Bilal Gallery
3.9K subscribers
270 photos
9 videos
3 files
260 links
መቼም ሰው ነኝና ስህተት አይታጣብኝም ስህተት ካያችሁ በዚህ @Amir8979 አድርሱኝ ከስህተቴ ሁሌም ተመላሽ ነኝ! "ጥፋቴን በነገረኝ ሙስሊም ሁሉ የአላህ እዝነት ይውረድ"
Download Telegram
🕌 የመስጂድ ምርቃት
እና የኪታብ ኮርስ በቡታጅራ


እነሆ ነገ ቅዳሜ (ዙልሒጃ 6) ጠዋት ጀምሮ ለተከታታይ 2ቀናት የሚቆይ ለአይን የሚማርክ፣ ለጆሮ ቀለብ የሚሆንና ቀልብን በኢማን የሚያድስ ልዩ መንፈሳዊ ድግስ! በቡታጅራ ከተማ የሚገኘው የሰለፊያ መስጂድ ግንባታው ተጠናቆ ለምርቃት በቅቷል። በዚህ ታሪካዊና በበረከት የተሞላ እለት የዕውቀት ብርሃን ሊቀስሙ፣ ልቦናዎትን በቁርአንና በሀዲስ እውቀት ሊያርሱ ተጋብዘዋል።

♦️የፕሮግራሙ ልዩ ድምቀቶች
1/ ታላቁ የምርቃት ስነ-ስርዓት
የአላህ ቤት በደስታና በዚክር ሲመረቅ የታላላቅ ኡስታዞች የምክር ትውስታዎች ተሳታፊ ይሁኑ!

2/ ልዩ የ2 ቀናት የኪታብ ኮርስ በዕውቀታቸውና በዳዕዋቸው ስመ-ጥር የሆኑት ውዱ ዓሊም ሸይኽ አብዱልሐሚድ አል_ለተሚ በራሳቸው እጅ የተፃፈውን "ኣላኡላህ ፊ መካነቲ ላኢላሀኢለላህ" ኪታብ ኮርስ የሚሰጡበት የዕውቀት ማዕድ።

📙ኪታቡ፦ ኣላኡላህ ፊ መካነቲ ላኢላሀኢለላህ
✍️ፀሀፊ፦ ሸይኽ አብዱልሐሚድ አል_ለተሚይ
🎙አቅራቢ፦ በሸይኽ አብዱልሐሚድ ይቀርባል
⏰ሰዓቱ፦ ቅዳሜ ጠዋት ይጀመራል ኢንሻአላህ

📌 ማሳሰቢያ፦ ማደሪያ ቦታ ስለተዘጋጀ፤ እዛው ለማደር የለሊት ልብስ መያዝዎን አይዘንጉ።

👉 አዘጋጅ፦ የቡታጅራ ሰለፊዮች ጀማዓ
☎️ ለበለጠ መረጃ፦
+251911972644
+251930887210

https://t.me/albeyanbutajira/1334
❤2👍1💯1
ስለ ቢላል ኢብኑ ረባህ በ (ሸይ
<unknown>
📣 አዲስ ውብ የሆነ ሙሐደራ

👉 እሮብ ግንቦት 12/9/2018 E.C ከመግሪብ እስከ ዒሻ የተደረገ ሙሐደራ


🎙 ሸይኽ ዐብዱልሐሚድ ኢብኑ ያሲን አል'ለተሚ
ሐፊዘሁሏህ

🇸🇦 ርዕስ፦
مناقب بلال بن رباح (مؤذن الرسول ﷺ) 

📡 ከተዳሰሱ ነጥቦች በትንሹ

💦 የቢላል ኢብኑ ረባህ ደረጃ

💦 ቢላል ኢብኑ ረባህ ለዲን የከፈለው ስቃይ

💦 በማን ባርነት ውስጥ እንደነበር
💦 ማን ነፃ እንዳወጣው


💦 የበድር ጦርነት ክስተት

🍁 እንዲሁም ከቢላል ኢብኑ ረባህ የምንወስደው ትምህርት እና ቁም ነገር ብዙ እንዳሉ ተዳሶበታል ።

🎤 በመጨረሻ ሸይኹ የመከሩት የመንሐጅ ፅናት አደራ ተካቶበታል 🎬


💡አድራሻ፦ ካራ ቆሬ ሳሌ ህንጻ ጀርባ ቢላል ኢብኑ ረባህ ቁጥር ❹ መድረሳ ላይ
👇👇👇👇 jon 👇👇👇👇
https://t.me/bilalibnurebahmedresa
https://t.me/bilalibnurebahmedresa
👍1
አቤት ሞቅ የለ ደዕዋ በዉዱ ሸይካችን አ ሀሚድ(وفقه الله)

      ተጀመረ

             ተጀመረ

                    ተጀመረ

                             ተጀመረ    

    ➢ ገባ
         ➢ ገባ
                ➢ገባ
                    ➢ገ ባ
                             ➢ በሉ



➢ ገባ ገባ   በሉ  ጆይን በሉ ሸር አድርጉ ባረከላህ ፊኩም ጀዛኩሙሏሁ ኸይረን👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇


https://t.me/eibrahimkeyeredin
https://t.me/eibrahimkeyeredin
21_የኡዱሑያ_እርድን_የሚመለከቱ_ፈትዋዎች.pdf
2.6 MB
♦️| ወቅታዊ መፅሐፍ!

📚 21 የኡድሒያ እርድን የሚመለከቱ ፈትዋዋች!

✍ ከባህር ዳር መሻዪኾች ገፅ የተወሰደ

|| የመገናኛው ግሩፕ፦
t.me/Multeqa_Ahlissuneh
t.me/Multeqa_Ahlissuneh
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
❤2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🚫  የኻሊድ ክብሮም የአክፍሮትና ሽርክ ጉዞ

ኻሊድ ክብሮም የተባለው ግለሰብ ሰልሜያለሁ ብሎ ወደ እስልምና ከገባ በኋላ የትና ማን ጋር እንደተማረና ሸይኹ ማን እንደሆነ ሳይታወቅ ወደ ዳዕዋ ሜዳ በመግባት በተለይ ሴቶችን ያለ ሒጃብ ፊት ለፊት በማስተማር ሙሪዶቹ እንዲሆኑ ካደረገ በኋላ በጣም አደገኛ አካሄድ እየሄደ ይገኛል ።
ይህ ግለሰብ እየሄደበት ያለው አካሄ በጣም መርዛማና ትክክለኛውን እስልምና የሚበርዝ ነው ። ግለሰቡ እየሄደበት ያለው አካሄድ ምእራባዊያን የሰጡት የቤት ስራ ያለ እስኪመስል እየደረሰ ነው ። ይህ ግለሰብ በረቀቀ መልኩ የነብዩን ሐዲስ ውድቅ በሚያደርግ መልኩ ቁርኣንን ብቻ መያዝና የቁርኣንን መረጃነት ብቻ መቀበል የሚለውን የቁርኣናዊያን ቡድኖች አካሄድ እያሰረፀ ነው ። በዚህ ብቻ አላቆመም ቁርኣንን ራሱ ማንም ቢያብራራው ተቀባይነት እንደሌለውና በቀጥታ ቁርኣንን ብቻ በመገንዘብ መብቃቃት እንደሚቻል መሰረት በመጣል ላይ እየሰራ ነው ። ይህን አስተምሮ በሚቀጥለው ንግግሩ ተመልከቱት 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/bahruteka/7251
ይህ አካሄድ ሰለፎች ቁርኣንን የፈሰሩበትን መንገድ ውድቅ ለማድረግና ሰዎች በዝንባሌያቸውና ከስሜታቸው ጋር በሚስማማ መልኩ እንዲፈስሩት በዚህም ምእራቦች የሚፈልጉት አይነት ባህላዊ እስልምና እንዲስፋፋ ለማድረግ ያለመ አካሄድ ይመስላል ።
ሌላኛው የዚሁ የፈተና ሰው ዳዕዋ ሰዎች በኢማናቸው አማካይነት የፈለጉትን የማድረግ አቅም አላቸው የሚለውን የአሕባሾች ዐቂዳን ለማስፋፋት የሚያደርገው ጥረት ነው ። ይኸው ግለሰብ የለበሱት ልብስ ለሌሎች በረከት የሚያስተላልፍ ትራፊ ውሃቸው ለሌሎች መድሃኒት የሚሆንላቸው ፍፁም የሆነ ሀይል (ፓወር) ያላቸው አሉ እያለ የሰውን ልጅ የረቂቅ ሀይል ባልተቤትና ፍፁም ነው በማለት የቀብር አምልኮና በሙታን መንፈስ ወደ መታገዝ እየተጣራ ይገኛል ። ይህንን አስተምሮ በሚቀጥለው ሊንክ ገብታቸው አዳምጡ
⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️
https://drive.google.com/file/d/1nRc3dU70O311-ljNlE_JueD3-AeG6DQe/view?usp=drivesdk
ከዚህ የሚከፋውና በጣም አደገኛው ደግሞ የደጋጎችን ልብስ መልበስ የእነርሱ መንፈስ ወዳንተ እንዲተላለፍ ያደርጋል የሚለው አስተምሮ ነው ! ይሄኛውንም በሚቀጥለው ሊንክ ገብተው ያዳምጡ : –
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://drive.google.com/file/d/1dR8C1c5Tv4SIVCK1h4IyKFBd8dx75xFy/view?usp=drivesdk
ተመልከቱ አንድ ጃሂል ስለጠሃራ የማያውቅ የአንድን ወልይ ልብስ ቢለብስ ወልይ መሆን ይችላል ማለት ሽርክ አይደለም እያለ ነው የሚያስተምረው ። ለማንኛውም ይህ ግለሰብ ብዙ ሴቶችና ወጣቶች ዘንድ እንዲህ አይነቱን የኩፍርና የሽርክ አስተምሮ ተቀባይነት እንዲኖረው እያደረገ ያለ ግለሰብ ስለሆነ ሙስሊሞች ከግለሰቡና ከአስተምሮቱ እንዲርቁና የኢስላም ጠላቶችን ተልእኮ እያስፈፀመ መሆኑን በማስገንዘብ መታደግ ያስፈልጋል እላለሁ ።

http://t.me/bahruteka
👉 ሶላት ዒባዳ አይደለም !

ከላይ እንደ ምትመለከቱት ኡስታዝ ተብዬው ኻሊድ ክብሮም ተፍሲር ብሎ በሚዘባርቀው ፍልስፍናው ላይ የሶላት ትልቁ ሚና ዒባዳ እውን እንዲሆን የሚያግዝ መሳሪያ እንጂ ሶላት ዒባዳ አይደለም ይላል ‼ ። በጣም የሚያሳፍሩት ከሱ ስር ቁጭ ብለው ይህን የሚማሩት እንጂ እሱ አይደለም ። ምክንያቱም የሱ አላማ ሙስሊሞች ከስማቸው በላይ የሚያውቁዋቸውን የእስልምና ማእዘናቶች ላይ ጥርጣሬ ውስጥ እንዲገቡ በማድረግ ውስጣቸውን ከትክክለኛው እስልምና ባዶ ማድረግ ነውና !
እባካችሁን አላህን እንፈራለን የምትሉ ኡስታዞች ከዚህ ሰው በማስጠንቀቅ ሙስሊሞችን ታደጉ ! ።

http://t.me/bahruteka
▶️ ከሙብተዲዕ ማስጠንቀቅ ሌሊት ተነስቶ ከመስገድ ፣ ኢእቲካፍ ከማድረግ ይበልጣል

ኢብን ተይሚያ - ረሂመሁሏህ - እንዲህ አሉ :-

ለኢማም አህመድ - ረሂመሁሏህ -  እንዲህ ተባሉ :-

"ሰውየው ይጾማል ፣ ይሰግዳል ፣ መስጊድ ውስጥ ኢእቲካፍ ያደርጋል ካንተ ዘንድ ተወዳጁ እንዲህ አይነቱ ሰው ነው ወይስ ስለሙብተዲዖች የሚናገረው?"

ኢማም አህመድ እንዲህ አሉ  ፡ -

“ቢቆም ቢሰግድ ፣ ኢእቲካፍ ቢያደርግ  ጥቅሙ ለራሱ ነው ፤ በቢድዓ  ሰዎች ዙሪያ ቢናገር ግን ጥቅሙ ለሙስሊሞች ነው ፣ ስለዚህ እርሱ በላጭ ነው፡፡”


ይህ ለሙስሊሞች ሐይማኖት የሚሰጠው ጥቅም አጠቃላይ እንደሆነና በአላህ መንገድ የመታገል አይነት እንደሆነም አብራራ፡፡ የአላህን መንገድ ፣ ዲኑን ፣ ጎዳናውን ፣ ሸሪኣውን ከቢድዓና ከሙብተዲዖች ማጽዳት ፤ በዲኑ ላይ የሚያደርሱትን ድንበር ማለፍ መከላከል "ዋጅቡል ኪፋያ" መሆኑ የሙስሊሞች ስምምነት ነው፡፡ የእነዚህን ሰዎች ጉዳት የሚከላከሉ አካላትን አላህ ባያቆም ኖሮ ዲኑ በተበላሸ  ነበር፡፡ ብልሽቱ  ጦረኛ የሆኑ ከሐዲያን በሙስሊሞች ላይ የበላይ በሆኑ ጊዜ ከሚያበላሹት የከፋ ይሆን ነበር፡፡ ጦረኛ የሆኑ ከሐዲዎች ልቦችን እና በውስጥ ያለውን ዲን ቀድመው አያበላሹም - በተከታይነት እንጅ፡፡ (ሙብተዲዖች) ግን ቀድመው ልቦችን ያበላሻሉ፡፡”

فتاوى ابن تيمية (28\231-232)


https://t.me/alateriqilhaq

كن على بصيرة
💯1
🔶#ኻሊድ ክብሮም ከሀዲያንን በመልካም በመኗኗርና ክህደታቸውን በመጥላት መካከል የሚያደርገውን መደበላለቅ ግልፅ ማድረግ

🔈بيان خلط خالد كبروم بين معاملة الكفار بالحسنى وبغضهم لكفرهم.


17 ذو الحجة  1447هـ
الموافق ،3 يونيو 2026 م 


🔗 የዳውንሎድ ሊንኩን ይጫኑ Mp3
https://t.me/shakirsultan/2382

🔶በአዲስ አበባ አል- ወሰጢየህ መርከዝ እና መድረሳ ከሚሰጥ ደርስ የተወሰደ።

🎙 أستاذ شاكر بن سلطان - حفظه الله تعالى

🎙በኡስታዝ ሻኪር ቢን ሱልጣን (ሀፊዘውላህ)

📌 ትምህርቱን ለመከታተል ይህን ቻናል ይቀላቀሉ

👇👇👇
🌐 https://t.me/shakirsultan
مَنْ صَلَّى عَلَيَّ صَلَاةً صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ بِهَا عَشْرًا
💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫

إِنَّ اللَّهَ وَمَلَائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
👉የጁምዓ ቀን ዳሰሳዎች  በስሱ

የጁምዓ ቀን ከሳምንቱ ቀናት በላጭ ምያደርገው ብዙ ነገራቶች ኣሉት።
👌ኣደም በጁምዓ ተፈጠረ።
👌በሱዋም ጀነት ተገባ።
👌በሱዋም ከጀነት ተባረረ።
👌በጁምዓም ተውበቱን ተቀበለው ።
👌በጁምዓም ሞተ።
👌ቅያማ ምትቆመውም በጁምዓ ነው።
👌በሱዋም የሆነች ሰአት ኣለች በዝህች ሰአት ማንም ዱዓእ አያደርግም አሏህ ብቀበለው እንጂ።

👉የጁምዓ ቀን ግዴታዎች
🚦ሰውነቱ መታጠብ በጣም ቆሽሾ ከሆነ
🚦ጁምዓን መስገድ ሸርዓዊ ምክንያት ከሌለው
🚦ኹጥባን ጆሮ ጣል አድርጎ መስማት
🚦አዛንየ (ሁለተኛውን)ከሰማ በግዴታ ወደ መስጅ መሄድ 
👉የጁምዓ ቀን ሱናዎች
✅በግዜ ታጥቦ መሄድ
✅በነብያችን ሰ.ዐ.ወ ላይ ሰለዋትን መብዛት
✅ሽቶ መቀባት (ለወንድ)
✅ነጭ መልበስ ለወንድ
✅ሱረቱ አልከህፍ መቅራት
✅አወል ሰፍ መግባት ሌሎችም,,,,
✅መፋቅያ መጠቀም
👉ጁምዓ የማይወጅብባቸው
🌹ሴቶች በሱናነት በቀር ቤታቻው ይሻላዋል
🚘🚥ሙሳፊር ( መንገደኛ) 80 k m የምጓዝ
❓በሽተኛ መስጅድ መምጣት የማይችል
🥠ነጭ ሽንኩርት የበላ ወይም አዛ ምያደርግ ነገር የተጠቀመ ሰው , ,
🚫የጁምዓ ቀን ክልከላዎች
❌ለሴቶች ሽቶ መቀባት በሌላም ግዜ ከመከልከሉም ጋር ከቤትዋ ውጭ
❌ነጭ ሽንኩርት በልቶ ወደ መስጅድ መሄድ ሌላም በተመሳሳይ የሱን ይዘት የያዘ
❌አዛን ካለ ቦኀላ ንግድ መነገድ ሱቅም ይሁን ሌላም ዱንያ ንግድ ነክ ከሆነ
❌ሰዎችን ትከሻ አላስፈላጊ በሆነ መንገድ መራመድ
❌ኹጥባ ከጀመረ ቦኀላ ማውራት ጥሩም ይሁን ክፉ

🕌የጁምዓ ቀን በመጀመርያው ሰአት የገባ ግመል ሰደቋ እንዳደረገ ይቆጠራል

🏆 በሁለተኛው ሰአት የገባ በሬ ሰደቃ እንዳደረገ ይቆጠራል
⌛️ በሶስተኛው ሰአት የገባ የበግ ሙኩት ሰደቃ እንዳደረገ ይወሰዳል
⏳ በአራተኛው ደሞ ዶሮ ሰደቃ እንዳደረገ ይወሰዳል
🏝 በአምስተኛው የገባ ደሞ እንቁላል 🥚🥚ሰደቃ እንዳደረገ ይቆጠራ እማም ምንበር ላይ ስወጣ መዝገብ ያቆማል።
አሏህ የጁምዓ ሰው ያድርገን!!
🤲🤲🤲🤲🤲
የቴሌግራም ቻናል👇👇👇
https://t.me/darulekra
ሽርክ

ሽርክ (ማጋራት) ለአላህ ብቻ ከሚገቡ ነገሮች አንዱንም ቢሆን ከሱ ውጪ ለሆነ ፍጡር ማድረግ በመሆኑ የተውሂድ ተቃራኒ ነው፡፡ አላህ እንዲህ ይላል፡-

(وَاعْبُدُوا اللَّهَ وَلَا تُشْرِكُوا بِهِ شَيْئًا)النساء 36

“አላህንም ተገዙ በርሱም ምንንም አታጋሩ” (አን ኒሳእ 36)

ሽርክ ከኃጢአቶች ሁሉ የከፋ ከበደሎቸ ሁሉ የላቀ ሲሆን አንድ ሰው ተውበት ሳያደርግ በሽርክ ላይ እንዳለ ከሞተ ኃጢአቱ የማይማርና ጀነት እርም የሆነበት ሆኖ ጀሀነም ውስጥ ይዘወትራል፡፡ አላህ እንዲህ ይላል፡-

إِنَّ الشِّرْكَ لَظُلْمٌ عَظِيمٌ

“ማጋራት ታላቅ በደል ነው” (ሉቅማን 13)

إِنَّ اللَّهَ لَا يَغْفِرُ أَن يُشْرَكَ بِهِ وَيَغْفِرُ مَا دُونَ ذَٰلِكَ لِمَن يَشَاءُ وَمَن يُشْرِكْ بِاللَّهِ فَقَدِ افْتَرَى إِثْمًا عَظِيمًا

“አላህ በእርሱ ማጋራትን በፍጹም አይምርም፡፡ ከዚህ ሌላ ያለውንም (ኀጢአት) ለሚሻው ሰው ይምራል፡፡ በአላህም የሚያጋራ ሰው ታላቅን ኃጢአት በእርግጥ ቀጠፈ::” (አል ኒሳህ 48)

إِنَّ اللَّهَ لَا يَغْفِرُ أَن يُشْرَكَ بِهِ وَيَغْفِرُ مَا دُونَ ذَلِكَ لِمَن يَشَاءُ وَمَن يُشْرِكْ بِاللَّهِ فَقَدْ ضَلَّ ضَلَالًا بَعِيدًا

“አላህ በእርሱ ማጋራትን በፍጹም አይምርም፡፡ ከዚህ ሌላ ያለውንም (ኀጢአት) ለሚሻው ሰው ይምራል፡፡ በአላህም የሚያጋራ ሰው (ከውነት) የራቀን ጥመት በእርግጥ ጠመመ” (አን ኒሳእ 116)

إِنَّهُ مَن يُشْرِكْ بِاللَّهِ فَقَدْ حَرَّمَ اللَّهُ عَلَيْهِ الْجَنَّةَ وَمَأْوَاهُ النَّارُ وَمَا لِلظَّالِمِينَ مِنْ أَنصَارٍ

“እነሆ! በአላህ የሚያጋራ ሰው አላህ በርሱ ላይ ገነትን በእርግጥ እርም አደረገ:: መኖሪያውም እሳት ናት፡፡ ለበዳዮችም ምንም ረዳቶች የሏቸውም::” (አል ማአዳህ 72)

ሽርክን ዓለማዎች በሶስት ይከፍሉታል። አብዛኞቹ  በሁለት ይከፍሉታል፦

1ትልቁና                                               2ትንሹ

1ኛ. ትልቁ ሽርክ፡-

ለአላህ ቢጤ(ባላንጣ) በማድረግ ልክ እንደርሱ ማምለክ ሲሆን ይህ ከእስልምና የሚያስወጣና መልካም ስራን በአጠቃላይ የሚያበላሽ ተግባር ነው፡፡ ይህን ድርጊት ፈፃሚ በዚህ ሁኔታ ከሞተ ጀሀነም ውስጥ ዝንተ አለም ይዘወትራል፡፡ ሞቶ አያልቅለትም ቅጣትም አይቀልለትም፡፡

የትልቁ ሽርክ አይነቶች

ትልቁ ሽርክ  ጠቅለል ሲደረግ በአራት አይነት ልናስተውለው እንችላለን፦

1.   በልመና ማጋራት(በጥሪ ማጋራት)፡-

ልመና ከታላላቅ የአምልኮ ዘርፎች አንዱ ነው፡፡ እንዲያውም የአምልኮ ዋናው እና እራሱ አምልኮት ነው የተባለለት ክፍል ነው፡፡ ነብዩ እንዲህ ይላሉ ‹‹ዱዓዕ ዒባዳ ነው ብለዋል››። አላህም እንዲህ ብሏል

وَقَالَ رَبُّكُمُ ادْعُونِي أَسْتَجِبْ لَكُمْ إِنَّ الَّذِينَ يَسْتَكْبِرُونَ عَنْ عِبَادَتِي سَيَدْخُلُونَ جَهَنَّمَ دَاخِرِينَ

‹‹ጌታችሁም አለ «ለምኑኝ፤ እቀበላችኋለሁና፡፡ እነዚያ እኔን ከመግገዛት(ከመለመን) የሚኮሩት ተዋራጆች ኾነው ገሀነምን በእርግጥ ይገባሉ፡፡›› (አል ጋፊር 6ዐ)

 ዱዓእ አምልኮ መሆኑ የተረጋገጠ በመሆኑ ከአላህ ሌላ ለሆነ ፍጡር ማድረጉ ሽርክ ይሆናል፡፡ ስለዚህ ነብይን፣ መልአክን፣ ወልይን፣መሻይኽን፣ ቀብርን፣ ድንጋይንና ማንኛውንም ፍጡር የለመነ አጋሪ ከሃዲ ይሆናል፡፡                          አላህ እንዲህ ብሏል፦

‹‹ከአላህም ጋር ሌላን አምላክ ለእርሱ በእርሱ ማስረጃ የሌለውን የሚገዛ ሰው ምርመራው እጌታው ዘንድ ብቻ ነው፡፡ እነሆ ከሓዲዎች አይድኑም፡፡›› (ሙእሙኑን 11)

ዱዓእ አምልኮ ስለመሆኑና ከአላህ ውጭ ለሆነ ማድረግ ሽርክ እንደሚሆን ከማስረጃዎች ውስጥ እንዲህ የሚለው የአላህ ቃል አንዱ ነው፡፡

‹‹በመርከቦች ውስጥ በተሳፈሩ ጊዜም አላህን መገዛትን ለእርሱ ብቻ ያጠሩ ኾነው ይጠሩታል፡፡ ወደ የብስ (በማውጣት) ባዳናቸው ጊዜም ወዲያውኑ እነርሱ (ጣዖትን) ያጋራሉ፡፡›› (አንከቡት 65)

 እነዚህ አጋሪዎች ሲመቻቸው እንደሚያጋሩና ሲቸግራቸውና ሲጠባቸው ግን ዒባዳን ለአላህ ብቻ እንደሚያደርጉ ተናገረ፡፡ ታዲያ በአለንበት ዘመን ሁሌ በድሎትም በችግርም በአላህ ላይ የሚያጋራ እንዴት ሊሆን ነው? አላህ ይጠብቀን፡፡

2 በፍላጐትና የኒያ ማጋራት፡-

ማለት በሚሰራው ስራ ዱንያን ወይም ልክ እንደሙናፊቆች ሙሉ በሙሉ ለይዩልኝና ይስሙልኝ ብቻ መስራትና የአላህን ፊትና የአኺራን ሀገር አለመፈለግ፡፡ ይህ ትልቁ ሽርክ ነው፡፡  አላህ እንዲህ ይላል፦

‹‹ቅርቢቱን ሕይወትና ጌጧን የሚሹ የሆኑትን ሰዎች ሥራዎቻቸውን (ምንዳዋን) በእርሷ ውስጥ ወደነሱ እንሞላላቸዋለን፡፡ እነሱም በርሷ ውስጥ ምንም አይጎድልባቸውም፡፡ እነዚያ እነርሱ በመጨረሻይቱ ዓለም ለእነርሱ ከእሳት በቀር የሌላቸው ናቸው፡፡ የሠሩትም ሥራ በርሷ ውስጥ ተበላሸ፡፡ (በቅርቢቱ ዓለም) ይሠሩት የነበሩትም በጎ ሥራ ብልሹ ነው፡፡›› (ሁድ 15-16)

ይህ የሽርክ አይነት ስውር የሆነና አደገኝነቱ የከፋ ነው፡፡

3     በትዕዛዝ ማጋራት፡-

 አንድ ሰውን አላህ የፈቀደውን ሲከለክልና አላህ የከለከለውን ሲፈቅድ መታዘዝ እንዲሁም ሰዎች ሀላልና ሀራም ማድረግ እንደሚችሉና በዚህ ላይ እነሱን መታዘዝ እንደሚቻል ማመን ማለት ነው::ይህ ተግባር እስላምናን ሀይማኖት እንደሚጋጭ እያወቀ ይህን የሚያደርግን የሚታዘዝ አዛዡን ሰው የአላህ ቢጤ አድርጓል ማለት ነው፡፡ በመሆኑም ትልቁን ሽርክ ፈፃሚ ነው፡፡አላህ እንዲህ ይላል፦

 اتَّخَذُوا أَحْبَارَهُمْ وَرُهْبَانَهُمْ أَرْبَابًا مِّن دُونِ اللَّهِ وَالْمَسِيحَ ابْنَ مَرْيَمَ وَمَا أُمِرُوا إِلَّا لِيَعْبُدُوا إِلَهًا وَاحِدًا لَّا إِلَهَ إِلَّا هُوَ سُبْحَانَهُ عَمَّا يُشْرِكُونَ

‹‹ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የሌለውን አንድን አምላክ ሊገዙ እንጂ ያልታዘዙ ሲኾኑ ሊቃውንቶቻቸውንና መነኮሳታቸውን፣ የመርየምን ልጅ አልመሲሕንም ከአላህ ሌላ አማልክት አድርገው ያዙ፡፡ ከሚያጋሩት ሁሉ የጠራ ነው፡፡›› (አል ተውባህ 31)

 የዚህ አንቀፅ ትርጓሜ፡- ዑለማዎችንና ባህታዊያንን በኃጢአት መታዘዝ ማለት እንጂ እነርሱን መለመን ማለት እንዳልሆነ ነብዩ አብራርተዋል፡፡ ዓዲይ ኢብኑ ሃቲም ለነቢዩ “እኛኮ ስናመልካቸው አልነበረም” ሲላቸው እንዲህ በማለት እነርሱን ማምለክ ማለት የአላህን ህግ በመቀየር በወንጀል ሲያዙ ትዕዛዛቸውን መቀበል ማለት እንደሆነ ገለፁለት “አላህ ሀላል ያደረገውን ሲከለክሏችሁ እናንተ ትታዘዟቸው አልነበረምን? አላህ እርም ያደረገውን ደግሞ ሲፈቅዱ እነርሱን በመታዘዝ የተፈቀደ ታደርጉ አልነበርን? “እንዴታ” ሲላቸው እነርሱን ማምለክ ማለት ይኸው ነው አሉት፡፡››

4. በውዴታ ማጋራት፡-

 ማክበር፣ ማላቅ፣መዋረድና መተናነስን የሚያስከትል ለአላህ እንጂ የማይገባን ውዴታ ለፍጡር ማድረግ ትልቁ ሽርክ ነው፡፡  አላህ እንዲህ ይላል፦

https://t.me/sunah123
وَمِنَ النَّاسِ مَن يَتَّخِذُ مِن دُونِ اللَّهِ أَندَادًا يُحِبُّونَهُمْ كَحُبِّ اللَّهِ وَالَّذِينَ آمَنُوا أَشَدُّ حُبًّا لِّلَّهِ

‹‹ከሰዎችም ከአላህ ሌላ ባለንጣዎችን (ጣዖታትን) አላህን እንደሚወዱ የሚወዷቸው ኾነው የሚይዙ አልሉ፡፡ እነዚያ ያመኑትም አላህን በመውደድ (ከነርሱ) ይበልጥ የበረቱ ናቸው፡፡›› (አል በቀራህ 165)

2ኛ. ሁለተኛው የሽርክ አይነት ትንሹ ሽርክ ነው፦

 ትንሹ ሽርክ ማለት ማንኛውም ወደ ትልቁ ሽርክ መዳረሻ መንገድ የሆነ ወይም ደግሞ ሸሪዓዊ ጥቅሶች ላይ ሽርክ ተብሎ የተሰየመና ነገር ግን የትልቁን ሽርክ መጠን ያልደረሰ ሲሆን ነው
ይህ ሽርክ በስራዎች ሁኔታና በምላስ ንግግር የሚከሰት ሲሆን ሸሪዓዊ ብይኑ ይህን የሰራ ሰው ልክ እንደ ትላልቅ ወንጀሎች ፈፃሚ በአላህ ፈላጐት ስር ይሆናል፡፡  ለትንሹ ሽርክ ምሳሌ ሊሆኑ ከሚችሉ ነገሮች፦

ሀ. ትንሹ “ሪያእ” (ለይዩልኝ መስራት)፡-

ለዚህ ማስረጃው ኢማም አህመድና ሌሎችም ከነብዩ የዘገቡት የሚከተለው ሀዲስ ነው።‹‹እናንተ ላይ ከምፈራው ሁሉ የከፋው ትንሹ ሽርክነው፡ ሰሃቦችም “ትንሹ ሽርክ ምንድ ነው?” ሲሉ ነብዩም “መልካም ስራን ለይዩልኝ መስራት ነው”
 የትንሳኤው እለት አላህ ለሰዎች ምንዳን ሲሰጥ ለይዩልኝ ሚሰሩትን እንዲህ ይላቸዋል “በዱንያ ላይ እንዲያዩላችሁ የምታደርጉት የነበሩ ሰዎች ዘንድ ሂዱና እስቲ የሚሰጡዋችሁ ምንዳ ካለ እዩ፡፡”

ለ. “በአላህና በአንተ ፍላጐት…” የሚለው አባባል፡-

አቡ ዳውድ እንደዘገቡት ነብዩ እንዲህ ብለዋል ‹‹በአላህና በእገሌ ፍላጎት (ይህ ጉዳይ ተሳካልኝ) አትበሉ:: ነገር ግን ከአላህ ፍላጎት በኋላ እገሌም ስለሻው…… ማለት ትችላላችሁ”

መ. “አላህና እገሌ ባይኖሩ ኖሮ… ”

ወይም “ውሻ ባይኖር ሌባ ገብቶ ነበር” የመሳሰሉ ቃላቶችን መጠቀም፡፡ አቡ ሃቲም ተፍሲር መፅሐፋቸው ላይ እንደዘገቡት ኢብኑ ዓባስ ስለዚህ አንቀፅ ትርጉም እንዲህ ብለዋል ፡-

فَلَا تَجْعَلُوا لِلَّهِ أَندَادًا وَأَنتُمْ تَعْلَمُونَ

 ‹‹ቢጤ ማለት ተጋሪ ማለት ነው፡፡ የጉንዳን ኮቴ በሌሊት ጨለማና በልሙጥ ጥቁር ድንጋይ ላይ ስውር ከሚሆነው በላይ ስውር ነው፡፡
ለምሳሌ በአላህ በህይወትህና በህይወቴ እምላለሁ ፣ ውሻ ባይኖር ሌባ ይገባ ነበር ፣ ቤት ውስጥ ዶሮ ባይኖር ሌባ ይገባ ነበር ፣ በአላህና በአንተ ፍላጐት ፣ አላህና አንተ ባትኖሩ ኖሮ የመሳሰሉትን ቃላት መጠቀም ማለት ነው፡፡ “እገሌ” የገባበት ሁሉ ሽርክ ነው፡፡ ብለዋል››

https://t.me/sunah123
🔵ምዝገባ ተጀመረ
የአዳሪ ቁርኣን ሂፍዝ ለወንዶች

حفظ القرآن الكريم على منهج السلف الصالح !!

https://t.me/medresetulislah
ከ500 ተከታይ በላይ ቻናል ያላቹ
ቻናላቹን ማሳደግ ምፈልጉ ከታች ባለው Username አናግሩኝ👇👇👇
@Mujahid_Selefi
Forwarded from KHALID_MUSTEFA
የዓሹራ ቀን አጿጿም እና በዕለቱ የሚከሰቱ ቢድዓዎች
—————
እንደሚታወቀው የዓሹራ ቀን ፆም ማለትም ሙሀረም 10ኛውን ቀን መፆም ከታላላቅ ሶናዎች ነው። ነቢዩ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል:-

(أَفْضَلُ الصِّيَامِ بَعْدَ رَمَضَانَ شَهْرُ اللَّهِ الْمُحَرَّمُ) رواه مسلم

“ከረመዷን በኋላ በላጩ ፆም የሙሀረም ወር ፆም ነው።” [ሙስሊም 1163 ዘግበውታል።]
ይህ ፆም የረመዷን ወር ከመደንገጉ በፊት ግዴታ ነበርም ተብሏል።

የሚፆምበትን ምክንያት:-
በመሰረቱ እንደ ሙስሊም ማንኛውም በቁርኣን እና በሶሂህ ሀዲስ የመጣን መልካም ስራ፣ ትእዛዝም ይሁን ክልከላ ምክንያቱን አወቅነውም አላወቅነውም መተግበርና መቀበል ግዴታችን ነው። በግልፅ ማስረጃ የመጣ ነገር እስከሆነ ድረስ መተግበር ነው።

የዓሹራ ፆም ምክንያት አለው። በሚከተለው ሀዲስም ተብራርቷል:-

عن ابن عباس ((قَدِمَ النَّبِيُّ -صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ- المَدِينَةَ فَرَأَى الْيَهُودَ تَصُومُ يَوْمَ عَاشُورَاءَ فَقَالَ مَا هَذَا؟ قَالُوا: هَذَا يَوْمٌ صَالِحٌ، هَذَا يَوْمٌ نَجَّى اللَّهُ بَنِي إِسْرَائِيلَ مِنْ عَدُوِّهِمْ فَصَامَهُ مُوسَى، قَالَ فَأَنَا أَحَقُّ بِمُوسَى مِنْكُمْ فَصَامَهُ وَأَمَرَ بِصِيَامِهِ)).  في صحيح البخاري

ከኢብኑ ዐባስ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ:- “ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ወደ መዲና በገቡ ጊዜ አይሁዶች የዓሹራን ቀን (ሙሀረም 10ኛውን ቀን) ሲፆሙ አዩዋቸው፣ ነቢዩም ለአይሁዶች ይህ ምትፆሙት ምንድነው? አሉዋቸው፣ ይህ ምርጥ ቀን ነው፣ ይህ ቀን አላህ በኒ ኢስራኢሎችን ከጠላታቸው የገላገለበት ቀን ነው፣ ሙሳ ፆሞታል። አሉ፣ ነቢዩም እኔ ለሙሳ ከናንተ የበለጠ የቀረብኩኝ ነኝ ብለው ፆሙት፣ እንዲፆምም አዘዙ።” [ቡኻሪ ዘግበውታል።]

አጿጿሙን በተመለከተ:-
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል:-

( لَئِنْ بَقِيتُ إِلَى قَابِلٍ لَأَصُومَنَّ التَّاسِعَ ) ، أخرجه مسلم

“ወደፊት ከቆየሁ ዘጠነኛውንም (ቀን) እፆማለሁ።” [ሙስሊም ዘግበውታል።]
በዚህ መሰረት ዘጠነኛውንና አስረኛውን ቀን እንፆማለን ማለት ነው። ይህም ከምንም አይነት ጭቅጭቅ ነፃ የሆነው አጿጿም ነው።

10ኛው እና 11ኛው???
ዘጠነኛው ቀን ያመለጠው 10ኛውን እና 11ኛውን መፆሙን በተመለከተ ግን የተወሰኑ ጭቅጭቆች አሉበት።
እንደ ኢብኑል ቀይም (ረሂመሁላህ) ያሉ ሊቃውንቶች 10 እና 11 መፆም ይቻላል ሲሉ የሚከተለውን ሀዲስ ማስረጃ ያደርጋሉ:-

(صُومُوا يَوْمَ عَاشُورَاءَ ، وَخَالِفُوا فِيهِ الْيَهُودَ ، صُومُوا قَبْلَهُ يَوْمًا أَوْ بَعْدَهُ يَوْمًا). رواه أحمد في مسنده

“የዓሹራን ቀን ፁሙ፣ አይሁዶችን በመቃራንም ከፊቱ ወይም ከኋላው አንድ ቀን ፁሙ።” ኢማሙ አሕመድ በሙስነዳቸው የዘገቡት ሲሆን አልባኒን ጨምሮ ሌሎችም በርካታ ዓሊሞች ዷዒፍ ነው ብለውታል።

የዚህን ሀዲስ ዷዒፍነት ያመኑ ዑለማዎች ሆነው ዘጠነኛው ቀን ያመለጠው ሰው 11ኛውን ለመፆሙ ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) "በሚቀጥለው ካደረሰኝ 9ኛውን እፆማለሁ።” ማለታቸው፣ ምክንያቱ ለ11ኛው ቀንም ይሆናል። ይላሉ፣ 9ኛውን ቀን እፆም ነበር ያሉበት ምክንያቱ አይሁዶችን ለመቃረን ነውና። 9ኛውን እና 10ኛውን ቀን ብቻ መፆም ነው፣ 9ኛው ካመለጠ ደግሞ 10ኛውን ብቻ መፆም ነው እንጂ 11ኛው የለም የሚሉት ደግሞ፣ "9ኛውን ቀን እፆም ነበር" ያሉበት ምክንያት አይሁዶችን ለመቃረን ቢሆንም  11ኛውን ለመፆም ማስረጃ አይሆንም ብለዋል።

1ኛ, ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) በወቅቱ 10ኛውን ፆመው ነው ያቆሙት እንጂ 11ኛውን አልፆሙም።

2ኛ, በሚቀጥለው ካደረሰኝ 9ኛውን ወይም 11ኛውን እፆማለሁ ሳይሆን ያሉት 9ኛውን ብቻ ነው ከ10ኛው ጨምረው እንደሚፆሙት የተናገሩት። በነዚህ ምክንያቶች አንድ ሰው 9ኛው ካመለጠው 10ኛውን ብቻ ነው የሚፆመው ይላሉ።

እንደ ማስረጃው አመዛኝነት ግን ከጭቅጭቁ ለመውጣትም በተቻለ መጠን 9ኛው እንዳያመልጥ ጥረት አድርጎ 9 እና 10 መፆም፣ 9ኛው ካመለጠ ግን ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ንም 9ኛው አምልጧቸው 10ኛውን ብቻ ስለ ፆሙ 10ኛውን ብቻ መፆም ነው። ወላሁ አዕለም!!

የዓሹራ ቀን ቢድዓዎች።
ኢብኑል ቀይም (ረሂመሁላህ) እንዲህ ብለዋል:-
“መኳኳልን እና መጋጌጥን፣ በቀኑ ለየት ያለ ሶላትን መስገድም ሆነ ሌሎች ለየት ያሉ ተግባሮችን በላጭነት አስመልክተው የመጡ ሀዲሶች በጠቅላላ ዷዒፍ ናቸው። የዚያን ቀን ከመፆም ውጭ ሌሎችን ነገሮች የሚጠቁም አንድም ትክክለኛ ከነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የተረጋገጠ ሀዲስ የለም። "የዓሹራ ቀን ባለው አቅም ሰፋ አድርጎ ያመቻቸ ሰው፣ የሌሎችንም አመታት አላህ ሰፋ ያድርግለት።” የሚለው ሀዲስ ኢማሙ አሕመድ ሶሂህ አይደለም ብለውታል። የዚያን ቀን እለቱን አስመልክቶ መኳኳል፣ መቀባባት፣ ሽቶ መጠቀም፣ ውሸታሞች ያስቀመጡትና ሌላውም ተቀብሏቸው ከሀዘን ወደ ደስታ የሽግግር ቀን ብለው መጋጌጫ አድርገው የያዙት ነው። ይህን ያደረጉት ሙብተዲዕና ከአህሉ ሱንና ያፈነገጡ ጭፍሮች ናቸው። አህሉ ሱንናዎች ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ያዘዙበትን የሚፈፅሙና ሸይጧን ያዘዘበትን ቢድዐ የሚጠነቀቁ (የሚርቁ) ናቸው።” [አልመናር አልሙነይፍ ፊ ሶሂሂ ወዷዒፍ 89]

የሳዑዲ ቋሚ የፈትዋ ኮሚቴም "ይህን ቀን በመጋጌጥም ሆነ በምግብ ለየት ማድረግ አይፈቀድም። እንዲሁም ሺዓዎች እንደሚያደርጉትም የሀዘን ቀን አድርጎ ራስን በስለት መሰል ነገር መጉዳት አይፈቀድም። በዚያን ቀንም ሆነ በሌሎች ቀኖች ፋጢማን መለመን አይፈቀድም፣ በተውበት እንጂ አላህ ከማይምረው ከትልቁ ሺርክም ነው። ” ብሏል። [ቋሚ የፈትዋ ኮሚቴ ቁ. 22177]

ሸይኽ ረቢዕ ቢን ሃዲ ዑመይር አልመድኸሊ (ረሂመሁላህ) በዚያ ቀን ለዕለቱ ብሎ ለየት ያለ ምግብ አዘጋጅቶ መብላት ይፈቀዳል ወይ? ተብለው ተጠይቀው፣ ሲመልሱ:- "በዓሹራ ለየት ያለ ነገር መዘጋጀት አለበት፣ ወደ አላህ ያቃርባል የሚል እምነት ኖሯቸው ከሆነ የሰሩት ይህ ቢድዓ ነው። ባረከላሁ ፊኩም።” ብለዋል። በሀገራችን በዚህ ቀን የተለያዩ ቢድዐዎች በተለይ ሱፊዮች ዘንድ ይፈፀማልና በዚህ ቀን ከፆም ውጪ ምንም አይነት ለየት ያለ ተግባር እንደሌለ አውቀን ከተለያዩ ቢድዐዎች ተጠንቅቀን ልናስጠነቅቅ ይገባል!!።
✍🏻ኢብን ሽፋ (t.me/ibnshifa)
የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa

Follow Ibn Shifa's WhatsApp Channel: ⤵️⤵️ https://whatsapp.com/channel/0029VbAU7moHgZWXXXnNiL3f
💯2
🤝4
اَلسَلامُ عَلَيْكُم وَرَحْمَةُ اَللهِ وَبَرَكاتُهُ‎