Bank of Abyssinia
187K subscribers
2.19K photos
177 videos
51 files
649 links
Bank of Abyssinia – The Choice for All
Welcome to BoA’s official Telegram channel!

Use @BOA_ATM_bot to access:

ATM locators
Card services & support
Real-time updates
Download Telegram
የበጎነት ተግባራት ከምንግዜውም በላቀ በጉልህ በሚስተዋሉበት ታላቁ የረመዳን ወር፣ ባንካችን እየከወነው የሚገኘው ከወገኖቻችን ጋር በአብሮነት የመቆምና የኢፍጣር አስቤዛ የማቅረብ ተግባር ዛሬም ተጠናክሮ ቀጥሏል።
ለበጎነት የተዘረጉት የአቢሲንያ አሚን እጆች፣ እንደ ሁልጊዜውም በፆም ወቅት በቂ ማፍጠሪያ ማግኘት ለማይችሉና ለተቸገሩ ወገኖቹ በመድረስ ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ በዚህም በሐዋሳ ከተማ ከሚገኙ የተራድኦ ተቋማት ጋር በመቀናጀትና ድጋፍ በማድረግ ማኅበራዊ ኃላፊነቱን በመወጣት ላይ ይገኛል።
የበጎነት አሻራውን በማሳረፍም ከተቸገሩ ወገኖቹ ጎን እንደሚቆም አስመስክሯል።
አሚን ለበጎነት!
#AbyssiniaAmeen #IFB #bankofabyssinia #አቢሲኒያአሚን #Banking #BanksinEthiopia #AddisAbaba #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ #ዘህራ #የሴቶችቁጠባ #አቢሲንያአሚን
19👍14
የታላቁ የረመዳን ወር የበጎነት ተግባራት ከመቼውም ጊዜ በላይ በጉልህ የሚስተዋሉበት ጊዜ እንደመሆኑ፣ ባንካችን እየከወነው የሚገኘው ከወገኖቻችን ጋር በአብሮነት የመቆምና የኢፍጣር አስቤዛ የማቅረብ ተግባር ዛሬም ተጠናክሮ ቀጥሏል።
ለበጎነት የተዘረጉት የአቢሲንያ አሚን እጆች እንደ ሁልጊዜውም በፆም ወቅት በቂ ማፍጠሪያ ማግኘት ለማይችሉና ለተቸገሩ ወገኖቹ በመድረስ ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ በዚህም በዲላ ከተማ ከሚገኙ የተራድኦ ተቋማት ጋር በመቀናጀትና ድጋፍ በማድረግ ማኅበራዊ ኃላፊነቱን በመወጣት ላይ ይገኛል።
የበጎነት አሻራውን በማሳረፍም ከተቸገሩ ወገኖቹ ጎን እንደሚቆም አስመስክሯል።
አሚን ለበጎነት!
#AbyssiniaAmeen #IFB #bankofabyssinia #አቢሲኒያአሚን #Banking #BanksinEthiopia #AddisAbaba #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ #ዘህራ #የሴቶችቁጠባ #አቢሲንያአሚን
66👍12
2% ተጨማሪ ጉርሻ!

የውጭ ገንዘብ ምንዛሪ ተመን (የካቲት 25፣ 2018 ዓ.ም)

ከውጪ ሃገር በደሃብሺል፣ በዌስተርን ዩኒየን፣ መኒግራም፣ ትራንስ ፋስት፣ ቴራፔይ፣ ኢትዮ ዳሽ፣ ፋስትፔይ፣ ሪያና ሌሎች ገንዘብ አስተላላፊዎች በኩል የተላከልዎትን ገንዘብ በባንካችን በኩል ሲቀበሉ ወይም ሲመነዝሩ፤ በሁሉም ቅርንጫፎቻችን ከቀልጣፋ መስተንግዶ ጋር ተጨማሪ ጉርሻ እናበረክትልዎታለን!
አቢሲንያ የሁሉም ምርጫ!

March 04, 2026 - Exchange rate at Bank of Abyssinia

Facebook
| Instagram | LinkedIn | Twitter | Website |TikTok | Telegram
45👍11👏3😱2
በትጋት ከስበው ካፈሩት ላይ ከውጭ ሃገር ከቤተሰብዎ ለረመዳን የተላከልዎትን ገንዘብ በደሃብሺል፣ በዌስተርን ዩኒየን፣ መኒግራም፣ ትራንስ ፋስት፣ ቴራፔይ፣ ኢትዮ ዳሽ፣ ፋስትፔይ፣ በሪያና በሌሎች ገንዘብ አስተላላፊዎች የተላከልዎትን በባንካችን በኩል ሲቀበሉ ወይም ሲመነዝሩ፤ በሁሉም ቅርንጫፎቻችን ከቀልጣፋ መስተንግዶ ጋር ተጨማሪ 2% ጉርሻ እናበረክትልዎታለን!
አቢሲንያ አሚን
እሴትዎን ያከበረ!
28👏8👍5🔥1🤩1
ባንካችን ለጌርጌሴኖን የአዕምሮ ሕሙማን መርጃ እና ማገገሚያ ማዕከል የ 3 ሚሊዮን ብር  ድጋፍ አደረገ

ባንካችን አቢሲንያ ዛሬ የካቲት 25 ቀን 2018 ዓ.ም ለጌርጌሴኖን የአዕምሮ ሕሙማን መርጃ እና ማገገሚያ ማዕከል የህንጻ ግንባታ ዕገዛ ይውል ዘንድ የ 3 ሚሊዮን ብር  ድጋፍ አደረገ።

ባንካችንን በመወከል በስፍራው የተገኙት የባንካችን ዴፒዩቲ ቺፍ ከስተመር ሪሌሽንሺፕና አክዊዜሽን ኦፊሰር የሆኑት አቶ ወሰንየለህ አበራ  ድጋፉን ካስረከቡ በኋላ “እናንተ አብዛኞቻችንን በግልና በቡድን የማንችለውን ሸክም ተሸክማችኋል“ ያሉ ሲሆን አክለውም “መጥተን ስለጎበኘናችሁ እጅግ በጣም ተደስተናል፡ የዛሬው ድጋፋችንም የመጀመሪያው እንጂ የመጨረሻው አይሆንም” ብለዋል።


የጌርጌሴኖን የአዕምሮ ሕሙማን መርጃ እና ማገገሚያ ማዕከል መሥራችና ሥ/አስኪያጅ የሆኑት ሊቀህሩያን መለሰ አየለ በበኩላቸው ለተደረገላቸው ድጋፍ አመስግነው “አቢሲንያ ባንክ ዛሬ ያደረገልን የገንዘብ ድጋፍ በባንክ ደረጃ ከተደረጉልን ድጋፎች ሁሉ ከፍተኛው ነው“ሲሉ ተናግረዋል። “የባንኩ ሠራተኞች በተለይ በበዓል ወቅት በግልም ሆነ በጋራ መጥተው የሚጎበኙን ሲሆን የዛሬው ግን የተለየ ነው“በማለት አድናቆታቸውንም ገልጸዋል።

በዚህ የድጋፍ ርክክብ ሥነ-ሥርዓት ላይ የባንካችን የበላይ የሥራ አመራሮች እና ሠራተኞች የተገኙ ሲሆን 720 ለሚሆኑና በማዕከሉ ተጠልለው ለሚገኙ የአዕምሮ ሕሙማንም የምሳ ግብዣ ተደርጓል ።

በመጨረሻም የማዕከሉ መስራችና ሥ/አስኪያጅ የሆኑት ሊቀህሩያን መለሰ አየለ ለባንካችን የምስጋና የምስክር ወረቀትና ዋንጫ ያበረከቱ ሲሆን እንደ አቢሲንያ ሁሉ ሌሎች ባንኮችም የድጋፍ እጆቻቸውን እንዲዘረጉላቸው ጥሪ አቅርበዋል።
51👍14👏3
ለአቢሲንያ ባንክ አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ባፀደቀው የአቢሲንያ ባንክ አ.ማ የደንበኛ ሳቢ መግለጫ እና በተሠጠው ፈቃድ መሠረት 3,125,000 (ሶስት ሚሊዮን አንድ መቶ ሃያ አምስት ሺህ) መደበኛ አክሲዮኖችን በአንድ የአክሲዮን ዋጋ ብር አንድ ሺህ ስድስት መቶ (1,600) ሽያጭ ያከናውናል፡፡

ሆኖም ለአክሲዮን ሽያጭ የተፈቀደውን ጊዜ ማራዘም አስፈላጊ ሆኖ ስለተገኘ ቀደም ሲል እስከ የካቲት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ የነበረው የአክሲዮን መግዣ የጊዜ ገደብ እስከ መጋቢት 9 ቀን 2018 ዓ.ም የተራዘመ መሆኑን እያስታወቅን በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን እውቅና ከተሠጣቸው የሰነደ ሙዓለ ንዋይ አገበያዮች (ደላሎች) በኩል የግብይት ሂሳብ (Trading Account) በመክፈት የአክሲዮን ግዢውን ማከናወን የምትችሉ መሆኑን በአክብሮት እንገልፃለን፡፡

ማሳሰቢያ

ሁሉም ባለአክሲዮኖች የአቢሲንያ ባንክ ደንበኛ ሳቢ መግለጫውን በሙሉ እንዲያነቡ ይበረታታሉ፤ ለውሳኔ የተቸገሩ ከሆነ በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ፈቃድ ከተሰጣቸው ገለልተኛ የፋይናንስ አማካሪዎች ምክር ይጠይቁ። የደንበኛ ሳቢ መግለጫው መጽደቅ ሰነድ ሙዓለ ንዋዬችን ባለሀብቶች እንዲገዙ የተሠጠ ምክር ወይም ድጋፍ ተደርጎ አይወሰድም፡፡

ይህ ማስታወቂያ በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ፈቃድ አግኝቷል፡፡

ለበለጠ መረጃ ለገሐር በሚገኛው የአቢሲንያ ባንክ አክስዮን ማህበር ዋና መስሪያ ቤት በአካል ቀርቦ ማናገር ወይም በስልክ ቁጥር +25111526314 መደወል ይቻላል፤ እንዲሁም የባንኩን ድህረ ገፅ www.bankofabyssinia.com
በመጎብኘት ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
70👍22🔥9👏6😱3🤔2
2% ተጨማሪ ጉርሻ!

የውጭ ገንዘብ ምንዛሪ ተመን (የካቲት 26፣ 2018 ዓ.ም)

ከውጪ ሃገር በደሃብሺል፣ በዌስተርን ዩኒየን፣ መኒግራም፣ ትራንስ ፋስት፣ ቴራፔይ፣ ኢትዮ ዳሽ፣ ፋስትፔይ፣ ሪያና ሌሎች ገንዘብ አስተላላፊዎች በኩል የተላከልዎትን ገንዘብ በባንካችን በኩል ሲቀበሉ ወይም ሲመነዝሩ፤ በሁሉም ቅርንጫፎቻችን ከቀልጣፋ መስተንግዶ ጋር ተጨማሪ ጉርሻ እናበረክትልዎታለን!
አቢሲንያ የሁሉም ምርጫ!

March 05, 2026 - Exchange rate at Bank of Abyssinia

Facebook
| Instagram | LinkedIn | Twitter | Website |TikTok | Telegram
83👍15😱7👌4🤔3🤩3
2% ተጨማሪ ጉርሻ!

የውጭ ገንዘብ ምንዛሪ ተመን (የካቲት 27፣ 2018 ዓ.ም)

ከውጪ ሃገር በደሃብሺል፣ በዌስተርን ዩኒየን፣ መኒግራም፣ ትራንስ ፋስት፣ ቴራፔይ፣ ኢትዮ ዳሽ፣ ፋስትፔይ፣ ሪያና ሌሎች ገንዘብ አስተላላፊዎች በኩል የተላከልዎትን ገንዘብ በባንካችን በኩል ሲቀበሉ ወይም ሲመነዝሩ፤ በሁሉም ቅርንጫፎቻችን ከቀልጣፋ መስተንግዶ ጋር ተጨማሪ ጉርሻ እናበረክትልዎታለን!
አቢሲንያ የሁሉም ምርጫ!

March 06, 2026 - Exchange rate at Bank of Abyssinia

Facebook
| Instagram | LinkedIn | Twitter | Website |TikTok | Telegram
38👍3👏2😱2