ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
52.3K subscribers
1.64K photos
32 videos
16 files
1.86K links
በዚህ ቻናል የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ትምህርቶች እና የአበው ቀደምት የተናገሯቸው መንፈሳዊ ንግግሮች እንዲሁም ልዩ ልዩ ሐይማኖታዊ ትምህርቶችና መልዕክቶች ይተላለፉበታል፡፡
Download Telegram


የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ካልዕ ድርሳን ስለ ጌታችን ጥምቀት


የሁሉን ጌታ በተዋረደ አገልጋዩ እጅ ሲጠመቅ ያዩት ዘንድ ለሰዎች እንዴት ይቻላቸዋል? ሳር እሳትን ይዳስሰው ዘንድ እንደምን ይችላል? የሚያቃጥለው አይደለምን? ምድር መላእክትን የቀደሳቸው ከኃጢአተኛና ከበደለኛ አገልጋዩ እጅ ሲጠመቅ ታይ ዘንድ እንደ ምን ይቻላታል? እንደ ዳታንና እንደ አቤሮን ተከፍታ ትውጠኝ የለምን?

ውኃዎችስ ፈሳሾችን የቀደሳቸውን ባሕሮችንም የፈጠራቸውን ከደካማ አገልጋዩ እጅ ሲጠመቅ ያዩት ዘንድ እንዴት ይቻላቸዋል? መላእክት የሚሰግዱለት እርሱ ከድኃ አገልጋዩ እጅ ሲጠመቅ ማየት ለልዑል ኃይላት እንዴት ይቻላቸዋል? በእሳት ጦር አይገድሉኝምን?

አቤቱ ጌታ ሆይ አንተስ አሁን ራስህን እንደ ድኃ በፊቴ ስለምን ዝቅ ታደርጋለህ? ራስህን ቀና አድርግ እንጂ፡፡ አቤቱ ጌታዬ ሆይ አንተ የሁሉ አለቃ (ራስ) ነህና፡፡ የመሬታውያንና የሰማያውያን ሁሉ ጌታቸው አንተ ነህ፡፡ አንተ የሚታይና የማይታይ ጌታ ነህ፡፡ አንተ የፍጥረት ሁሉ ጌታ ነህ፡፡ በዚህ የቆሙ አሕዛብም ሁሉ ታጠምቃቸው ዘንድ አንተን በተስፋ ይጠባበቃሉ፡፡ እኔንም ከእነሱ ጋር አጥምቀኝ፡፡ ስለምን ከእኔ መጠመቅን ትሻለህ? በአንተ ላይ ምንም ምን ኃጢአት የለብህምና፡፡

እነሆ ዮርዳኖስ አንተ እንደ ፈጠርከው አወቀ፡፡ ጥልቁም አንተ የምስጋና ጌታ እንደ ሆንህ አወቀ፡፡ እነሆ አሁን ፍጥረት ሁሉ ፈጣሪያቸው አንተ እንደ ሆንህ አወቁ፡፡ እኔስ የማላውቅህ ይመስልሃልን? መጠመቅም ግድ ከሆነ ራስህ ተጠመቅ፡፡ እኔ ግን አጠምቅህ ዘንድ እጄን አልዘረጋም፡፡ ይልቁንም አንተ እኔን ታጠምቀኝ ዘንድ እሻለሁ አለው፡፡

ዳግኛም አቤቱ ጌታዬ ሆይ በእናቴ ሆድ ሳለሁ ወደ እኔ በመጣህ ጊዜ በእናቴ አንደበት የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጪ ዘንድ እኔ ምንድን ነኝ? ብዬ ተናገርሁ። በዚያ አልተሳሳትሁም በዚህም ባለ ማወቅ አልበደልሁም፡፡

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም መልሶ አንዲህ አለው፡፡ ዮሐንስ ሆይ እኔ በመለኮቴ ክብር የማደርገውን ሁሉ አውቃለሁና ሆይ ተወኝ፡፡ አንተ ክብሬን በአሕዛብ ዘንድ ልትገልጠው ትወዳለህ፡፡ እነርሱ ግን ስለ እኔ የምትናገረውን ምስክርነትህን አይቀበሉም፡፡

ይቀጥላል....

(ድርሳነ ሠለስቱ ሊቃውንት በመምህር ቃለጽድቅ ሕግነህ የተተረጎመ ገጽ 89-103)
50👍14🙏9
#በዓለ_ሥሉስ_ቅዱስ (ጥር 7)

ጥር ሰባት በዚች ቀን በዓለ ሥላሴ የሚከበረው ስለ ሁለት ምክንያቶች ነው:: ቀዳሚው ሕንጻ ሰናዖርን ማፍረሳቸው ሲሆን ሌላው ደግሞ ቅዳሴ ቤታቸው ነው::

#ሕንጻ_ሰናዖር
ሰናዖር ከሺዎች ዓመታት በፊት በአሁኗ ኢራቅ አካባቢ እንደ ነበረ የሚነገርለት ግዛት ሲሆን ስሙ ለሃገሪቱም: ለንጉሡም በተመሳሳይ ያገለግል ነበር:: ከናምሩድ ክፋት በሁዋላ ሰናዖርና ወገኖቹ ከሰይጣን ተወዳጁ::

ከጥፋት ውሃ (ከኖኅ ዕረፍት) በሁዋላ በሥፍራው በአንድነት ይኖሩ ነበርና እርስ በርሳቸው "ኑ ሳንበተን ስማችን የሚጠራበትን ሕንጻ እንሥራ:: በዚያውም አባቶቻችን በውሃ ያጠፋ እግዚአብሔርን እንውጋው" ተባባሉ::

ቀጥለውም ሰማይ ጠቀስ ፎቅን ገነቡ:: ከሕንጻው መርዘም የተነሳ በጸሐይ አብስለው በልተዋል ይባላል:: ቀጥለውም ጦር እያነሱ ፈጣሪን ሊወጉ ወርውረዋል::

መቼም የእነዚህን ሰዎች ክፋትና ቂልነት ስንሰማ ይገርመን ይሆናል:: ግንኮ ዛሬ ሰለጠንኩ በሚለው ዓለም እየተሠራ ያለው ከዚህ የከፋ ነው:: ቸርነቱ ቢጠብቀን እንጂ እንደ ክፋታችንስ ጠፊ ነበርን::

ርሕሩሐን ሥላሴ ግን የሰናዖር ሰዎች የሠሩትን አይተው ማጥፋት ሲችሉ አላደረጉትም:: የባሪያቸውን የኖኅን ቃል ኪዳን አስበዋልና:: ይልቁኑ "ንዑ ንረድ ወንክአው ነገሮሙ ለከለዳውያን-ቁዋንቁዋቸው እንደባልቀው" አሉ እንጂ::

ከለዳውያን ልሳናቸው ተደበላልቆ 71 ቁዋንቁዎች ተፈጠሩ:: እነርሱም ስምምነት አጥተው ተበተኑ:: ሥላሴም ያን ሕንጻ በነፋስ ትቢያ እንዲሆን በተኑት:: ስለዚህም እስከ ዛሬ ሥፍራው "ባቢሎን (ዝሩት)" ሲባል ይኖራል::

#ቅዳሴ_ቤት
ልክ የዛሬ 324 ዓመት አድያም ሰገድ ኢያሱ በኢትዮዽያ በነገሡ በ10ኛው ዓመት (በ1684 ዓ.ም) በጐንደር ከተማ ንግሥተ አድባራት ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ተሰርታ ተጠናቃለች::

ጥር 7 ቀንም ሊቁ ክፍለ ዮሐንስን ጨምሮ በርካታ ምዕመናን ሠራዊት መሣፍንትና ሊቃውንት ባሉበት ቅዳሴ ቤታቸው ተከብሯል። በዕለቱም ታላቅ ሐሴት ተደርጉዋል። ኢያሱ አድያም ሰገድ ኃያል ደግ ጥበበኛ አስተዋይ መናኝ ንጉሥ ነውና።

ቤተ ሥላሴን አስጊጿታልና ከዚህ ቀን ጀምሮ ጥር ሥላሴ በድምቀት የሚከበር ሆኗል:: ነገር ግን በተሠራች በ16 ዓመቷ ደጉ ኢያሱ ከተገደለ በሁዋላ ቤተ ክርስቲያኑ በአደጋ ፈርሷል:: ዛሬ የምናየው በ1708 ዓ.ም በልጁ በአፄ ዳዊት ሣልሳዊ የታነጸውን ነው::

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን ለዘላለሙ አሜን።

(ስንክሳር ዘተዋሕዶ)
🙏40👍2720💯1🏆1
122🙏11👍3🕊3
፯ (የመጨረሻ)
የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ካልዕ ድርሳን ስለ ጌታችን ጥምቀት


አንተ በእውነት ትናገራልህ ነገር ግን እነርሱ ቃልህን አያምኑም፡፡ ከአይሁድ ወገን በዚህ የቆሙትስ አንተ የእፉኝት ልጆች ያልካቸው አይደሉምን? ዮሐንስ ሆይ ጽድቅን ሁሉ እናደርግ ዘንድ ይገባናልና ፈጽመህ ተወኝ። ዮሐንስ ሆይ ትእዛዛትን ሁሉ እፈጽም ዘንድ ተወኝ፡፡ ዳግማዊ አዳምንም አትመልስለት፡፡ እኔ ይህን ሁሉ እታገሥ ዘንድ ሁለተኛው አዳም ሆኛለሁና፡፡

ዮሐንስ ሆይ ተጠምቄ ሁልን አነጻ ዘንድ ተወኝ፡፡ እኔ ካልተጠመቅሁ በደልና ኃጢአት አይወገድምና ዮሐንስ ሆይ ተወኝ፡፡ ጳውሎስ የሕግ ፍጻሜው ክርስቶስ በእርሱ ያመነውን ሁሉ ይቀድስ ዘንድ ነው ብሎ ይጽፍ ዘንድ ዮሐንስ ሆይ እጠመቅ ዘንድ ተወኝ፡፡

እኔ ከአንተ ዘንድ ካልተጠመቅሁ ሀብቱና ትምክሕቱ ብዙ የሆነ ንጉሥ ዝቅ ወደ አለው ወደ አገልጋዩ ካህን ይጠመቅ ዘንድ አይመጣምና፡፡ ዮሐንስ ሆይ አብ ስለ ልጁ ምስክር ይሆን ዘንድ ተወው፡፡ ዮሐንስ ሆይ በምጠመቅ ጊዜ የአባቴን የሀብቱን ብዛት ታይ ዘንድ እኔንም ተወኝ ልጠመቅ አለው፡፡

ያን ጊዜ ዮሐንስ ፈቃዱን ይፈጽም ዘንድ ተወው፡፡ ከዚህም በኋላ ወልድ ዋሕድ ወደ ዮርዳኖስ ወርዶ በውኃ መካከል ዕራቁቱን ቆመ፡፡ ከጌታ ከግርማው ክብር የተነሣ በውኃው ውስጥ የሚንቀሳቀሰው ሁሉ ዝም አለ፡፡ ከመባርቅት፣ ከደመናት፣ ከጠሎች፣ ከአውሎና ከነጎድጓድ ብዛት የተነሣ ድንቅ ነገር ሆነ፡፡

ዮሐንስም ታላቅ ድንጋጤን ደነገጠ፡፡ የእግዚአብሔር የሀብቱ ጸጋ ተገለጠ፡፡ ሰማይ ተከፈተ መንፈስ ቅዱስም በነጭ ርግብ አምሳል ወርዶ በተወደደ ልጁ ላይ ተቀመጠ፡፡ በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው ሲል የአብ ቃልም ከሰማይ ተሰማ፡፡ በዚያ የቆሙ ሰዎችም ሰምተው ይህን ነገር ዕፁብ ዕፁብ አሉ፡፡

ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስም ምስጋና ይሁን አሜን ለዘለዓለሙ፡፡ ይሁን ይሁን፡፡

(ድርሳነ ሠለስቱ ሊቃውንት በመምህር ቃለጽድቅ ሕግነህ የተተረጎመ ገጽ 89-103)
63👍16🙏11


የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ድርሳን ስለ ቃና ዘገሊላ


አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስም ብፁዕ የሚሆን ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በቃና ዘገሊላ ስለ ተደረገው ሰርግ የተናገረው ድርሳን ይህ ነው፡፡ ጸሎቱና በረከቱ በሁላችን ላይ ለዘለዓለሙ ጸንቶ ይኑር አሜን፡፡

መሬታውያንና ሰማያውን ለሚያመሰግኑት ለእግዚአብሔር ምስጋና ይገባል፡፡ መንፈሳውያን ሠራዊት ለሚያመሰግኑት ጻድቃንና ደጋጎች አገልጋዮቹም ለሚዘምሩለት ለእግዚአብሔር ምስጋና ይገባል፡፡ ተኣምራትን ሁሉ በጸና ኃይሉ ላደረገ ለእግዚአብሔር ጌትነትና ሥልጣን ይገባል፡፡

ድንቅን ሥራውን ጠቢባን ሊናገሩለት የማይቻላቸው እግዚአብሔር ይመስገን፡፡ ቃሉን የላከ ፈጣሪ በመንፈስ ቅዱስ ግብር ቅድስት ድንግል ከምትሆን ከእመቤታችንም ከጥበብ ሁሉ በሚበልጥ ጥበቡ ሰው የሆነ ከፍጥረት ሁሉ የተሠወረ፤ ከእርሷም አምላክ በሥጋ ተገለጠ፡፡ አንድ መሢሕ አንድ አምላክ አንድ አኗኗር፣ አንድ መለኮትም፣ አንድ ፈቃድ፣ አንድ ሥልጣን፣ አንድ ኃይል አንድ ጌታም ነው፡፡ ከእርሱ በቀር ማንም ማን ማድረግ የማይቻለውን ተአምራት በልደቱ የገለጠ፤ ሰብአ ሰገልን ከምሥራቅ ሀገር ወደ እርሱ ያመጣቸው እርሱ ነው፡፡ እጅ መንሻም አመጡለት፡፡ በሥልጣኑ ገናናነት እና በመለኮቱ ጌትነትም አመኑ፡፡

ዳግመኛም ከዚህ በኋላ የሰማይ ሠራዊት እንዲያመሰገኑት፣ ልዩ የምትሆን ልደቱንም ለዓለም ሁሉ እንዲሰብኩ ለእረኞች የገለጠላቸው እርሱ ነው፡፡ ከጠላት መገዛት እንደ ዳኑም አስረዳቸው፡፡ “በመለኮቱና በሥልጣኑ ገናናነት በመንበረ መንግሥቱ ላለ ለእግዚአብሔር በሰማይ ምስጋና ይሁን፤ በምድርም ሰላም ይሁን፡፡ የሚወደው ልጁ በዚያ ተገልጧልና ለሰውም በጎ ፈቃዱ ተደረገለት” ብለዋልና፡፡ ለሰው በጎ ፈቃዱ ተደረገልት ማለትም የሰውን ወገን ከኵነኔ ሥቃይ አዳናቸው፣ ከጨለማ ወደ ብርሃንም አወጣቸው ማለት ነው፡፡

ከተወለደ ከአርባ ቀን በኋላም ወደ ቤተ መቅደስ በገባ ጊዜ ተኣምርን አደረገ፡፡ የስምዖንንም ዐይኖች ገለጠ፡፡ በክንዱ በታቀፈውም ጊዜ ነቢያት ስለ እርሱ ትንቢት የተናገሩለትና ፍጥረት ሁሉ መምጣቱን ተስፋ የሚያደርጉት ክርስቶስ እርሱ እንደ ሆነ ዐወቀ፡፡ ስለዚህም መናገር ጀመረ፡፡ እንዲህ ብሎ አቤቱ ዐይኖቼ በሕዝብ ፊት ያዘጋጀኸውን ማዳንህን አይተዋልና ባርያህን በሰላም አሰናብተው፡፡

ዳግመኛም በእርሷ ሰውን ከኃጢአቱ ሁሉ ያነጻበትና በመንፈስ ቅዱስ አድሶ ሁለተኛ መንፈሳውያን ልጆች ይሁኑ ዘንድ ትእዛዙንም ቢጠብቁ የመንግሥቱ ወራሾች ያደረገበት የጥምቀቱ ጊዜ እስኪደርስ ድረስ ሰው ሊናገራቸው የማይችለውን ብዙ ድንቆችን የሠራ እርሱ ነው፡፡ ከተጠመቀ በኋላም በመለኮቱ ኃይል መንግሥተ ሰማያትን ያስተምርና ይሰብክ ጀመር፡፡

ስለዚህም ንስጥሮስ ትልቅ ስሕተትን ተሳሳተ፡፡ ፈጽሞ ከሓዲም ሆነ፡፡ ክርስቶስ እንደኛ ሰው ነው፤ መንፈስ ቅዱስም ምንም ምን አላደረበትም፤ የባሕርይ ገንዘቡ አይደለም፡፡ ከተጠመቀ በኋላ የመለኮት ኃይል ተሰጠው እንጂ ብሏልና፡፡ መልአኩ ለእመቤታችን ለማርያም ‹‹ጸጋን የተሞላሽ ሆይ እግዚአብሔር ከአንች ጋር ነውና ደስ ይበልሽ እነሆ ትጸንሻለሽ፤ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፤ ስሙም ኢየሱስ ይባላል፤ እርሱ ሕዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋልና›› ያላትን አላስተዋለም፡፡

እመቤታችን ማርያም ግን የመልአኩን ቃል ትረዳው ዘንድ ወደደች፡፡ ወንድ ስለማላውቅ ይህ እንዴት ይሆንልኛል በማለትም መለሰችለት፡፡ መልአኩም “መንፈስ ቅዱስ ወደ አንቺ ይመጣል፤ የልዑል ኃይልም ይጋርድሻል፤ ይህ የሚወለደውም ቅዱስ ነው፤ የልዑል እግዚአብሔር ልጅም ይባላል” አላት፡፡ ይህንን የመልአኩን ቃል ሰምቶ የማያምን ሐሰተኛ ከሓዲም ይባላል፡፡ በፍርድ ጊዜም ከከሓዲዎችና ከመናፍቃን ጋራ መከራን ይቀበላል፡፡

ይቀጥላል......

(ድርሳነ ሠለስቱ ሊቃውንት በመምህር ቃለጽድቅ ሕግነህ የተተረጎመ ገጽ 69-87)
👍5319🙏15
አርዮስፋጎስ

በመጋቤ ሐዲስ ኤርምያስ አዳነ የቤተክርስቲያን ታሪክ በኢትዮጵያ ትምህርት በአርዮስፋጎስ ቴሌግራም ቻናል በመሰጠት ላይ ነው። ይቀላቀሉ። የቤተክርስቲያንን ታሪክ ይወቁ።

አርዮስፋጎስ ማለት ፦ግሪካዊ ቃል ሲሆን ለሕዝብ ይፋ የሆነ የምርምር አደባባይ ማለት ነው።
➛ ቻናሉ በመንፈሳዊ ምርምር እንጅ በሥጋዊ ምርምር ልንረዳቸው የማንችል ጥልቅ የቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ  ትምህርቶች፣ ስብከቶች እና ጽሑፎች የሚለቀቁበት እንዲሁም ሌሎች ተከታታይ ትምህርቶችን የሚያስተምሩበት የቴሌግራም ቻናል ነው።

https://t.me/Ariosfagos1271

https://t.me/Ariosfagos1271
19👍7🕊1
#ጥር_10

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ጥር አስር በዚህች እለት #የገሃድ_ጾም ነው፣ የከበረ አባት #አባ_ታውብንጦስ_ዘሲሐት ዕረፍቱ ነው፡፡

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ጾመ_ገሃድ

ጥር አስር በዚህች ዕለት ምንም ምን መብልን ሰይቀምሱ ምእመናን ሁሉ እስከ ምሽት ይጾሙ ዘንድ ከእኛ አስቀድመው የነበሩ ታላላቅ ሊቃውንት የቤተ ክርስቲያን መምህራን ሥርዓትን ሠሩ በምሽትም ቢሆን በታላቁ ጾም ከሚበላው በቀር ጥሉላትን እንዳይቀምሱ። በዚች ዕለት ምእመናን እስከ ምሽት እንደመጾሙን ያዘዙበት ምክንያቱ ይህ ነው የልደትና የጥምቀት በዓል በዓል በረቡዕ ወይም በዓርብ ቀን ቢሆን በበዓለ ኃምሳ የሚበላውን የጥሉላት መብል በጥዋት በመብላት ምእመናን ሁሉ በዓሉን እንዲአከብሩ የከበሩ አባቶቻችን ሐዋርያት አዝዘዋል እሊህ ሁለቱ የእግዚአብሔር ታላላቅ በዓላቶቹ ናቸውና።

እኛ በዚህ በኅላፊው ዓለም ተድላ ደስታ ደስ የሚለን ለሌሎች እንዳይመስላቸው እንደ አይሁድና እንደ አረማውያን በዓል በመብልና በመጠጥ ብቻ እንዳናደርግ ስለዚህ ከልደትና ከጥምቀት በዓል በዋዜማ ያሉትን ሁለቱን ዕለታት እንድንጾም አዘዙን የልደትና የጥምቀት በዓል በረቡዕና በዓርብ ላይ በሚሆን ጊዜ በረቡዕና በዓርብ ፈንታ እንድንጾማቸው ይገባልና በዚህም ሁለት ሥራ ይፈጸምልናል የጾም ሥራና የበዓል ማክበር ሥራ ነው። እንዲሁም በግብፃውያን አብያተ ክርስቲያን የተሠራ ነው።

በይረሙን በእሑድ ወይም በአይሁድ ሰንበት ቀን ቢሆን ይህም ጌታ የተገለጸበት ጥር ዐሥራ ቀን ነው በዋዜማው ዐርብ እስከ ምሽት ይጹሙ አስቀድመን እንደተናገርን ጥሉላት አይብሉ የልደትና የጥምቀት በዓልም ሰኞ ቀን ቢሆን በሰንበት ቀን ይጾም ዘንድ አይቻልም ነገር ግን ጥሉላትን ከመብላት ይጠበቁ።

በጥምቀትም ዕለት ከእኵለ ሌሊት በፊት ተነሥተው በውኃው ላይ ይጸልዩና ይጠመቁ ሕፃናትም በሚጠመቁ ጊዜ በውኃ እንዳይገድፉ ካህናቱም ከመንጋቱ በፊት ቀድሰው ቊርባኑን ያሳርጉ እጅግም ማልደው በጥዋት ከቤተ ክርስቲያን ይውጡ በከበረ ሥርዓታቸው ጌቶቻችን ሐዋርያት እንዳዘዙ።

የመለካውያን ወገኖች ግን የልደትና የጥምቀት ዋዜማ በቅዳሜ ቀን ወይም በእሑድ ቀን ቢሆን በሦስት ሰዓት ይቀድሳሉ ከወደዱም የተባረከ ኅብስት ተመግበው ውኃ ይጠጣሉ ከዚህም በኋላ ካህናቱ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሁነው በየሰዓቱ በመጸለይ ለበዓሉ የሚገባውን የነቢያትን ትንቢቶች ያነባሉ በዚያች ቀን በምሽት ይኸውም ጥር ዐሥር ነው በውኃው ላይ ይጸልያሉ ይህም አባቶቻችን ሐዋርያት እንዳዘዙት አልሆነም። እርሳቸው የኤጲፋንያን በዓል እንዲአክብሩ አዘዋል ይኸውም መድኃኒታችን የተገለጠበት ካኑን በሚባል በሮም ሁለተኛ ወር በሰባት ይህም ጥር ዐሥራ አንድ ቀን ነው።

መለካውያን ግን የከበሩ አባቶች የቤተ ክርስቲያን መምህራን ያዘዙትን ይተላለፋሉ በልደትና በጥምቀት በዓል ዓርብም ረቡዕም ቢሆን አስቀድመው በርሱ ፈንታ ሳይጾሙ በጥዋት ተነሥተው ይበላሉና።

እኛንም ከበደላችን ያነጻን ዘንድ በዮርዳኖስም ወንዝ እንደ ተገለጸ የጌትነቱን ክብር በልቡናችን ይገልጥልን ዘንድ የክብር ባለቤት የሆነ ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን እንለምነው ጌትነት ክብር ስግደት ለእርሱ ይገባልና ከቸር አባቱ ጋር ይቅር ባይ ከሆነ መንፈስ ቅዱስም ጋር ዛሬም ዘወትርም ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ጥር)
32👍26🙏10🕊1
ከተራ ምንድን ነው?

ከተራ 'ከበበ' ካለው የግእዝ ግሥ የወጣ ነው፡፡ ፍችው ውኃ መከተር፣ መገደብ ማለት ነው፡፡

በጥምቀት ዋዜማ ታቦተ ሕጉ ከቤተ መቅደስ ወጥቶ ውኃ ባለበት አካባቢ ስለሚያድር የየአጥቢያው ሕዝብ እየተሰበሰቡ በወንዝ ዳር ወይም በምንጭ አካባቢ ድንኳን ይተከላሉ፡፡ ድንኳንም ከሌለ ዳስ ሲጥሉ ይውላሉ፡፡ የምንጮች ውኃ እንዲጠራቀም ይከተራሉ (ይገድባሉ) ጉድጓድ እየተቆፈረ ውኃው እንዳይሄድ በመገደብ ለመጠመቂያ (ለጥር 11) ዝግጁ የሚያደርጉበት ዕለት ነው፡፡

በተጨማሪ በአቅራቢያ የሚገኙት ቤተክርስቲያናት ተሰብስበው ከዚሁ ከተቆፈረው ገንዳ ወይም ከተገደበው ጅረት አጠገብ ባለው ዳስ ወይም ድንኳን ታቦቶቻቸውን ያሳድራሉ ሊቃውንቱም በዚያው እግዚአብሔርን በማህሌት ሲያመሰግኑ ያድራሉ።

በበዓለ ጥምቀት የታቦታቱ ወደ ወንዝ መውረድ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ በእደ ዮሐንስ ለመጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ የመሄዱ ምሳሌ ነው፡፡ ታቦቱ የጌታችን፣ ምሳሌ ሲሆኑ ካህናቱ የመጥምቁ ዮሐንስ ምሳሌ ናቸው፡፡ መዘምራኑና ሕዝቡ ደግሞ ዮሐንስ ያጠመቃቸው ሕዝቦች ምሳሌዎች ናቸው፡፡

መልካም የከተራ በዓል
👍8561🙏37🕊2
#በጥምቀት_ዙሪያ_የሚነሱ_ጥያቄዎች_እና_መልሶቻቸው
#ጌታችን_ለምን_ተጠመቀ?
1. ምሥጢርን ለመግለጥ፡-
ጌታችን በፈለገ ዮርዳኖስ ሲጠመቅ ምስጢረ ሥላሴ ግልፅ ሆኗል፡፡ አብ በደመና “የምወደው የምወልደው ልጄ ይህ ነው” በማለቱ አብ የወልድ አባት መሆኑ ታወቀ፡፡ መንፈስ ቅዱስም የባሕርይ ሕይወቱ መሆኑን ሲያስረዳ በአምሳለ ርግብ በራሱ ላይ ተቀመጠ ወልድም በተለየ አካሉ በዮርዳኖስ ሲጠመቅ ታየ፡፡ ስለዚህ ምሥጢርን ለመግለጥ ስንል የአንድነት የሦስትነት ምስጢር በጐላ ሁኔታ እንዲታወቅ ተጠመቀ ማለት ነው፡፡ /ማቴ. 3፥16/

2. ትንቢቱን ለመፈፀም፡-
በመዝሙር 46/47/፥16 ላይ “አቤቱ ውሆች አዩህ፣ ውሆችም አይተውህ ፈሩ ጥልቆች ተነዋወጡ ውሆችም ጮኹ፡፡” ተብሎ በቅዱስ ዳዊት የተነገረውን ትንቢት ለመፈፀም ተጠመቀ፡፡

3. አርአያ ሊሆነን፡-
ተጠምቆ እንድንጠመቅ አደረገን ሥርዓትን ሠራልን ቀድሞ በአርአያውና በአምሳሉ እንደፈጠረን አሁንም አርአያ ምሳሌ ሆነን፡፡ ለዚህም ነው ምሳሌን ከእኔ ተማሩ ያለን፡፡ /ማቴ 11፥29/ ለትምህርት ለአርአያ /ዮሐ. 13፥1-17/

4. የዕዳ ደብዳቤያችንን ለመደምሰስ፡-
አዳምና ሔዋን ፍዳው በፀናባቸው መከራው በበዛባቸው ጊዜ የሚያቃልልላቸው መስሏቸው ዲያብሎሰ ስመ
ግብርናችሁን ጽፋችሁ ስጡኝ ባላቸው ጊዜ አዳም ገብሩ ለዲያቢሎስ (አዳም የዲያብሎስ የወንድ አገልጋይ) ሔዋን ዓመቱ ለዲያብሎስ (ሔዋን የዲያብሎስ ሴት አገልጋይ) ብለው ጽፈው ሰጡት፡፡ ዲያብሎስም ይህንን ደብዳቤ አንዱን በሲኦል አንዱን በዮርዳኖስ አስቀመጠው፡፡ በዮርዳኖስ ያስቀመጠውን ጌታችን ሲጠመቅ እንደሰውነቱ ረግጦ ደምስሶታል፡፡ ይህንን ጽሕፈት ለመደምሰስ ነው ጌታችን በዮርዳኖስ የተጠመቀው፡፡ ለዚህም ነው ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ “በእኛ ላይ የነበረውን የሚቃወመንንም በትእዛዛት የተፃፈውን የዕዳ ጽሕፈት ደመሰሰው፡፡” ያለው ቆላ 2፥14

#ጌታችን_መች_ተጠመቀ?

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተጠመቀው በ5531 ዓመተ ዓለም ዘመነ ሉቃስ ማክሰኞ ጥር 11 ቀን ከሌሊቱ በ10ኛው ሰዓት ነበር፡፡ ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 19 በተጠመቀም ጊዜ ዕድሜው 30 ዓመት ከ13 ቀን ነበር፡፡ /ሉቃ. 3፥23/

#ጌታችን_ስለምን_በ30_ዓመት_ተጠመቀ?
በብሉይ ኪዳን ሥርዓትና ልማድ ካህናት ለቤተ እግዚአብሔር ተልእኮ እና መንፈሳውያን አገልግሎቶች ከ30 ዓመት ዕድሜ በፊት አደባባይ አይወጡም ነበር፡፡ እጅግ አስፈላጊ እንኳ ቢሆን ከ20 እና 25 ዓመት አስቀድሞ ለአገልግሎት መሰየም ልማድ አልነበረም፡፡ የቤተ እግዚአብሔር አገልጋዮች በዕድሜና በዕውቀት የበሰሉ፣ በጠባይና በሥራ ልምድ የተፈተኑ ተልዕኳቸውን በብቃት ለመወጣት በተገልጋዩ ሕዝብ ዘንድ የተመሰከረላቸው መሆን ነበረባቸው፡፡ /ዘፀ. 4፥3፤1ዜና መዋ. 23፥24፤ 1ጢሞ. 3፥6-10/ ያንን ሥርዓት ለመፈጸም ጌታችን የተጠመቀውና ለትምህርተ ወንጌል የተገለጠው በ30 ዓመቱ ነበር፡፡

ዮሐንስ መጥምቅም የጌታን መምጣት ለማወጅ በዮርዳኖስ ይሁዳ ምድረ በዳዎች ወጥቶ የታየው ከ30 ዓመት ዕድሜው በኋላ ነው፡፡ ሌላው ዐቢይ ምክንያት የሰው ሁሉ መጀመሪያ አዳም የ30 ዓመት ጎልማሳ ሆኖ ተፈጥሮ በ40ኛ ቀን ተሰጥቶት ኋላም በኃጢአት ምክንያት ያስወሰደውን ልጅነት ለማስመለስ ነው፡፡

ክርስቶስ የተጠመቀው ክብር ሽቶ ሳይሆን የአብ የባሕርይ ልጅነቱን (የባሕርይ አምላክነቱን) ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ለማስመስከር፣ ውኃውን ለመቀደስ፣ የአዳምን ልጆች የእዳ ደብዳቤ ለመደምሰስና በስህተት የጠፋውን የልጅነት ክብር ለመመለስ ነው፡፡ ጌታ ተጠምቆ ከውኃው ከወጣ በኋላ መንፈስ ቅዱስ በርግብ አምሳል ወርዶ በራሱ ላይ በማረፍ አብ በደመና ‹‹ይህ ልጄ ነው›› ብሎ ሲመሰክርለት ምሥጢረ ሥላሴ አንድነትና ሦስትነት በጉልህ ተረጋግጧል፡፡ /ማቴ. 3፥16/

#ጌታችን_በዮሐንስ_እጅ_ለምን_ተጠመቀ?

ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ የባሕርይ አምላክ ሲሆን በአገልጋዩ በቅዱስ ዮሐንስ እጅ ይጠመቅ ዘንድ በፍጹም ትሕትና ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ መጣ ይህንንም ያደረገልን አብነት ሊሆነን ነው፡፡ ምክንያቱም ጌታችን ቅዱስ ዮሐንስን ‹‹መጥተህ አጥምቀኝ ›› ብሎት ቢሆን ኖሮ ነገ ነገሥታቱና መኳንንቱ ካህናቱን መጥታችሁ አጥምቁን ባሉ ነበር ስለዚህ እንዲህ እንዳይሆን ነው፡፡ ጌታችን ‹‹ጌታ ስሆን በባርያዬ እጅ እንደተጠመቅሁ እናንተም ወደ ቤተክርስቲያን ሄዳችሁ በካህናት እጅ ተጠመቁ›› ሲል ነው፡፡

ጌታችን በዮርዳኖስ የተጠመቀው ልጅነትን የምታሰጥ ጥምቀትን ባርኮ ቀድሶ ሊሰጠን እንጂ ክብር እንዲሆነው አይደለም፡፡ ምክንያቱም፡- እርሱ እከብር አይል ክቡር እጸድቅ አይል ጻድቅ ነውና፡፡

#ቅዱስ_ዮሐንስ_ጌታችንን_በማን_ስም_አጠመቀው?

ጌታችን ዮሐንስን አጥምቀኝ ባለው ጊዜ "ሌላውን በአንተ ስም አጠምቃለሁ አንተን በማን ስም ላጥምቅህ? በአብ ስም እንዳላጠምቅህ አብ አባትህ ባንተ ሕልው ነው በወልድ ስም እንዳላጠምቅህ ወልድ አንተ ነህ በመንፈስ ቅዱስ ስም እንዳላጠምቅህ መንፈስ ቅዱስ ሕይወትህ ባንተ ሕልው ነው ታዲያ በማን ስም ላጥምቅህ?" ብሎ ቢጠይቀው ጌታም ‹‹እንደ መልከጼዴቅ ሥርዓት አንተ የዓለም ካህን ብርሃንን የምትገልጥ የአብ የባሕርይ ልጅ ሆይ ይቅር በለኝ›› ብለህ አጥምቀኝ አለው፡፡

#ዮሐንስ_ጌታን_ሲያጠምቀው_እጁን_ለምን_አልጫነበትም?
- ዮሐንስ በጥምቀት አከበረው /ልዕልና ሰጠው/ እንዳይባል፡፡
- መለኮትን በእጅ መንካት ስለማይቻል

#ጌታችን_ጥምቀቱን_ለምን_በዮርዳኖስ_አደረገው?
በኢየሩሳሌም አካባቢ ብዙ ወንዞች ኩሬዎችና ሐይቆች መኖራቸው የታወቀ ነው፡፡ ጌታ ጥምቀቱን በዮርዳኖስ ያደረገው ስለዚሁ አስቀድሞ የተነገረውን ትንቢት መፈጸሙን ለማረጋገጥ ነው፡፡ ‹‹ባሕር አይታ ሸሸች ዮርዳኖስም ወደ ኋላው ተመለሰ›› /መዝ.113፥3/ ከዚህም ጋር ከላይ ምንጩ አንድ የሆነው ዮርዳኖስ ዝቅ ብሎ በደሴት ተከፍሎ እንደገና እንደሚገናኝ በግዝረት በቁልፈት (በመገዘርና ባለመገዘር) ተለያይተው የነበሩ ሕዝብና አሕዛብ መላው የአዳም ልጆች በጌታችን ጥምቀት አንድ መሆናቸውን የሚገልጽ ትርጉም አለው፡፡ እስራኤል ዮርዳኖስን ተሻግረው ምደረ ርስት ገብተዋል፡፡ ያመኑ የተጠመቁ ምዕመናንም በጥምቀት ገነት መንግሥተ ሰማያትን ይወርሳሉ፡፡ ሌላው በዮርዳኖስ ተጥሎ የነበረውን የዕዳ ደብዳቤ ይደመስስልን ዘንድ /ቈላ. 2፥14/

#ጌታችን_ለምን_በውሃ_ተጠመቀ?
እግዚአብሔር አምላክ በዘመነ ኦሪት ሰብዐ ትካትን በንፍር ውሃ ፈርኦንና ሰራዊቱን በኤርትራ ባሕር ካጠፋ በኋላ ሰዎች ውሃ ለመዓት እንጂ ለምሕረት አልተፈጠረም ይሉ ነበርና ለምሕረት እንደተፈጠረ ለማጠየቅ በውሃ ተጠመቀ ( ዘፍ 7÷17፤ ዘጸ 14÷1-29)

አንድም ውሃ እሳትን ያጠፋል እናንተም በውሃ ብትጠመቁ ከገሃነመ እሳት ትድናላችሁ ሲል ነው፡፡

አንድም ውሃ መልክን ያሳያል እናንተም በውሃ ብትጠመቁ መልክዓ ሥላሴን የአምላክን ቸርነት ርህራሔ ታያላችሁ ሲል ነው፡፡

አንድም በማር በወተት ቢጠመቅ ኖሮ እነዚህ ለባለጸጎች እንጂ ለድሆች አይገኝም ውሃ ግን በሁሉ ይገኛል፡፡ ስለሆነም ጥምቀት የታዘዘ ለሁሉ ነው ሲል ነው፡፡

አንድም ማርና ወተት ቢታጠብበት ያቆሽሻል እንጂ አያነጣም ውሃ ግን እድፍን ያስለቅቃል እናንተም በማየ ገቦ ብትጠመቁ ከኃጢአት ትጠራላችሁ ሲል ነው፡፡

አንድም ማርና ወተት ተክል ላይ ቢያፈሱት ያደርቃሉ እንጂ አያለመልሙም ውሃ ግን ያለመልማል እናንተም በውሃ ብትጠመቁ ልምላሜ ሥጋ ወነፍስ ታገኛላችሁ ሲል ነው፡፡ (ዮሐ 19÷35)
👍4036🙏6🕊1💯1
#ጌታችን_ለምን_በሌሊት_ተጠመቀ?
በኃጢአት ጨለማ ስለነበረ ሕዝብ የጽድቅ ብርሃን እንዲወጣለትና በጨለማ የሚመስል ኦሪት ይኖር ስለነበረ ለሕዝብ ብርሃን የሆነ ወንጌል መገለጡን ለማሳየት ነው፡፡ ኢሳ.9፥2

አንድም ጌታ ልደቱ፣ ጥምቀቱ፣ ትንሣኤው እንዲሁም ምጽአቱ በሌሊት ነው፡፡ ይኽም የሆነበት ምክንያት፡- ሌሊቱን ተከትሎ የሚመጣው ብርሃን በመሆኑ ከሞት ወደ ሕይወት ከጨለማ ወደ ብርሃን ከሲኦል ወደ ገነት የመሸጋገራችን ምሳሌ ነው፡፡

አንድም መንፈስ ቅዱስ በርግብ አምሳል የሚወርድ ነውና በጌታ ላይ የወረደው ርግብ እንጂ መንፈስ ቅዱስ አይደለም ባሉ ነበር፡፡ በሌሊት ርግብ የለም ስለዚህ መንፈስ ቅዱስ እንደሆነ ይታወቅ ዘንድ፡፡

#መንፈስ_ቅዱስ_ለምን_ጌታ_ከውኃ_ከወጣ_በኋላ_ወረደ?
ሀ. ዮሐንስን ያከብሩት ነበርና መንፈስ ቅዱስ የወረደው ለዮሐንስ እንጂ ለጌታ አይደለም ይሉ ነበርና ምክንያቱን ጌታ ውኃ ውስጥ እያለ ከዮሐንስ አልተለየም ነበርና፡፡
ለ. ውኃን የሚባርክ መልአክ እንዳለ ያውቁ ነበርና ውኃውን ለመባረክ አንጂ ለጌታ አይደለም እንዳይባል፡፡
ሐ. ማረፊያ ያጣች ርግብ በባሕር ስትበር አረፈችበት ይሉ ነበርና ሐሳባቸውን በሙሉ ያጠፋ ዘንድ ከውኃ ውስጥ ከወጣ በኋላ መንፈስ ቅዱስ በርግብ አምሳል ወረደ፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
133👍30🙏14💯5🕊2

የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ድርሳን ስለ ቃና ዘገሊላ

የተወደዳችሁ ወንድሞች ሆይ ጌታ በቅዱስ ወንጌል ያለውን ስሙ። በሦስተኛው ቀን በቃና ዘገሊላ ሰርግ ተደረገ፡፡
የኢየሱስም እናት በዚያ ነበረች፤ ኢየሱስንና ደቀመዛሙርቱንም ወደ ሰርጉ ጠሯቸው፤ ሲበሉ ሲጠጡም ወይኑ አለቀ፡፡

የመብልና የመጠጥ ፍቅር እንዲሁም ዘፈን ጭፈራ ወዳለበት የሰርግ ቤት ጌታ ኢየሱስ ስለምን ገባ? የሚል ሰው ቢኖር እንዲህ ብለን እንመልስለታለን፡፡ ስለ መባልዕት ፍቅር ወደ እነሱ የሄደ አይደለም፡፡ እርሱ በትንሽ እንጀራ ብዙ ሕዝብ ያጠገበ ነውና፡፡ ነገር ግን እርሱ እንደ ሰው ተገለጠ፡፡ ከእነርሱ ጋራም ተመላለሰ፡፡ እንደ እነርሱም ሆነ። ከውድቀታቸው አንሥቶ እርሱን ወደማመን ይመልሳቸው ዘንድ ይህን አደረገ፡፡

ከዚያም በኋላ ፈሪሳውያን ደቀ መዛሙርቱን መምህራች ሁ ስለምን ከቀራጮችና ከኃጢአተኞች ጋር ይበላል? ያ ሏቸውን አልሰማችሁምን? ጌታ ኢየሱስም ይህንን ሰምቶ ፈሪሳውያንን በሽተኞች እንጂ ጤነኞች ባለመድኃኒቱን አይሹትም አላቸው፡፡ ዳግመኛም ኃጥአንን በንስሓ ልጠራ እንጂ ጻድቃንን ልጠራ አልመጣሁም አላቸው፡፡

ድንግል ማርያምም ወይኑ እንዳለቀ ባወቀች ጊዜ በመለኮቱ ጌታዬ በሰውነቱ ልጄ ብላ የምትጠራው ክርስቶስን ወይን እኮ የላቸውም አለችው፡፡ የሰርግም የደስታው ፍጻሜ የወይን መጠጥ ነውና፡፡ እመቤታችን እርሱ ሁሉን ማድረግ እንደሚችል የሚሳነውም እንደሌለ ታውቃለችና፡፡

ጌታ ኢየሱስም መልሶ “አንቺ ሆይ ከአንቺ ጋር ምን አለኝ ጊዜዬ ገና አልደረሰም እና” አላት፡፡ እንዲህ ማለቱም እኔ ተአምራትን የማደርገው በትምክሕት አይደለም፡፡ ነገር ግን እንዲደረግላቸው ከእኔ ሳይለምኑ ምንም ምን አላደርግላቸውም ሲላት ነው፡፡

እመቤታችንም ይህን ነገር በተረዳች ጊዜ የሚላላኩትን እናንተ ብትለምኑት ፈቃዳችሁን ይፈጽምላችኋል አለቻቸው፡፡ እነሱም እንዳለቻቸው አደረጉ፡፡ በዚያም አይሁድ የማንፃትን በዓል የሚያደርጉባቸው ስድስት የድንጊያ ጋኖች ነበሩ፡፡ ሁለት ሁለት ሦስት ሦስትም እንስራ የሚይዙ ነበሩ፡፡ ጌታ ኢየሱስም “እነዚያን ጋኖች እስከ አፋቸው ውኃን ሙሏቸው” አላቸው፡፡ አፋቸውም ሞሏቸው፡፡ እስከ ከዚህም በኋላ በመለኮቱ ሥልጣን ባረካቸው፡፡ ከዚያም አሁን ቀድታችሁ ለአሳዳሪው ስጡት አላቸው፤ ሰጡትም፡፡ አሳዳሪውም ያንን ወይን የሆነውን ውኃ ቀምሶ አደነቀ፤ ከወዴት እንደ አመጡት አያውቅም ነበርና፡፡ የቀዱት አሳላፊዎቹ ግን ወይን የሆነው ይህ ውኃ ከወዴት እንደ አመጡት ያውቁ ነበር፡፡

አሳዳሪውም ሙሽራውን ጠርቶ “ሰው ሁሉ አስቀድሞ መልካሙን ወይን ያጠጣል፤ ከሰከሩም በኋላ ተርታውን ወይን ያጠጣል፤ አንተ ግን መልካሙን ወይን እስከ አሁን ከወዴት አዘገየኸው አለው፡፡ ' ውኃውን ወይን እንዳደረገው ባወቀ ጊዜ ግን ታላቅ ድንጋፄን ደነገጠ፡፡ ሥራውንም ትቶ ከእርሱ የሕይወት ውኃ የሚፈሰውን ምንጭ ይፈልግ ዘንድ ተመለሰ፡፡

ይህ የሰርግ ቤት ደስታው ምነኛ ታላቅ ነው! ተአምራቱስ ምነኛ ይበዛ! በዚያ ያሉ ሁሉም በክርስቶስ አምነዋልና፡፡ ሁሉም በእዚያ ወይን ከደዌያቸው ተፈውሰዋልና፡፡ ከእዚያ ወይን የጠጣ ሁሉ መንፈሳዊ ፍቅር በውስጡ ይነድ ነበር። በክርስቶስ ማመንም በልቡናው ይጸና ነበር። በምድር ያለው ደስታቸውም ወደ ሰማያዊ ደስታ ተለወጠ፡፡

በመብልና በመጠጥ ፈንታም ነቢዩ ዳዊት ‹‹የእግዚአብሔር ፍርድ እውነት ነው፤ ልብንም ደስ ያሰኛል፤ ከከበረ ዕንቍና ከወርቅ ይልቅ ይወደዳል፤ ከመዓርና ከሥኳር ይልቅ ይጣፍጣል›› በማለት እንደተናገረ ከመብልና ከመጠጥ ሁሉ የበለጠ የሚጣፍጡ ጣዕም ያላቸው ቃላትንና በጎ ትምህርትን መስማት ጀመሩ፡፡

ይቀጥላል......

(ድርሳነ ሠለስቱ ሊቃውንት በመምህር ቃለጽድቅ ሕግነህ የተተረጎመ ገጽ 69-87)
👍3830🙏7


የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ድርሳን ስለ ቃና ዘገሊላ


በዘፈንና በጨዋታ ፈንታም አዲስ ምስጋናን ማመስገን ያማረ መዝሙርንም መዘመር ጀመሩ። ለመብል በመሳሳት ፈንታም ሕሊናቸው የእግዚአብሔርን ሕግ ወደ መጠበቅ ተመለሰ፡፡ ይህን ዓለምንም ንቀው መንግሥተ ሰማያትን ፈለጉ፡፡ ወዳጆቼ ሆይ በእውነት በእዚያ የሰርግ ቤት የተደረገው ታላቅ ደስታ ፍጹምና ያማያልቅ መሆኑ የተረዳ የታወቀ ሆነ፡፡

ስለዚህ እኛም በሰርጉ ከተጠሩትና በእርሱ ካመኑት ጋር አንድ እንሆን ዘንድ በቀናች ሃይማኖት መጽናት ይገባናል፡፡ እውነተኛውን ወይን ለመጠጣት የበቃን ያደርገን ዘንድም ዐይነ ሕሊናችንን ወደ እርሱ አቅንተን እንለምነው፡፡ ይህችውም ለሰማያዊው ሰርግ ቤት የምትሰጥ አዳኝ የሆነች ደሙ ናት፡፡ ከእውነተኛው ሙሽራ ጋራም የቅድስናና የንጽሕናን ልብስ በመልበስ እንደሰት፡፡ ከዚች ደስታ እንዳንወጣ በእኛ ላይ ምንም ምን ምክንያተ ኃጢአት እንዳይገኝብን እንሁን፡፡

ጌታችን በቅዱስ ወንጌል እንዲህ ብሎ እንደ ተናገረ “መንግሥተ ሰማያት ለልጁ ሰርግን ያደረገ ንጉሥን ትመስላለች፤ የታደሙትንም ወደ ሰርጉ ይጠሩ ዘንድ ባሮቹን ላከ፡፡ ባሮቹም ያገኙትን ሁሉ ክፉዎችንም በጎዎችንም ሰበሰቡ የሰርጉንም ቤት ተቀማጮች ሞሉት፡፡

ንጉሡም የተቀመጡትን ለማየት በገባ ጊዜ በዚያ የሰርግ ልብስ ያለበሰ አንድ ሰው ዐየና ወዳጄ ሆይ የሰርግ ልብስ ሳትለብስ እንዴት ወደዚህ ገባህ? አለው፡፡ እርሱም ዝም አለ”፡፡ ኃጥአን በዚያች ዕለት የሚያመካኙት ምክንያት አያገኙምና። ልዑል እግዚአብሔርም በእውነተኛ ፍርድ ይፈርድባቸዋልና፡፡

በዚያን ጊዜም ንጉሡ አገልጋዮቹን እጁንና እግሩን አስረው በውጭ ወዳለው ጨለማ ያወጡት ዘንድና ለቅሶና ጥርስ ማፋጨት ወዳለበት ይጥሉት ዘንድ አዘዘ፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም መዳናችንን ወዶ ነቢያትንና ሐዋርያትን ላከ፡፡

ከዚህም ሁሉ የሚበልጥ ራሱ ከሰማያት ወርዶ ስለ እኛ ሰው ሆነ፡፡ ትእዛዛቱን ሁሉ ለምንጠብቅና ወደ እርሱ ለምንመለስ የንስሓን በርም ከፈተልን፡፡ ለክብር ሁሉም የተገባን አደረገን፡፡ ችላ ያለውና ለበጎ ነገር ያልተጋው ግን ከክብሩ ልብስ የተራቆተ ይሆናልና፡፡ እግሩንና እጁንም አሥረው ወደ ውጭ ወዳለው ጨለማ ይጥሉታል፡፡

ስለዚህም የነፍሳችንን መድኃኒት ልንፈልግ በቅዱሳት መጻሕፍት ያሉትን ቃላትም ልንረዳ ትርጓሜያቸውንም በንጹሕ ሕሊና ሁነን በቀናች ሃይማኖት ልንጠይቅ ይገባል፡፡ የመጻሕፍትን ቃልም ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ አፍ እንደሚሰማ ሰው እንሁን፡፡ በሰማንም ጊዜ ዘሩን በጭንጫ ላይ እንደሚዘራ፣ ፈጥኖ በቅሎ እንደሚደርቅም፣ በሾህ ላይ ዘርቶ በላዩም ፍሬ እንደማይገኝበት አንሁን፡፡

ይቀጥላል......

(ድርሳነ ሠለስቱ ሊቃውንት በመምህር ቃለጽድቅ ሕግነህ የተተረጎመ ገጽ 69-87)
48👍16🙏11💯2
የመጨረሻ

የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ድርሳን ስለ ቃና ዘገሊላ

በዘፈንና በጨዋታ ፈንታም አዲስ ምስጋናን ማመስገን ያማረ መዝሙርንም መዘመር ጀመሩ። ለመብል በመሳሳት ፈንታም ሕሊናቸው የእግዚአብሔርን ሕግ ወደ መጠበቅ ተመለሰ፡፡ ይህን ዓለምንም ንቀው መንግሥተ ሰማያትን ፈለጉ፡፡ ወዳጆቼ ሆይ በእውነት በእዚያ የሰርግ ቤት የተደረገው ታላቅ ደስታ ፍጹምና ያማያልቅ መሆኑ የተረዳ የታወቀ ሆነ፡፡

ስለዚህ እኛም በሰርጉ ከተጠሩትና በእርሱ ካመኑት ጋር አንድ እንሆን ዘንድ በቀናች ሃይማኖት መጽናት ይገባናል፡፡ እውነተኛውን ወይን ለመጠጣት የበቃን ያደርገን ዘንድም ዐይነ ሕሊናችንን ወደ እርሱ አቅንተን እንለምነው፡፡ ይህችውም ለሰማያዊው _ ሰርግ ቤት የምትሰጥ አዳኝ የሆነች ደሙ ናት፡፡ ከእውነተኛውለ መሽራ ጋራም የቅድስናና የንጽሕናን ልብስ በመልበስ እንደሰት፡፡ ከዚች ደስታ እንዳንወጣ በእኛ ላይ ምንም ምን ምክንያተ ኃጢአት እንዳይገኝብን እንሁን፡፡

ጌታችን በቅዱስ ወንጌል እንዲህ ብሎ እንደ ተናገረ “መንግሥተ ሰማያት ለልጁ ሰርግን ያደረገ ንጉሥን ትመስላለች፤ የታደሙትንም ወደ ሰርጉ ይጠሩ ዘንድ ባሮቹን ላከ፡፡ ባሮቹም ያገኙትን ሁሉ ክፉዎችንም በጎዎችንም ሰበሰቡ የሰርጉንም ቤት ተቀማጮች ሞሉት፡፡

ንጉሡም የተቀመጡትን ለማየት በገባ ጊዜ በዚያ የሰርግ ልብስ ያለበሰ አንድ ሰው ዐየና ወዳጄ ሆይ የሰርግ ልብስ ሳትለብስ እንዴት ወደዚህ ገባህ? አለው፡፡ ፡፡ እርሱም ዝም አለ”፡፡ ኃጥአን በዚያች ዕለት የሚያመካኙት ምክንያት አያገኙምና። ልዑል እግዚአብሔርም በእውነተኛ ፍርድ ይፈርድባቸዋልና፡፡

በዚያን ጊዜም ንጉሡ አገልጋዮቹን እጁንና እግሩን አስረው በውጭ ወዳለው ጨለማ ያወጡት ዘንድና ለቅሶና ጥርስ ማፋጨት ወዳለበት ይጥሉት ዘንድ አዘዘ፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም መዳናችንን ወዶ ነቢያትንና ሐዋርያትን ላከ፡፡

ከዚህም ሁሉ የሚበልጥ ራሱ ከሰማያት ወርዶ ስለ እኛ ሰው ሆነ፡፡ ትእዛዛቱን ሁሉ ለምንጠብቅና ወደ እርሱ ለምንመለስ የንስሓን በርም ከፈተልን፡፡ ለክብር ሁሉም የተገባን አደረገን፡፡ ችላ ያለውና ለበጎ ነገር ያልተጋው ግን ከክብሩ ልብስ የተራቆተ ይሆናልና፡፡ እግሩንና እጁንም አሥረው ወደ ውጭ ወዳለው ጨለማ ይጥሉታል፡፡

ስለዚህም የነፍሳችንን መድኃኒት ልንፈልግ በቅዱሳት መጻሕፍት ያሉትን ቃላትም ልንረዳ ትርጓሜያቸውንም በንጹሕ ሕሊና ሁነን በቀናች ሃይማኖት ልንጠይቅ ይገባል፡፡ የመጻሕፍትን ቃልም ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ አፍ እንደሚሰማ ሰው እንሁን፡፡ በሰማንም ጊዜ ዘሩን በጭንጫ ላይ እንደሚዘራ፣ ፈጥኖ በቅሎ እንደሚደርቅም፣ በሾህ ላይ ዘርቶ በላዩም ፍሬ እንደማይገኝበት አንሁን፡፡

የተወደዳችሁ ወንድሞች ሆይ የሥልጣን ዘመናቸው ትንሽ ወደ ሆነ ወደ ምድር ነገሥታት ተመልከቱ፡፡ ባሮቻቸውን ባዘዟቸው ጊዜ ትእዛዛቸውን ለመፈጸምና ንጉሦቻቸውን ለማስደሰት በፍጥነት የሚሮጡና የሚቀዳደሙ አይደለምን? በዚህም ምክንያት የገዦቻቸው ፍቅር በእነርሱ ላይ ይጨምራል፡፡

እንዲህም ከሆነ ያማረ ፍሬ እናፈራ ዘንድና ቃሌን ሰምታችኋል፤ ትእዛዜንም ጠብቃችኋል ለመንግሥቴም የተገባችሁ ስለ ሆናችሁ እናንተ የአባቴ ቡሩካን ዓለም ሳይፈጠር የተዘጋጀላችሁን መንግሥቴን ትወርሱ ዘንድ ወደ እኔ ኑ ያለውን ቃል ያሰማን ዘንድ የጌቶችን ጌታና የነገሥታትንም ንጉሥ አብዝተን ቃሉን ልንሰማና ትእዛዙን ልንጠብቅ ይገባል፡፡

ወዳጆቼ ሆይ ክፉና በጎ የሚደረግባት የዚች ዓለም ተድላ ደስታዋ አያስታችሁ፡፡ በውስጧ የሚደረገው ክፉውም ሆነ በጎው ዘመኑ ትንሽ ነውና ፈጥኖ ይጠፋል፡፡ መልካሙስ ለደስታው ፍጻሜ የሌለበት በኋለኛው ዓለም የሚደረገው ደስታ ነው:: በዚህ ዓለም ለትንሽ ዘመን ሕማምን፣ ችግርንና ኀዘንን የታገሡ ንዑዳን ክቡራን ናቸው፡፡ ፍጻሜ የሌለውን ታላቅ ደስታ በመንግሥተ ሰማያት ያገኛሉና፡፡

በዚህ ዓለም ለትንሽ ጊዜ ሕማምን፣ ችግርንና ኀዘንን ያልታገሠና ወደ መብል ወደ መጠጥ ወደምታልፍ ደስታም የተመለሰ ሰው ወዮለት፡፡ በዳግም ምጽአት ኀዘን የተሞላበት እናንተ ርጕማን ከኔ ወግዱ ለሰይጣንና ለመልክተኞቹ ወደ ተዘጋጀ ወደ ዘለዓለም እሳት ሂዱ የሚል ቃልን ይሰማልና፡፡

ስለዚህ ወንድሞቼ ሕሊናችንን ልናነቃ ነፍሳችንንም ልናበራ ይገባናል፡፡ በጾም በፍቅርና በምጽዋትም ልንኖር ይገባናል፡፡ ለመንግሥቱም የበቃን ያደርገን ዘንድ የእግዚአብሔርን ቸርነቱን ልንፈልግ ይገባናል፡፡ ዐይነ ልቡናችንንም አንሥተን ቅድስት ንጽሕት በምትሆን በእመቤታችን በድንግል ማርያም ልመና እና በቅዱሳንና በሰማዕታት ሁሉ ምልጃ እንለምን፡፡

ክብርና ምስጋና ለእርሱ ዛሬም እስከ ዘለዓለምም ይገባልና ለዘለዓለሙ አሜን፡፡

(ድርሳነ ሠለስቱ ሊቃውንት በመምህር ቃለጽድቅ ሕግነህ የተተረጎመ ገጽ 69-87)
59👍25🙏13🤩1👌1
አንኳኩቼ አላገኘሁም” አትበል፡፡ ብቻ የለመንከው፣ ደጅ የጠናኸው አንተ የምትወደው ሳይሆን እግዚአብሔር የሚወድልህ ይሁን፡፡ ወደ እግዚአብሔር የተዘረጋ እጅ ፈጽሞ ባዶውን አይመለስም፡፡ ስለዚህ ራስህን፣ ልመናህን ምን ዓይነት እንደሆነ ፈትሽ እንጂ አንኳኩቼ አላገኘሁም አትበል፡፡ እንኳንስ ንጹሐ ባሕርይ የሆነው እግዚአብሔር ክፋት የሚስማማው ምድራዊ አባትም ለልጁ ጀሮውን አይደፍንም፡፡

አስቀድሞ ሕያዊት ነፍስን “እፍ” ብሎ እንዲሁ የሰጠን ጌታ፣ ኋላም ተቀዳሚ ተከታይ የሌለው አንድ ልጁን ሳይራራ ከሰጠን እንደምን በዚህ ይታማል? እንደምንስ አይሰጠንም እንላለን? /ሮሜ.8፥32/፡፡ ልጁን የሰጠው እኮ ጭራሽ “ስጠን” ብለው ላልለመኑ አሕዛብም ጭምር ነው፡፡ ታድያ እንዲህ የምንለምን እኛማ እንዴት አብልጦ አይሰጠንም? የሚበልጠውን ሰጥቶን ሳለስ እንደምን ትንሹን አይሰጠንም እንላለን? ስለዚህ ከእኛ የሚጠበቀውን ሳናደርግ “እግዚአብሔር ጸሎቴን አይሰማም” የሚል የሰነፎች አባባል የምንናገር አንሁን፡፡ ጀሮን የፈጠረ ይሰማል!”

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

(ሰማዕትነት አያምልጣችሁ በገብረ እግዚአብሔር ኪደ የተተረጎመ ገጽ 178)
203🙏49👍35
"ሌቦች ወርቅና ብር ያለውን እንጂ ድርቆሽና ገለባ እንዲሁም ሰንበሌጥ ያለውን ቤት አይበረብሩም፡፡ ዲያብሎስም የሚያጠቃው (የሚፈትነው) መንፈሳዊ ምግባራትን የሚያበዙትን ሰዎች ነው፡፡"

(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)
255🙏33👍22😍4