የባሕር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ለመካከለኛ አመራሮች ስልጠና ሰጠ
ታህሳስ 12 ቀን 2018 ዓ.ም፣ ISC/BiT]
በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የባሕር ዳር ቴክኖሎጅ ኢንስቲትዩት በተለዋዋጭ የአመራር ክህሎት እና ለስራ እና ለቡድን አመራር ዝግጁ መሆን "Adaptive Leadership Training and Ready for work and team leadership" በሚሉ ርእሰ ጉዳዮች ላይ ለሁለት ተከታታይ ቀናት በጃን ሞስኮቭ ቤተ መጽሀፍት አዳራሽ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡
ስለስልጠናው ሂደት ገለጻ ያደረጉት የባሕር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ምክትል ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ዶ/ር አማረ ካሳው እንደገለጹት ለሁለት ቀናት የተሰጠው ስልጠና የአመራሮችን አመለካከትና ክህሎት የሚያሳድግ ሲሆን ሰልጣኞችም ከስልጠናው በተጨማሪ በቅርቡ በዩኒቨርሲቲው በተካሄደው የሰራተኞች መዋቅራዊ ምደባ ምክንያት ከተለያዩ ግቢዎች ወደ ባሕር ዳር ቴክኖሎጅ ኢንስቲትዩት ግቢ የተመደቡ አመራሮች እርስ በእርስ እንዲተዋወቁና ልምድ እንዲለዋወጡ እድል የሚፈጥርና በቀጣይ ተግባብተውና ተናበው መስራት እንዲችሉ ማድረግ ያስችላል ብለዋል፡፡
ስልጠናውን ሁለት የዘርፉ ምሁራን የሰጡ ሲሆን "Adaptive Leadership Training workshop በሚል ርእስ ዶ/ር ሲሳይ ገረመው እንዲሁም ሁለተኛውን "Ready for work and team leadership" በሚል ርእሰ ጉዳይ አቶ የቻለ ስልጠናውን ሰጥተዋል፡፡
በስልጠና መርሀ ግብሩ ላይ የመዝጊያ ንግግር ያደረጉት የባሕር ዳር ቴክኖሎጅ ኢንስቲትዩት ማኔጅንግ ዳይሬክተር ዶ/ር በላይ ተፈራ እንደገለጹት ተቋሙ የከፍተኛ ትምህርት ተቋም እንደመሆኑ መጠን ተማሪዎች፤ መምህራንና የአስተዳደር ሰራተኞች በአጠቃላይ የአካዳሚክና የአስተዳደር ዘርፎች ተናበውና ተቀናጅተው በመስራት ውጤታማ ስራ ማስመዝገብ ይጠበቅባቸዋል ብለዋል፡፡
ስልጠናውን ያዘጋጀው የባሕር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት አጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማስፋፊያና ማረጋገጫ ጽ/ቤት ሲሆን በስልጠናው ስራ አስፈጻሚዎች፤ ዳይሬክተሮች፤ የአካዳሚክ ፕሮግራም ኦፊሰሮች እና ቡድን መሪዎች ተሳትፈዋል፡፡

❤2👍1