Bilal Gallery
3.93K subscribers
268 photos
9 videos
3 files
259 links
መቼም ሰው ነኝና ስህተት አይታጣብኝም ስህተት ካያችሁ በዚህ @Amir8979 አድርሱኝ ከስህተቴ ሁሌም ተመላሽ ነኝ! "ጥፋቴን በነገረኝ ሙስሊም ሁሉ የአላህ እዝነት ይውረድ"
Download Telegram
🔷 ዱና ትንፋሽ አጥሯታል !

ከአመታት በፊት የሱፍያ ሙሪዶች ወደ ጠሪቃ ሱፍያ ሀድራዎች ለቀብር አምልኮትና በወልይ ስም የሙታን መንፈስን ለመለማመን ሲተሙና ሀድራዎቹ በሙሪዶች ሲጨናነቁ ነበር የምናየው ! ያሻውን ሰሪ የሆነው አምላካችን አላህ ባሮቹን ፊታቸውን ወደ ሱና አዙሮ በቁርኣንና ሐዲስ በሰለፎች ግንዛቤ ተሰባስበው ዱናን ትንፋሽ አሳጥተውዋታል ። ዱና በሱና ሰዎች ትንፋሽ አጥሯት ጉድ እያለች ነው ።
ከመላ ሀገሪቱ በሚተሙ ሰለፍዮች የተጨናነቀችው ዱና ተውሒድ እየተነፈሰች ሱና እያገሳች ነው ። አየሩም ሱና ንፋሱም ተውሒድ ነው ። ከዱና የሚፈነጥቀው የተውሒድና ሱና ጮራ ፍንጣቂ ተጎራባች ከተማና መንደር አዳርሶ መአዛው ያገኘውን እያወደ ነው ። ከቢላሎ ጀምሮ ያጨናነቀው የሱናው ወጣት ሌራን አቋርጦ ወደ ዱና መንደር ሲተም የሚነሳው አባራ ከሻም የሚመጣው የዐብዱራሕማን ኢብኑ ዐውፍ የንግድ ቃፊላ ወደ መዲና ሲገባ ይመስል ነበር ።
አላህ ይህ ስብስብ የሁሉንም ልብ ለሐቅ የሚከፍት ያድርግልን ! ።

http://t.me/bahruteka
👍2
''ይቀላቀሉ''
https://t.me/IBNU_SHAYKH
👉 ፕሮግራሙ በሰላም ተጠናቋል !

ምስጋና ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ የተገባ ይሁን ። የዱናው ሀገር አቀፍ ፕሮግራም ለሶስት ቀናት ሲካሄድ ቆይቶ በሰላም ተጠናቋል ። በዚህ ፕሮግራም ላይ ከተለያዩ የሀገራችን ክፍል የመጡ መሻኢኾችና ኡስታዞች እንዲሁም በሺዮች የሚቆጠሩ ሰለፍዮች የተሳተፉ ሲሆን በሚያስደንቅ ስርኣትና በሚያስደምም ሰላም ተጠናቆ ሁሉም ወደየመጡበት በሰላም ተመልሰዋል ።
ይህ ሀገር አቀፍ ፕሮግራም በዚህ መልኩ አስጀምሮ ላስጨረሰን አምላካች ለልቅናው የሚገባውን ምስጋና ይድረሰው ካልን በኋላ ለመሳካቱ ቀና ደፋ ያሉና በገንዘባቸው በእውቀታቸውና እንዲሁም በጉልበታቸው የሚችሉትን ሁሉ ጥረት ያደረጉ ወንድሞቻችን አላህ የኸይር ምዳቸውን ይክፈላቸው እላለሁ ።

http://t.me/bahruteka
👍6