Bilal Gallery
3.88K subscribers
270 photos
9 videos
3 files
258 links
መቼም ሰው ነኝና ስህተት አይታጣብኝም ስህተት ካያችሁ በዚህ @Amir8979 አድርሱኝ ከስህተቴ ሁሌም ተመላሽ ነኝ! "ጥፋቴን በነገረኝ ሙስሊም ሁሉ የአላህ እዝነት ይውረድ"
Download Telegram
Bilal Gallery
Photo
6).ኡሙ ሀቢባህ(ረምላህ ቢንት አቡ ሱፍያን):-------

ሙሉ ስሟ ረምላህ ቢንት አቡ ሱፍያን ሲሆን እስከ መካ
መከፈት ድረስ የቁረይሽ አጋሪዎች ዋና መሪ የነበረው
የአቡ ሱፍያን ቢን ሀርብ ልጅ ናት። ምንም እንኳን አባቷ
በዚያን ጊዜ አጋሪ ቢሆንም እሷ ግን ኢስላምን ተቀብላ
ነበር። ረምላህ(ረ.ዐ) በኢስላም ላይ እያለች ያጋጠማትን
ማንኛውንም መከራና ችግር የአላህን ምንዳ በማስታወስ
በትእግስት አሳልፋለች። ባሏ እንደርሷው ሙስሊም
የነበረው ዑበይዱላህ ኢብኑ ጃህሽ ሲሆን ሙስሊሞች
ሁሉ መካ ላይ የካሀዲያኑ ግፍና ጭቆና ሲበረታባቸው
ሁለቱ ጥንዶች ወደ ሀበሻ ከተሰደዱት ሰዎች ጋር በመሆን
ከሄዱ ቡኃላ እዚያ እያሉ ሐቢባህ የምትባል ልጅ ወለዱ።
ኡሙ ሀቢባህ(ረ.ዐ) ልክ እንደ ሎሎቹ አብረዋት የተሰደዱ
ሙስሊሞች ሁሉ በሀበሻ ሀገር የሚደርስባትን
የባይተዋርነት ስሜት አንድ ያልጠበቀችው ሁኔታ
እስኪገጥማት ደረስ ተቋቁማው ትኖር ነበር።
የኡሙ ሀቢባህ(ረ.ዐ) ባለቤቴ ዑበይዱላህ ኢብኑ ጀህሽ
መጠጥ መጣት ይጀምርና እስልምና ያስጠለዋል።
እምነቱንም ቀየረ(ከፈረ)። ይባስ ብሎ ሚስቱን ወደ ኩፍር
ይጠራታል። እሷም ከእስልምና ፍንክች እንደማትል
ገለፅችለት። ከዚያ ቡኃላ አስካሪ መጠጥ አብዝቶ
መውሰድ ጀመረ። በዚያ ሁኔታ ብዙም መቆየት አልቻለም።
ወዲያው ሞተ። ኡሙ ሀቢባህ(ረ.ዐ) ይህ ከሆነ ቡኃላ
ከሀገሯ ውጪ በባይተዋርነት መኖሯ ሳያንሳት ባል አልባ
በመሆን የብቸኝነት ህይወት ለመግፋት ተገደደች።
እንደዚያም ቢሆን ይህን ሁሉ ትካዜና ብቸኝነቷን በፅናትና
በታላቅ ትእግስት ተቋቁማ ነበር የቆየችው። ምክንያቱም
ሀያሉ አላህ በቅዱስ ቃሉ የሚከተለውን ማለቱን
ታዉቃለችና:-
ﻓَﺈِﺫَﺍ ﺑَﻠَﻐْﻦَ ﺃَﺟَﻠَﻬُﻦَّ ﻓَﺄَﻣْﺴِﻜُﻮﻫُﻦَّ ﺑِﻤَﻌْﺮُﻭﻑٍ ﺃَﻭْ ﻓَﺎﺭِﻗُﻮﻫُﻦَّ ﺑِﻤَﻌْﺮُﻭﻑٍ
ﻭَﺃَﺷْﻬِﺪُﻭﺍ ﺫَﻭَﻱْ ﻋَﺪْﻝٍ ﻣِّﻨﻜُﻢْ ﻭَﺃَﻗِﻴﻤُﻮﺍ ﺍﻟﺸَّﻬَﺎﺩَﺓَ ﻟِﻠَّﻪِ ۚ ﺫَٰﻟِﻜُﻢْ ﻳُﻮﻋَﻆُ ﺑِﻪِ ﻣَﻦ
ﻛَﺎﻥَ ﻳُﺆْﻣِﻦُ ﺑِﺎﻟﻠَّﻪِ ﻭَﺍﻟْﻴَﻮْﻡِ ﺍﻟْﺂﺧِﺮِ ۚ ﻭَﻣَﻦ ﻳَﺘَّﻖِ ﺍﻟﻠَّﻪَ ﻳَﺠْﻌَﻞ ﻟَّﻪُ ﻣَﺨْﺮَﺟًﺎ
ﻭَﻳَﺮْﺯُﻗْﻪُ ﻣِﻦْ ﺣَﻴْﺚُ ﻟَﺎ ﻳَﺤْﺘَﺴِﺐُ ۚ ﻭَﻣَﻦ ﻳَﺘَﻮَﻛَّﻞْ ﻋَﻠَﻰ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﻓَﻬُﻮَ ﺣَﺴْﺒُﻪُ ۚ ﺇِﻥَّ
ﺍﻟﻠَّﻪَ ﺑَﺎﻟِﻎُ ﺃَﻣْﺮِﻩِ ۚ ﻗَﺪْ ﺟَﻌَﻞَ ﺍﻟﻠَّﻪُ ﻟِﻜُﻞِّ ﺷَﻲْﺀٍ ﻗَﺪْﺭًﺍ
ጊዜያቸውንም ለመዳረስ በተቃረቡ ጊዜ በመልካም
ያዙዋቸው፡፡ ወይም በመልካም ተለያዩዋቸው፡፡ ከእናንተም
ውስጥ ሁለት የትክክለኛነት ባለቤቶችን አስመስክሩ፡፡
ምስክርነትንም ለአላህ አስተካክሉ፡፡ ይህ በአላህና
በመጨረሻው ቀን የሚያምን የኾነ ሰው ሁሉ በእርሱ
ይገሰጽበታል፡፡ አላህንም የሚፈራ ሰው ለእርሱ መውጫን
ያደርግለታል፡፡ ከማያስበውም በኩል ሲሳየን ይሰጠዋል፡፡
በአላህም ላይ የሚጠጋ ሰው እርሱ በቂው ነው፡፡ አላህ
ፈቃዱን አድራሽ ነው፡፡ አላህ ለነገሩ ሁሉ የተወሰነ ጊዜን
በእርግጥ አድርጓል፡፡ (አል-ጦላቅ 2-3)
ኡሙ ሀቢባህ(ረ.ዐ) ባሏ ከመሞቱ ከትንሽ ቀን በፊት
በህልሟ ቤቷ ውስጥ ጨረቃ ገብቶ ቤቱን ሲያበራ አየች።
የጨረቃው መታየት ግራ አጋብቷት ዱአ አደርገች አላህ
ሆይ! ኸይር ነገር ግጠመኝ አለች።
ረሱል(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሰቡ:- “ኡሙ
ሀቢባህን ባገባት በእኔና በአቡ ሱፍያን መካከል ያለው
ክፍተት ይቀንሳል” ምክንያቱም አቡ ሱፍያን ማለት
የቁረይሾች ዋና ነው ስለሆነ ጋብቻውን ለእርቅ ፈልገው
ነው። በሁለተኛ ደረጃ ልጅ አላት ባሏ የሞተባት እንስት
ነች። በአላህ ትዛዝ ለጋብቻው መህር ከረሱል(ሰለላሁ
አለይሂ ወሰለም) ውክልና ከተሰጣቸው ከንጉስ ነጃሺ
በ400 ዲናር ሰርጉ ተደረገ። ብዙ ሀዲያዎችንም ከንጉስ
ነጃሺ ተቀበለች። ኡሙ ሀቢባህ(ረ.ዐ) የረሱል(ሰለላሁ
አለይሂ ወሰለም) ሚስት ሆነች። በብዙ ሰሀቦች ታጅባ ወደ
መዲና ሄደች። ከንጉስ ነጃሺ ለረሱል(ሰለላሁ አለይሂ
ወስለም) የተበረከተውን ስጦታም አስረከበች።
ከስጦታዎቹ መሀል 3 ዱላ(ከረዛን) ነበር። እነዚን ዱላ
አንዱን ለአቡበከር አንዱን ለዑመር አንዱን ደግሞ ያ
ቢላል አሉና ና ይሄ ከወንድምህ አህመድ ነጃሺ የመጣ
ነው አሉትና ሰጡት። የኡሙ ሀቢባህ(ረ.ዐ) አባት አቡ
ሱፍያን ልጃቸውን ረሱል(ሰለላሁ አለይሂ ወሰላም)
እንዳገቧት ሲሰሙ ተንቀጠቀጠ፣ ተገረመ። ትላንት
ሙስሊሞችን ሰብስበን ማቃጠል ነበረብን ሲል የነበረው
ረሱል(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሲሰድብ የነበረው አሁን
ቀዝቀዝ አለ። እንዲህም ሲል ተናገረ ልጄን ያገባት እኳ
በጣም ክብር ያለውን ሰው ነው። ተመለከታቹ አደል
የአላህና የረሱል(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሀሳብ ተሳካ።
ትላንት ረሱል(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለምን) ለመግደል
ይፈልግ የነበረው ዛሬ ግን አወደሳቸው። በማወደስም
አልተወገደም እስልምናም ተቀበለ። እስልምናን በመቀበል
ብቻ አላበቃም። ትልቅ ዳኢም ሆነ የእስልምናን ብርሀን
የበላይ ለማድረግ ከጠላት ተዋግቷል አጂብ በጣም
የሚገርም ታሪክ ነው። ለአላህ ጥራት ይገባው። ጠላቶች
የረሱል(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ብዙ ሚስት ማግባት
ለስጋዊ ስሜት ብለው ይናገራሉ እውነታው ግን ታሪክ
ይናገራል። ለጥበብ፣እዝነት፣ለሰላም ነበር። ኡሙ ሀቢባህ
(ረ.ዐ) አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላት።

https://t.me/sunah123
❤1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Bilal Gallery
Photo
7).መይሙና ቢንት አል ሀሪስ(ረ.ዐ)፦


በሺዎች የሚቆጠሩ ሴቶች ለረሱል(ሰለላሁ አለይሂ
ወሰለም) ነፍሴን ሰጥቼዎታለው በማለት ለትዳር
ቢጠይቁም ምላሽ የሰጡት ግን ለመይሙና ብቻ ነው።
መይሙና ቢንት አል ሀሪስ ኢብን ሃዚን ኢብን ቡጅይር
የዐባስ(ረ.ዐ) ባለቤት የሆነችው የኡም አል-ፈድል እህት
የኻሊድ ኢብን አል ወሊድና የአብደላህ ኢብን ዐባስ(ረ.ዐ)
አክስት ስትሆን ከቁረይሽ የተከበሩ ወይዛዝርት መካከልም
ተጠቃሽ ናት። መይሙና ከመጀመርያ ባሏ
ባለመስማማታቸው ይፋታሉ። ለብዙ ጊዚያት ያለባል
ከቆየች ቡኃላ ሁለተኛ ባል ታገባለች ይሄ ያገባችው ሰውዬ
ደግሞ ይሞታል። ስለዚህ መይሙና ሁለት ጊዜ አግብታ
የፈታች እንስት ናት ማለት ነው። መይሙና(ረ.ዐ) ወደ
ረሱል(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሄዳ እንዲህ አለቻቸው:-
“ያ ረሱለላህ ነፍሴን ሰጥቼዎታለው አለች።” ይህ በመሆኑ
አላህ ይህን የቁርአን አንቀፅ አወረደ
ﻳَﺎ ﺃَﻳُّﻬَﺎ ﺍﻟﻨَّﺒِﻲُّ ﺇِﻧَّﺎ ﺃَﺣْﻠَﻠْﻨَﺎ ﻟَﻚَ ﺃَﺯْﻭَﺍﺟَﻚَ ﺍﻟﻠَّﺎﺗِﻲ ﺁﺗَﻴْﺖَ ﺃُﺟُﻮﺭَﻫُﻦَّ ﻭَﻣَﺎ ﻣَﻠَﻜَﺖْ
ﻳَﻤِﻴﻨُﻚَ ﻣِﻤَّﺎ ﺃَﻓَﺎﺀَ ﺍﻟﻠَّﻪُ ﻋَﻠَﻴْﻚَ ﻭَﺑَﻨَﺎﺕِ ﻋَﻤِّﻚَ ﻭَﺑَﻨَﺎﺕِ ﻋَﻤَّﺎﺗِﻚَ ﻭَﺑَﻨَﺎﺕِ ﺧَﺎﻟِﻚَ
ﻭَﺑَﻨَﺎﺕِ ﺧَﺎﻟَﺎﺗِﻚَ ﺍﻟﻠَّﺎﺗِﻲ ﻫَﺎﺟَﺮْﻥَ ﻣَﻌَﻚَ ﻭَﺍﻣْﺮَﺃَﺓً ﻣُّﺆْﻣِﻨَﺔً ﺇِﻥ ﻭَﻫَﺒَﺖْ ﻧَﻔْﺴَﻬَﺎ
ﻟِﻠﻨَّﺒِﻲِّ ﺇِﻥْ ﺃَﺭَﺍﺩَ ﺍﻟﻨَّﺒِﻲُّ ﺃَﻥ ﻳَﺴْﺘَﻨﻜِﺤَﻬَﺎ ﺧَﺎﻟِﺼَﺔً ﻟَّﻚَ ﻣِﻦ ﺩُﻭﻥِ ﺍﻟْﻤُﺆْﻣِﻨِﻴﻦَ ۗ ﻗَﺪْ
ﻋَﻠِﻤْﻨَﺎ ﻣَﺎ ﻓَﺮَﺿْﻨَﺎ ﻋَﻠَﻴْﻬِﻢْ ﻓِﻲ ﺃَﺯْﻭَﺍﺟِﻬِﻢْ ﻭَﻣَﺎ ﻣَﻠَﻜَﺖْ ﺃَﻳْﻤَﺎﻧُﻬُﻢْ ﻟِﻜَﻴْﻠَﺎ ﻳَﻜُﻮﻥَ
ﻋَﻠَﻴْﻚَ ﺣَﺮَﺝٌ ۗ ﻭَﻛَﺎﻥَ ﺍﻟﻠَّﻪُ ﻏَﻔُﻮﺭًﺍ ﺭَّﺣِﻴﻤًﺎ
አንተ ነቢዩ ሆይ! እኛ እነዚያን መህሮቻቸውን የሰጠሃቸውን
ሚስቶችህን፣ አላህ ባንተ ላይ ከመለሰልህም እነዚያን
እጅህ የጨበጠቻቸውን ምርኮኞች፣ እነዚያንም ከአንተ ጋር
የተሰደዱትን የአጎትህን ሴቶች ልጆች፣ የአክስቶችህንም
ሴቶች ልጆች፣ የየሹማህንም ሴቶች ልጆች፣
የየሹሜዎችህንም ሴቶች ልጆች (ማግባትን) ለአንተ
ፈቅደንልሃል፡፡ የአመነችንም ሴት ነፍሷን (ራሷን) ለነቢዩ
ብትሰጥ ነቢዩ ሊያገባት የፈለገ እንደ ኾነ ከምእምናን ሌላ
ላንተ ብቻ የጠራች ስትኾን (ፈቀድንልህ)፡፡ በእነርሱ
(በምእምናን) ላይ በሚስቶቻቸውና እጆቻቸው
በጨበጧቸው (ባሮች ነገር) ግዴታ ያደረግንባቸውን
በእርግጥ ዐውቀናል፡፡ ባንተ ላይ ችግር እንዳይኖር
(ያለፉትን ፈቀድንልህ)፡፡ አላህም መሓሪ አዛኝ ነው፡፡ (አል
አህዛብ 50)
መይሙና(ረ.ዐ) በዚህ አንቀፅ መሰረት የረሱል(ሰለላሁ
አለይሂ ወሰለም) ሚስት ሆነች በራሷ ፍቃድ መጥታ
ነፍሷን በመስጠቷ ያለ ማህር አገቧት ማለት ነው።
ከቁርአኑ አንቀፅ እንደምንረዳው ይህ አይነት ጋብቻ
የተፈቀደው ለውዱ ነቢ ሙሀመድ(ሰለላሁ አለይሂ
ወሰለም) ብቻ ነው። ብዙ ሴቶች ልክ እንደ መይሙና(ረ.ዐ)
ለረሱል(ሰለላሁ አለይሂ ወሰላም) ነፍሴን ሰጥቼዎታለው
ብለው ነበር ነገር ግን ከመይሙና ውጪ ማንንም
አልተቀበሉም።
መይሙና(ረ.ዐ) የነብዩ ሙሀመድ(ሰለላሁ አለይሂ
ወሰለም) ባለቤት በመሆን ከሌሎች ሚስቶቻቸው ጋር
ተቀላቀለች። ኢስላም የሚያዘውን ኢባዳ በመፈፀም
ግንባር ቀደም ነበረች። ለባሏ እንዲሁ ታዛዥ ነበረች።
አላህ መልካም ስራዎን ይቀበላት።

https://t.me/sunah123
❤1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Bilal Gallery
Photo
8).ጁወይሪያህ ቢንት አል ሀሪስሀሪስ፦


✅ረሱል(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ጁወይሪያህን
በማግባታቸው ወደ 700 የሚጠጉ ከሀዲያን እስልምናን
ተቀብለዋል። ሙሉ ታሪኩን ያንብቡት ይገረማሉ።
ሙሉ ስሟ ጁወይሪያህ ቢንት አል ሀሪስ ኢብን አቡ ዲራር
ኢብን ለቢብ አል ኹዛኢያ ነው። ጁወይሪያህ(ረ.ዐ) ከጎሳዎ
መሳፍንት ወገን የምትወደድና ቆንጆ ሴት ስትሆን
በሙስሊሞች እጅ ስትገባ እድሜዋ 20 ቤቱ ውስጥ
ነበር። በኑ ሙስጠሊቆች ከመዲና ራቅ ብለው የሚገኙ
ህዝቦች ናቸው። እነዚህ ህዝቦች ረሱል(ሰለላሁ አለይሂ
ወሰለም) እና ሰሀቦችን ሊያጠቁ እንደሆኑ ለረሱል(ሰለላሁ
አለይሂ ወሰለም) ዜናው ይደርሳቸዋል። ይህን ጊዜ
ብልሀተኛው ነቢይ ሙሀመድ(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)
ሳንቀደም እንቅደም በማለት ወታደር ይዘው ከበቧቸው።
ነገራቸው ከዛም ጦርነት ተከፈተ። ለሰዐአታት ያክል
ከተዋጉ ቡኃላ ጦርነቱ በሙስሊሞች ድል ይጠናቀቃል።
ብዙ የጦርነት መሳሪያዎች እና 350 የሚጠጉ ምርኮኛ
ወታደሮች አንዳንድ ኡለማዎች 700 ነው ይላሉ፣ ወርቅ፣
ጨርቅ ይህን ይዘው ተመለሱ። ይህን የውጊያ ውርስ
ለረሱል(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ይሰጧቸዋል። እሳቸው
ሁሉንም ለሰሀቦቻቸው አከፋፈሉት። ጁወይርይ(ረ.ዐ)
ከተማረኩት ምርኮኞች አንዷ ናት። ምርኮ ለተዋጊዎች
ሲከፋፈል ጁወይሪያ ለሳቢት ኢብን ቀይስ ደረሳት።
ጁወይሪያ(ረ.ዐ) አቧቷም ሆነ ባሏ ትልልቅ ነገስታት ነበሩ።
በምቾት ያደገች ናት። ሳቢት ደግሞ የገጠር ልጅ፣ ደሀ
ነው። ከሱ ጋር መሆንን አልወደድችም። ሳቢት ደግሞ ነፃ
አውጣኝ ስትለው 9 እቁያ ወርቅ ጠየቃት። ከዛም ወደ
ረሱል(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ዘንድ ሄዳ ያ ረሱለላህ!
እኔ ምርኮኛ ነኝ። ምርኮ ሲከፋፈል እጣ የደረሰኝ ደግሞ
ከሳቢት ኢብን ቀይስ ነው። እኔ ደግሞ ከእሱ ጋር መሆንን
አልፈለኩም። ነፃ በለይ ስለው 9 እቁያ ጠየቀኝ እኔ
ምርኮኛ ነኝ ይሄ ሁሉ ገንዘብ የለኝም በሀገሬ ቢሆን
እሰጠው ነበር ብላ አቤቱታ አቀረበች። ስምሽ ማነው
አሏት ጁወይሪያ ቢንት አል ሀሪስ አለች። ተገርመውም
የአል ሀሪስ ልጅ ነሽ አሏት። አዎ አለች። የተገረሙት
የንጉስ ልጅ ስለነበረች ነው። ባልሽስ እገሌ ብላ ነገረቻቸው
እሱም ንጉስ ነበር በጦርነቱ ሞቷል። አስገራሚው ታሪክ
እዚህ ጋር ይጀመራል። የረሱል(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)
ብዙ ሴት ማግባት የሚያንገሸግሻቹ እውነታውን
ተመልከቱ። ነብዩ(ሰለላሁ አለይሁ ወሰለም) እንዲህ አሏት
ከዚህ የተሻለ ባቀርብልሽ አትቀበይኝም? አሏት እሷም
በጉጉት ምንድን ነው እርሱ የአላህ መልእክተኛ አለች?
“እኔ ነፃ እንድትሆኚ ክፍያውን እፈፅማለው ከዚያም
አገባሻለው አሏት” ጁወይሪያ የቀረበላት ምርጫ በጣም
ስላስደሰታት ያለማቅማማት እሺ ነው ያለችው። በዚህ
ሁኔታ የረሱል(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሚስት ሆነች።
በማግስቱ ሰሀቦች ተሰባስበው ጅወይሪያ የረሱል(ሰለላሁ
አለይሂ ወሰለም) ሚስት ሆነች። የጁወይሪያ ቤተሰቦች
እኮ የረሱል(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) አማች ሆኑ ማለት
ነው። አዎ ብለው ተስማሙ። እንዴት እኛ የረሱል(ሰለላሁ
አለይሂ ወሰለም) አማቾች ምርኮኛ አርገን እንይዛለን አሉ?
ይህማ አይሆንም አሉ። ለነቢያችን(ሰለላሁ አለይሂ
ወሰለም) ክብር ስንል የእሳቸውን አማቾች(የእሷን
ቤተሰቦች) ነፃ አንልም ተባባሉ? እሺ ብለው ተስማሙ
ትላንት ባርያ የነበሩ እንደፈለጉ መሸጥ መለወጥ
የሚችሏቸውን ሰዎች ለረሱል(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)
ክብር ሲሉ ነፃ አሏቸው። ሱብሀነላህ የሚገርም ነው። እነዛ
ነፃ የተባሉት ሰዎች ደግሞ ይሰበሰቡና እናንተ ሰዎች ከእኛ
መሀል ነብያቸው ስላገባ ለሱ ክብር ሲሉ ነፃ አሉን። መዲና
ብንሄድ ኖሮ እንሸጥ ነበር። እኛስ ለልጃችን ስንል ለአላህ
ስንል ወደ እስልምና ለምን አንገባም? ብለው ሁሉም ወደ
ረሱል(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) በመሄድ እስልምና ገቡ።
አይሻ(ረ.ዐ) እንዲህ ትላለች:- ረሱል(ሰለላሁ አለይሂ
ወሰለም) ጁወይሪያን(ረ.ዐ) የመጀመርያ ቀን ወደ ቤት
ይዘዋት ሲገቡ በጣም ቀንቼ ነበር። ነገር ግን በእሷ
ምክንያት 700 ወጣቶች መስለማቸውን ስሰማ እየሮጥኩ
ሄድኩና እቅፍ አድርጌ “ያ ጁወይሪያ ከረሱል(ሰለላሁ
አለይሂ ወሰለም) ሚስቶች እንዳንቺ የተባረከ አላየሁም።
ምክንያቱም በአንቺ ምክንያት በመቶ የሚቆጠሩ ሰዎች
ወደ እስልምና ገብተዋል።” እናም ወደድኳት አለች። አያቹ
አደል የመጋባቱን ጥበብ። እንደው ጠላቶች
የሚያቅጥላቸው ለምን 9 ለምን 13 አገቡ አደል የሚሉት
ለእንደዚህ አላማ 1000 ቢያገቡ? ከ 1000 የጠላት
(ቀቢላ) ጋር ቢታረቁ ነውር ነው? ነውር አደለም። ነገር ግን
ረሱል(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ያገቧቸው ሚስቶች አንዷ
ልጆች ያሏት፣ አንዷ ሁለቴ የትፈታች፣ አንዷ ባሏ
የሞተባት፣ አንዷ በሽተኛ፣ አንዷ ትልቅ ሴት ነበሩ።
https://t.me/sunah123
❤1
|| ተጣራ ... ስበክ !!

በበጎ ማዘዙ መሥፈርቱን ጠብቆ
ከክፉ መከልከል ገደቦቹን አውቆ

ፍጹም አይቀንስም አንዲትንም ጉርሻ
አሏህ ከጻፈልን ከሪዝቃችን  ድርሻ

ማቅረብም አይችልም አንዲትን ደቂቃ
የተጻፈው እድሜ ደርሶ እስኪያበቃ

እናልህ አንበሳው በርትተህ ተጣራ
እድፏ ምድር ከሺርክ እስትትጠራ

ዒባዳ  እስኪሰጥ ለጌታችን ብቻ

አንድም አታገኝም ከርሱ ሚሆን አቻ

ሱናዋ እስትትሆን የሰው ልጆች መሪ
ከጥላዋ በታች ሁሉ ነፍሶች ኗሪ ....

t.me/Abdul_halim_ibnu_shayk
t.me/Abdul_halim_ibnu_shayk
➛➛➛➛➛➛➛
✨🌙 ۞ የቁርአን ተፍሲር ۞ 🌙✨


📖 ╭─❖ በሸይኽ አቡዘር ሀሰን ( አቡ ጦልሃ ) حَفِظَهُ الله ❖─╮
🔗 https://t.me/TefsirALQuran114⁠�
╰────────────────────────────╯

📖 ╭─❖ በኡስታዝ ባህሩ ተካ አቡ (ዑበይዳህ) حَفِظَهُ الله ❖─╮
🔗 https://t.me/amir897977⁠�
╰────────────────────────────╯
➛➛➛➛➛➛➛
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
👍3💯2
♦️ «ዙል-ሒጀህ ነገ መሆኑ ተረጋገጠ!»

— በመሆኑም ነገ ሰኞ (ግንቦት 10) ዙል-ሒጀህ አንድ ብሎ ይጀምራል። የፊታችን ማክሰኞ ሳምንት የውሙል-ዐረፈህ ሲሆን የፊታችን ኦሮብ ሳምንት ደሞ ዒድ አል-አድሓ ሆኗ ይውላል።

— አ'ሏሁ ተዓላ እነዚህ 10 ቀናት ቦቶ ሰጥቶ (በአስሮቹ ሌሊቶችም። ||  وَلَيَالٍ عَشْرٍ) እያለ ምሎባቸዋል። ዒባዳዎችን በተቻለን ያህል እናብዛ።

|| የመገናኛው ግሩፕ፦
t.me/Multeqa_Ahlissuneh
t.me/Multeqa_Ahlissuneh
🔖አስርቱ ወርቃማ የዙል-ሒጃ ቀናት!!


➠አላህ ከቀናት ሁሉ ያላቃቸው ቀናቶች አስሩ የዙልሂጃ ቀናት ናቸው።

🌴ጃቢር ኢብኑ አብዲላህ ባስተላለፉት ሀዲስ የአላህ መልዕክተኛ ( እንዲህ ብለዋል:-"ከዱንያ ቀናት ሁሉ ብልጫ ያላቸው አስርቱ የዙልሂጃ ቀናት ናቸው።
📌ከተከበሩ ወራቶች መካከል አንዱ የሀጅ ወር የሚሆነው በዙልሂጃ ወር ነው።
📌ከቀናት ሁሉ አላህ ዘንድ የተወደዱ ደግሞ አስሩ የዙልሂጃ ቀናት ናቸው።
📌እንዲሁም ከዱንያ ቀናት ሁሉ በላጭ ናቸው።
🍁ከኢብኑ አባስ (ረድየላሁዐንሁ) በተዘገበው ሀዲስ የአላህ መልእክተኛ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል ፦
"በነዚህ አስር ቀናቶች ውስጥ ከሚፈፀሙ መልካም ስራዎች በበለጠ መልካም ስራዎች አላህ ዘንድ የተወደዱ የሚሆንባቸው ቀናት የሉም ፤በአላህ ከሚደረግ ጅሀድም ጭምር ተብለው ሲጠየቁ። እሳቸውም፦ እራሱን እና ንብረቱን ይዞ ወጥቶ ምንም ያልተመለሰ ሰው ሲቀር ጅሀድም ከዚህ አይበልጥም አሉ።
[📚 ቡኻሪ ዘግበውታል]

📝በእነዚህ ቀናቶች ትኩረት ልንሰጣቸው ከሚገቡ የዒባዳ አይነቶች መካከል የሚከተሉት ይገኛሉ፦

❶ ፆም


ፆም ከስራዎች ሀሉ በላጭ ነውና በእነዚህ ቀናት መፆም እጅግ የተወደደ ተግባር ነው።

➣ከአቢ ቀታዳህ እንደተዘገበው የአላህ መልእክተኛ(ﷺ) ስለ ዐረፋ ቀን ፆም ተጠየቁ። እንዲህም አሉ፡-
ﻳﻜﻔِّﺮ ﺍﻟﺴﻨﺔ ﺍﻟﻤﺎﺿﻴﺔ ﻭﺍﻟﺒﺎﻗﻴﺔ
“ያለፈውንና የሚመጣውን አመት ወንጀል
ያብሳል።”

[📚ኢማም ሙስሊም እና አህመድ ዘግበውታል]

❷ ዚክሮችን ማብዛት


➢ ዐብዱላህ ኢብኑ ዑመር ባስተላለፉት ሀዲስ ነብዩ(ﷺ)እንዲህ ብለዋል፦

«ከእነዚህ አስር ቀናት በበለጠ አላህ ዘንድ ታላቅ የሆኑና መልካም ስራ እጅግ የተወደደባቸው ቀናት የሉም፤ ስለዚህ ተህሊል ተክቢር እና ተህሚድ አብዙ»

[📚አል ኢማም አህመድ ዘግበውታል።]

#ይህን_ተክቢራ_ከዙልሒጃ_1_ጀምሮ_እስከ_አያመ_ተሽሪቅ (ከዒድ በኋላ ያሉትን 3 ቀናት ጨምሮ) ማለቱ ሱና በመሆኑ ቤተሰቦቻችንን በዚህ ላይ በማነሳሳት ቤታችንን በተክቢራ እናድምቅ።
~የተክቢራ አደራረጉም
"አሏሁ አክበር፤ አሏሁ አክበር፤ አሏሁ አክበር፤ ላኢላሃ ኢለሏህ አሏሁ አክበር ወሊላሂል ሐምድ"......

❹ ሀጅና ዑምራ


~በነዚህ ቀናቶች ከሚደረጉ መልካም ስራዎች ሌላው ሀጅ ማድረግ ይገኝበታል በእነዚህ አስር ቀናት የሀጅ ኢባዳ ላይ ተገኝቶ በተገቢው መንገድ ከፈፀመው በአላህ ፈቃድ ከተከታዩ የአላህ መልእክተኛﷺ ብስራት ድርሻ ይኖረዋል።

➣ከአቡ ሁረይራ ረድየሏሁአንሁ በተላለፈው ሀዲስ የአላህ መልዕክተኛ (ﷺ)እንዲህ ብለዋል ፦
"ከወንጀል የራቀና ተቀባይነት ያለው ሀጅ (አል ሃጅ አል መብሩር)ምንዳው ጀነት እንጂ ሌላ አይደለም።"ብለዋል
[📚ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]

🍁❹ ኡድሂያ


ከነዚህ አስር ቀናት ከሚሰሩ መልካም ስራዎች ሌላኛው ኡድሂያ በማረድ ወደ አላህ መቃረብ ነው።
ኡድሂያ በጣም ከጠነከሩ የነብዩ ﷺ ሱናዎች መካከል አንዱ ነው። የነብዩ ኢብራሂም (ዓለይሂ ሰላም) ሱና ህያው ከማድረግ በተጨማሪ ለድሆችና ችግረኞች መድረስ ነው።

📍የመልካም ስራ በሮች ብዙ ናቸው እና የቻልነውን ሁሉ በመፈፀም ወደ አላህ መቃረብ ይገባናል።

💫 የታሰረን ወይም የታመመን ሰው መጠየቅ፤ ዝምድናን መቀጠል፤ በመልካም ማዘዝ ከመጥፎ መከልከል፤ የተጣላን ማስታረቅ ፤ ሶደቃ ማብዛት፤ ሱና ሶላቶችን ማብዛት፤ ቁርአን መቅራት ዚክር ማብዛት ፤ዱዓ ማብዛት ያስፈልጋል።

🤲"አላህ በነዚህ ወርቃማ ጊዜያት ከሚጠቀሙና አላህ ዘንድ መልካም ምንዳን ከሚያገኙ ጠንካራና ብልህ ባሮች ያድርገን።"

t.me/Mehfuza_os99
t.me/Mehfuza_os99
❤1