ባንካችን አቢሲንያ “ማርች 8” አስመልክቶ ያዘጋጀውን የእችላለሁ መርሐ-ግብር የመዝጊያ ፕሮግራም አካሄደ
ባንካችን አቢሲንያ ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ማርች 8ን አስመልክቶ ለ4ተኛ ጊዜ ባዘጋጀው መርሐ-ግብር በድምጽ፣ በቲክቶክ ቪዲዮ እና በሥራ ፈጠራ ውድድሮች ላይ ተሳትፈው ያሸነፉ እንስቶችን ሸለመ፡፡
ተወዳዳሪዎቹ በድምጽ እና በቲክቶክ ቪዲዮ ያቀረቡት ሥራ በባለሙያና በማህበራዊ ሚዲያ በተሰጠ የሕዝብ ድምጽ ተለይተው አሸናፊ ሆነው ከ1ኛ-3ኛ ለወጡ እንስቶች ከብር 50,000 - 100,000 የሚደርስ ሽልማት የተበረከተ ሲሆን፣ በሥራ ፈጠራ ውድድር አሸናፊ ለሆኑ 50 እንስቶችም ለሥራ ማስፋፊያ የሚሆን በአነስተኛ የወለድ ምጣኔ ካለመያዣ እስከ ብር 500,000 (አምስት መቶ ሺህ) የብድር አገልግሎት የሚሰጥ ይሆናል፡፡
በዚህ ውድድር ከቀደሙት ዙሮች በተለየ ሁኔታ የተለያዩ ሕብረተሰቡን አሳታፊ የሆኑና ባንካችን ማኅበራዊ ኃላፊነቱን በተጨማሪ እንዲወጣ የሚያስችሉ ሥራዎች የተሠሩ ሲሆን ከእነዚህም አንዱ ለአንድ ሳምንት የቆየ የደም ልገሳ ፕሮግራም በመላው ሃገራችን በሚገኙ አስሩም የባንካችን ዲስትሪክት ጽ/ቤቶች ተከናውኗል፡፡
በተጨማሪም ሴት ደንበኞችና ከባንካችን ብድር ወስደው ሥራቸውን ማስፋፋት የቻሉ ሴት ሥራ ፈጣሪዎች ሥራቸውን ያስተዋወቁበትና ለሽያጭ ያቀረቡበት የንግድ ትርዒትና ባዛር የተከናወነ ሲሆን ከዚህም ባሻገር ከ400 በላይ ለሚሆኑ ሴት ሥራ ፈጣሪዎችም ስልጠና ተሰጥቷል፡፡
የዘንድሮውን እችላለሁ የሽያጭ ዘመቻ አካቶ ባለፉት ሦስት ዓመታት በተከናወኑት ዘመቻዎች ባንካችን ከብር 80 ሚሊዮን በላይ ብድር ለ175 ሴት ደንበኞች ያለዋስትና በመስጠት ባንካችን የሴት ደንበኞችን ስኬት ለማገዝ ያለውን ፍላጎት በሚገባ ያሳየ ሲሆን በሴቶች ዘንድ ያለውን ዝቅተኛ የባንክ አገልግሎት ተጠቃሚነትም ወደ ተሻለ ደረጃ ለማምጣት ችሏል፡፡

👍54❤25🔥3👏3👌3
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በአቢሲንያ ባንክ የክፍያ አማራጮች ለሚቀበሉ የንግድ ቤቶች እስከ 1.6 ሚሊዮን ብር ጉርሻ እንዲሁም ለደንበኞች የአፓርታማ መኖርያ ቤት እጣ!
👍45❤9🤩4
ባንካችን አቢሲንያ በኢትዮጵያ የፋይናንስ ፎረምና የቴክኖሎጂ ኤክስፖ ላይ ተሳተፈ
ባንካችን አቢሲንያ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባዘጋጀውና በሳይንስ ሙዚየም ከግንቦት 7 እስከ ግንቦት 8 ቀን 2017 ዓ.ም እየተካሄደ ባለው የኢትዮጵያ የፋይናንስ ፎረም ላይ ተሳተፈ ።
አቢሲንያ ባንክ በዚህ ፖሊሲ አውጪዎች፣ የፋይናንስ ተቋማት፣ የልማት አጋሮች፣ የግሉ ዘርፍ ባለድርሻ አካላት፣ የዘርፉ ከፍተኛ ባለሙያዎች እና የዳያስፖራ ኮሚዩኒ ተገናኝተው ልምድ በተለዋወጡበትና ለፋይናስ ዘርፉ እድገት ባሉ ዕድሎች ላይ በተወያዩበት ፎረም ላይ በመሳተፍ ጥሩ ልምድ ቀስሟል።
በተመሳሳይ ባንካችን አቢሲንያ ከግንቦት 8 እስከ ግንቦት 10 ቀን 2017 ዓ.ም. በአዲስ አበባ አዲስ ዓለም አቀፍ የኮንቬንሽን ማዕከል እየተካሄደ በሚገኘው የቴክኖሎጂ ኤክስፖ ላይም ተሳትፎ ጥሩ ልምዶችን ወስዷል።
በዚህ ኤክስፖ ላይ ከመላው ዓለም የተውጣጡ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች፣ የፖሊሲ አውጭዎች፣ ተመራማሪዎችና ምሁራን በመሳተፍ ላይ የሚገኙ ሲሆን እናንተም እንድትጎበኙት እንጋብዛለን።

👍55❤23