Biranna Tech ብራና ቴክ
14.7K subscribers
639 photos
5 videos
123 files
415 links
ወደ ብራና Apps እንኳን በደህና መጡ። ታላላቅ መጻሕፍትን የያዙ አፕሊኬሽኖችን ያውርዱ ይግዙ ።

ውይይቶችን ፣ ጥያቄዎችን ፣ ማብራሪያዎችን ከፈለጉ ወደ ግሩፓችን ይቀላቀሉን ።

ወደ ሽያጭ ቻናላችን ይቀላቀሉ ። @birannasales

Website: https://biranna.com
Email: support@biranna.com
Phone: +251901008562
Download Telegram
አዲሱ 1
👍6👎4
ለመዝገበ ሕይወት አፕ ሎጎ የትኛውን ይመርጣሉ?
Final Results
21%
የቀድሞው 1
49%
የቀድሞው 2
40%
አዲሱ 1
🕊4
#ግእዝ
ወብዙኃን እለ ነጸፉ ቈጽለ መቲሮሙ እምዕፀው ወቦ እለ ነጸፉ አልባሲሆሙ ውስተ ፍኖት። እለሂ ይመርሑ ወእለሂ ይተልዉ ይኬልሑ ወይብሉ ሆሣዕና «ቡሩክ ዘይመጽእ በስመ እግዚአብሔር ።» ወቡርክት እንተ ትመጽእ መንግሥት በስመ እግዚአብሔር እንተ አቡነ ዳዊት #ሆሣዕና_በአርያም
ማር 11፡8-10

#አማርኛ
ብዙ ሰዎችም ልብሳቸውን በመንገድ ላይ አነጠፉ፤ ሌሎችም ከዛፍ ቅጠሎችን እየቈረጡ ያነጥፉ ነበር። የሚቀድሙትም የሚከተሉትም “ሆሣዕና! በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው፤ በጌታ ስም የምትመጣ የአባታችን የዳዊት መንግሥት የተባረከች ናት፤ #ሆሣዕና_በአርያም!” እያሉ ይጮኹ ነበር።
ማር 11፡8-10

#Afaan_Oromoo
Namoonni baayʼeen uffata isaanii karaa irra afan; warri kaan immoo dameewwan baala qaban kanneen alaa kukkutan sana karaa irra bubuusan. Warri dura deemaa turanii fi warri duukaa buʼaa turan iyyanii akkana jedhan; “Hoosaaʼinaa!” “Inni maqaa Gooftaatiin dhufu eebbifamaa dha!” “Mootummaan abbaa keenya Daawit inni dhufu sun eebbifamaa dha!” #Hoosaaʼinaa_ol_gubbaatti!
Mar 11፡8-10

#ትግርኛ
ብዙሓት ድማ ኣብቲ መገዲ ኽዳውንቶም ኣንጸፉ፡ ካልኦት ከኣ ካብ ኣእዋም ጨጨንፈሩ ሰሊዖም ነስነሱ። ቀቅድሚኡ ዚኸዱን ደድሕሪኡ ዚስዕቡን ከኣ ዓው ኢሎም፡ ሆሳእና፡ ብስም እግዚኣብሄር ዚመጽእ ብሩኽ እዩ። እታ እትመጽእ ዘላ መንግስቲ ኣቦና ዳዊት ብርኽቲ እያ፡ #ሆሳእና_ኣብ_ኣርያም፡ በሉ።
ማር 11፡8-10

እንኳን አደረሰን ።
👍72
ሰሙነ ሕማማት
ሰኑይ - ሰኞ

1. መርገመ በለስ የተፈጸመበት ሰኞ ይባላል፦
በዚህ ዕለት ጌታችን ከቢታኒያ ሲወጣ ተራበ ቅጠል ያለባትን በለስ ተመልክቶ ወደ በለሲቱ ቢቀርብ ከቅጠል በቀር ምንም ነገር ባለማግኘቱ “ከአሁን ጀምሮ ለዘላለም ምንም ካንቺ ፍሬ አይበላ” ማር ፲፩፥፲፬ በማለት ስለረገማት መርገመ በለስ የተፈጸመበት ሰኞ ይባላል።

2. አንጽሖተ ቤተ መቅደስ ይባላል፡-
ጌታ ወደ ቤተመቅደስ ሄዶ በቤተመቅደሱ የሚሸጡትን እና የሚለውጡትን “ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች” ማቴ ፳፩፥፲፫ በማለት ከቤተመቅደስ ገርፎ አስወጥቷቸዋልና።

"እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ፃማ ወድካም አመ ከመ ዮም ያብጽሐነ ያብጽሕክሙ ለብርሃነ ትንሣኤሁ እግዚአብሔር በፍስሓ ወበሰላም አሜን !"

"ያለ ደዌና ያለ ሕማም ያለ ፃማና ያለ ድካም እግዚአብሔር ለትንሣኤው ብርሃን እንደ ዛሬ ቀን በደስታና በፍቅር በአንድነት ያድርሰን ያድርሳችሁ አሜን !"

፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠

Birana Apps ብራና አፕስ
Web: https://biranapps.com
Tel: +251901008562
Email: biranapps@gmail.com
Facebook: https://facebook.com/biranapps
Twitter: https://twitter.com/biranapps
Instagram: https://instagram.com/biranapps
Telegram: https://t.me/biranapps
YouTube: https://youtube.com/channel/UCujhMLdL_MhZrHJAHIzyOQQ
👍2
ሰሙነ ሕማማት
ሠሉስ - ማክሰኞ

1. የጥያቄ ቀን ይባላል፦
ሰኞ ዕለት በቤተመቅደስ ሲሸጡ እና ሲለውጡ የነበሩትን ሁሉ እየገረፈ በማባረሩ ምክንያት ለሰው ልጅ ሹመትንና ስልጣንን የሰጠ ጌታ “በምን ስልጣን ይህንን ታደርጋለህ?” ማቴ ፳፩፥ ፳፫ ተብሎ በፈሪሳውያን ተጠይቋልና የጥያቄ ቀን ይባላል።

2. የትምህርት ቀን ይባላል፡-
በዚህ ዕለት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከመሰቀሉ አስቀድሞ ለመጨረሻ ግዜ በቤተመቅደስ ረጅም ትምህርት ስላስተማረም የትምህርት ቀን ይባላል። ሉቃ ፳፩ ፥፳፰ ፣ ማር ፲፪፥፪።

"እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ፃማ ወድካም አመ ከመ ዮም ያብጽሐነ ያብጽሕክሙ ለብርሃነ ትንሣኤሁ እግዚአብሔር በፍስሓ ወበሰላም አሜን !"

"ያለ ደዌና ያለ ሕማም ያለ ፃማና ያለ ድካም እግዚአብሔር ለትንሣኤው ብርሃን እንደ ዛሬ ቀን በደስታና በፍቅር በአንድነት ያድርሰን ያድርሳችሁ አሜን !"

፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠

Birana Apps ብራና አፕስ
Web: https://biranapps.com
Tel: +251901008562
Email: biranapps@gmail.com
Facebook: https://facebook.com/biranapps
Twitter: https://twitter.com/biranapps
Instagram: https://instagram.com/biranapps
Telegram: https://t.me/biranapps
YouTube: https://youtube.com/channel/UCujhMLdL_MhZrHJAHIzyOQQ
👍32
ሰሙነ ሕማማት ረቡዕ

1. ምክረ አይሁድ ይባላል

ረቡዕ እለት የአይሁድ ሊቃነ ካህናትና ጸሐፍት ጌታን እንዴት መያዝ እንዳለባቸው የመከሩበትና ውሳኔ ያሳለፉበት ቀን በመሆኑ ምክረ አይሁድ ይባላል። ወቅቱ የፋሲካን በዓል የሚያከብሩበት ቀን በመሆኑ እና ብዙ ህዝብም ጌታን ይከተለው ስለነበር ሁከት እንዳይነሳ ስጋት ነበራቸው ። ነገር ግን ከአስራ ሁለቱ ሐዋርያት አንዱ የአስቆሮቱ ይሁዳ አሳልፎ እንደሚሰጣቸው ስለነገራቸው ( ሉቃ ፳፪፥፩-፮ ) ጭንቀታቸው ተወግዶ በጌታ መያዝ ተስማምተዋል።

2. የመልካም መዓዛ ቀንም ይባላል

ጌታችን በዚህ ዕለት በለምጻሙ በስምዖን ቤት ተቀምጦ ሳለ መላ ሕይወቷን ለዝሙት አስገዝታ ትኖር የነበረችው ማርያም እንተ እፍረት ( ባለሽቶዋ ማርያም) ዋጋው እጅግ ውድ የሆነ የአልባጥሮስ ሽቱ አምጥታ በራሱ ላይ በማርከፍከፍ ስለቀባቸው ( ማቴ ፳፮፥፮-፯ ) የመዓዛ ቀን ይባላል።

3. የእንባ ቀን ይባላል

ባለሽቱዋ ሴት ( ማርያም እንተ እፍረት ) ኃጢአቷን ይቅር እንዲላት እየለመነች በእግሩ ስር ተደፍታ በእንባዋ እግሩን አርሳለችና ( ማር ፲፬፥፱ ) የእንባ ቀን ይባላል።

"እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ፃማ ወድካም አመ ከመ ዮም ያብጽሐነ ያብጽሕክሙ ለብርሃነ ትንሣኤሁ እግዚአብሔር በፍስሓ ወበሰላም አሜን !"

"ያለ ደዌና ያለ ሕማም ያለ ፃማና ያለ ድካም እግዚአብሔር ለትንሣኤው ብርሃን እንደ ዛሬ ቀን በደስታና በፍቅር በአንድነት ያድርሰን ያድርሳችሁ አሜን !"

፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠

Birana Apps ብራና አፕስ
Web: https://biranapps.com
Tel: +251901008562
Email: biranapps@gmail.com
Facebook: https://facebook.com/biranapps
Telegram: https://t.me/biranapps
3👍2
የሰሙነ ሕማማት ሐሙስ

፩ኛ. ጸሎተ ሐሙስ ይባላል።

ይኸውም:-ኅብስቱን ለውጦ ሥጋ መለኮት፥ወይኑንም ደመ መለኮት ባደረገ ጊዜ ስለ ጸለየ እና እንዲሁም በዮሐንስ ምዕራፍ ፲፯ ላይ ያለውን በመጸለዩ ነው።

፪ኛ. ትእዛዘ ሐሙስ ይባላል።
ይኸውም:-የደቀ መዛሙርቱን እግሮች ካጠበ በኋላ “እናንተም እንዲሁ አድርጉ፤”ብሎ በማዘዙ እና በጌቴሴማኔ ጴጥሮ ስን፥ዮሐንሰን፥ያዕቆብን “ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸልዩ፤”የሚል ትእዛዝ ስለ ሰጣቸው፤ እንዲሁም:-ሥርዓተ ቁርባንን አሳይቶ “ከመዝ ግበሩ ተዝካርየ፤”ብሎ በማዘዙ ነው።

፫ኛ. የነፃነት ሐሙስ ይባላል።
ይኸውም ጌታ ደቀ መዛሙርቱን:-“ከእንግዲህ ባሮች አለላችሁም፥ወዳጆች ግን ብያችኋለሁ፤”ያለውን በማሰብ ነው።

፬ኛ. ኅፅበተ ሐሙስ ይባላል።
ይኸውም:-በዚህ ዕለት የደቀ መዛሙርቱን እግሮች በማጠቡ ነው።

፭ኛ. አረንጓዴው ሐሙስ ይባላል።
ይኸውም አረንጓዴ በሆነ የአትክልት ሥፍራ መጸለዩን ለማስታወስ ነው።

፮ኛ. የአዲስ ኪዳን ሐሙስ ይባላል።

ይኸውም ጽዋውን አንስቶ “ይህ የአዲስ ኪዳን ደሜ ነው፤”በማ ለቱ ነው።ትርጉሙም ሥጋውና ደሙ የአዲስ ሕግ የወንጌል፥የአዲስ ርስት የመንግሥተ ሰማይ መጥኛ መሆኑን የሚያመለክት ነው።

"እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ፃማ ወድካም አመ ከመ ዮም ያብጽሐነ ያብጽሕክሙ ለብርሃነ ትንሣኤሁ እግዚአብሔር በፍስሓ ወበሰላም አሜን !"

"ያለ ደዌና ያለ ሕማም ያለ ፃማና ያለ ድካም እግዚአብሔር ለትንሣኤው ብርሃን እንደ ዛሬ ቀን በደስታና በፍቅር በአንድነት ያድርሰን ያድርሳችሁ አሜን !"

፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠

Birana Apps ብራና አፕስ
Web: https://biranapps.com
Tel: +251901008562
Email: biranapps@gmail.com
🙏31👍1
ሰሙነ ሕማማት ዓርብ

፩፤ የስቅለት ዓርብ ይባላል።

ጌታችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአዳምና ለልጆቹ ሁሉ ቤዛ ሆኖ በመልዕልተ መስቀል ላይ ተሰቅሎ የዋለበት ዕለት ነውና የስቅለት ዓርብ ይባላል። ማቴ ፳፯፥፴፭

፪፤ መልካሙ ዓርብ ይባላል።

ከጌታ ስቅለት በፊት በተለይም በሮማውያን ህግ የወንጀለኛ መቅጫ ምልክት የነበረውን መስቀል ጌታችን በደሙ ቀድሶ የምህረት ፣ የሕይወት አርማ ፣ የዲያቢሎስ ድል መንሻ ስላደረገው ፤ በሞቱ መልካሙን ሕይወት ስላገኘን መልካሙ ዓርብ ይባላል።

"እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ፃማ ወድካም አመ ከመ ዮም ያብጽሐነ ያብጽሕክሙ ለብርሃነ ትንሣኤሁ እግዚአብሔር በፍስሓ ወበሰላም አሜን !"

"ያለ ደዌና ያለ ሕማም ያለ ፃማና ያለ ድካም እግዚአብሔር ለትንሣኤው ብርሃን እንደ ዛሬ ቀን በደስታና በፍቅር በአንድነት ያድርሰን ያድርሳችሁ አሜን !"

፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠

Birana Apps ብራና አፕስ
Web: https://biranapps.com
Tel: +251901008562
Email: biranapps@gmail.com
Facebook: https://facebook.com/biranapps
Twitter: https://twitter.com/biranapps
Instagram: https://instagram.com/biranapps
Telegram: https://t.me/biranapps
YouTube: https://youtube.com/channel/UCujhMLdL_MhZrHJAHIzyOQQ
3👍1
ሰሙነ ሕማማት ቀዳም ሥዑር (የተሻረች ቅዳሜ)

1. ቀዳም ሥዑር ትባላለች።

ይኽች ዕለት ከድሮው በተለየ መልኩ የጌታችንን መከራ በማሰብ በጾም ታስባ ስለምትውል እና የማትጾመው ቅዳሜ ስለምትጾም የተሻረችው ቅዳሜ ትባላለች

2. ለምለም ቅዳሜ ትባላለች።

ካህናቱ ለምእመናን ለምለም ቀጤማ የሚያድሉበት ዕለት ስለሆነ በዚህ ተሰይሟል። ቀጤማውንም ምእመናን እስከ ትንሣኤ ሌሊት በራሳቸው ላይ ያስሩታል።

ምዕመናን ቄጤማውን በራሳቸው ያስራሉ ምክንያቱም አይሁድ ጌታችንን እያሰቃዩ ሊሰቅሉት ባሉ ጊዜ የእሾህ አክሊል ጭንቅላቱ ላይ ያሠሩበትን ድርጊት የሚያስታውስ ነው።

3. ቅዱስ ቅዳሜ ትባላለች።

ቅዱስ ቅዳሜ መባሉ ቅዱስ የሆነ እግዚአብሔር በጥንተ ተፈጥሮ ፍጥረታትን አከናውኖ ከፈጠረ በኋላ በዚህ ቀን ከሥራው ሁሉ ያረፈበት ዕለት ስለሆነ ነው።

በዘመነ ሐዲስ የማዳን ሥራውን ሁሉ ፈጽሞ በሥጋው በመቃብር ሲያርፍ፣ በነፍሱ ሲዖልን በርብሮ ባዶዋን ስላስቀራት ይች ቀን የተባረከች ዕለት ስለሆነች ቅዱስ ቅዳሜ ተብላለች

"እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ፃማ ወድካም አመ ከመ ዮም ያብጽሐነ ያብጽሕክሙ ለብርሃነ ትንሣኤሁ እግዚአብሔር በፍስሓ ወበሰላም አሜን !"

"ያለ ደዌና ያለ ሕማም ያለ ፃማና ያለ ድካም እግዚአብሔር ለትንሣኤው ብርሃን እንደ ዛሬ ቀን በደስታና በፍቅር በአንድነት ያድርሰን ያድርሳችሁ አሜን።"

፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠

Birana Apps ብራና አፕስ
Web: https://biranapps.com
Tel: +251901008562
Email: biranapps@gmail.com
Facebook: https://facebook.com/biranapps
Instagram: https://instagram.com/biranapps
Telegram: https://t.me/biranapps
👍5
እግዚአብሔር ከእንቅልፍ እንደሚነቃ ተነሣ
የወይን ስካር እንደ ተወው እንደ ኃያልም ሰው፤ ጠላቶቹንም በኋላው ገደለ። መዝ ፸፯፥፷፭

እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው  አደረሳችሁ ።
👍43👏1
ከትንሣኤ በኋላ ያሉ ዕለታት ስያሜ

ትንሣኤ ማግሥት የሚውለው ሰኞ ማዕዶት ይባላል ፡፡

#ማዕዶት ማለት መሻገር፣ ማለፍ ማለት ነው፡፡ ፤ በዚህችም ዕለት በፋሲካችን በክርስቶስ ትንሣኤ ከድቅድቅ ጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃን፣ ከሞት ወደ ሕይወት፣ ከሲኦል ወደ ገነት፣ ከሃሳር ወደ ክብር መሻገራችንን እናስባለን፡፡

ጌታችን በሞትና ትንሣኤው ነፍሳትን ከሲኦል አውጥቶ ወደ ገነት አሻግሮ ለማስገባቱ መታሰቢያ ሆና «ፀአተ ሲኦል ማዕዶት» ትባላለች፡፡ ዮሐ. 19-18 ሮሜ. 5-10-17
የዳግም ትንሣኤው ማግሥት ያለችው ግን ገበሬው፤ ወንዶቹ እርሻ ቁፋሮውን፣ ንግዱን፣ ተግባረ እዱን ሁሉ ሴቶቹ ወፍጮውን፣ ፈትሉን፣ ስፌቱን የሚጀምሩባት ዕለት ስለሆነች «እጅ ማሟሻ» ሰኞ ትባላለች፡፡

Birana Apps ብራና አፕስ
Web: https://biranapps.com
Tel: +251901008562
Email: biranapps@gmail.com
Facebook: https://facebook.com/biranapps
Twitter: https://twitter.com/biranapps
Instagram: https://instagram.com/biranapps
Telegram: https://t.me/biranapps
YouTube: https://youtube.com/channel/UCujhMLdL_MhZrHJAHIzyOQQ
👍7
የትንሣኤ ማግስት ማክሰኞ ቶማስ ይባላል

"…በትንሣኤ ማግሥት ማግሰኞ በዚህ ዕለት ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ የጌታን የተወጋ ጎኑን፣ የተቸነከሩ እጆቹን ካላየሁ አላምንም ብሎ ነበርና የጌታችንን የተወጋ ጎኑን፣ የተቸነከሩ እጆቹን ማየት ብቻ ሳይሆን ዳስሶ ጭምር "ጌታዬና አምላኬ" በማለት ጌትነቱ ከአምላክነቱ ጋር አስተባብሮ የመሰከረበት ዕለት በመሆኑ ለቅዱስ ቶማስ መታሰቢያ ይሆን ዘንድ ዕለቱ ቶማስ ተብሎ ይከበራል። ዮሐ 20፥ 27-29

"…ታሪኩ የተፈጸመው በትንሣኤ ሳምንት ባለው በእለተ እሑድ በዳግማይ ትንሣኤ ዕለት ቢሆንም የቅድስት ቤተ ክርስቲያን አበው ታሪክ ከታሪክ እንዳይደራረብ ብቻ ሳይሆን ዳግማይ ትንሣኤ የጌታ ዳግም መነሣት ብቻ ሲታወጅ እንዲውል ብለው በትንሣኤ ማግስት ከሰኞ በኋላ በሚከተለው ቀን በዕለተ ማክሰኞ በዛሬው ዕለት ተከብሮ እንዲውል ሥርዓት ሠርተዋል። ቅዱስ ቶማስ በእመቤታችን ትንሣኤ ዕለትም ከሐዋርያቱ ጋር ያልነበረ፤ ከሀገረ ስብከቱ ህንድ ቆይቶ ሲመለስ በደመና ላይ እመቤታችን ስታርግ ያገኘ ሐዋርያም ነው። የሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ በረከቱ ይደርብን። አሜን።

Birana Apps ብራና አፕስ
Web: https://biranapps.com
Tel: +251901008562
Email: biranapps@gmail.com
Facebook: https://facebook.com/biranapps
Twitter: https://twitter.com/biranapps
Instagram: https://instagram.com/biranapps
Telegram: https://t.me/biranapps
YouTube: https://youtube.com/channel/UCujhMLdL_MhZrHJAHIzyOQQ
ከትንሣኤ በኋላ ያሉ ዕለታት ስያሜ
ረቡዕ - አልዓዛር

አልዓዛር ክርስቶስ ያስነሣው የማርያምና የማርታ ወንድም ነው፤ የስሙም ትርጓሜ እግዚአብሔር ረድቷል ማለት ነው፤ (ዮሐ. ፲፩፥፯-፵፰)፤
አልዓዛር የሞተው መጋቢት ፲፯ ነበር፡፡ እህቶቹም ክርስቶስ እንዲመጣ መልእክት ልከውበት ነበር፤ ክርስቶስ ግን በ፬ኛው ቀን ማለትም መጋቢት ፳ መጥቶ ከሞት አስነሥቶታል፤(ዮሐ.፲፩፥፵፬)፡፡

Birana Apps ብራና አፕስ
Web: https://biranapps.com
Tel: +251901008562
Email: biranapps@gmail.com
Facebook: https://facebook.com/biranapps
Twitter: https://twitter.com/biranapps
Instagram: https://instagram.com/biranapps
Telegram: https://t.me/biranapps
YouTube: https://youtube.com/channel/UCujhMLdL_MhZrHJAHIzyOQQ
👍6
የገደብ አልባ ጥቅል አገልግሎትን በተመለከተ ማብራርያ

1. እስከ በዓለ ትንሣኤ መዝገበ ሕይወትን የገዙ ደንበኞች በሙሉ የገደብ አልባ ጥቅል አገልግሎት ደንበኞች ሆነዋል።

2. የገደብ አልባ ጥቅል አገልግሎት ማለት #መዝገበ_ሕይወትን (21 አፖችን በአንድ ላይ የያዘ)፣ #ከሦስቱ_መዝገበ ቃላት (ግዕዝ አማርኛ መዝገበ ቃላት ፣ አማርኛ በአማርኛ መዝገበ ቃላት እና ትግርኛ በአማርኛ መዝገበ ቃላት) የፈለጉትን በአንድ ላይ ያጠቃለለ ነው። ነባር የገደብ አልባ ጥቅል አገልግሎት ደንበኞችም ከዚህ በኋላ በዚህ መሠረት የሚስተናገዱ ይሆናሉ ።

3. የገደብ አልባ ጥቅል አገልግሎት ደንበኞች በአንድ ጊዜ ከሁለት ቀፎዎችን በላይ መጠቀም አይችሉም። ነገር ግን ቀፎ በቀየሩ ቁጥር እስከ ዕድሜ ልክ ያለ ክፍያ መጠቀም ይችላሉ።

4. ከሁለት ቀፎዎች በላይ በአንድ ጊዜ ለመጠቀም የሚፈልግ በተለየ ፓኬጅ የተዘጋጀ ስለሚኖር በእርሱ መሠረት መስተናገድ ይችላል።

5. ከዚህ ቀን ጀምሮ መዝገበ ሕይወት እንደ አንድ አፕሊኬሽን መሸጥ የሚያቆም ሲሆን መዝገበ ሕይወትን መግዛት የሚፈልጉ በሙሉ የገደብ አልባ ጥቅል አገልግሎት ደንበኞች ይሆናሉ ።

Birana Apps ብራና አፕስ
Web: https://biranapps.com
Tel: +251901008562
Email: biranapps@gmail.com
Facebook: https://facebook.com/biranapps
Twitter: https://twitter.com/biranapps
Instagram: https://instagram.com/biranapps
Telegram: https://t.me/biranapps
YouTube: https://youtube.com/channel/UCujhMLdL_MhZrHJAHIzyOQQ
👏2👍1
#ከትንሣኤ_በኋላ_ያሉ_ዕለታት_ስያሜ
ሐሙስ አዳም ይባላል ። የአዳም ምሉዕ ተስፋ የተፈጸመለትን ምስጢር የምናስታውስበትና የምንዘክርበት ዕለት ነው። ምክንያቱም ለክርስቶስ ሰው መሆን ዋና ምክንያቱ ጸሎተ አዳም ወሔዋን ስለሆነ ርደተ ሲኦልን በሚጠታቸው፣ ርደተ መቃብርን በሙስና መቃብር፣ ጽልመተ ሲኦልን በብርሃነ መለኮት ለውጦ ሞተ ሥጋ ወነፍስ ተፈርዶባቸው የነበረው ሁሉ አልፎ “ኃጢአት ከበዛችበት ዘንድ ጸጋ እግዚአብሔር ትበዛለች” ብለው ያመሰገኑበት መታሰቢያ ስለሆነ፤ አዳምና ሔዋን ከሲኦል የወጡት ዓርብ ሲሆን እዚህ መከበሩ ለምንድ ነው ከተባለ ዓርብ ለበለጠው ለአምላካቸውና ለአዳኛቸው ለክርስቶስ ስቅለት ስለሆነ በዚሁ ዕለት ይከበራል። ያውስ ይሁን ሰኞ፣ ማክሰኞ፣ ረቡዕ አለመዋሉ ሐሙስ መዋሉ ለምንድ ነው ቢሉ፥ ከእሑድ እስከ ሐሙስ አምስት ቀን ይሆናል። አምስት ከእኩል ሲፈጸም አድንሃለሁ ብሎት ነበርና ያ እንደተፈጸመ ለማጠየቅ ነው።

Birana Apps ብራና አፕስ
Web: https://biranapps.com
Tel: +251901008562
Email: biranapps@gmail.com
Facebook: https://facebook.com/biranapps
Twitter: https://twitter.com/biranapps
Instagram: https://instagram.com/biranapps
Telegram: https://t.me/biranapps
YouTube: https://youtube.com/channel/UCujhMLdL_MhZrHJAHIzyOQQ
👍2
ልደታ ለማርያም
እንኳን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም የልደት በዓል አደረሰን፤ አደረሳችሁ!!!

ንጽሕተ ንጹሐን፣ ቅድስተ ቅዱሳን፣ ከተለዩ የተለየች፣ ከተመረጡ የተመረጠች ክብርት እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በከበረች ቀን ግንቦት አንድ ቀን ተወለደች፡፡
5
የገደብ አልባ ጥቅል አገልግሎት ደንበኞችን በተመለከተ የተደረጉ ማስተካከያዎች ።

1. እስከ በዓለ ትንሣኤ መዝገበ ሕይወትን የገዙ ደንበኞች በሙሉ የገደብ አልባ ጥቅል አገልግሎት ደንበኞች ሆነዋል።
2. የገደብ አልባ ጥቅል አገልግሎት ማለት መዝገበ ሕይወትንና #ሌሎች_23_አፕሊኬሽኖችን ላይ ያጠቃለለ ነው። ነባር የገደብ አልባ ጥቅል አገልግሎት ደንበኞችም ከዚህ በኋላ በዚህ መሠረት የሚስተናገዱ ይሆናሉ ።
3. የገደብ አልባ ጥቅል አገልግሎት ደንበኞች በአንድ ጊዜ ከሁለት ቀፎዎችን በላይ መጠቀም አይችሉም። ነገር ግን ቀፎ በቀየሩ ቁጥር እስከ ዕድሜ ልክ ያለ ክፍያ መጠቀም ይችላሉ።
4. ከሁለት ቀፎዎች በላይ በአንድ ጊዜ ለመጠቀም የሚፈልግ በተለየ ፓኬጅ የተዘጋጀ ስለሚኖር በእርሱ መሠረት መስተናገድ ይችላል።
5. ከዚህ ቀን ጀምሮ መዝገበ ሕይወት እንደ አንድ አፕሊኬሽን መሸጥ የሚያቆም ሲሆን መዝገበ ሕይወትን መግዛት የሚፈልጉ በሙሉ የገደብ አልባ ጥቅል አገልግሎት ደንበኞች ይሆናሉ ።

በተጨማሪ የገደብ አልባ ጥቅል አገልግሎት ደንበኞች ብቻ አፖችን አውርደው የሚጠቀሙባቸው የቴሌግራም ግሩፕ ፈጥረናል ። የገደብ አልባ ጥቅል አገልግሎት ደንበኞች ብቻ እንዲቀላቀሉ ጋብዘናል።
https://t.me/+IjpzgmDzg4kxYjRk

በአዲሱ ሕጋችን መሠረት የገደብ አልባ ጥቅል አገልግሎት ደንበኞች
1. በአንድ የመክፈቻ ኮድ 24ቱንም አፕሊኬሽኖች መክፈት ይችላሉ ።
2. የተለያዩ ተጨማሪ ማሻሻያ የተደረገባቸውን አፕሊኬሽኖች ያገኛሉ ።
3. አዳዲስ አፕሊኬሽኖችን በተሰጣቸው የመክፈቻ ኮድ መክፈት ይችላሉ ።
4. ሌሎችም ጥቅሞች በግሩፑ ውስጥ ተካተዋል ።

በዚህ አጋጣሚ በአንድ ኮድ የሚከፈቱ አፕሊኬሽኖችን በግሩፑ በቅርብ የምንለቅ ሲሆን በትዕግስት እንድትጠብቁን በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን ።
5👍1👏1
#ከትንሣኤ_በኋላ_ያሉ_ዕለታት_ስያሜ

#ዓርብ፦ ቤተ ክርስቲያን ትባላለች።
ጌታችን ከልደቱ እስከ ሞቱ ያደረገው የማዳን ጉዞ በሙሉ የተፈጸመው ዓርብ ነው። “ወይቤ ተፈጸመ ኵሉ” እንዲል። ዓርብ የቤተ ክርስቲያን ሁለመናዊ ምስጢር የተፈጸመበት ዕለት ስለሆነ ቤተ ክርስቲያን ትባላለች። ማለትም ዓርብ ለቤተ ክርስቲያን መሠረት የሆኑ ዋና ዋና ምሥጢራት ተሟልተዋል። ለምሣሌ የመስቀል አዳኝነቱ ከእርግማንነቱ ተለይቶ ታውቋል፤ የሕንጻዋ መሠረት ቀራንዮ ተተክሎላታል፤ ሥጋ መለኮት የምትፈትተው በቀራኒዮ ተቆርሶላታል፤ ልጆቿን ከማኅጸነ ዮርዳኖስ ከአብራከ መንፈስ ቅዱስ የምትወልድበት ማየ ገቦ ፈስሶላታል። ስብከት፣ ትምህርት፣ ተአምራት፣ ትንሣኤ ተደርጎላታል። ይህንን ሁሉ ምሥጢር ያገኘችው በዕለተ ዓርብ ስለሆነ ቤተ ክርስቲያን ተባለች። የዓርብ ትርጓሜው የሥራ መክተቻ፣ ምዕራብ፣ መግቢያ ማለት ነውና። ኤፌ 2፤19፤ ራዕ 1፤6-8

#Contact_us

Birana Apps ብራና አፕስ
Web: https://biranapps.com
Tel: +251901008562
Email: biranapps@gmail.com
Facebook: https://facebook.com/biranapps
Twitter: https://twitter.com/biranapps
Instagram: https://instagram.com/biranapps
Telegram: https://t.me/biranapps
YouTube: https://youtube.com/channel/UCujhMLdL_MhZrHJAHIzyOQQ
👍32
#ከትንሣኤ_በኋላ_ያሉ_ዕለታት_ስያሜ

#ቅዳሜ፦ አንስት አንከራ (ቅዱሳት አንስት) ትባላለች። በዕለተ ትንሣኤ ሌሊቱን ሲመላለሱ ያደሩ ሴቶች የድካማቸውና ጌታን የመሻታቸው ዋጋ መታሰቢያቸው ነው። አንስት አንከራ (ቅዱሳት አንስት) መባሉ ሌሊት ሲመላለሱ ሁለት መላእክት አይተው ከብሩህነታቸው የተነሳ የተደነቁበትና በመቃብሩ ያለውን መዓዛ ትንሣኤ አሽትተው የተመሰጡበት ዕለት ስለሆነ እንዲሁም ድካማቸው ከንቱ እንዳልሆነ ለማጠየቅ ነው። አንድም ጌታችን አስቀድሞ ለእነርሱ ታይቶ ትንሣኤውን ያረጋገጠበት ስለሆነ እነርሱ ከአምላክነቱ ግርማ የተነሳ ረቡኒ ብለው ያደነቁበት ዕለት መታሰቢያ ስለሆነ። አንድም በጠቅላላው ከሕማማቱ እስከ ትንሣኤው ብዙ የእንባ መሥዋዕት ያቀረቡ እናቶች የሚታሰቡበት ስለሆነ አንስት አንከራ (ቅዱሳት አንስት) ይባላል።