“ሁሉን የያዘውን ያዙት፣ ሁሉን የሚገዛውን አሰሩት፣ የሕያው አምላክን ልጅ አሰሩት፣ በቁጣ ጎተቱት በፍቅር ተከተላቸው፣ በሚሸልተው ፊት እንደማይናገር እንደ የዋህ በግ በኋላቸው እየተከተለ ወሰዱት።
ሊቃነ መላእክት በመፍራትና በመንቀጥቀጥ በፊቱ የሚቆሙለትን በአደባባይ አቆሙት ኃጢኣትን ይቅር የሚለውን ኃጢኣተኛ አሉት፣ በፈራጆች ላይ በሚፈርደው በእርሱ ላይ ፈረዱበት።
ለሱራፌል ዘውድ የሚያቀዳጃቸውን የእሾሀ ዘውድ አቅዳጁት።ለኪሩቤል የግርማ ልብስ የሚያለብሳቸውን ቀይ ግምጃ አለበሱት።
የመላእክት ሠራዊት በፍጹም መደንገጥ ለሚሰግዱለት እየዘበቱበት በፊቱ ተንበረከኩ።
ይህን ያህል ትህትና እንደምን ያለ ትህትና ነው?
ይህን ያህል ትዕግስት እንደምን ያለ ትዕግስት ነው?
ይህን ያህል ዝምታ እንደምን ያለ ዝምታ ነው?
ይህን ያህል ሰውን ማፍቀር እንደምን ያለ ፍቅር ነው?
ፍቅር የአምላክን ልጅ ከዙፍኑ ሳበው እስከ ሞትም አደረሰው”
መፅሐፈ ቅዳሴ

("የዛሬ ሚያዝያ 27ቀን 2012ዓ.ም የአንድ ወር የማጠቃለያ ጸሎት መርሐ ግብር")
++===========+====+=========+++
የዛሬው ምሽት የአንድ ወር የማጠቃለያ የጸሎት መርሐ ግብር ከምሽቱ 2:30 ጀምሮ በሁሉም የቴልቪዥን ጣቢያዎች ይተላለፋል።
የጸሎት መርሐ ግብሩ በብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት መሪነት እና በብጹዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ተራዳኢነት የሚካሔድ ይሆናል።
የጸሎት ስነ-ሥርዓቱንም የቤተ ክርስቲያናችን ሊቃውንት የሆኑት ክቡር ንቡረዕድ ኤልያስ አብርሃና ክቡር መጋቤ ካህናት ኃ/ሥላሴ ዘማርያም ከፍ ባለ አቀራረብ በጣፋጭ አንደበታቸው የቤተክርሰቲያኒቱን ጸሎት በመገናኛ ብዙሃን አማካኝነት ለመላው ሕዝበ ክርስቲያን የሚያቀርቡልን ስለሆነ ኦርቶዶክሳዊያን ሁሉ በዛሬው ምሽት በየቤታችን ሆነን በመጸለይ ከፈጣሬዓለማት መድኃኔዓለም ጋር እንገናኝ።
"ልዑል እግዚአብሔር ጸሎትና ልመናችንን ይቀበለን"
አ ሜ ን

"የልደትሽ ቀን ልደታችን ነው"
ጴጥርቃ እና ቴክታ የሚባሉ ሰዎች በኢየሩሳሌም በአንድነት ተጋብተው ይኖሩ ነበር። እነዚህም በእግዚአብሄር የሚያምኑ የተወደዱ ጻድቃን ደግ ሰዎች ነበሩ። እነዚህም ሰዎች በእግዚአብሔርም በሰውም ዘንድ የበቁ ባለጸጎች ነበሩ። ነገር ግን የሚወርሳቸው ልጅ አልነበራቸውምና መካን ነበሩ። አንድ ቀን ጴጥርቃም ቴክታን እህቴ ሆይ ይህን ሁሉ የሰበሰብነውን ገንዘባችንን ምን እናደርገዋለን የሚወርሰን ልጅ የለን አንቺም መካን ነሽ እኔም ካንቺ በቀር ሌላ ሴት አላውቅም አላት። እርሷአም ወንድሜ ሆይ አምላከ እስራኤል ለኔ ልጅ ቢነሳኝ አንተም እንደኔው ሆነህ ትቀራለህን ? ከሌላ ደርሰህ ውለድ እንጂ ብላ ብታሰናብተው እንደዚ ያለ ነገር እንኳአንስ ላደርገው በልቦናዬ እንዳላስበው አምላከ እስራኤል ያውቅብኛል አላት። እሷአም አምላከ እስራኤል የሚያደርገውን የሚያውቅ የለም። ትላንትና ማታ በህልሜ ነጭ ጥጃ ከማህጸኔ ስትወጣ ያችም ነጭ ጥጃ ሌላ ነጭ ጥጃ ስትወልድ እንዲሁ እስከ 7ት ትውልድ ሲዋለድ ሰባተኛይቱ ጨረቃን ስትወልድ ጨረቃዋም ፀሃይን ስትወልድ አየሁ አለችው።
እርሱም በጠዋት ከህልም ፈቺ ዘንድ ሂዶ የነገረችውን ሁሉ ነገረው። ያም ህልም ፈቺ እግዚአብሄር በምህረቱ አይቷአቹአል በሳህሉ መግቡአችኋአል። 7 አንስት ጥጆች መውለዳቹ 7 ሴቶች ልጆች እና የልጅ ልጆች ትወልዳላቹ ከቤታቹ ሰባተኛይቱ ጨረቃ መውለዷ ከሰው የበለጠች ከመላእክትም የከበረች ደግ ፍጥረት ትወልዳላቹ። የፀሃይ ነገር ግን አልታወቀኝም አለው። እርሱም የነገረውን ሁሉ ሄዶ ነገራት እርሷአም እንጃ አምላከ እስራኤል የሚያደርገውን ማን ያውቃል ብላ ዝም አለች። ከዛም ፀንሳ በ9 ወሯ ሴት ልጅ ወለደች። ስሙአንም ሄኤሜን ብለው አወጡላት። ሄኤሜንም አድጋ ለአካለ መጠን ስትደርስ አጋብተዋት ሴት ልጅ ወለደች በስምንተኛ ቀኑአም ደርዲ ብለው ስም አወጡላት ደርዲም አድጋ እንዲሁ ሴት ወለደች እና ቶና አለቻት። ቶናም እንዲሁ ሴት ልጅ ወልዳ ሲካር አለቻት። ሲካርም እንዲሁ ሴት ልጅ ወልዳ ሴትና አለቻት። ሴትናም እንዲሁ ሴት ልጅ ወልዳ ሄርሜላ አለቻት።
ሄርሜላም እንዲሁ ሴት ልጅ ወልዳ ንጽህት ቅድስት ክብርት የምትሆን እመቤታችንን የምትወልደውን ሃናን ወለደች። ከጴጥርቃና ከቴክታ የተወለዱ 67 ወንዶች ልጆች አሉ የእመቤታችን የድንግል ማርያምን ትውልድ ለመቁጠር ትንቢት አልተነገረላቸውም ሱባኤ አልተቆጠረላቸውምና አልተፃፈም። ይህቺም ሃና በስራት በቅጣት አደገች። ለአእምሮ ስትበቃ አካለ መጠን ስትደርስ ከቤተ መንግስት ወገን ከነቅዱስ ዳዊት ወገን ከሆነው ከቅዱስ እያቄም ጋር አጋቧአት። እነዚህ ቅዱሳን እያቄም እና ሃና በአንድነት ተጋብተው ሲኖሩ ልጅ አጡ። ከእለታት አንድ ቀን ወደ ቤተ እግዚአብሄር ሄደው ሲፀልዩ ሲያዝኑ ዋሉ። ሃዘናቸው እንዴትስ ነው ቢሉ እያቄም ""አቤቱ ጌታዬ ያባቶቼ የእስራኤል አምላክ እኔ ባርያህ እለምንሃለው አትጣለኝ አትናቀኝ ፀሎቴን ስማኝ ፈቃዴን ፈጽምልኝ ለአይኔ ማረፊያ ለልቤ ተስፋ የሚሆን የተባረከ ወንድ ልጅ ስጠኝ"" ብሎ ሲለምን ዋለ።
ሃናም በበኩሏ ""አቤቱ ጌታዬ የአባቶቼ የእስራኤል አምላክ እኔ ባርያህ እለምንሃለው ስማኝ ለአይኔ ማረፊያ ለልቤ ተስፋ የምትሆነኝ የተባረከች ሴት ልጅ የማህፀኔን ፍሬ ስጠኝ"" ብላ ስትለምን ስታለቅስ ዋለች። እንዲ ብለው ሲያዝኑ ሲጸልዩ ውለው ርግብ ከልጆቿ ጋር ስትጫወት አይታ አቤቱ ጌታዬ ለዚች ግእዛን ለሌላት እንስሳ ልጅ የሰጠህ አምላክ ምነው ለኔ ልጅ ነሳኸኝ ብላ ምርር ብላ አለቀሰች። እንዲ ብለው ሲያዝኑ ሲፀልዩ ውለው ከዘካርያስ ከሊቀ ካህናቱ ሄደው አቤቱ ጌታችን ሆይ ወንድ ልጅ ብንወልድ ተምሮ ቤተ እግዚአብሄርን አገልግሎ እንዲኖር እንሰጣለን። ሴት ልጅም ብንወልድ ውሀ ቀድታ መሶብ ወርቅ ሰፍታ ፈትል ፈትላ ካህናትን አገልግላ እንድትኖር እንሰጣለን ብለው ስለት ገቡ። ዘካርያስም እግዚአብሄር ጸሎታችሁን ይስማላቹ ስእለታችሁን ይቀበልላቹ ጻህቀ ልቦናችሁን ይፈጽምላቹ ብሎ አሳረገላቸው።
ከዚያም በኋአላ ቅድስት ሃና እና ቅዱስ እያቄም እለቱን ራእይ አይተው ነገር አግንተው አደሩ። ራእዩም እንዴት ነው ቢሉ ኢያቄም 7ቱ ሰማያት እንደ መጋረጃ ተገልጠው ከላይኛው ሰማይ ነጭ ወፍ ወርዶ በራሴ ላይ ሲቀመጥ አየሁ አላት። ወፍ የተባለው ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ነጭነቱ ንጽሃ ባህሪው ነው። ከላይኛው ሰማይ ነጭ ወፍ ወርዶ በራሴ ላይ ሲቀመጥ አየሁ ማለቱ። የኢያቄምን ባህርይ ባህርይ እንዳደረገው እወቅ ሲል ነው። 7ቱ ሰማያት የተባሉ የጌታችን ልዩ ልዩ ባህሪው ምልአቱ ስፍሃቱ ርቀቱ ልእልናው ዕበዩ መንግስቱ ናቸው። ሃናም እኔም አየሁ አለችው። ምን አየሽ ቢላት ነጭ ርግብ መጥታ በራሴ ላይ ወርዳ በጆሮዬ ገብታ በማህጸኔ ስትተኛ አየሁ አለችው።
ርግብ የተባለች እመቤታችን ድንግል ማርያም ናት። ነጭነቷ ንጽህናዋ ቅድስናዋ ድንግልናዋ ነው። ነጭ ርግብ መጥታ በራሴ ላይ ተቀምጣ ከራሴ ወርዳ በጆሮዬ ገብታ በማህጸኔ ስትተኛ አየሁ ማለቷ ብስራተ ገብርኤልን በጆሮዋ ሰምታ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጌታችንን መፀነሷ ነው። ይህንኑም ራእይ ያዩት ሃምሌ 30 ዕለት ነው። እነሱም እንዲ ያለ ራዕይ ካየን ነገር ካገኘን ብለው ዕለቱን በሩካቤ ሥጋ አልተገናኙም። ፈቃደ እግዚአብሔር ቢሆን ብለው አዳምንና ሄዋንን ብዙ ተባዙ ምድርንም ሙሏት ብሎ ያበሰረ አምላክ ለኛስ ይልክልን የለምን ? ብለው ዕለቱን አልጋ ምንጣፍ ለይተው እስከ 7 ቀን ድረስ ለየብቻቸው ሰነበቱ። ነሃሴ ሰባት በሰባተኛው ቀን ከሰው የበለጠች ከመላእክት የከበረች ዓለሙ ሁሉ ተሰብስቦ ቢመዘን አንድ የራሷን ፀጉር የማያህል ደግ ፍጥረት ትወልዳላችሁ ዛሬ በሩካቤ ስጋ ተገናኙ ብሎአችኋል ጌታ ብሎ መልአኩ ለሃና ነገራት በፈቃደ እግዚአብሔር በብስራተ መልአክ እመቤታችን ቅድስት ድንፍል ማርያም እሁድ እለት ተፀነሰች። በኦሪት ስርአት እሁድ ዕለት ባል እና ሚስት መገናኘት ልማድ ነበርና እመቤታችን የተፀነሰች ዕለት አይሁድ ቀንተው ተነሱባቸው። ቅናቱ እዲህ ነው ሳሚናስ የሚባል የጦሊቅ ልጅ ከኤዶቅ ካጎቱ ቤት ሄዶ ሞተ እነርሱም እንቀብራለን ብለው ባልጋ ይዘው ሲሄዱ ከመንገድ አሳረፉት።
የሃናም የአጎቷ ልጅ ነበርና ለማልቀስ ብትደርስ ዘመዶቿ ሁሉ ተሰብስበው ሲላቀሱ ጠበቋት። እርሷም አብራ እየዞረች ስታለቅስ ጥላዋ ቢያርፍበት መግነዝ ፍቱልኝ ሳይል ብድግ ብሎ ተነስቶ "ስብሃት ለኪ ማርያም እሙ ለፀሃየ ጽድቅ ለአብ መራቱ ለወልድ ወላዲቱ ለመንፈስ ቅዱስ ጽርሃ ቤቱ ተፈስሂ ኦ ማርያም" ብሎ የፀጋ ስግደት ሰገደላት አይሁድ ከዛ ነበሩና ምነው ሳሚናስ ምን አየህ ? ምን ትላለህ ? ቢሉት ከዚች ከሃና ማህፀን የምትወለደው ህፃን ሰማይን ምድርን አየርን የፈጠረ አምላክን ትወልዳለች እያሉ መላእክት ሁሉ ሲያመሰግኗት ሰማኋቸው አለው።እኔንም ያነሳችኝ የፈወሰችኝ ያዳነችኝ እርሷ ናት አላቸው በል ተወው ሰማንህ ብለው ቅናት ጀመሩ።
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በተፀነሰች በ9 ወር ከአምስት ቀን የግንቦት መባቻ ዕለት ግንቦት 1 ተወለደች። እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የተወለደችበት እለት በአቷ በእናቷ ቤት ፍስሐ ደስታ ተደረገበት ቤቱንም ብርሃን መላው በስምንተኛውም ቀን ""ማርያም"" ብለው ስም አወጡላት።ስለምን ማርያም ብለው ስም አወጡላት። እነሆ በዚ አለም ከሚመገቡት ሁሉ ምግብ ለአፍ የሚጥም ለልብ የሚመጥን "ማር" ነው። በገነትም በህይወት የተዘጋጁ ጻድቃን ቅዱሳን "ያም" የሚባል ምግብ አላቸው ከዚህ ሁሉ የበለጥሽ የከበርሽ ነሽ ሲሉ "ማርያ

የልደትሽ ቀን ልደታችን ነው"
የቀጠለ
ም" ብለው ስም አወጡላት። የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ስም ተነቦ ሳይተረጎም ይቀር ዘንድ አይገባምና፦
ማ ፦ ማለት ማህደረ መለኮት
ር ፦ ማለት ርግብየ ይቤላ
ያ ፦ማለት ያንቀዓዱ ኃቤኪ ኩሉ ፍጥረት
ም ፦ ማለት ምስሃል ወምስጋድ ወምስተሰርይ ኃጥያት ማለት ነው።
"ማርያም" ማለት ፦ልዩ ከጣዖት ክብርት እምፍጥረታት ንጽሕት እምሃጥያት መልክ ከደም ግባት የተሰጣት ማለት ነው። ዳግመኛም "ማርያም" ማለት ፦ተፈስሒ ቤተ ይሁዳ ወተሐሰይ ቤተ እስራኤል ማለት ነው። "ማርያም" ማለት ፦መርህ ለመንግስተ ሰማያት ማለት ነው።እነሆ ዛሬ በዚህ አለም ለዕውር መሪ በትር እንዲሰጡት ሁሉ እርሷም በፍቅሯ በጣዕሟ የሰውን ሁሉ ኃጥያት ክፋት ፍቃ ከልጁአ ከወዳጁአ አስታርቃ ከገሃነመ እሳት አውጥታ መንግስተ ሰማያት የምታስገባ ስለሆነች ነው። ስለዚህ መርህ ለመንግስተ ሰማያት አሏት። "ማርያም" ማለት ፦ሰረገላ ፀሃይ ማለት ነው። "ማርያም" ማለት ፦ተላኪተ እግዚአብሔር ወሰብእ ማለት ነው። "ማርያም" ማለት ውብህት ስጥውት ማለት ነው። በዚህ በግንቦት አንድ ቀን እመቤታችን
አለምን ልታስምር ከቅድስት ሃና እና ከቅዱስ
እያቄም በብዙ ፀሎት ልመና ተገኘች።
የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም
ፍቅሯ ጣዕሟ በረከቷ ረድኤቷ አይለየን
በአማላጅነቷ ከልጇ ከመድኀኒአለም ታማልደን
ከአንዱአምላክ ለማ

[ግንቦት 11 የቅዱስ ያሬድ ዓመታዊ በዓል]
✍️ በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
♥️ኢትዮጵያዊው ሊቅ ቅዱስ ያሬድ አባቱ አብዩድ (ይሥሐቅ) እናቱ ክርስቲና (ታውክልያ) ሲባሉ የተወለደውም በ፭፻፭ ዓ.ም. በአክሱም ነው፡፡ ሰባት ዓመት ሲመላው አባቱ ስላረፈ፤ እናቱ የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት እንዲያስተምረው ለአባ ጌዴዎን ሰጠችው፡፡
❤️ ነገር ግን ማጥናት ስላልቻለ አባ ጌዴዎን ይቈጣው ነበርና ሸሽቶ ከዱር ውስጥ ገባ፤ ከዐዘኑም ብዛት የተነሣ በዛፍ ሥር ተጠልሎ ሳለ አንዲት ታናሽ ትል ከዛፍ እኩሌታ ደርሶ ሲወድቅ ሲነሣ በመጨረሻም በጭንቅ ከዛፉ ላይ ሲወጣ በማየቱ እግዚአብሔር በዚኽች ታናሽ ፍጥረት እንዳስተማረው በመረዳት ይቅርታ ጠይቆ ወደ መምህሩ ተመልሷል፡፡
♥️ “ወእምዝ ሶበ ሰአለ ኀበ እግዚአብሔር በብካይ ብዙኅ ተርኅወ ልቡናሁ ወተምህረ በሐጺር ዕለት መጻሕፍተ ብሉይ ወሐዲስ” ይላል ከዚኽ በኋላ ቅዱስ ያሬድ ወደ እግዚአብሔር በለመነ ጊዜ ልቡናው ብሩህ ኾኖለት በዐጭር ጊዜ ውስጥ የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍትን ተምሮ በመጨረስ ዲቁናን ተሾመ፤ እስከ ርሱ ዘመን በማነብነብ እንጂ በከፍተኛ ድምፅ የመዝሙር ማሕሌት አልነበረም፤ እግዚአብሔርም ለዚኽ አባት የመላእክትን ዝማሬ ሊያሳየው ስለወደደ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እስከ ሦስተኛው ሰማይ እንደተነጠቀ ኹሉ ሊቁም ተነጥቆ የኻያ አራቱ ካህናተ ሰማይን የምስጋና ዝማሬ ሰምቶ ተመለሰ፡፡
♥️ ቅዱስ ያሬድ ከአርያም ወርዶ ወደ ምድር እንደ ደረሰ ወደ አክሱም ጽዮን ቤተ ክርስቲያን ገብቶ፡- “ሃሌ ሉያ ለአብ ሃሌ ሉያ ለወልድ ሃሌ ሉያ ለመንፈስ ቅዱስ ቀዳሚሃ ለጽዮን ሰማየ ሣረረ ወበዳግም አርአዮ ለሙሴ ዘከመ ይገብር ግብራ ለደብተራ” (ለአብ ምስጋና ይገባል፣ ለወልድም ምስጋና ይገባል፣ ለመንፈስ ቅዱስም ምስጋና ይገባል፡፡ ከጽዮን አስቀድሞ ሰማይን ፈጠረ ዳግመኛም ለሙሴ የድንኳኑን ሥራ እንዴት እንደሚሠራ አሳየው) ሲል ዘምሮ ይቺኑ መዝሙር ከሰማይ መላእክት አገኘኹት፣ በማለት "አርያም" በሚል ሥያሜ ጠርቷታል፡፡
♥️ይኽነኑ ድርሳነ ዜማ የጻድቁ ካሌብ ልጅ ንጉሥ ገብረ መስቀል በሰማ ጊዜ ጫማውን ሳይጫማ ንግሥቲቱም ደንገጡሮቿን አጃቢዎቿን ሳታስከትል መኳንንቱ፣ ካህናቱና መምህራኑ እነሱን ተከትለው እየተጣደፉ ወደ ዐደባባዩ በመኼድ በተመስጦ ሲሰሙት ውለዋል፡፡
♥️ ቅዱስ ያሬድ ዐምስት የዜማ መጻሕፍትን የደረሰ ሲኾን እነርሱም፦
፩ኛ) ድጓ
፪ኛ) ጾመ ድጓ
፫ኛ) ምዕራፍ
፬ኛ) ዝማሬ
፭ኛ)መዋሥዕት ናቸው፡፡
♥️ እነዚኽንም ታላላቅ ድርሰቶቹን በሦስት የዜማ ስልቶች ማለት በግእዝ፣ በዕዝል፣ በአራራይ አዘጋጅቷቸዋል፡፡ “ወአሐተ ዕለተ እንዘ ይዜምር ያሬድ ቀዊሞ ታሕተ እገሪሁ ለንጉሥ ገብረ መስቀል ወእንዘ ያጸምዕ ንጉሥ ቃሎ ለያሬድ ተከለ በትረ ኀጺን ውስተ መከየደ እግሩ ለያሬድ” ይላል፤ ከዕለታት ባንዳቸው ቅዱስ ያሬድ በተመስጦ ልዑል እግዚብሔርን በዝማሬ ሲያመሰግን ንጉሥ ገብረ መስቀል ሳያውቁት ልባቸው በጣዕመ ዜማው በመመሰጡ የብረት ዘንጉን በቅዱስ ያሬድ እግር ላይ ተክለውታል፤ ከእግሩም ብዙ ደም ቢፈስስም ቅዱስ ያሬድ ግን ማሕሌቱን እስከሚፈጽም ድረስ ምንም አልሰማውም ነበር፡፡
♥️ንጉሡም የደሙን መፍሰስ አይቶ ደንግጦ ቅዱስ ያሬድን “የደምኽ ዋጋ የፈለግኸውን ንገረኝ” አለው፤ ቅዱስ ያሬድም ተምኔቱ ወደ ገዳም መኼድ እንደኾነ ነገረው፤ ያን ጊዜ ንጉሡ እያዘነ አሰናብቶታል፡፡
♥️ “ወእምዝ ቦአ ያሬድ ውስተ ቤተ ክርስቲያን ወቆመ ቅድመ ታቦተ ጽዮን” ይላል ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብቶ በታቦተ ጽዮን ፊት በመቆም የአንቀጸ ብርሃንን ምስጋና ከመዠመሪያው እስከ መጨረሻው በተናገረ ጊዜ በእግዚአብሔር ኀይል ክንድ ያኽል ከምድር ከፍ ከፍ አለ።
❤️ ከዚኽ በኋላ ወደ ሰሜን ተራራዎች ወደ ገዳም ሲኼድ የአኲስም ጽዮን ካህናት እስከ ተከዜ ወንዝ ድረስ ሸኙት ርሱም እጅግ ባማረ ጣዕመ ዜማ ድምፁን ከፍ አድርጎ “ሰላም እግዚአብሔር ኲሉ ባቲ ተሃሉ ወትረ ምስለ ኲልክሙ” (በኹሉ ላይ ጸንታ የምትኖር የእግዚአብሔር ሰላም ዘወትር ከኹላችኊ ጋር ትኑር) ብሎ የስንብት መዝሙርን ዘመረ፤ ካህናቱም ይኽነን ቃል ሰምተው መሪር እንባን አለቀሱና ተሰነባበቱ፡፡
♥️ በትርጓሜ ቅዳሴ ማርያም መቅድም ላይ እንደምናነብበው ቅዱስ ያሬድ ማይ ኪራህ በተባለው ቦታ ተሰውሮ ጸዋትወ ዜማን ሲያስተምር እመቤታችን ሶርያዊው ቅዱስ ኤፍሬምን የብህንሳውን አባ ሕርያቆስን በአካለ ነፍስ እንዲመጡ አድርጋ ኤፍሬም ውዳሴዬን፤ ሕርያቆስ ቅዳሴዬን ነግራችኹት ቅዱስ ያሬድ በዜማ ይድረስልኝ ብላ ነግረውት በዜማ ደርሶታል፤ ይኽም ሊታወቅ ሥረይ በቅዳሴ ማርያም ይበዛል፡፡
♥️ ርሱም ጸዋትወ ዜማን ለደቀ መዛሙርቱ እያስተማረ መላእክት ዘወትር እየጐበኙት በጾም በጸሎት ተወስኖ በተጋድሎ ለኻያ ኹለት ዓመት ጸንቶ ኖረ፤ በመጨረሻም ጌታችንም ለቅዱስ ያሬድ ተገልጾለት፦
“ኦ ፍቁርየ ቀዳሚኒ በከመ ሰመርኩ ትርአይ ሥርዐተ ስብሐተ መላእክት ዘበሰማያት ወአስተኀለፍከ ዘንተ ማሕሌተ ዲበ ምድር... ” (ወዳጄ ሆይ ቀድሞ በሰማይ ያለ የመላእክትን ሥርዐተ ማሕሌት እንድታይና ወደ ምድርም አስተላልፈኽ ይኽነኑ ዜማ እንድትመሠርት እንደ ወደድኊ ኹሉ እኔ ዳግም ተመልሼ በምመጣበት ጊዜ ከካህናተ ሰማይና ሄሮድስ ደማቸውን ካፈሰሰው ሕፃናት ጋር በደብረ ጽዮን ትዘምር ዘንድ ሰማያዊ የክብር አክሊልና የብርሃን ልብስ ተዘጋጅቶልኻል” ብሎት ቃል ኪዳንን ሰጥቶት ጌታ በክብር ዐረገ፡፡ የቅዱስ ያሬድ መታሰቢያውም ግንቦት ዐሥራ አንድ ነው፡፡
♥️ ሊቁ አርከ ሥሉስም የቅዱስ ያሬድን ነገር በአርኬው ላይ፦
“ሰላም ለያሬድ ስብሐተ መላእክት ለሕዋጼ
እንተ አዕረገ በልቡ ኅሊና መንፈስ ረዋጼ
ለትምህርተ መጽሐፍ ገብአ እምኀበ ኮነ ነፋጼ
በብዙኅ ጻማ ዘአልቦ ሑጻጼ
መልዕልተ ጒንደ ዖም ነጺሮ እንዘ የዐርግ ዕጼ”
(የመላእክትን ምስጋና ለመጐብኘት ከመንፈስ ቅዱስ የሚሰጥ ፈጣን ዐሳብን ወደ ልቡናው ያሳረገ ለኾነ፤ ጒድለት በሌለበት በብዙ ድካምም ወደ ዛፍ ግንድ ጫፍ ላይ ትል ሲወጣ ተመልክቶ፤ ኰብልሎ ከኼደበት መጻሕፍትን ለመማር የተመለሰ ለኾነ ለያሬድ ሰላምታ ይገባል) በማለት ሊቁ ማሕሌታይን አመስግኖታል፡፡
♥️ ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ በተአምኆ ቅዱሳን መጽሐፉ ላይ ማኅቶተ ቤተ ክርስቲያን ሊቁ ቅዱስ ያሬድን ሲያወድስ፡-
“ሰላም ለያሬድ ቀሲስ ዘጽጉብ እክለ መንፈስ ቅዱስ፤
ዘአስተጋብአ ምድራሳተ እምኲሎሙ መጻሕፍት
ወአሰርገዋ በሐዋዝ ስብሐት ወበጥዑም ማሕሌት
ለብሔረ ኢትዮጵያ በስብሐት ሃሌ ሉያ
ዘከዐወ ቃለ መለኮት ዲቤሃ
ከመ አስራበ ወርቅ ንጹሐ”፡፡
(የመንፈስ ቅዱስን ምግብን የጠገበ፤ ከመጻሕፍት ኹሉ ትርጓሜያተ ድርሰትን ያሰባሰበ፤ ሃሌ ሉያ በሚል ምስጋና የኢትዮጵያ ሀገርን በጥዑም ማሕሌትና በሚያምር ምስጋና ያስጌጠ፤ የመለኮት ቃልን በላይዋ ላይ እንደ ንጹሕ የወርቅ ሻሻቴ ያፈሰሰ ለኾነ ለካህኑ ያሬድ ሰላምታ ይገባል) ይለዋል፡፡
የቅዱስ ያሬድ በረከት ይደርብን፤ እናንተም ይኽነን ሊቅ አወድሱት።

#ስላልሠጠኽኝ_አመሰግንሃለሁ!
በአንድ ወቅት አንዲት ወፍ እንቁላል የምጥትልበት እና የክረምቱን ዝናባማ ወራት የምታሳልፍበት ጎጆ መሥሪያ ቦታ እየፈለገች ነበር። በዚህ ፍለጋዋ ወቅት ሁለት ዛፎችን ተመለከተችና ቀርብ ብላ መጠለያ ቦታ ልትጠይቃቸው ወሰነች። ወደ አንደኛው ዛፍ ጠጋ ብላ ፤ መጠለያ መፈለጓን ነገረችው ፤ ዛፉም መጠለያ ይሰጣት ዘንድ ፈቃደኛ እንዳልሆነ ገለጸላት።
ወፏም በመጀመሪያው ዛፍ ምላሽ ተናድዳ ፤ ወደ ሁለተኛው ዛፍ ተጠጋች ፤ መጠለያ መፈለጓን ነገረችው። ሁለተኛውም ዛፍ በደስታ "ጥያቄሽን በእሺታ ተቀብያለሁ እኔ ላይ ተጠለዪ ፣ ቤትሽም ፣ መኖሪያሽም በዚሁ ይሁን" አላት። ወፊቱም ተደስታ በሁለተኛው ዛፍ ላይ ቤቷን አበጃጅታ ፤ እንቁላልዋን ጣለች ፤ ዝናባማው ወራትም ወዲያውኑ ጀመረ። የሚዘንበው ዝናም ታላቅ ከመሆኑ የተነሣ ፤ የመጀመሪያው ዛፍ ወደቀና ጎርፍ ወሰደው። ይህን የተመለከተችው ወፍ በሽሙጥ አነጋገር "አየህ ዕጣ ፈንታህ ይኼ ነው ፤ ለእኔ መጠለያን እምቢ ስላልኽ ፤ እግዚአብሔር በዚህ ቀጣህ" አለችው። ዛፉም ፈገግ እያለ "ከነበርኩበት ኹኔታ አንፃር ይህን ክረምት እንደማላልፍ እንደምወድቅ አውቅ ነበር ፤ የአንቺ እና የልጆችሽ ሕይወት አደጋ ላይ እንዳይወድቅ በማሰብ መጠለያ ስትጠይቂኝ እምቢ አልኩሽ" ሲል መለሰላት። ወፊቱም የእምቢታውን ምክንያት በተረዳች ጊዜ ስለዛፉ አዘነች ፤ ከእርሷ ሀሳብ ልቆና ርቆ ስላሰበላት ስለበጎነቱም በልቧ ውስጥ አከበረችው።
+
"የምትለምኑትን አታውቁም።" (ማቴ. 20: 22)
++
በሕይወታችን የምንሻውን ነገር መከልከላችን ፤ ማጣት ወይም ከስኬት መጓደል ማለት አይደለም። ማን ያውቃል የለመነው ነገር የማጣታችን ምንጭ ፣ የመጥፊያችን ምክንያት ሊሆን ይችላል። ስለዚህ ፤ "የፈለጉትን አለማግኘትም ሥጦታ ነው!"
+++
በእምቢታ የመለሱልን ወይም የከለከሉን ሁሉ ደግነት የራቃቸው ፣ ፍቅር አልባዎች አይደሉም። እናት ልጇ እሳት መንካት ሲፈልግ ፤ ጥቅምና ጉዳቱን እንደማይለይ አውቃ እንደምትከለክለው ፤ ክልከላዋም የጥላቻ ሳይሆን የፍቅር እንደሆነ ፤ እንዲሁ የሚከለክለን ሁሉ ጠላታችን ሳይሆን ወዳጃችንም እንደሆነ እናስተውል!!
++++
የአንዳችን መውደቅ ሌሎችንም ለውድቀት እንዳይዳርግ ፤ እያንዳንዳችን ስለራሳችንም ፣ በዙሪያችን ስላሉ ስለሌሎች ወንድሞቻችንና እኅቶቻችንን እናስብ!!!
+++++
በእኛ ሕሊና "እገሌ እኮ እንዲህ ነው ፤ እንዲህ ለማለትም ፈልጎ ነው" ብለን ስለሰዎች በእርግጠኝነት የምናስበው ሀሳብ የምንገልጠው ቃል ፤ ሁልጊዜ አሸናፊና የመጨረሻው ትክክለኛ ሀሳብ ነው ብለን ከማሰብ እንከልከል ፤ የሰውን ልቡና የሚመረምር እግዚአብሔር ነውና!!!

✝ #ሰኔና_ሰኞ ✝
=>ሰኔና ሰኞ በልማዳዊ አነጋገር በ7 ዓመት አንዴ ብቻ የሚፈጠር መገጣጠም ነው:: (በቀመር ትምህርት ግን በዘመነ ዮሐንስ ምክንያት በ5 እና በ6 ዓመታት ይመላለሳል)
☞በሃገራችን ብዙ ሰው ነገሮች ድንገት ሲደራረብበት የሃዘኔታ አግራሞቱን ለመግለጽ "#ወይ_ሰኔና_ሰኞ!" ይላል::
☞ነገሩም እየዋለ ሲያድር ወደ ምልኪነት (ባዕድ አምልኮ) እየተቀየረ በመሔዱ በተለይ በገጠሩ የሃገራችን አካባቢ ሰኔና ሰኞ ሲገናኙ (ሰኔ ሰኞ ሲብት) መፍራቱ አለ:: (ልክ በሰንበት ላይ #ደብረ_ዘይት እንደሚከብደው ሁሉ)
☞በተቃራኒው ደግሞ የሰኔና ሰኞ መግጠም በትክክልም የፈጣሪ ማስጠንቀቂያ ነው የሚሉም አሉ፡፡ በተለይም ለቀመር መምህራንና ልጆቻቸው፡፡
☞ዋናው ነገር ግን ሰኔና ሰኞ: ታሪካዊ ዳራውን ሳንዘነጋ ደስ የሚል ቀን ማድረግ እንችላለን:: ይገባልም:: ምክንያቱም:- ሰኔ እና ሰኞ ሥርወ ቃላቸው (የወጡበት ግስ) ተመሳሳይና ጥሩ መሆኑን ማየት እንችላለን::
☞የ2ቱም መሠረታቸው "ሰነየ (አማረ)" የሚል ነውና:: ሰኔም: ሰኞም ማማርን: መበጀትን: መልካምነትን የሚገልጹ ናቸውና::
☞በዚያውም ላይ ከሠራን የማናተርፍበት፡ ከጸለይን ጸጋውን የማናገኝበት ምንም ምክንያት የለም፡፡ ችግሩ ከግጥምጥሞሹ ሳይሆን ከያዝነው #ሰብእና እና #ጎዳና ላይ ነው፡፡
☞ስለዚህ #እንጸልይ ፤ #እንሥራ ፤ ስለክፋታችንም #እንጸጸት ፤፤
☞ከዚህ በሁዋላ ሰኔና ሰኞ የሚገናኙት ከ6 ዓመታት በሁዋላ (በ2018) መሆኑ ነው::
☞እስኪ ደግሞ የዚያ ሰው ይበለን!
" መቼም ዕድሜ አይጠገብ! "
<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

Forwarded from የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ(ዕረፍተ ሕሊና)
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ዘለአለም ሥላሴ! ብለን እንጀምራለን ስመ እግዚአብሔርን ካልጠሩ ረድኤት አይገኝምና ‹‹ እግዝእትየ ኩኒ ለሕይወትየ ጸወኖ›› እያልንም በመጮኽ ያለ እመቤታችን መጠጊያ መሸሸጊያ የለንምና ‹‹ተዘከር እግዚኦ ኪዳነ አግብርቲከ ቅዱሳን›› እያልንም በመጮኽ ያለቅዱሳን ምልጃ ሰላምና እረፍት አናገኝምና …. ይህንን እያልን ዘመኑን በዋጀ መንገድ ከአባቶቻችንን ሊቃውንት አንደበት የሚወጣውን የሕይወት ቃል እንማራለን
በዘህ መስመር ታላላቅ የቤተክርስቲያን ሊቃውንት ያስተማሯቸውን ትምህርቶች ፣ ከአባቶች እግር ስር በተማሩ ወንድሞቻችን በሚቀርቡ ተከታታይ ትምህርቶች ፣ ያሬዳዊ ዝማሬዎች ፣ በፈገግታ የሚማሩባቸው ኪነጥበባዊ ስራዎች ቀናቸውን ጠብቀው ይቀርባሉ
እነሆ እድምተኞች ትሆኑ ዘንድ በእግዚአብሔር ስም ተጠርታችኋል…
👇👇👇👇Join👇👇👇👇
https://t.me/joinchat/AAAAAFDW-7lcOTVwjdMNFg

ሰኔ ፩፪ ( እንኳን አደረሳችሁ )
ሊቀ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል አፎምያን ከሰይጣን እጅ ያዳነበት ቀን
ሰኔ 12 በዚህች ቀን ሊቀ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል አፎምያን ከሰይጣን እጅ ያዳነበት ቀን ነው። ዳግመኛም በዛሬዋ ቀን ጻድቁ ንጉስ ቅዱስ ላሊበላ ያረፈበት ቀን ነው። ቅድስት አፎምያ የቅዱስ ሚካኤልን ዝክር ታዘክር ነበር ለድሆችም አብዝታ ትረዳ ነበር፤ በዚህ ሰይጣን ቀናባት በመነኩሴ ተመስሎ ሊያስታት ሞከረ በቅዱስ ሚካኤል ስዕል አሳፍራ መለሰችው ከ 3 ወራት በኃላ ሰኔ 12 ቀን ዳግመኛ ቅዱስ ሚካኤል ነኝ ብሎ ሊፈትናት መጣ፤ ሚካኤል ከሆንክ መስቀልህ የት አለ አለችው ከዚህ በኃላ አፉን ከፍቶ አይኑን አጉረጥርጦ አንገቷን አነቃት “ቅዱስ ሚካኤል ድረስልኝ” ብላ ተጣራች ቅዱስ ሚካኤል ከሰማይ ፈጥኖ ወረደ በበትረ መስቀሉም መታው ጊዜዬ ሳይደርስ አታጥፋኝ ስዕልህ ባለበት፤ ስምህ በተጠራበት፤ ድርሳንህ በሚነበብበት፤ ፈጽሞ አልደርስም ብሎ ማለ፤ ተገዘተ ሸሸም፤ ከዚህ በኃላ ቅዱስ ሚካኤል ቅድስት አፎምያን “ወዳጄ አፎምያ ባነቺ ደስ አለኝ ወጋሽ በሰማይ ታላቅ ነው” ብሎ ባርኳት አርጓል። ቅዱስ ላሊበላ (ላልይበላል) ላል ማለት ማር ማለት ነው፤ሲወለድ በንብ ተከቦ ነበርና ማር ይበላል “ላልይበላል” አሉት ሚስቱ ቅድስት መስቀል ክብራ ትባላች እረፍቷ ሐምሌ 27 ነው ልጁ ይትባረክ እረፍቱ መስከረም 24 ቀን ነው ቅዱስ ላሊበላ 40 ዓመት ኢትዮጰያን አስተዳደረ ዓለምን የሚያስደንቅ እጹብ እጽብ የሚያሰኝ ከአንድ አለት ብቻ እጀታ በሌለው መጥረቢያ 12 ውቅር አብያተክርስቲያናትን አነጸ፤ እነዚህ በአንድ ቦታ ስላሉ ነው እንጂ በወሎ በጎንደር በሸዋ ለቁጥር የሚበዙ አብያተክርስቲያናትን አንጿል፤ ታህሳስ 29 ቀን ተወልዶ በ 80 ዓመቱ ሰኔ 12 በዛሬዋ ቀን አርፏል። መጨረሻ ያነጸው ቤተክርስቲያን አዳዲ ማርያምን ነው፤ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ናቸው እንዲያንጽ የጠየቁት እርሱም ጀምሮ ሳይጨርስ አቡነገብረመንፈስ ቅዱስ ወደርሱ ቀርበው ወዳጄ ላሊበላ የእረፍትህ ቀን ደርሷልና ወደ ላስታ ተመለስ አሉት እርሱም ተመለሰ በዚያም አረፈ፤ እራሱ ባነጸው በቤተ ጎሎጎታ ተቀበረ በመቃብሩም ላይ ለ 10 ቀን የማይጠፋ ብርሃን ሲበራ ይታይ ነበር። ከበዓሉ በረከት ያሳትፈን።

ሐምሌ 19 ዕለት የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል አምላካቸው ክርስቶስን አንክድም በማለታቸው የፈላ ጋን ውስጥ የተወረወሩት ቅዱስ ቂርቆስና እናቱን ቅድስት ኢየሉጣ ተራድቶ ያዳነበት በዓል ነው። ❖ ይኸውም የቅድስት ኢየሉጣን ልጅ ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ ከሐዲው መኰንኑ ይዞ “ስምኽ ማነው” ብሎ በጠየቀው ጊዜ “ነቅዕ ዘእምዐዘቅት ንጹሕ ወእማይ ዘኢይማስን ክርስቲያን ስምየ” (ከንጹሕ ዐዘቅትና ከማይለወጥ ከማይጠፋ ውሃ የተገኘ ስሜ ክርስቲያን ነው ሞክሼ ስም ከፈለግኽ ደግሞ እናቴ የሠየመችኝ ቂርቆስ ነው) በማለት ክርስትናው መመኪያው የኾነው ይኽ ቅዱስ ሕፃን መለሰለት፡፡ ❖ መኰንኑም ለአማልክት ከሠዋኽ ስታድግ እሾምኻለኊ ክርስቶስን ካድ ቢለው ቅዱስ ቂርቆስ ግን “የሰይጣን መልእክተኛ ለእውነትም ጠላቷ የኾንኽ ከእኔ ራቅ” አለው፡፡ መኰንኑም ይኽነን ሰምቶ በመቈጣት የቅዱስ ቂርቆስ ደሙ እንደ ውሃ እስኪፈስስ ድረስ እንዲጨምቁት እና ጨውና ሰናፍጭ በኹለቱ የአፍንጮቹ ቀዳዳዎች እንዲጨመሩ ቢያደርግበት፤ በመንፈስ ቅዱስ ጸጋ የጠነከረው ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ ግን “ትእዛዝኽ ለጒረሮዬ ጣፋጭ ኾነ ከማርና ከሥኳርም ለአፌ ጣመኝ” እያለ አምላኩ ክርስቶስን አመሰገነ፡፡ ❖ መኰንኑ በዚኽ ሳያበቃ እናትና ልጇ በክፉ አሟሟት እንዲሞቱ በማሰብ የረዘሙና የተሳሉ በእሳትም እንደ ፍም የጋሉ ዐሥራ አራት የብረት ችንካሮች እንዲመጡ አስደርጎ ሰባቱ በእናቱ አካላት፤ ሰባቱ በሕፃኑ ሰውነት ላይ እንዲሰካ ቢያስደርግም በጌታችን ትእዛዝ ግለቱ ጠፍቶ እንደ በረዶ በመቀዝቀዝ ምንም ምን ጒዳት ሳያደርስባቸው ቀረ፡፡ ❖ ከዚያም ወደ ወኅኒ ቤት እንዲገቡና እንዲዘጋባቸው አደረገ፤ ከዚያም ሕፃኑና እናቱ የሚሠቃዩበት ታላቅ መንኰራኲር ለ፵ ቀናት ተሠርቶ ካለቀ በኋላ ኹለቱንም በደራቁ ራሳቸውን ላጭተው የእሳት ፍሕምን በላያቸው ላይ ቢያደርጉም የእግዚአብሔር መልአክ ሥቃዮቹን ኹሉ ከእነርሱ አራቀላቸው፡፡ ❖ የሕፃኑ ምላስ እንዲቈረጥ አዝዞ ቢያስቈርጠውም ጌታችን ምላሱን መልሶለታል፡፡ “ወአዘዘ ካዕበ ያፍልሑ ማየ ውስተ ጽሕርት ዐቢይ ወይደይዎሙ ለሕፃን ቂርቆስ ወለእሙ ኢየሉጣ” ይላል በታላቅ ጋን ውሃ አፍልተው ሕፃኑንና እናቱን እንዲጨምሯቸው ሲያዝዝ ከሚፍለቀለቀው ውሃ ድምፅ የተነሣ ለጊዜው እናቱ ፍርሀት ሥጋዊ ቢያገኛትም ልጇም ወደ ጌታችን በጸለየላት ጊዜ ፍርሃቱ ርቆላት ከልጇ ጋር ስትገባ መልአከ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ወርዶ ውሃውን አቀዝቅዞ ሐምሌ ፲፱ አውጥቷቸዋል፡፡ ❖ በመጨረሻም የሰማዕትነትን አክሊል የሚያገኝባት ጊዜ ሲደርስ ጌታችን ተገልጾለት ስሙን ለሚጠራ ኹሉ ቃል ኪዳንን ከሰጠው በኋላ ሥጋኽን በኤልያስ ሠረገላ ላይ አኖርልኻለኊ አለው፤ ይኽነን በሰማ ጊዜ በእጅጉ ተደሰተ፤ ከዚኽም በኋላ ጥር ፲፭ በሌሊቱ እኲሌታ ከእናቱ ጋር አንገቱ ተቈረጠ የሰማዕትነትን ክብር ተቀዳጅተዋል። ❖ ጥር ፲፮ ደግሞ የቅዱስ ቂርቆስ ማኅበር የኾኑ ዐሥራ አንድ ሺሕ አራት በሰማዕትነት ዐልፈዋል፡፡ ሊቁ አርከ ሥሉስም የቅዱስ ቂርቆስን ተጋድሎ በማዘከር፡- “እግዚአብሔር ሤመ ረድኤቶ ለንእስናከ ዐቃቤ ወስምዖ መጥበቤ ፍትወ ምግባር ቂርቆስ ወምዑዘ ኂሩት እምከርቤ ለዘተጽዕረ በምንዳቤ ወለዘቈስለ በጥብጣቤ ለአባልከ ሰላም እቤ” (እግዚአብሔር ረድኤቱን ለታናሽነትኽ ጠባቂን አስቀመጠ፤ ብልኅ የሚያደርግ ምስክርነቱንም፤ ምግባርኽ ያማረ በጎነትኽ ከከርቤ ይልቅ የሚሸት ቂርቆስ፤ በመከራ የተቸገረ በግርፊያ የቈሰለ ለኾነ ሰውነትኽ ሰላም እላለኊ) እያለ ሕፃኑን ሰማዕት ያወድሳል፡፡ ❖ ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫም በመጽሐፉ፦ “ሰላም ለቂርቆስ ወሬዛ በመንፈስ በልደት ንዑስ፤ ንጹሕ ከመ ዕጣን ወፍሡሕ ከመ ወይን”፡፡ (በልደተ ሥጋ ታናሽ በመንፈስ ጐልማሳ፤ እንደ ዕጣን ንጹሕ እንደ ወይንም አስደሳች ለኾነ ለቂርቆስ ሰላምታ ይገባል) ❖“ሰላም ለሰማዕታት እለ ምስሌሁ ፭፼ ወ፬፻፤ ፬፼ ወ፪፻፲ወ፬”፡፡ (ከርሱ ጋር ያሉ ፭፼ ከ፬፻፤ ፬፼ከ፪፻፲፬ ሰማዕታት ሰላምታ ይገባቸዋል) በማለት አመስግኗል፨ [የሊቀ መላእክት የቅዱስ ገብርኤል ተራዳኢነት የቅዱስ ቂርቆስ የእናቱ የኢየሉጣ፤ ስለአምላካቸው ስለ ክርስቶስ ፍቅር አንገታቸው በሰይፍ የተቆረጡት የሰማዕታት በረከት ይደርብን፨ [ከመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ]
እንኳን አደረሳችሁ መልከአ ዑራኤል ሐምሌ 22
"ዑራኤል ሆይ ያለመናገር በጥንተ አርምሞ ከነፋስና ከእሳት ለተፈጠረ ተፈጥሮህ ሰላም እላለሁ።
ዑራኤል ሆይ፤ የይቅርታና የቸርነት ክብር መልአክ ነህና ስለኛ ሰለሰው ልጆች ወደ ልዑል እግዚአብሔር ማልድ። አማላጅነትህ ዘወትር ከጥፋት ያድናልና።
ዑራኤል ሆይ፤ያለ ዝምታና ያለ ቸልታ ፈጣሪያቸውን ለሚያመሰግኑ አፍህና ከናፍርህ ሰላም እላለሁ።
ዑራኤል ሆይ፤ ትጉህ የኾንህ የትጉሃን አለቃ እንደመሆንህ ሁሉ ዓለምን ለመቀደስ የእግዚአብሔር ልጅ በፈሰሰው ደሙ እኛን የቅድስት ወንጌል ልጆች አድነን፤ ቤዛም ሁነን።
ዑራኤል ሆይ፤ በደዌ ሥጋ በደዌ ነፍስ የተያዙትን ሕሙማን ለሚፈውስ ቃልህና እስትንፋስህ ሰላም እላለሁ።
ዑራኤል ሆይ፤ ሰማያዊ አገልጋይ ቄስ ነህና ምድርን በከበረ
በክርስቶስ ደም እንደባረክሃት እንደዚሁ ቤተ መቅደስህን ሕያው በሚሆን በክርስቶስ መስቀል ባርካት።"
እንኳን ለቅዱስ ዑራኤል ዓመታዊ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን ።
ቅዱስ ዑራኤል በምልጃ አይለየን!!

እንኳን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ጾመ ፍልሰታ ፍቺ በዓል በሰላምና በጤና አደረሰን አደረሳችሁ! በየትም ዓለም የምትኖሩ የክርስትና እምነት ተከታዮች ሰላምታችን ይድረሳችሁ፡፡
#የእመቤታችን_ትንሣኤና_ዕርገት
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዚህ ምድር የኖረችው ስልሳ አራት ዓመት ነው፡፡ እነዚህ ዓመታት ሲተነተኑ ሦስት ዓመት በወላጆቿ ሐናና ኢያቄም ቤት፣ ዐሥራ ሁለት ዓመት በቤተ መቅደስ፣ ሠላሣ ሦስት ዓመት ከሦስት ወር ከልጇ ከወዳጇ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር አሥራ አምስት ዓመት ከሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ ጋር ነው፡፡
ያረፈችውም ጥር 21 ቀን በ50 ዓ.ም ነው፡፡ ባረፈችበት ወቅት ቅዱሳን ሐዋርያት ክቡር ሥጋዋን ለማሳረፍ ወደ ጌቴ ሴማኒ ሲሔዱ አይሁድ "ቀድሞ ልጇ በሦስተኛው ቀን ሞትን ድል አድርጎ ተነሣ፤ በአርባኛውም ቀን ወደ ሰማይ ዐረገ፤ ተመልሶም ይህን ዓለምን ለማሳለፍ ይመጣል እያሉ በማስተማር ሕዝባችንን ወስደውብናል፡፡ አሁን ደግሞ ዝም ብለን ብንተዋት እርሷም እንደ ልጇ ተነሳች እያሉ በማስተማር ሊያውኩን አይደለምን? ኑ! ተሰብስበን በእሳት እናቃጥላት" ብለው ክፉ ምክር ተማከሩ፡፡
ከመካከላቸውም ብርቱ ሰው የሆነው #ታውፋንያ የተባለ ቅድስት ሥጋዋን ከሐዋርያት ነጥቆ ለማስቀረት ክቡር ሥጋዋ ያለበትን የአልጋ ሸንኮር ሲይዝ በመልአከ እግዚአብሔር እጁ ተቆርጣ ከአልጋው ላይ ተንጠልጥላ ቀረች፤ ከዚህ የጥፋቱ ሥራው ተምሮ እመቤታችንን በመለመኑ እመቤታችን የተቆረጠች እጁን መልሳለታለች፡፡
ከዚህ በኋላ መልአከ እግዚአብሔር የእመቤታችንን የተቀደሰ ሥጋዋን ጌታችን ይወደው የነበረ ተብሎ የተነገረለት ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስን ይዞ በገነት በዕፀ ሕይወት ሥር አስቀመጠው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስም የሆነውን ሁሉ ለወንድሞቹ ቅዱሳን ሐዋርያት ነገራቸው፡፡ እነሱም የእመቤታችን ሥጋ በክብር ለማሳረፍ ካላቸው ጉጉት የተነሣ ከነሐሴ 1 ቀን ጀምሮ ሱባኤ ገቡ፡፡
ከሁለተኛ ሱባኤ ቆይታቸው በኋላ በአሥራ አራተኛ ቀናቸው ጌታችን የእመቤታችንን ትኩስ ሥጋ ሰጣቸው፡፡ ሐዋርያትም በዝማሬና በታላቅ ምስጋና በጌቴ ሴማኔ ቀበሯት፡፡ ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት ‹‹አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ አንተና የመቅደስህ ታቦት› › ተብሎ ትንቢት የተናገረውን ሲተረጉሙት ‹‹ፈጣሪያችን እግዚአብሔር ሆይ፥ ወደ መንግሥተ ሰማያት የምታሳርፈው የመቅደስህ ታቦት የሆነችውን ድንግል ማርያምን ይዘህ ተነሥ›› ብለው ያመሰጥሩታል፡፡ /መዝ. 131፥8/፡፡
የእመቤታችንን ቅድስት ሥጋዋን ሐዋርያት ሲቀብሯት በሀገረ ስብከቱ ሕንድ የነበረው ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ ከሀገረ ስብከቱ ሲመለስ እመቤታችን ስታርግ ያገኛታል ለምልክት እንዲሆነው ሰበኗን (የመግነዟን ጨርቅ) ተቀብሏት ይለያያሉ፡፡ ለወንድሞቹ ሐዋርያት ያየውን ይነግራቸዋል፡፡
ለበረከት የሰጠችውንም ሰበን ያካፍላቸዋል፤ ሐዋርያት ‹ ‹ዕርገቷን እንዴት እሱ ብቻ ተመልክቶ ለምን እኛ ይቀርብናል› › ብለው በዓመቱ ነሐሴ አንድ ቀን ሱባኤ ገቡ፡፡ ነሐሴ 16 ቀን የልባቸው መሻት ተፈጸመላቸው፡፡ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እመቤታችንን መንበር፣ ቅዱስ ጴጥሮስን ንፍቀ (ረዳት) ቄስ፣ ቀዳሚ ሰማዕት ቅዱስ እስጢፋኖስን ገባሬ ሰናይ (ዋና ዲያቆን) አድርጎ ቀድሶ ሁሉንም አቆረባቸው፡፡
በትኅትና የያዙት ሱባኤም የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያምን ዕርገቷን ለማየት አበቃቸው፡፡ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንም ይህን መሠረት አድርጋ ከነሐሴ 1-16 ጾመ ፍልሰታ በማለት ከሰባቱ አጽዋማት አንዱ አድርገን እንድንጠቀምበት ሥርዐት ሠራችልን፡፡
በነቢያና በሐዋርያት መሠረት ላይ የታነጽን ኦርቶዶክሳውያን የተዋሕዶ ልጆች በየዓመቱ ይህን ጾም በሱባኤ በማሳለፍ ከእመቤታችን ጸጋና በረከት ተሳታፊዎች እንሆናለን፤ ሆነናልም፡፡ የዓመት ሰዎች ይበለን፡፡
ከእመቤታችን ረድኤት በረከት ተቋዳሾች ያድርገን፡፡
አሜን!

ነሐሴ 24
ድካም በማብዛት እንደ ነቢያት፣ ወንጌልን በማስተማር እንደ ሐዋርያት፣ በመገረፍ እንደ ሰማዕታት፣ አጥንቱ ከስጋው ጋር እስኪጣበቅ ከሰውነቱ ማለቅ ብዛትና የሚያቃጥለውን ላብ እንደ ደም ዥረርታ በማፍሰስ፥ ከስግደቱ የተነሳ የሰውነቱ መለያ እስኪቆጠር ድረስ ተባህትዎን በመያዝ እንደ መነኮሳት ሆኖ መንፈሳዊ መገዛቱን ለመጨረስ ቆርጦ የተነሳ።
አይን እያለው እንደማያይ፣ ጆሮ እያለው እንደማይሰማ፣ ክረምትና በጋን ሳያያቸው 8 ጦር ዙሪያው ተክሎ የእግሩ አገዳ እስኪቆረጥ ድረስ ያለ ምግብ ያለ ውሃ ቅጠል እንኩአን ሳይቀምስ በፅኑ ተጋድሎ እንባውን እያፈሰሰ በብዙ የደከመ። ብጹዕ አባታችን በህመም በተያዘ ጊዜ በመንፈስ ልጆቹ የሆኑ ሁሉ ወንዶችም ሴቶችም ተሰብስበው ብዙ አለቀሱለት፡፡
አባታችንም ‹‹ልጆቼ አታልቅሱ ነገር ግን የሽማግሌውን ቃል ስሙ ከሁሉ አስቀድሞ እምነታችን በእግዚአብሔር ላይ ይሁን፡፡ ልጆቼ ሆይ ሰላም ለእናንተ ይሁን እንግዲህ ወዲ ግን ተሰናበትኳችሁ የእግዚአብሔር ፍቅሩ የክብሩም ባለቤትነት የረዳትነቱም ሀብት ዘወትር ከእኔና ከሁላችሁም ጋር ለዘላዓለሙ በእውነት ይኑር፡፡›› በማለት እንደዚህች ባለች እለት በምግባር ፍጹም የሆነ ተጋድሎው የበዛ ትሩፋቱ ያማረ፣ ሌሊትና ቀን በመቆም እግሩ የተሰበረ፣ በክረምትና በበጋ ውርጭ መልኩ የጠቆረ፣ በጌታችን ስም ደም ተቀብቶ ሰማዕት የሆነ፣ የዓለም ፀሐይ የትምህርት ብርሃን #ብጹዕ_አባታችን_አቡነ_ተክለሃይማኖት በተወለዱ በ 99 ዓመት ዐረፉ፡፡
የአባታችን ረድኤት በረከት አይለየን፡፡

#ሥርዓተ_ጸሎት_ወስግደት_ዘዓርብ_ስቅለት
👉🏽ዐርብ #ጠዋት በ፲፪ ሰዓት
አቡን
ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ(፫) ነአምን ሕማሞ ለዘኢየሐምም፤ ርግዘተ ገቦሁ ነአምን፤ ወቅንዋተ እደዊሁ ነአምን፤ ዬ ዬ ዬ፤ ነአምን ሞቶ ወትንሣኤሁ።
በመቀጠል "#ለከ_ሃይል" ይባላል። ከኦሪት ምንባብ እስከ እስከ ተአምረ ኢየሱስ ያለው ምንባብ ይነበባል።
ምስባክ
መዝ: ፳፮ ፣ ፲፪
እስመ ቆሙ ላዕሌየ ሰማዕተ ዐመፃ፤
ወዘኢየአምር ነበቡ ላዕሌየ፤
እስመ ቆሙ ላዕሌየ ሰማዕተ ዐመፃ።
ከአራቱም ወንጌል ካህኑ ካነበበ በኋላ ቀጥሎ ያለውን ቃል ከስግደት ጋር በዜማ በኅብረት ይበሉ:-
👉🏽ማቴ: ፳፯ : ፩ - ፲፬ ከተነበበ በኋላ
ወጸቢሆ ተማከሩ ሊቃነ ካህናት ይስቅልዎ ለኢየሱስ ዲበ ዕፀ መስቀል።
👉🏽ማር: ፲፭ : ፩ - ፭ ከተነበበ በኋላ
ወጸቢሆ ተማከሩ ሊቃነ ካህናት አውጽእዎ አፍአ ለኢየሱስ ወወሰድዎ ይስቅልዎ።
👉🏽ሉቃ: ፳፪ : ፷፮ - ፸፩ ከተነበበ በኋላ
ወጸቢሆ ተማከሩ ሊቃነ ካህናት አውጽዕዎ ለኢየሱስ ወመጠውዎ ለጲላጦስ።
👉🏽ዮሐ: ፲፰ : ፳፰ - ፵ ከተነበበ በኋላ
ወጸቢሆ ተማከሩ ሊቃነ ካህናት አውጽዕዎ ለኢየሱስ ወነበረ ዐውደ ሶቤሃ።
ከዚህ በኋላ ተግሣጻትን የ"#ኪርያላይሶን" ጸሎትና ስግደት እስከ ቡራኬ ድረስ ያድርሱ። ከዚያም በመቀጠል #የሰዓቱን "#መልክዐ_ሕማማት" ያድርሱ።
👉🏽ዐርብ #ጠዋት በ፫ ሰዓት
አቡን
ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ(፫) አርዑተ መስቀል ፆረ (፪)፤ ይስቅልዎ ሖረ፤ ዬ ዬ ዬ፤ ከመ ኪያነ ይቤዙ እግዚእ ኮነ ገብረ።
በመቀጠል "#ለከ_ሃይል" ይባላል። ከኦሪት ምንባብ እስከ ተአምረ ኢየሱስ ያለው ምንባብ ይነበባል።
ዲያቆኑ መዝሙር ፴፬ትን ፫ ቦታ ከፍሎ በውርድ ንባብ ይበል። በቀመጠል ካህኑ ከሕዝቡ ጋር በቅብብል እየተሰገደ:-
ግፍኦሙ እግዚኦ ለእለ ይገፍኡኒ፤
ጽብኦሙ እግዚኦ ለእለ ይጸብኡኒ፤
ግፍኦሙ እግዚኦ ለእለ ይገፍኡኒ።
ይ.ዲ ምስባክ:- መዝ: ፳፩ : ፲፮
ዐገቱኒ ከለባት ብዙኃን፤
ወአኃዙኒ ማኅበሮሙ ለእኩያን፤
ዐገቱኒ ከለባት ብዙኃን።
👉🏽ማቴ: ፳፯ : ፲፭ - ፲፯ ከተነበበ በኋላ
ጊዜ ፫ቱ ሰዓት አኃዝዎ ለኢየሱስ ወወሰድዎ ይስቅልዎ።
👉🏽ማር: ፲፭ : ፮ - ፲፭ ከተነበበ በኋላ
ጊዜ ፫ቱ ሰዓት አሕየወ ሎሙ በርባንሃ ወወሀበ ሎሙ ኢየሱስሃ ይስቅሉ።
👉🏽ሉቃ: ፳፫ : ፲፫ - ፳፭ ከተነበበ በኋላ
ጊዜ ፫ቱ ሰዓት ወሰድዎ ለኢየሱስ ውስተ ዓውደ ምኲናን።
👉🏽ዮሐ: ፲፱ : ፩ - ፲፪ ከተነበበ በኋላ
ጊዜ ፫ቱ ሰዓት ቀሠፎ ጲላጦስ ለኢየሱስ ወመጠዎሙ ይስቅልዎ።
ከዚህ በኋላ ተግሣጻትን የ"#ኪርያላይሶን" ጸሎትና ስግደት እስከ ቡራኬ ድረስ ያድርሱ። ከዚያም በመቀጠል #የሰዓቱን_መልክዓ_ሕማማት ያድርሱ።
#ዐርብ_በስድስት_ሰዓት
አቡን
ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ(፫) ተሰቅለ (፫)፤ ወሐመ ቤዛ ኲሉ ኮነ፤ ዬ ዬ ዬ፤ በመስቀሉ ቤዘወነ እሞት ባልሐነ።

ዲያቆኑ ከሐዋርያው ከቅዱስ ጳውሎስ መልዕክት ከገላትያ በውርድ ንባብ ይበል። ከዚያም ካህኑ ከሕዝቡ ጋር በቅብብል በዜማ እየተሰገደ:-
ለመስቀልከ ንሰግድ ኦ ሊቅነ፤
ወለትንሣኤከ ቅድስት ንሴብሕ ኲልነ፤
ይእዜኒ ወዘልፈኒ።
ይ.ዲ ምስባክ መዝ: ፳፩ : ፲፮
ቀነዉኒ እደውየ ወእገርየ
ወኆለቊ ኲሎ አዕፅምትየ
ቀነዉኒ እደውየ ወእገርየ
ከአራቱም ወንጌል ካህኑ ካነበበ በኋላ ቀጥሎ ያለውን ቃል ከስግደት ጋር በኅብረት ይበሉ:-
👉🏽ማቴ: ፳፯ : ፳፯ - ፵፭ ከተነበበ በኋላ
ጊዜ ፮ቱ ሰዓት አልበስዎ አልባሲሁ ለኢየሱስ ወወሰድዎ።
👉🏽ማር: ፲፭ : ፲፮ - ፴፫ ከተነበበ በኋላ
ጊዜ ፮ቱ ሰዓት ዐበጥዎ ለስምኦን ከመ ይፁር መስቀሉ።
👉🏽ሉቃ: ፳፫ : ፳፯ - ፵፬ ከተነበበ በኋላ
ጊዜ ፮ቱ ሰዓት ሰቀልዎ ለኢየሱስ በቀራንዮ መካን።
👉🏽ዮሐ: ፲፱ : ፲፫ - ፳፯ ከተነበበ በኋላ
ጊዜ ፮ቱ ሰዓት ቀትር ሶቤሃ ሊቃነ ካህናት ሰቀልዎ ለኢየሱስ ማዕከለ ፪ኤ ፈያት።
ከዚህ በኋላ ተግሣጻትን የ"#ኪርያላይሶን" ጸሎትና ስግደት እስከ ቡራኬ ድረስ ያድርሱ። ከዚያም በመቀጠል የሰዓቱን መልክአ ሕማማት ያድርሱ።
#ዐርብ_በዘጠኝ_ሰዓት
አቡን
ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ(፫) ሶበ ሰቀልዎ(፫) ለእግዚእነ፤ ፀሐይ ጸልመ ወወርኅ ደመ ኮነ፤ ዬ ዬ ዬ፤ አድለቅለቀት ምድር ወተከሥቱ መቃብራት።
በመቀጠል "#ለከ_ሃይል" ይባላል። ከኦሪት ምንባብ እስከ ተአምረ ኢየሱስ ምንባብ ይነበባል። ከዚያም በኃላ ካህኑ ከሕዝቡ ጋር በቅብብል በዜማ እየተሰገደ:-
ኦ ዘጥዕመ ሞተ በሥጋ፤
ኦ ዘጥዕመ ሞተ በሥጋ፤
ኦ ዘጥዕመ ሞተ በሥጋ።
ዲያቆኑ ከሐዋርያው ከቅዱስ ጳውሎስ መልዕክት ከ ግብረ ሕማማት በውርድ ንባብ ይበል። በመቀጠልም ሶስት ካህናትና አንድ ዲያቆን ጥቁር ልብሰ ተክህኖ ለብሰው በስዕለ ስቅለት ፊት ይቀመጡ፤ ከአንዲት መብራት በቀር ሌላውን ያጥፉና አንድ ግምጃ በራሳቸውና ገፃቸው ላይ ያድርጉ (ምዕመናን ደግሞ በነጠላቸው ይሸፈኑ)። አንገታቸውን ዝቅ አድርገው በዕዝል ዜማ በታላቅ ድምጽ በሀዘንና በፍርሃት በለቅሶና በዕንባ ጭምር ካህኑና ሕዝቡ በመቀባበል "አምንስቲቲ"ንና "ተዘከረነ እግዚኦ"ን እያንዳንዱን ሦስት ሦስት ጊዜ ይዝለቁ። እንደገናም "አምንስቲቲ"ንና "ተዘከረነ እግዚኦ"ን እያንዳንዱን አንድ አንድ ጊዜ በመቀባበል በሁለት ዙር (አጠቃላይ ቁጥሩ ፲፪ እስኪሞላ ድረስ) ይበሉ። ዲያቆኑም በየክፍሉ በሐዘን ዜማ (በውርድ ንባብ) እያስገባ ያንብብ።
ይ.ካ ከሕዝቡ ጋር በቅብብል:-
አምንስቲቲ ሙኪርያ አንቲ ፋሲልያሱ
አምንስቲቲ ሙዓግያ አንቲ ፋሲልያሱ
አምንስቲቲ ሙዳሱጣ አንቲ ፋሲልያሱ
ይ.ካ ከሕዝቡ ጋር በቅብብል:-
ተዘከረነ እግዚኦ በውስተ መንግሥትከ፤ ተዘከረነ እግዚኦ ኦ ሊቅነ፤ ተዘከረነ እግዚኦ በውስተ መንግሥትከ።
ይ.ሕ በከመ ተዘከርኮ ለፈያታዊ ዘየማን እንዘ ሀሎከ ዲበ ዕፀ መስቀል ቅዱስ።
ይ.ዲ ምስባክ መዝ: ፷፰ : ፳፮
ወወደዩ ሐሞተ ውስተ መብልዕየ፤
ወአስተዩኒ ብሒዐ ለጽምዕየ፤
ወወደዩ ሐሞተ ውስተ መብልዕየ።

👉🏽ማቴ: ፳፯ : ፵፮ - ፶ ከተነበበ በኋላ
ጊዜ ተስዓቱ ሰዓት ጸርሐ ኢየሱስ በቃሉ ወይቤ ኤሎሄ ኤሎሄ።
👉🏽ማር: ፲፭ :፴፬ - ፴፯ ከተነበበ በኋላ
ጊዜ ተስዓቱ ሰዓት ገዓረ ኢየሱስ በቃሉ ወወጽአት መንፈሱ ሶቤሃ።
👉🏽ሉቃ: ፳፫ : ፵፭ - ፵፯ ከተነበበ በኋላ
ጊዜ ተስዓቱ ሰዓት ከልሐ ኢየሱስ በቃሉ ወአማኅጸነ ነፍሶ ሶቤሃ።
👉🏽ዮሐ: ፲፱ : ፳፰ - ፴ ከተነበበ በኋላ
ጊዜ ተስዓቱ ሰዓት አጽነነ ርእሶ ኢየሱስ ወይቤ ተፈጸመ ኲሉ።
ከዚህ በኋላ ተግሣጻትን የ"#ኪርያላይሶን" ጸሎትና ስግደት እስከ ቡራኬ ድረስ ያድርሱ። ከዚያም በመቀጠል #የሰዓቱን_መልክዐ_ሕማማት ያድርሱ።
#ዐርብ_በአስራ_አንድ_ሰዓት
አቡን
ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ(፫) ንዜኑ (፫) ዘአምላክነ ኂሩተ ትሕትና ወየውሃተ ዘእንበለ ዐቅም፤ ዬ ዬ ዬ፤ እንዘ ይጼዕልዎ ኢጸዐሎሙ፤ እንዘ ያሐምምዎ ኢተቀየሙ።
በዚህ ሰዓት "ለከ ሃይል፣ ኪርያላይሶንና መልክዐ ሕማማት" #የለም።
..............

Forwarded from Yg
ሰላም ወንድሞቼ እና እህቶቼ ይህ የchange.org ሊንክ ሞዓ ተዋህዶ ያነሳቸው 7ቱ አቁዓም የኔም ጥያቄ ነው የሚል ስለሆነ register አርጋችሁ በemailaቹ በሚላከው link confirm እንድታረጉ እጠይቃለሁ
https://chng.it/YqsSkHzyxW
ይሄንኑ link ደሞ ለሌሎች share እንድታረጉ እጠይቃችሁአለው

Change.org
Sign the Petition
Prevent Cultural and Religious Based Genocide of Ethiopian Orthodox Christians.
Forwarded from Janderebaw Media
"እርሱም የዚህን ዓይነት ትእዛዝ ተቀብሎ ወደ ውስጠኛው ወኅኒ ጣላቸው፥ እግራቸውንም በግንድ አጣብቆ ጠረቃቸው። በመንፈቀ ሌሊት ግን ጳውሎስና ሲላስ እየጸለዩ እግዚአብሔርን በዜማ ያመሰግኑ ነበር፥ እስረኞቹም ያደምጡአቸው ነበር" ሐዋ. 16:24
"የጠገበች ነፍስ የማር ወላላ ትረግጣለች፤ ለተራበች ነፍስ ግን የመረረ ነገር ሁሉ ይጣፍጣታል" ምሳ. 27:7
ለመመዝገብ ይህንን ይጫኑ
https://forms.gle/XGBUJspsT9KydX2a8