Bilal Gallery
3.92K subscribers
271 photos
10 videos
3 files
262 links
መቼም ሰው ነኝና ስህተት አይታጣብኝም ስህተት ካያችሁ በዚህ @Amir8979 አድርሱኝ ከስህተቴ ሁሌም ተመላሽ ነኝ! "ጥፋቴን በነገረኝ ሙስሊም ሁሉ የአላህ እዝነት ይውረድ"
Download Telegram
👍1
ናይክ 2020 ጫማ

    ጣኦት አምላኪያን አላህ የሚለው ስም ህሌናቸውንም ዐቅላቸውንም ህልማቸውንም ያጨልምባቸዋል ። በመሆኑም ይህን ስም ላለመስማትና ላለማየት ሌላ ዐለም በኖሩ ይመኛሉ ግን አይችሉም እየተቃጠሉና ናላቸው እየዞረ ምኞታቸው እየከሰመ ህያው ሆነው በቁጭት እየሞቱ ይኖራሉ ። እነዚህ አካላት ከአላህ ስም ጋር ያላቸው ፀብ ምንም ነገር እንዲያደርጉ ያነሳሳቸዋል ። በተለያየ ጊዜ የአላህን ስም ለማዋረድ የማይሞክሩት ነገር የለም ። ይሁን እንጂ ራሳቸውን ከማዋረድ የዘለለ ውጤት አያመጡም ። አሁን ደግሞ ለዚህ እርካሽ አላማቸው ማሳኪያ ይሆናል በሚል ናይክ በሚለው 2020 ጫማ መርገጫ ላይ አላህ የሚል ፁሑፍ ፅፈው እንዲረገጥ ለገበያ አቅርበዋል ።
    እነዚህ ዐቅለቢስ ኮተቶች የሰሩት ማይካ እንጂ የሚረገጠው የአላህ ስም አይደለም ። የአላህ ስም ባህሪው ሲሆን ከሱ የማይለይ ነውና ። በፊደል ተፅፎ ለባሮች ጌታቸውን ሊያወሱበትና ሊያወዱሱበት የቀረቡት የዐረብኛ ፊደላትን ከጫማ ስር ማድረግ የአላህን ስም ለማዋረድ መጠቀማቸው ውርደታቸውን ነው የሚያመለክተው ። ለማንኛውም ማንኛውም ነጋዴ ይህን ጫማ ወደሀገር አስገብቶ ሲሸጥ የእነዚህን ጣኦት አምላኪያን እርኩስ አላማ በማሰራጨት ላይ መተባበር ስለሚሆን ከዚህ መቆጠብ ያስፈልጋል ። የትኛውም የአላህን ስምና ባህሪ የሚያከብር ሙስሊም እንዲህ አይነቱን የከንቱዎች ስራ ውጤት የሆነውን ጫማ ገዝቶ ከማድረግ መቆጠብ ይኖርበታል ።
    አላህ የስሙና የባህሪያቶቹን ጠላቶች የሁለት ሀገር ውርደት እንዲያከናንባቸው እንለምነዋለን ።

     http://t.me/bahruteka
❤1
👍1
👌1
Forwarded from በረከቲል ሀበሺያ (Amir)
👍2