Bilal Gallery
3.93K subscribers
270 photos
9 videos
3 files
262 links
መቼም ሰው ነኝና ስህተት አይታጣብኝም ስህተት ካያችሁ በዚህ @Amir8979 አድርሱኝ ከስህተቴ ሁሌም ተመላሽ ነኝ! "ጥፋቴን በነገረኝ ሙስሊም ሁሉ የአላህ እዝነት ይውረድ"
Download Telegram
🔹 በእውቀታቸው የሰሩ የእውቀት ባልተቤቶች ሲሞቱ ምንዳቸው እየጨመረ ይሄዳል !

‏قال العلامة عبد الرحمٰن السعدي - رحمه الله تعالىٰ-:

“إذا انقطعت الأعمال بالموت، وطويت صحيفة العبد، فأهل العلم حسناتهم تتزايد؛ كلما انْتُفِع بإرشادهم، واهْتُدِيَ بأقوالهم وأفعالهم،
فحقيق بالعاقل الموفق أن ينفق فيه نفائس أوقاته، وجواهر عمره، وأن يعده ليوم فقره وفَاقَتِهِ”

          ‏الفتاوىٰ السعدية (١١٣/١)

    🔹  ኢማሙ ሰዕዲይ እንዲህ ይላሉ : –

" ስራ በሞት ተቋርጦ የስራ መዝገብ ሲጠቀለል የእውቀት ባልተቤቶች ምንዳ እየጨመረ ይሄዳል ። ሰዎች በመሪነታቸው በንግግራቸውና በተግባራቸው በተጠቀሙና ቀጥተኛውን መንገድ በተመሩ ቁጥር ምንዳቸው እየጨመረ ይሄዳል ። በመሆኑም አላህ በወፈቀው የዐቅል ባልተቤት በሆነ ሰው ላይ ውድ የሆነ ጊዜውንና ወርቃማው እድሜውን በእውቀት ላይ ሊያደርግ የተገባ ነው ። ይህንንም ለዛ ለችግሩና ለድህነቱ ቀን ሊያዘጋጀው ይገባል "።

http://t.me/bahruteka
👍5
👍3💯2
Bilal Gallery
Photo
⚠️ በሰዎች አነጋገር ውስጥ የሚከሰቱ የሽርክ ተግባራት
✅ በሰዎች ንግግር ውስጥ የሚከሰቱ የሽርክ ተግባራት ብዙ ናቸው። ከእነሱ መካከል አንዳንዶቹ ታላቅ ሽርክ (الشرك الأكبر) ሲሆኑ ሌሎቹ ደግሞ ትንሽ ሽርክ (الشرك الأصغر) ሊሆኑ ይችላሉ። ሙስሊም ሰው ቃላቱን መጠበቅ አለበት።
━━━━━━━━━━━━━━━
❶ ከአላህ ውጭ በሆነ ነገር መማል
❌ "በነቢዩ!" ❌ "በእናቴ!" ❌ "በካዕባ!" ❌ "በሕይወቴ!"
ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
«من حلف بغير الله فقد أشرك»
"ከአላህ ውጭ በሆነ ነገር የማለ ሽርክ አድርጓል።"
ይህ ትንሽ ሽርክ ነው፤ ሰውየው ያ ነገር እንደ አላህ ካከበረው ግን ወደ ታላቅ ሽርክ ሊደርስ ይችላል።
━━━━━━━━━━━━━━━
❷ “አላህ እና አንተ ብቻ ነህ ያዳንከኝ”
“አላህ እና አንተ ብቻ ነህ ያወጣኸኝ”
“በአላህ እና ባንተ እተማመናለሁ”
ይህ ስህተት ነው።
ትክክለኛው አነጋገር፦ “ከአላህ በኋላ አንተ ምክንያት ሆንክ” ማለት ነው።
ምክንያቱም “እና” በማለት ከአላህ ጋር እኩል ማድረግ ይገኝበታል።
━━━━━━━━━━━━━━━
❸ ከሞቱ ሰዎች ወይም ከጠፉ ሰዎች እርዳታ መጠየቅ
❌ “ያ ጀይላኒ እርዳኝ!” ❌ “ያ ረሱለላህ ድረስልኝ!”
ይህ ታላቅ ሽርክ ነው፤ ዱዓ እና እርዳታ መጠየቅ የዒባዳ አይነት ስለሆነ ለአላህ ብቻ ይገባል።
━━━━━━━━━━━━━━━
❹ ምክንያቶችን ከአላህ በላይ ማክበር
❌ “ዶክተሩ ባልኖረ እሞት ነበር” ❌ “ይህ መድሀኒት አዳነኝ”
ይህ ንግግር ስህተት ነው።
ትክክለኛው፦ “አላህ በዚህ ምክንያት አዳነኝ” ማለት ነው።
━━━━━━━━━━━━━━━
❺ የአላህን ፈቃድ ከፍጥረት ፈቃድ ጋር ማያያዝ
❌ “አላህ እና አንተ ካልፈለጋችሁ” ❌ “የአላህ እና ያንተ ፈቃድ”
ትክክለኛው፦ “አላህ ከፈለገ ከዚያም አንተ” ማለት ነው።
━━━━━━━━━━━━━━━
❻ ኮከብ፣ እድል ወይም ጥላቻ ነገሮችን ምክንያት ማድረግ
❌ “ኮከቤ ጥሩ ነው” ❌ “እድሌ አዳነኝ”
ይህ ስህተት ነው።
ሁሉም ነገር በአላህ ፈቃድ እንደሚሆን ማመን አለብን።
━━━━━━━━━━━━━━━
❼ ሪያእ (ለሰዎች ማሳየት)
❌ “ሰዎች ሊወዱ ዘንድ ዒባዳን ማሳመር” ❌ “እንዲያመሰግኑኝ ቁርአን አነባለሁ”
ይህ ደግሞ ከትንሽ ሽርክ ውስጥ ይገባል።
━━━━━━━━━━━━━━━
📌 መደምደሚያ
ሽርክ በጣም ከባድ ኃጢአት ነው። አንዳንድ ጊዜ ሰው ሳያውቅ በቃላቱ ውስጥ ይወድቅበታል። ስለዚህ ንግግራችንን በቁርአንና በሱና መመዘን አለብን።
አላህ ከሽርክ ይጠብቀን።
https://t.me/almuhajrinmedresa
👍4
👍2
🔵ልዩ የኮርስና የሙሃደራ ዝግጅት በወራቤ ከተማ
ሼርርርር

https://t.me/darulhijreh
https://t.me/darulhijreh
https://t.me/darulhijreh
Bilal Gallery
Photo
የእለተ ጁምዓ ሱንናዎችና ስርኣቶች
—————
① መታጠብና መቀባባት
ከሰልማነል ፋሪሲይ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል አለ:- “አንድ ሰው በእለተ ጁምዓ ታጥቦ፣ ከመፀዳዳትም የቻለውንም ተፀዳድቶ፣ ከሚቀባባ ነገርም ተቀባብቶ፣ ቤቱ ውስጥ ከሚገኝ ሽቶ ተቀብቶ፣ ከዚያም ከቤቱ ወጥቶ በሁለት ሰዎች መካከል ካልለያየ፣ ከዚያም የተፃፈለትን ከሰገደ፣ ከዚያም ኢማሙ በተናገረ ጊዜ ዝም ካለ፣ በዚያች ጁምዓ እና በቀጣዩዋ ጁምዓ መካከል ያለውን ወንጀል ይቅር ይባላል።” [ቡኻሪ 883 ላይ ዘግበውታል]

② ከሌላ ጊዜ የተሻለ ቆንጆ የሆነውን ልብስ መልበስ
ከሙሀመድ ኢብን የህያ ኢብን ሂባን (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል:- “አንዳችሁ ለእለተ ጁምዓ ከሌላ ጊዜ የተሻሉ ሁለት ልብሶችን ብይዝ የተሻለ ነው” [አቡዳውድ 1078 ላይ የተዘገበ ሲሆን አልባኒ ሶሂህ ብለውታል]

③ በጊዜ ወደ መስጂድ መግባት
ከአቢሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል:- “በእለተ ጁምዓ ለጀናባ የሚታጠብ አይነትን ትጥበት የታጠበ፣ ከዚያም (ወደ መስጂድ) የተጓዘ ሰው ልክ ግመል ለሶደቃ እንዳቀረበ ነው፣ በሁለተኛው ጊዜ ወደ መስጂድ የተጓዘ ሰው ልክ ለሶደቃ ከብት (ላም) እንዳቀረበ ነው፣ በሶስተኛው ጊዜ የተጓዘ ሰው ልክ ቀንዳማ የሆነ ሙክት እንዳቀረበ ነው፣ በአራተኛው ጊዜ ወደ መስጂድ የተጓዘ ሰው ለሶደቃ ዶሮ እንዳቀረበ ነው፣ በአምስተኛው ጊዜ ወደ መስጂድ የተጓዘ ሰው ለሶደቃ እንቁላል እንዳቀረበ ነው፣ ኢማሙ  ሚንበር ላይ ከወጣ መላኢካዎች ኹጥባውን ለማዳመጥ ይሳተፋሉ።” [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል]

④ መስጂድ ከገቡ በኋላ በሁለት ሰዎች መካከል አለመለያየት (በሁለት ሰዎች ትከሻ ላይ አለመረማመድ)
ጃቢር ኢብን ዐብደላህ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዲህ አለ:- የአላህ መልእክተኛ ﷺ እየኾጠቡ እያለ አንድ ሰው ገባ፣ ሰዎች ላይ እየተረማመደ ነበርና የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ አሉት:- “ቁጭ በል! በእርግጥም አስቸግረሃል አርፍደሃልም።” [ኢብን ማጀህ 923 ላይ የዘገቡት ሲሆን አልባኒ ሀሰን ብለውታል]

⑤ ሱረቱል ከህፍን መቅራት (ማንበብ)
ከአቢ ሰዒድ አል-ኹድሪይ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል:- “በእለተ ጁምዓ ሱረቱል ከህፍን ያነበበ ሰው በእርሱና በበይተል ዐቲቅ መካከል ብርሃን ይበራለታል።” [አልባኒ በሶሂሁል ጃሚዕ 6471 ላይ ሶሂህ ነው ብለውታል።]

⑥ ዱዓ ማብዛትና በእለተ ጁምዓ ዱዓ ተቀባይ የሚሆንባትን ሰኣት መጠባበቅ
ዐብደላህ ኢብኑ መስዑድ (ረዲየላሁ ዐንሁ)  የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል አለ:- “የጁምዓ ቀን አስራ ሁለት ሰኣት ነው፣ ከእርሷ ውስጥ አንዲት ሰኣት አለች ሙስሊም የሆነ ባሪያ በዚያች ሰኣት አላህን ከጠየቀ አላህ የጠየቀውን ይሰጠዋል፣ (ያቺን ሰኣት) በመጨረሻ ሰኣት ከአስር በኋላ አካባቢ ፈልጓት።” [ሶሂሁል ጃሚዕ 8190 ላይ አልባኒ ሶሂህ ነው ብለውታል።]

ከአነስ ኢብን ማሊክ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል:- “የዱዓ ተቀባይነት የሚከጀልባትን ሰኣት ከአስር በኋላ ፀሀይ ወደ መግቢያዋ እስከምትቃረብ ድረስ ባለው ጊዜ ፈልጓት።” [ትርሚዚይ 1237 ላይ የዘገቡት ሲሆን አልባኒ ሀሰን ብለውታል።]

⑦ በነቢዩ ﷺ ላይ ሶለዋት ማብዛት
ከሶፍዋን ኢብን ሱለይም (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል:- “የጁምዓ ቀን እና የጁምዓ ሌሊት ከሆነ (ከገባ) በኔ ላይ ሶለዋት አብዙ።” [በሶሂሁል ጃሚዕ 776 ላይ አልባኒ ሶሂህ ብለውታል።]

ማሳሰቢያ:- ይህ ተግባር የሚመለከተው ወንዶችን ነው። በተለይ ሽቶ ተቀብቶ መውጣት ለሴት ልጅ ሙሉ በሙሉ ሀራም ነው። ሴቶች ምንም አይነት ጌጣጌጥ ያለውን እና ወንዶችን ሊፈትን የሚችል ልብስም ሆነ ሽታ ያለው ቅባትና ሽቶ ሳይጠቀሙ ሙሉ በሙሉ የሴቶችን ሸሪዓዊ ስርኣት ያሟላ አለባበስ ለብሰው በአደብ ወደ መስጂድ መሄዱ አይከለከሉም።
✍🏻ኢብን ሽፋ (t.me/ibnshifa)
የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://telegram.me/IbnShifa
👍3
🎤 ═ ❁ ታላቅ የዳዕዋ ጥሪ ❁ ═ 📢

اَلسَّلَامُ عَلَيْكُمْ وَرَحْمَةُ اللَّهِ وَبَرَكَاتُهُ

🌿 ውድና የተከበራችሁ የሱና ቤተሰቦቻችን!
በእለተ ሰኞ 20/11/2018 ዓ.ል.፣
📍 ለኢሎስ ከተማና አካባቢዋ፣ እንዲሁም 🌍 በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭ ለምትገኙ ሙስሊሞች በሙሉ፣

🕌 በፉርቃን መድረሳ በአይነቱ ለየት ያለ የዳዕዋ ፕሮግራም ማዘጋጀታችንን በታላቅ ደስታ እናበስራችኋለን።
━━━━━━━━━━━━━━━
📖 «እውቀት ከንግግርና ከተግባር ይቀድማል!»
🔎 ቤተሰቦቻችንን ከባዕድ አምልኮና ከተለያዩ ሸሪዓዊ ጥሰቶች እንታደግ!
━━━━━━━━━━━━━━━
📌 ማሳሰቢያ
1️⃣ ይህ በአይነቱ ለየት ያለ የዳዕዋ ፕሮግራም ስለሆነ፣ የእርስዎን መገኘት በጉጉት እንጠብቃለን።
2️⃣ ለሴቶችም በቂ ቦታ ተዘጋጅቷል።
━━━━━━━━━━━━━━━
🔔 ሼር በማድረግ የዳዕዋ ተጋሪ እንሁን።

بَارَكَ اللَّهُ فِيكُمْ

👇 ለተጨማሪ መረጃ 👇

https://t.me/KHALID_ASELEFY
💯3👍2✍1
👍5
ፈገግታም ቁምነገርም

አንድ ሰውዬ በውኃ ጉድጓድ አጠገብ ተቀምጣ ወደነበረች አንዲት ሴት ቀርቦ እንዲህ ሲል ጠየቃት፦“የሴቶች ብልህነት ምንድን ነው?”

እሷም ይህንን ስትሰማ ከጉድጓዱ አጠገብ በመቆም የሰፈሯ ሰዎች እንዲሰሟት ጮክ ብላ ማልቀስ ጀመረች።

ሰውዬው በመደናገጥ፡- “ፈርተሽኝ ነው? ለምን ፈራሽኝ እኔ እኮ ምንም ላደርግሽ አይደለም!።”

እሷም፡- “የመንደሩ ሰዎች እንደሚመጡ ስላወቅክ እንጂ ልትጎዳኝና ልትገድለኝ ነበር”

ሰውዬውም፦ “አንቺን ለመጉዳት ወደዚህ አልመጣሁም ነገር ግን ብልህነትሽን አይቻለሁና ጠየቅኩሽ። እና ካንቺ ጋር ለመነጋገር ያለኝ ፍላጎት ከመጥፎ እምነት የመነጨ አይደለም ምክንያቱም ቆንጆ ሴት ነሽ”

ልጅቷ የሰውዬውን ንግግር ስትሰማ። ከጉርጓዱ አጠገብ የነበረውን የውሃ ባልዲ በማንሳት በራሷ ላይ አፈሰሰችው። ሰውዬው በልጅቷ ተግባር ተደንቆ ጠየቃት፡-“ለምንድነው ይህን ያደረግሽው?” ንግግሩን ሳይጨርስ ጩኸቱን የሰሙት የመንደሩ ሰዎች በአጠገባቸው ተሰበሰቡ።

ልጅቷም የፈጠነ፡- “ጉርጓድ ውስጥ ወድቄ ነበር እና ይህ ሰውዬ ነው ያዳነኝ” አለቻቸው። ሰዎቹም በደሰታ እንደጀግና አመስግነው ሸለሙት።

ከሄዱ በኋላ ጠየቃት፦“ከተግባርሽ በስተጀርባ ያለው ጥበብ ምንድን ነው?”

እሳም መለሰች:- ሴቶች እንደዚህ ናቸው። ከጎዳሀት ትገድልሀለች!፤ ብታስደስታት ግን የበለጠ ደስ ታሰኝሃለች።
copied

ወንዶች ጠንቀቅ በሉ


https://t.me/ABUREYANMUSTEFA
📖በቁርዓን እንተዋወስ

إِنَّ ٱلَّذِينَ تَدْعُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ عِبَادٌ أَمْثَالُكُمْ ۖ
እነዚያ ከአላህ ሌላ የምትገዟቸው ብጤዎቻችሁ ተገዢዎች ናቸው፡፡


فَٱدْعُوهُمْ فَلْيَسْتَجِيبُوا۟ لَكُمْ إِن كُنتُمْ صَٰدِقِينَ

እውነተኞችም እንደኾናችሁ ጥሩዋቸውና ለእናንተ ይመልሱላችሁ፤ (መመለስ ግን አይችሉም)፡፡
(6 : 194)


يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّاسُ ضُرِبَ مَثَلٌۭ فَٱسْتَمِعُوا۟ لَهُۥٓ
እናንተ ሰዎች ሆይ! አስደናቂ ምሳሌ ተገለጸላችሁ፡፡ለእርሱም አድምጡት፡፡
ۚ إِنَّ ٱلَّذِينَ تَدْعُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ لَن يَخْلُقُوا۟ ذُبَابًۭا وَلَوِ ٱجْتَمَعُوا۟ لَهُۥ
እነዚያ ከአላህ ሌላ የምትግገዟቸው (ጣዖታት) ዝንብን ፈጽሞ አይፈጥሩም፡፡

ۖ وَإِن يَسْلُبْهُمُ ٱلذُّبَابُ شَيْـًۭٔا لَّا يَسْتَنقِذُوهُ مِنْهُ ۚ

እርሱን (ለመፍጠር) ቢሰበሰቡም እንኳን (አይችሉም)፡፡ አንዳችንም ነገር ዝንቡ ቢነጥቃቸው ከእርሱ አያስጥሉትም፡፡

ضَعُفَ ٱلطَّالِبُ وَٱلْمَطْلُوبُ
ፈላጊውም ተፈላጊውም ደከሙ፡፡
(21 : 73)

https://t.me/darulekra
https://t.me/darulekra
♦️| ስልጢ ወረዳ - ኢሎስ ቀበሌ
♦️| ምስራቅ ስልጢ - ባሎ ቀሪሶ
♦️| ኮርስና ሙሓደራ  - ከስልጤ ዋራቤ

ኮርሱ በዳሩል-ሂጅራ - ሙሓደራው አዩብ አል-አንሷሪይ
👍8
👍2
Bilal Gallery
Photo
《የጤንነት ፀጋ》

አላህ የለገሰን
በፀጋው ያደለን
በማንዘልቀው ቆጥረን
ሲጉድል ሲያመለጠን
ይገባናል አሁን
ትልቅ ሀብትነቱ
ምትክ አልባነቱ
የጤንነት ፀጋ
ተዘናግቷል ለካ
ጤናው ያልተነካ

አይኑ ሲያይለት ያላነበበት
ጆሮውን መልካምን ያላዳመጠበት
ምላሱን ለእውነት ያላንቀሳቀሳት
አካሉን በጤናው ያልተጠቀመበት
ኢባዳን አጥሮቶ ያላጠራቀመ
የታያዘ ጊዜ ሁለቴ ታመመ
ህመምና ቁጭት
የለፈው ጤንነት

ዋጋው ይገባዋል
ፀጋውን ያውቀዋል
ስንፍናውን ያምናል
ጤንነት ሲነካ
ይታወቀል ለካ
የአላህ ውለታ
የታመሙ ለታ
በጤና እንበርታ !!

አቡ ሀመውያ

https://t.me/Abuhemewiya
👍4💯4❤1