Bilal Gallery
3.88K subscribers
270 photos
9 videos
3 files
259 links
መቼም ሰው ነኝና ስህተት አይታጣብኝም ስህተት ካያችሁ በዚህ @Amir8979 አድርሱኝ ከስህተቴ ሁሌም ተመላሽ ነኝ! "ጥፋቴን በነገረኝ ሙስሊም ሁሉ የአላህ እዝነት ይውረድ"
Download Telegram
Bilal Gallery
Photo
(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ወደ ዓኢሻ(ረ.ዐ) ቤት
ተዛዉረዉ እዚያ እርሷ ቀንና ሌሊት ትንከባከባቸዉ ጀመር።
ህመሙ የጠናባቸዉ በመሰላት ጊዜ “አባትና እናቴ
መስዋዕት ይሁኑልዎ የአላህ መልእክተኛ!(ሰለላሁ አለይሂ
ወሰለም) ትላለች። የአላህ መልእክተኛ(ሰለላሁ አለይሂ
ወሰለም) የመጨረሻዋን ህይታቸዉን የተነፈሱት
ጭንቅላታቸዉን በዓኢሻ(ረ.ዐ) ደረት ላይ እንዳደረጉ
ነበር።
የአላህ መልእክተኛ(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) የተቀበሩት
በሞቱበት ቦታ ላይ ነበር፤ ያም የዓኢሻ(ረ.ዐ) መኖርያ ቤት
ሲሆን ጉድጓድ እዚያዉ ተቆፍሮ ግብዓተ መሬቱ ተፈፀመ።
ተወዳጇና ብልኋ ባልተቤታቸዉ ዓኢሻ(ረ.ዐ) ከእርሳቸዉ
ጋር የቆየችዉ አስር ለሚሆኑ ዓመታት ብቻ ሲሆን
እርሳቸዉን በሞት ካጣች ብኃላ ግን ብቻዋን ሃምሳ
ለሚሆኑ ዓመታት አሳልፋለች። እነዚያን ሁሉ ዓመታትም
ከአራቱም ማዕዘናት የሚመጡትን ወንዶችም ሆኑ ሴቶች
አላህ ከሰጣት የእዉቀት ፀጋዋ በማካፈልና ከሞላ ጐደል
መጪዉን ትዉልድ በመቅረፅ፣የአላህን ሃይማኖት ለሰዎች
በማስተላለፍ፣ፈጣሪዋን፣በማምለክና የእርሱን ዉዴታ
የሚያስገኙ በጐ ምግባራትን በመፈፀም ነበር
ያሳለፈቻችዉ። ዓኢሻ(ረ.ዐ) ከረሱል(ሰለላሁ አለይሂ
ወሰለም) በቆየችባቸዉ አስርት አመታት ከእነዚህ
ጊዚያቶች አብዛኛዉን ያሳለፈችዉ የአላህ መመርያ
የሆኑትን ሁለት ታላላቅ የእዉቀት ምንጮች ቁርአንና ሱናን
በማጥናት ነበር። ዓኢሻ(ረ.ዐ) ቁርአንን በልባቸዉ
ከቋጠሩት ሶስት የነብዩ(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሚስቶች
አንዷ ነበረች። ሁለቱ ደግሞ ሀፍሷ ቢንት ዑመር እና ዑሙ
ሰለማ ነበሩ። ሀፍሷ እና ዓኢሻ(ረ.ዐ) ነብዩ(ሰለላሁ አለይሂ
ወሰለም) ካለፉ ቡኃላ የተከተበ የቁርዐን ቅጅ ነበራቸዉ።
ሀዲስ ወይንም የነብዩን ንግግር በተመለከተ ዓኢሻ(ረ.ዐ)
ከ2000 በላይ ሀዲሶችን ካስተላለፉልን አራት አንጋፋ
ሰሀባዎች(አቡ ሁረይራ፣አብደላህ ኢብን ዑመር፣አነስ
ኢብን ማሊክ) መካከል ትመደባለች።
ታላቋ የእዉቀት እመቤት በረመዳን ወር 17ኛዉ ቀን
በዕለተ ማክሰኞ 57ኛዉ ዓ.ሂ.  ይህችን አለም
ተሰናብታለች። አላህ ይዘንላት መልካም ስራዎቿንም
ይዉደድላት

https://t.me/sunah123
https://t.me/sunah123
❤1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Bilal Gallery
Photo
4).ሐፍሳህ ቢንት ዑመር፦

ሐፍሳህ ከግንባር ቀደሞቹ የነብዩ ሙሀመድ(ሰለላሁ
አለይሂ ወሰለም) የቅርብ ሰዎች መካከል የሆኑት ኢብኑ
አል-ኸጣብ(ረዲያላሁ አንሁ) ልጅ ነበረች። ሀፍሳህ
(ረዲያላሁ አንሀ) ገና በአስራዎቹ የእድሜ ክልል ዉስጥ
እያለች ከቁረይሽ ጐሳ የሚወለደዉን ሁነይስ ኢብኑ
ሁዘይፋ ኢብኑ ቀይስ አስ-ሰሃሚን(ረዲያላሁ አንሁ)
አግብታ ነበር። ይህ ሰዉ የሁለት ስደቶች(ወደ ሀበሻና ወደ
መዲና) ባለቤት ሲሆን የበድርንና የኡሑድን ዘመቻዎችንም
ተካፍሏል። በኡሑድ ዉሎ ክፉኛ ከቆሰለ ቡኃላ በዚያዉ
ጦርነት ብዙም ሳይቆይ ሞቷል። ዑመር(ረዲያለሁ ዐንሁ)
ልጃቸዉ ገና በወጣትነቷ ባሏ በመሞቱና ብቸኛ በመሆኗ
ሀዘን ይሰማቸዉ ነበር። ይህን ሀዘናቸዉ ለመግፈፍ
ቆርጠዉ ተነሱ። በመጀመርያ ለዚህ ጉዳይ ያጩት
ጓደኛቸዉን አቡበከርን(ረዲያላሁ አንሁ) ሲሆን ወደርሳቸዉ
ሄደዉም ልጃቸዉን ሃፍሳን እንዲያገቡ በግልፅ ጠየቋቸዉ።
እርሳቸዉ ያሰቡት ይችን አባቷ የኢስላም ክንድ የሆነ
ወጣት ለማግባት አቡበከር(ረዲያላሁ አንሁ) አያቅማሙም
ብለዉ ነበር። ሆኖም ግን አቡበከር(ረዲያላሁ አንሁ)
የጓደኛቸዉን ሃሳብ በፅሞና ካዳመጡ ቡኃላ ምንም
አስተያየት ሳይሰጡ ዝም አሉ። ዑመር(ረዲያላሁ አንሁ)
ግን የተፈጠረዉን ነገር ባለማመን ልባቸዉ እንደ ተሰበረ
ወደ ቤታቸዉ ተመለሱ። ከዚያም ይህንኑ ክቡር ሀሳብ
ይዘዉ ወደ ዑስማን ኢብኑ ዐፍፋን ዘንድ ሄዱ። ይህ
ከመሆኑ ከጥቂት ጊዚያት በፊት የነብዩ ሙሀመድ(ሰለላሁ
አለይሂ ወሰለም) ልጅና የዑስማን(ረዲያላሁ አንሁ)
ባለቤት የነበረችዉ ሩቂያ(ረዲያላሁ አንሀ) ሞታ ነበር።
ዑመር(ረዲያላሁ አንሁ) ልጃቸዉን ሐፍሳህን
እንዲያገቡላቸዉ ዑስማንን ሲጠይቋቸዉ ዑስማን
(ረዲያላሁ አንሁ) በትህትና እንዲህ አሉ፦ “አሁን ባለሁበት
ሁኔታ ማግባት አልሻም።”
የዑመር(ረዲያላሁ አንሁ) መንፈስ አሁን ደግሞ የበለጠ
ተከፋ። ከአቡበከር(ረዲያላሁ አንሁ) ያልጣበቁት ሁኔታ
እንዳጋጠማቸዉ ሁሉ ከዑስማንም ቢሆን ያገኙት
ያልጠበቁትን መልስ ነበርና። ዑመር(ረዲያላሁ አንሁ)
ቅስማቸዉ ድቅቅ እንዳለ ወደ ነብዩ ሙሀመድ(ሰለላሁ
አለይሂ ወሰለም) በመሄድ አቡበከርና ዑስማን(ረዲያላሁ
አንሁማ) ያደረጉትን ነገር ነገሯቸዉ። በዚህ ጊዜ ነብዩ
ሙሀመድ(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ፈገግ ብለዉ እንዲህ
አሏቸዉ፦
“ሐፍሳህ ከዑስማን የሚበልጥን ሰዉ ታገባለች።
ዑስማንም ከሀፍሳህ የምትበልጥ ሴት ያገባል።” (ቡኻሪ
ዘግበዉታል)
ሐፍሳህ ከዑስማን የተሻለ ሰዉ ታገባለች ያሉት እሳቸዉ
ሀፍሳን እንደሚያገቧት ለዑመር እየነገሯቸዉ ነዉ። ዑስማንን
ደግሞ ከሀፍሳ የበለጠች ያገባል ያሉት ዑስማንን
ለልጃቸዉ እሙኩልሱም ሊድሩት ስለፈለጉ ነዉ። በዚህ
ጊዜ ዑመር(ረዲያላሁ አንሁ) ይህን ከዚህ በፊት አስበዉት
የማያዉቁትን ዜና ሲሰሙ እጅግ ተደሰቱ። ነብዩ(ሰለላሁ
አለይሂ ወሰለም) ሀፍሳህ ቢንት ዑመርን(ረዲያላሁ አንሀ)
በማግባታቸዉ የመዲና ህዝብ ሁሉ ተደሰተ። ሐፍሳህ
(ረዲያላሁ አንሀ) የነብዩ ሙሀመድ(ሰለላሁ አለይሂ
ወሰለም) ሚስት በመሆን ሁሉም ሴቶች የሚመኙትን
የምእመናን እናት የመሆን ደረጃን ተጐናፀፈች። ረሱል
(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሀፍሷን ፈተዋት ነበር። ከዚያም
ጅብሪል(አለይሂ ሰላም) እንዲመልሷት እንደሚከተለዉ
በማለት ካዘዛቸዉ ቡኃላ መልሰዋታል፦
“ሐፍሳህን(ረዲያለሁ አንሀ) የነብዩን(ሰለላሁ አለይሂ
ወሰለም) መልሳት እርሷ ቀን ትፆማለች በሌሊትም ለሰላት
ትቆማለችና።”
ሀፍሳህ(ረዲያላሁ አንሀ) አላህን በፍፁም ተመስጦ
በማምለክ፣በመፆም፣ሌሊት በመቆም እንዲሁም
የተሰጣትን የቅዱስ ቁርአን ግልባጭ በሚገባ በመጠበቅ ፣በመሀፈዝ
ስራ ተጠምዳ ህይወቷን ትገፋ ነበር። የቁርአን ኮፒ
ጠባቂና ተንከባካቢ የነበረችዉን የምእመናን እናት ሀፍሳ
(ረዲያላሁ አንሀ) ስራ ሁሉ አላህ ይዉደድላት
ይቀበላትም። አሚን!

https://t.me/sunah123
ታላቅ የኦንላይን የዳዕዋ እና
        የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም

           የተከበራችሁ የሱና ቤተሰቦች እነሆ የፊታችን ጁመአ ከኢሻ ብሀላ 2:30 ሸዋል 15/1447 هـ (መጋቢት 25/7/2018)የቢላል ኢብኑ ረባህ መድረሳ እና መርከዝ የዳዕዋና ገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም  በመሻይኾችና ኡስታዞች ተዘጋጅቶ ይጠብቃችኋል
።

      🪑የእለቱ ብርቅዬ እንግዶች

❶🎙️ሸኽ አቡዘር ሀሰን ከኮምቦልቻ (ሀፊዘሁሏህ)
❷ 🎙️ ሸኽ ሙሀመድ ሀያት ከሀራ (ሀፊዘሁሏህ)
❸ 🎙️ ሸኽ ሙሀመድ ሙሳ ከአዲስ አበባ (ሀፊዘሁሏህ)
❹🎙️ኡስታዝ መሀመድ ሰልማን ከስልጤ (ሀፊዘሁሏህ)
❺🎙️ኡስታዝ አቡ ሙስሊም ከዱባይ(ሀፊዘሁሏህ)
❻ በአላህ ፍቃድ ሌሎችም ወንድሞች ይኖራሉ

        ቢላል  ኢብኑ ረባህ  መድረሳ እና መርከዝ  በስሩ  አምስት መድረሳና የወንዶች አዳሪና ተመላላሽ መርከዝ እንዲሁም የሴቶች ተመላላሽ መርከዝ በስሩ ያስተዳድራል። በአጠቃላይ ከ1000  በላይ ለሆኑ ተማሪዎች  የቂርአት(ደርስ) አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።አሁን ላይ ይህንን ቂርአት ለማስቀጠል የፋይናንስ ችግር ስላጋጠመን  መድረሳውን ለማስቀጠል  የሁላቹንም ድጋፍ እና  ትብብር ይሻል ።በመሆኑም ሁላችሁም  ባላችሁ አቅም ድጋፍ እንድታደርጉልን በአላህ ስም እንጠይቃችኋለን።

🕰የፕሮግራሙ ሰዐት በኢትዮ
🇪🇹2:30 (ማታ)
                         በሰዑዲያ 🇸🇦    8:30
                         በዱባይ   🇦🇪    3:30

      በሰአቱ በመገኘት የፕሮግራሙ እና የኸይር ተካፋይ ይሁኑ ለሌሎች ሼር በማድረግ አድርሱ

እንዳናረፍድ በግዜ እንገኝ

አካውንት ንግድ ባንክ፦1000742324242


አድራሻ፦👇👇👇👇👇👇
በቢላል ኢብኑ ረባህ መርከዝ ስም በተከፈተው የኢሞ ሩም ላይቭ የሚተላለፍበት ይሆናል
https://s.imoim.net/wPalwg?from=copy_link

https://t.me/bilalibnurebahmedresa
https://t.me/bilalibnurebahmedresa
አሰላሙ ዐለይኩም ወራህመቱላሂ  ወበረካቱህ

            ስለ ቢላል በጥቂቱ

ቢላል ኢብኑ ረባህ መድረሳ በወርሃ ሀምሌ በቀን 9; 2010 አ/ል (09/11/2010) በአዲስ አበባ ኮልፌ ቀራንዮ ልዩ ቦታው ካራቆሬ ውሀ ልማት አካባቢ  6 ተማሪዎችን ብቻ በመያዝ አንድ ሲል ጉዞውን ጀመረ።

    ከተጀመረ ጊዜ አንስቶ እለት ከእለት አመት ከአመት በየጊዜው አመርቂ እድገቶችን እያሳየ ዛሬ ላይ በካራ ቆሬ እና በተለያዩ ቦታዎች ወደ አምስት(❺) የሚጠጉ ቅርንጫፎችን በመክፈት እንዲሁም ከስሩ አል-ቡርሀን መድረሳ በኳስ ሜዳ እና ዳሩ-ነድዋ በአጃንባ የሚገኙ መድረሳዎችን እያስተዳደረ ለማህበረሰቡ የሚመቸውን የሰኣት መርሃግብር ከግምት በማስገባት :-

✅ ለተማሪዎች ከአስር እስከ መግሪብ

✅ ለእናቶች ከጠዋቱ 2:30 -5:00

✅ ለሴቶች ተመላላሽ  የሂፍዝ መርከዝ

✅ ለወንዶች ተመላላሽ እና አዳሪ  የሂፍዝ መርከዝ

በማመቻቸት የቁርኣን እና የኪታብ ደርሶችን
ከ1,100 በላይ ለሚሆኑ ተማሪዎች ተደራሽ እያደረገ ይገኛል። መድረሳችን ለሰባት አመታት በነበረው ቆይታ በአላህ ፈቃድ ደህና የሚባሉ መሬት የወረዱ እንቅስቃሴዎችን አኑሯል።
አሁን ላይ ግን በገጠመው የገንዘብ (የፋይናንስ) እጥረት ምክንያት እነኚህን መልካም አሻራዎች ማስቀጠል የከበደው ይመስላል።
የሁላችንም የሆነው መርከዝ አንግቦ የተነሳውን አላማ እና እቅድ ከግብ እንዲያደርስ  የሁላችንንም ትብብር ይሻል

" مَّن ذَا ٱلَّذِى يُقْرِضُ ٱللَّهَ قَرْضًا حَسَنًۭا فَيُضَٰعِفَهُۥ لَهُۥٓ أَضْعَافًۭا كَثِيرَةًۭ ۚ وَٱللَّهُ يَقْبِضُ وَيَبْصُۜطُ وَإِلَيْهِ تُرْجَعُونَ" [البقرة: 245]

" ያ ለአላህ መልካም ብድርን የሚያበድርና ለእርሱ (አላህ) ብዙ እጥፎች አድርጎ የሚያነባብርለት ማነው? አላህም ይጨብጣል፤ ይዘረጋልም፤ ወደ እርሱም ትመለሳላችሁ፡፡ "

        ኑ!! ጠፊ በሆነችው ዱንያ ዘላለማዊ የሆነውን አኼራችንን እንገምባ!!!!

💦 ለመድረሳው የመሬት ግዢን ያሳኩ

        💦 ለመድረሳው ቋሚ የገቢ ምንጭ ማቋቋሚያ ላይ የድርሻዎን ያስቀምጡ

እያልን ሀምሳ ሎሚ ለአንድ ሰው ሸክሙ ለሀምሳ ሰው ጌጡ ነውና ቢላል ኢብኑ ረባህ መድረሳን ወደ ላቀ ተቋም የማሻገር ሃላፊነት የሁሉም ሃላፊነት በመሆኑ ሁላችንም በቻልነው ልክ እና አቅም ሃላፊነታችንን እንወጣ ዘንድ የአክብሮት ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

           አካውንት
👉 1000742324242                          
👉

አሰላሙ ዐለይኩም ወራህመቱላሂ  ወበረካቱህ

            ስለ ቢላል በጥቂቱ

ቢላል ኢብኑ ረባህ መድረሳ በወርሃ ሀምሌ በቀን 9; 2010 አ/ል (09/11/2010) በአዲስ አበባ ኮልፌ ቀራንዮ ልዩ ቦታው ካራቆሬ ውሀ ልማት አካባቢ  6 ተማሪዎችን ብቻ በመያዝ አንድ ሲል ጉዞውን ጀመረ።

    ከተጀመረ ጊዜ አንስቶ እለት ከእለት አመት ከአመት በየጊዜው አመርቂ እድገቶችን እያሳየ ዛሬ ላይ በካራ ቆሬ እና በተለያዩ ቦታዎች ወደ አምስት(❺) የሚጠጉ ቅርንጫፎችን በመክፈት እንዲሁም ከስሩ አል-ቡርሀን መድረሳ በኳስ ሜዳ እና ዳሩ-ነድዋ በአጃንባ የሚገኙ መድረሳዎችን እያስተዳደረ ለማህበረሰቡ የሚመቸውን የሰኣት መርሃግብር ከግምት በማስገባት :-

✅ ለተማሪዎች ከአስር እስከ መግሪብ

✅ ለእናቶች ከጠዋቱ 2:30 -5:00

✅ ለሴቶች ተመላላሽ  የሂፍዝ መርከዝ

✅ ለወንዶች ተመላላሽ እና አዳሪ  የሂፍዝ መርከዝ

በማመቻቸት የቁርኣን እና የኪታብ ደርሶችን
ከ1,100 በላይ ለሚሆኑ ተማሪዎች ተደራሽ እያደረገ ይገኛል። መድረሳችን ለሰባት አመታት በነበረው ቆይታ በአላህ ፈቃድ ደህና የሚባሉ መሬት የወረዱ እንቅስቃሴዎችን አኑሯል።
አሁን ላይ ግን በገጠመው የገንዘብ (የፋይናንስ) እጥረት ምክንያት እነኚህን መልካም አሻራዎች ማስቀጠል የከበደው ይመስላል።
የሁላችንም የሆነው መርከዝ አንግቦ የተነሳውን አላማ እና እቅድ ከግብ እንዲያደርስ  የሁላችንንም ትብብር ይሻል

" مَّن ذَا ٱلَّذِى يُقْرِضُ ٱللَّهَ قَرْضًا حَسَنًۭا فَيُضَٰعِفَهُۥ لَهُۥٓ أَضْعَافًۭا كَثِيرَةًۭ ۚ وَٱللَّهُ يَقْبِضُ وَيَبْصُۜطُ وَإِلَيْهِ تُرْجَعُونَ" [البقرة: 245]

" ያ ለአላህ መልካም ብድርን የሚያበድርና ለእርሱ (አላህ) ብዙ እጥፎች አድርጎ የሚያነባብርለት ማነው? አላህም ይጨብጣል፤ ይዘረጋልም፤ ወደ እርሱም ትመለሳላችሁ፡፡ "

        ኑ!! ጠፊ በሆነችው ዱንያ ዘላለማዊ የሆነውን አኼራችንን እንገምባ!!!!

💦 ለመድረሳው የመሬት ግዢን ያሳኩ

        💦 ለመድረሳው ቋሚ የገቢ ምንጭ ማቋቋሚያ ላይ የድርሻዎን ያስቀምጡ

እያልን ሀምሳ ሎሚ ለአንድ ሰው ሸክሙ ለሀምሳ ሰው ጌጡ ነውና ቢላል ኢብኑ ረባህ መድረሳን ወደ ላቀ ተቋም የማሻገር ሃላፊነት የሁሉም ሃላፊነት በመሆኑ ሁላችንም በቻልነው ልክ እና አቅም ሃላፊነታችንን እንወጣ ዘንድ የአክብሮት ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

           አካውንት
👉 1000742324242 ንግድ ባንክ                

https://t.me/bilalibnurebahmedresa
https://t.me/bilalibnurebahmedresa
❤2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ኑ!! ጠፊ በሆነችው ዱንያ ዘላለማዊ የሆነውን አኼራችንን እንገምባ!!!!

ተቀላቀሉ Share & joine
👇👇👇👇👇

https://t.me/bilalibnurebahgroup
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Bilal Gallery
Photo
5).ዘይነብ ቢንት ጀህሽ(ረ.ዐ)

የዘይነብ ቢንት ጀህሽ(ረ.ዐ) እና የረሱል(ሰለላሁ አለይሂ
ወሰለም) ጋብቻ አላህ(ሱ.ወ) በቅዱስ ቁርአኑ ተርኮልናል።
ዘይነብ ቢንት ጀህሽ(ረ.ዐ) የነብዩ(ሰለላሁ አለይሂ
ወሰለም) የአክስት ልጅ ስትሆን እናቷ ኡማማ የነብዩ
(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) የአባታቸዉ እህት ነች። ነብዩ
(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ዘይነብን ባሪያቸዉ ለነበረዉና
ብኃላ ነፃ ላወጡት ለዘይድ ኢብን ሀሪሳ(ረ.ዐ) ሊድሯት
እንደሚፈልጉ ሲገልፁላት እርሷም ሆነች ቤተሰቧ ፍቃደኛ
አልነበሩም። ሆኖም ግን ነብዩ(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)
“እኔ ግን ይህን ላንቺ ጥሩ በመሆኑ ወድጄልሻለሁ”
በማለት ሊጋቧት ሞከሩ። እርሷ ግን እንዲህ አለች።
“የአላህ መልእክተኛ ሆይ!(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እኔ
ይሄን ጋብቻ አልወደድኩትም። ከዚህም በላይ እኔ
ለቤተሰቤ ተወዳጅ የሆንኩ ልጅ ስሆን የአክስትዎም ልጅ
በመሆኔ የዝምድናችንን ነገር አይዘንጉት። ይህን ጋብቻ
አልፈልገዉም። በዚህ ጊዜ አላህ የሚከተለዉን ቁርአን
አወረደ:-
ﻭَﻣَﺎ ﻛَﺎﻥَ ﻟِﻤُﺆْﻣِﻦٍ ﻭَﻟَﺎ ﻣُﺆْﻣِﻨَﺔٍ ﺇِﺫَﺍ ﻗَﻀَﻰ ﺍﻟﻠَّﻪُ ﻭَﺭَﺳُﻮﻟُﻪُ ﺃَﻣْﺮًﺍ ﺃَﻥ ﻳَﻜُﻮﻥَ
ﻟَﻬُﻢُ ﺍﻟْﺨِﻴَﺮَﺓُ ﻣِﻦْ ﺃَﻣْﺮِﻫِﻢْ ۗ ﻭَﻣَﻦ ﻳَﻌْﺺِ ﺍﻟﻠَّﻪَ ﻭَﺭَﺳُﻮﻟَﻪُ ﻓَﻘَﺪْ ﺿَﻞَّ ﺿَﻠَﺎﻟًﺎ
ﻣُّﺒِﻴﻨًﺎ
አላህና መልክተኛውም ነገርን በፈረዱ ጊዜ ለምእምናንና
ለምእምናት ከነገራቸው ለእነርሱ ምርጫ ሊኖራቸው
አይገባም! የአላህንና የመልክተኛውንም ትእዛዝ የጣሰ
ሰው ግልጽ የሆነን መሳሳት በእርግጥ ተሳሳተ። (አል-
አህዛብ 36)
ይህ የቁርአን አንቀፅ ከወረደ ቡኃላ ዘይነብ የአላህና
መልእክተኛዉን(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ትእዛዝ ማክበር
ስለነበረባት ዘይድን አገባች። ኢስላም የሰዎችን ደረጃ
በዘርና በደም ሳይሆን የሚፈርጀዉ ለአላህ ባላቸዉ
ቀረቤታ እንደመሆኑ ሰዉን ‘ይህ የዚህኛዉ ጐሳ ነዉ’
‘ይኸኛዉ ደግሞ ዘሩ እንዲህ ነዉ’ ብሎ ሰዉን ዝቅ
ማድረግን ፈፅሞ አይቀበልም። የሆነ ሆኖ የዘይድና
የዘይነብ ትዳር አልሰመረም። በመካከላቸዉ ሰላምና ደስታ
ጠፋ። ዘይነብ ከከፍተኛዉ የህብረተሰብ ክፍል የመገኘቷን
ያህል በአንድ ወቅት በባርነት ተፈንግሎ ከኸድጃ(ረ.ዐ)
ቤት የኖረዉንና ቡኃላም ለነብዩ(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)
በንብረትነት ተላልፎ ከተሰጠ ቡኃላ ነፃ የተደረገዉን
ዘይድን በንቀት አይን መመልከት ጀመረች። ሁለቱም ሰዎች
በየራሳቸዉ መንገድ መልካም የነበሩና ነብዩንም(ሰለላሁ
አለይሂ ወሰለም) የሚወዱ ቢሆንም በጋራ የሚያስተሳስር
ነገር ስላልነበረ ትዳራቸዉ ተገዝግዞ ከመዉደቅ ሊድን
አልቻለም። ስለሆነም ዘይድ(ረ.ዐ) ሊፈታት ወሰነ። ሆኖም
ግን ነብዩ(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሚስቱን እንዲይዝና
አላህንም እንዲፈራ ነገሩት። ነብዩ(ሰለላሁ አለይሂ
ወሰለም) ይህን ይበሉኝ እንጂ ቀደም ሲል ዘይነብን(ረ.ዐ)
ዘይድ እንዲፈታትና እርሳቸዉም እንዲያገቧት አላህ ግድ
እንዳረገባቸዉ አጥተዉት አደለም። ይህ መለኮታዊ ትእዛዝ
በዋነኝነት ያጠጠረዉ በቅድመ-ኢስላም የድንቁርና ባህል
በመሆን ለዘመናት የኖረዉን የማደጐ ልጅና በስጋ
የተወለደን ልጅ አንድ አድርጐ የማየት ልማድ ለመስበር
ነበር። ይሁን እንጂ ነብዩ(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ይህን
ሁኔታ ግልፅ አድርገዉ ለዘይድ በመንገር እንዲፈታት
በማድረግ ፋንታ ሰዎች በተለይም ደግሞ ከሀዲያኑ
ሙሀመድ የልጁን ሚስት አፋትቶ አገባ ይሉኛል ብለዉ
በመፍራት ያንን ከማድረግ ተቆጥበዉ ቆዩ። ይሁን እንጂ
ይህን ሁሉ ፍርሀትና የዘመና ጃሂሊያ ጎታች ልማድ ኃያሉ
አላህ በአንድ ጊዜ በማፈራረስና እርሳቸዉንም በመዉቀስ
የሚከተለዉን የቁርአን አንቀፅ አወረደ:-
ﻭَﺇِﺫْ ﺗَﻘُﻮﻝُ ﻟِﻠَّﺬِﻱ ﺃَﻧْﻌَﻢَ ﺍﻟﻠَّﻪُ ﻋَﻠَﻴْﻪِ ﻭَﺃَﻧْﻌَﻤْﺖَ ﻋَﻠَﻴْﻪِ ﺃَﻣْﺴِﻚْ ﻋَﻠَﻴْﻚَ ﺯَﻭْﺟَﻚَ
ﻭَﺍﺗَّﻖِ ﺍﻟﻠَّﻪَ ﻭَﺗُﺨْﻔِﻲ ﻓِﻲ ﻧَﻔْﺴِﻚَ ﻣَﺎ ﺍﻟﻠَّﻪُ ﻣُﺒْﺪِﻳﻪِ ﻭَﺗَﺨْﺸَﻰ ﺍﻟﻨَّﺎﺱَ ﻭَﺍﻟﻠَّﻪُ
ﺃَﺣَﻖُّ ﺃَﻥ ﺗَﺨْﺸَﺎﻩُ ۖ ﻓَﻠَﻤَّﺎ ﻗَﻀَﻰٰ ﺯَﻳْﺪٌ ﻣِّﻨْﻬَﺎ ﻭَﻃَﺮًﺍ ﺯَﻭَّﺟْﻨَﺎﻛَﻬَﺎ ﻟِﻜَﻲْ ﻟَﺎ ﻳَﻜُﻮﻥَ
ﻋَﻠَﻰ ﺍﻟْﻤُﺆْﻣِﻨِﻴﻦَ ﺣَﺮَﺝٌ ﻓِﻲ ﺃَﺯْﻭَﺍﺝِ ﺃَﺩْﻋِﻴَﺎﺋِﻬِﻢْ ﺇِﺫَﺍ ﻗَﻀَﻮْﺍ ﻣِﻨْﻬُﻦَّ ﻭَﻃَﺮًﺍ ۚ ﻭَﻛَﺎﻥَ
ﺃَﻣْﺮُ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﻣَﻔْﻌُﻮﻟًﺎ
“ለእዚያም አላህ በእርሱ ላይ ለለገሰለትና (አንተም ነጻ
በማውጣት) በእርሱ ላይ ለለገስክለት ሰው (ለዘይድ)
አላህ ገላጩ የሆነን ነገር በነፍስህ ውስጥ የምትደብቅና
አላህ ልትፈራው ይልቅ የተገባው ሲሆን ሰዎችን የምትፈራ
ሆነህ «ሚስትህን ባንተ ዘንድ ያዝ፤ (ከመፍታት) አላህንም
ፍራ» በምትል ጊዜ (አስታውስ)። ዘይድም ከእርሷ ጉዳይን
በፈጸመ ጊዜ(ፍላጐትን አርክቶ በፈታትና ኢዳዋን
በጨረሰች ጊዜ) በምእምናኖች ላይ ልጅ አድርገው
ባስጠጉዋቸው (ሰዎች) ሚስቶች ከእነርሱ ጉዳይን
በፈጸሙ ጊዜ (በማግባት) ችግር እንዳይኖርባቸው እርሷን
አጋባንህ። የአላህም ትእዛዝ ተፈጻሚ ነው።” (አል-አህዛብ
37)
እንግዲህ ከላይ በተጠቀሰዉ ሁኔታ ነበር። ዘይነብ(ረ.ዐ)
ከነብዩ(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ጋር የተጋባቸዉ።
ስለሆነም የጋብቻዉ ዉል የተገለፀዉ በተቀደሰዉ ቁርአን
ላይ ነዉ። እናም ዘይነብ በሌሎቹ የነብዩ(ሰለላሁ አለይሂ
ሰላም) ባለቤቶች ላይ ይህን ሁኔታ እያነሳች የበላይነቷን
ለማንፀባረቅ ትሞክር ነበር። በተደጋጋሚም እንዲህ ስትል
ተደምጣለች:-
የእናንተን የጋብቻ ዉል ያረቀቁትና የተዋዋሉት
ቤተሰቦቻችሁ ሲሆኑ የእኔን ግን ከአርሹ በላይ የሆነዉ
አላህ ነዉ።” በሌላ ዘገባ ደግሞ “አላህ የእኔን ጋብቻ
ከሰማይ ሆኖ ነዉ ያፀደቀዉ” ብላለች።
ዘይነብ(ረ.ዐ) በእምነቷ የተመሰጠች አላህን ፈሪ
እዉነተኛና ቸር ነበረች። የእጅ ስራና የዕደ-ጥበባት እዉቀት
ስለነበራትም ያንን እየሰራች በምታገኘዉ ገንዘብ ድሆችንና
ወላጅ አልባ ልጆችን ትረዳበት ነበር። አኢሻ(ረ.ዐ) እንዲህ
ትላለች:- አንድ ጊዜ ነብዩ(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)
እንዲህ ብለዉ ነበር:- “ከባለቤቶቼ ሁሉ ከእኔ ቡኃላ
የምትሞተዉ እጀ ረዥሟ ነዉ።” ከዚያም ከነብዩ(ሰለላሁ
አለይሂ ወሰለም) ሞት ቡኃላ ሁላችንም አንድ ላይ
ተሰባስበን እጆቻችንን እያስተያየን የማንኛችን
እንደሚረዝም እንለካ ነበር። ከሁላችንም እጆች የሰዉዳ
ቢንት ዘምዓህ እጅ በርዝማኔ ይበልጥ ነበር። ሆኖም ግን
የጉዳዩ ምስጢር የገባን ዘይነብ ከሞተች ብኃላ ነበር።
ነብዩ(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ለካስ እጀ ረዥም ያሉት
ቸር የሆነችዉ ለማለት ነበር። በርግጥ ከሁላችንም
የበለጠ ቸር የነበረችዉ ዘይነብ ነበረች። አላህ ስራዎን
ሁሉ ይዉደድላት።

https://t.me/sunah123
https://t.me/sunah123
❤1
ኑ!! ጠፊ በሆነችው ዱንያ ዘላለማዊ የሆነውን አኼራችንን እንገንባ!!!!

ተቀላቀሉ Share & join
👇👇👇👇👇

https://t.me/bilalibnurebahgroup
❤1
ውድ የፉሪ አቡበከር መስጂድ የቅዳሜና እሁድ የቁርኣን ትርጉም ማብራሪያ ደርስ ታዳሚዮች በረመዳን ምክንያት ተቋርጦ የነበረው ፕሮግራም ከነገ ቅዳሜ መጋቢት 26/2018 ሸዋል 16/1447 አመተ ሂጅሪያ የሚጀመር መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን ።
👍1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ውድ ሸይኻችን ሸይኽ ሙሀመድ ሙሳ ዳዕዋ ጀምረዋል
ውዱ ሸይኻችን ሸይኽ አቡዘር ጀምሯል
❤1
በመቀጠል ውዱ ሸይኻችን ሸይኽ ሙሀመድ ሀያት የሚቀጥሉ ይሆናል
Bilal Gallery
Photo
6).ኡሙ ሀቢባህ(ረምላህ ቢንት አቡ ሱፍያን):-------

ሙሉ ስሟ ረምላህ ቢንት አቡ ሱፍያን ሲሆን እስከ መካ
መከፈት ድረስ የቁረይሽ አጋሪዎች ዋና መሪ የነበረው
የአቡ ሱፍያን ቢን ሀርብ ልጅ ናት። ምንም እንኳን አባቷ
በዚያን ጊዜ አጋሪ ቢሆንም እሷ ግን ኢስላምን ተቀብላ
ነበር። ረምላህ(ረ.ዐ) በኢስላም ላይ እያለች ያጋጠማትን
ማንኛውንም መከራና ችግር የአላህን ምንዳ በማስታወስ
በትእግስት አሳልፋለች። ባሏ እንደርሷው ሙስሊም
የነበረው ዑበይዱላህ ኢብኑ ጃህሽ ሲሆን ሙስሊሞች
ሁሉ መካ ላይ የካሀዲያኑ ግፍና ጭቆና ሲበረታባቸው
ሁለቱ ጥንዶች ወደ ሀበሻ ከተሰደዱት ሰዎች ጋር በመሆን
ከሄዱ ቡኃላ እዚያ እያሉ ሐቢባህ የምትባል ልጅ ወለዱ።
ኡሙ ሀቢባህ(ረ.ዐ) ልክ እንደ ሎሎቹ አብረዋት የተሰደዱ
ሙስሊሞች ሁሉ በሀበሻ ሀገር የሚደርስባትን
የባይተዋርነት ስሜት አንድ ያልጠበቀችው ሁኔታ
እስኪገጥማት ደረስ ተቋቁማው ትኖር ነበር።
የኡሙ ሀቢባህ(ረ.ዐ) ባለቤቴ ዑበይዱላህ ኢብኑ ጀህሽ
መጠጥ መጣት ይጀምርና እስልምና ያስጠለዋል።
እምነቱንም ቀየረ(ከፈረ)። ይባስ ብሎ ሚስቱን ወደ ኩፍር
ይጠራታል። እሷም ከእስልምና ፍንክች እንደማትል
ገለፅችለት። ከዚያ ቡኃላ አስካሪ መጠጥ አብዝቶ
መውሰድ ጀመረ። በዚያ ሁኔታ ብዙም መቆየት አልቻለም።
ወዲያው ሞተ። ኡሙ ሀቢባህ(ረ.ዐ) ይህ ከሆነ ቡኃላ
ከሀገሯ ውጪ በባይተዋርነት መኖሯ ሳያንሳት ባል አልባ
በመሆን የብቸኝነት ህይወት ለመግፋት ተገደደች።
እንደዚያም ቢሆን ይህን ሁሉ ትካዜና ብቸኝነቷን በፅናትና
በታላቅ ትእግስት ተቋቁማ ነበር የቆየችው። ምክንያቱም
ሀያሉ አላህ በቅዱስ ቃሉ የሚከተለውን ማለቱን
ታዉቃለችና:-
ﻓَﺈِﺫَﺍ ﺑَﻠَﻐْﻦَ ﺃَﺟَﻠَﻬُﻦَّ ﻓَﺄَﻣْﺴِﻜُﻮﻫُﻦَّ ﺑِﻤَﻌْﺮُﻭﻑٍ ﺃَﻭْ ﻓَﺎﺭِﻗُﻮﻫُﻦَّ ﺑِﻤَﻌْﺮُﻭﻑٍ
ﻭَﺃَﺷْﻬِﺪُﻭﺍ ﺫَﻭَﻱْ ﻋَﺪْﻝٍ ﻣِّﻨﻜُﻢْ ﻭَﺃَﻗِﻴﻤُﻮﺍ ﺍﻟﺸَّﻬَﺎﺩَﺓَ ﻟِﻠَّﻪِ ۚ ﺫَٰﻟِﻜُﻢْ ﻳُﻮﻋَﻆُ ﺑِﻪِ ﻣَﻦ
ﻛَﺎﻥَ ﻳُﺆْﻣِﻦُ ﺑِﺎﻟﻠَّﻪِ ﻭَﺍﻟْﻴَﻮْﻡِ ﺍﻟْﺂﺧِﺮِ ۚ ﻭَﻣَﻦ ﻳَﺘَّﻖِ ﺍﻟﻠَّﻪَ ﻳَﺠْﻌَﻞ ﻟَّﻪُ ﻣَﺨْﺮَﺟًﺎ
ﻭَﻳَﺮْﺯُﻗْﻪُ ﻣِﻦْ ﺣَﻴْﺚُ ﻟَﺎ ﻳَﺤْﺘَﺴِﺐُ ۚ ﻭَﻣَﻦ ﻳَﺘَﻮَﻛَّﻞْ ﻋَﻠَﻰ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﻓَﻬُﻮَ ﺣَﺴْﺒُﻪُ ۚ ﺇِﻥَّ
ﺍﻟﻠَّﻪَ ﺑَﺎﻟِﻎُ ﺃَﻣْﺮِﻩِ ۚ ﻗَﺪْ ﺟَﻌَﻞَ ﺍﻟﻠَّﻪُ ﻟِﻜُﻞِّ ﺷَﻲْﺀٍ ﻗَﺪْﺭًﺍ
ጊዜያቸውንም ለመዳረስ በተቃረቡ ጊዜ በመልካም
ያዙዋቸው፡፡ ወይም በመልካም ተለያዩዋቸው፡፡ ከእናንተም
ውስጥ ሁለት የትክክለኛነት ባለቤቶችን አስመስክሩ፡፡
ምስክርነትንም ለአላህ አስተካክሉ፡፡ ይህ በአላህና
በመጨረሻው ቀን የሚያምን የኾነ ሰው ሁሉ በእርሱ
ይገሰጽበታል፡፡ አላህንም የሚፈራ ሰው ለእርሱ መውጫን
ያደርግለታል፡፡ ከማያስበውም በኩል ሲሳየን ይሰጠዋል፡፡
በአላህም ላይ የሚጠጋ ሰው እርሱ በቂው ነው፡፡ አላህ
ፈቃዱን አድራሽ ነው፡፡ አላህ ለነገሩ ሁሉ የተወሰነ ጊዜን
በእርግጥ አድርጓል፡፡ (አል-ጦላቅ 2-3)
ኡሙ ሀቢባህ(ረ.ዐ) ባሏ ከመሞቱ ከትንሽ ቀን በፊት
በህልሟ ቤቷ ውስጥ ጨረቃ ገብቶ ቤቱን ሲያበራ አየች።
የጨረቃው መታየት ግራ አጋብቷት ዱአ አደርገች አላህ
ሆይ! ኸይር ነገር ግጠመኝ አለች።
ረሱል(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሰቡ:- “ኡሙ
ሀቢባህን ባገባት በእኔና በአቡ ሱፍያን መካከል ያለው
ክፍተት ይቀንሳል” ምክንያቱም አቡ ሱፍያን ማለት
የቁረይሾች ዋና ነው ስለሆነ ጋብቻውን ለእርቅ ፈልገው
ነው። በሁለተኛ ደረጃ ልጅ አላት ባሏ የሞተባት እንስት
ነች። በአላህ ትዛዝ ለጋብቻው መህር ከረሱል(ሰለላሁ
አለይሂ ወሰለም) ውክልና ከተሰጣቸው ከንጉስ ነጃሺ
በ400 ዲናር ሰርጉ ተደረገ። ብዙ ሀዲያዎችንም ከንጉስ
ነጃሺ ተቀበለች። ኡሙ ሀቢባህ(ረ.ዐ) የረሱል(ሰለላሁ
አለይሂ ወሰለም) ሚስት ሆነች። በብዙ ሰሀቦች ታጅባ ወደ
መዲና ሄደች። ከንጉስ ነጃሺ ለረሱል(ሰለላሁ አለይሂ
ወስለም) የተበረከተውን ስጦታም አስረከበች።
ከስጦታዎቹ መሀል 3 ዱላ(ከረዛን) ነበር። እነዚን ዱላ
አንዱን ለአቡበከር አንዱን ለዑመር አንዱን ደግሞ ያ
ቢላል አሉና ና ይሄ ከወንድምህ አህመድ ነጃሺ የመጣ
ነው አሉትና ሰጡት። የኡሙ ሀቢባህ(ረ.ዐ) አባት አቡ
ሱፍያን ልጃቸውን ረሱል(ሰለላሁ አለይሂ ወሰላም)
እንዳገቧት ሲሰሙ ተንቀጠቀጠ፣ ተገረመ። ትላንት
ሙስሊሞችን ሰብስበን ማቃጠል ነበረብን ሲል የነበረው
ረሱል(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሲሰድብ የነበረው አሁን
ቀዝቀዝ አለ። እንዲህም ሲል ተናገረ ልጄን ያገባት እኳ
በጣም ክብር ያለውን ሰው ነው። ተመለከታቹ አደል
የአላህና የረሱል(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሀሳብ ተሳካ።
ትላንት ረሱል(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለምን) ለመግደል
ይፈልግ የነበረው ዛሬ ግን አወደሳቸው። በማወደስም
አልተወገደም እስልምናም ተቀበለ። እስልምናን በመቀበል
ብቻ አላበቃም። ትልቅ ዳኢም ሆነ የእስልምናን ብርሀን
የበላይ ለማድረግ ከጠላት ተዋግቷል አጂብ በጣም
የሚገርም ታሪክ ነው። ለአላህ ጥራት ይገባው። ጠላቶች
የረሱል(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ብዙ ሚስት ማግባት
ለስጋዊ ስሜት ብለው ይናገራሉ እውነታው ግን ታሪክ
ይናገራል። ለጥበብ፣እዝነት፣ለሰላም ነበር። ኡሙ ሀቢባህ
(ረ.ዐ) አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላት።

https://t.me/sunah123
❤1