Berbir Mereja / በርብር መረጃ
5.85K subscribers
17.4K photos
596 videos
5 files
15K links
Welcome back to our channel, where we bring you the latest updates and news from around the world.
Download Telegram
የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ለጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ እና ለእስራኤል ከፍተኛ ባለስልጣናት በጋዛ ጦርነት ምክንያት የእስር ማዘዣ ሊያወጣ ይችላል ሲል ዘ ታይምስ ምንጮቹን ጠቅሶ ዘግቧል።

▪️እንደ ጋዜጣው ከሆነ ከናታንያሁ በተጨማሪ በመከላከያ ሚኒስትሩ ዮአቭ ጋላንት ፣ በመከላከያ ሰራዊቱ ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም እና በደህንነት ባለስልጣናት ላይ የእስር ማዘዣው ሊወጣ ይችላል።

▪️ይህም በቀጣዩ ሳምንት መጀመሪያ ላይ እውን ሊሆን እንደሚችል ህትመቱ አስነብቧል።

▪️ኔታንያሁ በበኩላቸው ማንኛውም ዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት የሚያሳልፈው ውሳኔ የእስራኤልን ድርጊት እንደማይጎዳ ነገር ግን “አደገኛ ቅድመ ሁኔታን ይፈጥራል” ብለዋል።

ለጠቅላላ ግንዛቤ
@እስራኤል የ #ICC አባል አይደለችም።

አዳዲስ አለማቀፍ ሰበር ዜናዎችን ለማግኘት በነዚህ አማራጮች ይጠቀሙ 👇👇👇

👉👉Telegram :- https://t.me/berbirmereja

👉👉Facebook--› https://www.facebook.com/berbirmereja/

👉👉YouTube: -, https://youtube.com/@BerbirMereja
የስፔን መከላከያ ሚኒስቴር ፓትርዮት የአየር መከላከያ ሚሳይሎችን እና ሊዮፓርድ ታንኮችን ወደ ዩክሬን መላኩን ዛሬ በሰጠው መግለጫ አረጋገጠ።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ...
የኖርዌይ መንግስት ሊዮፓርድ 2A4 የተባሉት ታንኮችን ለመጠገን የሚውል 13 ሚሊዮን ዶላር ፣ ስምንት የተጠገኑ ሊዮፓርድ 2A4 ታንኮችን እና ተጨማሪ የድጋፍ ተሽከርካሪዎችን ወደ ኪይቭ ማስተላለፉን የአገሪቱ የመከላከያ ሚኒስትር አሪልድ ግራም አስታወቁ !

አዳዲስ አለማቀፍ ሰበር ዜናዎችን ለማግኘት በነዚህ አማራጮች ይጠቀሙ 👇👇👇

👉👉Telegram :- https://t.me/berbirmereja

👉👉Facebook--› https://www.facebook.com/berbirmereja/

👉👉YouTube: -, https://youtube.com/@BerbirMereja
የጣና ገዳማትን በዮኔስኮ አለም አቀፍ ቅርስነት ለማስመዝገብ ጥረቶች እየተደረጉ ይገኛሉ ተባለ

የጣና ገዳማት በዩኔስኮ አለም አቀፍ ቅርስነት መዝገብ ውስጥ እንዲሰፍሩ ለማድረግ የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ ሲል የአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ አስታውቋል።

የቢሮው የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ አበበ እምቢአለ ለብስራት ሬድዮና ቴሌቪዥን አንደተናገሩት ቢሮው በክልሉ የሚገኙ የመስህብ ሀብቶችን በማልማትና በማስተዋወቅ የባህልና ቱሪዝም ኢንዱስትሪውን በማሳደግ የክልሉን ህዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየሰራ ይገኛል።

በአሁኑ ወቅት የጣና ገዳማት ባህረ ደሴትና ረግረግ መሬቶች በዮኔስኮ አለም አቀፍ ቅርስነት መዝገብ እንዲመዘገቡ ለማድረግ ጥረቶች እየተደረጉ መሆናቸውን አስረድተዋል።ለዚህም የሚረዳ አለም አቀፍ ቅርስ መምረጫ ሰነድ እና የቅርስ አስተዳደር እቅድ ዝግጅት ስራዎችን ቢሮው ከኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን እንዲሁም ከአንድ የሆቴልና ቱሪዝም አማካሪ ድርጅት ጋር በመተባበር እያከናወነ ይገኛል ሲሉ አቶ አበበ ጨምረው ለብስራት ሬድዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።

ከጉዳዮ ጋር በተያያዘ የጣና ሀይቅ ደሴት ገዳማትና አዋሳኝ ባህር ሸሽ መልክአ ምድር ባህላዊና ተፈጥሮአዊ ቅርሶች ስር የተከለሉ ስፍራዎችን ሊያመለክት የሚያስችል ረቂቅ ደንብ እየተዘጋጀ እንደሚገኝ ከቢሮው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

አዳዲስ አለማቀፍ ሰበር ዜናዎችን ለማግኘት በነዚህ አማራጮች ይጠቀሙ 👇👇👇

👉👉Telegram :- https://t.me/berbirmereja

👉👉Facebook--› https://www.facebook.com/berbirmereja/

👉👉YouTube: -, https://youtube.com/@BerbirMereja
በአዲስ አበባ በዛሬዉ እለት ባጋጠመ የጎርፍ አደጋ የአራት ሰዎች ህይወት አልፏል

በዛሬው ዕለት ሚያዚያ 21 ቀን 2016 ዓ.ም ንጋት ላይ በቦሌ ክ/ከተማ በወረዳ 11 ወረገኑ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የጣለዉን ዝናብ ተከትሎ በተከሰተ የጎርፍ አደጋ የአራት ሰዎች ህይወት ማለፉን የአዲስ አበባ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታዉቋል።

የከተማ አስተዳደሩ ማስተር ፕላናቸዉን ያልተከተሉ የወንዝ ዳርቻ ግንባታዎች ህብረተሰቡን ለጎርፍ አደጋ እንደሚያጋልጡ በጥናት በመለየት ይህንን የአደጋ ስጋትና ተጋላጭነት በመሠረታዊነት የሚፈታ ፕላኑን የጠበቀ ዘላቂ የመፍትሄ ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ አስታዉቋል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ በደረሰው በዚህ ድንገተኛ አደጋ ምክንያት ህይወታቸውን ላጡ ወገኖቻችን የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገልጿል::በመሆኑም ተመሳሳይ አደጋዎች እንዳያጋጥሙ ህብረተሰቡ ከከተማ አስተዳደሩና ከእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የሚተላለፉ የጥንቃቄ መልእክቶችን ተግባራዊ እንዲያደርግ አሳስቧል::

ለእሳትና ለሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁም ለአንቡላንስ አገልግሎት በ939 ህብረተሰቡ ፈጥኖ እንዲያሳዉቅ ጥሪ ቀርቧል፡፡

አዳዲስ አለማቀፍ ሰበር ዜናዎችን ለማግኘት በነዚህ አማራጮች ይጠቀሙ 👇👇👇

👉👉Telegram :- https://t.me/berbirmereja

👉👉Facebook--› https://www.facebook.com/berbirmereja/

👉👉YouTube: -, https://youtube.com/@BerbirMereja
በኢትዮጵያ 46 በመቶ የሚሆነው የህብረተሰብ ክፍል የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ እንዳልሆነ ተነገረ

👉 ከግማሽ በመቶ በላይ የሚሆነው የህብረተሰብ ክፍል በጨለማ ውስጥ ይኖራል

በሁሉም የኢትዮጵያ አካባቢዎች የኤሌክትሪክ አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ የተለያዮ ስራዎች ቢከናወኑም እንደ ሀገር 46 በመቶ የሚሆነው የህብረተሰብ ክፍል የአሌክትሪክ አገልግሎት አያገኝም ሲል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታውቋል።በአገልግሎቱ የኮርፖሬት ኮሚኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ መላኩ ታዬ ለብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን እንደገለፁት ቀደም ባሉት ጊዜያት ከ6 በመቶ ያልበለጡ ዜጎች ብቻ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ ነበሩ።

አገልግሎቱ ከልማት አጋር ድርጅቶች በሚያገኘው ድጋፍ እንዲሁም በመንግስት አማካኝነት በሚመደብ በጀት የኤሌክትሪክ አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ ባደረገው ጥረት በርካታ ለውጦች መኖራቸውን ገልፀው ከ8 ሺህ በላይ የሚሆኑ የኢትዮጵያ የገጠር ዋና ዋና ከተሞች በአሁኑ ወቅት የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ መሆን ችለዋል።ባለፋት ዘጠኝ ወራት ውስጥም ከዚህ በፊት የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ያልነበሩትን 66 አዳዲስ የገጠር መንደሮችን እና ከተሞችን የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ ተችሏል ሲሉ የተናገሩት አቶ መላኩ ሁሉም የኢትዮጵያ ህዝብ የኤሌክትሪክ አገልግሎትን እንዲያገኝ ከማድረግ አንፃር ግን ውስንነቶች መኖራቸውን ጠቅሰዋል።

ከተሞች እያደጉ በመጡ ቁጥር የሚፈልጉት የሀይል መጠን በዛው ልክ የሚጨምር በመሆኑ ይህንን ከግምት ውስጥ በማስገባት በዋና ዋና የኢትዮጵያ ከተሞች ላይ የኤሌክትሪክ አገልግሎትን የማስፋፋት ስራዎችን ለማከናወን ታቅዷል ።

አዳዲስ አለማቀፍ ሰበር ዜናዎችን ለማግኘት በነዚህ አማራጮች ይጠቀሙ 👇👇👇

👉👉Telegram :- https://t.me/berbirmereja

👉👉Facebook--› https://www.facebook.com/berbirmereja/

👉👉YouTube: -, https://youtube.com/@BerbirMereja
#EU #Visa

የአውሮፓ ህብረት ም/ቤት የኢትዮጵያውያን ዜጎች ቪዛ አሰጣጥ ላይ ጊዜያዊ ገደብ ጣለ።

የአውሮፓ ህብረት ም/ቤት በኅብረቱ አባል ሀገራት ውስጥ ለኢትዮጵያውያን ዜጎች ቪዛ አሰጣጥ ላይ ገደብ ማስቀመጡን ባወጣው መግለጫ አሳውቋል።

ከዚህ በኋላ ኢትዮጵያውያን ቪዛ አመልካቾች ቪዛ ሲፈልጉ ፦

- አስፈላጊ ሰነዶችን እንዲያቀርቡ እና በአውሮፓ ህብረት ህግ የተቀመጠውን መደበኛ መስፈርቶች እንዲያሟሉ እንደሚገደዱ፤

- አባል ሀገራት ከአሁን በኋላ ከ2 ጊዜ በላይ ወደ ህብረቱ አባል ሀገራት ለመግባት የሚያስችለውን ቪዛ ለኢትዮጵያውያን መስጠት እንደማይችሉ ፤

- የዲፕሎማቲክ ወይም የሰርቪስ ፓስፖርት የያዙ ኢትዮጵያውያን ቪዛ ሲፈልጉ መደበኛ የቪዛ ክፍያ ለመክፈል እንደሚገደዱ ተነግሯል።

በተጨማሪ መደበኛ ቪዛ ለማግኘት የሚጠበቀው የ15 ቀን ጊዜ ወደ 45 ቀን ተቀይሯል።

ይህ ውሳኔ የተወሰነው የአውሮፓ ህብረት ም/ቤት ባደረገው ግምገማ መሰረት ኢትዮጵያ በህገ-ወጥ መንገድ በአውሮፓ ህብረት ሀገራት የሚቆዩትን ዜጎቿን በማስመለስ ረገድ የምታደርገው ጥረት በቂ ባለመሆኑ ነው ተብሏል።

ገደቡ እንከመቼ እንደሚቆይ የተባለ ነገር የለም።

አዳዲስ አለማቀፍ ሰበር ዜናዎችን ለማግኘት በነዚህ አማራጮች ይጠቀሙ 👇👇👇

👉👉Telegram :- https://t.me/berbirmereja

👉👉Facebook--› https://www.facebook.com/berbirmereja/

👉👉YouTube: -, https://youtube.com/@BerbirMereja
📍 ወደ ፍትሃዊው ዓለም የሚወስደው መንገድ በሰኔ ወር መጀመሪያ ላይ ሊጀምር ይችላል !
📍 ለመጀመሪያው የሰላም ጉባኤ የመክፈቻ ስነ ስርዓት በዝግጅት ላይ ነን !
📍 ለኔቶ ስብሰባም እየተዘጋጀን ነው - ህብረቱ በራሱ ጥንካሬ መተማመን አለበት እንጂ መፍራት የለበትም !
📍 ዩክሬን ለኅብረቱ አባልነት መጋበዝ አለባት !

ዘለንስኪ
ኮሜዲያንና የዩክሬን ፕሬዚዳንት

አዳዲስ አለማቀፍ ሰበር ዜናዎችን ለማግኘት በነዚህ አማራጮች ይጠቀሙ 👇👇👇

👉👉Telegram :- https://t.me/berbirmereja

👉👉Facebook--› https://www.facebook.com/berbirmereja/

👉👉YouTube: -, https://youtube.com/@BerbirMereja
#Update

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ሆነ።

የ2016 የትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ (12ኛ ክፍል) ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ሆኗል።

የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከሐምሌ 3 እስከ ሐምሌ 5 ለማህበራዊ ሳይንስ ፤ ከሐምሌ  9 እስከ ሐምሌ 11/2016 ዓ/ም ለተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች በበይነ መረብ (Online) እና በዩኒቨርሲቲ ውስጥ በወረቀት ይሰጣል።

በወረቀት ላይ የሚፈተኑ የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች ከሰኔ 30 እስከ ሐምሌ 01/2016 ዓ/ም እንዲሁም የተፈጥሮ ሳይንስ ከሐምሌ 6 እስከ 7/2016 ዓ/ም ወደ ዩኒቨርስቲ የሚገቡ ይሆናል። 

መረጃው የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ነው።

አዳዲስ አለማቀፍ ሰበር ዜናዎችን ለማግኘት በነዚህ አማራጮች ይጠቀሙ 👇👇👇

👉👉Telegram :- https://t.me/berbirmereja

👉👉Facebook--› https://www.facebook.com/berbirmereja/

👉👉YouTube: -, https://youtube.com/@BerbirMereja
አለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት በኒታንያሁ ላይ የእስር ማዘዣ ለማውጣት እያሰበ ነው ተባለ፡፡

ኒታንያሁና ሌሎች የእስራዔል ከፍተኛ ባለስልጣናት የእስር ማዘዣ ሊወጣባቸው እንደሚችል የእስራዔል መንግሰት ከፍርድ ቤቱ አመራሮች አመላካች ሁኔታዎችን እየተቀበሉ እንደሚገኙ ኢውሮኒውስ ዘግቧል፡፡

እስራዔል በዌስት ባንና በጋዛ ፈጽማዋለች በተባለው ወንጀል ደቡብ አፍሪካ ወደ ፍርድ ቤቱ እንዲወሰድ ምክንያት ሆኗል ተብሏል፡፡

የአለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤቱ በአሁኑ ወቅት እስራዔል በተቆጣጠረቻቸው ዌስትባንክና ጋዛ ምርመራ እያደረገ ይገኛል፡፡

አዳዲስ አለማቀፍ ሰበር ዜናዎችን ለማግኘት በነዚህ አማራጮች ይጠቀሙ 👇👇👇

👉👉Telegram :- https://t.me/berbirmereja

👉👉Facebook--› https://www.facebook.com/berbirmereja/

👉👉YouTube: -, https://youtube.com/@BerbirMereja
«ከታላቁ ህዳሴ ግድብ እስከ 250 ኪሎ የሚደርስ ዓሳ በቀን ይሰገራል»

የክልሉ ግብርና ቢሮ በበኩሉ በግድቡ ላይ በተገነባው ግዙፍ የዓሳ ምርት ላይ ለማሰማራት ከ2 መቶ በላይ ወጣቶችን ማደራጀቱን አመልክቷል፡፡ እስካሁን የተወሰኑት ወደ ስራ መግባታቸውን ገልጿል፡፡ የቢሮው ኃላፊ አቶ ባበክር ሀሊፋ በ8 ወራት ውስጥ 1ሺ7 መቶ ቶን የሚሆን ዓሳ ከግድቡ በተደራጁ ወጣቶች መገኙትን አመልክተዋል፡፡

አዳዲስ አለማቀፍ ሰበር ዜናዎችን ለማግኘት በነዚህ አማራጮች ይጠቀሙ 👇👇👇

👉👉Telegram :- https://t.me/berbirmereja

👉👉Facebook--› https://www.facebook.com/berbirmereja/

👉👉YouTube: -, https://youtube.com/@BerbirMereja
የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን በሊባኖስ ቴል አቪቭ የሚለውን መለያ ቃል እንዲሸፍን ተገደደ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ለእስራኤል እንደ ሀገር እውቅና ባልሰጠችው ሊባኖስ  ሀሙስ እለት በቤሩት አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ በአውሮፕላኑ ላይ "ቴል አቪቭ" የሚለውን መለያ ቃል ለመሸፋፈን ተገዷል። ኤርፖርቱ የፀጥታ ጥበቃው ET-ኤኤክስኬ የሚል መለያ ቁጥር ያለው አውሮፕላኑን ቴል አቪቭን ማድረጉን የሊባኖስ የሲቪል አቪዬሽን ዋና ዳይሬክተር ዘግቧል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላኑን ከገዛ በኋላ ያረፈበትን የመጀመሪያ አውሮፕላን ማረፊያ ስም ማተም የተለመደ መሆኑን ገልጾ አውሮፕላኑ ራፊቅ አል ሃሪሪ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ እስኪደርስ ድረስ ዝርዝሩን እንዳላስተዋለ ተሰምቷል። ሊባኖስ እና እስራኤል አሁን ላይ ጦርነት ውስጥ ይገኛሉ። ቤይሩት እና ሌሎች የሊባኖስ ከተሞች ላለፉት አስርት አመታት በእስራኤል ወረራ ስር ናቸው።

ይህም የሊባኖስ አቪዬሽን ዳይሬክቶሬት ከቤሩት ከመነሳቱ በፊት የቴል አቪቭ ምልክት እንዲሸፍን እና አየር መንገዱ ከእስራኤል ጋር የተያያዙ አርማዎችን ወይም ህትመቶችን የያዙ  አውሮፕላኖች ዳግም ወደ ሊባኖስ እንዳይጠቀም አስጠንቅቋል። በጥቅምት 8 በሊባኖስ ቡድን ሂዝቦላህ እና እስራኤል መካከል ድንበር ዘለል ጦርነት ከጀመረ በኋላ እስራኤል በሊባኖስ ከተሞች እና መንደሮች ላይ ተከታታይ ጥቃት አድርሳለች።

አዳዲስ አለማቀፍ ሰበር ዜናዎችን ለማግኘት በነዚህ አማራጮች ይጠቀሙ 👇👇👇

👉👉Telegram :- https://t.me/berbirmereja

👉👉Facebook--› https://www.facebook.com/berbirmereja/

👉👉YouTube: -, https://youtube.com/@BerbirMereja
የሩሲያ ጥቃት መጠናከሩን ተከትሎ የዩክሬን ጦር እያፈገፈገ መሆኑ ተነገረ

የሩሲያን የተጠናከረ ጥቃት ተከትሎ የዩክሬን ጦር ተቆጣጥሯቸው ከነበሩ ቦታዎች እየለቀቀ መሆኑን የሰራዊቱ ዋና አዛዥ ጄኔራል አሌክሳንደር ሲርስኪ ተናገሩ።

ዋና አዛዡ የዩክሬን ጦር ተቆጣጥሯቸው ከነበሩት ምስራቃዊ ዶኔስክ ግዛት ለቆ መውጣቱን ተናግረዋል።

አሁን ላይ ሩሲያ ካላት የሰው ሃይልና የጦር መሳሪያ የበላይነት አንጻር በጦር ግንባር ያለው ሁኔታ እየከፋ መሆኑንም ነው የተናገሩት።

ሩሲያ ባለፈው የካቲት ወር የአቪዲቪካን ግዛቶች ከተቆጣጠረች በኋላ የሃይል የበላይነት መውሰዷንም አረጋግጠዋል።

አያይዘውም የሩሲያ ጦር አዳዲስ ግዛቶችን በመቆጣጠር ወደ ፊት እየገፋ ነው ማለታቸውን ቢቢሲ አስነብቧል።

ዩክሬን በሩሲያ እየተወሰደባት ያለውን የበላይነት ለማስመለስ የአሜሪካ ወታደራዊ ድጋፍ ወሳኝ መሆኑን ስትገልጽ ቆይታለች።

አሜሪካ ባለፈው ሳምንት ለዩክሬን ወታደራዊ ድጋፍ የሚውል 61 ቢሊየን ዶላር የዕርዳታ ጥቅል ማፅደቁ ይታወሳል።

አዳዲስ አለማቀፍ ሰበር ዜናዎችን ለማግኘት በነዚህ አማራጮች ይጠቀሙ 👇👇👇

👉👉Telegram :- https://t.me/berbirmereja

👉👉Facebook--› https://www.facebook.com/berbirmereja/

👉👉YouTube: -, https://youtube.com/@BerbirMereja
ኢትዮ ቴሌኮም በቴሌ ብር አማካኝነት 4 ቢሊዮን ብር ብድር መስጠቱን ገለጸ::

ኢትዮ ቴሌኮም ለቴሌ ብር ተጠቃሚዎች እስካሁን 4 ቢሊዮን ብር ብድር መስጠቱን ለአራዳ ኤፍኤም አስታውቋል::

ቴሌ ብር ላይ የተመዘገበ ሰው ሁሉ እንደየደረጃው ብድር ማግኘት ይችላል ያለው ተቋሙ ለኢንተርፕራይዞች እስከ 50 ሺህ ብር ድረስ እያበደረ እንደሆነ ነው የገለፀው::

ያለማስያዣ ብድር እንደመሰጠቱ ከተመላሽነት ጋር ተያይዞ የሚፈጠሩ ችግሮችን በሚመለከት ጥያቄ ያነሳው ጣቢያችን በዚህ ዙርያ ተቋሙ እስከአሁን ችግር አልገጠመውም የሚል ምላሽ አግኝቷል::

ሆኖም ብደር የወሰደ ደንበኛ በወቅቱ ብድሩን ካልከፈለ በህግ የሚጠየቅበት አግባብ እንዳለ በኢትዮ ቴሌኮም የደንበኞችና የጥራት አስተዳደር ዋና ኃላፊ አቶ ሰሎሞን አበራ ለአራዳ ተናግረዋል::

በአርቴፍሻል ኢንተለጀንስ አማካኝነት የተበዳሪውን ታማኝነት፤ ግለሰቡ ያለው የአገልግሎቱ ቋሚ ተገልጋይነትና መሰል ጉዳዮችን በመለካት የብድር ምጣኔው ይወሰናልም ተብሏል::

አራዳ ኤፍኤም

አዳዲስ አለማቀፍ ሰበር ዜናዎችን ለማግኘት በነዚህ አማራጮች ይጠቀሙ 👇👇👇

👉👉Telegram :- https://t.me/berbirmereja

👉👉Facebook--› https://www.facebook.com/berbirmereja/

👉👉YouTube: -, https://youtube.com/@BerbirMereja