Bilal Gallery
3.91K subscribers
269 photos
9 videos
3 files
260 links
መቼም ሰው ነኝና ስህተት አይታጣብኝም ስህተት ካያችሁ በዚህ @Amir8979 አድርሱኝ ከስህተቴ ሁሌም ተመላሽ ነኝ! "ጥፋቴን በነገረኝ ሙስሊም ሁሉ የአላህ እዝነት ይውረድ"
Download Telegram
📢 አስደሳች ዜና!

         ቢላል ኢብኑረባህ የቁርአን ሒፍዝ
           እና የሸሪዓ እዉቀት ማዕከል


💎 መርከዝ ቢላል ኢብኑ ረባህ ከዚህ በፊት ለወንድና ለሴት የሸሪአ እውቀት ተማሪዎች  በተመላላሽ  የቂርአት መርሀ ግብር ብቻ ሲያስተምር  መቆየቱ ይታወቃል። ሁሌም አዳዲስ የቂርአት ኘሮግራሞችን ለተማሪዎች በማመቻቸት  የሱናውን ማህበረሰብ ማስደሰት ማያቆመው መርከዛችን  አሁን ደግሞ ለመጪው 2018 በጋ በአዳሪና በተመላላሽ  የቂርአት መርሀግብር  ተማሪዎችን ተቀብለን ለማስተማር ሙሉ ዝግጅታችንን አጠናቀን በምዝገባ ላይ እንገኛለን ።

☑️ በአዳሪ መርኃግብር ለመመዝገብ፦
➠ በአዳሪ ለወንዶች ብቻ
➠ እድሜው ከ10 ዓመት በላይ የሆነ
➠ወርሐዊ ክፍያ በአግባቡ መክፈል የሚችል
➠ ለመቅራት ፍላጎት ያለዉ 
➠ ለመርከዙ ህግና ደንቦች ተገዢ መሆን የሚችል
➠ የቆይታ ጊዜ ሁለት አመት
➠ ከተላላፊ በሽታ ነፃ የሆነ

☑️በተመላላሽ መርኃግብር ለመመዝገብ፦
➻ ለወንዶችና ለሴቶች
➻ እድሜ ከ10 ዓመት በላይ
➻ ወርሐዊ ክፍያ በአግባቡ መክፈል የሚችል/የምትችል
➻ለመቅራት ፍላጎት ያለዉ (ያላት)
➻ለመርከዙ ህግና ደንቦች ተገዢ መሆን የሚችል (የምትችል)
➻የሴቶች ሰአት፦ 2:30-9:15
➻ለወንዶች፦ 2:30-11:00
➻ ኪታብ 3:00-6:30

☑️ የሚሰጡ የትምህርት አይነቶች ፦
🔘 ቁርአን በሒፍዝና በነዝር 
🔘 ቁርአን ሙራጀዓ  
🔘 ተጅዊድ
✅የአቂዳ
🔘 የመንሀጅ
🔘የፊቂህ ሌሎችም በደረጃ ይሰጣሉ።

☎️ ለምዝገባ እና ለበለጠ መረጃ፦
📞0999553107
📞0937948156
📞0921566720
🔍 የምዝገባ ቦታ፦ለወንዶች ካራ ቆሬ ሳሌ ህንጻ ጀርባ ቢላል ኢብኑ ረባህ መድረሳ (ቁጥር 4) ለሴቶች ቢላል ኢብኑ ረባህ መድረሳ (ቁጥር 3)

https://t.me/bilalibnurebahmedresa
❤1👏1
በዑመይድ ስሮ መንግስት ነገስታት ላይ የአሏህ እዝነት ይሰፈን ፤ እንደነሱ የኢስላምን ቆዳ የለጠጠ አንድም ስሮ መንግስት የለም !!

t.me/Abdul_halim_ibnu_shayk
❤2💯2👍1
🟢  ኢዕቲካፍ

   ኢዕቲካፍ ማለት በቋነቋ ደረጃ አንድ ቦታ ላይ መዘውተር ማለት ሲሆን በሸሪዓዊ ትርጓሜው መስጂድ ላይ ለዒባዳ መቀመጥም ማለት ነው ።
   ይህ ተግባር ዒባዳ ለመሆኑ የአላህ መልእክተኛ – ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም – የሰሩት መሆኑ ነው ።

    عن عائشة – رضي الله عنها – أن النبي – صلى الله عليه.وسلم– " كان يعتكف العشر الأواخر من رمضان حتى توفاه الله عز وجل "
                    متفق عليه

ዓኢሻ – ረዲየላሁ ዐንሃ – የአላህ መልእክተኛ
" በረመዳን የመጨረሻዎቹ አስሩ ቀኖች ኢዕቲካፍ ይቀመጡ ነበር እስኪሞቱ ድረስ " ትላለች ።
    ኢዕቲካፍ በዒባዳ ንያ በመስጂድ እንጂ አይሆንም ። የኢስላም ሊቃውንቶች መስጂድ የሚባለው ለመስጂድ ተነይቶ ተገንብቶ በመስጂድነት ሲታወቅ ነው ይላሉ ።
   ሙዕተኪፍ ለመሆን መፆም ይወደዳል አመዛኝ በሆነው የዑለሞች ቀውል ለኢዕቲካፍ ፆም ሸርጥ አይደለም ። ኢዕቲካፍ በራሱ ዒባዳ ስለሆነ በማንኛውም ጊዜ ያለ ፆምም ይቻላል ።
  ኢዕቲካፍ የሚቀመጥ ሰው ቢያስ አንድ ለሊት መቀመጥ አለበት ። ዑመር ለነብዩ አንድ ለሊት ኢዕቲካፍ ልቀመጥ ነዝር አድረጌያለሁ ሲላቸው በነዝርህ ሙላ ብለውዋቸዋል ። ይህን መረጃ በማድረግ ከፊል ዑለሞች ትንሹ የኢዕቲካፍ ጊዜ አንድ ለሊት ነው አሉ ። ኢማሙ ማሊክ የተለያየ ቀውል አላቸው ። 10 ቀን ፣ 3ቀን ፣ አንድ ቀንና አንድ ለሊት የሚል ። በቀን ወይም በማታ ክፍለ ጊዜ ትንሽ ሳኣትም ቢሆን ይቻላል የሚሉ አሉ ። ይህ የአቡ ሐኒፋና የኢማሙ ሻፍዕይም እይታ ነው ። መረጃ የለውም በሚል አይሆንም የሚል መልስ ተሰጥቶበታል ።
    አስሩን የመጨረሻ ቀኖች ኢዕቲካፍ የሚያደርግ ሰው በ20ኛው ቀን ፀሀይ ከመግባቱ በፊት መግባቱ ይመረጣል ። የ21ኛው ቀን ከፈጅር በኋላ መግባቱ ይሻላል የሚሉ አሉ ። ይህ ከሆነ የሚወጣው የዒድ ቀን ከፈጅር በኋላ መሆን አለበት ። በ20ኛው ቀን ፀሀይ ከመግባቱ በፊት ከገባ የሚወጣው የዒድ ለሊት ፀሀይ ከገባ በኋላ ስለሆነ ይኛው ይመረጣል ይላሉ ። 
   የአላህ መልእክተኛ አዒሻ 21ኛው ቀን ፈጅር ከሰገዱ በኋላ ድንኳን እጥልላቸውና ይገቡ ነበር ትላለች ። ጁሙሁሮች በ20ኛው ገብተው ቦታ ይዘው በ21ኛው ይገለሉ ነበር ይላሉ ።
  እዚ ጋር ትኩረት መደረግ ያለበት በ21ኛው ቀን ከፈጅር በኋላ ገብቶ የዒድ ለሊት ፀሀይ ከገባ በኋላ ከወጣ አስር ቀን አይሞላም ይጎልበታል ። ስለዚህ ጁሙሁሮቹ እንዳሉት በ20ኛው ቀን ፀሀይ ከመግባቱ በፊት መግባቱ ይመረጥለታል ። ወላሁ አዕለም ።
      ኢዕቲካፍ የሚያበላሹ ነገሮች :–
– ከተቃራኒ ፆታ ጋር ግንኙነት መፈፀም
– ያለ በቂ ምክንያት ከመስጂድ መውጣት
– ኢዕቲካፉን የማቋረጥ ንያ

   ኢዕቲከፍ ላይ ላለ ሰው የሚፈቀዱ ነገሮች የሚከተሉት ናቸው ።

– ግዴታ ለሆኑ ጉዳዮች መውጣት
– ጠያቂውን እስከ መስጂድ በር ድረስ መሸኘት
– ትልቅ መስጂድ ከሆነ አንድ ጥግ ላይ ድንኳን ለራሱ ማድረግ ።
– ፍራሽ ማንጠፍና የመሳሰሉ ነገሮች

       ሙዕተኪፍ የሆነ ሰው ጊዜውን በዒባዳ ማሳለፍ ይኖርበታል ። ሶላት በመስገድ ፣ ቁርኣን በመቅራት ፣ ዚክር በማድረግ ፣ ዱዓእ በማብዛት ፣ ደርስ ካለ በመከታተል እና በመሳሰሉ ዒባዳዎች ።
        ኢዕቲካፍ ላይ ያለ ሰው ሊርቃቸው የሚገቡ ነገሮች :–

– ከአልባሌ ንግግሮች መራቅ !
– በቡድን ሆኖ የማይጠቅም ወሬ ከማውራት መራቅ !
– ሞባይል ከመጎርጎር መራቅ
– እንቅልፍ ከማብዛት መራቅ
–  ሙዕተኪፎችን አዛ ከሚያደርግ ተግባር መራቅ !
– መስጂድን ከሚያበላሽ ተግባር መራቅና የመስጂዱን አዳብ መጠበቅ ይገኙበታል ።

አላህ ከተጠቃሚዎች ያድርገን ።

      በድጋሚ የተለቀቀ

https://t.me/bahruteka
👉 ዘካተል ፊጥር

      –  ብይኑ

➽ በወንድም በሴትም በጨዋም በባሪያም የዒድ ቀንና ለሊት ከነቤተሰቡ በልቶ የሚተርፈው ባለው ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው። በሆድ ላለ ላልተወለደ ልጅ ቢወጣለት ይወደዳል።

  –  የታዘዘበት ምክንያት

➲ ድሆችን የዒድ ቀን የሰው እጅ ከማየት ወጥተው ከሙስሊሞች እኩል ተደስተው እንዲውሉ ለማድረግ
➲ በፆም ውስጥ የተፈጠሩ ስህተቶችን ለመጠገን
➲ አስጀምሮ ላስጨረሰ አምላክ ምስጋና ለማቅረብ

    –  ዘካ በምን ይወጣል

➩ ዘካ የሚወጣው የአካባቢው ሰው ከሚመገበው የምግብ አይነት ነው። በገንዘብ ቀይሮ ማውጣት አይበቃም። ነገር ግን እህል ገዝቶ ለሚሰጥለት ተወካይ ገንዘቡን መስጠት ይችላል።

  –  የዘካ መጠን ምን ያክል ነው

 ✅ በአንድ ሰው በኪሎ ከ2·5 – 3ኪሎ ማውጣት ይቻላል ። ይህም እንደየ እህሉ ስለሚለያይ ነው ። ጤፍና ዱቄት የመሳሰሉትን 2·5 ኪሎ በቆሎና ማሽላ የመሳሰሉት 3ኪሎ ቢሆን ይመረጣል። አንድ አባወራ በስሩ ላሉትና ቀለባቸው በሱላይ ለሆኑ ሰዎች ማውጣት አለበት።

    – መቼ ነው የሚወጣው

 ➧ ግዴታ የሚሆነው የዒድ ለሊት ፀሀይ ከገባች በኃላ ጀምሮ ነው። መስጠት የሚቻለው እስከ ዒድ ሶላት ነው። ከዒድ ሶላት በኃላ ዘካተል ፊጥር ሳይሆን ፀደቃ ነው የሚሆነው።
➻ አንድ ሰው ዘካተል ፊጥር ሳያወጣ ቢያልፈው ቀዳእ ማውጣት አለበት (መጠኑን ለድሀ መስጠት አለበት)  ጫንቃውን ከተጠያቂነት ነፃ ለማውጣት ሲባል።

https://t.me/bahruteka
❤1
||ሰበር

የሸዋል ጨረቃ በመታጣቷ ነገ 30ኛው የረመዷን ቀን ሁኖ ይውላል ፤ በዚህ መሠረት ዒዱ ከነገ ወዲያ  (ጁሙዓ)ነው።
✅ ዒድ እና ጁምዓ ሲገጣጠሙ

🎙 لفَضِيلَةِ الشَّيخِ عبد الحميد بن ياسين السني السلفي السلطي اللتمي «حفظه الله ورعاه»
🎙 በሸይኽ ዐብዱልሐሚድ ብን ያሲን አል'ለተሚይ! አላህ ይጠብቃቸው!

https://t.me/abdulham/2643
https://t.me/abdulham/2643
|| ዒድ ሙባረክ !

በኢስላም ታሪክ ለ1445ኛ ግዜ
ለሚከበረው ለዘንድሮው (ለ1447ኛው አመተ - ሒጅራ) የዒድ አል ፊጥራ በዓል እንኳን አደረሳችሁ !!

ፆማቸውን ከተቀበላቸው ተርታ ያሰልፈን !!
https://t.me/bilalgallery
❤1👍1
ታላላቅ ዑለማወችን ያግኙ

የኢብኑ ተይሚያህ ኪታቦች
👉https://t.me/abntaymia3

የኢብኑል ቀዪይም ኪታቦች
👉https://t.me/ktbibnalqaim

የኢማም ኢብኑ ረጀብ ኪታቦች
👉 t.me/abnrajab2

የኢማም ኢብኑ ከሢር ኪታቦች
👉 t.me/abnkthyr

የኢማም ሙሐመድ ብኑ ዐብዲል ወሃብ ኪታቦች
👉http://t.me/ktbMBinAbdulwahab

የሸይኽ ዐብዱል ዐዚዝ ብኑ ባዝ ኪታቦች
👉 t.me/ktbEmambinbaz

የሸይኽ ሙሐመድ አልአሚን አሺንቂጢ ኪታቦች
👉https://t.me/ktbalshengiti

የሸይኽ ዐብዱ ረሕማን አሰዕዲ ኪታቦች
👉https://t.me/ktbbinsaadi

የሸይኽ ሙሐመድ ናሲሩዲን አልባኒ ኪታቦች
👉 t.me/Aallbany/3328

የሸይኽ ሙሐመድ ብኑ ሷሊሕ አልዑሠይሚን ኪታቦች
👉 t.me/ktbmB_othaimen

የሸይኽ ዶር. ሷሊሕ አልፈውዛን ኪታቦች
👉 t.me/ktbalfawzan

የሸይኽ ዐብዱል ሙሕሲን አልዐባድ ኪታቦች
👉 http://t.me/Ktbalabbaad

የሸይኽ ዐብዱል ዐዚዝ አራጂሒ ኪታቦች
👉 t.me/ktbAlRajhi

የሸይኽ ዐብዱል ከሪም ኹዶይር ኪታቦች
👉 t.me/ktbAlkhudheir

የሸይኽ ሙሐመድ ዐሊይ አደም ኪታቦች
👉 t.me/Ktbaletiopi

የሸይኽ ሷሊሕ ኣሊ ሸይኽ ኪታቦች
👉 t.me/Salehshaikh/2052

የሸይኽ ሷሊሕ አልዑሶይሚ ኪታቦች
👉 t.me/mnmhln

join #Telegram ቻናል
https://t.me/abumuawiyahalhalaby
https://t.me/abumuawiyahalhalaby
https://t.me/abumuawiyahalhalaby