Bilal Gallery
3.9K subscribers
270 photos
9 videos
3 files
260 links
መቼም ሰው ነኝና ስህተት አይታጣብኝም ስህተት ካያችሁ በዚህ @Amir8979 አድርሱኝ ከስህተቴ ሁሌም ተመላሽ ነኝ! "ጥፋቴን በነገረኝ ሙስሊም ሁሉ የአላህ እዝነት ይውረድ"
Download Telegram
ኑ!! ጠፊ በሆነችው ዱንያ ዘላለማዊ የሆነውን አኼራችንን እንገምባ!!!!

ተቀላቀሉ Share & joine
👇👇👇👇👇

https://t.me/bilalibnurebahgroup
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Bilal Gallery
Photo
5).ዘይነብ ቢንት ጀህሽ(ረ.ዐ)

የዘይነብ ቢንት ጀህሽ(ረ.ዐ) እና የረሱል(ሰለላሁ አለይሂ
ወሰለም) ጋብቻ አላህ(ሱ.ወ) በቅዱስ ቁርአኑ ተርኮልናል።
ዘይነብ ቢንት ጀህሽ(ረ.ዐ) የነብዩ(ሰለላሁ አለይሂ
ወሰለም) የአክስት ልጅ ስትሆን እናቷ ኡማማ የነብዩ
(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) የአባታቸዉ እህት ነች። ነብዩ
(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ዘይነብን ባሪያቸዉ ለነበረዉና
ብኃላ ነፃ ላወጡት ለዘይድ ኢብን ሀሪሳ(ረ.ዐ) ሊድሯት
እንደሚፈልጉ ሲገልፁላት እርሷም ሆነች ቤተሰቧ ፍቃደኛ
አልነበሩም። ሆኖም ግን ነብዩ(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)
“እኔ ግን ይህን ላንቺ ጥሩ በመሆኑ ወድጄልሻለሁ”
በማለት ሊጋቧት ሞከሩ። እርሷ ግን እንዲህ አለች።
“የአላህ መልእክተኛ ሆይ!(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እኔ
ይሄን ጋብቻ አልወደድኩትም። ከዚህም በላይ እኔ
ለቤተሰቤ ተወዳጅ የሆንኩ ልጅ ስሆን የአክስትዎም ልጅ
በመሆኔ የዝምድናችንን ነገር አይዘንጉት። ይህን ጋብቻ
አልፈልገዉም። በዚህ ጊዜ አላህ የሚከተለዉን ቁርአን
አወረደ:-
ﻭَﻣَﺎ ﻛَﺎﻥَ ﻟِﻤُﺆْﻣِﻦٍ ﻭَﻟَﺎ ﻣُﺆْﻣِﻨَﺔٍ ﺇِﺫَﺍ ﻗَﻀَﻰ ﺍﻟﻠَّﻪُ ﻭَﺭَﺳُﻮﻟُﻪُ ﺃَﻣْﺮًﺍ ﺃَﻥ ﻳَﻜُﻮﻥَ
ﻟَﻬُﻢُ ﺍﻟْﺨِﻴَﺮَﺓُ ﻣِﻦْ ﺃَﻣْﺮِﻫِﻢْ ۗ ﻭَﻣَﻦ ﻳَﻌْﺺِ ﺍﻟﻠَّﻪَ ﻭَﺭَﺳُﻮﻟَﻪُ ﻓَﻘَﺪْ ﺿَﻞَّ ﺿَﻠَﺎﻟًﺎ
ﻣُّﺒِﻴﻨًﺎ
አላህና መልክተኛውም ነገርን በፈረዱ ጊዜ ለምእምናንና
ለምእምናት ከነገራቸው ለእነርሱ ምርጫ ሊኖራቸው
አይገባም! የአላህንና የመልክተኛውንም ትእዛዝ የጣሰ
ሰው ግልጽ የሆነን መሳሳት በእርግጥ ተሳሳተ። (አል-
አህዛብ 36)
ይህ የቁርአን አንቀፅ ከወረደ ቡኃላ ዘይነብ የአላህና
መልእክተኛዉን(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ትእዛዝ ማክበር
ስለነበረባት ዘይድን አገባች። ኢስላም የሰዎችን ደረጃ
በዘርና በደም ሳይሆን የሚፈርጀዉ ለአላህ ባላቸዉ
ቀረቤታ እንደመሆኑ ሰዉን ‘ይህ የዚህኛዉ ጐሳ ነዉ’
‘ይኸኛዉ ደግሞ ዘሩ እንዲህ ነዉ’ ብሎ ሰዉን ዝቅ
ማድረግን ፈፅሞ አይቀበልም። የሆነ ሆኖ የዘይድና
የዘይነብ ትዳር አልሰመረም። በመካከላቸዉ ሰላምና ደስታ
ጠፋ። ዘይነብ ከከፍተኛዉ የህብረተሰብ ክፍል የመገኘቷን
ያህል በአንድ ወቅት በባርነት ተፈንግሎ ከኸድጃ(ረ.ዐ)
ቤት የኖረዉንና ቡኃላም ለነብዩ(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)
በንብረትነት ተላልፎ ከተሰጠ ቡኃላ ነፃ የተደረገዉን
ዘይድን በንቀት አይን መመልከት ጀመረች። ሁለቱም ሰዎች
በየራሳቸዉ መንገድ መልካም የነበሩና ነብዩንም(ሰለላሁ
አለይሂ ወሰለም) የሚወዱ ቢሆንም በጋራ የሚያስተሳስር
ነገር ስላልነበረ ትዳራቸዉ ተገዝግዞ ከመዉደቅ ሊድን
አልቻለም። ስለሆነም ዘይድ(ረ.ዐ) ሊፈታት ወሰነ። ሆኖም
ግን ነብዩ(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሚስቱን እንዲይዝና
አላህንም እንዲፈራ ነገሩት። ነብዩ(ሰለላሁ አለይሂ
ወሰለም) ይህን ይበሉኝ እንጂ ቀደም ሲል ዘይነብን(ረ.ዐ)
ዘይድ እንዲፈታትና እርሳቸዉም እንዲያገቧት አላህ ግድ
እንዳረገባቸዉ አጥተዉት አደለም። ይህ መለኮታዊ ትእዛዝ
በዋነኝነት ያጠጠረዉ በቅድመ-ኢስላም የድንቁርና ባህል
በመሆን ለዘመናት የኖረዉን የማደጐ ልጅና በስጋ
የተወለደን ልጅ አንድ አድርጐ የማየት ልማድ ለመስበር
ነበር። ይሁን እንጂ ነብዩ(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ይህን
ሁኔታ ግልፅ አድርገዉ ለዘይድ በመንገር እንዲፈታት
በማድረግ ፋንታ ሰዎች በተለይም ደግሞ ከሀዲያኑ
ሙሀመድ የልጁን ሚስት አፋትቶ አገባ ይሉኛል ብለዉ
በመፍራት ያንን ከማድረግ ተቆጥበዉ ቆዩ። ይሁን እንጂ
ይህን ሁሉ ፍርሀትና የዘመና ጃሂሊያ ጎታች ልማድ ኃያሉ
አላህ በአንድ ጊዜ በማፈራረስና እርሳቸዉንም በመዉቀስ
የሚከተለዉን የቁርአን አንቀፅ አወረደ:-
ﻭَﺇِﺫْ ﺗَﻘُﻮﻝُ ﻟِﻠَّﺬِﻱ ﺃَﻧْﻌَﻢَ ﺍﻟﻠَّﻪُ ﻋَﻠَﻴْﻪِ ﻭَﺃَﻧْﻌَﻤْﺖَ ﻋَﻠَﻴْﻪِ ﺃَﻣْﺴِﻚْ ﻋَﻠَﻴْﻚَ ﺯَﻭْﺟَﻚَ
ﻭَﺍﺗَّﻖِ ﺍﻟﻠَّﻪَ ﻭَﺗُﺨْﻔِﻲ ﻓِﻲ ﻧَﻔْﺴِﻚَ ﻣَﺎ ﺍﻟﻠَّﻪُ ﻣُﺒْﺪِﻳﻪِ ﻭَﺗَﺨْﺸَﻰ ﺍﻟﻨَّﺎﺱَ ﻭَﺍﻟﻠَّﻪُ
ﺃَﺣَﻖُّ ﺃَﻥ ﺗَﺨْﺸَﺎﻩُ ۖ ﻓَﻠَﻤَّﺎ ﻗَﻀَﻰٰ ﺯَﻳْﺪٌ ﻣِّﻨْﻬَﺎ ﻭَﻃَﺮًﺍ ﺯَﻭَّﺟْﻨَﺎﻛَﻬَﺎ ﻟِﻜَﻲْ ﻟَﺎ ﻳَﻜُﻮﻥَ
ﻋَﻠَﻰ ﺍﻟْﻤُﺆْﻣِﻨِﻴﻦَ ﺣَﺮَﺝٌ ﻓِﻲ ﺃَﺯْﻭَﺍﺝِ ﺃَﺩْﻋِﻴَﺎﺋِﻬِﻢْ ﺇِﺫَﺍ ﻗَﻀَﻮْﺍ ﻣِﻨْﻬُﻦَّ ﻭَﻃَﺮًﺍ ۚ ﻭَﻛَﺎﻥَ
ﺃَﻣْﺮُ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﻣَﻔْﻌُﻮﻟًﺎ
“ለእዚያም አላህ በእርሱ ላይ ለለገሰለትና (አንተም ነጻ
በማውጣት) በእርሱ ላይ ለለገስክለት ሰው (ለዘይድ)
አላህ ገላጩ የሆነን ነገር በነፍስህ ውስጥ የምትደብቅና
አላህ ልትፈራው ይልቅ የተገባው ሲሆን ሰዎችን የምትፈራ
ሆነህ «ሚስትህን ባንተ ዘንድ ያዝ፤ (ከመፍታት) አላህንም
ፍራ» በምትል ጊዜ (አስታውስ)። ዘይድም ከእርሷ ጉዳይን
በፈጸመ ጊዜ(ፍላጐትን አርክቶ በፈታትና ኢዳዋን
በጨረሰች ጊዜ) በምእምናኖች ላይ ልጅ አድርገው
ባስጠጉዋቸው (ሰዎች) ሚስቶች ከእነርሱ ጉዳይን
በፈጸሙ ጊዜ (በማግባት) ችግር እንዳይኖርባቸው እርሷን
አጋባንህ። የአላህም ትእዛዝ ተፈጻሚ ነው።” (አል-አህዛብ
37)
እንግዲህ ከላይ በተጠቀሰዉ ሁኔታ ነበር። ዘይነብ(ረ.ዐ)
ከነብዩ(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ጋር የተጋባቸዉ።
ስለሆነም የጋብቻዉ ዉል የተገለፀዉ በተቀደሰዉ ቁርአን
ላይ ነዉ። እናም ዘይነብ በሌሎቹ የነብዩ(ሰለላሁ አለይሂ
ሰላም) ባለቤቶች ላይ ይህን ሁኔታ እያነሳች የበላይነቷን
ለማንፀባረቅ ትሞክር ነበር። በተደጋጋሚም እንዲህ ስትል
ተደምጣለች:-
የእናንተን የጋብቻ ዉል ያረቀቁትና የተዋዋሉት
ቤተሰቦቻችሁ ሲሆኑ የእኔን ግን ከአርሹ በላይ የሆነዉ
አላህ ነዉ።” በሌላ ዘገባ ደግሞ “አላህ የእኔን ጋብቻ
ከሰማይ ሆኖ ነዉ ያፀደቀዉ” ብላለች።
ዘይነብ(ረ.ዐ) በእምነቷ የተመሰጠች አላህን ፈሪ
እዉነተኛና ቸር ነበረች። የእጅ ስራና የዕደ-ጥበባት እዉቀት
ስለነበራትም ያንን እየሰራች በምታገኘዉ ገንዘብ ድሆችንና
ወላጅ አልባ ልጆችን ትረዳበት ነበር። አኢሻ(ረ.ዐ) እንዲህ
ትላለች:- አንድ ጊዜ ነብዩ(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)
እንዲህ ብለዉ ነበር:- “ከባለቤቶቼ ሁሉ ከእኔ ቡኃላ
የምትሞተዉ እጀ ረዥሟ ነዉ።” ከዚያም ከነብዩ(ሰለላሁ
አለይሂ ወሰለም) ሞት ቡኃላ ሁላችንም አንድ ላይ
ተሰባስበን እጆቻችንን እያስተያየን የማንኛችን
እንደሚረዝም እንለካ ነበር። ከሁላችንም እጆች የሰዉዳ
ቢንት ዘምዓህ እጅ በርዝማኔ ይበልጥ ነበር። ሆኖም ግን
የጉዳዩ ምስጢር የገባን ዘይነብ ከሞተች ብኃላ ነበር።
ነብዩ(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ለካስ እጀ ረዥም ያሉት
ቸር የሆነችዉ ለማለት ነበር። በርግጥ ከሁላችንም
የበለጠ ቸር የነበረችዉ ዘይነብ ነበረች። አላህ ስራዎን
ሁሉ ይዉደድላት።

https://t.me/sunah123
https://t.me/sunah123
❤1
ኑ!! ጠፊ በሆነችው ዱንያ ዘላለማዊ የሆነውን አኼራችንን እንገንባ!!!!

ተቀላቀሉ Share & join
👇👇👇👇👇

https://t.me/bilalibnurebahgroup
❤1
ውድ የፉሪ አቡበከር መስጂድ የቅዳሜና እሁድ የቁርኣን ትርጉም ማብራሪያ ደርስ ታዳሚዮች በረመዳን ምክንያት ተቋርጦ የነበረው ፕሮግራም ከነገ ቅዳሜ መጋቢት 26/2018 ሸዋል 16/1447 አመተ ሂጅሪያ የሚጀመር መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን ።
👍1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ውድ ሸይኻችን ሸይኽ ሙሀመድ ሙሳ ዳዕዋ ጀምረዋል
ውዱ ሸይኻችን ሸይኽ አቡዘር ጀምሯል
❤1
በመቀጠል ውዱ ሸይኻችን ሸይኽ ሙሀመድ ሀያት የሚቀጥሉ ይሆናል
Bilal Gallery
Photo
6).ኡሙ ሀቢባህ(ረምላህ ቢንት አቡ ሱፍያን):-------

ሙሉ ስሟ ረምላህ ቢንት አቡ ሱፍያን ሲሆን እስከ መካ
መከፈት ድረስ የቁረይሽ አጋሪዎች ዋና መሪ የነበረው
የአቡ ሱፍያን ቢን ሀርብ ልጅ ናት። ምንም እንኳን አባቷ
በዚያን ጊዜ አጋሪ ቢሆንም እሷ ግን ኢስላምን ተቀብላ
ነበር። ረምላህ(ረ.ዐ) በኢስላም ላይ እያለች ያጋጠማትን
ማንኛውንም መከራና ችግር የአላህን ምንዳ በማስታወስ
በትእግስት አሳልፋለች። ባሏ እንደርሷው ሙስሊም
የነበረው ዑበይዱላህ ኢብኑ ጃህሽ ሲሆን ሙስሊሞች
ሁሉ መካ ላይ የካሀዲያኑ ግፍና ጭቆና ሲበረታባቸው
ሁለቱ ጥንዶች ወደ ሀበሻ ከተሰደዱት ሰዎች ጋር በመሆን
ከሄዱ ቡኃላ እዚያ እያሉ ሐቢባህ የምትባል ልጅ ወለዱ።
ኡሙ ሀቢባህ(ረ.ዐ) ልክ እንደ ሎሎቹ አብረዋት የተሰደዱ
ሙስሊሞች ሁሉ በሀበሻ ሀገር የሚደርስባትን
የባይተዋርነት ስሜት አንድ ያልጠበቀችው ሁኔታ
እስኪገጥማት ደረስ ተቋቁማው ትኖር ነበር።
የኡሙ ሀቢባህ(ረ.ዐ) ባለቤቴ ዑበይዱላህ ኢብኑ ጀህሽ
መጠጥ መጣት ይጀምርና እስልምና ያስጠለዋል።
እምነቱንም ቀየረ(ከፈረ)። ይባስ ብሎ ሚስቱን ወደ ኩፍር
ይጠራታል። እሷም ከእስልምና ፍንክች እንደማትል
ገለፅችለት። ከዚያ ቡኃላ አስካሪ መጠጥ አብዝቶ
መውሰድ ጀመረ። በዚያ ሁኔታ ብዙም መቆየት አልቻለም።
ወዲያው ሞተ። ኡሙ ሀቢባህ(ረ.ዐ) ይህ ከሆነ ቡኃላ
ከሀገሯ ውጪ በባይተዋርነት መኖሯ ሳያንሳት ባል አልባ
በመሆን የብቸኝነት ህይወት ለመግፋት ተገደደች።
እንደዚያም ቢሆን ይህን ሁሉ ትካዜና ብቸኝነቷን በፅናትና
በታላቅ ትእግስት ተቋቁማ ነበር የቆየችው። ምክንያቱም
ሀያሉ አላህ በቅዱስ ቃሉ የሚከተለውን ማለቱን
ታዉቃለችና:-
ﻓَﺈِﺫَﺍ ﺑَﻠَﻐْﻦَ ﺃَﺟَﻠَﻬُﻦَّ ﻓَﺄَﻣْﺴِﻜُﻮﻫُﻦَّ ﺑِﻤَﻌْﺮُﻭﻑٍ ﺃَﻭْ ﻓَﺎﺭِﻗُﻮﻫُﻦَّ ﺑِﻤَﻌْﺮُﻭﻑٍ
ﻭَﺃَﺷْﻬِﺪُﻭﺍ ﺫَﻭَﻱْ ﻋَﺪْﻝٍ ﻣِّﻨﻜُﻢْ ﻭَﺃَﻗِﻴﻤُﻮﺍ ﺍﻟﺸَّﻬَﺎﺩَﺓَ ﻟِﻠَّﻪِ ۚ ﺫَٰﻟِﻜُﻢْ ﻳُﻮﻋَﻆُ ﺑِﻪِ ﻣَﻦ
ﻛَﺎﻥَ ﻳُﺆْﻣِﻦُ ﺑِﺎﻟﻠَّﻪِ ﻭَﺍﻟْﻴَﻮْﻡِ ﺍﻟْﺂﺧِﺮِ ۚ ﻭَﻣَﻦ ﻳَﺘَّﻖِ ﺍﻟﻠَّﻪَ ﻳَﺠْﻌَﻞ ﻟَّﻪُ ﻣَﺨْﺮَﺟًﺎ
ﻭَﻳَﺮْﺯُﻗْﻪُ ﻣِﻦْ ﺣَﻴْﺚُ ﻟَﺎ ﻳَﺤْﺘَﺴِﺐُ ۚ ﻭَﻣَﻦ ﻳَﺘَﻮَﻛَّﻞْ ﻋَﻠَﻰ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﻓَﻬُﻮَ ﺣَﺴْﺒُﻪُ ۚ ﺇِﻥَّ
ﺍﻟﻠَّﻪَ ﺑَﺎﻟِﻎُ ﺃَﻣْﺮِﻩِ ۚ ﻗَﺪْ ﺟَﻌَﻞَ ﺍﻟﻠَّﻪُ ﻟِﻜُﻞِّ ﺷَﻲْﺀٍ ﻗَﺪْﺭًﺍ
ጊዜያቸውንም ለመዳረስ በተቃረቡ ጊዜ በመልካም
ያዙዋቸው፡፡ ወይም በመልካም ተለያዩዋቸው፡፡ ከእናንተም
ውስጥ ሁለት የትክክለኛነት ባለቤቶችን አስመስክሩ፡፡
ምስክርነትንም ለአላህ አስተካክሉ፡፡ ይህ በአላህና
በመጨረሻው ቀን የሚያምን የኾነ ሰው ሁሉ በእርሱ
ይገሰጽበታል፡፡ አላህንም የሚፈራ ሰው ለእርሱ መውጫን
ያደርግለታል፡፡ ከማያስበውም በኩል ሲሳየን ይሰጠዋል፡፡
በአላህም ላይ የሚጠጋ ሰው እርሱ በቂው ነው፡፡ አላህ
ፈቃዱን አድራሽ ነው፡፡ አላህ ለነገሩ ሁሉ የተወሰነ ጊዜን
በእርግጥ አድርጓል፡፡ (አል-ጦላቅ 2-3)
ኡሙ ሀቢባህ(ረ.ዐ) ባሏ ከመሞቱ ከትንሽ ቀን በፊት
በህልሟ ቤቷ ውስጥ ጨረቃ ገብቶ ቤቱን ሲያበራ አየች።
የጨረቃው መታየት ግራ አጋብቷት ዱአ አደርገች አላህ
ሆይ! ኸይር ነገር ግጠመኝ አለች።
ረሱል(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሰቡ:- “ኡሙ
ሀቢባህን ባገባት በእኔና በአቡ ሱፍያን መካከል ያለው
ክፍተት ይቀንሳል” ምክንያቱም አቡ ሱፍያን ማለት
የቁረይሾች ዋና ነው ስለሆነ ጋብቻውን ለእርቅ ፈልገው
ነው። በሁለተኛ ደረጃ ልጅ አላት ባሏ የሞተባት እንስት
ነች። በአላህ ትዛዝ ለጋብቻው መህር ከረሱል(ሰለላሁ
አለይሂ ወሰለም) ውክልና ከተሰጣቸው ከንጉስ ነጃሺ
በ400 ዲናር ሰርጉ ተደረገ። ብዙ ሀዲያዎችንም ከንጉስ
ነጃሺ ተቀበለች። ኡሙ ሀቢባህ(ረ.ዐ) የረሱል(ሰለላሁ
አለይሂ ወሰለም) ሚስት ሆነች። በብዙ ሰሀቦች ታጅባ ወደ
መዲና ሄደች። ከንጉስ ነጃሺ ለረሱል(ሰለላሁ አለይሂ
ወስለም) የተበረከተውን ስጦታም አስረከበች።
ከስጦታዎቹ መሀል 3 ዱላ(ከረዛን) ነበር። እነዚን ዱላ
አንዱን ለአቡበከር አንዱን ለዑመር አንዱን ደግሞ ያ
ቢላል አሉና ና ይሄ ከወንድምህ አህመድ ነጃሺ የመጣ
ነው አሉትና ሰጡት። የኡሙ ሀቢባህ(ረ.ዐ) አባት አቡ
ሱፍያን ልጃቸውን ረሱል(ሰለላሁ አለይሂ ወሰላም)
እንዳገቧት ሲሰሙ ተንቀጠቀጠ፣ ተገረመ። ትላንት
ሙስሊሞችን ሰብስበን ማቃጠል ነበረብን ሲል የነበረው
ረሱል(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሲሰድብ የነበረው አሁን
ቀዝቀዝ አለ። እንዲህም ሲል ተናገረ ልጄን ያገባት እኳ
በጣም ክብር ያለውን ሰው ነው። ተመለከታቹ አደል
የአላህና የረሱል(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሀሳብ ተሳካ።
ትላንት ረሱል(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለምን) ለመግደል
ይፈልግ የነበረው ዛሬ ግን አወደሳቸው። በማወደስም
አልተወገደም እስልምናም ተቀበለ። እስልምናን በመቀበል
ብቻ አላበቃም። ትልቅ ዳኢም ሆነ የእስልምናን ብርሀን
የበላይ ለማድረግ ከጠላት ተዋግቷል አጂብ በጣም
የሚገርም ታሪክ ነው። ለአላህ ጥራት ይገባው። ጠላቶች
የረሱል(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ብዙ ሚስት ማግባት
ለስጋዊ ስሜት ብለው ይናገራሉ እውነታው ግን ታሪክ
ይናገራል። ለጥበብ፣እዝነት፣ለሰላም ነበር። ኡሙ ሀቢባህ
(ረ.ዐ) አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላት።

https://t.me/sunah123
❤1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Bilal Gallery
Photo
7).መይሙና ቢንት አል ሀሪስ(ረ.ዐ)፦


በሺዎች የሚቆጠሩ ሴቶች ለረሱል(ሰለላሁ አለይሂ
ወሰለም) ነፍሴን ሰጥቼዎታለው በማለት ለትዳር
ቢጠይቁም ምላሽ የሰጡት ግን ለመይሙና ብቻ ነው።
መይሙና ቢንት አል ሀሪስ ኢብን ሃዚን ኢብን ቡጅይር
የዐባስ(ረ.ዐ) ባለቤት የሆነችው የኡም አል-ፈድል እህት
የኻሊድ ኢብን አል ወሊድና የአብደላህ ኢብን ዐባስ(ረ.ዐ)
አክስት ስትሆን ከቁረይሽ የተከበሩ ወይዛዝርት መካከልም
ተጠቃሽ ናት። መይሙና ከመጀመርያ ባሏ
ባለመስማማታቸው ይፋታሉ። ለብዙ ጊዚያት ያለባል
ከቆየች ቡኃላ ሁለተኛ ባል ታገባለች ይሄ ያገባችው ሰውዬ
ደግሞ ይሞታል። ስለዚህ መይሙና ሁለት ጊዜ አግብታ
የፈታች እንስት ናት ማለት ነው። መይሙና(ረ.ዐ) ወደ
ረሱል(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሄዳ እንዲህ አለቻቸው:-
“ያ ረሱለላህ ነፍሴን ሰጥቼዎታለው አለች።” ይህ በመሆኑ
አላህ ይህን የቁርአን አንቀፅ አወረደ
ﻳَﺎ ﺃَﻳُّﻬَﺎ ﺍﻟﻨَّﺒِﻲُّ ﺇِﻧَّﺎ ﺃَﺣْﻠَﻠْﻨَﺎ ﻟَﻚَ ﺃَﺯْﻭَﺍﺟَﻚَ ﺍﻟﻠَّﺎﺗِﻲ ﺁﺗَﻴْﺖَ ﺃُﺟُﻮﺭَﻫُﻦَّ ﻭَﻣَﺎ ﻣَﻠَﻜَﺖْ
ﻳَﻤِﻴﻨُﻚَ ﻣِﻤَّﺎ ﺃَﻓَﺎﺀَ ﺍﻟﻠَّﻪُ ﻋَﻠَﻴْﻚَ ﻭَﺑَﻨَﺎﺕِ ﻋَﻤِّﻚَ ﻭَﺑَﻨَﺎﺕِ ﻋَﻤَّﺎﺗِﻚَ ﻭَﺑَﻨَﺎﺕِ ﺧَﺎﻟِﻚَ
ﻭَﺑَﻨَﺎﺕِ ﺧَﺎﻟَﺎﺗِﻚَ ﺍﻟﻠَّﺎﺗِﻲ ﻫَﺎﺟَﺮْﻥَ ﻣَﻌَﻚَ ﻭَﺍﻣْﺮَﺃَﺓً ﻣُّﺆْﻣِﻨَﺔً ﺇِﻥ ﻭَﻫَﺒَﺖْ ﻧَﻔْﺴَﻬَﺎ
ﻟِﻠﻨَّﺒِﻲِّ ﺇِﻥْ ﺃَﺭَﺍﺩَ ﺍﻟﻨَّﺒِﻲُّ ﺃَﻥ ﻳَﺴْﺘَﻨﻜِﺤَﻬَﺎ ﺧَﺎﻟِﺼَﺔً ﻟَّﻚَ ﻣِﻦ ﺩُﻭﻥِ ﺍﻟْﻤُﺆْﻣِﻨِﻴﻦَ ۗ ﻗَﺪْ
ﻋَﻠِﻤْﻨَﺎ ﻣَﺎ ﻓَﺮَﺿْﻨَﺎ ﻋَﻠَﻴْﻬِﻢْ ﻓِﻲ ﺃَﺯْﻭَﺍﺟِﻬِﻢْ ﻭَﻣَﺎ ﻣَﻠَﻜَﺖْ ﺃَﻳْﻤَﺎﻧُﻬُﻢْ ﻟِﻜَﻴْﻠَﺎ ﻳَﻜُﻮﻥَ
ﻋَﻠَﻴْﻚَ ﺣَﺮَﺝٌ ۗ ﻭَﻛَﺎﻥَ ﺍﻟﻠَّﻪُ ﻏَﻔُﻮﺭًﺍ ﺭَّﺣِﻴﻤًﺎ
አንተ ነቢዩ ሆይ! እኛ እነዚያን መህሮቻቸውን የሰጠሃቸውን
ሚስቶችህን፣ አላህ ባንተ ላይ ከመለሰልህም እነዚያን
እጅህ የጨበጠቻቸውን ምርኮኞች፣ እነዚያንም ከአንተ ጋር
የተሰደዱትን የአጎትህን ሴቶች ልጆች፣ የአክስቶችህንም
ሴቶች ልጆች፣ የየሹማህንም ሴቶች ልጆች፣
የየሹሜዎችህንም ሴቶች ልጆች (ማግባትን) ለአንተ
ፈቅደንልሃል፡፡ የአመነችንም ሴት ነፍሷን (ራሷን) ለነቢዩ
ብትሰጥ ነቢዩ ሊያገባት የፈለገ እንደ ኾነ ከምእምናን ሌላ
ላንተ ብቻ የጠራች ስትኾን (ፈቀድንልህ)፡፡ በእነርሱ
(በምእምናን) ላይ በሚስቶቻቸውና እጆቻቸው
በጨበጧቸው (ባሮች ነገር) ግዴታ ያደረግንባቸውን
በእርግጥ ዐውቀናል፡፡ ባንተ ላይ ችግር እንዳይኖር
(ያለፉትን ፈቀድንልህ)፡፡ አላህም መሓሪ አዛኝ ነው፡፡ (አል
አህዛብ 50)
መይሙና(ረ.ዐ) በዚህ አንቀፅ መሰረት የረሱል(ሰለላሁ
አለይሂ ወሰለም) ሚስት ሆነች በራሷ ፍቃድ መጥታ
ነፍሷን በመስጠቷ ያለ ማህር አገቧት ማለት ነው።
ከቁርአኑ አንቀፅ እንደምንረዳው ይህ አይነት ጋብቻ
የተፈቀደው ለውዱ ነቢ ሙሀመድ(ሰለላሁ አለይሂ
ወሰለም) ብቻ ነው። ብዙ ሴቶች ልክ እንደ መይሙና(ረ.ዐ)
ለረሱል(ሰለላሁ አለይሂ ወሰላም) ነፍሴን ሰጥቼዎታለው
ብለው ነበር ነገር ግን ከመይሙና ውጪ ማንንም
አልተቀበሉም።
መይሙና(ረ.ዐ) የነብዩ ሙሀመድ(ሰለላሁ አለይሂ
ወሰለም) ባለቤት በመሆን ከሌሎች ሚስቶቻቸው ጋር
ተቀላቀለች። ኢስላም የሚያዘውን ኢባዳ በመፈፀም
ግንባር ቀደም ነበረች። ለባሏ እንዲሁ ታዛዥ ነበረች።
አላህ መልካም ስራዎን ይቀበላት።

https://t.me/sunah123
❤1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Bilal Gallery
Photo
8).ጁወይሪያህ ቢንት አል ሀሪስሀሪስ፦


✅ረሱል(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ጁወይሪያህን
በማግባታቸው ወደ 700 የሚጠጉ ከሀዲያን እስልምናን
ተቀብለዋል። ሙሉ ታሪኩን ያንብቡት ይገረማሉ።
ሙሉ ስሟ ጁወይሪያህ ቢንት አል ሀሪስ ኢብን አቡ ዲራር
ኢብን ለቢብ አል ኹዛኢያ ነው። ጁወይሪያህ(ረ.ዐ) ከጎሳዎ
መሳፍንት ወገን የምትወደድና ቆንጆ ሴት ስትሆን
በሙስሊሞች እጅ ስትገባ እድሜዋ 20 ቤቱ ውስጥ
ነበር። በኑ ሙስጠሊቆች ከመዲና ራቅ ብለው የሚገኙ
ህዝቦች ናቸው። እነዚህ ህዝቦች ረሱል(ሰለላሁ አለይሂ
ወሰለም) እና ሰሀቦችን ሊያጠቁ እንደሆኑ ለረሱል(ሰለላሁ
አለይሂ ወሰለም) ዜናው ይደርሳቸዋል። ይህን ጊዜ
ብልሀተኛው ነቢይ ሙሀመድ(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)
ሳንቀደም እንቅደም በማለት ወታደር ይዘው ከበቧቸው።
ነገራቸው ከዛም ጦርነት ተከፈተ። ለሰዐአታት ያክል
ከተዋጉ ቡኃላ ጦርነቱ በሙስሊሞች ድል ይጠናቀቃል።
ብዙ የጦርነት መሳሪያዎች እና 350 የሚጠጉ ምርኮኛ
ወታደሮች አንዳንድ ኡለማዎች 700 ነው ይላሉ፣ ወርቅ፣
ጨርቅ ይህን ይዘው ተመለሱ። ይህን የውጊያ ውርስ
ለረሱል(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ይሰጧቸዋል። እሳቸው
ሁሉንም ለሰሀቦቻቸው አከፋፈሉት። ጁወይርይ(ረ.ዐ)
ከተማረኩት ምርኮኞች አንዷ ናት። ምርኮ ለተዋጊዎች
ሲከፋፈል ጁወይሪያ ለሳቢት ኢብን ቀይስ ደረሳት።
ጁወይሪያ(ረ.ዐ) አቧቷም ሆነ ባሏ ትልልቅ ነገስታት ነበሩ።
በምቾት ያደገች ናት። ሳቢት ደግሞ የገጠር ልጅ፣ ደሀ
ነው። ከሱ ጋር መሆንን አልወደድችም። ሳቢት ደግሞ ነፃ
አውጣኝ ስትለው 9 እቁያ ወርቅ ጠየቃት። ከዛም ወደ
ረሱል(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ዘንድ ሄዳ ያ ረሱለላህ!
እኔ ምርኮኛ ነኝ። ምርኮ ሲከፋፈል እጣ የደረሰኝ ደግሞ
ከሳቢት ኢብን ቀይስ ነው። እኔ ደግሞ ከእሱ ጋር መሆንን
አልፈለኩም። ነፃ በለይ ስለው 9 እቁያ ጠየቀኝ እኔ
ምርኮኛ ነኝ ይሄ ሁሉ ገንዘብ የለኝም በሀገሬ ቢሆን
እሰጠው ነበር ብላ አቤቱታ አቀረበች። ስምሽ ማነው
አሏት ጁወይሪያ ቢንት አል ሀሪስ አለች። ተገርመውም
የአል ሀሪስ ልጅ ነሽ አሏት። አዎ አለች። የተገረሙት
የንጉስ ልጅ ስለነበረች ነው። ባልሽስ እገሌ ብላ ነገረቻቸው
እሱም ንጉስ ነበር በጦርነቱ ሞቷል። አስገራሚው ታሪክ
እዚህ ጋር ይጀመራል። የረሱል(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)
ብዙ ሴት ማግባት የሚያንገሸግሻቹ እውነታውን
ተመልከቱ። ነብዩ(ሰለላሁ አለይሁ ወሰለም) እንዲህ አሏት
ከዚህ የተሻለ ባቀርብልሽ አትቀበይኝም? አሏት እሷም
በጉጉት ምንድን ነው እርሱ የአላህ መልእክተኛ አለች?
“እኔ ነፃ እንድትሆኚ ክፍያውን እፈፅማለው ከዚያም
አገባሻለው አሏት” ጁወይሪያ የቀረበላት ምርጫ በጣም
ስላስደሰታት ያለማቅማማት እሺ ነው ያለችው። በዚህ
ሁኔታ የረሱል(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሚስት ሆነች።
በማግስቱ ሰሀቦች ተሰባስበው ጅወይሪያ የረሱል(ሰለላሁ
አለይሂ ወሰለም) ሚስት ሆነች። የጁወይሪያ ቤተሰቦች
እኮ የረሱል(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) አማች ሆኑ ማለት
ነው። አዎ ብለው ተስማሙ። እንዴት እኛ የረሱል(ሰለላሁ
አለይሂ ወሰለም) አማቾች ምርኮኛ አርገን እንይዛለን አሉ?
ይህማ አይሆንም አሉ። ለነቢያችን(ሰለላሁ አለይሂ
ወሰለም) ክብር ስንል የእሳቸውን አማቾች(የእሷን
ቤተሰቦች) ነፃ አንልም ተባባሉ? እሺ ብለው ተስማሙ
ትላንት ባርያ የነበሩ እንደፈለጉ መሸጥ መለወጥ
የሚችሏቸውን ሰዎች ለረሱል(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)
ክብር ሲሉ ነፃ አሏቸው። ሱብሀነላህ የሚገርም ነው። እነዛ
ነፃ የተባሉት ሰዎች ደግሞ ይሰበሰቡና እናንተ ሰዎች ከእኛ
መሀል ነብያቸው ስላገባ ለሱ ክብር ሲሉ ነፃ አሉን። መዲና
ብንሄድ ኖሮ እንሸጥ ነበር። እኛስ ለልጃችን ስንል ለአላህ
ስንል ወደ እስልምና ለምን አንገባም? ብለው ሁሉም ወደ
ረሱል(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) በመሄድ እስልምና ገቡ።
አይሻ(ረ.ዐ) እንዲህ ትላለች:- ረሱል(ሰለላሁ አለይሂ
ወሰለም) ጁወይሪያን(ረ.ዐ) የመጀመርያ ቀን ወደ ቤት
ይዘዋት ሲገቡ በጣም ቀንቼ ነበር። ነገር ግን በእሷ
ምክንያት 700 ወጣቶች መስለማቸውን ስሰማ እየሮጥኩ
ሄድኩና እቅፍ አድርጌ “ያ ጁወይሪያ ከረሱል(ሰለላሁ
አለይሂ ወሰለም) ሚስቶች እንዳንቺ የተባረከ አላየሁም።
ምክንያቱም በአንቺ ምክንያት በመቶ የሚቆጠሩ ሰዎች
ወደ እስልምና ገብተዋል።” እናም ወደድኳት አለች። አያቹ
አደል የመጋባቱን ጥበብ። እንደው ጠላቶች
የሚያቅጥላቸው ለምን 9 ለምን 13 አገቡ አደል የሚሉት
ለእንደዚህ አላማ 1000 ቢያገቡ? ከ 1000 የጠላት
(ቀቢላ) ጋር ቢታረቁ ነውር ነው? ነውር አደለም። ነገር ግን
ረሱል(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ያገቧቸው ሚስቶች አንዷ
ልጆች ያሏት፣ አንዷ ሁለቴ የትፈታች፣ አንዷ ባሏ
የሞተባት፣ አንዷ በሽተኛ፣ አንዷ ትልቅ ሴት ነበሩ።
https://t.me/sunah123
❤1