ብርጭቆ [high school ] MEMES
693 subscribers
1.28K photos
72 videos
49 links
# Ethiopian [High school] life meme

በሁሉም ት/ቤት meme የሚሰራበት channel

Tik tok
Download Telegram
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታይ ኢትዮጵያውያን በሙሉ እንኳን ለ1443ኛው ኢድ አል - አደሀ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን። መልካም በዓል ይሁንላችሁ 🙏🌙
https://vm.tiktok.com/ZMNP6HTuy/?k=1
አዲስ አበባ ውስጥ 12 ለመማር ምርጥ የሆኑ ት /ቤቶች part 1
😂😂😊
ለቀጣይ አመት ምን ይሰራ??
Anonymous Poll
57%
Meme
58%
School videos on tik tok
እንኳን ደስ አላቹ ።
Forwarded from ETHIO-MEREJA®
የ2014 12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተናን በ12 ኮድ (በጥያቄ አቀማመጥ ስብጥር) ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ ነው።

የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ከዚህ በፊት እንደነበረው በ4 ኮድ (4 የተለያዩ ፈተናዎች/በጥያቄ አቀማመጥ) ሳይሆን እስከ 12 እንዲሆን እየተሰራ መሆኑን የትምህርት ሚኒስትር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ተናግረዋል።

ይህ የፈተና ኩረጃን ለመከላከል ከሚሰሩት ስራዎች መካከል አንዱ መሆኑን የሚገልፁት ፕ/ር ብርሃኑ ጎን ለጎን ያሉ ተማሪዎች እርስ በእርስ የሚፈተኑት ፈተና የጥያቄው(order) በፍፁም የተገናኘ እንዳይሆን እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል። ፈተናው በዩኒቨርሲቲዎችና በፌዴራል ተቋማት እንደሚሰጥም ገልፀዋል።

ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ለኢፕድ የሰጡት ቃል፦

"...የክልል ባለሟሎች፣ የክልል ኃላፊዎችን ከፈተና ጉዳይ ጋር እንለያቸው ፤ ፈተናው እራሱ የፌዴራል ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ስለሆነ በፌዴራል ተቋማት ውስጥ ብቻ እንስጥ ብለን አሁን በሙሉ ተማሪዎቹን አጓጉዘን ቢቻል ሁሉንም ከክልላቸው ውጭ በሆኑ ክልሎች ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች እና የፌዴራል ተቋማት ውስጥ ለመስጠት ነው እየተዘጋጀን ያለነው።

ያ የሚያደርገው ሁለት ነገር ነው። 1ደኛ በመንገድ ላይ ሊኖር የሚችለውን የመሰረቅ አደጋ ይቀንሰዋል። 2ተኛ ክፍል ውስጥ ከተገባ በኃላ ለመስረቅ የሚቻልበትን አደጋ ይቀንሰዋል።

ከዛም በላይ ፈተናዎቹን በማዘጋጀት ደረጃ በፊት በ4 የተለያዩ ፈተናዎች ነበር የምናዘጋጀው እስከ 12 አድርገን Completely scrambled እንዲሆኑና ማንም ጎኑ ያለው ተማሪ የሚፈተነው ፈተና አንተ ከምትፈተነው ፈተና order ጋር በፍፁም ያልተገናኘ እንዲሆን አድርገን እየሰራን ነው። ይሄ በጣም በብዙ ደረጃ የፈተና ስርቆትን ይቀንሰዋል ብለን ነው ተስፋ የምናደርገው" ብለዋል።
T.me/ethio_mereja
@ethio_mereja