ሳሙና ማምረት የሚያስችል ስልጠና ለወሰዱ ወጣቶች የእውቅና ምስክር ወረቀት ተሰጠ
ታህሳስ 7/2018 ዓ.ም ባሕር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት፣ (ቢአይቲ-ቢዲዩ) በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የባሕር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ኬሚካልና ምግብ ምህንድስና ፋኩሊቲ ከፕላን ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ለተከታታይ 15 ቀናት ያሰለጠናቸውን ወጣቶች የስልጠናውን ውጤታማነት የሚገመግም የግማሽ ቀን አውደ ጥናት በማካሄድ ተባባሪ አካላት በተገኙበት የእውቅና የምስክር ወረቀት ሰጥቷል፡፡
በአውደ ጥናቱና በእውቅና አሰጣጥ ፕሮግራሙ ለተሳተፉ አካላት የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ምክትል ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ዶ/ር አማረ ካሰው እንደገለጹት ሰልጣኞች ከማምረት ባለፈ የገበያ ጥስስር በመፍጠር ለሌሎች ወጣቶችም ሰፊ የስራ እድል መፍጠር አለባችው ብለዋል፡፡
በአውደ ጥናቱና በእውቅና አሰጣጥ ፕሮግራሙ ለታደሙ አካላት ስልጠናውን አስመልክተው ማብራሪያ የሰጡት በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ኬሚካልና ምግብ ምህንድስና ፋኩሊቲ ዲን ፕሮፌሰር ሰሎሞን ወርቅነህ እንደገለጹት ፋኩሊቲው ከመጀመሪያ ድግሪ እስከ ሶስተኛ ድግሪ በርካታ ተማሪዎችን እያሰለጠነ እንደሚገኝ ተናግረው ከዚህ ጎን ለጎን አጫጭር ስልጠናዎችንም በመስጠት ወጣቶችን ወደ ስራ የማስገባት ስራ እየሰራን እንገኛለን ብለዋል፡፡
በአውደ ጥናቱ ለተሳተፉ አካለት መልክት ያሰተላለፉት የባሕር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ሳይንትፊክ ዳይሬክተር ዶ/ር ሙሉቀን ዘገየ እንደገለፁት የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከመማር ማስተማርና ከምርምር በተጨማሪ በማህበረሰብ ተሳትፎ ስራዎች ላይ የላቀ አስተዋፅኦ እያበረከተ እንደሚገኝ ገልጸው ለሰልጣኞችም ስልጠናውን ከመውሰድ ባለፈ ወደ ስራ ለመግባት ከገንዘብና ከመስሪያ ቦታ በተጨማሪ ከፍተኛ የራስ ተነሳሽነት ስለሚጠይቅ ሰለቸኝ ደከመኝ ሳትሉ ለሌሎች ወጣቶችም አርዓያነት ያለው ስራ እንዲሰሩ አደራ እላለሁ ብለዋል፡፡
በስልጠናውም አስራ አምስት ሴቶች እና አንድ ወንድ በድምሩ አስራ ስድስት ወጣቶች በደረቅና ፈሳሽ ሳሙና አመራረት ዙሪያ ስልጠናውን ወስደው ያጠናቀቁ ሲሆን በሰልጣኞች የተሰሩ ምርቶችም በተሳታፊዎች ተጎብኝተዋል፡፡
Information and Strategic Communication Directorate
• Facebook: https://www.facebook.com/bitpoly
• Telegram: https://t.me/bitpoly
• Website: https://bit.bdu.edu.et
• Twitter: https://twitter.com/BiT_BDU
• LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/bitpo

Facebook
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.