Biranna Tech ብራና ቴክ
14.7K subscribers
639 photos
5 videos
123 files
415 links
ወደ ብራና Apps እንኳን በደህና መጡ። ታላላቅ መጻሕፍትን የያዙ አፕሊኬሽኖችን ያውርዱ ይግዙ ።

ውይይቶችን ፣ ጥያቄዎችን ፣ ማብራሪያዎችን ከፈለጉ ወደ ግሩፓችን ይቀላቀሉን ።

ወደ ሽያጭ ቻናላችን ይቀላቀሉ ። @birannasales


Website: https://biranna.com
Email: support@biranna.com
Phone: +251901008562
Download Telegram
ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን ። ከዚህ በፊት በገባነው ቃል መሠረት የአዲሱ አፕሊኬሽናችን የመጀመሪያ ዕትም (ንድፍ) በዚህ ሣምንት እንደለሚለቀቅ አሳውቀናችሁ ነበር ። አፕሊኬሽኑን በዚህ ሣምንት ለሙከራ ለብራና አፕስ ደንበኞች የምንለቅ መሆኑን እያረጋገጥን፣ ለመተግበርያው ስያሜ በመስጠት ተባበሩን ።

#ለስያሜው_እንዲጠቅማችሁ መተግበርያው በየዕለቱ የሚነበቡ
1. የግጻዌ ምንባባትን (የነግህ ፣ የቅዳሴ እና የሠርክ)
2. ስንክሳር
3. ጸሎቶች
4. ገድላት
5. የዜማ ክፍሎች
6. ባሕረ ሐሳብ
7. ቀን መቁጠርያ
8. መጽሐፍ ቅዱስ
9. ትምህርቶች
10. ሌሎችንም የያዘ ነው ።


ይህንን ለመወከል የሚችል ስያሜ ይስጡን ።
ስያሜው ቢበዛ ከሁለት ቃል ባይበልጥ ይመረጣል ።

እግዚአብሔር ለፍጻሜ ያብቃን ።
30👍10
ከወንድማችን ዲ/ን መንግሥቱ ልነሳና ደስ የሚሉ ስያሜዎች ናቸው። ቀጥሉበት ።

በአፕሊኬሽን ስታንዳርድ መሠረት
ስያሜው ቢሆን አንድ ቃል፣ ቢበዛ ከሁለት ቃላት ባይበልጥ ይመረጣል ።


ሀ. መራሔ አምልኮ ዘኦርቶዶክስ
ለ. ፍኖተ አምልኮ ዘኦርቶዶክስ
ሐ. ሥርዐተ አምልኮ ዘኦርቶዶክስ
መ. ሲሳይ ዘለለዕለት /የየዕለት እንጀራ

ሠ. ኅብስተ ሠርክ /የዘወትር ምግብ
ረ. መራሔ ሕይወት
ሰ. መጽሔተ አምልኮ /መጽሔተ ኦርቶዶክስ
15👍4
እስካሁን ከተሰጡን ስያሜዎች የተሻሉትን ዘርዝረናል ። ድምጽ ስጡበት ። አንድ ሰው ከአንድ ምርጫ በላይ መምረጥ አይችልም።

የአፕሊኬሽኑን ዓላማ ከግምት ውስጥ በማስገባት ድምፅ ይስጡን።
Final Results
28%
ፍኖተ ተዋሕዶ/ብርሃን/አምልኮ
20%
መራሔ ፍኖት/ጽድቅ/ሕይወት
7%
ኆኅተ ምሥጢር/ሰማይ
13%
ስምዓ ተዋሕዶ
16%
ኅብስተ ሕይወት
17%
ግጻዌ + (ግጻዌ plus)
👍17🥰1
የድምጽ አሰጣጥ ሂደቱ ተጠናቋል ። 28% በማግኘት ፍኖተ ተዋሕዶ ቀዳሚ ሆኗል ። የተለየ ሐሳብ ያለው ሰው አለ?
👍13👏2
#ይቅርታ_ስመጠየቅ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችሁ ጋር ይሁን። ከቀናት በፊት በገባነው ቃል መሠረት አዲሱን አፕሊኬሽን ባለፈው ሣምንት ለመልቀቅ ቃል ገብተን ነበር።

ነገር ግን ባጋጠመን ጊዜያዊ ችግር ወቅቱን ጠብቀን ባለማቅረባችን በእግዚአብሔር ስም ይቅርታ እንጠይቃለን። ሰው ነንና ብዙ ሥጋዊ ሩጫዎችና ፈተናዎች አሉብን። በዚያ ምክንያት በቃላችን አልተገኘንም። በዚህ ሣምንት ወይም በሚቀጥሉት ሦስት አራት ቀናት ይለቀቃል።

እግዚአብሔር ለፍጻሜ ያብቃን።
🥰31👍1714
ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን ።

በገባነው ቃል መሠረት የመጀመሪያው #ግጻዌ+ የሙከራ መተግበርያ እነሆ ።

አፕሊኬሽኑ #በአራት ቋንቋዎች እንዲሠራ ተደርጎ የተዘጋጀ ነው ። መተግበርያው ለሙከራ አገልግሎት (Testing) የተዘጋጀ በመሆኑ ያልተጠናቀቁ ፣ ያልተሟሉና የሌሉ አገልግሎቶች አሉ።

#አጠቃቀም

1. ግጻዌ፤ በተውሳክና በዘወትር (በዘወትር ፣ በሰንበታት ፣ በዓቢይ ጾም ፣ በሕማማት) የተከፈለ ነው ። አፑ ቀኑን አስልቶ የመወሰን የራሱ ብቃት አለው ።

2. ስንክሳር፣ ሙሉ የስንክሳር መጽሐፍ፣ በወራትና በዓመታት የሚታሰቡ ተጨማሪ ዝርዝሮች ተካተዋል ።

3. የጸሎት ክፍሎች ፤ ለዕለቱ የሚያስፈልጉ ጸሎቶች ተውጣጥተው ተቀምጠዋል ።

4. ገድላት ወድርሳናት ፤ (ለጊዜው አገልግሎቱን ለማሳየት የስንክሳር ክፍሎችን ነው የተጠቀምነው )

4. የዜማ ክፍሎች ፣ መዝሙሮች (የሰንበታት) እና አቋቋሞች ለጊዜው አልተካተቱም ። በጣም ሰፊ ዝግጅትና የሊቃውንቱ አስተያየትና ምክር ስለሚፈልጉ ሲጠናቀቅ ብቻ ነው የሚካተተው ።

5. ባሕረ ሐሳብ ፣ የዘመን መቁጠርያ፣ ቀን መቀየርያ መሠረታዊ የቤተ ክርስቲያኗን ቀመሮች አካተዋል ።

6. መጽሐፍ ቅዱስ፤ (ለግጻዌውም ለብቻውም)።

ከላይ የገለጽናቸው አገልግሎቶች በሙሉ (ከዜማዎች ውጪ) በአራቱም ቋንቋዎች (በአማርኛ ፣ ኦሮምኛ ፣ ትግርኛና እንግሊዝኛ) የተዘጋጁ ናቸው ።


#የሚቀያየሩ_ካርዶች (ቀን ወይም ሰዓት ሲቀይሩ)
1. በዕለቱ የሚታሰቡ ቅዱሳን (ከግጻዌው የተውጣጡ)
2. የሣምንቱ ስያሜ በመዝሙሩ መሠረት (ቀኑ እሑድ ሲሆን ብቻ የሚታይ)
3. የምንገኝበት የጸሎት ሰዓት (በሰዓቱ መሠረት የሚቀያየር)
4. የምንገኝበት የጾም ወቅት
5. የምንገኝበት ዘመን


#አስተያየት_እንድትሰጡባቸው_የሚፈለጉ_ነገሮች
1. ዲዛይን (ቀለም ፣ User interface, )
2. ይዘት (ሊካተቱና ሊወገዱ የሚገባቸው ይዘቶች)


#አማራጮች (ማስተካከያዎች)
1. የቋንቋ ምርጫ
2. የፊደል መጠን ፣ ዓይነት ምርጫ
3. የግእዝ ቁጥር ማብርያና ማጥፊያ
4. በጨለማና በቀን ማንበብያ ገጽታ


#የአፑ_ደካማ_ጎን
1. የመተግበርያው መጠን ከፍ ማለት (162 MB)
2. ገና ያልተጠናቀቀ መሆኑ

#ማሳሰቢያ
የግጻዌው ክፍል ውስጥ የተካተቱ ማውጫዎች በላይ ቤቱ በታች ቤቱ የተወሰነ ልዩነት ስላላቸው በቀጣይ ለያይተን በግልጽ እናስቀምጣቸዋለን ።

ግጻዌው ላይ ዕለቱ #እሑድ ሲሆን የሰንበታት ምንባባት ፣ #ዓቢይ_ጾም ሲሆን የዓቢይ ጾም ምንባባት ፣ #ሕማማት ሲሆን የሕማማት ምንባባት ናቸው የሚታዩት ። #የዘወትሩን ግጻዌ ዕለቱ ከእነዚህ ቀናት ውጪ ከሆነ ብቻ ነው የሚያገኙት ።

የመተግበርያውን አገልግሎት ቀኑን ፣ ወሩን ፣ ዓመተ ምሕረቱን እየቀያየሩ መሞከር ይችላሉ ። በመጀመርያው ገጽ ላይ በቀይ ያከበብኩባት ምልክት ቀን ሲመርጡ የተለያዩ ቀናትን ወይም ዘመናትን መርጠው ከሆነ #ቀኑን_ወደ_ዛሬ ማስተካከያ ናት ።

ወደ አፕሊኬሽኑ ለመግባት በመመዝገቢያ ስክሪኑ ላይ የተቀመጡትን Email እና Password ይጠቀሙ ። በራስዎ መመዝገብ አይችሉም (ሙከራ በመሆኑ)
👍13🙏64🔥1
👍124
GitsaweV1.apk
161.6 MB
ወደ አፑ ለመግባት የሚከተሉትን ይጠቀሙ ።

Email: gitsawe@g.com
Password: 123456

ከዚህ ጋር በተያያዘ ብዙ ሰው በውስጥ መስመር እየጻፈ ነው ።

ተጨማሪ መረጃ https://t.me/biranapps/1127
19👍9🔥6
#ማሳሰቢያ

አፑን እየሞከራችሁ የሚከተሉትን ትጠቁሙናላችሁ ።
1. አሁን በአፑ ከተካተቱ ይዘቶች በተጨማሪ ምን ይካተት
2. የሚስተካከሉ ነገሮች
3. ግራፊክስ ዲዛይን ጥቆማዎች (ለግራፊክስ ዲዛይነሮች)
4. የትርጉም ሥራ ላይ የምታግዙን ብዙ ወንድሞች ትኖራላችሁ ። በተለይ ትግርኛና አፋን ኦሮሞ ።
5. ተጨማሪ የቋንቋ አማራጮች (መጻሕፍትና ጽሑፎች መኖር አለባቸው)

ከተሳኩ በእኛ የታሰቡትን እናስታውሳችሁ (አንዳንዶቹ ከፍተኛ ወጪና አቅም ያለው VPS server ይፈልጋሉ። ወጪውን አስቡበት😲)

1. የመጽሐፍ ቅዱስ የንባብ ዕቅዶችና ጥናቶች
2. መንፈሳዊ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው (ውድድሮች)
3. የክርስትና ምግባራትን መመዘኛ (የራስን የየዕለት መንፈሳዊ ተግባራት መከታተያ)
4. በሰፊው ትምህርቶችን (Audio, video… live streaming እና ጽሑፍ)


እናንተ ቢሆን ብላችሁ የምታስቡትን ሁሉ ጠቁሙን
👏2012👍12
#ለጠየቃችሁን

አዲሱ አፕሊኬሽን (ግጻዌ +) ሲለቀቅ በነጻ የሚሰጠው ለገደብ አልባ ደንበኞች ብቻ ነው ።

ከዚህ በፊት በገባነው ቃል መሠረት ፣ ብራና አፕስ በየትኛውም ጊዜ አዘጋጅቶ የሚለቃቸውን #ነባርም ይሁን #አዳዲስ_አፕሊኬሽኖች ለገደብ አልባ ደንበኞች በነጻ ለመስጠት ቃል መግባቱ ይታወሳል ።
🙏3214👍7👏7
ብራና አፕስ #10ኛ ዓመት የምሥረታ በዓሉን መጋቢት 10፣ 2017 ዓ.ም ያከብራል። ይህንን ምክንያት በማድረግ #ከጥር 24፣ 2017 እስከ #ሚያዝያ 12፣ 2017 (በዓለ ትንሣኤ) ድረስ በሁሉም አፕሊኬሽኖቻችን ላይ #የ50%፣ በገደብ አልባ ጥቅል አገልግሎት ላይ ደግሞ #የ20% ቅናሽ ማድረጋችንን በደስታ እናሳውቃለን ።

የአፖቹ ዋጋ #በ50% ቅናሽ
1.መዝገበ ሃይማኖት =300 ብር
2 .አንድምታ ትርጓሜ: =200 ብር
3 .መዝገበ ሃይማኖት ብግእዝን ትግርኛን =100 ብር
4 .Galmee Amnataa =50 ብር
5 .መዝገበ ጸሎት =50 ብር
6 .መዝገበ ጸሎት ብግእዝን ትግርኛን =50 ብር
7 .መጽሐፍ ቅዱስ ፹፩ = 100 ብር
8 .መጽሐፍ ቅዱስ ብግእዝን ትግርኛን =50 ብር
9 .ጸዋትወ ዜማ =50 ብር
10 .አብነት ዘኦርቶዶክስ =25 ብር
11 .መጽሐፈ ስንክሳር =50 ብር
12 .መጽሐፈ ቅዳሴ =20 ብር
13 .ግእዝ ትግርኛ መጽሐፈ ቅዳሴ =25 ብር
14 .መዓዛ ቅዱሳን =150 ብር
15.መጽሐፈ ሰዓታት =25 ብር
16.ግብረ ሕማማት =50 ብር
17.Utubaa Amantaa =25 ብር
18.መልክዐ ጉባኤ =75 ብር
19.ማኅሌተ ጽጌ ወሰቆቃወ ድንግል =25 ብር
20.ግእዝ አማርኛ መዝገበ ቃላት =25 ብር
21.አማርኛ በአማርኛ መዝገበ ቃላት =25 ብር
22.ትግርኛ አማርኛ መዝገበ ቃላት =25 ብር
23.ሃይማኖተ አበው =25 ብር
ለማውረድ
Https://t.me/biranappsapk
ወይም
https://biranapps.com

ሁሉንም አፖች በአንድ ኮድ ያለገደብ መጠቀም ከፈለጉ የፕሪሚየም ጥቅል ተጠቃሚ በመሆን #በ20% ቅናሽ #በ800 ብር ብቻ የጥቅሉ ተጠቃሚ መሆን ይችላሉ ።

ለማውረድ
እዚህ ይጫኑ ወይም እዚህ ይጫኑ

ለተጨማሪ ለመረጃ
+251901008562
👍104
ዐቢይ ጾም

ዐቢይ ጾም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶሰ ከተጠመቀ በኋላ ዐርባ ቀን የጾመው፤ እኛም እንድንጾማቸው በቤተ ክርስቲያናችን ከታዘዝናቸው ሰባቱ የአዋጅ አጽዋማት አንዱ ነው፡፡ ምእመናን ጌታችን ያደረገውን ምሳሌ ተከትለን ጾሙን በየዓመቱ እንጾመዋለን፡፡ ዐቢይ ጾም ስምንት ሳምንታት (፶፭ ቀኖች) አሉት፡፡ በውስጡ ስምንት ቅዳሜዎች፣ ሰባት እሑዶች ይገኛሉ፡፡ ይኸውም ዐሥራ አምስት ቀን ማለት ነው፡፡ እነዚህ ቀናት ከጥሉላት እንጂ ከእህል ውኃ ስለማይጦሙ የጦሙ ወራት ዐርባ ቀን ብቻ ይሆናል፡፡ ጾሙ በተለያዩ ስሞች ይጠራል፤ አንደኛ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከተጠመቀ በኋላ የጾመው በመሆኑ፣ እንደዚሁም ‹‹ዐቢይ እግዚአብሔር ወዐቢይ ኀይሉ ዐቢይ እግዚአብሔር ወብዙኅ አኰቴቱ›› /መዝ.፵፯፥፩፤ መዝ.፻፵፮፥፭/ የተባለ ጌታችን የጾመው ጾም ስለሆነ ‹‹ዐቢይ ጾም›› ይባላል፡፡ ሁለተኛ ‹‹ሁዳዴ ጾም›› ይባላል፡፡ ይህም የመንግሥት እርሻ ወይም ማንኛውም የሕዝብ ብዛት ያለበት ሥራ ሁዳድ ስለሚባል ሲሆን፣ ዐቢይ ጾምም ከአጽዋማት ሁሉ ብዙ ቀናት ስለሚጾምና ኃያሉ አምላካችን ስለጾመው ነው /አሞ.፯፥፩/፡፡ ሦስተኛ ‹‹በአተ ጾም›› ይባላል፡፡ የጾም መግቢያ፣ መባቻ ማለት ነው፡፡ አራተኛ ‹‹ጾመ ዐርባ›› ይባላል፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የጾመው ፵ ቀን ስለሆነ /ማቴ.፬፥፩/፡፡ አምስተኛ ‹‹ጾመ ኢየሱስ›› ይባላል፡፡ ጌታችን እርሱ ጾሞ፣ ጹሙ ብሎ ስላዘዘን፡፡ ስድስተኛ ‹‹ጾመ ሙሴ›› ይባላል፡፡ ቅዱስ ያሬድ በዘወረደ ጾመ ድጓው ‹‹ከመዝ ይቤ ሙሴ እስመ ለዓለም ሙሴኒ ይቤ በውስተ ኦሪት›› እያለ ስለዘመረ /የሰኞ ዕዝል/፡፡

‹‹ዘወረደ (ዘመነ አዳም)››
ከዐቢይ ጾም ሳምንታት መካከል የመጀመሪያው ሳምንት ‹‹ዘወረደ (ዘመነ አዳም)›› ይባላል፡፡ ዘወረደ ማለት ከላይ የመጣ፣ የወረደ ማለት ነው፡፡ ይህም አምላካችን አዳምንና ልጆቹን ከሞት ለማዳን ሲል ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው መሆኑንና የፈጸመውን የማዳን ሥራ ያመለክታል፡፡ ‹‹ከሰማይ ከወረደው በቀር ወደሰማይ የወጣ የለም›› ካለው ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ቃል በመነሣት ሊቁ ቅዱስ ያሬድ ‹‹ዘወረደ እምላዕሉ አይሁድ ሰቀሉ ወሚመ ኢያእመሩ እግዚአ ኵሉ ዘየሐዩ በቃሉ›› በማለት በጾመ ድጓው መጀመሪያ ላይ ይህን ዕለት ገልጾታል፡፡ ትርጕሙም ‹‹አዳምን ለማዳን ከሰማይ የወረደውን አምላክ አይሁድ ሰቀሉት፤ የሰማይ ሥልጣን ያለው የዅሉ ጌታ እንደሆነም ምንም አላወቁም›› ማለት ነው፡፡ ይህም ድርሰት በቤተ ክርስቲያናችን የጾም መጀመሪያ የሆነው ዕለተ ሰንበት ዋዜማ፣ መግቢያ (መሐትው) ሆኖ ከዋዜማ በፊት ምንጊዜም በየዓመቱ ይቆማል፤ ይዘመራል፤ ይመሰገናል፡፡
በዚህ ሳምንት በተለይም እሑድና ሰኞ የሚነገሩት ውዳሴያት ከመጻሕፍተ ኦሪትና ነቢያት የተወሰዱ ናቸው፡፡ ሁለተኛም ሳምንቱ ‹‹ሙሴኒ›› በመባል ይታወቃል፡፡ እግዚአብሔር አምላክ አዳምን ለማዳን ከሰማይ መውረዱንና በመስቀል መሰቀሉን ስለሚያወሳ ነው፡፡ በተጨማሪም ይህ የመጀመሪያው ሳምንት ‹‹ጾመ ሕርቃል›› ይባላል፡፡ ሕርቃል (ኤራቅሊየስ) የቤዛንታይን ንጉሥ ነበር፡፡ ይህ ሳምንት በስሙ የተጠራበት ምክንያት በዘመኑ ፋርሶች ኢየሩሳሌምን ወርረው፣ የጌታችንን መስቀል ማርከው ወስደውት ነበር፡፡ እርሱ ወደ ፋርስ ዘምቶ መስቀሉን ከእነርሱ ነጥቆ ይዞ ወደ ኢየሩሳሌም ተመልሷል፡፡

ሕርቃል ከፋርሶች ጋር ከመዋጋቱ በፊት ሐዋርያት በሲኖዶሳቸው ‹‹ነፍስ የገደለ ሰው እስከ ዕድሜ ልኩ ይጹም›› ብለው ሥርዓት ሠርተዋልና ጾሙን ፈርቶ ስለነበር በኢየሩሳሌም የነበሩ ምእመናን አሳቡን ደግፈው ‹‹አንተ ጠላታችንን አጥፋልን፤ መስቀሉን አስመልስልን እንጂ የአንድ ሰው ዕድሜ ቢበዛ ሰባ፣ ሰማንያ ዓመት ነው፡፡ ጾሙን አምስት አምስት ቀን ተከፋፍለን እኛ እንጾምልሃለን›› ብለው ጾመውለታል፡፡ ይህንን መሠረት በማድረግ ያላወቁት አንድ ጊዜ ጾመው ትተውታል፡፡ ያወቁት ግን ቀድሞም ሐዋርያት ጾመውታል ብለው ሥርዓት አድርገው በዓመት በዐቢይ ጾም መጀመሪያ ላይ ጾመ ሕርቃል እያሉ የሚጾሙት ሆነዋል፡፡ ቤተ ክርስቲያናችን ይህንን ሥርዓት መሠረት በማድረግ ከጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጾም የመጀመሪያውን ሳምንት ጾመ ሕርቃል በሚል ስም ሰይማ እንዲጾም አድርጋለች (ስንክሳር ዘመጋቢት ፲ ቀን)፡፡
በቅዱስ ያሬድ ጾመ ድጓ ዘወረደ እየተባለ የሚታወቀው፣ በጾመ ዐርባው ወቅት በተለይም በመጀመሪያው ሳምንት የሚገኘው ድርሰት በነግህ በሠለስት፣ በቀትርና በሠርክ እንደዚሁም ቅዳሜና እሑድ በሌሊት የሚዘመር ነው፡፡ በውስጡም የያዘው ፍሬ ሐሳብ የጾምን፣ የጸሎትን፣ የምጽዋትንና የፍቅርን ጠቃሚነት አጕልቶ የሚያስተምር ነው፡፡ ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በዘወረደ ጾመ ድጓው ‹‹አዘዞ እግዚአብሔር ለሙሴ ወይቤሎ ሰብእከ ወላህምከ ወኵሉ ቤትከ ያዕርፉ በሰንበት፤ እግዚአብሔር ሙሴን ሕዝብህ የከብትህ መንጋህ ቤተሰብህ ሁሉ በሰንበት ቀን ከድካማቸው ይረፉ በማለት አዘዘው፤›› በማለት ሰንበት ለሰው ልጆች ብቻ ሳይሆን፣ ሕይወት ላለው ነገር ሁሉ ጸጥታና ሰላም የሰፈነባት የዕረፍት ቀን ስለመሆኗ ተናግሯል /ዘፀ.፳፥፲፤ ፳፫፥፲፪/፡፡ በዚህም ወቅቱ ‹‹ዘመነ ጾም›› ወይም ‹‹ጾመ ሙሴ›› ይባላል፡፡

ጾምን መጾም የፈቃድ ብቻ ሳይሆን የትእዛዝም ነው፡፡ ነቢዩ ኢዩኤል ‹‹ቀድሱ ጾመ ወስብኩ ምሕላ…፤ ጾምን ያዙ፤ አጽኑ፡፡ ምሕላንም ዐውጁ፡፡ ሸማግሌዎቹን ከፈጣሪያችን ቤት ሰብስባችሁ በአንድነት ሆናችሁ ወደ እግዚአብሔር ጩኹ(ለምኑ)፤›› ብሏል /ኢዩ.፩፥፲፩፤ ፪፥፲፪፤ ፲፪፥፲፭-፲፮/፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም ‹‹ወኩኑ ላእካነ ለእግዚአብሔር በጾም ወበንጽሕ፤ በጾም፣ በንጽሕና ተወስናችሁ እግዚአብሔርን አገልግሉ፤›› ብሏል /፪ቆሮ.፮፥፬-፮/፡፡

ጾም ባያስፈልግ ኖሮ ጌታችን ‹‹በምትጾሙበት ጊዜ እንደ ግብዞች አትኹኑ … ስለ ጽድቅ የሚራቡ የሚጠሙ ንዑዳን ክብራን ናቸው፤›› ባላለም ነበር /ማቴ.፭፥፮-፲፮/፡፡ ነቢዩ ዳዊትም ‹‹ጕልበቶቼ በጾም ደከሙ፤ ሥጋዬም ቅባት በማጣት ከሳ፤›› /መዝ.፻፰፥፳፬/ ማለቱ የጾምን አስፈላጊነት ያስረዳል /ዳን. ፱፥፫-፬፤ ፲፬፥፭/፡፡ በቁራኝነት አብሮ የሚኖር መንፈስ ርኩስ (ሰይጣን) እንኳን በጾም የሚወገድ መሆኑን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተናግሮአል /ማቴ.፲፯፥፳፩፤ ማር.፱፥፪/፡፡
ቅዱሳን ሐዋርያት ‹‹ሙሽራውን ከእነሱ ለይተው የሚወስዱበት ጊዜ ይመጣል፡፡ ያን ጊዜ ይጾማሉ፤›› ያለውን የጌታን ቃል መሠረት በማድረግ ጌታችን ሞቶ ከተነሣ እና ካረገ በኋላ ጾመዋል፤ የጾምንም ሕግ ሠርተዋል /ሐዋ.፲፫፥፫/፡፡ ሠለስቱ ምዕትም ‹‹ሐዋርያት የጾሙትንና እንዲጾም የወሰኑትን መጾም ይገባል›› ብለው አጽዋማትን እንድንጾም መወሰናቸው ይህን የጌታችንን ቃል መሠረት በማድረግ ነው፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ሠራዔ ሕግ እንደመሆኑ ዐርባ ቀን ዐርባ ሌሊት ጾሞ እንጂ ዝም ብሎ ጾሙ አላለንም፡፡ ስለዚህ ጾም ትእዛዝ (ሕግ) መሆኑን ተገንዝበን ሁላችንም መጾም አለብን፡፡ ጾመን ለማበርከት ያብቃን!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
© Mahibere Kidusan

የብራና አፕስ ትክክለኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾች
Website | Telegram | Facebook | Tiktok | Twitter | Whatsapp | Instagram
25👍20
#ጥቆማ
ቅናሹ ግልፅ ላልሆነላችሁ

ብራና አፕስ #10ኛ ዓመት የምስረታ በዓላችንን  ምክኒያት በማድረግ እስከ #ትንሳኤ ድረስ የሚቆይ 50% ቅናሽ በሁሉም አፖች ላይ 20% ቅናሽ ደግሞ በፕሪሚየም ፓኬጅ ላይ ማድረጋችን ይታወሳል ።

ይሁን እንጂ አንዳንድ ተጠቃሚዎች ቅናሹ አልተደረገም አፖቹ ላይ ከዚህ በፊት የነበረው መደበኛ ዋጋ ነው ያለው በማለት ይጠይቃሉ ።

እንደሚታወቀው የትኛውንም ቅናሽ በምናደርግበት ግዜ አፕሊኬሽኖች ላይ ያለውን መደበኛ ዋጋ አንቀይረውም ነገር ግን ቅናሽ አልተደረገም ማለት አይደለም ።

ቅናሽ ባደረግን ቁጥር ዋጋውን በየጊዜው አፕዴት ማድረግ ከባድ ስለሚሆንብን አፖቹን መግዛት የፈለገ ተጠቃሚ ማስታወቂያ ላይ ባስቀመጥነው ዋጋ በ50% ቅናሽ መግዛት ይችላል።

ተጠቃሚው የቅናሹ ተጠቃሚ ለመሆን ክፍያ በሚፈፅምበት ግዜ አፖች ላይ #በተፃፈው_ዋጋ_ሳይሆን_ማስታወቂያ #ላይ_ባስቀመጥነው_ዋጋ_ይሆናል

የአፕሊኬሽኖች ዋጋ በ50% ቅናሽ
1.መዝገበ ሃይማኖት =300 ብር
2 .አንድምታ ትርጓሜ: =200 ብር
3 .መዝገበ ሃይማኖት ብግእዝን ትግርኛን =100 ብር
4 .Galmee Amnataa =50 ብር
5 .መዝገበ ጸሎት =50 ብር
6 .መዝገበ ጸሎት ብግእዝን ትግርኛን =50 ብር
7 .መጽሐፍ ቅዱስ ፹፩ = 100 ብር
8 .መጽሐፍ ቅዱስ ብግእዝን ትግርኛን =50 ብር
9 .ጸዋትወ ዜማ =50 ብር
10 .አብነት ዘኦርቶዶክስ =25 ብር
11 .መጽሐፈ ስንክሳር =50 ብር
12 .መጽሐፈ ቅዳሴ =20 ብር
13 .ግእዝ ትግርኛ መጽሐፈ ቅዳሴ =25 ብር
14 .መዓዛ ቅዱሳን =150 ብር
15.መጽሐፈ ሰዓታት =25 ብር
16.ግብረ ሕማማት =50 ብር
17.Utubaa Amantaa =25 ብር
18.መልክዐ ጉባኤ =75 ብር
19.ማኅሌተ ጽጌ ወሰቆቃወ ድንግል =25 ብር
20.ግእዝ አማርኛ መዝገበ ቃላት =25 ብር
21.አማርኛ በአማርኛ መዝገበ ቃላት =25 ብር
22.ትግርኛ አማርኛ መዝገበ ቃላት =25 ብር
23.ሃይማኖተ አበው =25 ብር

ለማውረድ እዚህ ይጫኑ ወይም እዚህ ይጫኑ

#ልብ_ይበሉ
ቅናሹን ተጠቅመው ክፍያ ሲፈፅሙ አፖቹ ላይ ከተፃፈው ዋጋ በግማሽ ቀንሰው ይሆናል ።


ከላይ የዘረዘርናቸውን ሁሉንም አፖች ያለገደብ በአንድ ኮድ ለመጠቀም ከፈለጉ ደግሞ የፕሪሚየም ጥቅል ተጠቃሚ በመሆን በ800 ብር ሁሉንም አፕሊኬሽኖች ያለገደብ መጠቀም ይችላሉ ።

ለማውረድ እዚህ ይጫኑ ወይም እዚህ ይጫኑ

ለፕሪሚየም ጥቅል ተጠቃሚ ደግሞ አፑ ላይ ያለው መደበኛ ዋጋ 1000 ብር ሲሆን ክፍያ ሲፈፅሙ ግን 20% ቀንሰው 800 ብር ይሆናል ።

ለተጨማሪ መረጃ +251901008562

ብራና አፕስ
የብራና አፕስ ትክክለኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾች
Website | Telegram | Facebook | Tiktok | Twitter | Whatsapp | Instagram
👍124😱1
ይቅርታ መጠየቅን ይመለከታል።

ብራና አፕስ በመጽሐፈ ቀሌምንጦስ 3:29 "ሕዝቡ በሴት ሞት ምክንያት አርባ ቀን አለቀሰ። ሴት ከሞተ በኋላ ኄኖስ ሕዝቦቹን በቅንና በእውነት መራቸው። " የሚለው ላይ በTyping በተፈጠረ ስሕተት ጸያፍ ቃል ገብቶ ብዙዎችን አስቆጥቷል። ችግሩ የተፈጠረው በSpelling correction አፕሊኬሽን ምክንያት እንጂ ታስቦበት ያልተፈጠረ መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን። ግደፈቱ የተከሰተው #በመዝገበ_ሕይወት#በመዝገበ_ሃይማኖት እና #በመጽሐፍ_ቅዱስ_ሰማንያ_አሐዱ ላይ ሲሆን እነዚህን #ሦስት_መተግበርያዎች አስተካክለን እንደገና ለቀናቸዋል።

ችግሩ በምንም ይከሰት በምን አርሞ ማቅረብ የእኛ ድርሻ ቢሆንም ይህንን ኃላፊነት በአግባቡ ባለመወጣት ለፈጠርነው ግድፈት በእግዚአብሔር ስም ይቅርታ እንጠይቃለን። ይህ ችግር በድጋሚ እንዳይደገምና በአፕሊኬሽኖቻችን ላይ ለሚታዩ ሰፊ የቃላት ግድፈት ሥራውን የሚያግዙን ሊቃውንት በመጋበዝ እርማቶችን የምናደርግ መሆኑን በዚሁ አጋጣሚ ለማሳወቅ እንወዳለን።

ግድፈቶችን ለምትጠቁሙን ደንበኞቻችንም ምስጋናችንን እግዚአብሔር ስም እናቀርባለን።


ብራና አፕስ Birana Apps
የብራና አፕስ ትክክለኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾች
Website | Telegram | Facebook | Tiktok | Twitter | Whatsapp | Instagram


አፖቹን ለማውረድ የሚከተለውን ሊንክ ይጠቀሙ

መደበኛ ደንበኞች https://t.me/biranappsapk

ገደብ አልባ ደንበኞች
https://t.me/biranapremium
👍1310🙏4
በጎ ፈቃደኛ ይፈለጋል ።

1ኛ. ግጻዌ በገብረ ሥላሴ ብርሃኑ የተዘጋጀውን የዘወትር የነግህና የቅዳሴ ምንባባትን ምዕራፍና ቁጥር በአረብኛ ቁጥሮች በእጅ መጻፍ (ለምሳሌ መዝ ፳፬᎓፬-፭፣ ማቴ ፬፡፯-፲፬ የመሳሰሉትን ወደ Mez 24:4-5, Mat 4:7-14 መቀየር) ። ጥሩ የእጅ ጽሑፍ ያለው ቢሆን ይመረጣል ።


2ኛ. በአርትዖት ሥራ የሚታወቁና ሊያግዙን የሚችሉ ሊቃውንትን መጠቆም ።
👍3314👏5
ገደብ አልባ ደንበኝነትን(Premium Membership) እናበረታታለን።

የምንለቃቸውን አዳዲስ መተግበርያዎችና ይዘቶችን ለማግኘት በተናጠል ለእያንዳንዱ አፕሊኬሽን update ከማዘጋጀት አፖችን ሰብሰብ አድርገን በተወሰኑ አፖች ብቻ ለመቀጠል እያሰብን ነው ። ይህም ሥራዎችን ከማቅለሉም በላይ ድግግሞሽን ያስቀራል ። ተጠቃሚውም ያለሐሳብ አንዴ ከፍሎ ለዕድሜ ልክ ያለ ገደብ መጠቀም እንዲችል ይረዳል ።

በዚህ መሠረት በቅርቡ ከሚለቀቁ መተግበርያዎች ውስጥ #መጽሐፍ_ቅዱስ_፹፩ አንዱ ሲሆን ከወትሮው በተለየ መልኩ ነባሩን አገልግሎት ጨምሮ #አንድምታ_ትርጓሜን#የግእዝ_መጽሐፍ_ቅዱስ_ክፍሉን_በድምጽ፣ የመጽሐፍ ቅዱስ #የጥናት_ዕቅድን#ጥያቄዎችንና የመሳሰሉትን አዳዲስ አገልግሎቱን በማካተት እየተዘጋጀ ነው ። ይህንን አገልግሎት ለጊዜው ማግኘት የሚችሉት ገደብ አልባ ደንበኞች (Premium Members) ብቻ ናቸው ።

መጽሐፍ ቅዱሱ በይዘትም በዓይነትም የመጀመርያው ነው ።

ገደብ አልባ ደንበኛ በመሆን የዚህ ዕድል ተጠቃሚ ይሁኑ።

ገደብ አልባ ደንበኞች ሁሉንም አፖች በአንድ የመክፈቻ ቁልፍ ከፍተው ለዕድሜ ልክ ያለ ገደብ መጠቀም ይችላሉ ።


ብራና አፕስ  Birana Apps
+251901008562

የብራና አፕስ ትክክለኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾች
Website | Telegram | Facebook | Tiktok | Twitter | Whatsapp | Instagram
👍269🥰4
#ድጋሜ_የማይገኝ_ዕድል

ላልሰሙት ያሰሙ ።

#ብራና_አፕስ የገደብ አልባ ደንበኝነትን (Premium Membership) ለመጨረሻ ጊዜ #በ800ብር ብቻ ስናቀርብልዎ በደስታ ነው። ይህ ዋጋ ከመደበኛው የአፕሊኬሽኖች ዋጋ የ80% ቅናሽ ሲኖረው፣ ለወደፊት ከሚኖሩን የአፕሊኬሽኖቻችን ዋጋ ደግሞ 150% ቅናሽ ይኖረዋል። ይህንን ዕድል በድጋሜ አያገኙትም።

የዚህ ዕድል ተጠቃሚ መሆን የሚቻለው እስከ ሚያዝያ 12፣ 2017 ዓ.ም (በዓለ ትንሣኤ) ነው ።

ገደብ አልባ ደንበኝነት (Premium Membership) ማለት እስካሁን የተዘጋዘጁትን 24ቱንም አፕሊኬሽኖች ጨምሮ ለወደፊት የሚዘጋጁ አፕሊኬሽኖችን በአንድ የመክፈቻ ቁልፍ ከፍተው #ለዕድሜ_ልክ ያለ ገደብ መጠቀም እንዲችሉ የሚያደርግዎት ልዩ ፓኬጅ ነው።

ብራና አፕስ  Birana Apps
+251901008562

የብራና አፕስ ትክክለኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾች
Website | Telegram | Facebook | Tiktok | Twitter | Whatsapp | Instagram
👍19👏42
የ10ኛ ዓመት የምሥረታ በዓላችንን ምክንያት በማድረግ #የሥጦታ ፕርግራም አዘጋጅተናል። ይጠብቁን ።
👍2718
ብራና አፕስ 10ኛ ዓመት የምሥረታ በዓሉን ምክንያት በማድርግ ደንበኞቹ ተጠቃሚ የሚሆኑበትን መንገድ አዘጋጅቷል ።

እንደሚታወቀው በብዙ ድካም የተዘጋጁ መተግበርያዎች #በማስታወቂያ ችግር ምክንያት ለተጠቃሚዎች በሰፊው የመድረስ ዕድላቸው በጣም ውስን ሆኖ ቆይቷል ። ይህም ተጠቃሚዎች ከግንዛቤ እጥረትና በቂ ግንዛቤ ካለማግኘት የተነሣ መጠቀም እየፈለጉ በፍርሃትና እምነት በማጣት ለመግዛት ሲቸገሩ እየተስተዋለ ነው ።

ችግሩን ለመፍታት በነባርና አዳዲስ ደንበኞች አማካኝነት አፖቹን ለማስተዋወቅና የሚያስተዋውቁ ደንበኞችንም ለመደጎም ይህ ፕሮግራም ተዘጋጅቷል ።

የዚህ ዕድል ተጠቃሚ ለመሆን የሚከተለውን ይተግብሩ።

1.በቅድሚያ ተመዝግበው የኩፖን ኮድ ማግኘት ይኖርብዎታል ። ከዚያም ገደብ አልባ ደንበኞችን ይጋብዛሉ። በእርስዎ ምክንያት የተጋበዙ ደንበኞች ክፍያ ፈጽመው የመክፈቻ ኮድ ለማግኘት መልዕክት ወደ እኛ ሲልኩ የእርስዎንም ኩፖን ኮድ አብረው መላክ ይኖርባቸዋል።

2. በእርስዋ ግብዣ የገዙ ደንበኞችን ዝርዝር መመዝገብ ይችላሉ ። ከእኛም ማግኘት ይችላሉ ።

3. የ20% ድርሻዎን 500ብር ጀምሮ ከእኛ መውሰድ ይችላሉ። በየቀኑ የሚሠሩት ብር ከ500 ብር በላይ ከሆነ በዕለቱ ብርዎን ወደ አካውንትዎ እናስተላልፍልዎታለን ።


ለመመዝገብና ኩፖን ኮድ ለማግኘት በ @birana_premium ያናግሩን።

#ያስታውሱ፣ ገደብ አልባ ደንበኝነት ማለት በአንድ የመክፈቻ ኮድ ሁሉንም አፖች መክፈትና መጠቀም የሚያስችል አገልግሎት ነው። እስከ በዓለ #ትንሣኤ ድረስ ገደብ አልባ ደንበኝነት ዋጋው 800ብር ነው። ከበዓለ ትንሣኤ በኋላ መደበኛ ዋጋው 1000ብር ነው። በገደብ አልባ ደንበኝነት የተካተቱ አፕሊኬሽኖች ብዛት 24+ ናቸው ። አፖችም የሚገኙት እዚህ https://t.me/biranapremium ብቻ ነው።
10👍6👏3🥰2😁2🤔1
Channel photo updated
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የብዙ ሰው ጥያቄ ለሆነው "#ገደብ_አልባ_ጥቅል" የተሰጠ አጭር የቪዲዮ ማብራሪያ

የዚህ ጥቅል ተጠቃሚ ለመሆን ከፈለጉ አፖችን ከዚህ ቴሌግራም ቻናላችን ወይም ድረ ገፃችን ብቻ ያውርዱ ።

Telegram: Https://t.me/biranapremium

Website: https://biranapps.com/premium-members/

#ማሳሰቢያ

ከላይ ባሉት ቴሌግራም ቻናል እና ድረ ገጽ ላይ የተለቀቁት አፖች #ገደብ_አልባ_ደንበኛ  ለሆኑና መሆን ለሚፈልጉ ብቻ ነው ። ገደብ አልባ ደንበኛ ያልሆነ ደንበኛ እዚህ ቻናል እና ድረ ገጽ ላይ የሚለቀቁ አፖችን በማውረድ የመክፈቻ ኮድ ቢጠይቅ ፣ እኛን ከማድከም ውጪ የሚላከው ኮድ አይከፍትለትም ።

ብራና አፕስ Birana Apps
+251901008562

የብራና አፕስ ትክክለኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾች
Website | Telegram | Facebook | Tiktok | Twitter | Whatsapp | Instagram
👍113👎3