Bilal Gallery
3.91K subscribers
270 photos
9 videos
3 files
260 links
መቼም ሰው ነኝና ስህተት አይታጣብኝም ስህተት ካያችሁ በዚህ @Amir8979 አድርሱኝ ከስህተቴ ሁሌም ተመላሽ ነኝ! "ጥፋቴን በነገረኝ ሙስሊም ሁሉ የአላህ እዝነት ይውረድ"
Download Telegram
በዑመይድ ስሮ መንግስት ነገስታት ላይ የአሏህ እዝነት ይሰፈን ፤ እንደነሱ የኢስላምን ቆዳ የለጠጠ አንድም ስሮ መንግስት የለም !!

t.me/Abdul_halim_ibnu_shayk
❤2💯2👍1
🟢  ኢዕቲካፍ

   ኢዕቲካፍ ማለት በቋነቋ ደረጃ አንድ ቦታ ላይ መዘውተር ማለት ሲሆን በሸሪዓዊ ትርጓሜው መስጂድ ላይ ለዒባዳ መቀመጥም ማለት ነው ።
   ይህ ተግባር ዒባዳ ለመሆኑ የአላህ መልእክተኛ – ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም – የሰሩት መሆኑ ነው ።

    عن عائشة – رضي الله عنها – أن النبي – صلى الله عليه.وسلم– " كان يعتكف العشر الأواخر من رمضان حتى توفاه الله عز وجل "
                    متفق عليه

ዓኢሻ – ረዲየላሁ ዐንሃ – የአላህ መልእክተኛ
" በረመዳን የመጨረሻዎቹ አስሩ ቀኖች ኢዕቲካፍ ይቀመጡ ነበር እስኪሞቱ ድረስ " ትላለች ።
    ኢዕቲካፍ በዒባዳ ንያ በመስጂድ እንጂ አይሆንም ። የኢስላም ሊቃውንቶች መስጂድ የሚባለው ለመስጂድ ተነይቶ ተገንብቶ በመስጂድነት ሲታወቅ ነው ይላሉ ።
   ሙዕተኪፍ ለመሆን መፆም ይወደዳል አመዛኝ በሆነው የዑለሞች ቀውል ለኢዕቲካፍ ፆም ሸርጥ አይደለም ። ኢዕቲካፍ በራሱ ዒባዳ ስለሆነ በማንኛውም ጊዜ ያለ ፆምም ይቻላል ።
  ኢዕቲካፍ የሚቀመጥ ሰው ቢያስ አንድ ለሊት መቀመጥ አለበት ። ዑመር ለነብዩ አንድ ለሊት ኢዕቲካፍ ልቀመጥ ነዝር አድረጌያለሁ ሲላቸው በነዝርህ ሙላ ብለውዋቸዋል ። ይህን መረጃ በማድረግ ከፊል ዑለሞች ትንሹ የኢዕቲካፍ ጊዜ አንድ ለሊት ነው አሉ ። ኢማሙ ማሊክ የተለያየ ቀውል አላቸው ። 10 ቀን ፣ 3ቀን ፣ አንድ ቀንና አንድ ለሊት የሚል ። በቀን ወይም በማታ ክፍለ ጊዜ ትንሽ ሳኣትም ቢሆን ይቻላል የሚሉ አሉ ። ይህ የአቡ ሐኒፋና የኢማሙ ሻፍዕይም እይታ ነው ። መረጃ የለውም በሚል አይሆንም የሚል መልስ ተሰጥቶበታል ።
    አስሩን የመጨረሻ ቀኖች ኢዕቲካፍ የሚያደርግ ሰው በ20ኛው ቀን ፀሀይ ከመግባቱ በፊት መግባቱ ይመረጣል ። የ21ኛው ቀን ከፈጅር በኋላ መግባቱ ይሻላል የሚሉ አሉ ። ይህ ከሆነ የሚወጣው የዒድ ቀን ከፈጅር በኋላ መሆን አለበት ። በ20ኛው ቀን ፀሀይ ከመግባቱ በፊት ከገባ የሚወጣው የዒድ ለሊት ፀሀይ ከገባ በኋላ ስለሆነ ይኛው ይመረጣል ይላሉ ። 
   የአላህ መልእክተኛ አዒሻ 21ኛው ቀን ፈጅር ከሰገዱ በኋላ ድንኳን እጥልላቸውና ይገቡ ነበር ትላለች ። ጁሙሁሮች በ20ኛው ገብተው ቦታ ይዘው በ21ኛው ይገለሉ ነበር ይላሉ ።
  እዚ ጋር ትኩረት መደረግ ያለበት በ21ኛው ቀን ከፈጅር በኋላ ገብቶ የዒድ ለሊት ፀሀይ ከገባ በኋላ ከወጣ አስር ቀን አይሞላም ይጎልበታል ። ስለዚህ ጁሙሁሮቹ እንዳሉት በ20ኛው ቀን ፀሀይ ከመግባቱ በፊት መግባቱ ይመረጥለታል ። ወላሁ አዕለም ።
      ኢዕቲካፍ የሚያበላሹ ነገሮች :–
– ከተቃራኒ ፆታ ጋር ግንኙነት መፈፀም
– ያለ በቂ ምክንያት ከመስጂድ መውጣት
– ኢዕቲካፉን የማቋረጥ ንያ

   ኢዕቲከፍ ላይ ላለ ሰው የሚፈቀዱ ነገሮች የሚከተሉት ናቸው ።

– ግዴታ ለሆኑ ጉዳዮች መውጣት
– ጠያቂውን እስከ መስጂድ በር ድረስ መሸኘት
– ትልቅ መስጂድ ከሆነ አንድ ጥግ ላይ ድንኳን ለራሱ ማድረግ ።
– ፍራሽ ማንጠፍና የመሳሰሉ ነገሮች

       ሙዕተኪፍ የሆነ ሰው ጊዜውን በዒባዳ ማሳለፍ ይኖርበታል ። ሶላት በመስገድ ፣ ቁርኣን በመቅራት ፣ ዚክር በማድረግ ፣ ዱዓእ በማብዛት ፣ ደርስ ካለ በመከታተል እና በመሳሰሉ ዒባዳዎች ።
        ኢዕቲካፍ ላይ ያለ ሰው ሊርቃቸው የሚገቡ ነገሮች :–

– ከአልባሌ ንግግሮች መራቅ !
– በቡድን ሆኖ የማይጠቅም ወሬ ከማውራት መራቅ !
– ሞባይል ከመጎርጎር መራቅ
– እንቅልፍ ከማብዛት መራቅ
–  ሙዕተኪፎችን አዛ ከሚያደርግ ተግባር መራቅ !
– መስጂድን ከሚያበላሽ ተግባር መራቅና የመስጂዱን አዳብ መጠበቅ ይገኙበታል ።

አላህ ከተጠቃሚዎች ያድርገን ።

      በድጋሚ የተለቀቀ

https://t.me/bahruteka
👉 ዘካተል ፊጥር

      –  ብይኑ

➽ በወንድም በሴትም በጨዋም በባሪያም የዒድ ቀንና ለሊት ከነቤተሰቡ በልቶ የሚተርፈው ባለው ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው። በሆድ ላለ ላልተወለደ ልጅ ቢወጣለት ይወደዳል።

  –  የታዘዘበት ምክንያት

➲ ድሆችን የዒድ ቀን የሰው እጅ ከማየት ወጥተው ከሙስሊሞች እኩል ተደስተው እንዲውሉ ለማድረግ
➲ በፆም ውስጥ የተፈጠሩ ስህተቶችን ለመጠገን
➲ አስጀምሮ ላስጨረሰ አምላክ ምስጋና ለማቅረብ

    –  ዘካ በምን ይወጣል

➩ ዘካ የሚወጣው የአካባቢው ሰው ከሚመገበው የምግብ አይነት ነው። በገንዘብ ቀይሮ ማውጣት አይበቃም። ነገር ግን እህል ገዝቶ ለሚሰጥለት ተወካይ ገንዘቡን መስጠት ይችላል።

  –  የዘካ መጠን ምን ያክል ነው

 ✅ በአንድ ሰው በኪሎ ከ2·5 – 3ኪሎ ማውጣት ይቻላል ። ይህም እንደየ እህሉ ስለሚለያይ ነው ። ጤፍና ዱቄት የመሳሰሉትን 2·5 ኪሎ በቆሎና ማሽላ የመሳሰሉት 3ኪሎ ቢሆን ይመረጣል። አንድ አባወራ በስሩ ላሉትና ቀለባቸው በሱላይ ለሆኑ ሰዎች ማውጣት አለበት።

    – መቼ ነው የሚወጣው

 ➧ ግዴታ የሚሆነው የዒድ ለሊት ፀሀይ ከገባች በኃላ ጀምሮ ነው። መስጠት የሚቻለው እስከ ዒድ ሶላት ነው። ከዒድ ሶላት በኃላ ዘካተል ፊጥር ሳይሆን ፀደቃ ነው የሚሆነው።
➻ አንድ ሰው ዘካተል ፊጥር ሳያወጣ ቢያልፈው ቀዳእ ማውጣት አለበት (መጠኑን ለድሀ መስጠት አለበት)  ጫንቃውን ከተጠያቂነት ነፃ ለማውጣት ሲባል።

https://t.me/bahruteka
❤1
||ሰበር

የሸዋል ጨረቃ በመታጣቷ ነገ 30ኛው የረመዷን ቀን ሁኖ ይውላል ፤ በዚህ መሠረት ዒዱ ከነገ ወዲያ  (ጁሙዓ)ነው።
✅ ዒድ እና ጁምዓ ሲገጣጠሙ

🎙 لفَضِيلَةِ الشَّيخِ عبد الحميد بن ياسين السني السلفي السلطي اللتمي «حفظه الله ورعاه»
🎙 በሸይኽ ዐብዱልሐሚድ ብን ያሲን አል'ለተሚይ! አላህ ይጠብቃቸው!

https://t.me/abdulham/2643
https://t.me/abdulham/2643
|| ዒድ ሙባረክ !

በኢስላም ታሪክ ለ1445ኛ ግዜ
ለሚከበረው ለዘንድሮው (ለ1447ኛው አመተ - ሒጅራ) የዒድ አል ፊጥራ በዓል እንኳን አደረሳችሁ !!

ፆማቸውን ከተቀበላቸው ተርታ ያሰልፈን !!
https://t.me/bilalgallery
❤1👍1
ታላላቅ ዑለማወችን ያግኙ

የኢብኑ ተይሚያህ ኪታቦች
👉https://t.me/abntaymia3

የኢብኑል ቀዪይም ኪታቦች
👉https://t.me/ktbibnalqaim

የኢማም ኢብኑ ረጀብ ኪታቦች
👉 t.me/abnrajab2

የኢማም ኢብኑ ከሢር ኪታቦች
👉 t.me/abnkthyr

የኢማም ሙሐመድ ብኑ ዐብዲል ወሃብ ኪታቦች
👉http://t.me/ktbMBinAbdulwahab

የሸይኽ ዐብዱል ዐዚዝ ብኑ ባዝ ኪታቦች
👉 t.me/ktbEmambinbaz

የሸይኽ ሙሐመድ አልአሚን አሺንቂጢ ኪታቦች
👉https://t.me/ktbalshengiti

የሸይኽ ዐብዱ ረሕማን አሰዕዲ ኪታቦች
👉https://t.me/ktbbinsaadi

የሸይኽ ሙሐመድ ናሲሩዲን አልባኒ ኪታቦች
👉 t.me/Aallbany/3328

የሸይኽ ሙሐመድ ብኑ ሷሊሕ አልዑሠይሚን ኪታቦች
👉 t.me/ktbmB_othaimen

የሸይኽ ዶር. ሷሊሕ አልፈውዛን ኪታቦች
👉 t.me/ktbalfawzan

የሸይኽ ዐብዱል ሙሕሲን አልዐባድ ኪታቦች
👉 http://t.me/Ktbalabbaad

የሸይኽ ዐብዱል ዐዚዝ አራጂሒ ኪታቦች
👉 t.me/ktbAlRajhi

የሸይኽ ዐብዱል ከሪም ኹዶይር ኪታቦች
👉 t.me/ktbAlkhudheir

የሸይኽ ሙሐመድ ዐሊይ አደም ኪታቦች
👉 t.me/Ktbaletiopi

የሸይኽ ሷሊሕ ኣሊ ሸይኽ ኪታቦች
👉 t.me/Salehshaikh/2052

የሸይኽ ሷሊሕ አልዑሶይሚ ኪታቦች
👉 t.me/mnmhln

join #Telegram ቻናል
https://t.me/abumuawiyahalhalaby
https://t.me/abumuawiyahalhalaby
https://t.me/abumuawiyahalhalaby
👆 አዎ በቃ እውነታው ነው!

💬◉◉◉💬◉◉◉💬     👇👇👇
https://t.me/AbuImranAselefy/10336
👍1
Forwarded from Bilal Gallery
Forwarded from Bilal Gallery