና የአቢሲንያ አሚን የብራንድ አምባሳደር በተገኙበት የረመዳን አስቤዛ ለተማሪዎች ማድረስ ተችሏል።
ድጋፉን በማስመልከት ምስጋናቸውን ያቀረቡት የአብደላህ ኢብኑ ኡሚ መክቱም የዓይነ ሥውራን ትምህርት ቤት ዳይሬክተር አቶ ኢብራሒም ሰዒድ፤ የአቢሲንያ አሚንን ድጋፍ በማድነቅና ከዚህ ቀደም ባንኩ ሲያደርግላቸው የነበረውን የተለያየ እገዛ በማውሳት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።


#AbyssiniaAmeen #IFB #bankofabyssinia #አቢሲኒያአሚን #Banking #BanksinEthiopia #AddisAbaba #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ #አቢሲንያአሚን
50👍13👌6🔥3
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሴቶችን ማክበር ቃል ብቻ አይደለም፤ ተግባርም ጭምር እንጂ። ባንካችንም ሴቶችን በኢኮኖሚ ለመደገፍና ለማበረታታት በቁርጠኝነት ይሠራል። መልካም የሴቶች ቀን!

አቢሲንያ የሁሉም ምርጫ !

#March8 #I_CAN_እችላለሁ #bankofabyssinia #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
109👍20👏13😱11
2% ተጨማሪ ጉርሻ!

የውጭ ገንዘብ ምንዛሪ ተመን (የካቲት 30፣ 2018 ዓ.ም)

ከውጪ ሃገር በደሃብሺል፣ በዌስተርን ዩኒየን፣ መኒግራም፣ ትራንስ ፋስት፣ ቴራፔይ፣ ኢትዮ ዳሽ፣ ፋስትፔይ፣ ሪያና ሌሎች ገንዘብ አስተላላፊዎች በኩል የተላከልዎትን ገንዘብ በባንካችን በኩል ሲቀበሉ ወይም ሲመነዝሩ፤ በሁሉም ቅርንጫፎቻችን ከቀልጣፋ መስተንግዶ ጋር ተጨማሪ ጉርሻ እናበረክትልዎታለን!
አቢሲንያ የሁሉም ምርጫ!

March 09, 2026 - Exchange rate at Bank of Abyssinia

Facebook
| Instagram | LinkedIn | Twitter | Website |TikTok | Telegram
31👍12👌3
"አሚን ለበጎነት" የረመዳን አስቤዛ ድጋፍ በድሬዳዋ ከተማ ተከናወነ!

አቢሲንያ ባንክ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎቱን በሚሰጥበት አቢሲንያ አሚን በኩል እየተከናወነ የሚገኘው የረመዳን አስቤዛ ድጋፍ፤ እሁድ የካቲት 29/2018 በድሬዳዋ ከተማ ተከናወነ።
የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር ከድር ጁሐር፣ የአስተዳደሩ የብልፅግና ጽ/ቤት ኃላፊ ክቡር ኢብራሒም ዩሱፍ እና የአቢሲንያ ባንክ ድሬዳዋ ዲስትሪክት ዳይሬክተር፣ የአቢሲንያ አሚን የሥራ ኃላፊዎች እና የብራንድ አምባሳደሩ በተገኙበት የተካሄደው የረመዳን አስቤዛ ድጋፍ ተግባር፤ ከሸይኽ በክሪ ሰበሎ ፋውንዴሽን ጋር በመቀናጀት የተከናወነ ነው።

አቢሲንያ አሚን ለወገን ድጋፍ ማድረጉንና ማኅበራዊ ኃላፊነቱን መወጣቱን በማድነቅ ምስጋናቸውን ያቀረቡት ክቡር ከንቲባው፤ የባንኩ ወገንን የማገዝ ተግባር የመሰል ተቋማት ቀዳሚ ኃላፊነት መሆኑን በማውሳት ለወደፊቱም ማኅበረሰብ አቀፍ ሥራዎች ላይ ያለው የባንኩ ተሳትፎ ተጠናክሮ እንዲቀጥል መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
አቢሲንያ አሚን በወርሐ ረመዳን እየከወነው የሚገኘው የበጎነት ተግባር በርካታ ወገኖችን ተጠቃሚ ማድረጉን የገለጹት የድሬዳዋ ዲስትሪክት ዳይሬክተር አቶ ሙሉጌታ በቀለ፤ የባንካችን አንድ እሴት የሆነው ማኅበራዊ ኃላፊነትን የመወጣት ተግባር በተለያዩ ከተሞችና ተቋማት መቀጠሉን ገልጸው፤ በድሬዳዋ ከተማ ከሁሉም ቀበሌዎች ለተውጣጡ አቅመ ደካማ ወገኖቻችን የተደረገው መሰረታዊ የአስቤዛ ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል።

#AbyssiniaAmeen #IFB #bankofabyssinia #አቢሲኒያአሚን #Banking #BanksinEthiopia #AddisAbaba #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ #አቢሲንያአሚን
39😱3👌3🤩2👍1
ጠንካራ የፋይናንስ ዐቅም ዛሬ ላይ ከአንድ ደፋር ውሳኔ ይነሣል!

የአደይ ወይም የ ዘህራህ አካውንትን በመክፈት ስኬታማ የ ፋይናንስ ጉዞሽን ዛሬውኑ ጀምሪ! ከአቢሲንያ ባንክ ጋር … ትችያለሽ!
#I_CAN_እችላለሁ #WomenAndFinance #bankofabyssinia #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
44👍16
አቢሲንያ ባንክ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎቱን በሚሰጥበት አቢሲንያ አሚን በኩል፤ በያዝነው የረመዳን ወር እየከወናቸው የሚገኙ የበጎነት ተግባራት ቀጥለዋል።

"አሚን ለበጎነት" በሚል መሪ ሐሳብ በተለያዩ ከተሞችና ተቋማት እየተደረገ የሚገኘው የአቢሲንያ አሚን ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት የረመዳን አስቤዛ የማድረስ ተግባር፤ በትላንትናው ዕለት በአንጋፋው አወሊያ ትምህርት ቤት ተከናውኗል። የአቢሲንያ አሚን የሸሪዓ አማካሪ ቦርድ ሰብሳቢ፣ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና የአቢሲንያ አሚን የብራንድ አምባሳደሩ በተገኙበት የተከናወነው የአስቤዛ ስጦታ፤ በኑሯቸው አቅመ ደካማ ለሆኑ አረጋዊያን፣ ለወላጅ አጥ ህፃናትና ጧሪ ለሌላቸው እናቶች የተበረከተ ነበር።

የረመዳን ወርን ምክንያት በማድረግ እየተከናወነ የሚገኘውን ወገንን የማገዝና ማኅበራዊ ኃላፊነትን የመወጣት ተግባር በማድነቅ፤ የባንኩን የድጋፍና እገዛ ሥራዎች ያመሰገኑት የአወሊያ እርዳታና ልማት ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሐጅ ሰዒድ አስማረ፤ አቢሲንያ አሚን ከረመዳን አስቤዛ ድጋፍ በተጨማሪ በትምህርታቸው የላቀ ውጤት ለሚያስመዘግቡ ተማሪዎች "በአሚን ስኩል አዋርድ" የሚሸልመው ማበረታቻና ለውጤታማ መምህራን የሚሰጠው የማትጊያ ሽልማት ሰፊ ትርጉም የሚሰጠው ተግባር መሆኑን አውስተዋል። "አሚን ለበጎነት" በሚል መሪ ሐሳብ ከተለያዩ ተቋማት ጋር በመቀናጀት እየተተገበረ የሚገኘው የባንካችን የረመዳን እንቅስቃሴ በቀጣዮቹ ቀናትም እንደሚቀጥል በባንኩ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በመድረኩ ተጠቅሷል።


#AbyssiniaAmeen #IFB #bankofabyssinia #አቢሲኒያአሚን #Banking #BanksinEthiopia #AddisAbaba #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ #አቢሲንያአሚን
99👍15👌4😱2🔥1
2% ተጨማሪ ጉርሻ!

የውጭ ገንዘብ ምንዛሪ ተመን (መጋቢት 01፣ 2018 ዓ.ም)

ከውጪ ሃገር በደሃብሺል፣ በዌስተርን ዩኒየን፣ መኒግራም፣ ትራንስ ፋስት፣ ቴራፔይ፣ ኢትዮ ዳሽ፣ ፋስትፔይ፣ ሪያና ሌሎች ገንዘብ አስተላላፊዎች በኩል የተላከልዎትን ገንዘብ በባንካችን በኩል ሲቀበሉ ወይም ሲመነዝሩ፤ በሁሉም ቅርንጫፎቻችን ከቀልጣፋ መስተንግዶ ጋር ተጨማሪ ጉርሻ እናበረክትልዎታለን!
አቢሲንያ የሁሉም ምርጫ!

March 10, 2026 - Exchange rate at Bank of Abyssinia

Facebook
| Instagram | LinkedIn | Twitter | Website |TikTok | Telegram
39👍4👌4
ታላቁ የረመዳን ወር የበጎነት ተግባራት ከመቼውም ጊዜ በላይ በጉልህ የሚስተዋሉበት ጊዜ እንደመሆኑ፣ ባንካችን እየከወነው የሚገኘው ከወገኖቻችን ጋር በአብሮነት የመቆምና የኢፍጣር አስቤዛ የማቅረብ ተግባር ዛሬም ተጠናክሮ ቀጥሏል።
ለበጎነት የተዘረጉት የአቢሲንያ አሚን እጆች እንደ ሁልጊዜውም በፆም ወቅት በቂ ማፍጠሪያ ማግኘት ለማይችሉና ለተቸገሩ ወገኖቹ በመድረስ ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ በዚህም በደሴ ከተማ ከሚገኙ የተራድኦ ተቋማት ጋር በመቀናጀትና ድጋፍ በማድረግ ማኅበራዊ ኃላፊነቱን በመወጣት ላይ ይገኛል።

የበጎነት አሻራውን በማሳረፍም ከተቸገሩ ወገኖቹ ጎን እንደሚቆም አስመስክሯል።

አሚን ለበጎነት!

#AbyssiniaAmeen #IFB #bankofabyssinia #አቢሲኒያአሚን #Banking #BanksinEthiopia #AddisAbaba #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ #አቢሲንያአሚን
90👍19🥰4👌2