Bilal Gallery
3.88K subscribers
270 photos
9 videos
3 files
259 links
መቼም ሰው ነኝና ስህተት አይታጣብኝም ስህተት ካያችሁ በዚህ @Amir8979 አድርሱኝ ከስህተቴ ሁሌም ተመላሽ ነኝ! "ጥፋቴን በነገረኝ ሙስሊም ሁሉ የአላህ እዝነት ይውረድ"
Download Telegram
Bilal Gallery
Photo
8).ጁወይሪያህ ቢንት አል ሀሪስሀሪስ፦


✅ረሱል(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ጁወይሪያህን
በማግባታቸው ወደ 700 የሚጠጉ ከሀዲያን እስልምናን
ተቀብለዋል። ሙሉ ታሪኩን ያንብቡት ይገረማሉ።
ሙሉ ስሟ ጁወይሪያህ ቢንት አል ሀሪስ ኢብን አቡ ዲራር
ኢብን ለቢብ አል ኹዛኢያ ነው። ጁወይሪያህ(ረ.ዐ) ከጎሳዎ
መሳፍንት ወገን የምትወደድና ቆንጆ ሴት ስትሆን
በሙስሊሞች እጅ ስትገባ እድሜዋ 20 ቤቱ ውስጥ
ነበር። በኑ ሙስጠሊቆች ከመዲና ራቅ ብለው የሚገኙ
ህዝቦች ናቸው። እነዚህ ህዝቦች ረሱል(ሰለላሁ አለይሂ
ወሰለም) እና ሰሀቦችን ሊያጠቁ እንደሆኑ ለረሱል(ሰለላሁ
አለይሂ ወሰለም) ዜናው ይደርሳቸዋል። ይህን ጊዜ
ብልሀተኛው ነቢይ ሙሀመድ(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)
ሳንቀደም እንቅደም በማለት ወታደር ይዘው ከበቧቸው።
ነገራቸው ከዛም ጦርነት ተከፈተ። ለሰዐአታት ያክል
ከተዋጉ ቡኃላ ጦርነቱ በሙስሊሞች ድል ይጠናቀቃል።
ብዙ የጦርነት መሳሪያዎች እና 350 የሚጠጉ ምርኮኛ
ወታደሮች አንዳንድ ኡለማዎች 700 ነው ይላሉ፣ ወርቅ፣
ጨርቅ ይህን ይዘው ተመለሱ። ይህን የውጊያ ውርስ
ለረሱል(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ይሰጧቸዋል። እሳቸው
ሁሉንም ለሰሀቦቻቸው አከፋፈሉት። ጁወይርይ(ረ.ዐ)
ከተማረኩት ምርኮኞች አንዷ ናት። ምርኮ ለተዋጊዎች
ሲከፋፈል ጁወይሪያ ለሳቢት ኢብን ቀይስ ደረሳት።
ጁወይሪያ(ረ.ዐ) አቧቷም ሆነ ባሏ ትልልቅ ነገስታት ነበሩ።
በምቾት ያደገች ናት። ሳቢት ደግሞ የገጠር ልጅ፣ ደሀ
ነው። ከሱ ጋር መሆንን አልወደድችም። ሳቢት ደግሞ ነፃ
አውጣኝ ስትለው 9 እቁያ ወርቅ ጠየቃት። ከዛም ወደ
ረሱል(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ዘንድ ሄዳ ያ ረሱለላህ!
እኔ ምርኮኛ ነኝ። ምርኮ ሲከፋፈል እጣ የደረሰኝ ደግሞ
ከሳቢት ኢብን ቀይስ ነው። እኔ ደግሞ ከእሱ ጋር መሆንን
አልፈለኩም። ነፃ በለይ ስለው 9 እቁያ ጠየቀኝ እኔ
ምርኮኛ ነኝ ይሄ ሁሉ ገንዘብ የለኝም በሀገሬ ቢሆን
እሰጠው ነበር ብላ አቤቱታ አቀረበች። ስምሽ ማነው
አሏት ጁወይሪያ ቢንት አል ሀሪስ አለች። ተገርመውም
የአል ሀሪስ ልጅ ነሽ አሏት። አዎ አለች። የተገረሙት
የንጉስ ልጅ ስለነበረች ነው። ባልሽስ እገሌ ብላ ነገረቻቸው
እሱም ንጉስ ነበር በጦርነቱ ሞቷል። አስገራሚው ታሪክ
እዚህ ጋር ይጀመራል። የረሱል(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)
ብዙ ሴት ማግባት የሚያንገሸግሻቹ እውነታውን
ተመልከቱ። ነብዩ(ሰለላሁ አለይሁ ወሰለም) እንዲህ አሏት
ከዚህ የተሻለ ባቀርብልሽ አትቀበይኝም? አሏት እሷም
በጉጉት ምንድን ነው እርሱ የአላህ መልእክተኛ አለች?
“እኔ ነፃ እንድትሆኚ ክፍያውን እፈፅማለው ከዚያም
አገባሻለው አሏት” ጁወይሪያ የቀረበላት ምርጫ በጣም
ስላስደሰታት ያለማቅማማት እሺ ነው ያለችው። በዚህ
ሁኔታ የረሱል(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሚስት ሆነች።
በማግስቱ ሰሀቦች ተሰባስበው ጅወይሪያ የረሱል(ሰለላሁ
አለይሂ ወሰለም) ሚስት ሆነች። የጁወይሪያ ቤተሰቦች
እኮ የረሱል(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) አማች ሆኑ ማለት
ነው። አዎ ብለው ተስማሙ። እንዴት እኛ የረሱል(ሰለላሁ
አለይሂ ወሰለም) አማቾች ምርኮኛ አርገን እንይዛለን አሉ?
ይህማ አይሆንም አሉ። ለነቢያችን(ሰለላሁ አለይሂ
ወሰለም) ክብር ስንል የእሳቸውን አማቾች(የእሷን
ቤተሰቦች) ነፃ አንልም ተባባሉ? እሺ ብለው ተስማሙ
ትላንት ባርያ የነበሩ እንደፈለጉ መሸጥ መለወጥ
የሚችሏቸውን ሰዎች ለረሱል(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)
ክብር ሲሉ ነፃ አሏቸው። ሱብሀነላህ የሚገርም ነው። እነዛ
ነፃ የተባሉት ሰዎች ደግሞ ይሰበሰቡና እናንተ ሰዎች ከእኛ
መሀል ነብያቸው ስላገባ ለሱ ክብር ሲሉ ነፃ አሉን። መዲና
ብንሄድ ኖሮ እንሸጥ ነበር። እኛስ ለልጃችን ስንል ለአላህ
ስንል ወደ እስልምና ለምን አንገባም? ብለው ሁሉም ወደ
ረሱል(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) በመሄድ እስልምና ገቡ።
አይሻ(ረ.ዐ) እንዲህ ትላለች:- ረሱል(ሰለላሁ አለይሂ
ወሰለም) ጁወይሪያን(ረ.ዐ) የመጀመርያ ቀን ወደ ቤት
ይዘዋት ሲገቡ በጣም ቀንቼ ነበር። ነገር ግን በእሷ
ምክንያት 700 ወጣቶች መስለማቸውን ስሰማ እየሮጥኩ
ሄድኩና እቅፍ አድርጌ “ያ ጁወይሪያ ከረሱል(ሰለላሁ
አለይሂ ወሰለም) ሚስቶች እንዳንቺ የተባረከ አላየሁም።
ምክንያቱም በአንቺ ምክንያት በመቶ የሚቆጠሩ ሰዎች
ወደ እስልምና ገብተዋል።” እናም ወደድኳት አለች። አያቹ
አደል የመጋባቱን ጥበብ። እንደው ጠላቶች
የሚያቅጥላቸው ለምን 9 ለምን 13 አገቡ አደል የሚሉት
ለእንደዚህ አላማ 1000 ቢያገቡ? ከ 1000 የጠላት
(ቀቢላ) ጋር ቢታረቁ ነውር ነው? ነውር አደለም። ነገር ግን
ረሱል(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ያገቧቸው ሚስቶች አንዷ
ልጆች ያሏት፣ አንዷ ሁለቴ የትፈታች፣ አንዷ ባሏ
የሞተባት፣ አንዷ በሽተኛ፣ አንዷ ትልቅ ሴት ነበሩ።
https://t.me/sunah123
❤1
|| ተጣራ ... ስበክ !!

በበጎ ማዘዙ መሥፈርቱን ጠብቆ
ከክፉ መከልከል ገደቦቹን አውቆ

ፍጹም አይቀንስም አንዲትንም ጉርሻ
አሏህ ከጻፈልን ከሪዝቃችን  ድርሻ

ማቅረብም አይችልም አንዲትን ደቂቃ
የተጻፈው እድሜ ደርሶ እስኪያበቃ

እናልህ አንበሳው በርትተህ ተጣራ
እድፏ ምድር ከሺርክ እስትትጠራ

ዒባዳ  እስኪሰጥ ለጌታችን ብቻ

አንድም አታገኝም ከርሱ ሚሆን አቻ

ሱናዋ እስትትሆን የሰው ልጆች መሪ
ከጥላዋ በታች ሁሉ ነፍሶች ኗሪ ....

t.me/Abdul_halim_ibnu_shayk
t.me/Abdul_halim_ibnu_shayk
➛➛➛➛➛➛➛
✨🌙 ۞ የቁርአን ተፍሲር ۞ 🌙✨


📖 ╭─❖ በሸይኽ አቡዘር ሀሰን ( አቡ ጦልሃ ) حَفِظَهُ الله ❖─╮
🔗 https://t.me/TefsirALQuran114⁠�
╰────────────────────────────╯

📖 ╭─❖ በኡስታዝ ባህሩ ተካ አቡ (ዑበይዳህ) حَفِظَهُ الله ❖─╮
🔗 https://t.me/amir897977⁠�
╰────────────────────────────╯
➛➛➛➛➛➛➛
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
👍3💯2
♦️ «ዙል-ሒጀህ ነገ መሆኑ ተረጋገጠ!»

— በመሆኑም ነገ ሰኞ (ግንቦት 10) ዙል-ሒጀህ አንድ ብሎ ይጀምራል። የፊታችን ማክሰኞ ሳምንት የውሙል-ዐረፈህ ሲሆን የፊታችን ኦሮብ ሳምንት ደሞ ዒድ አል-አድሓ ሆኗ ይውላል።

— አ'ሏሁ ተዓላ እነዚህ 10 ቀናት ቦቶ ሰጥቶ (በአስሮቹ ሌሊቶችም። ||  وَلَيَالٍ عَشْرٍ) እያለ ምሎባቸዋል። ዒባዳዎችን በተቻለን ያህል እናብዛ።

|| የመገናኛው ግሩፕ፦
t.me/Multeqa_Ahlissuneh
t.me/Multeqa_Ahlissuneh
🔖አስርቱ ወርቃማ የዙል-ሒጃ ቀናት!!


➠አላህ ከቀናት ሁሉ ያላቃቸው ቀናቶች አስሩ የዙልሂጃ ቀናት ናቸው።

🌴ጃቢር ኢብኑ አብዲላህ ባስተላለፉት ሀዲስ የአላህ መልዕክተኛ ( እንዲህ ብለዋል:-"ከዱንያ ቀናት ሁሉ ብልጫ ያላቸው አስርቱ የዙልሂጃ ቀናት ናቸው።
📌ከተከበሩ ወራቶች መካከል አንዱ የሀጅ ወር የሚሆነው በዙልሂጃ ወር ነው።
📌ከቀናት ሁሉ አላህ ዘንድ የተወደዱ ደግሞ አስሩ የዙልሂጃ ቀናት ናቸው።
📌እንዲሁም ከዱንያ ቀናት ሁሉ በላጭ ናቸው።
🍁ከኢብኑ አባስ (ረድየላሁዐንሁ) በተዘገበው ሀዲስ የአላህ መልእክተኛ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል ፦
"በነዚህ አስር ቀናቶች ውስጥ ከሚፈፀሙ መልካም ስራዎች በበለጠ መልካም ስራዎች አላህ ዘንድ የተወደዱ የሚሆንባቸው ቀናት የሉም ፤በአላህ ከሚደረግ ጅሀድም ጭምር ተብለው ሲጠየቁ። እሳቸውም፦ እራሱን እና ንብረቱን ይዞ ወጥቶ ምንም ያልተመለሰ ሰው ሲቀር ጅሀድም ከዚህ አይበልጥም አሉ።
[📚 ቡኻሪ ዘግበውታል]

📝በእነዚህ ቀናቶች ትኩረት ልንሰጣቸው ከሚገቡ የዒባዳ አይነቶች መካከል የሚከተሉት ይገኛሉ፦

❶ ፆም


ፆም ከስራዎች ሀሉ በላጭ ነውና በእነዚህ ቀናት መፆም እጅግ የተወደደ ተግባር ነው።

➣ከአቢ ቀታዳህ እንደተዘገበው የአላህ መልእክተኛ(ﷺ) ስለ ዐረፋ ቀን ፆም ተጠየቁ። እንዲህም አሉ፡-
ﻳﻜﻔِّﺮ ﺍﻟﺴﻨﺔ ﺍﻟﻤﺎﺿﻴﺔ ﻭﺍﻟﺒﺎﻗﻴﺔ
“ያለፈውንና የሚመጣውን አመት ወንጀል
ያብሳል።”

[📚ኢማም ሙስሊም እና አህመድ ዘግበውታል]

❷ ዚክሮችን ማብዛት


➢ ዐብዱላህ ኢብኑ ዑመር ባስተላለፉት ሀዲስ ነብዩ(ﷺ)እንዲህ ብለዋል፦

«ከእነዚህ አስር ቀናት በበለጠ አላህ ዘንድ ታላቅ የሆኑና መልካም ስራ እጅግ የተወደደባቸው ቀናት የሉም፤ ስለዚህ ተህሊል ተክቢር እና ተህሚድ አብዙ»

[📚አል ኢማም አህመድ ዘግበውታል።]

#ይህን_ተክቢራ_ከዙልሒጃ_1_ጀምሮ_እስከ_አያመ_ተሽሪቅ (ከዒድ በኋላ ያሉትን 3 ቀናት ጨምሮ) ማለቱ ሱና በመሆኑ ቤተሰቦቻችንን በዚህ ላይ በማነሳሳት ቤታችንን በተክቢራ እናድምቅ።
~የተክቢራ አደራረጉም
"አሏሁ አክበር፤ አሏሁ አክበር፤ አሏሁ አክበር፤ ላኢላሃ ኢለሏህ አሏሁ አክበር ወሊላሂል ሐምድ"......

❹ ሀጅና ዑምራ


~በነዚህ ቀናቶች ከሚደረጉ መልካም ስራዎች ሌላው ሀጅ ማድረግ ይገኝበታል በእነዚህ አስር ቀናት የሀጅ ኢባዳ ላይ ተገኝቶ በተገቢው መንገድ ከፈፀመው በአላህ ፈቃድ ከተከታዩ የአላህ መልእክተኛﷺ ብስራት ድርሻ ይኖረዋል።

➣ከአቡ ሁረይራ ረድየሏሁአንሁ በተላለፈው ሀዲስ የአላህ መልዕክተኛ (ﷺ)እንዲህ ብለዋል ፦
"ከወንጀል የራቀና ተቀባይነት ያለው ሀጅ (አል ሃጅ አል መብሩር)ምንዳው ጀነት እንጂ ሌላ አይደለም።"ብለዋል
[📚ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]

🍁❹ ኡድሂያ


ከነዚህ አስር ቀናት ከሚሰሩ መልካም ስራዎች ሌላኛው ኡድሂያ በማረድ ወደ አላህ መቃረብ ነው።
ኡድሂያ በጣም ከጠነከሩ የነብዩ ﷺ ሱናዎች መካከል አንዱ ነው። የነብዩ ኢብራሂም (ዓለይሂ ሰላም) ሱና ህያው ከማድረግ በተጨማሪ ለድሆችና ችግረኞች መድረስ ነው።

📍የመልካም ስራ በሮች ብዙ ናቸው እና የቻልነውን ሁሉ በመፈፀም ወደ አላህ መቃረብ ይገባናል።

💫 የታሰረን ወይም የታመመን ሰው መጠየቅ፤ ዝምድናን መቀጠል፤ በመልካም ማዘዝ ከመጥፎ መከልከል፤ የተጣላን ማስታረቅ ፤ ሶደቃ ማብዛት፤ ሱና ሶላቶችን ማብዛት፤ ቁርአን መቅራት ዚክር ማብዛት ፤ዱዓ ማብዛት ያስፈልጋል።

🤲"አላህ በነዚህ ወርቃማ ጊዜያት ከሚጠቀሙና አላህ ዘንድ መልካም ምንዳን ከሚያገኙ ጠንካራና ብልህ ባሮች ያድርገን።"

t.me/Mehfuza_os99
t.me/Mehfuza_os99
❤1
📢 ልዩ የደዕዋ ፕሮግራም በቴሌግራም!

— እነሆ ነገ ጁሙዓ ምሽት ግንቦት -𝟏𝟒- 𝟐𝟎𝟏𝟖 «በወሎ ዩኒቨር ሲቲ ሰለፍይ ተማሪዎች ግሩፕ » ልዩ የደዕዋ ፕሮግራም ተዘጋጅቷልና እዳያመልጣችሁ !

💺ተጋባዥ እንግዶቻችን፦

🎙ሸይኽ አቡ ዘር ሐሰን ' ኮምቦልቻ '
           -ሐፊዞሁ'ሏህ-


● ርእስ፦ አደገኛው የተክፊሮች መንሀጅ !

🎙ኡስታዝ አቡ ሙዓዝ ' ደሴ '
      -ሐፊዞሁ'ሏህ-

● ርእስ፦  የዘቀጠው የሙመይዐዎች መንሀጅ ! 

|| ኢንሻ አሏህ  ቆንጆ  ምሽት ይኖረናል

⏰ ሰዓት ፦ ከምሽቱ በኢትዮ 2:20 በሳዑድ 8:30 በኢማራት 9:20 አይለፋችሁ !

|| የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/Wollo_un_selefiy_stud
https://t.me/Wollo_un_selefiy_stud
👍4
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🔴 | በመቀጠል ...

🎙 ሸይኽ አቡ ዘር ሐሰን - ሐፊዞሁ'ሏህ-

● ርእስ፦ አደገኛው የተክፊሮች መንሀጅ !

♦️| ሊንኩን በመንካት ተከታተሉ፦👇

https://t.me/Wollo_un_selefiy_stud?videochat
🕌 የመስጂድ ምርቃት
እና የኪታብ ኮርስ በቡታጅራ


እነሆ ነገ ቅዳሜ (ዙልሒጃ 6) ጠዋት ጀምሮ ለተከታታይ 2ቀናት የሚቆይ ለአይን የሚማርክ፣ ለጆሮ ቀለብ የሚሆንና ቀልብን በኢማን የሚያድስ ልዩ መንፈሳዊ ድግስ! በቡታጅራ ከተማ የሚገኘው የሰለፊያ መስጂድ ግንባታው ተጠናቆ ለምርቃት በቅቷል። በዚህ ታሪካዊና በበረከት የተሞላ እለት የዕውቀት ብርሃን ሊቀስሙ፣ ልቦናዎትን በቁርአንና በሀዲስ እውቀት ሊያርሱ ተጋብዘዋል።

♦️የፕሮግራሙ ልዩ ድምቀቶች
1/ ታላቁ የምርቃት ስነ-ስርዓት
የአላህ ቤት በደስታና በዚክር ሲመረቅ የታላላቅ ኡስታዞች የምክር ትውስታዎች ተሳታፊ ይሁኑ!

2/ ልዩ የ2 ቀናት የኪታብ ኮርስ በዕውቀታቸውና በዳዕዋቸው ስመ-ጥር የሆኑት ውዱ ዓሊም ሸይኽ አብዱልሐሚድ አል_ለተሚ በራሳቸው እጅ የተፃፈውን "ኣላኡላህ ፊ መካነቲ ላኢላሀኢለላህ" ኪታብ ኮርስ የሚሰጡበት የዕውቀት ማዕድ።

📙ኪታቡ፦ ኣላኡላህ ፊ መካነቲ ላኢላሀኢለላህ
✍️ፀሀፊ፦ ሸይኽ አብዱልሐሚድ አል_ለተሚይ
🎙አቅራቢ፦ በሸይኽ አብዱልሐሚድ ይቀርባል
⏰ሰዓቱ፦ ቅዳሜ ጠዋት ይጀመራል ኢንሻአላህ

📌 ማሳሰቢያ፦ ማደሪያ ቦታ ስለተዘጋጀ፤ እዛው ለማደር የለሊት ልብስ መያዝዎን አይዘንጉ።

👉 አዘጋጅ፦ የቡታጅራ ሰለፊዮች ጀማዓ
☎️ ለበለጠ መረጃ፦
+251911972644
+251930887210

https://t.me/albeyanbutajira/1334
❤2👍1💯1
ስለ ቢላል ኢብኑ ረባህ በ (ሸይ
<unknown>
📣 አዲስ ውብ የሆነ ሙሐደራ

👉 እሮብ ግንቦት 12/9/2018 E.C ከመግሪብ እስከ ዒሻ የተደረገ ሙሐደራ


🎙 ሸይኽ ዐብዱልሐሚድ ኢብኑ ያሲን አል'ለተሚ
ሐፊዘሁሏህ

🇸🇦 ርዕስ፦
مناقب بلال بن رباح (مؤذن الرسول ﷺ) 

📡 ከተዳሰሱ ነጥቦች በትንሹ

💦 የቢላል ኢብኑ ረባህ ደረጃ

💦 ቢላል ኢብኑ ረባህ ለዲን የከፈለው ስቃይ

💦 በማን ባርነት ውስጥ እንደነበር
💦 ማን ነፃ እንዳወጣው


💦 የበድር ጦርነት ክስተት

🍁 እንዲሁም ከቢላል ኢብኑ ረባህ የምንወስደው ትምህርት እና ቁም ነገር ብዙ እንዳሉ ተዳሶበታል ።

🎤 በመጨረሻ ሸይኹ የመከሩት የመንሐጅ ፅናት አደራ ተካቶበታል 🎬


💡አድራሻ፦ ካራ ቆሬ ሳሌ ህንጻ ጀርባ ቢላል ኢብኑ ረባህ ቁጥር ❹ መድረሳ ላይ
👇👇👇👇 jon 👇👇👇👇
https://t.me/bilalibnurebahmedresa
https://t.me/bilalibnurebahmedresa
👍1
አቤት ሞቅ የለ ደዕዋ በዉዱ ሸይካችን አ ሀሚድ(وفقه الله)

      ተጀመረ

             ተጀመረ

                    ተጀመረ

                             ተጀመረ    

    ➢ ገባ
         ➢ ገባ
                ➢ገባ
                    ➢ገ ባ
                             ➢ በሉ



➢ ገባ ገባ   በሉ  ጆይን በሉ ሸር አድርጉ ባረከላህ ፊኩም ጀዛኩሙሏሁ ኸይረን👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇


https://t.me/eibrahimkeyeredin
https://t.me/eibrahimkeyeredin