ገዳማት ኤርትራ ምሕጋዝ እዩ ባህግና
297 subscribers
352 photos
37 videos
8 files
199 links
Download Telegram
Forwarded from Afomiya
አረጋዊም ልጄ እመነኝ እኔ ከእነርሱ ጋር ስኖር ዐሥራ ሁለት ዓመት ሆነኝ ያሳደግኋቸውም እኔ ነኝ ይህንንም እንጀራና ውኃ እንድታመጣ ያዘዝኩህ ለእነርሱ ነው አለው።

ከዚህም በኋላ በሩን በከፈተ ጊዜ እነዚያ አውሬዎች ወደርሱ መጥተው ቅዱስ አባ ማቴዎስን እግሮቹን ላሱ ባልንጀሮችም ሁነውት በታላቅ መለማመጥ ተገዙለት ያንንም ውኃ ከገንዳ ላይ አፍስሶላቸው ጠጡ እንጀራውንም በሉ ከዚያም በኋላ ወደ ዱር ሔዱ።

ይህም አባ ማቴዎስ የዜናው መሰማት በቦታው ሁሉ እስከመላ ድረስ ተአምራትን እያደረገ ኖረ በየዓይነቱ በሆነ ደዌ የተያዙትን ያመጡለታል። እርሱም በላዩ በአደረች በእግዚአብሔር ኃይል ይፈውሳቸዋል።

ከተአምራቶቹም አንዱ በአንዲት ቀን ጋኔን ያደረበት ዲዳ ሰውን ወደርሱ አመጡ ቅዱስ ማቴዎስንም በአየው ጊዜ በታላቅ ድምፅ ጮኾ ሰውዬውን ከምድር ላይ ጣለው ቅዱሱም በዘይት ላይ ጸለየ በመስቀል ምልክትም አማትቦ ቀባው በዚያንም ጊዜ ድኖ አእምሮው ተመለሰ የሚሰማና የሚናገርም ሆነ ደስ ብሎትም ወደቤቱ ሔደ።

ጨዋዎችም በመጡ ጊዜ ማዕድ ያቀርብላቸውና በሰላም በፍቅር ያሰናብታቸዋል እነርሱም ለበረከት እያሉ ጥቂት ቁራሽ ወደ ቤታቸው ይወስዳሉ በበሽተኞችም ላይም በአደረጉት ጊዜ ወዲያውኑ ድነው እግዚአብሔርን ያመሰግኑታል።

ሁለተኛ ተአምር በአንዲትም ዕለት ደም ግባቷ ያማረ ጋኔን ያደረባትን ብላቴና ወደርሱ አመጡ እርሷ ብዙ ጊዜ ልብሷን ትቀዳለች ወደርሷም መቅረብ የሚችል የለም ወላጆቿም በታላቅ ኀዘን ውስጥ ይኖራሉ ቅዱስ አባ ማቴዎስም በላይዋ ጸለየና ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ዘይቱን ቀብቶ አዳናት።

ሦስተኛ ተአምር በአንዲት ዕለት እጅግ በከፋችና ታላቅ በሆነች ኃጢአት ላይ የወደቀች ኃጢአተኛ ሴት ወደርሱ አመጡ እርሷ ፀንሳ የመውለጃዋ ጊዜ የደረሰ ነው በቀንና በሌሊትም በምጥ ሕማም ትሠቃይ ነበረ አባ ማቴዎስም ልጄ ሆይ ኃጢአትሽን እመኚ በእግዚአብሔር ፊት አትዋሺ አላት። እርሷም እንዲህ አለችው እኔ ከሁለት ወንድማማቾች ጋር እነርሱ ሳያውቁ ሳመነዝር ኖርኩ በጸነስኩም ጊዜ ሕፃኑን በመርዝ አውጥቼ ለውሾች ሰጠሁት አባ ማቴዎስም በሰማ ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ በዚያንም ጊዜ ለሌሎች መቀጣጫ ትሆን ዘንድ ምድር አፏን ከፍታ ዋጠቻት።

የዚህም አባት ተአምራቶቹ ብዙ ናቸው ተነግሮ አያልቅም በአንዲትም ቀን በበረሀ ውስጥ ሲጓዝ ጅብ ልብሶቹን በጥርሶቻ ይዛ ሳበችውና በሠንጣቃ ገደል ውስጥ የወደቁ ልጆቿን አሳየችው በአወጣላትም ጊዜ ሰገደችለት እግሮቹንም ላሰች።

ከዚህም በኋላ ዕረፍቱ ሲቀርብ በታኅሣሥ ሦስት ቀን ወደ ሠርግ እንደሚጠራው ራእይን አየ ይኸውም የቅዱሳን አባቶች የአባ እንጦንስ፣ የአባ መቃርስ፣ የአባ ጳኪሚስ፣ የአባ ቴዎድሮስ፣ የአባ ሙሴ ጸሊም፣ የአባ ሲኖዳ የአንድነት ተድላ ደስታ ወዳለበት ነው። እነርሱም በኢየሩሳሌም ሰማያዊት ከእኛ ጋር ትኖር ዘንድ ወደእኛ መምጣትህ መልካም ነው አሉት ብዙ አትክልቶችና ዙፋኖች ወዳሉት ታላቅ አዳራሽም ደጅ አደረሱት ማቴዎስ ይገባ ዘንድ የአዳራሹን ደጆች ክፈቱ የሚልንም ቃል ሰማ ከዚህም በኋላ በዚሁ ወር በሰባት አረፈ ሦስት አክሊላትንም ተቀበለ።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ ጻድቅ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

፨፨፨
አርኬ
ሰላም ዕብል ለዘሱታፌሁ አሐዱ። ምስለ አብ ወምስለ ወልዱ። ማቴዎስ ነዳይ ለዓለመ ፍትወት ወእመፍቅዱ። እምብዝኀ ኂሩቱ ሶበ ኪያሁ ለመዱ። አራዊተ ገዳም ያበልዕ እኂዞ በእዱ።
፨፨፨

=>በዚችም ዕለት ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነሥቶ እንደሚወለድ በከበሩ ነቢያት አፍ ለመሰበኩ መታሰቢያ ሆነ ይቅርታውና ቸርነቱ ከእኛ ጋር ለዘላለሙ ይኑር አሜን።

፨፨፨
አርኬ
ሰላም ለስብከትከ መዓዛ ርኄ ጽጌረዳ። በአፈ ነቢያት ቅዱሳን በቤተ ልሔም ዘይሁዳ። ኢየሱስ ክርስቶስ ከመ ታድኅነነ እምተ ዕዳ። ዘኀረይከ እግዚኦ በጥበብከ እንግዳ። ለድንግል ማርያም ከመ ትኩን ወልዳ።
ሰላም እብል መቤዛዌ አምላከ። ምሥጢረ ትሥጉቱ ይንብቡ ከናፍረ ነቢያት ዘሆከ። በእንቲአሁ ዳዊት። እንዘ ያቀድም ሰቢከ። ቦ ኀበ ይቤ ፈኑ እዴከ። ወቦ ኀበ ይቤ አንሥእ ኃይለከ።
፨፨፨

ታኅሣሥ 7 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ስብከተ ነቢያት
2.አባ ዳንኤል ገዳማዊ
3.አባ ማቴዎስ ገዳማዊ
4.ብጽዕት ዲዮጥርስ

=>ወርሐዊ በዓላት
1.ሥሉስ ቅዱስ (አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ)
2.አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
3.አባ ሲኖዳ (የባሕታውያን አለቃ)
4.አባ ባውላ ገዳማዊ
5.ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ
6.ቅዱስ አግናጥዮስ (ለአንበሳ የተሰጠ)

=>+"+ ይህን በመጀመሪያ እወቁ:: በመጽሐፍ ያለውን ትንቢት ሁሉ ማንም ለገዛ ራሱ ሊተረጉም አልተፈቀደም:: ትንቢት ከቶ በሰው ፈቃድ አልመጣምና:: ዳሩ ግን በእግዚአብሔር ተልከው ቅዱሳን ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው ተናገሩ:: +"+ (2ዼጥ. 1፥20)

፨፨፨፨
ዘአቅረብኩ ማኅሌተ አዘኪርየ አእላፈ። እምእለ ተጸምዱከ ዘልፈ። ለለአነብብ ተወከፍ ዘንዴትየ መጽሐፈ። እንተ ረሰይከ እግዚኦ ጸሪቀ መበለት ውኩፈ። እምእለ አብኡ ብዑላን ዘተርፈ።
ነቢያት ቅዱሳን ወሐዋርያት ሰባኪያን። ሰማዕት ወጻድቃን ወመላእክት ትጉሃን። ደናግል ዓዲ ወመነኰሳት ኄራን። ባርኩ ባርኮ ጉባኤ ዛቲ መካን። እስከ አረጋዊ ልሒቅ ወንኡስ ሕፃን።
ለዘጸሐፎ በክርታስ ወለዘአጽሐፎ እንዘ ይደርስ። ለዘአንበቦ ወለዘተርጐሞ በልሳን ሐዲስ። ወለዘሰምዐ ቃሎ በዕዝነ መንፈስ። በጸሎተ እሙ ማርያም ዐራቂተ ኵሉ እምባእስ። ኅቡረ ይምሐረነ ኢየሱስ ክርስቶስ።
፨፨፨፨

( ጌታ ሆይ ከብልጽግናቸው ብዛት የተነሳ ብዙ መባ ካገቡት ይልቅ የደሀዪቱን አነስተኛ መባ እንደተቀበልህ ለሁል ጊዜ የሚያገለግሉህ አእላፍ መላእክትን እያሳሰብሁ በችግሬ ጊዜ የማቀርብልህን ምስጋና ተቀበል።
እናንተም ቅዱሳን ነቢያት የወንጌል ሰባኪያን ሐዋርያት ሰማዕታትና ጻድቃን ትጉሃን መላእክት ፍጹማን ደናግል እንዲሁም ደጋጎች መነኰሳት ሆይ ልጅ አዋቂ ሳይለይ የምንሰበሰብበትን የጉባኤ ቦታ ባርኩ።
ይህን መጽሐፍ ወረቀት አዘጋጅቶ ብራና ደምጦ የጻፈውና ያጻፈውም ከግዕዝ ወደ አማርኛ የተረጐመውን ቃለ ንባቡን በእርጋታ መንፈስ እና በተመስጦ ሕሊና ያዳመጠ በደለኛን ሁሉ የምታስምር የጌታ እናቱ በማርያም ጸሎት ኢየሱስ ክርስቶስ በአንድነት ይማረን።)

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር አሜን።
Forwarded from ✞ ባሮክ ✞
💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ
           አሜን

       ✥••┈••●◉ ✞ ◉●••┈••✥
              ስለ ቅዱሳን ምልጃ
       ✥••┈••●◉ ✞ ◉●••┈••✥

#ከእናተው #ለተጠየቀው #ጥያቄ #የተሰጠ #መልስ #እነሆ

📌 በመጀመሪያ ለምልጃ 3 አካላት ያስፈልጋሉ

1ኛ.የሚማለድለት (እኛ)
2ኛ.የሚማልድ (ቅዱሳን መላዕክትና ሰዎች ) 3ኛ.የሚማለደው ( እግዚአብሔር ) ነው።

ይህም ሐዋርያው
"...ትፈወሱም ዘንድ እያንዳንዱ ስለ ሌላው ይፀልይ፤ የጻድቅ ሰው ጸሎት በሥራዋ እጅግ ኃይል ታደርጋለች ባለው ተረጋግጧል ።
📖ያዕ 5፥16

ቅዱሳንም ራሳቸው ሌሎች ሰዎች እንዲጸልዩላቸው ጠይቀዋል።
"...ስለኛ ጸልዩ "
📖2ኛ ተሰ 3፥1

ለዕብራውያንም
"ጸልዩልን በነገር ሁሉ በመልካም ሁሉ እንድንኖር
📖ዕብ 13፥18

በመጽሐፍ ቅዱስ አንዱ ለሌላው እንዲጸልይ የተጠየቀበት ሁኔታ ብዙ ነው፤ ታድያ ቅዱሳን እንድንጸልይላቸው እኛን ከጠየቁን እኛ ደግሞ እነርሱ ስለኛ እንዲጸልዩልን አንጠይቃቸውምን

ገና በዚህ ዓለም በመንፈሳዊ ጦርነት ሳሉ ለመከራ የተጋለጡትን ቅዱሳንን እንዲጸልዩልን ከጠየቅን ተጋድሏቸውን የፈፀሙና በገነት ከክርስቶስ ጋር ያሉትን እንዲጸልዩልን አንለምናቸውምን

ሌላው እግዚአብሔር ሰዎች የቅዱሳንን ምልጃ እንዲጠይቁ ፈቅዷል።

እግዚአብሔር እራሱ የቅዱሳንን ምልጃ ጠይቋል ተቀብሏልም፤ እንዲሁም ምልጃ እንዲቀርብ ሰዎችን ወደ ቅዱሳን ልኳል እስቲ ለዚህ ማስረጃ እናቅርብ።

"አባታችን አብርሃም ሣራን እህቴ ነች ስላለ ንጉሱ አቤቤሜሌክ ሣራን ወደ ቤተ መንግስት ወሰዳት፤ ጌታም ወደ አቤሜሌክ በህልም መጣ በሞትም አስፈራራው አሁንም የሰውዬውን ሚስት መልስ ነብይ ነውና ስላንተም ይፀልያል ትድናለህም ባትመልሳት ግን አንተ እንድትሞት ለአንተ የሆነውም ሁሉ እንዲሞት በእርግጥ እወቅ"
📖ዘፍ 20፥7

አቤሜሌክን እግዚአብሔር ሣራን እንደመለሰ ወዲያውኑ ሊምረው ይችል ነበር፤ ነገር ግን ይቅር ይባልና በሕይወት ይኖር ዘንድ እግዚአብሔር የአብርሃምን ምልጃ ጠየቀ።

የኢዩብ ታሪክ "...በእግዚአብሔር ቴማናዊውን ኤልፋዝን እንደ ባሪያዬ በአንተ በሁለቱ ባለንጀሮችህ ላይ ነድዶአል፤ አሁን እንግዲህ 7 ወይፈኖችና 7 አውራ በጎች ይዛችሁ ወደ ባሪያዬ ወደ ኢዮብ ዘንድ ሂዱ የሚቃጠልንም መስዋዕት ስለራሳችሁ አሳርጉ ባሪያዬም ኢዮብ ስለእናንተ ይጸልያል፤ እኔም እንደ ስንፍናችሁ እንዳላደርግባችሁ ፊቱን እቀበላለው።
📖ኢዮ 42፥7

ከላይ ባየናቸው በሁለቱም ሁኔታዎች እግዚአብሔር ራሱ ለበደለኛ ሰዎች ተናገረ፤ ሆኖም ራሱ በቀጥታ  ይቅርታን አላደረገም፤ ነገር ግን የቅዱሳንን ጸሎት ጠየቀ፤ ይህም ቅዱሳን በሰዎች ፊት ይከብሩ ዘንድ ነው ። 

ስለ ሰዶም የአብርሃም ምልጃ አብርሃም ጉዳዩን ሳያውቀው እግዚአብሔር ሰዶምን ሊቀጣ ይችል ነበር፤ አብርሃም በእግዚአብሔር ፈቃድ ጣልቃ አልገባም፤ ነገር ግን ጌታ ለአብርሃም ስለ ሰዶም ምልጃን ያቀርብ ዘንድ ጉዳዩን ገለፀለት፤ ምልጃውንም ተቀበለው፤ አብርሃም በሰዎች ፊት ከፍ ከፍ ይል ዘንድና እኛም ስለቅዱሳን ክብር እንድንረዳ ይህ በመጽሐፍ ይጻፍ ዘንድ የእግዚአብሔር ፍቃድ ሆነ።
📖ዘፍ 18፥17

ሙሴ ስለእስራኤል ምልጃን እንዳቀረበ በወርቅ የሰሩትን የጥጃ ምስል አምልከዋልና እግዚአብሔር ሕዝቡን ሊያጠፋ ወደደ ይህንንም ለነብዩ ሙሴ አሳወቀው፤ ስለ ህዝቡ ምልጃ እንዲያቀርብ ዕድል ሰጠው፤ ከዚያም ምልጃውን ተቀበለው፤ ልክ አብርሃም "እግዚአብሔርን እንዲህ ያለው አድራጎት ከአንተ ይራቅ " እንዳለው፤ ሙሴም " ... እግዚአብሔር በሕዝብህም በክፋታቸው ላይ ራራ አለ ..." እግዚአብሔርም በሕዝቡ ላይ ሊያደርግ ስላሰበው ክፋት ራራ።
📖ዘጸ 32፥7

እኛም ይህን አብነት አድርገን ቅዱሳን ይጸልዩልንና ይማልዱን ዘንድ እንጠይቃለን

💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️

"አንተ ሰው ቃለ እግዚአብሔርን ተማር፤ ባትለወጥም ዝም ብለህ ተማር! ኹልጊዜ ተማር። ላትስተካከል ትችላለህ፤ ላትለወጥ ትችላለህ፤ ግን ተማር፤ ቢያንስ ቢያንስ ጥሩ ሰው እንኳን ባትኾን ራስህን ለመውቀስ የምትችልበት ዓቅም ታገኛለህ፤ ካልተማርክ ግን ራስህን እንኳን መውቀስ የምትችልበት ዓቅም አታገኝም፤ ስለዚህ ተማር ስትማር ቢያንስ ኃጢአት እንኳን ስትሠራ ራስህን እየወቀስክ ትሠራለና፤ ይህች የንስሐ በር ትኾንልሃለች፤ አንድ ቀን ወደ ንስሐም ትመራሃለች"

📘ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

               ወስብሐት ለእግዚአብሔር
                       ይቆየን
ዓመታዊ በዓል ናይ ጻድቁ ኣቡነተክለሃማኖት ናይ ልደቱ በዓል ኣብ ዝተወልደሉ ሃገረ ቡልጋ ጽላላሽ ኢንቲሳ ገዳም ንምክባር ንዕለት 23 ሓሙስ ከይድካ 24 ዓርቢ ምምላስ ጉዕዞ ተዳልዩ ኣሎ ክንከይድ ንድሊ ዋጋ 300 ኮይኑ ኣቀዲምና ንመዝገብ
የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት
#ታኅሣሥ_፲፱ #በዓለ_ቅዱስ_ገብርኤል#ወሥርዐተ_ማኅሌት፡፡
ቅዱስ ገብርኤል፤
#ሊቀ_መላእክት_በመላእክት_ሁሉ_ላይ_የተሾመ_ነው_ሄኖክ_10፥14
#የአርባብ_የ10ሩ_ነገደ_መላእክት_አለቃ_ነው
#ከከበሩ_መላእክት_አንዱ_ነው_ሄኖክ_6፥7፤
#አካሉ እንደ ቢረሌ የሚመስል (ጽሩይ የሆነ) ፥ ፊቱም እንደ መብረቅ አምሳያ የሆነ፤ ዐይኖቹም እንደሚንበለበል ፋና፣ ክንዶቹና እግሮቹም እንደ ጋለ ናስ፣ የቃሉም ድምፅ እንደ ብዙ ሕዝብ ድምፅ ነው፡፡/ዳን.10፥5-9/
#መልአከ_ራማ_ዘራማ_ልዑል_ነው፤ (የራማ ልዑል ነው)
#አብሣሬ_ትስብእት_ነው
#መጋቤ_ሐዲስ_ነው
#በእግዚአብሔር_ፊት_የሚቆም_መልአክ_ነው_ሉቃ_1፥19፤
#ለቅዱሳን_እውቀትን_የሚገልጽላቸውና_ከአላውያን_የሚታደጋቸው_ነው_ /ድርሳነ_ገብርኤል/
#መልአከ_ሰላሞሙ_ወመልአከ_ኪዳኖሙ_መልአከ_አድኅኖ_መልአከ_ኀይል_መልአከ_ፍስሐ (የሰላም መልአክ ፥ የኪዳን መልአክ፥ አዳኝ መልአክ፥ ኀያል መልአክ ፥ የደስታ መልአክ ነው)
#ከሣቴ ጥበብ (ጥበብን የሚገልጽ ነው) /ት.ዳን./
#ናዛዜ_ኅዙናን_ (ያዘኑትን_የሚያጽናና_) መልአክ_ነው፨
✤ ገብርኤል ማለት የእግዚአብሔር ልጅ ማለት ነው፤ የወልደ እግዚአብሔርን መወለድ አብሥሯልና፨ አንድም የሁለት ቃለት ጥምር ነው እነዚህም ገብር እና ኤል ሲሆኑ ትርጕማቸውም ገብር አገልጋይ ማለት ሲሆን ኤል ማለት ደግሞ አምላክ ማለት ነው፤ በተገናኘ ገብርኤል ማለት የአምላክ አገልጋይ /የእግዚአብሔርን ልጅ የሚመስል የአምላክ አገልጋይ/ ማለት ነው፡፡
✼ ነቢዩ ዳንኤል “ዐይኖቼንም አነሣሁ” አለና አስከትሎ “እነሆም በፍታ የለበሰውን ጥሩም የአፌዝን ወርቅ በወገቡ ላይ የታጠቀውን ሰው አየሁ፡፡ አካሉም እንደ ቢረሌ ይመስል ነበር፤ ፊቱም እንደ መብረቅ አምሳያ ነበረ፤ ዐይኖቹም እንደሚንበለበል ፋና፣ ክንዶቹና እግሮቹም እንደ ጋለ ናስ፣ የቃሉም ድምፅ እንደ ብዙ ሕዝብ ድምፅ ነበረ፡፡… ይህንንም ታላቅ ራእይ አየሁ፤ ኃይልም አልቀረልኝም፤ ክብሬም ወደ ውርደት ተለወጠብኝ ኃይልም አጣሁ፡፡ የቃሉንም ድምፅ ሰማሁ፤ የቃሉን ድምፅ በሰማሁ ጊዜ ደንግጬ በምደር ላይ በግምባሬ ተደፋሁ” አለ፡፡(ዳን.10፥5-9) ነቢዩ ዳንኤል እንዲህ ብሎ የተናገረው የመላእክት አለቃ የቅዱስ ገብርኤልን አስፈሪ ግርማ በተመለከተ ጊዜ ነበር፡፡
፠ “እነሆ ከዋነኞቹ አለቆች” አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ”(ዳን.10፥13) ብሎ በተናገረው ንግግሩ በመላእክት ላይ የተሾሙ ሌሎች አለቆች እንዳሉ ማስተዋል እንችላለን፡፡ ቅዱስ ጳውሎስም በቅዱሳን መላእክት ዘንድ ስላሉት ነገዶች ሲገልጽ “… በሰማይ ያለውን በምደር ያለውን የሚታየውንና የማይታየውን መናብርትም ቢሆኑ አጋእዝትም ቢሆኑ መኳንንትም ቢሆኑ ቀደምትም ቢሆኑ ሁሉም በእጁ ሆነ፤ ሁሉም በእርሱ ለእርሱ ተፈጠረ” (ቈላ.1፥16) በማለት ይዘረዝራቸዋል፡፡ ከዚህ ተነሥተን መላእክት በተለያዩ ዐበይት ነገዶች የተከፈሉና ለእያንዳንዱም ነገድ የራሱ የሆነ አለቃ እንዳለው ማስተዋል እንችላለን፡፡ ቅዱስ ገብርኤልም ከእነዚህ ዐበይት የመላእክት ነገዶች መካከል አንዱ በሆነው አርባብ በሚባለው ዐቢይ ነገድ ላይ የተሾመ ሲሆን ከ100ው ነገደ መላእክት መካከል ከበታቹ የሚመራቸው ዐሥር ነገደ መላእክት አሉት፤ ከተማቸውም በሰማየ ራማ ነው፡፡
✼ ቅዱሳን መላእክት በቅዱስ ሚካኤል ፊት አውራሪነት የሰው ልጆች ጠላት የሆነውን ዲያብሎስን ተዋግተው ድል ከመንሳታቸው አስቀድሞ፤ እንደ አምላክ ሊመለክ የወደደውን ሳጥናኤልን ቅዱስ ገብርኤል በመቃወም ‹‹ንቁም በበህላዌነ እስከ ንረክቦ (ነአምሮ) ለአምላክነ “አይዟችሁ ፈጣሪያችን እስክናገኘው፣ እስክናውቀው ድረስ በያለንበት ጸንተን እንቁም፡፡” (አክሲማሮስ ገጽ.35) በማለት መላእክትን ያረጋጋ መልአክ ነው፡፡ ✼ ቅዱስ ገብርኤል በተወዳጁ መልአክ በቅዱስ ሚካኤል መሪነት የሰው ልጆች ጠላት የሆነውን ዲያብሎስን ተዋግተው ድል እንዲያደርጉ ወደ ጥልቁ እንዲጣል አድርጓል ራእ12፥7፤ ነቢዩ ኢሳይያስ በሰማያት የሳጥናኤል ትዕቢትና ውድቀት ምን እንደሚመስል ሲጽፍልን “አንተ በንጋት የሚወጣ አጥቢያ ኮከብ ሆይ እንዴት ከሰማይ ወደቅህ! ወደ አሕዛብ መልእክትን የላክ አንተ ሆይ እንዴት እስከ ምድር ድረስ ተቀጠቀጥህ! አንተም በልብህ ወደ ሰማይ ዐርጋለሁ ዙፋኔንም ከእግዚአብሔር ከዋክብት በላይ ከፍ ከፍ አደርጋለሁ፤… በልዑልም እመሰላለሁ አልህ፡፡ ዛሬ ግን ወደ ሲኦል ትወድቃለህ፤ ወደ ምድር ጥልቅም ትወርዳለህ” (ኢሳ.14፥16) በማለት ገለጠልን፤ ወደ ምድር የጣሉት በመላእክት አለቃ በቅዱስ ሚካኤል መሪነት እነ ቅዱስ ገብርኤል ናቸው፡፡
✼ ቅዱስ ገብርኤል ወንጌላዊው ቅዱስ ሉቃስ ከሊቃነ መላእክት አንዱና በእግዚአብሔር ፊት የሚቆመው ታማኝ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ነው ብሏል (ሉቃ 1፥19)፤
✼ ታላቁ ነቢይ ሄኖክም ስለ ነገረ መላእክት በተናገረበት አንቀጽ እንዲህ ሲል መስክሯል ‹‹በአበቦች ላይ በገነትም በጻድቃን ላይ በኪሩቤልም ላይ የተሾሙ ከከበሩ መላእክት አንዱ ገብርኤል ነው፡፡›› ሄኖክ 6፥7፤ ‹‹በሦስተኛውም በመላእክት ሁሉ ላይ የተሾመ ቅዱስ ገብርኤል ነው›› ሄኖክ 10፥14 እያለ የመልአኩን ክብር ተናግሯል፡፡
** ቅዱስ ገብርኤል መንፈሳዊ እውቀቱን የሚያካፍላቸው መልአክ ብቻ አይደለም፤ ለእግዚአብሔር በመገዛታቸው ምክንያት ከአላውያን ገዢዎች ከሚደርስባቸው መከራም የሚታደጋቸው መልአክም ነው፡፡ ነገር ግን ያደረጋቸው ተዓምራቶች በመጽሐፍ ቅዱስ፣ በመልክኡ፣ በድርሳኑ፣ በተአምሩ፣ …. የተጻፉ ቢሆንም፤
✤✼ #ታኅሣሥ_19 #ካደረጋቸው_ተራዳኢነት_ዋናውን_እንደከሚተለው_እናያለን_
፠ አናንያና(ሚሳቅ)፣ አዛርያ(ሲድራቅ) እና ሚሳኤል(አብደናጎ) ያዳናቸው ያዳነበት ቀን ነው፡፡ አናንያና(ሚሳቅ)፣ አዛርያ(ሲድራቅ) እና ሚሳኤል(አብደናጎ) የፋርስ ባቢሎን ንጉሥ የነበረው ናብከደነፆር በዱራ(አዱራን) በሚባል ስፍራ ላይ ላቆመው ጣየዖት ምስል ስገዱ ሲላቸው …. የምናምነው አምላክ ያድነናል፤ ባያድነን እንኳን (አምላካችን በእሳት ሰማዕት እንድንሆን ፈቃዱ ቢሆነረ አንኳን) አንተ ላቆምከው ምስል አንሰግድም ብለውታል፡፡ ንጉሡም ወደ እቶን እሳት እንዲጣሉ አድርጓቸዋል፤ በመልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ተራዳኢነት ግን ከእቶን እሳቱ የልብሳቸው ዘርፍ እንኳን እሳት ሳይነካው ከእሳቱ ድነዋል፡፡
እንዲሁም ዛሬ፤
#ቅዱስ_ዮሐንስ_ዘሀገረ_ቡርልስ_በዓለ_ዕረፍቱ_ እንዲሁም
#ኢትዮጵያዊው_አቡነ_ስነ_ኢየሱስ_ (#ገዳማቸው_በሰሜን_ጎንደር_ትክል_ድንጋይ_አካባቢ_የሚገኘው_) #በዓለ_ዕረፍታቸው_ነው_፡፡
በፌስቡክ ሊያገኙን ከፈለጉ፤ የቀጨኔ ደ/ሰላም መድኀኔዓለምና ደ/ትጉሃን ቅ/ገብርኤል ቤ/ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት ሰሌዳ መጽሔት፡፡
በቴሌግራም ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://t.me/medihanaelem
ዓመታዊ በዓል ናይ ጻድቁ ኣቡነተክለሃማኖት ናይ ልደቱ በዓል ኣብ ዝተወልደሉ ሃገረ ቡልጋ ጽላላሽ ኢንቲሳ ገዳም ንምክባር ንዕለት 23 ሓሙስ ከይድካ 24 ዓርቢ ምምላስ ጉዕዞ ተዳልዩ ኣሎ ክንከይድ ንድሊ ዋጋ 300 ኮይኑ ኣቀዲምና ንመዝገብ 0983340375/0967821460
ቀጻሊ ቀዳም ብምክንያት ልደት ጎይታናን ኣምላክና መድኋኒናን ኢየሱስ ክርስቶስ ናይ ልደት በዓል ናይ ቅዱስ ላሊባል ድማ በዓሉ ምኳኑ ናብ ገዳም ድንቂ ተኣምር ካብ ጎቦ 11 ቤተመቅደስ ዝሰርሓሉ ላስታ ላሊበላ ጉዕዞ ተዳልዩ ኣሎ ንብገሰሉ ቀዳም 25 እዩ ስለዚ ንከይድ ንደሊ ኣቀዲምና ንመዝገብ ክሳብ 40 ገዳማት ክንሳለም ኢና ጣና ሓይቅ ወሲክካ ብጃልባ እንዳተጓዓዝካ ዝክየድ 0983340375/0967821460 ደውሉ ቦታ ሕዙ።
Forwarded from You Must Know
ኢትዮ-ቴሌኮም በግማሽ አመት ውስጥ 22.04 ቢሊየን ብር ገቢ በማድረጉ ታላቅ ደስታ ስለተሰማው.....
❖በዚህ 👇በyoutube አድራሻችን
https://www.youtube.com/channel/UC4TvLlWLggrOYj-04jSSJMQ
..................በመግባት Subscribe (ሰብስክራይብ) ለሚያደርጉ ደንበኞች ሁሉ......! የ2 GB ነፃ ኢንተርኔት እና የ80 ደቂቃ ነፃ የአየር ሰዓት ይሸለማሉ! እናመሰግናለን!!!!
በዚህ👇https://www.youtube.com/channel/UC4TvLlWLggrOYj-04jSSJMQ
👆ይህንን አድራሻ(link) በመጫን ኢትዮ-ቴሌኮምን ሰብስክራይብ በማድረግ ይሸለሙ...!

@zemarian
ሥርዓተ ማኅሌት ዘጥምቀት 11

የማንኛውም ወርኃ በዓልና ክብረ በዓል ሥርዓተ ማኅሌት መጀመሪያ "ሥርዓተ ነግሥ"
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኃቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል።

መልክአ ሥላሴ
ሰላም ለአእዛኒክሙ አናቅጸ ጸሎት ሠናይ ምሥጢራተ ሰሚዕ ሥላሴ ዘይተልዎ ርእይ
በአብትረ ያዕቆብ በርሀ ሥላሴክሙ ፀሐይ
ወተመሰሉ ሰብአ ዓይን አባግዓ ላባ ወማይ
ለኀበ አባግዕ ዘዮም ወጥምቀት ዓባይ።

ዚቅ
መኑ ይወርድ ውስተ ቀላይ፤ ክርስቶስ ውእቱ ዘወጽአ እማይ፤ እመንፈስ ቅዱስ ሠለስቲሆሙ፤ እለ አሐዱ እሙንቱ ፫ቲሆሙ፤ እለ ይከውኑ ሰማዕተ ፫ቲሆሙ፤ ለሊሁ ወረደ መንፈስ ቅዱስ፤ ከመ ይቀድስ ማያተ፤ ስቡሕኒ ውእቱ ወልዑልኒ ውእቱ ለዓለም፤ ጸጋ ወጽድቅሰ፤ በኢየሱስ ክርስቶስ ኮነ።

ነግሥ
ሰላም ለማየ ዮርዳኖስ ዮሐንስ ዘአተቦ፤ መንፈስ ቅዱስ ከመ አጥበቦ፤ ሶበ መጽአ ቃል እምሰማይ ለተናብቦ፤ ነድ ለማየ ባሕር ከበቦ፤ ማይ ኀበ የሐውር ጸበቦ።

ዚቅ
ርእዩከ ማያት እግዚኦ፤ ርእዩከ ማያት ወፈርሑ፤ ደንገፁ ቀላያተ ማያት ወደምጸ ማያቲሆሙ።

ወረብ
ርእዩከ 'እግዚኦ'/፪/ ርእዩከ ማያት/፪/
'ደንገፁ'/፪/ ቀላያተ ማያት ደንገፁ ቀላያተ ማያት/፪/

ትምህርተ ኅቡዓት
እምሰማያት እምኀበ አብ አይኅዓ፤ በሕማማተ ሥጋሁ ቤዘወነ፤ ወደሞ ክቡረ መንፈሰ ሕይወት፤ ወቅድሳተ መንፈስ ወሀበነ፤ ወማየ መንጽሔ ዚአነ።

ወረብ
'ወደሞ ክቡረ'/፪/ መንፈሰ ሕይወት ወቅድሳተ መንፈስ ወሀበነ/፪/
ወማየ መንጽሔ ዚአነ/፬/

አንገርጋሪ
ክርስቶስ ተወልደ ክርስቶስ ተጠምቀ፤ ወለደነ ዳግመ እማይ ወእመንፈስ ቅዱስ፤ እሙነ ኮነ ለፀሐየ ጽድቅ አስተርእዮቱ፤ አማን፤ መንክር ስብሐተ ጥምቀቱ።

ወረብ
ክርስቶስ ተወልደ ክርስቶስ ተጠምቀ ክርስቶስ ተወልደ/፪/
'ወለደነ ዳግመ'/፪/ እመንፈስ ቅዱስ ወማይ/፪/

እስመ ለዓለም
ሖረ ኢየሱስ እምገሊላ ኀበ ዮሐንስ፤ ከመ ያጥምቆ በፈለገ ዮርዳኖስ፤ ወወጺኦ እማይ ተርኅወ ሰማይ፤ መጽአ ቃል እምደመና ዘይብል ዝንቱ ውእቱ ወልድየ፤ ዘአፈቅር ሎቱ ስምዕዎ።

ወረብ
ሖረ ኢየሱስ እምገሊላ ኀበ ዮሐንስ/፪/
ከመ ያጥምቆ በፈለገ ፈለገ ዮርዳኖስ/፪/

ዕዝል
ቀዳሚሁ ቃል ውእቱ ቃል፤ ቃለ እግዚአብሔር፤ ውእቱ ቃል ሥጋ ኮነ፤ ወተገሠ በሥጋ፤ መንፈስ ዘኢይትገሠሥ ወዘኢይትለከፍ፤ ዘመልዕልተ ሰማያት ዘመልዕልተ ሥልጣናት፤ ወገብረ መንጦላዕተ ሥጋ ሰብእ መዋቲ፤ ወረደ ዲበ ምድር፤ ወአንሶሰወ ውስተ ዓለም፤ በበህቅ ልህቀ በ፴ ክረምት፤ በዮርዳኖስ ተጠምቀ።

ምልጣን
ዘመልዕልተ ሰማያት ዘመልዕልተ ሥልጣናት፤ ወገብረ መንጦላዕተ ሥጋ ሰብእ መዋቲ።

አመላለስ
ወገብረ መንጦላዕተ/፪/
ሥጋ ሰብእ መዋቲ/፪/
@zemarian
አቡን
በ፭: እስመ ሰምዓ ይቀውም ሎቱ አብ ናዛዚ በርእየተ ርግብ ውስተ ምጥማቃት እንዘ ይብል፤ ዝንቱ ውእቱ ወልድየ ዘአፈቅር፤ ዘኪያሁ ሠምርኩ ይቤ፤ ወበይእቲ ሥጋ እንተ ነሥአ መድኅን እምቅድስት ድንግል፤ ኪያሃ ሠምረ አብ በሥጋ ምጽአቶ።

ቅንዋት
እምሰማያት ወረደ፤ ወእማርያም ተወልደ፤ ከመ ይሥዓር መርገማ ለሔዋ ዲበ ዕፅ ተሰቅለ፤ በ፴ ክረምት በዮርዳኖስ ተጠምቀ፤ ዘነቢያት ሰበክዎ ወአስተርአየ ገሃደ።

ሰላም
ተሣሐልከ እግዚኦ ምድረከ ሃሌ ሉያ፤ ዮም ፍሥሐ ኮነ በእንተ ልደቱ ለክርስቶስ፤ ወበእንተ ጥምቀቱ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፤ ኃዲጎ ፺ወ፱ ነገደ፤ ቆመ ማዕከለ ባሕር፤ ገብአ ወወጽአ በሰላም።

ምልጣን
ኃዲጎ ፺ወ፱ ነገደ፤ ቆመ ማዕከለ ባሕር፤ ገብአ ወወጽአ በሰላም።

ወረብ
ኃዲጎ ፺ወ፱ ነገደ/፪/
ማዕከለ ባሕር ቆመ ማዕከለ ባሕር/፪/


እመሒ ስሕተኩ አንትሙ እለ በመንፈስ አፀርትዕዎ ''የተሳሳትኩት ቢኖር እናንተ በመንፈስ ያላችሁ አቃኑት''።

አዘጋጅ ፦ ©ዲ/ን መሣይ ና ዲ/ን ሱራፊ
🌹መልካም በአል 🌹

ከመምህር ዳንኤል ዜማው
@zemarian
ዝመጽእ ዘሎ ሶኒ ዕለት 16 ለካቲት ብግእዝ ናይ ወላዲተ ኣምላክ ድንግል ማርያም ቃል ኪዳን ካብ ወዳ ዝተቀበለትሉ ኪዳነ ምህረት ዝተዋሃበትሉ ዝተሰመየትሉን ዓቢ ክብረ በዓላ ስለዝኮነ በዚ ምክንያት ጉዕዞ ገዳም ናብ ቅድስቲ ሰሚነሽ ኪዳነ ምህረትን ቅዱስ ሚካኤልን ተዳልዩ ኣሎ ክንከይድ ንደሊ ኣደቂምና ክሳብ ቀደም ደዊልና ንመዝገብ ሓደሪና ደልሶመልሶን ኣሎ። 0983340375
ብምክንያት ዓመታዊ ክብረ ብዓል ኣቡነ ገብረመንፈስቅዱስ 5 መጋቢት በዓለ ዕረፍቶም ናብቲ ዓቢ ገዳሞም ምድረ ከብድ ጉዕዞ ተደልዩ ኣሎ በረከቶም ክሓድረና ምእንቲ ናብ ገዳሞም ክንሳለም፡ንደሊ ኣቀዲምና ንመዝገብ ቦታ ከይመልኣና 0983340375 ንደውል።
ጉዕዞ ናብ ገዳም ምድረከብድ ሓዳር እዩ ምክንያቱ ዓመታዊ በዓል ስለዝኮነ ዕለት 4 መጋቢት ኬድና 5 መጋቢት ድሕሪ ቅዳሴ ምምላስ ናይ መኪና ዋጋ 200 ብር እዩ ብስላም የብጽሓና ናይ በረከቱ ተሳተፊቲ ይበላና ጻድቁ።
ጉዕዞ ናብ ገዳም ምድረከብድ ሓዳር እዩ ምክንያቱ ዓመታዊ በዓል ስለዝኮነ ዕለት 4 መጋቢት ኬድና 5 መጋቢት ድሕሪ ቅዳሴ ምምላስ ናይ መኪና ዋጋ 200 ብር እዩ ብስላም የብጽሓና ናይ በረከቱ ተሳተፊቲ ይበላና ጻድቁ። 0983340375 ደዊልና ብዘለናዩ ኮይና ክንምዝገብ ንክእል ኢና።
Solomon mehari ኩሉ ስም ወጋገን ባንክ 751190830101 ኣዋሽ ባንክ 01320192117000 ንግድ ባንክ 1000180820462 ብሰለስቲኡ ኣብ ዘዘለናዩ ክንከፍን ንክእል ኢና ምስከፈልና ግን ክንሕብር ኣለና ደዊልና ሰሰናዩ። ብሩክ ጾም ንኩልና ይግበረልና ኣሜን።
ናብ ገዳም ጻድቅ ኣቡነ ሃብተማርያም ናይ ለሚን ጸበል ዘለዎ ናይ ክፉእ ግብሪ ጸላኢ ሰናያት ዘይቀርበካ ጸበሉ ካብ ኩሉ ሕማቅ ወረ ንሰምዖ ዕጣኑ ፈዋሲ ዝኮነ ኣቦና ጻድቁ ኣቡነ ተክለሃይማኖት ኣብ ገዳማይ ኢካ ትቅበር ዝበልዎ ዓቢ ገዳም እዩ እሞ ዘይሰምዑ ንገርዎ እቶም ዝሰማዕኩም ድማ ጽባሕ ናይ መወዳእታ እዩ ምዝገባ ቀልጢፍኩም ተመዝገቡ ዋጋ 170 በጺሕካ ምምላስ።