እግዚአብሔርን የሚያምንና የሚወድ ቢኖር፥ እርሱ በዚህ አንፀባራቂና የደስታ በዓል ደስ ይበለው፡፡ ብልህ አገልጋይ ቢኖር፥ እርሱ ወደ ጌታው ሐሴት ገብቶ ዕልል ይበል፡፡
በጾም የደከመ ቢኖር፥ አሁን ደመወዙን ይቀበል፡፡ በመጀመሪያው ሰዓት ወደ አምላኩ የቀረበ ቢኖር፥ ዛሬ ሽልማቱን ይውሰድ፡፡
በሦስተኛው ሰዓት የመጣ ቢኖር፥ እርሱ በዓሉን በምስጋና ያክብር፡፡ በስድስተኛው ሰዓት የደረሰ ቢኖር፥ አይጎድልበትምና አይጠራጠር፡፡ እስከ ዘጠነኛ ሰዓት የዘገየ ቢኖር፥ ሳይጠራጠር ይቅረብ፡፡ እስከ ዐሥራ አንደኛዋ ሰዓት የዘገየ ቢኖር፥ ስለ መዘግየቱ አይደንግጥ፡፡ ጌታ ቸር ነውና፤ በመጨረሻ የመጣውንም እንደ መጀመሪያው አድርጐ ይቀበሏልና፡፡ በዐሥራ አንደኛው ሰዓት ለመጣው ከመጀመሪያው ሰዓት አንሥቶ ሲደክም ከነበረው ጋራ እኩል ይሰጧልና፡፡
መጨረሻ ለመጣው ጌታ ምሕረቱን ይለግሰዋል፤ መጀመሪያ ለመጣውም ያስብለታል፡፡ ለአንደኛው ይሰጠዋል፤ ለሌላኛውም ጸጋውን ያድለዋል፡፡ ለአንደኛው መልካም ምግባሩን ይቀበልለታል፡፡ ለሌላኛውም መልካም ፍቃዱን ይቀበልለታል፡፡ ለአንዱ ምግባሩን ያከብርለታል፤ ለሌላኛውም በቅን ልቡና የሚያደርገውን ጥረት ያደንቅለታል፡፡ ስለዚህ ኹላችሁም ወደ ጌታችሁ ደስታ ግቡ፡፡
ፊተኞች ኋለኞችም ሆይ! እኩል ደመወዛችሁን ተቀበሉ፡፡ ባለጸጐች ድኾችም ሆይ! በአንድነት ዘምሩ፡፡ እናንተ ብርቱዎች ደካሞችም ሆይ! በዓሉን አክብሩት፡፡ እናንተ የጾማችሁ መጾም ያልቻላችሁም ሆይ! ዛሬ ላይ ደስ ይበላችሁ፡፡
መሠዊያው ሙሉ ነውና ኹሉም በማዕዱ ደስ ይበለው፡፡ ፍሪዳው የሰባ ነውና አንድ ሰው ስንኳ እንደ ተራበ እንዳይሔድ፡፡ ኹላችንም የእምነት በዓሉን እንካፈል፤ ከቸርነቱና ከፍቅሩ ሀብትም እንቋደስ፡፡
ማንም ስለ ድኽነቱ አይዘን፥ ኵላዊቷ መንግሥት ተገልጣለችና፡፡ ማንም በኃጢአቱ አያንባ፥ ከመቃብሩ የይቅርታ ብርሃን ተንቦግቧልና፡፡ ማንም ሞትን አይፍራ፥ የመድኃኒታችን ሞት ከዚህ ነጻ አውጥቶናልና፡፡ ለእርስዋ በመታዘዝም ጌታ አጥፍቷታልና፡፡
በሞቱ ሞትን ገደለው፡፡ ወደ ሲዖል በመውረድ ሲዖልን በዘበዘው፡፡
ኢሳይያስም አሰምቶ እንደ ተናገረ ሲዖል ከጌታችን ጋር ፊት ለፊት ተገናኘች፤ መረራትም! ከንቱ አድርጓታልና መረራት! ሸንግሏታልና መረራት! ሽሯታልና መረራት!
ነፍሳትን ይዛ እንዳታስቀር አስሯታልና መረራት!
[መቃብር የዕሩቅ ብእሲ] ሥጋ አገኘሁ ብላ ዋጠችው፤ ስትውጠው ግን እግዚአብሔር ኾኖ አገኘችው - መረራትም!
ሞት ሆይ! መውጊያህ ወዴት አለ? ሲዖል፥ መቃብርም ሆይ! ድል መንሣትህ ይዞም ማስቀረትህ ወዴት አለ?
ክርስቶስ ተነሣ፤ ሞት ሆይ፥ አንተም ጠፋህ!
ክርስቶስ ተነሣ፣ አጋንንትም አዘኑ!
ክርስቶስ ተነሣ፤ መላእክትም ሐሴት አደረጉ!
ክርስቶስ ተነሣ፤ የሰው ሕይወትም ነጻ ወጣች!
ክርስቶስ ተነሣ፤ መቃብርም ባዶ ኾነች!
ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ተነሥቶ ለአንቀላፉት ኹሉ በኵር ኾኖላቸዋልና፡፡
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
@beteafework @beteafework

ሰው እንደ መሆኑ በጨርቅ ተጠቀለለ፤ አምላክ እንደ መሆኑ የተገነዘበትን ጨርቅ ጥሎት ተነሣ፡፡
ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ
ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ
ከትንሳኤ እሁድ በኋላ ያሉ ዕለታት ስያሜ፡-
#ሰኞ- ማዕዶት ይባላል፡-
ማዕዶት ማለት መሻገር፣ ማለፍ ማለት ነው፡፡ በዚህ ዕለት በፋሲካችን በክርስቶስ ትንሣኤ ከድቅድቅ ጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃን፣ ከሞት ወደ ሕይወት፣ ከሲኦል ወደ ገነት፣ ከሃሳር ወደ ክብር መሻገራችንን እናስባለን፡፡
#ማክሰኞ- ቶማስ ይባላል፡-
በዚህ ዕለት ቶማስ ጌታን አይቶ ማመኑ፤ ጌታዬና አምላኬ ብሎ መመስከሩ ይዘከራል፡፡ ዮሐ. 20፡27-29
#ረቡዕ- አልአዛር ይባላል፡-
በዚህ ዕለት ትንሣኤና ሕይወት የሆነው ጌታ ኢየሱስ አልአዛርን ከሞት እንዳስነሳው እናስባለን፡፡ ክርስቶስ የሞትን ስልጣን የሻረ የሕይወት ራስ፤ የመቃብርን ሥርዓት ያጠፋ ትንሣኤ፡ በድልም ያረገ ንጉሥ መሆኑን እንመሰክራለን፡፡
#ሐሙስ- አዳም ሐሙስ ይባላል፡-
በዚህ ዕለት ለአዳም የተሰጠው ተስፋ እና የተገባለት ኪዳን እንደተፈጸመ አዳምና ልጆቹ ነጻ እንደወጣን እናስባለን፡፡
#አርብ- ቅድስት ቤተክርስቲያን ይባላል፡-
በዚህ ዕለት ቤተክርስቲያን በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ስለመመስረቷ ይሰበካል፡፡ ክርስቶስ ስለ እርሷ ራሱን አሳልፎ ሰጥቶ ቤዛ ሆኖ በደሙ አንጽቶ በትንሣኤው ድል ሰጥቶ እንዳከበራት ይነገራል፡፡ ቤተክርስቲያን ስንል ሕንፃውን ሳይሆን አማኞችን ነው፤ ክርስቶስ ለሕንፃ አልሞተምና፡፡
#ቅዳሜ- ቅዱሳት አንስት ይባላል፡-
በዚህ ዕለት ቅዱሳት አንስት የክርስቶስን አካል ሽቶ ለመቀባት ጨለማ አቋርጠው ወደ መቃብር መምጣታቸውና ትንሣኤውንም ቀድመው ማየታቸው ይሰበካል፡፡
#እሁድ- ዳግም ትንሳኤ ይባላል፡-
በዚህ ዕለት ክርስቶስ ለሦስተኛ ጊዜ ለደቀመዛሙርቱ ተገልጦ ሰላምን መስበኩ እና ሥልጣንን መስጠቱ ይሰበካል፡፡

"አሻጋሪዎች"
ሰባኪው በ አንድ ቤተክርስቲያን እየተገኘ ዘወትር
ያስተምራል። በየ እለቱ በርካታ ምእመናን በቦታው እየተገኙ ይሰበካሉ። ከ እነዚህ በርካታ ምእመናን ውስጥ አንደኛው ራቅ ካለ ቦታ ነው ሚመጣው። ወደ ቤተክርስቲያን ሲመጣም ሆነ ሲመለስ የመሻገሪያ ድልድይ የሌለውን ወንዝ እየዞረ ስለሆነ ከሌሎች ይልቅ ብዙ የሚደክመው እሱ ነው።
አንድ ቀን ግን እንዲህም ሆነ፡-
ሰባኪው የሚያስተምረው ስለ ጽኑ እምነት ነበር። " የሰናፍጭ ቅንጣት ታክል እምነት ቢኖራቹ ይህን ተራራ በገፋችሁት ሂድ እልፍ በል ባላችሁት ግዜ በሄደ። " የሚለውን የመጽሃፍ ቅዱስ ሃይለ ቃል ገልጾ በ እምነቱ ጽኑ ሲሆን የሚሳነው ነገር እንደሌለ ለምእመኑ አስረዳ።
በሚዞረው ትልቅ ወንዝ ምክንያት ከሌሎቹ ምእመን ይልቅ ብዙ የሚደክመው ያ ሰው ከ ቤተክርስቲያኑ ቅጥር ወጥቶ ወደ ቤቱ ሲያቀና እንደተለመደው እዛ ድልድይ አልባ ወንዝ ላይ ደረሰ።
ወንዙን ሲያየው ሰባኪው ያስተማረው የእምነት ትምህርት ድቅን አለበት። ወዲያውኑ "እኔ እኮ በእግዜብሔር አምናለው እግዜብሔርም ይህን ለ እኔ ማድረግ አይሳነውም" በፍጹም እምነት ወደ ጥልቁ ወንዝ በመሄድ ረገጠው እንዳለውም ተሳካለት መራመድም ቻለ። ያን ዙሪያ ጥምጥም ይሆነ የቤቱን ጎዳና በጣም አጭር በሆነ ደቂቃ አጠናቆ እቤቱ ግባ።
ሚስቱም በመደንገጥ " ቤተክርስቲያን አልሄድክም እንዴ? ምነው በጊዜ መጣህ?" ብላ ብትጠይቀው የሆነውን ሁሉ ነገራት። እሷም በጣም ተደንቃ" ባለቤቴ ይህ ተዐምር ከተደረገለት መምህሩማ ምን ያህል ኣምላክ የመረጠው ቅዱስ ነው ብላ በል ነገ ይዘኸው ና! ቤታችንን በበረከት ይጎብኝልን።" ብላ ባለቤቷን ተማጸነች።
በማግስቱ የዋሁ ባል ያለምንም ፍርሃት እና ጥርጣሬ በወንዙ ላይ ተረማምዶ ከተሻገረ በኋላ፡ ትምህርት ተከታትሎ ጉባኤው ሲፈጸም ሰባኪውን ሄዶ፥ " ባለቤቴ እቤት እየጠበቀችን ነው፡ እባክህን አብረን እንሂድ አለው።" ሰባኪውም ግብዣውን ተቀብሎ ጉዞ ጀመሩ። ሁለቱም እዚያ ወንዝ አጠገብ ሲደርሱ፡ የዋሁ ሰውዬ እንደለመደው በውሃው ላይ እየተራመደ ጥቂት ከተጓዘ በኋላ ዞር ብሎ ሰባኪውን ሲመለከት ከወንዙ ዳር እንደቆመ ነው።
በሰባኪው መቆም ተገርሞ "ና እንጂ መምህር ምን ሆነሃል?" ሲል ጠየቀው። ሰባኪውም "ፈራሁ" ሲል ይመልስለታል። ውሃውን እየረገጠ ወደኋላ ተመልሶ "ምነው መምህር? እኔን ለዚህ አብቅተህ እንዴት ትፈራለህ? ና ተሻገር እባክህን " ሲል ጠየቀው በሰውዬው ንግግር ጭንቅላቱ የተነካው መምህርም፡ "ወዳጄ እኛ እናሻግራለን እንጂ አንሻገርም!" ሲል መለሰለት።
እኛስ በእውነቱ የምንናገረውን የምናስተምረውን የምንሰብከውን እየኖርን ነውን? መልሱን ለእናንተ ትቻለው።
(እኔም ያነበብኩትን እንዲህ አካፈልኳችሁ እናንተም ከተመቻችሁ ለሌሎች ታድርሱት ዘንድ በድጋሚ ፖሰትኩት)

"አንድ ወንድና አንዲት ሴት የተጋቡት (የሚጋቡት) መንግሥተ ሰማያትን ለመውረስ በሚያደርጉት ጉዞ ላይ አብረው እየተጋገዙ ለመሔድ ከኾነ፥ ትዳራቸው ታላቅ የኾነ ደስታን ያመጣላቸዋል፡፡"
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
@beteafework @beteafework
@beteafework @beteafework
@beteafework @beteafework
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
@beteafework @beteafework
@beteafework @beteafework
@beteafework @beteafework
ተወዳጆች ሆይ እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ
የተወደዳችሁ የ"ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ" ቻናል ቤተሰብና ተከታታዮች አገልግሎታችን ይበልጥ ለማስፋት ይቻል ዘንድ ይህንን ሊንክ (@beteafework) ለሌሎች እህቶችና ወንድሞች ወዳጅ ጓደኞቻችን እንዲሁም ግሩፖችና ቻናሎች ሼር እናድርግ
@beteafework @beteafework
@beteafework @beteafework
ይህ ቻናል የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ትምህርቶች እና አበው ቀደምት የተናገሯቸው መንፈሳዊ ንግግሮች እንዲሁም ልዩ ልዩ ሐይማኖታዊ ትምህርቶችና መልዕክቶች ይተላለፉበታልና ቤተሰቦቻችን በማብዛት አገልግሎቱን እናስፋ። forward እያደረግን ሼር እናድርግ።
@beteafework @beteafework
@beteafework @beteafework
⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
ከእኛ ጋር°°°👇👇°°°ይቀላቀሉ

"እያመሰገነ፣ እየማለደ፣ የእግዚአብሔርን አንድነትና ሦስትነት እየመሰከረ፣ ኃጢአቱንም እያመነ ሳያስታጉል የሚጸልይ ሰው ከኹሉም ሰው ይልቅ እጅግ ድኻው ቢኾንም እንኳ፥ አማን በአማን ባለጸጋው ግን እርሱ ነው፡፡ እንደዚህ ያለ ጸሎትን የማያደርስ (የማይጸልይ) ሰው ግን፥ ምንም እንኳ ንግሥናን ሳይቀር ገንዘብ አድርጎ በትረ መንግሥትን ጨብጦ በዙፋን ላይ ቢቀመጥም እጅግ ድኻው እርሱ ነው፡፡"
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
@beteafework @beteafework
@beteafework @beteafework
@beteafework @beteafework
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
@beteafework @beteafework
@beteafework @beteafework
@beteafework @beteafework
"የብርሃናት ንጉሥ ብርሃን ኢየሱስ ክርስቶስን ለመውለድ ዛሬ የብርሃን እናት ቅድስት ድንግል ማርያም በእውነት ተወለደች። ከሊባኖስ ተራሮች ርግብ ጸዐዳ ተወለደች፤ በሔዋን ምክንያት የተዘጋው የሕይወት መንገድ ይከፈትልን ዘንድ የሕይወት እናት ዛሬ ተወለደች፡፡ የዓለም ብርሃን ኢየሱስ ክርስቶስን ከእርሷ ይወለድ ዘንድ እመብርሃን ዛሬ ተወለደች፡፡
ኢያቄምና ሐና ዳግሚት ሰማይ ተብላ የተጠራችውን ድንግልን ወለዱ፤ እውነተኛው ፀሐይ ኢየሱስ ክርስቶስ ከእርሷ ይወለድ ዘንድ እመ ፀሐይ (የፀሐይ እናት) ቅድስት ድንግል ዛሬ ተወለደች፤ ብርሃንን ለማስገኘት መወለድ መታደል ነው፤ ከሰው ልጆችም መካከል መመረጥ ዕፁብ ድንቅ ነው፤ የመድኃኔዓለም እናት ለመሆን መወለድ ሰማያዊ ፀጋ ነው።
በእውነት እመብርሃን ቅድስት ድንግል ማርያም የእግዚአብሔር ስጦታ ናት። ንጽሕተ ንጹሐን ቅድስተ ቅዱሳን እመብርሃን ዛሬ ተወልዳልናለችና ደስ ይበለን እልልም እንበል።"
የአለሙን ሁሉ መድኃኒት ለወለደች ለብርሃናት ጌታ እናት በቀራንዮ በመስቀሉ ስር እናት ትሆነን ዘንድ ለተሠጠችን ለመመኪያችን ዘውድ ለተወዳጇ ለቅድስተ ቅዱሳን እናታችን ልደት በዓል እንኳን አደረሰን
(Orthodox and Bible fb page)

ከመሬት የተገኘች ሰማይ ከሰማይ የሰፋች አለም። እግዚአብሔር ለእግዚአብሔርነቱ በራሱ ለራሱ ያበጃት መቅደስ፤ ኮሬብ ያልቻለችውን፣ ሲና የተንቀጠቀጠችለትን፣ ታቦር የራደችለት፣ ዮርዳኖስ የሸሸችለትን፣ ግሩምና ታላቅ ኃይል በማህፀኗ የተሸከመች ደብር ነባቢት፤ ቃል የማይገልጣት ንፁህ፣ ለቅድሱ አምላክ ፍፁምና ቅዱስ ማደሪያ የሆነች፣ ከሰው ተገኝታ ከመላዕክት የበለጠች፤ የፍቅር እናት የጌታ እናት የቤተ ክርስትያን እናት የአለም እናት የእኛ እናት የፍጥረት ሁሉ ጌጥ ወላዲተ አምላክ #ዛሬ_ተወለደች እንኳን ደስ አለን።
#አቡኑ_ማሞ
#አቡኑ_ማሞ
#የግንቦት_ልደታ_በዓል_አከባበር
በቤተ ክርስቲያናችን ትዉፊት መሰረት ሃና እና ኢያቄም ከአይሁድ ለማምለጥ ተሰደዉ በአድባረ ሊባኖስ ስር እመቤታችንን ወለዱ በወቅቱ ከቤት የወጡት ለሽሽት ነበርና ስንቅ ስላልያዙ ምግባቸዉ ‹‹ንፍሮና ጥራጥሬ›› ነበር፡፡ ይኼንን ትውፊት በመያዝ በዓሉ ከቤት ዉጭ ንፍሮ እየተበላ ይከበራል፡፡
ሆኖም በበጎ ነገሮች ሰበብ ክፉ ዓላማዉን ማስፈጸም የሚፈልገዉ ዲያቢሎስ በማር መሃል መርዝን ከሚጨምርባቸው መንፈሳዊያት በዓላት አንዱ የግንቦት ልደታ የእመቤታችን በዓል ነዉ፡፡ አንዳንዶች በድፍረት ለአድባር ለዉጋር ነዉ፣ ቆሌዉን ለመለመን ነዉ፣ እያሉ ንፍሮ የሚበትኑ፣ ቡና የሚረጩ፣ ቂቤ የሚቀቡ፣ የከብት ደም የሚያፈሱ፣ እነዚህ በእርግጥም ጣዖት አምላኪዎች ናቸዉ፡፡ እኛም ከእንደነዚህ ዓይነት አሰናካዮች በመለየት ይኼንን ታላቅ በዓል በተገባና በተረዳ ነገር እንድናከብረዉ እና ራሳችንን መልዕክቴ ነው፡፡
ለዚህም የእመቤታችን ረድኤት በረከት አይለየን፡፡

እነኋት እናታችን
ተወዳጅ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰጠን የመስቀል ስር ስጦታ ውዷ እናታችን ማርያም እነኋት ፡ የውድቀት ምክንያት የተሰኘ የሄዋንን ስም ለውጣ የድኅነት ምክንያት የሆነች እናታችን ማርያም እነኋት፤ በአንዲት ሴት አለመታዘዝ ሞት ቢመጣብን በአንዲቷ ሴት መታዘዝ ሞት የተሻረልን ድንግል ማርያም እነኋት፤ የባህርያችን መመኪያ የመድኃኒታችን እናት ከቤተልሄም እስከቀራኒዮ ከልጇ ከወዳጇ ያልተለየች የፍቅር እናት እነኋት፤ የምትወደድ የምትፈቀር እናት እነኋት። የሰው ሁሉ ወዳጅ ደግ ሩህሩህ አዛኝ ሰማያዊ እናት እነኋት፤ አዳም ሆይ ከወዴት አለህ? እነሆ ተስፋ ያደረካት ሴት፣ ህዝቅኤል ያያት መቅደስ፣ ኢሳይያስ ያያት ድንግል እነሆ ዛሬ ተወለደች።
ንፁህ ክቡር ቅዱስ ክርስቶስን ትወልድ ዘንድ ሞትህን በሞቱ የሚያሽንፈውን ባለድል ባለግርማ ኢየሱስ ክርስቶስን ትወልደው ዘንድ እዳ በደልህን የሚደመስስ ሃጥያትህን በደሙ የሚያጥብ ገናና ሊቀካህን ኢየሱስ ክርስቶስ ይገለጥ ዘንድ ሙሽራዋ እመቤት እነሆ ተወለደች፡፡ በሴት እንዳዘንክ በሴት ሃሴት ታደርግ ዘንድ፡ በሴት መታለል ድል እንደሆንክ፣ በሴት መታዘዝ ድል ታደርግ ዘንድ እነሆ አንዲቷ እንከን የሌለባት ሴት ዛሬ ተወለደች።
ከትውልዱ መካከል የሆንክ የክርስቶስ ልጅ ከወዴት አለህ? እነሆ ትውልድ ሁሉ የሚያመሰግናት የአምላክ እናት ዛሬ ተወለደች። ገብርኤል ሊያበስራት፣ ኤልሳቤጥ ልታወድሳት፣ አብ መንፈስ ቅዱስ ሊያርፍባት ወልድ ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ ሊያድርብት እነሆ ዛሬ ተወለደች። በመንፈስ ቅዱስ ብርሃን አይንህ እንደ ኤልሳቤጥ ይገለጥ እንደሆነ በትህትና በመንፈስ ቅዱስ ረድኤት ስራ ራስህን ያዘነበልክ አንተ ሆይ፦ እነሆ አይንህ የእግዚአብሄርን ማዳን ሊመለከት ነው።
የሰው ልጅ ሃሴትን አደረገ፡ መላእክት የቀኑን መድረስ አይተው ምስጋናን አቀረቡ እነሆ ጌታ ከፀባኦት ሊወርድ ነው። እነሆ የሁሉ አባት ሊወለድ ነው። አብርሃም ተስፋ ያደረገው፣ ሙሴ ሊያየው የጓጓው፣ ዳዊት ልጄ ያለው ኢየሱስ ክርስቶስ ሊወለድ ነው፤ እነሆ ምልክቷ ድንግል ዛሬ ተወለደች። ጌታ ራሱ የሰጠን ምልክት ይህች ናት። የተዋህዶ ምልክት ይህቺ ናት። በእሷ እኛ እንጠራለን፡ በእሷ እኛ እንወከላለን፡ እኛ ሁላችን ለእሷ ልጆቿ ነን እሷም ለእኛ እናታችን ናት። ተወዳጅ ክርስቶስ አፍቅሯታልና ተፈቃሪ ናት። ወዷታልና ተወዳጅ ናት፡፡ መርጧታልና ምርጥ ናት።
አክብሯታልና ክብርት ናት። ለይቷታልና ልዩ ናት። ጠብቋታልና
ንፁህ ናት። እነኋት እናታችን፡፡
ተወዳጅ ልጇ የራቀውን አቀረበልን የተጣላነውን አስታረቀን
ሰማይን ከምድር አገናኘው፡ ጨለማውን ገፈፈው በክርስቶስ የሞቱ ቢኖሩ ስለክርስቶስ ህያዋን ናቸው። በክርስቶስ ሆነው ምድር ያሉ ቢሆን ስለክርስቶስ ሰማያውያን ናቸው ፡ በሰማይ በአፀደ ነፍስ ያሉ ቢሆን ስለክርስቶስ ምድራውያን ናቸው። አንድ ክርስቶስ አለና፡ በክርስቶስ የተጠመቁ ሁሉ አንድ ሆነዋልና፡ ስለዚህም በክርስቶስ ባለኝ እምነት በሰማይ ያለች ድንግል ማርያም በምድር ከእኔ ጋር እንዳለች አወቅሁ፡ በእምነትም ምድራዊ የሆንኩ እኔ ሰማያዊያን ጋር ህብረት ሳደርግ አስተዋልኩኝ ፡ ስለተወዳጅ ልጇ ይህ ሁሉ ተቻለኝ ሰለተወዳጅ ልጇም ተወዳጅ እናቱን እናቴ አደረኩኝ፡፡
እነሆ እናታችን ዛሬ ተወለደች። የንጋት ውጋጋን ታየ፣ የራቀን
ምስራቅ ቀረበ። ብርሃን ክርስቶስ ሊግለጥ ፀሃይ ክርስቶስ ሊወጣ እንደሆነም አወቅን ይህቺን የፀሃይ መውጫ ምስራቅ እመቤታችንን አየናት፤ ባየናትም ጊዜ ምልክታችን እንደሆነች አወቅናት፣ ወደድናት፣ ያዝናት፣ እንደማህተምም በአንገታችን አሰርናት ክብራችን ጌጣችንም ናትና ከእርሷ ከልጇም ልንሽሽ በፍፁም አንችልም፡፡
ክብርና ምስጋና ለአምላካችን ይሁን፡፡ አሜን፡፡
(ከታምራት ፍስሐ የተወሰደ)

“በቤት ውስጥ በሚስትህ ምክንያት አንድ ደስ የማያሰኝ ስሕተት ቢፈጠር ‘አይዞሽ’ ልትላት ይገባል እንጂ ኀዘኗን ልታባብሰው አይገባህም፡፡ ኹሉንም ነገር ብታጣም እንኳን ከጎኗ ኹን፡፡ እርግጥ ነው ለባልዋ ደንታ ከሌላት ሚስት በላይ ምንም አሳዛኝ ነገር የለም፡፡ በእናንተ መካከል ጸብ ክርክር ከሚፈጥር የሚስትህ ጥፋት በላይ አሳዛኝ ነገር የለም፡፡ ስለዚሁ ዋና ምክንያት ግን ለእርስዋ ያለህ ፍቅር እጅግ ጽኑዕ ሊኾን ይገባዋል፡፡ እኛ ክርስቲያኖች አንዳችን የሌላችንን ሸክም እንድንሸከም የታዘዝን ከኾነ፥ ከዚህ በላይ ደግሞ አንተ የሚስትህን ሸክም ልትሸከም ይገባሃል፡፡ በመኾኑም ድኻ ብትኾን ስለዚሁ ምክንያት በፍጹም አትናቃት፡፡ ሰነፍ ብትኾን ስለዚሁ ምክንያት አስተካክላት እንጂ አታዋርዳት፡፡ እርስዋ አካልህ ነችና፤ አንተም አካልዋ ነህና፤ አንድ አካል ናችሁና፡፡ ‘ክፉ ነች፤ ቁጡ ነች፤ ራስዋን መቈጣጠር የማትችል ግልፍተኛ ነች’ ልትለኝ ትችላለህ፡፡ ስለዚሁ ጠባይዋ እጅግ ልታዝን ይገባሃል፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር ይህን ጠባይ ያርቅላት ዘንድ ጸልይላት እንጂ አንተም መልሰህ አትቈጣት፡፡ ልታሳምናት ሞክር እንጂ ወደ ሙግት አትግባ፡፡ እነዚህን ክፍተቶችዋን ከእርስዋ ለማራቅ ኹሉንም ዓይነት በጎ ዘዴዎችን ተጠቀም፡፡”
“ይህን እንደማድረግ ሚስትህን የምትመታትና የምታሠቃያት ከኾነ ግን እነዚህ ሕመሞችዋ እንዲድኑ አታደርጋቸውም፡፡ ኃይለኝነት የሚወገደው በጭካኔ ሥራ ሳይኾን በየውሃት ነውና፡፡ ከዚሁ በተጨማሪም ሚስትህ በየውሃት ስትይዛት ከእግዚአብሔር ዘንድ ሹመት ሽልማት እንደምታገኝ አስታውስ፡፡ ከአሕዛብ ፈላስፎች አንዱ ክፉ፣ መራራና ሥርዓት የለሽ ሚስት ነበረችው ይባላል፡፡ ከዕለታት በአንዱ ቀን ለምን ከእርስዋ ጋር እንደሚኖር (ለምን እንደማይፈታት) በተጠየቀ ጊዜ ጠቢቡ ሰው በገዛ ቤቱ ውስጥ የፍልስፍና ትምህርት ቤት እንዳለው ነበር የመለሰው፡፡ ‘ዕለት ዕለት በዚህ ትምህርት ቤት የምማር ከኾነ ከሌሎች ሰዎች ይልቅ ታጋሽ እኾናለሁ’ ነበር ያለው፡፡ በዚህ ተደነቅህን? እኔ ግን መላእክትን እንዲያውም ከእነርሱም በላይ የዋሃን ኾነን እግዚአብሔርን እንድንመስለው ከታዘዝነው ከእኛ ይልቅ አረማውያን ሰዎች ጠቢባን ኾነው ስመለከታቸው ፈጽሜ አለቅሳለሁ፡፡ ያ ፈላስፋ ሚስቱን እንዳይፈታት ምክንያት የኾነው የእርስዋ ክፉ ጠባይ ነው፡፡ እንዲያውም አንዳንድ ሰዎች ‘ይህ ፈላስፋ ይህቺን ሴት ሚስት ትኾነው ዘንድ ያገባት ይህን ለማግኘት ብሎ ነው’ ይላሉ፡፡ አንተም ዕጮኛ ስትመርጥ በምርጫህ ተሳስተህ ክፉ ሚስት አግብተህ ከኾነ (ብታገባ) ቢያንስ ቢያንስ ይህን አረማዊ ፈላስፋ አብነት አድርገው፡፡ ሚስትህን ለማስተካከል የተቻለህን አድርግ፡፡ ክፋትዋን በሌላ ክፋት አትመልስላት፡፡ ከእርስዋ ጋር ኾነህ የትዳርን ቀንበር የምትሸከም ከኾነ ሌሎች ብዙ ረብ ጥቅሞችንም ታገኛለህና፤ መንፈሳዊ ተግባራትን ለመተግበር ቀላል ይኾንልሃልና፡፡”
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ via ገብረ እግዚአብሔር ኪደ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
ወቅታዊ ጉዳዮችን በማስመልከት ከማኅበረ ቅዱሳን የተሰጠ መግለጫ
ቤተ ክርስቲያን ስደት ላይ ናት!
ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ከ1950ዎቹ ጀምሮ ሁለንተናዊ የአስተሳሰብ ውጊያ ሲደረግባት ቆይቷል፡፡ ይህ የአስተሳሰብ ውጊያ በጊዜ ሂደት መዋቅራዊ ወደመሆን እያደገ ሄዶ አሁን ያለንበት ወቅት ላይ ደርሰናል፡፡ በእነዚህ ረጅም ዓመታት ውስጥ ሲካሄድ የቆየውን ጥቃት ማሳያ የሆኑ በርካታ ክስተቶች መጥቀስ ይቻላል፡፡
ለምሳሌ ባለፉት ዓመታት በየአካባቢው የሚደረጉ የክርስቲያኖች በክርስቲያንነታቸው ተለይተው መገደል፣መሰደድ የአብያተ ክርስቲያናት መቃጠልና የምእመናን ሀብትና ንብረት መዘረፍ አንዱ ሲሆን የማንነትዋ መገለጫ የሆኑት ሀብቶችዋን ከዳር እስከ መሀል የመቀማትና የማጥፋት ብሎም ለሌሎች አካላትና አገልግሎቶች እንዲውሉ መደረጉ ደግሞ ሌላኛው ዓይነተኛ ማሳያ ነው፡፡
በተለይም ባለንበት ዘመን በቤተ ክርስቲያን ላይ የሚደረገውን ጥቃት ለየት የሚያደርገው ነጻነት፤ እኩልነት፣ መቻቻልና አብሮ መኖር የሚሉ ቃላትን ሽፋን ያደረገ መሆኑ ነው፡፡ ነጻነት፤ እኩልነት እና ሌሎችን እንደራስ አድርጎ መውደድ መሠረታዊ የክርስትና አስተምህሮ እንደመሆኑ መጠን ክርስቲያኑ ይህንን ባህል አድርጎ ሲኖረው ቆይቷል፡፡ በመሆኑም ሕዝበ ክርስቲያኑ እስከ አሁን ያለውን መከራና ጥቃት የሀገርን ሰላምና አንድነት በማስቀደምና በአርቆ አሳቢነት እንዲሁም ነገሮች ሊለወጡና ሊሻሻሉ ይችላሉ በሚል ተስፋ በትዕግሥት ሲያልፍ ቆይቷል፡፡ ሆኖም ግን ጉዳዩ ከመሻሻል ይልቅ በየቦታው ሲደረግ የነበረው የቅድስት ቤተ ክርስቲያን የማንነትዋ መገለጫ የሆኑ የእምነት ቦታዎች መነጠቅ እየባሰ መጥቷል፡፡ ከዚህም የተነሳ በገጠር የተጀመረው ቅድስት ቤተከርስቲያን ለአደባባይ በዓላት የምትጠቀምባቸውን የአምልኮ ቦታዎች መቀማትና ለሌላ አገልግሎት መስጠት እያደገ መጥቶ በዓለም አቀፍ ደረጃ በዓል የምታከብርበትን የመስቀል በዓል ማክበሪያ ቦታ ለሌላ አገልግሎት የማዋልና አሳልፎ ለመስጠት ሙከራዎች ማየት ደረጃ ላይ መድረሳችን ጥቃቱ ከፍተኛ ደረጃ ለመድረሱ ማሳያ ነው፡፡
ከዚህ ሁሉ ጋር ይዘቱ ምንም ይሁን ምን ቅዱስ ፓትርያርኩ እንደ ሰው የሚሰማቸውን ስሜትና ሀሳባቸውን መግለጽ መቻላቸው ተፈጥሮአዊ መብት ሆኖ እያለ የእርሳቸውን ንግግር ፖለቲካዊ ፍላጎትን ለማሳካት እንደ ምቹ ሁኔታ ተጠቅሞ ሲኖዶሱን ለመከፋፈልና ለማዳከም ብሎም ተቋማዊ አንድነትዋን ለማናጋት የሚደረገው ርብርብ በእጅጉ የሚያሳዝን ሆኖ አግኝተነዋል፡፡
በተጨማሪም ለዚህ ቤተ ክርስቲያንን የማሳደድ ተግባር የራስዋን አካላት ለጉዳዩ መጠቀሚያ ለማድረግ የተሄደበት ርቀት ጉዳዩን በእጅጉ አሳሳቢ ያደርገዋል፡፡
እነዚህን ሁሉ በአንድ ላይ ስናያቸው ለዓለም አቀፍ ማኅበረሰብና ለሌሎች አካላት ቀርቶ ለሁሉም ክርስቲያኖች እኩል ግልጽ ባልሆነ መንገድ ቤተ ክርስቲያን በስደት ላይ መሆንዋን ያሳያል፡፡
ስለዚህ:-
1ኛ፡ ሁላችንም ሕዝበ ክርስቲያን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ከመቼውም ጊዜ በላይ በስደት ላይ መሆንዋን ተረድተን እንደ ቀደምት አባቶቻችን የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ስደት በተቀበሉበት መንገድ ለመቀበል መዘጋጀት አለብን፡፡
2ኛ፡ የቤተ ክርቲያን አካላት ሆናችሁ ነገር ግን ይህንን በቤተ ክርስቲያን ላይ እየደረሰ ያለውን ስልታዊ እና የረቀቀ ጥቃት ባለመረዳት በተለያየ ደረጃ የችግሩ አካል በመሆን ላይ ያላችሁ ከዚህ ድርጊታችሁ እንድትቆጠቡ እናሳስባለን፡፡
3ኛ፡ በቤተ ክርስቲያን ኃላፊነት ቦታ ላይ ተቀምጣችሁ የቤተ ክርስቲያንን መብት ለማስጠበቅና ምእመናንን ለመጠበቅ የተሰጣችሁን አደራ ለጊዜያዊ ጥቅምና የፖለቲካ ፍላጎት መጠቀሚያ ያደረጋችሁ አካላት ከዚህ ድርጊታችሁ እንድትቆጠቡ ማሳሰብ እንወዳለን፡፡ በተጨማሪም ከቅዱስ ፓትርያርኩ ጋር በተያያዘ ከቅዱስ ሲኖዶስ ዕውቅናና መመሪያ ውጭ እና የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ሥርዓት ባልተከተለ መልኩ እንቅስቃሴዎችን የሚያደርጉ አካላት ከዚህ ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ማሳሰብ እንወዳለን፡፡
4ኛ፡ ሀገር እና ሰላም ወዳድ ኢትዮጵያውያን ዜጎች ይህንን በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ላይ እየተደረገ ያለውን የተቀናጀና የተደራጀ መገፋትና ስደት በመረዳት ከቤተ ክርስቲያን ጎን እንዲቆሙ እና ችግሮቹን ለማስወገድ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ እንጠይቃለን፡፡
5ኛ፡ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የቤተ ክርስቲያን ጠላቶች የመንግሥት መዋቅርን ተጠቅመው ቤተ ክርስቲያናችንን በልዩ ልዩ መንገድ ሲያጠቁ ክርስቲያኖችን ሲገድሉና ሲያሳድዱ ሲያፈናቅሉ እንደነበር መንግሥት ሲገልጽ የቆየ ቢሆንም መንግሥት አንድም ጊዜ በይፋ ይቅርታ ጠይቆ አያውቅም፡፡ በአንጻሩ ሌሎች አካላት በቤተ ክርስቲያኒቱ ይዞታዎች ላይ ያለአግባብ ለሚያነሱት ጥያቄ መልስ ለመስጠት በሚያደርገው ሂደት ረጅም ርቀት በመሄድ ይቅርታ ሲጠይቅ ይታያል፡፡ ይህም በቤተ ክርስቲያን ላይ እየደረሰ ያለው ስደት በመንግሥት የሚፈጸም ጥቃት ተደርጎ እንዲወሰድ አድርጎታል፡፡ ስለዚህም መንግሥት ቤተ ክርስቲያን ላይ ያለው ስደት እንዲቆም የማድረግ ድርሻውን እንዲወጣ ጥሪ እናስተላልፋለን፡፡
6ኛ፡ መንግሥት ውሳኔዎችን ሲወስን አሁን እየታየ ባለው መልኩ በጩኸትና የቤተ ክርስቲያንን መብት በመግፋት ፍትሕ እያዛባ የሚሄድና በቤተ ክርስቲያን ላይ እየደረሰ ያለው ስደት እንዲቆም የማድረግ ድርሻውን የማይወጣ ከሆነ ለሚደርሰው ሰላም ማጣትና ችግር ኃላፊነቱን የሚወስድ መሆኑን ማስገንዘብ እንወዳለን፡፡
7ኛ፡ በመጨረሻም ምእመናንን ከዚህ ጉዳይ ጋር ተያይዞ የሚኖሩ ቀጣይ ሁነቶችን እየተከታተልን የምንገልጽ መሆኑን ተረድተው በንቃት እንዲከታተሉ ማሳሰብ እንወዳለን፡፡
ግንቦት 3 ቀን 2013 ዓ.ም
ማኅበረ ቅዱሳን

"ልብህን በእርጋታ አኑረው፤ የሁሉም መጨረሻ እና የሁሉም አገልጋይ ለመሆን በጣም ትጋ ለከንቱ ንግግር ዘገምተኛና ሰነፍ ሁን፤ ነገር ግን የቅዱሳት መጻህፍትን ቃል በማወቅ በመስማት ድኅነትን የሚሰጡ ናቸውና ብልህ ሁን"
ታላቁ ባስልዮስ ዘቂሳሪያ
ታላቁ ባስልዮስ ዘቂሳሪያ
“ደጋግመህ ኃጢአት ብትሠራም ደጋግመህ ንስሐ ግባ፡፡ ቤተክርስቲያን ሐኪም ቤት እንጂ ፍርድ ቤት አይደለችምና፡፡”
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
"ባለንጀሮችህ አንድ ሺሕ ሊኾኑ ይችላሉ ምሥጢርህን ጠብቆ የሚይዘው ግን ከሺዎቹ አንዱ ነው፡፡"
ቅዱሰ ዮሐንስ አፈወርቅ
ቅዱሰ ዮሐንስ አፈወርቅ
ኦርቶዶክሳዊ የሕፃናት አስተዳደግ ማለት፥ ልጆቻችን እኛ አየናቸውም አላየናቸውም በሕሊናቸው ጓዳ በልቡናቸው ሰሌዳ ላይ መንግሥተ እግዚአብሔርን መቅረፅ ነው፡፡
ኦርቶዶክሳዊ የሕፃናት አስተዳደግ ማለት ስንጠራቸው አቤት ስናዛቸው ወዴት የሚሉንን ሳይኾን ትዕግሥትን፣ ቸርነትን፣ በጎነትን፣ እምነትን፣ የውሃትን፣ ራስን መግዛትን፥ በአጭር ቃል የመንፈስ ፍሬዎችን ገንዘብ ያደረጉ ልጆችን ማሳደግ ነው (ገላ.5፡22-24)፡፡
ኦርቶዶክሳዊ የሕፃናት አስተዳደግ ማለት፥ ልጆቻችን የገዛ ክብራቸውን እንዲያውቁና በዚያ መሠረት እንዲያድጉ - ይኸውም የእግዚአብሔር ልጆች፣ ክርስቶስን የሚመስሉ፣ በእግዚአብሔር አርአያና አምሳል ቅዱሳን እንዲኾኑ አድርጎ ማሳደግ ነው (ዘፍ.1፡26)፡፡
ኦርቶዶክሳዊ የሕፃናት አስተዳደግ ማለት ልጆቻችን የእኛ ንብረት እንዲኾኑ ሳይኾን የእግዚአብሔር ልጆች እንዲኾኑ አድርጎ ማሳደግ ነው፡፡ መጥምቁ ዮሐንስ እስራኤላውያንን ለክርስቶስ ያዘጋጃቸው እንደ ነበረ፥ እኛም በዚያ መንገድ ልጆቻችን የእግዚአብሔር ልጆቸ እንዲኾኑ ማዘጋጀት ነው፡፡
ኦርቶዶክሳዊ የሕፃናት አስተዳደግ ማለት የልጆቻችንን መጥፎ ጠባይ ከማራቅና እንዲታዘዙን ከማድረግ በላይ፥ እግዚአብሔርን በፍጹም ኃይላቸው እንዲወድዱ ማድረግ ነው፡፡ ቅዱሳንን እንዲያፈቅሩ፣ በቃል ኪዳናቸው ታምነው እነርሱን እንዲመስሉ ማድረግ ነው፡፡
#ትንሿ_ቤተ_ክርስቲያን፣ ገጽ. 507-508

"ባልና ሚስት እንደ እጅና እንደ ዓይን ሊሆኑ ይገባል፡፡ እጅ ሲጎዳ ዓይን ሊያለቅስ፥ ዓይን ሲያለቅስም እጅ እንባን ሊያብስ ይገባል፡፡"
#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ