Bahir Dar Institute of Technology
3.18K subscribers
1.03K photos
2 videos
36 files
175 links
ይህ የቴሌግራም ቻናል የባህር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ኦፊሺያል ቻናል ሲሆን በዋናነት ለተቋሙ ተማሪዎች የሚሆኑ መልዕክቶች ይተላለፉበታል:: ቻናሉ ለሁሉም ተማሪዎች ተደራሽ እንዲሆን ቻናሉን ለሌሎች ተማሪዎች እንድታጋሩልን እየጠየቅን ለተቋሙ እንዲደርሰ የምትፈልጉትን ማንኛውም ጥያቄ ወይም አስተያየት በ @Contact_bit_bot ቦት ማድረስ የምችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
Download Telegram
📣 CALL FOR BiT STUDENTS!

🌟 English Language Training – ELIC-BiT 2025

The English Language Improvement Center (ELIC-BiT) is excited to announce a new round of English Language Training designed specifically for BiT students.
This training helps you improve your communication, academic writing, presentation, and critical thinking skills — essential tools for your academic and professional success.

🎯 Training Focus Areas

Academic Speaking & Presentation Skills
Internship & Final Year Project Writing
Professional Communication
Critical Thinking & Public Speaking

🗓 Registration Period:

📅 November 21 – 28, 2025

👉 Register Here:
🔗 https://forms.gle/hj7VuoUnLMoifuvy6

📍 Contact Information

📌 ELIC Office – Janmoscove Library, G+2
📧 Email: elic.bit@gmail.com
📞 Phone: 0969047065
📣 Join Telegram: https://gqr.sh/NyCE
7ኛው ዓለም አቀፍ የአይሲቲ ጉባዔ ተካሄደ
[November 22, 2025 Bahir Dar, ISC/BiT]
*********************************
(ህዳር 13/2018 ዓ.ም/ ባሕርዳር) 7ኛው ዓለም አቀፍ የአይሲቲ ጉባዔ የአይሲቲ እድገት ለአፍሪካ በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት አይሲቲ ምርምርና እድገት ማዕከል አዘጋጅነት በርካታ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ሀገራት ምሁራን እና ተመራማሪዎች በተገኙበት በጃንሞስኮቭ ቤተ መፃህፍት መሰብሰቢያ አዳራሽ ተካሄደ፡፡
የኮንፈረንሱን አጠቃላይ ይዘት ለተሳታፊዎች ያብራሩት የአይሲቲ 4ዳ ዳይሬክተር ዶ/ር እሱባለው አለምነህ በዚህ ዓመት 125 የምርምር ወረቀቶች ቀርበው በቅድመ ልየታ 90 ወረቀቶች ለገምጋሚዎች ተሰጥተዋል ብለዋል፡፡ ለዚህ ኮንፈረንስ ከተመረጡ 54 ወረቀቶች 47ቱ ተመዝግበው በገፅ ለገፅ እና በበይነ መረብ እንደሚቀርቡ ተናግረዋል፡፡

በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ መምህርን ተመራማሪ እንዲሁም የአይሲቲ 4D 2025 አዘጋጅ ኮሚቴ አባል የሆኑት ዶ/ር መሀመድ አበበ በበኩላቸው ኮንፈረንሱን ስናዘጋጅ የዲጂታል ቴክኖሎጂን ጥቅም በምርምር አስደግፈን ለተጠቃሚዎች ለማስተዋወቅ ነው ብለዋል፡፡የቴክኖሎጂ አጠቃቀማችን እንደ ኢትዮጵያ ብሎም እንደ አፍሪካ ብዙ ይቀረናል ያሉት ዶ/ር መሀመድ ከችግሩ ለመውጣት መሰል ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል አለባቸው ብለዋል፡፡አክለውም ዩኒቨርሲቲዎች ምርምሮችን በመስራትና በመምራት ፣መንግስት ፖሊሲዎችን በማውጣት ዲጂታል ቴክኖሎጂን ለተጠቃሚዎች የማድረስ ግደታዎችን መወጣት አለባቸው ብለዋል፡፡

7ኛው ዓለም አቀፍ የአይሲቲ ጉባዔ ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር መንገሻ አየነ ለተሳታፊዎች እንኳን ወደ ውቢቱ ባሕር ዳር በደህና መጣችሁ ካሉ በኋላ ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከ30000 በላይ ተማሪዎች፣ከ2000 በላይ የአካዳሚክ እና 5000 በላይ የአስተዳደር ሰራተኞችን ይዞ በ9 ካምፓሶች፣በ3 ትምህርት ቤቶች፣በ3 ኢንስቲትዩቶችና በአምስት ኮሌጆች ተደራጂቶ በርካታ የመማር ማስተማር፣የምርምር እና የማህበረሰብ አገልግሎት ዘርፍ ላይ እሰራ የሚገኝ ዩኒቨርሲቲ መሆኑን ጠቅሰው በዚህ ኮንፈረንስ ሚቀርቡ የምርምር ሃሳቦችም ዩኒቨርሲቲውን የምርምረ ዩኒቨርሲቲ የማድረግ ተልዕኮ አጋዥ ተደርገው ይወሰዳሉ ብለዋል፡፡አክለውም በሀገር አቀፍ ደረጃ ለተያዘው የዲጅታል ትራንስፎርሜሽን ስራ ተጨባጭ አስተዋፅኦ እያደረግን እንገኛን ብለዋል፡፡ሌሎች የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎችም የአይሲቲ 4D አካል እንዲሆኑ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ዶ/ር ምትኩ ዳምጤ ዩኒቨርሲቲዎች ከተሰጣቸው ተልዕኮዎች መካከል አንዱ የሆነው የምርምር ስራ በማዘጋጀት የምርምር ወረቀቶችን አቅርቦ እውቀትን ማጋራት ነው በማለት ከንፈረንሱ ከዚህ ባለፈ ጀማሪ ተመራማሪዎችና ተማሪዎች ከትልልቅ ፕሮፌሰሮች ልምድ የሚያገኙበት መድረክ ነው ብለዋል፡፡በተቋሙ በአይሲቲ 4D እና በአይካስት በአመት በትንሹ 100 ወረቀቶች እንደሚታተሙ ተናግረው የዚህ ኮንፈረንስ ዋና አላማም የምርምር ውቴቶችን ማጋራት፣መወያየትና አዲስ ሃሳብ ማመንጨት ነው ብለዋል፡፡
7ኛው ዓለም አቀፍ የአይሲቲ ጉባዔ ለሁለት ቀናት ያህል በበይነ መረብ እና በቡድን መድረኮች ሲካሄድ ቆይቶ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል፡፡
Information and Strategic Communication Directorate
Facebook፡- https://www.facebook.com/bitpoly
Telegram፡- https://t.me/bitpoly
Website፡- https://bit.bdu.edu.et
Twitter: - https://twitter.com/BiT_BDU
LinkedIn: -https://www.linkedin.com/company/bitpoly
1