Bilal Gallery
3.93K subscribers
269 photos
9 videos
3 files
260 links
መቼም ሰው ነኝና ስህተት አይታጣብኝም ስህተት ካያችሁ በዚህ @Amir8979 አድርሱኝ ከስህተቴ ሁሌም ተመላሽ ነኝ! "ጥፋቴን በነገረኝ ሙስሊም ሁሉ የአላህ እዝነት ይውረድ"
Download Telegram
#አጠራጣሪን_ቀን_መፆም
      
#ክልክል_ነው‼️❗️
➪➪➪➪➪➪➪➪➪➪
➲ አጠራጣሪ ቀን የተሰኘው #ረመዷን መግባት አለመግባቱን የሚያጠራጥር እለት በመሆኑ ነው፡፡
➽ ይህ ቀን ሰላሳኛው የሸዕባን ቀን ሆኖ ደመናማ ሲሆን ነው፡፡ ለዚህም ማስረጃው ዓማር ባስተላለፉት ሀዲስ ነቢያችን (ﷺ) እንዲህ ስላሉ ነው፦
   “አጠራጣሪን ቀን #የፆመ የቃሲምን አባት #አምጿል፡፡” በሌላም ሀዲስ እንዲህ ብለዋል
     “ረመዳንን አንድ ወይም ሁለት ቀን #በመፆም_አትቅደሙት የተለመደ ፆም እየፆመ የነበረ ሰው ግን ገጥሞት ቢፆም ምንም አይደል”
        አል ቡኻሪ (1976)

➜ ነብዩ (ﷺ) በግልፅ እንዳዘዙን አጠራጣሪ  የሆነን ቀን መፆም የለብንም። ⛔️ #ለጥንቃቄ በሚል #ሰበብ ይህንን አጠራጣሪ ቀን ከመፆም #መቆጠብ ተገቢ ነው። ምክንያቱም የፆመው ሰው ነብዩ ሙሐመድን ﷺ  እንዳመፀ ወይም ትዕዛዛቸውን እንደጣሰ ነው። 
“አጠራጣሪን ቀን
#የፆመ የቃሲምን አባት #አምጿል፡፡” እንዳሉት ማለት ነው።
የቃሲም አባት ማለት #ነብዩ_ሙሐመድ ﷺ  ናቸው።

#صوم يوم الشك ممنوع شرعا ﻫﺬﺍ ﻣﺎ ﻳﺴﻤﻰ ﺑﻴﻮﻡ ﺍﻟﺸﻚ ‏
(ﻷﻧﻪ ﻣﺸﻜﻮﻙ ﻓﻴﻪ ، ﻫﻞ ﻫﻮ ﺁﺧﺮ ﻳﻮﻡ ﻣﻦ
#ﺷﻌﺒﺎﻥ ﺃﻭ ﺃﻭﻝ ﻳﻮﻡ ﻣﻦ ﺭﻣﻀﺎﻥ)

➜ ይህ የጥርጣሬ ቀን በመባል ይታወቃል ለምን ቢባል የ"ሸዕባን" የመጨረሻው ቀን ነው ወይስ የረመዳን መጀመሪያ በሚል ስለሚያሰጋ
ﻭﺻﻮﻣﻪ ﻣﺤﺮﻡ
ታዲያ እሱን መፆም እርም (ክልክል) ነው።
ﻟﻘﻮﻝ ﺍﻟﻨﺒﻲ ﺻﻠﻰﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ
#መልዕክተኛው ﷺ እንድህ ብለዋል፦
"ﺻﻮﻣﻮﺍ ﻟﺮﺅﻳﺘﻪ ﻭﺃﻓﻄﺮﻭﺍ ﻟﺮﺅﻳﺘﻪ ﻓﺈﻥ ﻏُﺒِّﻲَ ‏(ﺃﻱﺧﻔﻲ) ﻋﻠﻴﻜﻢ ﻓﺄﻛﻤﻠﻮﺍ ﻋﺪﺓ ﺷﻌﺒﺎﻥ ﺛﻼﺛﻴﻦ"
ﺭﻭﺍﻩ ﺍﻟﺒﺨﺎﺭﻱ ‏(1909)

''ጨረቃን ስታዩ ፁሙ ስታዩም ፍቱ  በናንተ ላይ ቢሸፈንባቹህ የ"ሸዕባን"ን ቁጥር ሰላለሳ ሙሉ።''

ﻭﻗﺎﻝ ﻋﻤﺎﺭ ﺑﻦ ﻳﺎﺳﺮ "ﻣﻦ ﺻﺎﻡ ﺍﻟﻴﻮﻡ ﺍﻟﺬﻱ ﻳُﺸﻚ ﻓﻴﻪ ﻓﻘﺪ ﻋﺼﻰ ﺃﺑﺎﺍﻟﻘﺎﺳﻢ ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ."
ﺭﻭﺍﻩ ﺍﻟﺘﺮﻣﺬﻱ ﻭﺻﺤﺤﻪ ﺍﻷﻟﺒﺎﻧﻲ ﻓﻲ
ﺻﺤﻴﺢ ﺍﻟﺘﺮﻣﺬﻱ٥٥٣.


ዐማር ኢብኑ ያሲር ረዲየሏሁ ዐንሁ እንዲህ ይላል፦
"በሱ የሚጠረጠርበትን ቀን የፆመ ሰው የቃሲምን አባት በእርግጥ አመፀ"

ﻗﺎﻝ ﺍﻟﺤﺎﻓﻆ ﺍﺑﻦ ﺣﺠﺮ:-
  "ﺍﺳﺘُﺪﻝ ﺑﻪ ﻋﻠﻰ ﺗﺤﺮﻳﻢ ﺻﻮﻡ ﻳﻮﻡ ﺍﻟﺸﻚ ﻷﻥ ﺍﻟﺼﺤﺎﺑﻲ ﻻ ﻳﻘﻮﻝ ﺫﻟﻚ ﻣﻦ ﻗﺒﻞ ﺭﺃﻳﻪ ﻓﻴﻜﻮﻥ ﻣﻦ ﻗﺒﻴﻞ ﺍﻟﻤﺮﻓﻮﻉ ﻗﺎﻝ ﻋﻠﻤﺎﺀ ﺍﻟﻠﺠﻨﺔ ﺍﻟﺪﺍﺋﻤﺔ ﻋﻦ ﻳﻮﻡ ﺍﻟﺸﻚ ﺩﻟﺖ ﺍﻟﺴﻨﺔ ﻋﻠﻰ ﺗﺤﺮﻳﻢ ﺻﻮﻣﻪ"
ﻓﺘﺎﻭﻯ ﺍﻟﻠﺠﻨﺔ 10/117

➽ ኢብኑ ሐጀር በዚህ ሐዲሥ የጥርጣሬን ቀን መፆም ሐራም ለመሆኑ መረጃ ተደርጓል ይላሉ።

#ስለዚህ ማንም ሙስሊም ገና ለገና ጨረቃ ሊወጣ ይችላል በሚል ግምት ያለ መረጃ ሊፆም አይገባውም።

✍ ኡስታዝ አቡ ሙዓዝ «حَفِظَهُ اللَّهُ»

ከተወሰነ editing ጋር የቀረበ

https://t.me/AbuImranAselefy
👍5🥰2
سنة مهجورة
ما يقال بعد الوتر عن أبي بن كعب رضي الله عنه كان رسول الله صلى الله عليه وسلم "إذا سلم من الوتر قال سبحان الملك القدوس ثلاث مرات وفي رواية يطيل في آخرهن" أبو داود "1430"


➛የተተወች ሱና

◉ከዊትር ሶላት በኋላ የምባል ነገር ፦ ኡበይ ብኑ-ከዕብ እንዳሉት ረሱል ﷺ ➛ከዊትር ሶላት በተሰላመቱ ግዜ "ሶስቴ ሱብሃነል መሊኪል ቁዱስ ይሉ ነበር ። በሌላ ዘገባም በመጨረሻቸው አርዝመው ይሉ ነበር ።
(አቡ ዳውድ "1430")

Share & joine
👇👇👇👇👇
https://t.me/AbuMerwanAselefy
👍3
➛ካፈጠርክ በኋላ እንዲህ በል!

✍️ذَهَبَ الظَّمَأُ، وَابْتَلَّتِ العُرُوقُ، وَثَبَتَ الأجْرُ إِنْ شَاءَ اللهُ
➛ጥማት ተወገደ
➛የደም ሥሮች ረጠቡ
➛የአላህ ፈቃድ ከሆነ ምንዳም ተረጋገጠ


Share & joine
👇👇👇👇👇
https://t.me/AbuMerwanAselefy
👍6❤2
ባፍንጫው ይደፋ
◅◅◅◅◅◅◅◅


የአላህ መልእክተኛ – ﷺ – ረመዳንን አግኝቶ ምህረት ሳያገኝ ረመዳን የወጣበትን ሰው አስመልክተው እንዲህ ይላሉ፦
"አንድ ሰው ባፍንጫው ይደፋ ረመዳን በሱ ላይ ገብቶ (በህይወት እያለ እረመዳን ላይ ደርሶ) ከዚያም ምህረት ሳይደረግለት ረመዳን የተገፈፈበት"
   
➚ ይህ ሐዲስ በጣም አስደንጋጭ ነው። የሁላችንንም የልብ ጓዳ የሚያንኳኳ ነው። ጥቅል ንግግር ሆኖ በውስጡ ብዙ መልእክት የያዘ ነው። አላህ ከተጠቃሚዎች ያድርገን።

https://t.me/abumuawiyahalhalaby
https://t.me/abumuawiyahalhalaby
👌2
🇦🇪 ዱባይ ላይ የተደረገው ፕሮግራም ኦዲዮ ተገኘ!

— በሸይኽ ዐብዱል-ሐሚድ፣ በሸይኽ አቡ ዘር ኮምቦልቻ፣ በኡስታዝ ሻኪር ሱልጧን፣ በሀገረ ዱባይ (ኢማራት) የተካሄደውን ልዩ የሙሐደራ ሪከርድ እነሆ እንኩ ብለናችኋል።

● ክፍል -1-
— በሸይኽ ዐብዱል-ሐሚድ -ሐፊዞሁ'ሏህ-
= t.me/Multeqa_Ahlissuneh/3446

● ክፍል -2-
— በሸይኽ ዐብዱል-ሐሚድ -ሐፊዞሁ'ሏህ-
= t.me/Multeqa_Ahlissuneh/3447

● ክፍል -3-
— በሸይኽ አቡ ዘር ሐሰን -ሐፊዞሁ'ሏህ-
= t.me/Multeqa_Ahlissuneh/3448

● ክፍል -4-
— ኡስታዝ ሻኪር ሱልጧን -ሐፊዞሁ'ሏህ-
= t.me/Multeqa_Ahlissuneh/3450

● ክፍል -5-
— ኡስታዝ ሻኪር ሱልጧን -ሐፊዞሁ'ሏህ-
= t.me/Multeqa_Ahlissuneh/3451

● ፈትዋ
— በሸይኽ ዐብዱል-ሐሚድ -ሐፊዞሁ'ሏህ
= t.me/Multeqa_Ahlissuneh/3452

​📅 ፕሮግራሙ የተካሄደበት ቀን፦ ቅዳሜ 26 እና እሁድ ሸዕባን 27/1447 ዓ.ሂ

= ለሌሎች በሰፊው ሼር ማድረግን አትዘንጉ፤ በጥሩ ነገር ያመላከተ እንደ ሰሪው ነውና።

|| #የመገናኛው_ግሩፕ፦
t.me/Multeqa_Ahlissuneh
t.me/Multeqa_Ahlissuneh
👍2
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته

ልቦናዎች ሲናፍቁት ቆይተው እንግዳው ብቅ ብሏል!!!   
                
                          أتاكم رمضان شهر مبارك!!!!
" መጣላችሁ ረመዷን የተባረከው ወር ''

መስተንግዷችን እንዴት እየሄደ ነው???

የጀሃነም በሮች ተዘግተዋል ፣ የጀነት በሮች ተከፋፍተዋል ፣ ገሃዱ ጠላታችን ተቀፍድዷል!!!

ከዚህ ሁላ መመቻቸቶች ጋር አንቺስ እንዴት አለሽ???

ከፆሙ ረሃብን ፤ ከሰላቱ መቆምን ብቻ ካተረፉት?? ወይስ ላለፈ ጥፋታቸው እያነቡ የጌታቸውን እዝነት ከጅለው በዒባዳ ወገባቸውን ካጠበቁት ጋር ነሽ???

"አዋጅ! ይህ ወራችሁ እየጎደለ እና እየቀነሰ ይገኛል ፤ እናንተ ደግሞ ስራችሁን ጨምሩ!!!"
ታላቁ ኢማም ሀሰነል በስሪይ

የምእመናን ልቦና ለሚናፍቁት የተከበረው የረመዳን ወር እንኳን በሰላም አደረሳችሁ!!!

🗯የቢላል ኢብኑ ረባህ ሴቶች ጀምዓ በየወሩ ጊዜውን እየጠበቀ የሚያሰናዳላችሁን ወርሃዊ ፕሮግራም የረመዳን ወር መግባትን አስመልክቶ
"ስለረመዳናችን እንመካከር"
በሚል ፕሮግራሙን አሰናድቶ እየጠበቃችሁ ይገኛል።

🗓እሁድ 22/06/18

🌅ከጠዋቱ  2:30


💎አድራሻ፦ ካራ ቆሬ ወደ ባማ ሆስፒታል በሚወስደው ቅያስ 500 ሜትር ዝቅ ብሎ ውሃ ታንከሩ አጠገብ

📞 0963152454
      0919017040
@bilalibnurebahmedresa
@bilalibnurebahmedresa
✅ ረመዳንና መንዙማ

➪ ረመዳን ቁርኣን የወረደበት ወር ሲሆን በዚህ ወር ቁርኣንን በተቻለ መጠን መቅራት፣ ትርጉሙን ማስተንተን፣ ያዘዘውን መልእክት በተቻለ መጠን ተረድቶ በስራ ላይ ማዋል የቁርኣንን በረካ ለማግኘት ይረዳል። ቁርኣን የወረደው ልንሳለመው ሳይሆን ልንመራበትና ልንሰራበት ነው። ቁርኣን መለኮታዊ የህይወት መመሪያ፣ የልብ ብርሀን፣ የውስጥም የውጭም መድሃኒት፣ የሁለት ሀገር ስኬት ቁልፍ ነው።
➽ የመጀመሪያዎቹ ሙስሊሞች የበላይነት የተቀዳጁት፣ ከነበሩበት ዝቅጠት የወጡት፣ ዐለም ላይ ተፅኖ መፍጠር የቻሉት፣ የዘመኑን አምባገነኖች አንገት ያስደፉት በቁራን በመመራታቸውና በመስራታቸው ነው። ቁርኣንን የበላይ አደረጉ ቁርኣን የበላይ አደረጋቸው። ይህ የቁርኣን የበላይነት ዘመን የማይሽረው አላህ ሰማይና ምድርን እስኪወርስ ዘላቂነው።
➻ በየትኛውም ቦታና ዘመን ላይ ያሉ ሙስሊሞች ቁርኣንን የበላይ ካደረጉ የበላይ ይሆናሉ። ከሰሩበትና ከተመሩበት የማይጠፋውን ዘላለማዊ የተድላ ሀገር ይወርሳሉ።
 

✅ የኢስላም ጠላቶች የሙስሊሞችን የበላይነትና ልቅና ለመንጠቅ በገዛ እጃቸው ወደ ኩፍር ዝቅጠት እንዲወርዱ ለማድረግ ከፈበረኳቸው የሽርክና የኩፍር ፋብሪካዎች አንዱ የመንዙማ ማምረቻ ፋብሪካ ነው። የዚህ ፋብሪካ ባልተቤቶች በዋነኝነት አሕባሾች ሲሆኑ አሽዓሪያ ሱፍዮችም ትልቅ ድርሻ አላቸው። ኢኽዋኖች ኢስላማዊ ኪነ ጥበብ፣ ኢስላማዊ አርት ብለው በማስተዋወቅና እንዲሰራጭ በማድረግ የበኩላቸውን ሚና እየተወጡ ነው።
➧ ይህ ከሺርክና ኩፍር ፋብሪካ እየተመረተ የሚወጣው መንዙማ በዚህ በቁርኣን ወር ከምንጊዜውም በላይ ጨምሮ አላህ ካዘነለት በስተቀር ሁሉም ቤት ያዳርሳል። መንዙማ ተብሎ ሽርክና ኩፍር የሌለበት ማግኘት በበጋ የዝናብ ጠብታ እንደ ማግኘት ነው። አብዛኛው መንዙማ የአላህን ጌትነት አምላክነትና ስምና ባህሪ ለፉጡር የሚሰጥበት ነው። ሽንቱን መቆጣጠር የማይችልን ፍጡር የፍጥረተ ዐለሙ ፈጣሪና ተቆጣጣሪ የሚያደርግ ከነብዩ ዘመን ከሀዲያን የበለጠ ክህደት ያለበት ነው። ይህን ኩፍርና ሽርክ ለሙስሊሙ ማህበረሰብ በነብዩ ስም እየበረዙ የሚግቱበት የማክፈሪያ መሳሪያ ነው። አሕባሾች ይህን የሽርክና የኩፍር ብርዝ የሙሀባ መጠጥ ይሉታል ‼ ለዚህ ነው
"ጠጥቼ ልስከር የሙሀባው ኸምር" ‼ የሚሉት። እውነታቸውን ነው የኩፍር መጠጥ እየጠጡ ነው የሚሰክሩት። የዚህ አይነቱ ስካር በቁርኣን ወር መሆኑ ልብ ያደማል።
 
✔️ ሙስሊሞች ከልባቸው ወደ አላህ ተውበት አድርገው ተመልሰው ተፀፅተው እሱን ብቻ ተገዝተውና እሱን ብቻ ምህረት ለምነው ከጌታቸው ጋር በሚታረቁበትና ምህረት በሚያገኙበት ወር በአላህ ላይ አምፀው ከትእዛዙ ወጥተው ወደ ሽርክና ኩፍር እንዲገቡ የሚያደርግ መንዙማ እንዲጋቱ ይደረጋል።
➭ በመሆኑም የተውሒድ ተጣሪዎች ሆይ ከምን ጊዜውም በላይ በረመዳን ሙስሊሙን ከዚህ የአሕባሽና ሱፍያ የማክፈር ዘመቻ መታደግ ጫንቃችሁ ላይ የተጣለ ሀላፊነት ነው።
      አላህ ይርዳን።

https://t.me/bahruteka
〰የረመዳን ተዝኪራ〰

(... أَبَا هُرَيْرَةَ 🇧🇳 يَقُولُ : قَالَ رَسُولُ اللّه(🕋) : " قَالَ اللَّهُ : كُلُّ عَمَلِ ابْنِ آدَمَ لَهُ إِلَّا الصِّيَامَ، فَإِنَّهُ لِي وَأَنَا أَجْزِي بِهِ،.....)

[رواه البخاري: ١٩٠٤]📚

🛫 https://t.me/Mehfuza_os99
🛫 https://t.me/Mehfuza_os99
👍2
📢 አስደሳች ዜና!

         ቢላል ኢብኑረባህ የቁርአን ሒፍዝ
           እና የሸሪዓ እዉቀት ማዕከል


💎 መርከዝ ቢላል ኢብኑ ረባህ ከዚህ በፊት ለወንድና ለሴት የሸሪአ እውቀት ተማሪዎች  በተመላላሽ  የቂርአት መርሀ ግብር ብቻ ሲያስተምር  መቆየቱ ይታወቃል። ሁሌም አዳዲስ የቂርአት ኘሮግራሞችን ለተማሪዎች በማመቻቸት  የሱናውን ማህበረሰብ ማስደሰት ማያቆመው መርከዛችን  አሁን ደግሞ ለመጪው 2018 በጋ በአዳሪና በተመላላሽ  የቂርአት መርሀግብር  ተማሪዎችን ተቀብለን ለማስተማር ሙሉ ዝግጅታችንን አጠናቀን በምዝገባ ላይ እንገኛለን ።

☑️ በአዳሪ መርኃግብር ለመመዝገብ፦
➠ በአዳሪ ለወንዶች ብቻ
➠ እድሜው ከ10 ዓመት በላይ የሆነ
➠ወርሐዊ ክፍያ በአግባቡ መክፈል የሚችል
➠ ለመቅራት ፍላጎት ያለዉ 
➠ ለመርከዙ ህግና ደንቦች ተገዢ መሆን የሚችል
➠ የቆይታ ጊዜ ሁለት አመት
➠ ከተላላፊ በሽታ ነፃ የሆነ

☑️በተመላላሽ መርኃግብር ለመመዝገብ፦
➻ ለወንዶችና ለሴቶች
➻ እድሜ ከ10 ዓመት በላይ
➻ ወርሐዊ ክፍያ በአግባቡ መክፈል የሚችል/የምትችል
➻ለመቅራት ፍላጎት ያለዉ (ያላት)
➻ለመርከዙ ህግና ደንቦች ተገዢ መሆን የሚችል (የምትችል)
➻የሴቶች ሰአት፦ 2:30-9:15
➻ለወንዶች፦ 2:30-11:00
➻ ኪታብ 3:00-6:30

☑️ የሚሰጡ የትምህርት አይነቶች ፦
🔘 ቁርአን በሒፍዝና በነዝር 
🔘 ቁርአን ሙራጀዓ  
🔘 ተጅዊድ
✅የአቂዳ
🔘 የመንሀጅ
🔘የፊቂህ ሌሎችም በደረጃ ይሰጣሉ።

☎️ ለምዝገባ እና ለበለጠ መረጃ፦
📞0999553107
📞0937948156
📞0921566720
🔍 የምዝገባ ቦታ፦ለወንዶች ካራ ቆሬ ሳሌ ህንጻ ጀርባ ቢላል ኢብኑ ረባህ መድረሳ (ቁጥር 4) ለሴቶች ቢላል ኢብኑ ረባህ መድረሳ (ቁጥር 3)

https://t.me/bilalibnurebahmedresa
❤1👏1