Bilal Gallery
3.93K subscribers
269 photos
9 videos
3 files
260 links
መቼም ሰው ነኝና ስህተት አይታጣብኝም ስህተት ካያችሁ በዚህ @Amir8979 አድርሱኝ ከስህተቴ ሁሌም ተመላሽ ነኝ! "ጥፋቴን በነገረኝ ሙስሊም ሁሉ የአላህ እዝነት ይውረድ"
Download Telegram
Forwarded from 📙ሱንና የኑሕ መርከብ ናት( Abu abdulwedud)📘 (ابوا عبد الودود)
የወሎው ወርቅ ዕንቁ

ሸይክ አቡ-ዘር
- የወሎው ወርቅ ዕንቁ፤
ከስነ-ምግባር ጋር - እውቀት የታጠቁ፤
በቁርዓን በሐዲስ - በኢልም የታጨቁ፤
በሁሉም የዲን ፈን - በጣም የመጠቁ፤
ተውሂድ ሲያስተምሩ - ወኔ የሚያሞቁ፤
ሱናን ሲያብራሩ - ተንትነው የሚያነቁ፤
በሰፊ ማብራሪያ - ልብን የሚያብቃቁ፤
በሙብተዲዖች ሁሉ - ሱናን በለቀቁ፤
የቁርዓን የሐዲስ - ሚሳኤል የሚለቁ፤
የሰለፎችን ጥቅስ - ከዚያ የሚለጥቁ፤
ከደዕዋው ጎን ለጎን - ኪታብ የሚያረቁ፤
ለዲን ተማሪዎች - ማርን የሚጨምቁ፤
ሱኒዮች ሁሉም ዘንድ - በቅርቡም በሩቁ፤
በጣም የሚወደዱ - በጣም የሚናፈቁ፤
ሸይክ አቡ-ዘር ሀሰን - ውድ ናቸው ዕንቁ፤

የሀገራችን ሙብተዲዖች - ሀቅን የለቀቁ፤
በሸይክ አቡዘር ረድ - ተጋልጠው ታወቁ፤

ሸይክ አቡ-ዘር - የወሎው ወርቅ ዕንቁ፤
የሐጁሪዮችን ወገብ - ሰብረው ያደቀቁ፤
የሙመይዖችን ባጢል - በይፋ ያሳወቁ፤
የከሚሴውን ከድር - እንደ ጤፍ የወቁ፤
የኢክዋኖችን ጥፋት - በማስረጃ ያነቁ፤
ከአህባሾች ጥመት - ሰው ያስጠነቀቁ፤
ወይዘሪት አህባሽን - አፈር ላይ ያንፏቀቁ፤

በሁሉም ሙብተዲዖች - ሀቅን በለቀቁ፤
የማስረጃ ክምችት - ሚሳኤል የሚለቁ፤

ቃላት አጣሁ ለሸይክ - የሚሆናቸው ብቁ፤
ምን ብዬ ልግለጻቸው - የወሎውን ዕንቁ፤
ሸይካችንን ልገልፅበት - ቃል ሳጠ በልቁ፤
ዝቅ አደረግኳቸው - ብያቸው ወርቅ ዕንቁ፤
እስኪ ቃላት ስጡኝ - ይበልጥ የምታውቁ።

✍️ (ኢብኑ ኑሪ) ጥር 21/2018
ስልጤ (ሳንኩራ)

አላህ ምስክሬ ነው ሸይክ አቡዘርን ከልቤ እወዳቸዋለሁ። ከብዙ ግዜ ናፍቆት በኋላ የዱናው ሀገር አቀፍ ፕሮግራም ላይ አየኋቸው።

https://t.me/Senkuraselafiya
https://t.me/Senkuraselafiya
https://t.me/Senkuraselafiya
👍4❤1
♦️| ልዩ የደዕዋ ፕሮግራም በቴሌግራም!

● እነሆ የፊታችን ጁሙዓ ማለትም ነገ ጥር 22 - 2018 «በሰለፊዮች መገናኛ» ግሩፕ ልዩ የደዕዋ ፕሮግራም ተዘጋጅቷል!።

🎙ተጋባዥ፦ ሸይኽ አቡ ዘር ሐሰን ኮምቦልቻ -ሐፊዞሁ'ሏህ-

● ርእስ፦ የሰለፊዮች አንድነት አሳሳቢነቱና ከስህተታቸው ጋር ሊኖረን የሚገባው አቋም!

⏰ ሰዓት ፦ ከምሽቱ በኢትዮ  3:00 በሱዑዲያ 9:00 በኢማራት 10:00 አይለፋችሁ!።

#ሼር_በማድርግ_ድርሻችንን_እንወዋጣ!
https://t.me/Multeqa_Ahlissuneh
https://t.me/Multeqa_Ahlissuneh
❤1
👍9