Bilal Gallery
3.91K subscribers
270 photos
9 videos
3 files
260 links
መቼም ሰው ነኝና ስህተት አይታጣብኝም ስህተት ካያችሁ በዚህ @Amir8979 አድርሱኝ ከስህተቴ ሁሌም ተመላሽ ነኝ! "ጥፋቴን በነገረኝ ሙስሊም ሁሉ የአላህ እዝነት ይውረድ"
Download Telegram
|| አይ.... ትንሹ !!

አንድ ነገር ያለ ቦታውና ያለ አግባቡ የሆነ ቦታ ላይ ከተሰየመ (ከተቀመጠ) ተገቢ አለመሆኑን ከሚጠቁሙ መረጃዎችም በተጨማሪ የሆነ አጠራጣሪ ነገር ትታዘባላችሁ ....

_ ለምሳሌ ብንወስድ
    🤏 ''ትንሹ ዒድ'' ለምን ትንሽ ተባለ ? በኢስላም የተደነገጉት የፊጥርና የአድሓ አመታዊ ክብረ በዐሎች ''ትንሽ ትልቅ '' የሚል ተጨማሪ ስያሜ አላስፈለጋቸውም። ማንም በማይናጋበት መልኩ የተረጋገጡ ስለሆኑ። ቢድዓው ዒድ ተብዬ ግን የመረጃ እጦት ስላለበት ያንን ክፍተት ለመሸፈን ''ትንሹ ዒድ '' የሚል ስያሜ ተለጠፈለት ።
ከንግግራቸው ራሱ እንደምንረዳው ይህ ቢድዓ ገና ትንሽ (ሕፃን) ነው ለአቅመ-ዒድ አልደረሰም ፤ ክብረ በዐሎች በደንጋጊው አንደበት ሲደነገጉ ገና አልተወለደም ነበር ፤ አርፍዶ ነው የደረሰው ስለሆነም ሊከበርና የዒድ ደረጃ ሊሰጠው አይገባም።

t.me/Abdul_halim_ibnu_shayk
👉 የነብዩላሂ ኢብራሂም ታሪክ

ክፍል አንድ

የነብዩላሂ ኢብራሂም ታሪክ ቁርኣን ላይ ቱክረት ከተሰጣቸው የነብያት ታሪክ ውስጥ በግንባር ቀደምትነት ይመደባል ። ታሪካቸው ቁርኣን ውስጥ በ17 ምእራፍ ወደ 69 ጊዜ ተጠቅሷል ። ይህ የሚያሳየው ታሪካቸው ምን ያክል አስፈላጊና ቁም ነገር አዘል መሆኑ ነው ።
ነብዩላሂ ኢብራሂም ዒራቅ ውስጥ ባቢል በሚባል ቦታ በጣኦት አምላኪ ማህበረሰብ ውስጥ ተወለዱ ። ከህብረተሰቡ ውስጥ ኮከብ የሚያመልክ ፣ ጨረቃ የሚያመልክና ፀሀይ የሚያመልክ እንዲሁም ከእንጨት የተሰራ ጣኦት የሚያመልክ ነበር ። አባታቸው ኣዘር ከእንጨት ጣኦት እየሰራ ይሸጥ ነበር ። እሳቸው በልጅነታቸው እርሻ ይሰሩ ነበር ። አባታቸው ጣኦት እያዞሩ እንዲሸጡላቸው ሲያዙዋቸው ተቀብለው መሬት ለመሬት እየጎተቱ የማይጠቅምና የማይጎዳ የሚገዛ እያሉ ያዞሩ ነበር ። በዚህም ምክንያት ማንም የሚገዛ ስለማያገኙ ይዘውት ይመለሳሉ ።
እድሜያቸው 13 አመት ሲሞላቸው ፈጣሪዬ ማን ነው ብለው ማሰብ ጀመሩ ። ቤተሰቦቻቸውና ማህበረሰቡ በሚያመልኩት ነገር ደስተኛ አልነበሩም ። ለብቻቸው ሲሆኑ ማን ነው የፈጠረኝ እያሉ ይብሰለሰላሉ ። በዚህ ስሜት ውስጥ ሆነው ከቤት ወጥተው ወደ ሰማይ በሚያዩበት ጊዜ የተከሰተውን አላህ ሲነግረን በአል አንዓም ምእራፍ ከ75 – 79 ድረስ እንዲህ ይለናል : –

وَكَذَٰلِكَ نُرِي إِبْرَاهِيمَ مَلَكُوتَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَلِيَكُونَ مِنَ الْمُوقِنِينَ

እንደዚሁም ኢብራሂምን (እንዲያውቅና) ከአረጋጋጮቹም ይኾን ዘንድ የሰማያትንና የምድርን መለኮት አሳየነው ፡፡

فَلَمَّا جَنَّ عَلَيْهِ اللَّيْلُ رَأَىٰ كَوْكَبًا ۖ قَالَ هَٰذَا رَبِّي ۖ فَلَمَّا أَفَلَ قَالَ لَا أُحِبُّ الْآفِلِينَ

ሌሊቱም በእርሱ ላይ ባጨለመ ጊዜ ኮከብን አየ ፡፡ «ይህ ጌታዬ ነው» አለ ፡፡ በጠለቀም ጊዜ ፡- «ጠላቂዎችን አልወድም» አለ ፡፡

فَلَمَّا رَأَى الْقَمَرَ بَازِغًا قَالَ هَٰذَا رَبِّي ۖ فَلَمَّا أَفَلَ قَالَ لَئِن لَّمْ يَهْدِنِي رَبِّي لَأَكُونَنَّ مِنَ الْقَوْمِ الضَّالِّينَ

ጨረቃንም ወጪ ኾኖ ባየ ጊዜ፡- «ይህ ጌታዬ ነው» አለ፡፡ በገባም ጊዜ፡- «ጌታዬ (ቅኑን መንገድ) ባይመራኝ በእርግጥ ከተሳሳቱት ሕዝቦች እኾናለሁ» አለ ፡፡

فَلَمَّا رَأَى الشَّمْسَ بَازِغَةً قَالَ هَٰذَا رَبِّي هَٰذَا أَكْبَرُ ۖ فَلَمَّا أَفَلَتْ قَالَ يَا قَوْمِ إِنِّي بَرِيءٌ مِّمَّا تُشْرِكُونَ

ፀሐይንም ጮራዋን ዘርግታ ባየ ጊዜ፡- «ይህ ጌታዬ ነው ፡፡ ይህ በጣም ትልቅ ነው» አለ ፡፡ በገባችም ጊዜ፡- «ወገኖቼ ሆይ! እኔ ከምታጋሩት ሁሉ ንጹሕ ነኝ» አለ ፡፡

إِنِّي وَجَّهْتُ وَجْهِيَ لِلَّذِي فَطَرَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ حَنِيفًا ۖ وَمَا أَنَا مِنَ الْمُشْرِكِينَ

«እኔ ለዚያ ሰማያትንና ምድርን ለፈጠረው (አምላክ) ቀጥተኛ ስኾን ፊቴን አዞርኩ ፡፡ እኔም ከአጋሪዎቹ አይደለሁም» (አለ) ፡፡

በዚህ መልኩ ካስተነተኑ በኋላ አላህ የማይታይ የማይዳሰስ አምሳያ የሌለው ብቸኛ አምላክ መሆኑን አሰቡ አላህም በጅብሪል አማካይነት ለአላህ ትእዛዝ እጅ እንዲሰጡ አዘዛቸው ። እሳቸውም ለጌታቸው ትእዛዝ ፍፁም ታዛዥ መሆናቸውን አረጋገጡ ። ይህን እውነታ አላህ በተከበረው ቃሉ በላሚቷ ምእራፍ ( ሱረቱል በቀራ ) 131ኛው አንቀፅ ላይ እንዲህ ብሎ ይነግረናል : –

إِذْ قَالَ لَهُ رَبُّهُ أَسْلِمْ ۖ قَالَ أَسْلَمْتُ لِرَبِّ الْعَالَمِينَ

ጌታው ለርሱ ታዘዝ ባለው ጊዜ (መረጠው) ፡፡ ለዓለማት ጌታ ታዘዝኩ አለ ፡፡

አላህ ካለ ይቀጥላል ።

http://t.me/bahruteka
⚡1❤1👍1
👉 የነብዩላሂ ኢብራሂም ታሪክ

ክፍል ሁለት

ነብዩላሂ ኢብራሂም አላህ ለትእዛዙ እጅ እንዲሰጡ ካዘዛቸው በኋላ ፍፁም ታዛዥነታቸውን ገልፀው ዳዕዋ ጀመሩ ። ማህበረሰባቸው አላህን አያውቅም ። ቤተሰቦቻቸው ጣኦት ያመልካሉ ያለባቸው ሀላፊነት ክብደት እረፍት አልሰጣቸውም ። ወደ አላህ መንገድ የመጣራቱን ሂደት ከጣኦት ቸርቻሪው አባታቸው መጀመር እንዳለባቸው ወሰኑ ። ወደ አባታቸውም ሄደው አባቴ ሆይ አላህ ሰዎች እሱን ብቻ እንዲያመልኩ ልጣራ አዞኛል ። ዳዕዋዬን ካንተ መጀመር መረጥኩኝ እነዚህ የማይጠቅሙና የማይጎዱ የማይሰሙና የማያዩ ጣኦታትን ትተህ አላህን ብቻ ተገዛ እያሉ ወደ አላህ አምልኮት መጣራታቸውን አላህ በሱረቱል መርየም ከ41 – 45 ድረስ በሚከተለው መልኩ ይነግረናል : –

وَاذْكُرْ فِي الْكِتَابِ إِبْرَاهِيمَ ۚ إِنَّهُ كَانَ صِدِّيقًا نَّبِيًّا

በመጽሐፉ ውስጥ ኢብራሂምንም አውሳ ፡፡ እርሱ በጣም እውነተኛ ነቢይ ነበርና ፡፡

إِذْ قَالَ لِأَبِيهِ يَا أَبَتِ لِمَ تَعْبُدُ مَا لَا يَسْمَعُ وَلَا يُبْصِرُ وَلَا يُغْنِي عَنكَ شَيْئًا

ለአባቱ ባለ ጊዜ (አስታውስ) «አባቴ ሆይ! የማይሰማንና የማያይን ከአንተም ምንንም የማይጠቅምህን (ጣዖት) ለምን ትግገዛለህ

يَا أَبَتِ إِنِّي قَدْ جَاءَنِي مِنَ الْعِلْمِ مَا لَمْ يَأْتِكَ فَاتَّبِعْنِي أَهْدِكَ صِرَاطًا سَوِيًّا

«አባቴ ሆይ! እኔ ከዕውቀት ያልመጣልህ ነገር በእርግጥ መጥቶልኛልና ተከተለኝ ፡፡ ቀጥተኛውን መንገድ እመራሃለሁና ፡፡

يَا أَبَتِ لَا تَعْبُدِ الشَّيْطَانَ ۖ إِنَّ الشَّيْطَانَ كَانَ لِلرَّحْمَٰنِ عَصِيًّا

«አባቴ ሆይ! ሰይጣንን አትግገዛ ፡፡ ሰይጣን ለአልረሕማን አመጸኛ ነውና ፡፡

يَا أَبَتِ إِنِّي أَخَافُ أَن يَمَسَّكَ عَذَابٌ مِّنَ الرَّحْمَٰنِ فَتَكُونَ لِلشَّيْطَانِ وَلِيًّا

«አባቴ ሆይ ! እኔ ከአልረሕማን ቅጣት ሊያገኝህ ለሰይጣንም ጓደኛ ልትኾን እፈራለሁ ፡፡»

ነብዩላሂ ኢብራሂ በጣም አስደናቂና አስተማሪ በሆነ መልኩ ክብር በተሞላበትና እኔ አዋቂ ነኝ የሚል የኩራት ስሜት በሌለበት የሚገርም አካሄድ አባቴ ሆይ እያሉ ላደረጉት ለዚህ ጥሪ ከአባታቸው የተቸሩት ምላሽ ተስፋ የሚያስቆርጥ ነበር ። የአባታቸው ምላሽ ምን እንደነበረ አላህ ሲነግረን እዛው በሱረቱል መርየም 46ኛው አንቀፅ እንዲህ ይለናል : –

قَالَ أَرَاغِبٌ أَنتَ عَنْ آلِهَتِي يَا إِبْرَاهِيمُ ۖ لَئِن لَّمْ تَنتَهِ لَأَرْجُمَنَّكَ ۖ وَاهْجُرْنِي مَلِيًّا

(አባቱም) «ኢብራሂም ሆይ! አንተ አምላኮቼን ትተህ የምትዞር ነህን ባትከለከል በእርግጥ እወግርሃለሁ ፡፡ ረዥም ጊዜንም ተወኝ» አለ ፡፡

ይሁን እንጂ ነብዩላሂ ኢብራሂም በአባታቸው መልስ ተስፋ ቢቆርጡም ሳይበሳጩ የሰጡት መልስ በዛው ምእራፍ 47 ኛው አንቀፅ እንዲህ የሚል መሆኑ ተነግሮናል : –

قَالَ سَلَامٌ عَلَيْكَ ۖ سَأَسْتَغْفِرُ لَكَ رَبِّي ۖ إِنَّهُ كَانَ بِي حَفِيًّا
«ደህና ኹን ፡፡ ወደፊት ከጌታዬ ምሕረትን እለምንልሃለሁ ፡፡ እርሱ ለኔ በጣም ርኅሩኅ ነውና» አለ ፡፡

ነብዩላሂ ኢብራሂም ዳዕዋቸው አባታቸው ዘንድ ፍሬ ባለማፍራቱ ስሜታቸው ቢጎዳም የዳዕዋ ጉዞዋቸውን ከመቀጠል አላገዳቸውም ። በዘመኑ ወደ ነበረው ነምሩድ ወደ ሚባለው ንጉስ ሄደው ዳዕዋ ማድረግ ጀመሩ የነመምሩድ ባለሟሎች ጌታችን ነምሩድ ነው የሚል መልስ ሲሰጡ ነብዩላሂ ኢብራሂም በቆራጥነትና በአላህ ላይ በመመካት ነምሩድ ጌታ እንዳልሆነና የሁላቸውም ፈጣሪ አላህ መሆኑን አስመልክቶ ያደረጉትን ዳዕዋ አላህ ሲነግረን እንዲህ ይለናል : –

قَالَ بَل رَّبُّكُمْ رَبُّ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ الَّذِي فَطَرَهُنَّ وَأَنَا عَلَىٰ ذَٰلِكُم مِّنَ الشَّاهِدِينَ

«አይደለም ጌታችሁ የሰማያትና የምድር ጌታ ያ የፈጠራቸው ነው ፡፡ እኔም በዚህ ላይ ከመስካሪዎቹ ነኝ» አለ ፡፡

የዚህን ጊዜ ነምሩድ ጌታ መሆኑን ሞገተ ። ነብዩላሂ ኢብራሂምም አላህ ማለት ምን አይነት ጌታ እንደሆነና የነምሩድን ደካማነት ያስመሰከሩበትን መረጃ አላህ በሱረቱል በቀራ 258 ኛው አንቀፅ ላይ ይነግረናል : –

أَلَمْ تَرَ إِلَى الَّذِي حَاجَّ إِبْرَاهِيمَ فِي رَبِّهِ أَنْ آتَاهُ اللَّهُ الْمُلْكَ إِذْ قَالَ إِبْرَاهِيمُ رَبِّيَ الَّذِي يُحْيِي وَيُمِيتُ قَالَ أَنَا أُحْيِي وَأُمِيتُ ۖ قَالَ إِبْرَاهِيمُ فَإِنَّ اللَّهَ يَأْتِي بِالشَّمْسِ مِنَ الْمَشْرِقِ فَأْتِ بِهَا مِنَ الْمَغْرِبِ فَبُهِتَ الَّذِي كَفَرَ ۗ وَاللَّهُ لَا يَهْدِي الْقَوْمَ الظَّالِمِينَ

ወደዚያ አላህ ንግሥናን ስለሰጠው ኢብራሂምን በጌታው ነገር ወደ ተከራከረው ሰው አላየህምን ኢብራሂም «ጌታዬ ያ ሕያው የሚያደርግና የሚገድል ነው» ባለ ጊዜ «እኔ ሕያው አደርጋለሁ እገድላለሁም» አለ፡፡ ኢብራሂም፡- «አላህ ፀሐይን ከምሥራቅ በኩል ያመጣል (አንተ) ከምዕራብ በኩል አምጣት» አለው ፡፡ ያም የካደው ሰው ዋለለ ፤ (መልስ አጣ) አላህም በዳዮች ሕዝቦችን አይመራም ፡፡

ነምሩድ በዚህ መልኩ ማላገጥ ሲጀምር አላህ አዋርዶት ነብዩላሂ ኢብራምን በሐቅ ላይ የበላይ አድርጎ ተአምረኛው ጌታ ያ እኔ አምላክ ነኝ ሲል የነበረውን ነምሩድ አንድ ትንኝ በአፍንጫው ገብታ እራሱን እንኳን ከመከራ ማዳን እንደማይችል በማሳየት ለዘመናት ስታሰቃየው ቆይታ በዛው ፍፃሜው እንዲሆን አደረገው ።

አላህ ካለ ይቀጥላል ።

http://t.me/bahruteka
👍2
🔷   የነብዩላሂ ኢብራሂም ታሪክ

              ክፍል ሶስት

      ነብዩላሂ ኢብራሂም ዳዕዋቸውን ከንግግር ወደ ተግባር ለመቀየር ወሰኑ ። ለጣኦት አምላኪያን የሚያመልኩዋቸው ጣኦታት ያልተገዛቸውን መጎዳትም ሆነ የተገዛቸውን መጥቀም እንደማይችሉ ከዚህም በላይ ራሳቸውንም ከጥቃት የማይከላከሉ መሆናቸውን ማሳየት እንዳለባቸው አመኑ ።
      የባአላቸው ቀን ጠብቀው ሁሉም ተሰባስበው ወደ በአሉ ሲሄዱ ነብዩላሂ ኢብራሂም መጥረጢያቸውን ተሸክመው ወደ ጣኦቶቻቸው አመሩ ። የተለያየ ስለት እንዲሁም ምግብም አጠገባቸው ተቀምጦ አዩ ‼ አትበሉም እንዴ እያሉ ያናግሯቸው ጀመር መልስ የለም ። ትልቁን ብቻ አስቀርተው ጣኦታቱን ፈላልጠው ጨረሱ ። ከዛም መጠረቢያውን በትልቁ ጣኦት ላይ አስቀምጠው ጥለው ሄዱ ። ጣኦትአምላኪያኖቹ ከባአል ማክበሪያ ሲመለሱ በጣኦቶቻቸው ላይ የተሰራውን ጉድ አዩ ። ስለጣኦቶቻቸው ደካማነትና ስለራሳቸው ዐቅለቢስነት ከማሰብ ይልቅ በአማልክቶቻችን ላይ ማነው ይህን የሰራው እያሉ መጠያየቅ ጀመሩ ። ኢብራሂም የሚባል ነው ተባለ ፈልገው ጠየቋቸው ። እሷቸውም ትልቁን ጠይቁት የሚናገር ከሆነ ብለው መለሱ ።
    ይህን ክስተት ቁርኣን በሚቀጥለው የአል ንቢያ ምእራፍ ከ59 – 67 በዝርዝር ያስቀምጥልናል : –

قَالُوا مَن فَعَلَ هَٰذَا بِآلِهَتِنَا إِنَّهُ لَمِنَ الظَّالِمِينَ

«በአማልክቶቻችን ይህንን የሠራ ማነው እርሱ በእርግጥ ከበደለኞች ነው» አሉ፡፡

قَالُوا سَمِعْنَا فَتًى يَذْكُرُهُمْ يُقَالُ لَهُ إِبْرَاهِيمُ

«ኢብራሂም የሚባል ጎበዝ (በመጥፎ) ሲያነሳቸው ሰምተናል» ተባባሉ፡፡

قَالُوا فَأْتُوا بِهِ عَلَىٰ أَعْيُنِ النَّاسِ لَعَلَّهُمْ يَشْهَدُونَ

«ይመሰክሩበት ዘንድ በሰዎቹ ዓይን (ፊት) ላይ አምጡት» አሉ፡፡

قَالُوا أَأَنتَ فَعَلْتَ هَٰذَا بِآلِهَتِنَا يَا إِبْرَاهِيمُ

«ኢብራሂም ሆይ! በአማልክቶቻችን ይህንን የሠራህ አንተ ነህን» አሉት፡፡

قَالَ بَلْ فَعَلَهُ كَبِيرُهُمْ هَٰذَا فَاسْأَلُوهُمْ إِن كَانُوا يَنطِقُونَ
«አይደለም ይህ ታላቃቸው ሠራው፡፡ ይናገሩም እንደ ኾነ ጠይቋቸው» አለ፡፡

فَرَجَعُوا إِلَىٰ أَنفُسِهِمْ فَقَالُوا إِنَّكُمْ أَنتُمُ الظَّالِمُونَ

ወደ ነፍሶቻቸውም ተመለሱ፡፡ «እናንተ (በመጠየቃችሁ) በዳዮቹ እናንተው ናችሁም» ተባባሉ፡፡

ثُمَّ نُكِسُوا عَلَىٰ رُءُوسِهِمْ لَقَدْ عَلِمْتَ مَا هَٰؤُلَاءِ يَنطِقُونَ

ከዚያም በራሶቻቸው ላይ ተገለበጡ፡፡ «እነዚህ የሚናገሩ አለመኾናቸውን በእርግጥ ዐውቀሃል፤» (አሉ)፡፡

     የዚህን ጊዜ ጥሩ መግቢያ አገኙ ። ጠንከር ባለ ሁኔታ ዳዕዋ አደረጉላቸው ። ይህንንም ቁርኣን በዛው ምእራፍ በሚቀጥሉት አንቀፆች ላይ ይነግረናል :–

قَالَ أَفَتَعْبُدُونَ مِن دُونِ اللَّهِ مَا لَا يَنفَعُكُمْ شَيْئًا وَلَا يَضُرُّكُمْ

«ታዲያ ለእናንተ ምንም የማይጠቅማችሁንና የማይጎዳችሁን ነገር ከአላህ ሌላ ትገዛላችሁን» አላቸው፡፡

أُفٍّ لَّكُمْ وَلِمَا تَعْبُدُونَ مِن دُونِ اللَّهِ ۖ أَفَلَا تَعْقِلُونَ

«ፎህ! ለእናንተ ከአላህ ሌላ ለምትገዙትም ነገር፤ አታውቁምን» (አለ)፡፡

    ጣኦት አምላኪያኑም በመረጃ ሲሸነፉ ሐቅን ከመቀበል ይልቅ ወደ ሀይል ተሸጋገሩ ። ይህ የሁሉም የባጢል ተከታዮች ባህርይ ነው ። መረጃ ሲያጡ ጡንቻን መረጃ ያደርጋሉ ‼ ።
     ኢብራሂምንም አቃጥሉ ጣኦቶቻችሁንም እርዱ አሉ ። ይህም እውነታ ቁርኣ በሚቀጥለው አንቀፅ ያስቀምጠዋል : –

قَالُوا حَرِّقُوهُ وَانصُرُوا آلِهَتَكُمْ إِن كُنتُمْ فَاعِلِينَ

«ሠሪዎች እንደ ኾናችሁ አቃጥሉት፡፡ አማልክቶቻችሁንም እርዱ» አሉ፡፡ (በእሳት ላይ ጣሉትም)፡፡
      ዐቅለ ቢሶቹም ነብዩላሂ ኢብራሂምን ለማቃጠል ወሰኑ ። ጥፋታቸው ጣኦታትን ራቁ አላህን ብቻ ተገዙ ማለታቸው ነው ። በወቅቱ የነበረው መንግስት ግንብ ገንቡና እሳት አቀጣጥላችሁ እዛ ውስጥ ጣሉት ብሎ አዘዘ ። ይህን ክስተት ቁርኣን እንዲህ ብሎ ይነግረናል : –

قَالُوا ابْنُوا لَهُ بُنْيَانًا فَأَلْقُوهُ فِي الْجَحِيمِ

«ለእርሱም ግንብን ገንቡ በእሳት ነበልባል ውስጥ ጣሉትም» አሉ ፡፡

      በመንግስት ትእዛዝ ከፍታው 30 ሜትር ጎኑ የተራራ ጫፍ የሚሆን ምሽግ ተገነባ ።
    ማንኛውም ህዝብ እንጨት እንዲሰበስብ ታዘዘ ። ሴት ወንድ ፣ አዋቂ ልጅ ሁሉም ወደ 40 ቀን አካባቢ ስራውን ትቶ መሰብሰብ ጀመረ ። በዚህ ታይቶም ተሰምቶም በማይታወቅ ክምር እሳት ተለኮሰበት ። ነበልባሉ ከሰማይ አሞራ ይጠልፍ ነበር ይባላል ።
    ጣኦት አምላኪያን ጉድ ተሰሩ ‼ ። ኢብራሂምን እንዴት በዚህ እሳት ይወርውሩ ? የሰው ሸይጣን መጥቶ ወስፈንጥር ( ምንጀኒቅ ) ዛሬ በዘመናዊ መልኩ መድፍ የሚባለው አይነት ማለት ነው እንዲሰሩና እዛ ላይ አድርገው እንዲወረውሩዋቸው ሐሳብ አቀረበ ።  እንደተባሉት አደረጉ ። በዚህ ሁኔታ ላይ እያሉ ጅብሪል መጣ ምን ትፈልጋለህ አላቸው ? ነብዩላሂ ኢብራሂምም ካንተ ምንም አልፈልግም ። አላህ በቂዬ ነው ምን ያማረ መጠጊያ ነው አሉ ። ወዲያውም የአላህ እርዳታ መጣ ። አላህ እሳትን አናገረ ። ይንንም ቁርኣን እንዲህ ብሎ አረጋገጠው : –

قُلْنَا يَا نَارُ كُونِي بَرْدًا وَسَلَامًا عَلَىٰ إِبْرَاهِيمَ
               الأنبياء    ( 69 )
«እሳት ሆይ! በኢብራሂም ላይ ቀዝቃዛ፤ ሰላምም ሁኚ» አልን፡፡

فَأَرَادُوا بِهِ كَيْدًا فَجَعَلْنَاهُمُ الْأَسْفَلِينَ
              الصافات  ( 98 )
በእርሱም ተንኮልን አሰቡ፡፡ ዝቅተኞችም አደረግናቸው ፡፡

     አላህ ካለ ይቀጥላል ።

http://t.me/bahruteka
❤1