✒️ ብዕር 🖊️
378 subscribers
32 photos
2 videos
29 links
Download Telegram
ልብ ወለድልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪኮች:
😘ነፍስ ስታፈቅር😘

🔥ክፍል 25
.
.
መቼ እንቅልፍ እንደወሰዳት አታውቅም፡፡ኃይለኛ የበር መንጓጓት ነበር ከእንቅልፎ ያባነናት፡፡በርግጋ ስትነሳ ስሯ መለሎ ወንድ ጉያዋ ውስጥ ተሸጉጦ ተኝቷል፡፡እሷ መላመላ እርቃኗን ነች..፡፡ደግነቱ እሱ ሙሉ በሙሉ እንደለበሰ ነው፡፡
ተነሳች ከአልጋው ወረደች፡፡የበራፉ መንኳኳት እደቀጠለ ነው፡፡‹‹ምን ተፈጥሮ ይሆን ?፡፡ወደ ቁምሳጥኗ ሄደችና ቀላል ያለ በቀላሉ የሚጠለቅ ቀሚስ አደረገችና ወደስልኳ ኄደችና አነሳችና፡፡ ሰዓት አየች.. አራት ሰዓት ከሩብ ሆኗል፡፡ከቢላል ጋር እዚህ ቤት ሲገቡ ገና 12 ሰዓት ተኩል አካባቢ ነበር፡፡
‹‹ምን አይት ጉድ ነው?››ቭላ እየተንደረደረች ፎቁን ወረደች፡፡የሳሎኑን በራፍ ከፈተች፡፡ተዘራ እየተንቀጠቀጠም እያለከለከም በተቆራረጠ ድምጥ‹‹አረ እትዬ ጉድ ተፈጥሮል?››አላት
ተነሳች ከአልጋው ወረደች፡፡የበራፉ መንኳኳት እደቀጠለ ነው፡፡‹‹ምን ተፈጥሮ ይሆን ?፡፡ወደ ቁምሳጥኗ ሄደችና ቀላል ያለ በቀላሉ የሚጠለቅ ቀሚስ አደረገችና ወደስልኳ ሄደችና አነሳችና፡፡ ሰዓት አየች.. አራት ሰዓት ከሩብ ሆኗል፡፡ከቢላል ጋር እዚህ ቤት ሲገቡ ገና 12 ሰዓት ተኩል አካባቢ ነበር፡፡
‹‹ምን አይት ጉድ ነው?››ብላ እየተንደረደረች ፎቁን ወረደች፡፡የሳሎኑን በራፍ ከፈተች፡፡ተዘራ እየተንቀጠቀጠም እያለከለከም በተቆራረጠ ድምፅ‹‹አረ እትዬ ጉድ ተፈጥሯል?››አላት
‹‹የም ጉድ ነው….?እሳት ተነሳ?››
‹‹ኸረ አይደለም››
‹‹እሺ ተናገራ ..ሌባ ገባ?››
‹‹ውይ እትዬ…የልጁ እናት ››
‹‹የየትኛው ልጅ?››
‹‹ይሄው ያንቺው ልጅ ነዋ…የእብድ››
‹‹ምን ሆነች?››
‹‹አብዳለች…››
‹‹እንዴ እናትዬውም እብድ ነች እንዴ?››
‹‹አይ አሁን ማለቴ ነው››
‹‹ምን ሆና?››
‹‹ልጄ ጠፋ ብላ …. እዚህ ሲገባ አይተነዋል ብለው ነግረዋት በራፍ ላይ ልጄን አምጡ ብላ ሰፈሩን እያተራመሰችው ነው፡፡››
‹‹ጭራሽ››
‹‹አዎ ጭራሽ..እትይ አንቺስ ብትሆኚ እንደው ምን ሊያደርግልሽ ነው እስከእዚህ ሰዓት የሰው እብድ ያኖርሺው..››
ንግግሩን ችላ ብላ‹‹አሁን የት ናቸው?››ስትል ጠየቀች፡፡
‹‹ውጭ በራፍ ላይ››
ሲፈን ወደበራፍ ተንደረደረች….ተዘራ‹‹ ቆይ አትዬ እንዳይተናኮሉሽ…. ›› አልሰማችውም በራፍን ስትከፍት አስር የሚበልጥ ሰዎች ልክ አድማ እንደመቱ የፋብሪካ ሰራተኞች በራፍን ዘግተው እያጉረመረሙ ስታይ ደነገጠችና ወደኃላዋ ሸሽት አለች
‹‹ልጄስ..?አብሽስ?››እድሜዋ ከሀምሳ ብዙም የማይዘል ደልደል ያለች ብስል ቀይ ማሀከሉ ላይ ነጭ ሽበት የተጋደመበት ግን ደግሞ ጥቁር ሀረ መሳይ ሉጫ ፀጉር ያላት ሴት ወገቧን በመቀነት አስራ ልቅሶዋ ታስነካዋለች፡፡

ይቀጥላል...
10
🔥 ክፍል 26
.
.
‹‹ኸረ ማዘር አለ እኮ…ሰላም ነው፡፡››
‹‹እኮ ካለ ጥሪልኛ››
‹‹ተኝቶል…ልቀስቅሰው?››
አካባቢውን የሞሉት ሰዎች ‹‹ተኝቶል !!››ስትል ሲሰሙ ሁሉም አጉረመረሙ…ግማሾቹም እጃቸው አፋቸው ላይ ጭነው የሚያሽሞጥጡም ነበሩ…አንድ የሰፈር ወመኔ ‹‹የአብደ እኮ ኃይለኛ ነው››ሲል ጆሮዋ ጥልቅ አለ..፡እንድምንም እራሷን ተቆጣጠረችና ትኩረቷን እናቱ ላይ አድርጋ ማውራት ቀጠለች፡፡
‹‹ግብ እርሷ ….ግብና ይዩት››
እናትዬው ተንደርድረው ወደ ውስጥ ጥልቅ አሉ ..ሎሎችምች አንድ ሶስት ሰዎችም ተከትለዋቸው ሊገብ ሲሉ ሰይፈ..‹‹ቆይ ቆይ እሷቸው ብቻ ይበቃሉ›› ብሎ አገዳቸው፡፡
ሲፈን እናትዬውን አስከላ ወደቤት ገባች…ወደፎቅ ይዛቸው ወጣች..መኝታ ቤት ገቡ፡፡
የተንጣለለ ባለሁለት ሜትር አልጋ ላይ ልኡል መስሎ የሰላም እንቅልፍ ተኝቷል፡፡ ድምፅ በማሰማት እንዳይቀሰቅሱ እየተጠነቀቁ ደረታቸውን ደቁ… እናትዬው‹‹ወይኔ ልጄ….የእኔ ጠምበለል….ልጄ አላመመውም አይደል?››በተረጋጋ እና በሰከነ ድምፅ ጠየቋት፡፡
‹‹ኸረ ሰላም ነው…ግን ቅድም ዝናብ ውስጥ ሄዶ ስለነበረ ደክሞት መሰለኝ፡፡››
‹‹አዎ ልጄ ዝናብ ውስጥ መሄድ ይወዳል…ከዛ ቡኃላ ረጂም የሰላም እንቅልፍ ይተኛል….ግን እንዲህ ውጭ ተኝቶ አያውቅም ነበር…ዝናቡ እንዳባራለት ሮጦ እኔ እናቱ እቅፍ ውስጥ ነበር የሚወሸቀው፡፡››
‹‹ሳያስበው መሰለኝ ድንገት እንቅልፍ የጣለው፡፡››
‹‹ውይ ልጄ ተባረኪ…አሁን ትቀሰቅሺው ወይስ እንዴት እናድርግ?››
‹‹ቢተኛም ችግር የለውም ጥዋት አመጣሎታለው››
‹‹ኸረ በለሊት እራሴ መጥቼ እወስደዋለው…በይ ልጄ ትልቅ ይቅርታ.. ያው ትረጂኛለሽ የእናት አንጀት ሆኖብኝ ነው እራሴ ተበጥብጬ አንቺንም በጠበጥኩሽ… .ሰው ስለማይረዳውና ይተናኮሉብኛል ብዬ ስለምሰጋ ነው እንዲ በርጋጋ የሆንኩት ፡፡ ››
‹‹በይ ልጄ…..ወይ እርስቼው››አሉና ከለበሱት የሹራብ ኪስ ውስጥ መድሀኒት በማውጣት‹‹ሲነሳ ከዚህ መድሀኒት አንድ ይወጥ…››ተቀበለቻቸው‹እሺ እንዲውጥ አደርገዋለው››
እናትየው መኝታ ቤቱን ለቀው ወጡ ….ተከተለቻቸው፡፡የውጭ በራፍ ጋር ሲደርሱ ወደራሳቸው ሳቧትና ጉንጮቾን አገላብጠው ስመው ይዘውት የመጡትን አጀብ እያንጋጉ ሰፈሩን ለቀው ሄዱ፡፡
እሷም የሳሎኑን በራ ዘግታ ተመልሳ ወደፎቅ ወጣች….መኝታ ቤት ገባች….አሁን ለሽ ብሎ የሰላም እንቅልፍ እንደተኛ ነው….የመኝታ ቤቷን የኃላ በራፍ ከፈተችና ወደ ባልኮሊው ወጣች ..ወንበር አመቻችታ ተቀመጠችና ከጨረቃዋና ከከዋክብቶች ጋር ማውራት ጀመረች፡፡
ህይወትን እንደፈለገው ያሽከረከራት ጀግና ማን ነው….….?ለሆነ የተገደበ ጊዜ አይደለም…ለሆነ ዓመታትም ብቻ ማለቴ አይደለም..የእድሜ ልክ የምድር ቆይታ ዘመኑን በሙሉ ህይወትን በቁጥጥሩ ስር አድርጎ እያሾራት ያለው ወይንም ከታሪክ ማህደር ውስጥም ቢሆን በፈለገው አይነትና ሁኔታ እስከወዲያኛው መኖር የተሳካለት ማነው…….?አይ ሕይወትማ እንዲህ ልፍስፍስ አትመስለኝም… ፡፡በቃ እንዲህ እንደዋዛ በቀየስንላት መንገድ የምትጓዝ ወይም በቀደድንላት ቦይ የምትፈስ አይደለችም ..::እኛ በእሷ ላይ ባለን ፍላጎት ልክ እሷም ራሷ በእኛ ህይወት ላይ የሆነ መርምረን ልንደርስበት የማንችለው ስውር ሚስጥራዊ ፍላጎት አላትና…..
…እኛ በህይወት ላይ ያለን ፍላጎትና ህይወት በእኛ ላይ ያላት ፍላጎት አንድ አይነት በሚሆንበት ጊዜ መንገዳችንም አንድ አይነት መነሻ እና ተመሳሳይ መዳረሻ ይኖረዋል ….እናም የኑሮ መስመራችን አልጋ በአልጋ የሚባል አይነት ስያሜ ይሰጠዋል..፡፡
ይህ ግን ብዙ ጊዜ በተደጋግሞ የሚከሰት አይደለም ፤የእኛ ፍላጎት እና ህይወት እየፈሰሰችበት ያለበት መስመር ብዙ ጊዜ ተቃራኒ አቅጣጫ ስለሚይዝ ብዙዎቻችን ሁለት ምርጫ እንመራጣለን፡፡ አንድም የራሳችን የውስጥ ፍላጎትን ብቻ በማዳመጥ ሕይወት በተቃራኒው እየተጓዘች እንደሆነ ብናውቅም ትግላችንን መቀጠል..ብንቆስልና ብንላላጥም ከዛም እልፎ እስከሞት የሚያደርስ መከራ ቢገጥመንም እስከመጨረሻዋ እስትንፋስ መፋለም
…ሌሎቻችን ደግሞ ፍላጎታችንና ከህይወት ተቃራኒ መሆኑን በተረዳን ጊዜ ቆም ብለን በማሳብ እንዴት ነው የእኛ ፍላጎት ውጤታማ የሚሆንበት መንገዱ በዚህ ቢሆንም ህይወት ግን እየወሰደችን ያለው በዚህ ነው…እና ህይወት መንገዷን በእኛ ፍላጎት እስክታስተካክል ድረስ ፍሰታችንን ከእሷ ፍሰት ጋር አስተካክለን እንዴት መጓዝ እንችላለን..….?የእኛ ቀን እስኪመጣ ከእነ አቋማችን መቆየት ስለሚገባን ሳንቆስል ፤ ሳንላላጥና ስንሰባበር ለመቆየት ህይወት እስከአስገደደችን ድረስ በማንፈልገውም መንገድ ቢሆን መጓዝ ብልህነት ነው በማለት ሁለተኛው መንገድ ይመርጣሉ….እና የትኛው ነው የተሸለ ዘዴ ….?የሚለው አጠያያቂ መልስ ነው ያለው

….ህይወትን እንደ ወንዝ ቁጠሩት ..እዛ ወንዝ ከመግባታችሁ በፊት ወንዙ በስክነት የሚፈስ የረጋ መሆኑን ስላያችሁ በቁጥጥራችሁ ውስጥ እደሚሆን ገምታችሁ ለመዋኘት ወደ ውስጥ ትገባላችሁ…ከዛም እንደ እናንተ ፍላጎት ስትፋልጉ ከወንዙ ፍሰት በተመሳሳይ አቅጣጫ በቀላል ጉልበት ወይንም ትንሽ ተጨማሪ ጉልበት በማውጣት ከወንዙ ፍሰት በተቃራኒ ወደላይ እየዋኛችሁ እያላችሁ ድንገት ሳታስቡት ደራሽ ወንዝ እየተስገመገመ ስራችሁ ቢደርስ ምንድነው ምታደርጉት..?ጥያቄው ያ ነው፡፡ በጀመራችሁት መንገድ ከፍሰቱ በተቃራኒ መዋኘታችሁን ትቀጥላላችሁ ወይስ አቅጣጫ ትቀይራላችሁ…..?ውሳኔያችሁ በጽናት ወደፊት ለመሄድ ከሆነ ያንን የሚያስገመግም እየተገለባበጠ የሚመጣ ማዕበል እየሰነጣጠቃችሀ ወደፊት የምትቀጥሉበት በቂ ኃይል አላችሁ..? ማዕበሉ ይዞ እያገላበጠ የሚመጣቸውን ግንድና መሰል ባዕድ ነገር ጋር የሚፈጠረውን መጋጨትና መላተም ተቋቁማችሁ ለመዝለቅ ጉዞችሁን ትቀጥላላችሁ ..?ወይስ የትም ይወሰደኝ የትም ቢያንስ ድንገተኛው ደራሽ እስኪቀንስ ድረስ በህይወት መቆየት የምችለው ከፍሰቱ ጋር አብሬ በአንድ አይነት አቅጣጫ ስፈስ ነው፤ለዛም እንዲያግዘኝ አንድ ግንድ ጉማጅ ላይ ተጠምጥሜ የወሰደኝ ድረስ መሄድ አለብኝ… ማዕበሉ እስኪቀንስ ወይም ወደ ዳር እስኪተፋኝ መታገስ ነው የሚጠቅመኝ ብላችሁ ያንን ታደርጋላችሁ …...?
እንግዲህ በደራሽ ውሃ በሚናጠው ወንዝ መሀከል ሆኖ ከፍሰቱ በተቃራኒ አቅጣጫ መጓዝ መሞከር መጋጋጥን፤ በግንድ መገጨትን ፤ብሎም ሞትንም ጭምር የሚያስከትል ቢሆንም የወንዙ ፍሰትን ተከትሎ መጓዝም የት ድረስ ..?ለምን ያህል ጊዜ..? ይዞን እንደሚጓዝ ስለማናውቅ የማናውቀውና ዓለም፤ የማናውቀው ሀገር ድረስ መጓዝና፤ በማናውቀው ኑሮ ውስጥ ተጠምዶ መጣልን ሊያስከትልብን ይችላል……በሲፈን ህይወት ቢላል እንደጎርፍ ነው.ድንገት ደራሽ ጎርፍ ሆኖ በህይወቷ የተከሰተው፡፡እሷም በዛ ጎርፍ ውስጥ ያለተቃውሞ መሀል ገባት እየተንቧራጨቀች ነው…መጨረሻዋ ምን ይሆን…;?
ከመኝታ ቤቷ የሚሰማ ያልተለመደ አይነት መንጎጎት ነበር ከሀሳቧ ያባነናት….ከተቀመጠችበት በፍጥነት ተነሳችና ወደ ውስጥ ገባች፡፡
ስትደርስ ቢላል ከእንቅልፉ ተነስቶል...አልጋውን ለቆ ወርዶ ከፍሉ ውስጥ ከወዲህ ወዲያ እየተራመደ ይወራጫል…ጭንቅላቱን ይይዛል .ፀጉሩን ይነጫል››
3
‹‹እንዴ ቢላል.ምን ሆንክ?››
‹‹ጭንቅላቴ ውስጠ ይሯሯጣሉ.እስወጪልኝ…አልፈልጋቸወም…ጭንቅላቴን ለቀው ይውጡ››
ፈረች በጣም ፈራች .ሰውነቷን ሁሉ መንቀጠቀጥ ጀምሯል.‹‹ማን ናቸው ጭንቅላትህ ውስጥ ያሉት?››
‹‹ዘመዶቼ ናቸዋ.,ከሌላ ፕላኔት ነው የመጡት…ምድር መኖር የለብህም .ወደእኛ ና እያሉኝ ነው፡፡እኔ ደግሞ አንቺና እናቴን ጥዬ መሄድ አልፈልግም፡፡እርግጥ እዚህ በሰዎች አለም ከመኖር እዛ ሄዶ ከእነሱ ጋር የሰለጠነ ኑሮ መኖር ይሻላል ..ግን ለጊዜው እዚህ ምድር ላይ ነው መኖር የምፈልገው፡›
ሚያወረው መላቅጡ አይታወቅም፡፡ፈፅሞ አልገባትም‹‹….ተነሳበት ማለት ነው››ስትል አሰበች እናትዬው አውጪው ያለቻት መድሀኒት ትዝ አላት፡፡
ቆየ መዳሀኒትህን .ካስቀመጠችበት አነሳችና ከብርጭቆ ውሀ ጋር ልትሰጠው ብትሞክርም ሊሰማት አልቻለም፡፡
‹‹አንቺ ደግሞ .እሱን ተይና የምነግርሽን አዳምጪ…ዘመዶቼ የሚኖሩት ኬብለር የምትባለው ውብ እስታር ላይ ነው፡፡በጣም ስልጡን እና የመጠቀ ጭንቅላት አላቸው..እና እኔ ድንገት በሚገርም አጋጣመሚ ነው ከዛ አምልጬ የመጣውት…በዛ ደግሞ እነሱ ደስተኛ ስላልሆኑ እንደዚህ አዕምሮዬ ውስጥ እየገቡ ያስጨንቁኛል‹‹….ተውኝ እኮ ነው ምላችሁ.. ተውኝ፡፡››ጭንቅላቱን ከግደግዳ ጋር አላተመው..

ይቀጥላል....
6
ልብ ወለድልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪኮች:
😘ነፍስ ስታፍቅር😘

🔥ክፍል 27
.
.
‹‹እንዲተውህ
ይሀችን ኪኒኒ ወጥ አባክህ፡››በመለማመጥ ለመነችው፡፡
ድንገት ከእጃ ኪኒኑን መንጭቆ ተቀባላትና አፉ ውስጥ ከተተው…ከዛ ብርጭቆውን ተቀበለና ውሀውን ገርገጭ ገርገጭ እያደረገ ሙሉ በሙሉ ጨርሶ ጠጣና ብርጭቆውን መለሰላት..
‹‹ምን እያወራውሽ ነበር?››
‹‹አልጋ ላይ ቁጭ በልናን ታወራኛለህ…››
‹‹እ ቁጭ ልበል..››ሄዶ ቁጭ አለ
ወዲያው ወደኃላ ተኛ…ኩርምትምት አለና ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ወሰደው ፡፡አልጋ ልብስ አለበሰችውና እሷም ሶፋው ላይ ሄዳ ኩርምት ብላ ተኛች…ብዙም ሳይቆይ እንቅልፍ ወሰዳት፡፡
//
ጥዋት አስራ ሁለት ሰዓት ሁለቱም ተነስተው ነበር፡፡አይን አይኑን እያየች ሁኔታውን አጠናቸው..ፍፅም ጤነኛና ንቁ ሰው ሆኖ ነበር የተነሳው..ለሊት የተፈጠረውን የሚያታውስም አይመስልም…እሷም አንስታ ልትጠይቀው አልደፈረችም፡፡
‹ቁረስ ልስራና ወደቤት እሸኝሀለው፡፡››
‹‹አይ መሄድ አለብኝ ….እናቴን ማግኘት እፈልጋለው››አላት ለድርድር በማይጋዝ ድርቅ ያለ ንግግር፡፡
‹‹እሺ ላድርስህና …ተመልሼ ለራሴ ሰራለው…ወይ ቢሮ ሄጄ እበላልው››
‹‹አይ በራፍ ድረስ ብቻ ሸኚኝ…..ከዛ ቡኃላ በራሴ ሄዳለው››
‹‹እሺ እንዳልክ›› ብላ ተያይዘው ወጡ፡፡ የውጪን በራፍ አስከፍታ ስታስወጣው አንድ ሰማያው ቪታራ መኪና አጥሯን ታካ ቆማ ነበር..ብዙም ትኩረት አልሰጠቻትም….ቢላል ግን ከእሷ ተነጠለና ወደ መኪናዋ መራመድ ጀመረ …ግራ ገባት፡፡ የመኪናዋ ገቢና ተከፈተና አንድ ሴት ከውስጡ ወጣች….እናቱ ነበረች፡፡ ..ግን ከማታው አቋሟ ጋር ፈፅሞ ተቃራኒ በሆነ ይዞታ ላይ ነበር ያለችው..ዝንጥ ያለች የሴት ሚኒስቴር የሚመስል አለባበስ ለብሳለች፡፡ማታ ተንጨፍርሮ የነበረው ፀጉሯ በስርዓት ተበጥሮ ወደኃላ ተኝቷል፡፡ በመሀከል ያለው ሽበት ግርማ ሞገስ ጨምሮላታል….፡፡ሲፈን ጭንቅላቷን የሆነ ነገር መታት፡፡ይህቺን ሴትዬ ታውቃታለች፡፡ግን የት ነው የምታውቃት? ሊመጣላት አልቻለም፡፡ሰፈር ውስጥ እንዳልሆነ እርግጠኛ ነች..፡፡ማሰቧን ለጊዜው ገታ አድርጋ እርሷም ተከተለችው…፡፡እናቱ አጠገብ ሲደርስ እንደህፃን ልጅ ተጠመጠመባት፣.አገላብጦ ጉንጮን ሳማት‹‹እማዬ የእኔ ውድ..ልትወስጂኝ ነው የመጣሽው››
‹‹አዎ ግን አንተን ብቻ ሳይሆን ጓደኛህንም ልወስዳ ነው፡፡እንዴት ነው ቁርስህን ታካፍላታለህ? ወደቤት ይዘናት እንሂድ?››
ወደኃላ ዞር አለና ወደሲፈን ተራመደ…ፍቃዷንም ሳይጠይቃት ቀኝ እጇን ያዘና እየጎተተ ወደመኪናዋ ይዞት ሄደ… የኃላው በር ከፈተና ቀድሞት ገባ፡፡ ከዛም ጎትቶ አስገባት፡፡
እናትዬውም ወደቦታዋ ተመልሳ የመኪናዋን መተር በማስነሳ መንዳት ጀመረች፡፡
‹‹ልጄ ፍቃዷን እንኳን ሳትጠይቅ እየጠለፋካት እኮ ነው››
‹‹ነፍሴ የነፍሶን ፍላጎት አንብባለች…..ለማስመሰል በአፌ መጠየቅ አልፈለኩም››
ሲፈን ምንም መናገር አልቻለችም..ድንዝዝ እንዳለች ነው
‹‹…የእኔ ስም ሰሎሜ ይባላል…ያንቺስ?››
‹‹ሲፈን››
ሲፈን ስሞን በምትናገርበት ቅፅበት ሌላ ነገር ትዝ አላት..‹‹ፕሮፌሰር ሰሎሜ….›ስትል ለማረጋገጥ መልሳ ጠየቀች፡
‹‹አዎ….ትክክል››
አስታወሰቻት ስድስት ኪሎ እልል የታባለላት ሌክቸር ነች ፡፡ለዛውም በስነልቦና..እዛ ጊቢ በምታማርበት ጊዜ ቀጥታ እሷን አስተምራት ባታውቅም ስለዝናዋ ግን በየእለቱ ትሰማ ነበር..፡፡ከደርዘን ለሚቆጠር ጊዜም በሚዲያ ሞያዊ ማብራሪያ ስትሰጥ አይተት ታውቃለች፡፡
‹‹ቢላል የእሷ ልጅ ነው?››ውስጧ ሊቀበልላት አልቻለም፡፡
አንቱ የተባለችው የስነልቦና ሙሁር ልጅ የአእምሮ መፋለስ የደረሰበት..ይቺ አለም ገራሚ ነች፡፡
እቤት እንደደረሱ የጠበቃቸው ጠረጳዛ ሙሉ ምግብ ነበር‹‹..ለሊቱን ሙሉ ሲሰሩ ነው እንዴ ያደሩት?››ስትል አሰበች››
‹‹እማዬ የእኔስ ቁርስ?››አለ ለንቦጩኝ ጥሎ
ይሄስ ጠረጳዛው ሙሉ ምግብ አይደለ አንዴ?;;ሲፈን ነች ጥያቂዋ ግራ አጋብቷት
‹‹አይ ይሄ ላንቺ የተዘጋጀ መሰለኝ..እኔ እንዲህ አይነት ቁርስ እልወድም፡፡..አሳማ የሆንኩ ይመስለኛል…ግን ዝም ብዬ ነው ሰው ከመሆን አሳማ መሆን ሊሻል ይችላል….ብቻ አልወድም››ቀበዣዠረባት፡፡
እናትዬው አንድ ብርጭቆ ወተት አምጥታ ሰጠችው፡፡እሱን ይዞ ጥሏቸው መኝታ ቤት ውስጥ ገባ፡፡እናትዬው መጥታ የምግብ ጠረጳዛው ላይ ከሲፈን ፊት ለፊት ተቀመጠች፡፡
‹‹በቃ ቁርስ አይበላም?››
‹‹ያው ጥዋት አንድ ብርጭቆ ወተት ከጠጣ በቃው››
‹‹ይገርማል››

.........*..........*....*...***..


/////
ለምንድነው አንዳንድ ቀን የልቤን ሽንቁር ጥልቅ ጨለማ የሚሞላው..?ለምንድነው ህይወት ትርጉመ ቢስና አስልቺ ሆና የምትታየኝ…?ለምንድነው ያለ ምክንያት መኖር እንዲህ ስልችት የሚለኝ…?.እንዴት የገነት ናፍቆትና የሲኦል ፍራቻ እንዲህ ለልቤ በጥቂቱ እንኳን የማይሰማኝ…. .?ለምንድነው እንደዚህ ማፍቀር የሚደክመኝ…..?ለምንድነው እንደዚህ የበቀል ጥምና የጥላቻ እሳት በውስጤ የማይበቅለው…?ለምንድነው እንደዚህ ጊዜ እየጠበቀ ለምንም ነገር ያለኝ ስሜታዊ ግብረ መልስ ከውስጤ ተንጠፍጥፎ ተሟጦ የሚከስመው….?ሰው እንዴት መብላት ይደክመዋል…?.በምን ምክንያትስ መሳቅ ጨጎራን ሊያቆስል ይችላል?፡፡መዝናናትስ በምን ስሌት ነው ጨለማና ጥቁር ስሜት የሚፈጥረው ?፡፡
ይሄንን ፅሁፍ ሲፈን የተንጣለለ ቢሮዋ ቁጭ ብላ ከማስተወሻ ደብተሯ እያነበበች ነው፡፡ሰው ፅፎ ያስቀመጠላት አይደለም፡፡እሷ እራሷ ከ3 ወር በፊት አሁን የተቀመጠችበት ቦታ ቁጭ ብላ በጥልቅ መመሰጥ ውስጥ ሆና ህመሟን ያሰፈረችበት የግሏ እውነታ ነበር ፡፡
ይገርማል..አሁን ግን ነበር ሆኖ የቀረ ይመስላል.. ዛሬ ከላይ የሰፈሩት ሀሳቦች ብዙዎቹ አይገልጻትም፡፡ዛሬ ብርሀን ነው የሚታያት…ዛሬ ለእያንዳንዱ ነገር ጉጉትና መደነቅ በውስጧ ይንቦገቦጋል….ትፈራለችም ትሰጋለችም….እና ደግሞ ማፍቀርም መቅናትም ጀምራለች…..ይህ ለውጥ ነው አሁን ከሶስት ወር በፊት የፃፈችውን የራሷን ሀሳብ ስታነብ ብቻዋን አንድትስቅ ያደረጋት፡፡
የቢሮዋ በር በስሱ ተንኳኳና ተከፈተ….ፃሀፊዋ ነች…
‹‹እንግዳ ይፈልጉሻል ላስገባቸው…››
‹‹ቀጠሮ አላቸው››
‹‹አይ የላቸውም››
‹‹ማን ነኝ አሉ ?››
‹‹ስማቸውን አቶ ወልደገብርኤል ነው ያሉኝ››
‹‹ወልደገኤል ወልደገብርኤል..አላወቅኩትም አስገቢው››
ወልደገብርኤል የተባለው ሰው የቢሮዋን በራፍ አልፎ ሲገባ ያልጠበቀችው ሰው ነበር..ምን ሊሰራ እሷ ቢሮ እንደመጣ መገመት አቃታት....የአባቷ ወዳጅ ነው፡፡በቀደም ሽምግልናው ላይ ምስክር ሆኖ ከተገኙት ውስጥ አንደኛው ነበር፡፡ነገሩን ካራገቡትም መካከል ዋነኛው እሱ ነው፡፡
‹‹እንዴ ጋሼ ምን እግር ጣለህ…..?ስድስት ወሩ ሞላ እንዴ…?››ከመቀመጫዋ ተነስታ ጠረጳዛውን በመዞር ወደእሱ እየተራመደች ነው እያወራች ያለችው፡፡
‹‹እሱን በተመለከተ ጥሩ ዜና ይዤልሽ መጥቼያለው››ኮስተር እና ዘብን ብለው፡፡
‹‹የእውነት…እስኪ ቁጭ በሉ ….››
የእንግዳ መቀበያ ሶፋ ላይ ቁጭ አሉ …እሷም ከፊት ለፊታቸው ተቀመጠችና፡፡‹‹ሻይ ወይስ ቡና?››ስትል ጠየቀቻቸው፡፡
2
‹‹ኸረ ምንም አልፈልግም… የመጣውበትን በአጭሩ ላውራሽና እሄዳለው…ያ ቀጠሮ መጥቼ ጊዜሽን አልወስድብሽም››
‹‹እሺ ካሉ ምን ልታዘዝ?››
‹‹ልጄን ታውቂዋለሽ አይደል?››
የተንኮል ፈገግታ ፈገግ አለችና ‹‹እንዴ ጋሼ በድንብ ነዋ..ዮሴፍን ማን ማያውቀው አለ?››
ፊታቸውን ቅጭም አደረጉ…‹‹አይ ስለእያሱ ነው እያወራውሽ ያለውት››አሉ ቆጣ ብለው… እሷም ስለማንኛው ሊያወሮት እንደመጡ ገና እንደጀመሩ ነው የገባት..አውቃ ነው የሌለኛውን ልጃቸውን ስም የጣራችባቸው…ምክያቶችም እሷ ዩሴፍ ያለችው ልጅ ከሀሽሽ ጋር ተያያዥ በሆነ ጉዳይ ወህኒ ወርዶ በእስር ላይ ነው ያለው..እናም ስለእሱ ማንሳትም ሲነሳ መስተፍም እንደማይፈልጉ በደንብ ታውቃለች…እሷ ከእሷቸው ጋር የሥነልቦና ጫወታ ነው የያዘችው፡፡ በተቃራኒው እያሱ የሚባለው ልጃቸው አሜሪካ በተሸለ ኑሮ ላይ ያለ ስለሆን በየሄዱበት የእሱን ስም በማንሳት መጎረር የእየእለት ተግባራቸው ነው፡፡
‹‹እሺ አውቀዋለው››
‹‹ትናንት ተደዋውለን ስለአንቺ ለረጂም ሰዓት እያወራን ነበር…››
‹‹ስለእኔ ?ይገርማል… ስለእኔ ምን?››
‹‹ልጄ እያሱ ከልጅነቱ ጀምሮ እንደሚወድሽ ነግሮኘል..አሁንም ሊያገባሽ ፍቃደኛ ነው››
እራሷን በግድ ለመቆጣጠር እየጣረች ነው…ፊቷ ላይ ያለው ደም ስር በደም ተሞልቶ መንገድ ላይ ተዘርግቶ አፈር እንዳለበሰው የውሀ ልማት የውሀ ቱቦ ከሩቁ ይታያል፡፡››
‹‹እውነቶትን ነው ሊያገባኝ ፍቃደኛ ነው?››
‹‹አዎ በደንብ ፍቃደኛ ነው››
‹‹እኔስ…?››
‹‹አንቺ ደግሞ ምን..?››
‹‹እኔስ እሱን ለማግባት ፍቃደኛ ነኝ?››
‹‹ይመስለኛል?››
‹‹እንዴት ሊመስሎት ቻሉ?››
‹‹ውስጡን አውቃለዋ››
‹‹ጋሼ ብዙ ጊዜ ሰዎች ነገሮችን የሚያበላሹት ያውቁ መስሎቸው በማያውቁት ነገር ላይ ለውሳኔ ሲጣደፉ ነው፡፡ለማንኛውም እኔ በጣም የማፈቅረው ፍቅረኛ አለኝ..እሱን ነው የማገባው ››
‹‹ፍቅረኛ..?ከየት የመጣ..?ሁሉን ነገር እኮ አጣርቼያለው..እቤትሽ ከአንድ ከነሆለለ እብድ በስተቀር ማንም ዝር የሚል የለም..ይሄ እኮ ለአንቺ ትልቅ እድል ነው››
መጮህ አማራት….ከመቀመጫዋ ተነሳችና ወደወንበሯ ተራመደች….. ስልኳን አነሳችና ደወለለች…ሄኖክ ጋ ….ስልኩን ወደእሷቸው አስጠጋችና ላውድላይ አደረገችው፡፡
‹‹ሄሎ ሄኖኬ..››
‹‹ሄሎ የእኔ ፍቅር…ልደውልላት ወይስ ስራ አስፈታ ይሆን ?እያልኩ ሳመነታ ነው የደወልሽለኝ፡፡››
‹‹ትናንት ስላልተገናኘን ብዬ ነው የደወልኩት››
‹‹ዛሬ ግን እንገናኛለን አይደል..ሳፈቅርሽ..በወደፊት ልጆቻችን …እምቢ እንዳትይኝ ….12 ሰዓት መጥቼ ወስድሻለው›››
‹‹በቃ በአንተ መጨከን አልችልም… እሺ ብዬሀለው..እንደውም እኔም የምነግርህ የምስራች አለኝ››
‹‹ምንን አስመልክቶ…?››
‹‹እስክንገናኝ ታገስ››
‹‹ኸረ ቢያንስ ቢያንስ ፍንጭ ስጪኝ ..እንዳልፈነዳብሽ››
‹‹የሚያስፈነድቅ ዜና ነው…ሁልጊዜ ስለምትመኘው ነገር..››
ልቡን አንጠለጠለችበት ‹‹እኔ ሁል ጊዜ የምመኘው አንድ ነገር ብቻ ነው››
‹‹ምንድነው?››እሷ የዘወትር ምኞቱ ምን እንደሆነ በደንብ ታውቃለች…ግን ጮክ ብሎ እንዲናዘዝ የፈለገችው እሷቸው እንዲሰሙና ተስፋ ቆርጠው ቢሮዋን ለቀውላት እንዲሄዱ ነው ፡፡
‹‹እሺ ብለሺኝ ካንቺ ጋር መጋባት ብቻ..››
የፈለገችውን ሲናዘዝላት‹‹በል ቸው ››ብላ በደስታ ሥልኩን ዘጋችው፡፡
‹‹ጋሼ አሁን ሁሉም ነገር የተመለሰሎት መሰለኝ››
‹‹እንዲህማ አይደረግም…›› ተመነጫጭቀው ከተቀመጡበት ተነሱ… መራመድ ጀመሩ… በንግግሯ አስቆመቻቸው፡፡
‹‹ጋሼ››
‹‹እ››
‹‹በነገራችን ላይ በዛን ቀን አባቴ ጠርቷችሁ ለምስክርነት ተቀምጣችሁ ከነበራችሁት ሰዎች መካከል ለጋብቻ ስትጠይቁኘ እርሶ ሶስተኛ ሰው ኖት..››
በንዴት ለድብድብ እንደተዘጋጀ ሰው ሰውነታቸውን ወጣጥረው ‹‹.ሌላ ደግሞ ማን ጠየቀሽ?››
‹‹አቶ ክፍሉ ልክ እንደእርሷ ለልጁ አቶ ይበልጣል ደግሞ ለራሱ››
‹‹ደደብ በያቸው…. ሁለቱም አንቺን ሳይሆን የምትወርሺውን ገንዘብ ፈልገው ነው…ሊበላ …በአቋራጭ ቢሊየነር ሊሆኑ?››
በንዴትም በግርምትም‹‹እርሶስ?››አለቻቸው ፡፡
‹‹እኔን ከእነሱ ጋር አቻ አድርገሽ ታወዳድሪኛለሽ…?ቆይ ለዚህ ድፍረታቸው የማደርጋቸውን አታውቂም…እንዲህ በቀላሉ…የምይደረገውን›› እየፈከሩ እያቅራሩ ቢሮዋን ለቀው ወጡ፡፡ከአመጣጣቸው በላይ አወጣጣቸው አስገረማት….
‹‹ምን እቅድ አቅደውብኝ ነበር?››እራሷን ጠየቀች…

እሷም በግማሽ እየተደሰተች በግማሽ ደግሞ እየተበሳጭ ወደስራዋ ተመለሰች፡፡
ልክ 11 ሰዓት ተኩል ሰልኳን ሲያንቃጭል ነበር ቀጠሮ እንደነበረባት ያስታወሰችው‹‹..አጉል ቀጠሮ ››አለች
አነሳችው‹‹ሄሎ››
‹‹እታች እየጠበቅኩሽ ነው››
‹‹ምነው ፈጠንክ?››
ባክሽ ከመጣው 40 ደቂቃ አልፎኛል…ያልደወልኩልሽ ልረብሽሽ ስላልፈለኩ ነው፡፡››
‹‹ምነው ይሄ ሁሉ ጥድፊያ.. .ሽሹ ተባለ እንዴ?››
‹‹ያው በይው …ሰርፕራይዝ አለህ ብለሺኝ..ይሄን ያህልም መታገሴ እኔ ስለሆንኩ ነው››
‹‹ወይ ጉዴ !!በል እሺ መጣው››ሰልኩን ዘጋችና ከተሸከርካሪ ወንበሯ ላይ ተስፈንጥራ ተነሳች፡፡
‹‹አሁን እሺ ምን ሚነገር ነገረ አለኝና ልንገረው….እኔ እኮ የሰውዬውን የተወጣጠረ ስነልቦና ላስተንፍስ ብዬ ነው በወቅቱ የቀባጠርኩት…ምነው በቀረበኝ››ስትል ተፀፀተች፡፡
ኮቷን ከመስቀያው አንስታ ለበሰች…ቦርሳዋ ከፈተቸና መዋቢያዎቾን ጠረጳዛ ላይ ዘረገፈቻቸው ...ከንፈሯን በሊፓስቲክ ቅንድቧን ደግሞ በኩል አደመቀችና ሁሉንም ወደቦታቸው መለሰች፡፡‹‹እንግዲህ ተነስቼ ልሄድና ሁሉንም እንዳመጣጡ ልመልሰው›› ስትል እራሷን አጀገነችና ቦርሳዋን አንጠልጥላ ቢሮዋን ለቃ ወጣችነ በአሳንሰሩ ወደ ታች ወረደች፡፡
ከቤዝመንት የራሷን መኪና አስነስታ እንደወጣች ህንፃቸው በራፍ ላይ መኪናውን አቁሞ ሲጠብቃት አየችው…መኪናውን አስጠጋችና፡፡
‹‹ እሺ ወዴት እንሂድ?››
‹‹ደስ ያለሽ ቦታ..››
‹‹እሺ ተከተለኝ…ለቤቷ እንዲቀርበት…. ወደቦሌ ነዳችው… .እስካይ ላይት ሆቴል››
ገና ደርሰው ወንበር እንደያዙ ነበር..ጨቅጭቁን የጀመረው
‹‹ሚገርም ነገር ነው የምነግርህ?››
የሄኖክ መላ ሰውነቱ ሁሉ ጆሮ ሆነ ..ወደ ጠረጳዛው የተቀመጠበትትን ወንበር አስጠጋና አንገቱን እስኪለጠፍባት ድረስ ወደእሷ አሰገገ …. ቁርጥ….ቀርጥ የሚለው ትንፋሹ ገረፋት…
‹‹ምሳ ሰዓት ከአባትህ ጋር ተገናኝተን ነበር..›ድንገት የመጣለት የወሬ ርዕስ ነው፡፡
‹‹ለምን?እንዴት? የት አገኘሽው…?››ከጠበቀው ውጭ የሆነ ርዕሰ ስላነሳችበት ግራ ተጋባ
‹‹በቃ ተደዋወልንና ምሳ ልጋበዞት እልኳቸው… እሺ አሉና መጡ ፤ምሳ አብረን በላን ..ብዙ ነገር ተጫወትንና ተለያየን፡፡››
‹‹ይገርማል …..አባዬ ምሳ ልጋብዝህ ስትይው እሺ ብሎ መጣ.?.››
‹‹አዎ ….በደስታ ነዋ፡፡››
‹‹ወይ አባዬ …በጣም እየገረመኝ ነው…ለማንኛውም ከአባቴ ጋር ስለተጋናኛችሁ ደስ ብሎኛል…መቀራረባችሁም አሪፍ ነው፡፡እስኪ አሁን እሱን ለጊዜው ተይና ወደ ሰርፕራይዙ ተሸጋገሪ፡፡››
‹‹እኮ ሰርፕራይዙ እኮ ይሄ ነው››
‹‹ይሄ ማለት?›.
1
‹‹ይሄ ነዋ ….አሁን ስለአባትህ የነገርኩህ?››
‹‹እየቀለድሽ ነው?››በብስጭት
‹‹እየቀለድኩ አይደለም…ልጃቸውን ባገባ በጣም ደስተኛ እንደሚሆኑና ሚስታቸው ማለት እናት ዳግመኛ ከሞት እንደተነሳች አንደሚቆጥሩ ነገሩኝ››
ስለጋብቻ ሲነሳ ደብዝዝ ብሎ የነበረው ስሜቱ ዳግም ተነቃቃ‹‹አና ምን አልሺው….መቼስ በእኔ እንደለመድሺው ለእሱም ቆይ ገና ማፍቀሬን እርግጠኛ አይደለሁም አላልሽውም አይደል?››
‹‹አይ እንደዛ አላልኳቸውም..ላስብበት ትንሽ ጊዜ ስጡኘ ነው ያልኳቸው?›
‹‹ያው ነው አማርኛውን ቀየርሺው እንጂ ምንም የተለየ ነገር አልነገርሺውም››
‹‹ግን እሷቸው እኮ ተረድተውኛል… እንደአንተ እልተነጫነጩም››
‹‹እንዴ እሱ እንዴት ይነጫነጫል ብለሽ ጠበቅሽ.?አፍቃሪውም በጉጉት ላብድ የደረስኩትም እኮ እኔ ነኝ››
‹‹አውቃለው››
‹‹ምገርም ጅል ነኝ…እኔ ደግሞ ሰርፓራይዝ ስትይኝ እሺ ልትይኝ መስሎኝ ቀለበት ሁሉ ገዝቼ ይዤ መጥቼ ነበር…››አላት በቅሬታ ተሞልቶ ኪስ ውስጥ ያለውን ቀለበት በጣቶቹ እያፍተለተለ፡፡
በዚህ ጊዜ ስልኮ ጠራ..የማታውቀው ቁጥር ነው….ግ በመጋት ለተወሰነ ደቂቃ ከተመለከተችው ቡኃላ አነሳችው፡፡
‹‹ሄሎ ማን ልበል?››
‹‹ሰሎሜ ነኝ››
በረገገች‹‹እንዴ..ፕሮፌሰር…ምነው ?ቢላል ሰላም አይደለም?›
‹‹ትንሽ አሞታል…ምትቺይ ከሆነ ብትመጪ ››በመለማመጥ ጠየቋት
‹‹እሺ መጣው..አሁን መጣው….››አጠገቧ ሰው ያለም አልመሰላት፤ መቀመጫዋን ለቃ ተነሳች፤ ወደውጭ ተንደረደረች፡፡፡


ይቀጥላል....
10
😘ነፍስ ስታፈቅር😘

🔥ክፍል 28
.
.
//

Love is cure
Love is power
Love is the magic of changes
Love is the mirror of divine beauty
///Rumi//
እንዴት መኪናዋን ነድታ ፤በየት በኩል አድርጋ እንደደረሰች አታውቅም…በ15 ደቂቃ ውስጥ እነ ቢላል ቤት ደርሳ እንዲከፍቱላት የመኪናዋን ክላክስ እያስጮኸች ነበር፡፡
ሄኖክ ሂሳብ ከፍሎ ሊከተላት ቢሞክርም አቅጣጫዋን ማግኘት ሰልላልተቻለው ሊሳካለት አልቻለም፡፡
‹‹ወዴየትኛው ጉድጓድ እንደገባች ሊጠይቃት ሞባይሎ ላይ ከሰላሳ ለበለጠ ጊዜ ቢደወላላትም ልታነሳለት አልቻለችም…ይሄም በስጋትና በቅናት የተበረዘ ስሜቱ የጨጎራው ቁስል እንዲነሳበት ነው ያደረገው›፡
እሷም የተወሰነ ቅሬታ አድሮባታል.ለሄኖክ ፍትሀዊ እንዳልሆነችለት በደንብ ታውቃለች፡፡‹‹ቢሆንም በፍቅር ውስጥ ፍትህ መች ቦታ ኖሮት ያውቃል››ሰትል እራሷን ለማፅናናት ሞከረች፡፡
ውጪን በራፍ ከፈቱላትና ወደውስጥ ዘልቃ ገች..ፕሮፌሰረን ሳሎሜን አገኘቻት
‹‹ምን ሆነ ?የት ነው?››ሲፈን አባቷ አሟቸዋል ተብላ ከደርዘን ለበለጠ ጊዜ ከቢሮዋም ሆነ ከቤት ተደውሎላት ተጠርታ ታውቃልች….በየጊዜው ሩሀን እስክትስት ድረስ በድንጋጤ ደንዝዛ እና ብርክ ይዞት ነበር የምትደርሰው..አሁን ስታስበው ግን ከዚህ ቀደም ድንጋጤ ምን እደነበር በውል እንደማታውቅ ነው የተረዳችው፡፡ነፍሷ እኮ ሾልካ ልትወጣ ከየሰውነቷ ተሰብስባ ጉሮሮዋ ላይ ተወትፋ ነው ያለችው…አክ ብላ ቱ ብትላት በቃ አለቀላት..ሹልክ ብላ ትወድቃለች.ያበቃላታል፡፡
ቅድም በስልክ እንደሰማችው የተሸበረና የሚርበተበት ድምፅ ሳይሆን ከዛ ተቃራኒ በሆነ በሰከነ ንግግር ‹‹ክፍሉ ነው…አሁን መድሀኒቱን ወስዶ እየተረጋጋ ነው.ቁጭ በይ ››አለቻት፡፡
‹‹ባየው አይሻልም?››ፈራ ተባ እያለች ፍላጎቷን አሳወቀች፡፡
‹‹አይ ትንሽ ሰዓት እንስጠው…አሁን ጭንቀቱ አልፎል..ይቅርታ ስምሽን እየደጋገመ እየጠራ እራሱን ከግድግዳ ጋር ማጋጨት ስለጀመ ነበር አንቺ ጋ የደወልኩት፡፡››
ከፕሮፌሰሯ ፊት ለፊት ሶፋው ላይ ቁጭ እያለች ማውራቷን ቀጠለች
‹‹አረ ችግር የለም….እራቅ ያለ ቦታ ስለሆንኩ ነወ ትንሽ የ ዘገየውት›
‹‹አረ በጣም ፈጥነሽ ነው የመጣሽው…አየሽ ልጄ ሲታም እንደባለሞያ ሳይሆን እንደእናት ነው የማሰበውም የምጨነቀውም….በዛ የተነሳ አንዳንዴ እንዲህ እንደዛሬ እራስ ወዳድ እሆናለው….አንቺ ያለሸበትን ሁኔታ ምንም ከግምት ሳላስገባ ቶሎ ድረሺ ብዬ መደወሌ ከእኔ ሚጠበቅ አልነበረም ያንን አውቃለው.››
‹‹.እንደውም በተቃራኒው ሲደወልልኝ ምንም እንኳን በጣም ብደነግጥም ግን ደግሞ ደስ ነው ያለኝ፡››
‹‹ግን ሁሌ እደዚህ ያመዋል ማለት ነው?›
‹‹አይ አሁንማ ምን ያመዋል ማለት ይቻላል ፡፡ይህቺን አንድ አመት እኮ ነው ሰው የሆነልኝ….ለሶስት አመት እግርና እጁ በሰንሰለት ታስሮ ከአኔ በስተቀር ሰው ሁሉ በሩቅ እንደአውሬ የሚሸሹት አስፈሪ ፍጡር ነበር…የእኔ መልዐክ ልጅ ከምታስቢው በላይ ተሰቃይቶል… ..የበፊቱን ህመሙን ብታይ ይሄ አሁን አልፎ አልፎ ወሰድ መለስ የሚያደርገው እንደ ቀልድ የሚቆጠር ነው….ልጄ ለአለም የሚተርፍ በየዘርፉ ጥልቅ እውቀት ያለው ጂኒየስ ነው…ግን ያው አሞልቶ አይሰጥ አይደል.ጤናው ትልቅ እንቅፋት ሆነበት››
በሰማችው ነገር በጥልቀት አዝና‹‹ያን ያህል ከባድ ነበር ማለት ነው?›አለች..
ብዙ ብዙ ነገር እወሩ …እራት አብረው በሉ …ቡና ተፈልቶ ጠጡ አራት ሰዓት ሲሆን
‹‹አሁን እንግዲህ በዚህ ሰዓት አትሄጂም …የእንግዳ ክፍሉን ላሳይሽ ተነሽ›
‹‹እሺ ግን ..ከመተኛቴ በፊት ባየው ደስ ይለኛል፡፡››ፍላጎቷን አሳወቀች፡፡
ፕሮፌሰሯ‹‹አይ መጀመሪያ ክፍልሽን ላሳይሽ…ልብስሽንም ቀይረሽ ቢጃማ ነገር ልበሺና ከዛ ታይዋለሽ…ነይ ተከተይኝ››በማለት እየመራች ወwደምታድርበት ክፍለል ወሰደቻትና ለብሳ የምታድረውን ቢጃማ ሰጠጠቻት…በይ ለባብሺና ሄደሸ እይውeውየእሱ ክፍል አይጠፋሽም አይደል.ከዚህ ቀጥሎ ያለው ነው››
‹‹አረ አይጠፋኝም.››
‹‹እሺ ድህና አደሪልኝ››
‹‹እሺ ማዘር ደህና እደሪ››
ፕሮፌሰሯ አንደሄደች ለብሳ የዋለችውን ልብስ ጡት ማስያዣ እና ፓንት ሲቀር ሙሉ በሙሉ አወላለቀችና የተሰጣትን ቢጃማ ለበሰች..ከዛ የቢላልን ሁኔታ ለማወቅ በጣም ስለቸኮለች ብዙም ጊዜ ሳታጠፋ ክፍሉን ለቃ ወደ ቢላል ክፍል ተራመደች...ደረሰችና ገርብ ያለውን በራፍ ገፋ አድርጋ ገባች፡፡
መኝታ ቤቱ ስትጋባ የመጀመሪያዋ ነው…እንዲህ አይነት መኝታ ክፍል አጋጥሟት አያውቅም….በጣም ሰፊ ሳሎን እንጂ መኝታ ቤት አይመስልም….መሀከሉ ላይ መሬት የተነጠፈ ፍራሽ ይታያል….የመኝታ ቤቱ ወለል ከጣውላ የተሰራ ነው…የግድግዳው አራቱም መዓዘን ሙሉ ልክ እንደጥንታዊ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያኖች ግድግዳ በስዕል ተጠቅጥቋል…አይኗን ወደላይ ወደኮርኒሱ አነሳች፡፡ኮርኒሱ ከምን እንደተሰራ ማወቅ አልቻለችም….ምክንያቱም ሙሉው በስዕል የተሞላ ነው…ቤቱ ሙሉ በቀለም ሽታ ታውዶ ላለመደው ሰው ጭንቅላት ያዞራል፡፡ቢላል ከፍራሹ በአንድ ሜትር ራቅ ብሎ ወለል ላይ ተዘርሯል የለበሰው ልብስም ሆነ ፊቱ ጠቅላላ በተዘበራራቀ የቀለም ፍንጥርጣሪ ተሞልቷል፡፡ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ውስጥ ያለ ይመስላል፡፡
አይኖቾን ከእሱ አነሳችና ወደ ግድግዳው አማተረች፡፡ፊት ለፊት ግድግዳ ላይ ከተሳሉት በርካታ ስዕሎች መካከል ጎላ የሚለው የፕሮፌሰር ሰሎሜ ምስል ነው፡፡ወደሌለኛው ግድግዳ ፊቷን ስታዞር የእሷ ምስል ግማሹን ግድግዳ ሸፍኖታል.ይህ የእሷ ስእል አላለቀም…ገና በመሳል ላይ ያለ መሆኑን ያስታውቃል..ምን አልባትም እንዲህ ዝርግትግት ብሎ ባዶ ወለል ላይ ከመተኛቱ በፊት ሲስል የነበረው እሱን ይሆናል፡፡ …ሰውነቷን ውርር አደረጋት….ሄደችና ስሩ ደረሰች…በርከክ አለችና እጇን ጭንቅላቱ ላይ አሳረፈች፡፡
አይሰማትም ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ወስዷታል ወይም ጭልጥ ያለ መመሰጥ ውስጥ ነው፡፡እሷም እንደእሱ ባዶው ወለል ላይ በእሱ ትይዩ ተኛች…እጀቾን በአንገቱ አዙራ ደረቷ ላይ አጣብቃ አቀፈችው..ምንም አይነት እንቅስቃሴ አላሳየም….፡፡እንደእሳተ ጎመራ የሚጋረፈውን ትንፋሹን ወደውስጧ ስባ የእሷን ትንፋሽ ወደ እሱ ረጨችበት ….ሙቀቱን ወደሰውነቷ መጣ በማስገባት ግለቷን አጋራችው፡፡
ሲፈን የተሰጣትን የእንግደ ክፍል ከነጭሩሹኑ ዘንግታ ልክ ባለ 5 ኮኮብ ሆቴል ውስጥ ባለ መኝታ ቤት በተዘረጋ አልጋ ለይ ሰውነቷን እንዳሳረፈች አይነት ጭልጥ ያለ በሚያሳፍፍ ሰላም የተሞላ እንቅልፍ ነበር የተኛችው..ከእንቅልፎ ባና ዙሪያ ገባዋን ስታማትር የተኛችበት ቦታ አልበረም እራሷን ያገኘችው..እርግጥ እዛው ክፍል ውስጥ ነበረች፤ግን ደግሞ ወለሉ ላይ ሳይሆን ፍራሹ ላይ በትክክክል ትራስ ተንተርሳ ከወገቧ በታች አልጋ ልብስ ከወጋቧ በላይ ደግሞ ጡት ማስዣዋን ብቻ አድርጋ ..ፀጉሯ ብትን ብሎ ትራሱን አልብሶት ነበር ያገኘችው...ህልም ውስጥ እዳልሆነች ለማረጋገጥ አይኖቾን በደንብ አድርጋ አሻሸችና መልሳ ገለጠች….በፍራሹ ትክክል ዙሪያዋን ሀያ የሚሆኑ ሻማዎች ተለኩሰው እየበሩ ነው፡፡

ይቀጥላል....
6👍1
😘ነፍስ ስታፈቅር😘

🔥ክፍል 29
.
.

እሱ በግማሽ ሜትር ከፍራሹ ራቅ ብሎ ቆሞ ቁልቁል እሷን በትዝብትም በመደነቅም እያስተዋላት ነው፡፡

ከተኛችበት ለመነሳት ስትሞክር
‹‹እሺሺሺ››ጣቱን ከንፈሩ ላይ በማሰፈረፍ ያለምንም እንቅስቀሴ ባለችበት ቦታ እንድትሆን አሳወቃት፡፡
እንቅስቃሴዋን አቆርጣ ባለችበት ሆነችና‹‹ቢላል ምንድነው ይሄ .?ሰላም ነህ አንተ? ›ጠየቀችው፡፡

ከንፈሮችሽ በፀደይ ወራት ለመበላት እንደደረሰ የጎመራ ብርቱካን ይመስላል..አይኖችሽ ብርሀናቸውን ከዋከብት የተዋሱት ይመስላል …አፍንጫሽ ዝንፈት በሌለው የሂሳብ ስሌትና ትንግርት በሚያበስር የስነ.ከዋክብት ትንቢታዊ ጥበብ እንደተሰራ የግብፃችን ፕራሚድ አይነት ነው።

ፀጉርሽ ምድረ አራዊት ሁሉ ተሰብስበው የሚኖሩበትና አማዞን ደን በይው፡፡እንዲህ ሳይሽ ይሄ ቢሰተከካከል ብዬ ምንም እንከን ወይም ጉድለት ላገኝብሽ አልቸልኩም .አሁን ይታይሻል ያ ግድግዳ..?››

ወደ ጠቆማት ግድግደ ፊቷን አዞረች….የደነገጠችው አደነጋገጥ የተለየ ነበር….ቅድም ከመተኞታ በፊት የእሷ ስዕል እየተሳለበት የነበረበት ቦታ አሁን ሙሉ ነጨ ቀለም ተቀብቶ ጠፍቷል…

‹‹ምነው ለምን አጠፋሀው…?አሪፍ ነበር››
‹‹አይ አሪፍ አልነበረም..አሪፍ እንዳልነበረ ያወቅኩት አሁን አንቺ መጥተሸ እንዲህ ክፍሌ ተኝተሸ በተመሰጦ ሳይሽ ነው..በእውነት እደዛ አጨመላልቄ ልስልሽ ስለሞከርኩ ይቅርታ ›>
‹‹መስሎህ ነው እንጂ እኔ በጣም ወድጄው ነበር››

‹‹እኔ ደግሞ አልወደድኩትማ…ከአንቺ ምንም ነገር ሲያንስ ማየት አልፈልግም….የፀጉርሽ አንድ ዘለላ እንኳን ቢሆን ሲረግፍ ማየት አልችልም….ከዛ በላይ ደግሞ እንደዛ ያደረኩት እኔ ስሆን እራሴን ይቅር አልለውም፡፡››

ልብሱን ከወገቡ በላይ አወለቀ…ቁጭ አለ…ሻማዎቹን ማንሳት ጀመረ ..አንድ አስር የሚሆኑትን አነሳና ደረቱ ላይ ማንጠባጠብ ጀመረ፡፡ተስፈንጥራ ተነሳችን በጩኸት ሻማ የያዙትን እጇቹን በሁለት እጆቾ ጠርቅማ ያዘች..

‹‹ምን እየሰራህ ነው?እረፍ እንጂ››
‹‹መቀጣት አለብኝ…አንቺን አበላሽቼ ስዬ መቀጣት ሲያንሰኝ ነው››
‹‹የእኔን ስእል አይደለም ያበላሸህው ?ምቀጣህ እኔ ነኛ›
‹‹እሺ ቅጪኛ›

‹‹መጀመሪያ ሻማውን ልቀቅ››
እያቅማማ ለቀለቀላት…ተቀበለችውና ሁሉን ሻማዎች አጠፋቻቸው

‹‹እሺ ቅጪኝ..ምን ላድርግ..እራሴን ልግረፍ…?ወይ ታንቄ ልሙት?››
አረ በስመአብ በል…እኔ ነኝ ቅጣቱን የምወስነው..››በድንጋጤ ደንዝዛ አሁንም እየተንዘፈዘፈች ነው..ምን ትቅጣው..አዎ መጣላት

‹‹መልሰህ አስተካክለህ ትስለኛለህ››
‹‹ትክክል አዎ አስልሻለው….በይ ተነሽና ቅድም አስተኝቼሽ እንደነበረ ተስተካክለሽ ተኚ››

‹‹አይ አሁንማ ለሊት እኮ ነው…ነገ ተነገወዲያ ቀስ ብለህ ትስለኛለህ፡፡አሁን እንተኛ››


‹‹ተመልሰሽ ቅድም ባስተኛውሽ ቦታ ተመለሺ…እናም አንቺ የሰላም እንቀልፍሽን ሳትጨናነቂ መተኛት ትቺያለሽ..እኔ ግን አሁኑን መሳል መጀመር አለብኝ›› ብሎ ካለበት ቦታ ተነስ ወደቀለም ማስቀመጫ ጠረጵዛ ሄደና ከአንዱ የቀለም ቆርቆሮ ወደሌላው እየቀናነሰ ማስተካከል ጀመረ.. ከዛ ዝግጅቱን ሲጨርስ ቀለሞቹንና ብሩሹን ይዞ ወደ ጉድግዳ ሂደና አንዴ ተመሰጦ እሷን እያያተዋለ አንዴ አይኖቹን ጨፍኖ ከውስጡ ጋር እየተሟገተ በርካታ ደቂቃዎችን ወሰደ ...ከዛ .ለእሷ ሊገባት በማይችሉ መስመሮችና ቀለማት ግድጋድውን ማዳረሰ ጀመረ..


‹‹ወይ ጉዴ … ያንን የመሰለ ደንቅ ስዕል አበላሸውሽ ብሎ አጥፍቶ አንበሳ ወይም ከረከሮ ነገር አድርጎ ሊስለኝ ነው እንዴ.?ከረሷ ጋር ስትሟገት ሳተስበው ጭልጥ ወዳለ እንቅልፍ ውስጥ ገበች…
አንፀባራቂዎ የጥዋት ፀሀይ ግንባሯ ላይ ስትደንስ ነበር ከእንቅልፎ የባነነችው…ወይ ቅሌት አሁን በዚህ ሰዓት በክብር እንግዳ ማረፊያ ከፍል መገኘት ሲገባት እሷ ግን ጎረምሳ ክፈል ተኝታ ሲነጋባት ‹‹ምን አይነት ግምት ነው ሚወስዱብኝ?›› ብላ በርግጋ ተነስታ ስትቆም.ቢላለ እንደስልክ እንጨት ተገትሮ ሁለት እጆቹን አቆላልፎ አይኖቹን ግድግዳ ላይ ሰክቶ ያሰላስላል፡፡


‹‹ምንድነው ያደነዘዘው?›› ብላ እሷም ግድግዳው ላይ አይኖቾን ስትተክል ብርክ ያዛት…‹‹.ስንት ቀን ነው የተኛውት.?.›› እራሷን ይሄንን ጥያቄ ልትጠይቅ የቻለችው በግድግዳው ላይ ተስሎ ባየችው የ ራሷ ስዕል እጅግ እስክትደነዘ ድረስ በመመሰጦ ነው፡፡እንዴት ከስድሰት ባነሱ ሰዓቶች ይሄንን የመሰለ ነፍስ ያለው የሚመስል ስዕል መሰል ቻለ?


እውነትም እሁን ከምታየው ጋር ስታነፃፅረው ማታ እንደመጣች ያየችው የእሷ ስዕል የተበላሸ ነበር..ወደእሱ ተንቀሳቀሰችና አጠገቡ ደረሰች ተንጠራራችና ጉንጩን በጥልቅ ፍቅር ሰመችው..የሳመችውን ቦታ በእጁ እየዳበሰ ፈገግ አለ፡፡

ይቀጥላል.....
8
ልብ ወለድልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪኮች:
😘ነፍስ ስታፍቅር😘

🔥ክፍል 30

///

አሁን ከረፋዱ አራት ሰዓት አካባቢ ነው፡፡ሲፈንና ሄኖክ አባት ጋር የሆነ ቦታ እየሄድ ነው፡፡የሆነ እሷ የማታውቅበት ቦታ እየወሰዷት ነው፡፡
‹‹የእኔ ልዕልት የሆነ ቦታ አብረሺኝ እንድትሄጂ ፈልጋለው›› አሏት፡፡ ሳታቅማማ ተስማምታ ተከተለቻቸው፡ ፡ደግሞ እኮ ዛሬ በጣም የተጣበበ ፕሮግራም ነው ያላት፡፡ገና የውበት ሳሎን ትሄዳለች ምክንያም ዛሬ በጣም መዋብና መቆነጃጀት የሚጠበቅባት ቀን ነው….፡፡ለእለቱ የሚሆናት ልብስም ለመግዛት ወደቡቲክ ጎራ ማለቷ አይቀርም….እና ልክ 10 ሰዓት ሲሆን ልደቷን ለማክበር ወላጇቾ ቤት መገኘት የግድ ይላታል፡፡
በዚህ ሁለት ወር ውስጥ በየሰበባ ሰበቡ ከቢሮዋ መቅረት እና መዘናጋት አብዝታለች ቢሆን አያሳስባትም፡፡ የሲፈን የካምፓኒ አስተዳደር ስልት ከወላጆቾ የሚለየው በሰራተኞች ምልመላ ነው፡፡ ሲፈን በጣም ምርጥ የተባሉ ሰራተኞችን መቅጠርና የሚገባቸውን ምርጥ ክፍያ ጠቀም ካለ ቦነስ ጋር መክፈሏ የስኬቷ ሚስጥር ነው፡፡በተለይ ቁልፍ በሚባሉ የስራ ዘርፎች ላይ በአለምአቀፍ ደረጃ መወዳደር የሚችሉ በጣም ብቁና በስነ ምግባራቸውም ምስጉን ሰዎች ስላሏት በእሷ አለመኖር የሚበላሽ ነገር እንደሌለ በርግጠኝነት መናገር ትችላለች፡፡
የሽማግሌው ሪቮ መኪና ውስጥ ነው ያሉት፡፡ ሹፌር እየነዳ እሷና አሷቸው ከኃላ በዝምታ ተቀምጠው እየተጓዙ ነው…የትራፊክ መጨናነቀ ስላለ መኪናው እየቆመና እየተነሳ በተንቀራፈፈ ሁኔታ ነው እየተጓዘ ያለው፡፡
ዝም ብሎ ያለንግግር መቀመጡ ምቾት ስለነሳት እራሷን ቢዚ ለማድረግ ፈለገችና ቦርሰዋን ከፈታ አንድ ማስታወሻ ደብተር አዋጣች…ይሄ ማስተዋሻ ደብተር የእሷ አይደለም፡፡ሰርቃው ነው፡፡ያው የሰው ንብረት ካለፍቃድ መውሰድ ከሌብነት ውጭ ሌላ ምን ስም ይሰጠዋል?፡፡ ማስታወሻ ደብተሩ የቢላል ነው፡፡ጥዋት ከክፍሉ ስትወጣ ነው ማንም እዳላያት አረጋግጣ ቦርሳዋ ውስጥ ጣል ያደረገችው፡፡
እንደዛ በማድረጓ እሯሷንም በጣም አስገርሟታል፡፡‹‹ምን ፍለጌ ነው?›› ብላ እራሷን ጠይቃ ያገኘችው መልስ አስቂኝ ነበር፡፡
ገለጠችና ፊትለፊት የመጣላትን ገፅ ማንበብ ጀመረች
ጥር-3/2014
I wish i could give you a taste of burning fire of love.
There is a fire burning inside of me,
If i cry about it, or if i don`t,
The fire is at work, night and day.
People make clothing to cover their intellect.
But the heart of lover is shroud,
Inflamed in golden hues of love.
(Rumi)
እኔ የትኛው ነኝ…?፡፡እኔ ማለት አካሌ ነኝ…?፡፡እኔ ማለት ነፍሴ ነኝ…?፡ወይስ እኔ ማለት ነፍስና ስጋዬ በአንድነት ሲሆኑ ወይም በጥምረታቸው ጊዜ ያለኝ ህልውና ነኝ…?፡፡ማን ነው በእርግጠኝነት አንተማ ማለት ይሄ ነህ የሚለኝ…?፡፡እርግጥ አውቃለው አንተ ማለት የነፍስና የስጋህ ጥምረት ውጤት ነህ ብሎ በቀላሉ መመለስ ይቻላል ፡፡አዎ አምናለው ይህ መልስ ለሁሉም የሰው ልጅ ይሰራ ይሆናል ለእኔ ግን …? ለእኔማ አይመስለኝም›፡፡እኔ ማለት ነፍስና ስጋዬ እየተነጣጠሉ ለየብቻ በመኖር መልሰው ደግሞ የሚዋሀዱ ደግሞም ብዙም ሳይቆዩ የሚነጣጠሉብኝ ..አዎ እኔ እንደዛ ሁለት አንድም የሆንኩ ሰው ነኝ፡፡
አሁን በዚህን ሰዓት ነፍሴ ተመንጭቃ ከስጋዬ ተለይታ እየበረረች ነው፡፡አዎ በድን ስጋዬ ተጋድሜ በነበረበት ፍራሽ ላይ እናቴ የደረበችለትን ብርድ ልብስ እንደለበሰ ተሰትሮ አቅመቢስ ሆኖ ነፍሴን እየታዘባት ነው..ወይንም መስሎኛል..ነፍሴ በዚህ ውድቅት ለሊት እየበረረች ወደ ውዴ ጋር እየተጓዘች ነው….፡፡
እቤቷ …መኝታ ቤቷ ….የመላ ክፍሉ ጠረን ከውዴ አካል መንጭቶ በአየሩ በሚበተን ልዩ መአዛ ታውዷል…ነፍሴ በውዴ መኝታ በአየር ላይ እየተንሳፈፈች እየተመለከተቻት ነው…ውዴ ከቆዳዋ በሚወዳደር ልስላሴ ያለው ሀጭ በረዶ በሚመስል ብርድ ልብስ ግማሽ አካሏ ተሸፍኖ ግምሽ አካሏ ደግሞ ተራቁቷል….፡፡
አዎ ውዴ የለበሰችው ብርድ ልብስ ብቻ አይደለም ነጭ ….አንሰሶላውም ነጭ ነው…የበረሀ ሸንበቆ መሳይ አንገቷን ደግፎ ነዶ ፀጉሯን የተሸከመውም ትራስ ነጭ ነው…..እና የመኝታ ቤቷም ግድግዳ ሙሉ ነጭ ነው …ለነገሩ ለማንም የማይታየው ለእኔ ግን ማለቴ ለነፍሴ ጥርት ብሎ የሚታየው ልቧም ነጭ ነው….በአጠቃለይ ፍቀሬ ንፅህ አና ቅዱስ ነች …ይሄንን ፈጣሪ ፊትም ቆሜ መመስከር እችላለው…፡፡
እና ሰርስሬ ማለት በከፊል እርቃኗን የሸፈነውን ብርድ ልብስና አንሶላ በቀስታ ገልጬ ውስጥ በመግባት ደረቷ ላይ ልለጠፍ…እና ደግሞ ጡቶቾ መካከል ጭንቅላቴን ልቀብር እና በውስጥ ከልቧ ጠረኗን እየመዘመዝኩ ወደ ውስጤ ልሳብና ልሰክር እናም ደግሞ ጠይምና ልጥልጥ የደደረ ግን ደግሞ ልስልስ ጭኗን ፈልፍዬ በመሀከል ልሰምጥበት አሰብኩ..ይህን ሁሉ አሰብኩ…ግን ደግሞ ግማሽ ነኝ ለካ…..ይሄን ሁሉ ማየት… ይሄን ሁሉ ማሰብ ብችልም ለማድረግ ግን እቤት የተጋደመው አካሌ ያስፈልገኛል፡፡አካሌን ደግሞ በምንም አይነት ተአምር ዙሪያውን በአደገኛ አጥር የታጠረውን እና በፈርጣማና ነገረኛ ዘበኛ የሚጠበውን ግቢ አልፎ መግባት ይችላል……? በምንም አይነት ብልሀት..…?በተአምር አልፎ ቢገባስ በልፀዱ እጆቹ ይሄን አካል መንካት ምን አይነት ጨካኝ ነብስ ቢኖረኝ ነው ምፈቅድለት .. …?ጭካኔ ነው ጭንቅላቴን ጡቶቾ ውስጥ መቅበር ብዬ መመኘትስ እንደው የነፍስ ምኞት ሆኖ ነው እንጂ በፍቅር ረሀብ የተጠበሰ ጨጎራ የሚያመነጨው አሲድ ትንፋሽ ሆኖ ሲወጣ ይንን የመሰለ የውዴን ናርዶሳዊ መዓዛ ምን ያህል ይበክለዋል..…?…አካሌ ከአካሏ ጋር ቢጣበቅ እና እግሮቼ ጭኗን ፈልቅቀው ቢገቡ..ስንት አጥንቶቾን ይሰባበራሉ..…?ምን ያህሉስ የቆዳዋ ክፍል ይላላጣል…..…?ወይ!!! ማይሆነውን…ወዴ……. በእኔ የማትነካ ….ግን ደግሞ በማየት ብቻ ምራቄ በአፌ ሞልቶ እኪንጠባጠብ የምጐመዡላት የፀደይ አበባ ነች፡፡አዎ ምንም አትጠራጠሩ ውዴ የእኔ ፍቅር ነች ….ግን ደግሞ የነፍሴ ፍቅር ….ለአካሌ ያልተፈጠረች…….ለነፍሴ ብቻ የተገባች…
ሳታስበው እንባዋ እየተንጠባጠበ የምታነበው ማስታወሻ ደብተር ላይ ዱብ ዱብ እያለ ነበር ፡፡ከጎኗ የተቀመጡት የፍቅረኛዋ አባት ሽማግሌ ከደስታ ውስጥ እየሾለከ የሚወጣውን የደስታ እንባ ስታነባ በግማሽ ግርምት ተመለከቷትና እና ምንም ሳይሏት ወደዝምታቸው ተመለሱ…
ሁለተኛውን ገፅ ከፈተችና ማንበቧን ቀጠለች፡፡
.
.
.
ጥር 23/2014
የበረሃ ዛፍ እንደሚያዝን ታውቂያለሽ አይደል..አዎ ያዝናል፡፡ምክንያቱም የበረሀ ኑሮ ከባድ ነው…በተለይ ውሀ ጥሙ ልብን በድርቀት አሟሾ ጉሮሮን በንቃቃት ይሰነጣጥቃል፡፡በዛን ጊዜ ታዲያ እንዳልኩሽ የበረሀ ዛፍ ያዝናል፡፡ሲያዝን ደግሞ ያለቅሳል..እንዴት ዛፍ ያለቅሳል አልሺኝ ….?ግድ የለሽም ያለቅሳል…፡፡ሲያለቅስ እንባው አየተንጠባጠበ በውጫው የግንዱ አካል ላይ ይዝረከረካል፡፡..ከዛ በቆይታ ንፍሳና ሙቀት በመፈራረቅ ሲወለውለው ቀስ በቀስ ይጠጥራል፡፡በዛን ጊዜ እጣን የሚል ስም ይወጣለታል፡፡
1
የሰው ልጅ ደግሞ ከግንዱ አካል ላይ ያንን እጣን እየቦጨቀ ይወስድና በፋመ የከሰል እሳት ላይ ሲበትነው የሚትጎለጎል ጭስ ከውስጡ እየወጣ ወደላይ ..ወደ ሰማየ ሰማየት ያርጋል፡፡እና የዛ ጭስ ዋና ተግባሩ ቅን የሆኑ መንፈሳዊያንን ሰማያዊ ፀሎት በጀርባው አዝሎ ከፈጣሪ ዘንድ አድራሽ ሰረገላ ሆኖ ማገልገል ነው፡፡
እና አንቺ የተፈጥሮ እጣን ነሽ …በመአዛው የሚያውድ በሚትጎለጎል ጭሱ ልብን የሚሰውር አይነት ልዩ የበረሀ እጣን..እና የእኔን የብቻዬን ፍቅር ውዳሴ በስውር አዝለሽ ከፃባኦት እመንበሩ ፊት የምትዞሪ ቅዱስ ጭስ ነሽ፡፡እና ዘወትር መመሰጫዬ ነሽ፡፡..
///
ሳታስበው ልቧን ደከማት… ማስታወሻ ደብተሩን ከደንችና ወደነበረበት ቦርሳ መለሰችው….እየሄዱ ያሉበት ቦታ ደረሱና መኪናዋም ቆመች፡፡
ዙሪዋ ስታይ ያሉት ዮሱፍ ቤተክርስቲያን ነው፡፡ግራ ገባት፡፡ ሽማግሌው ቀድመዋት ወረዱ ተከተለቻቸው፡፡ሹፌሩ ወደ ኃላ ሄደና ኮፈኑን ከፈተና እቃ አወረደ ..አበባ ነው….ተቀበሉት፡፡፡ወደመቀብር ስፍራ እየመሩ ወሰዷት፡፡


ይቀጥላል...
9
😘ነፍስ ስታፈቅር😘

🔥ክፍል 31
.
.
ወደመቀብር ስፍራ እየመሩ ወሰዷት፡፡በሰልፍ ከተደረደሩትና በእምነበረድ ሀወልት ካሸበረቁት መአት ሀውልቶች መካከል ወደአንዱ ተጠጉ፡፡አብራቸው ተጠጋች፡፡ የያዙትን አባባ በክብር አስቀመጡ፡፡ ከለበሱት ካፖርት ኪሳቸው ሻማና ክብሪት አወጡና ሻማውን ለኮሱትና ከሀውልቱ አንድ ተርዝ ላይ አስተካለው አስቀመጡት፡፡
ሲፈን በተፈጥሮዋ የቀብር ሰፍራ ሚባል አትወደም..ገና ስታስበው ሽክክ ነው የሚላት፡፡ በመጀመሪያ ወደእዚህ ቦታ ይዘዋት እንደሚመጡ ነግረዋት ቢሆን ኖሮ ምን አልባት የሆነ ምክንያት ፈጥራ አምቢ ልትላቸው ትችል ነበር፡፡
ወ.ሮ አፀደ ገ/መስቀል
(12/2/2033 - 17/7/1990 )
ሀውልቱ ላይ የተለጠፈው ፎቶ ፍቅረኛዋ ሄኖክ ቤት እግሯ በረገጠበት ቀን ነበር ከአንቺ ጋር ትመሳሰላለች ብለው ያሳዮት ፡፡
አስር ለሚሆኑ ደቂቃ ሁለቱም በዝምታ በየራሳቸው ሀሳብ እንደተዋጡ ከሳለፉ ቡኃላ ሽማግሌው ማውራት ጀመሩ.
‹‹የእኔ ልዕልት .እዚህ ለምን ይዤሽ እንደመጣው ታውቂያለሽ?››
‹‹ኸረ በፍፅም››
‹‹ዛሬ ሙት አመቷ ነው…ከሞተች ሀያ አምስት አመት ሆናት፡፡››
‹‹ያሳዝናል..እግዜያብሄር ያፅናዎት››
‹‹አፅናንቶኛል…አመሰግናለው፡፡…አሁንም ለምን ይዤሽ እንደማጣው ኣላወቅሽም?››
‹‹ያው ብቻዎትን ከሚሆኑ ብለው መሰለኝ..››
‹‹አይ እንደዛማ ቢሆን ከልጆቾ ጋር እመጣ ነበር፡፡››
‹‹እንግዲያው እኔ እንጃ…››
‹‹ከእዚህ ቀደም እሷ ማለት አንቺ ነሽ ስልሽ አላመንሺም አይደል?፡፡››
‹‹አረ አምኜያለው በጣም ነው የምንመሳሰለው››ፎቶዋን በትኩረት እያየች መለሰችላቸው፡፡
‹‹መመሳሰል አይደለም…እሷ የሞተችው በዛሬው ቀን ..ከሀያ አምስት አመት በፊት ነው….››
‹‹እና ?››
‹‹እና አንቺስ የተወለድሽው መቼ ነው?ዛሬ ስንት አመትሸ ነው?››
ደነገጠች….እስከአሁን ነገሩን ለማገናኘት አልሞከረችም ነበር..እንዴትስ ብላ በምን ምክንያት እንዲህ አይነት የእብደት ስሌት ውስጥ እራሷን ልታስገባ ትችላለች?፡፡››
‹‹አዎ እኔም ዛሬ ልደቴ ነው፡፡ቀኑ አንድ ነው፡፡››
‹‹ቀኑ ብቻ አይደለም አመቱም….ልክ እሷ ሞታ አባትሽ ቤት ፌሽታና ድግስ በነበረበት ቅፅበት እኔ ቤት ደግሞ ፅልመት የወረሰው ጭለማና በዋይታ የታጀበ ሀዘን ነበር፡፡››
‹‹የሚገርም መገጣጠም ነው››አለች የእውነትም እየሰማችው ባለው ታሪክ እጅግ ተመስጣ፡፡
‹‹አይ እስከአሁን የሰማሽው አይደለም የሚገርመው…››
‹‹ከዚህ የበለጠም የሚያስገርም ነገር አለ?››
‹‹አዎ….››አሉና ከለበሱት ግዙፍ ጥቁር ካፓርት ኪስ ውስጥ ሁለት ወረቀት አወጡና አቀበሏት፡፡
‹‹ምንድነው?››
‹‹የህክምና ማስረጃ ነው….አንዱ የሞት አንዱ የልደት ሰርተፍኬት፡፡ሁለቱም ከሚሊኒክ ሆስፒታል ነው የተገኙት…አንቺም እውነትነቱን ነገ ሄደሽ ማረጋገጥ ትቺያሽ፡፡
‹‹ምንድናቸው?››አዕምሮዋ ወደ መደንዝ ላይ ስለሆነ ብታነብም ሊገባት አልቻለም፡፡
‹‹አንቺም የተወለድሽው እሷም የሞተችው አንድ ሆስፒታል ነው፡፡ቀኑ አንድ ነው፡፡እይው ሰዓቱም የእሷ ከምሽቱ 8.25 ደቂቃ ሞተች ሲል ያንቺ ከምሽቱ 8.26 ተወለደች ይላል፡፡
‹‹የአንድ ደቂቃ ልዩነት ብቻ?››በድንጋጤ አፎን ከፍታ ጠየቀች፡፡
እሱም በእኔ ግምት ምን አልባት መረጃውን ያሰፈሩት ሀኪሞች ሰዓታቸውን ሲሞሉ የተፈጠረ ልዩነት ሊሆን ይችላል፡፡እና የባለቤቴ ነፍስ ከአካሏ ተነጥላ ወደማደሪያዋ አላረገችም.. እዛው በቅርብ ባገኘቻት ወደእዚህ ምድር አዲስ መጪ በሆነች ህፃን ውስጥ ገብታ ነው የተዳበለችው፡፡››
‹‹በእውነት እንደዛ ብለው ያምናሉ፡፡›
‹‹በደንብ….ደግሞ አረጋጥልሻለው››
‹‹እንዴት አድርገው፡፡›
ወደቤት እንሂድ እና የእሷ የብቸዋ የሆኑ የሚስጥር እቃዎች አሉ፡፡ እነዛን እንድታይ እና እድትመረምሪ አደርግሻለው ..ስለእነዛ ነገሮች ምንም ትውስታ ከሌለሽ ወይም ምንም ስሜት ከልተሰማሽ እኔ ተሳስቼያለው ማለት ነው፡፡ያልኩት እውነት ከሆነ ደግሞ እራስሽ ትመሰክሪያለሽ፡፡
‹‹አይ ሌላ ቀን ይሁንልኝ....ዛሬ እንደሚያውቁት ልደቴ ነው….ቤተሰቦቼም ይጠብቁኛል….እኔም ደግሞ ከዚህ በላይ የተወሳሰበ ነገር ለመስማት ዝግጁ አይደለውም፡፡
‹‹እሺ የእኔ ንግስት …እንዳልሽ…እኔ እዚህ ትንሽ ቆያለው ሹፌሩ የምትፈልጊው ቦታ ያድርስሽ››
‹እሺ ጋሼ፣..ልደቴ ላይ አትገኝም እንዴ?››
‹‹አይ ይቅርብኝ..የሙት አመትሽ ላይም ልደትሽ ላይም በአንድ ቀል መገኘት ይበዘባኛል..መቋቋም አልችልም››
‹‹እሺ ቸው ጋሼ….ሸሞኑን እቤት መጥቼ አገኝሀለው››
‹‹እጠብቅሻለው የእኔ ንግስት፡፡››
መኪናውስጥ ገብታ በዝምታ መጓዝ ጀመረች‹‹..ምን አይነት ጉድ ነው.?እንዴት ባለ ተአምር ነው እንዲህ ዙሪያዬን በእብዶች ልከበብ የቻልኩት?››ስትል ተብሰከሰከች፡፡.የሽማግሌው አካሄድ በጣም አስፈርቷታል፡እሺ እሳቸው እንዳሉት ትክክለ ናቸው ልበልና ልመን..እኔ ማለት ከሟች ሚስታቸው ጋር አንድ አይነት ሰው ነኝ ልበል…ያ ወዴት ያመረናል..?ከሄኖክ ጋር ያለኝስ የፍቅር ግንኙነት መጨረሻው ምን ይሆናል….?ልጄን ነው ማለት ነው የማገባው…?እሷቸውስ የልጆቼ እናትና የእኔ ፍቅር ነሽ…እና አሁንም እንደዛነው መቀጠል ያለበት ቢሉኝስ…?››
ሹፌሩ ሰምቶ ወደኃላ አንገቱን በመዞር እስኪያያት ድረስ በረጅሙ የጭንቀት ትንፋሽ ተነፈሰች..ከዚህ በፊት ‹‹ከሄኖክ ጋር ባትጋቢ እንኳን መኖሪያሽ ይሄ ቤት ነው››ያሏት ንግግር ምን ለመለት ፈልገው እንደሆነ ትርጉሙ አሁን ነው የገባት.እና ስለገባት ደግሞ በጣም ፈራች…ህይወቷ ካሰበችው በላይ እንቀቆቅልሽና የተወሳሰበ እየሆነባት ነው፡፡


ይቀጥላል.....
5
ነፍስ ስታፈቅር

🔥ክፍል 32


///
በጥዋቱ የቀብር ቦታ ገጠመኞ በጣም መደናገጧን ሚያሳውቀው ከሳምንት ጀመሮ ስታቅደው የነበረቸውን ዛሬ ጥዋት ከእንቅልፎ ስትነሳ ጀምሮ አንድ ሁለት ብላ እከናውነዋለው ካለቻቸው ተግባሮች መካከል ሩቡንም ሳትፈጽም ነው ወደ ቤተሰቦቾ ቤት ልደቷን ለማክበር መሄጃ ሰዓቷ የደረሰባት፡፡ለምሳሌ ፀጉር ቤት ሄዳ ፀሯን መሰራትና መዋዋብ ዋነኛ እቅዶ የነበረ ቢሆንም ከፍቅረኛዋ አባት ጋር ዬሴፍ መቃብር ቦታ ከተገኘች ቡኃላ ያንን ለማድረግ ምንም እንጥፍጣፊ ሞራል ስላጣች እቤቷ ገብቷ መኝታ ቤቷን ዘግታ በአልጋዋ ላይ ስትገለባበጥ ነው የዋለችው፡፡..ሰዓቱ ደርሶባት ልትሄድ ስትል በራሷ የተቻላትን ያህል እራሷን ለማሳመር የሞከረችው..፡፡
ለእለቱ የሚሆን አዲስ ልብስም አልገዛችም ..ያ ግን ብዙም አሳሳቢ ነገር አልሆነባትም ፡፡ …ገዝታ ከአንድ ቀን በላይ ያለበሰቻው ከደርዘን በላይ አዲስ የሚባሉ ልብሶች ቁምሳጥኗ ውስጥ ስላሏት ከእነሱ መካከል አንዱን መርጣ ለበሰች፡፡
ወላጆቾ ቤት ስትደርስ ያው እንደተለመደው ሙሽራ የሚወጣበት ቤት መስሏል፡፡ ዘመድ ወዳጅ ድግሱን ለማሳመር ከወዲያ ወዲህ ይሯሯጣሉ…አናትዬው ወገቧን በመቀነቷ አስራ ሁኔታዎችን ለመቆጣጠር ከኪችን ሳሎን ትንጎራዳለች፡ድግሱን ለማሳመር ተብለው በልዩ ሁኔታ የተቀጠሩ ከ8 በላይ የሚሆኑ ዩኒፎር የለበሱ ምግብ አብሳዬችና አስተናጋጆችም ኃላፊነታቸውን ለመወጣት ተፍ ተፍ እያሉ ናቸው፡፡
አባትዬው ሙሉ ሰማየዊ ሱፋቸውን ለብሰው በክብር ቦተቸው ተቀምጠው የእለቱን እንግዶቻቸውን ለመቀበል ዝግጅታቸውን አጠናቀው በር በሩን ያያሉ፡ሲፈን በውስጧ ነፍስ ዘርቶ ሲቦጫጭቃት የዋለውን ዛሬ ከፍቅረኛዋ አባት የሰማችው ግራ አጋቢ ሀሳቡ ሙሉ ስሜቷን ያጨለመው ቢሆንም ወላጆቾ ጋር ከደረሰች ቡኃላ ግን እንደምንም እራሷን ተቆጣጥራ ደስተኛ ለመምሰልና ከእለቱ ሁኔታ ጋር እራሷን ለማሳማማት በመጣር ላይ ነች…፡፡
..አስራ አንድ ሰዓት ሲሆን ከተጠሩት እንግዶች መካከል አብዛኛው ተገኝተው ነበር፡፡አብዛኞቹ ተጋባዦች በየአመቱ የሚጠሩ ዘመድአዝማድና ቤተኞች ናቸው፡፡ የተወሰኑት ደግሞ ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚካፈሉ አሉ፤ከእነዚህ ውስጥ አብዛኞቹ በራሷ በሲፈን የተጋበዙ ናቸው፡፡የመስሪያ ቤቷ ሰረተኞች…በዚህ አመት በተለያዩ የስራ አጋጣሚዎች ተዋውቃቸው በጣም የቀረበቻቸው ሰዎች ፍቅረኛዋ ሄኖክ (እሱም ለመጀመሪያ ጊዜ ይሄንን ዝግጅት መካፈሉ ነው)፡፡አሁን ሁሉ ነገር ተጠናቆ ዝግጅቱ ሊጀመር ነው፡፡ግን ሲፈን ከጠረቻቸው ወሳኝ ሰዎች መካከለ እስከአሁን ያልደረሱ አሉ..አዎ አይኗን የሳሎኑ በራፍ ላይ ተክላ እየጠበቀች ያለችው ቢላልንና አናትዬውን ነው፡፡ለምን እንደሆን ባይገባትም የእዚህ ዝግጅት ቁጥር አንድ ተመራጭ ተጋባዥች በእሷ በኩል እነሱ ናቸው፡፡ያ ማለት እነሱ ከቀሩ ውስጧ ቀብራው የነበረው መከፋት ሌላ ተጨማሪ መደበት ይታከልበትና ስሜቷን እንዳትቆጣጠር ይፈታተናታል ማለት ነው፡፡
‹‹ጎሽ ›አለች፡፡የሳሎኑ በረፍ ተከፈተና በልዩ የአፍሪካዊያን ባህላዊ አለባበስ አጊጣ ፕሮፌሰሯ ወደውስጥ ገበች፡፡ ግዙፍን ሳሎን ሞልተውት ያሉ ከ40 በላይ ሰዎችም አይኖች ፕሮፌሰሮ ላይ ተንከራተቱ፡፡ሲፈን ግን ከፕሮፌሰሯ ቡኃላ ሌላ ሰው ለማየት ነበር አይኖቸ እየባዘኑ የነበሩት፤ ግን ምንም ሰው ከኃላ የለም፡፡ ከነበረችበት ቦታ ተነሳችና ወደፕሮፌሰሯ ሄደች፡፡የሞቀ ሰላምታ ከተቀበለቻት ቡኃላ የምትቀመጥበት ምቹ ቦታ መርጣ ሰጠቻት…ከዛ ወደጆሮወ ጎንበስ ብላ‹‹ቢላልስ?›ስትል ጠየቀች፡
‹‹አይ…እሱ እንደዚህ አይነት ቦታ መምጣት በጣም ይከብደዋል፡፡››
‹‹ቢሆንም ለእኔ ሲል ቢያደርገው ደስ ይለኝ ነበር››አለች በቅሬታ፡፡‹‹ቆይ መልዕክት ልኮልሻል ››ብላ ከባርሳዋ ውስጥ በሚያምር መጠቅለያ ተጠቅልሎ የታሸገ አንስተኛ ፖስተ መሰል ነገር ሰጠቻት፡፡‹‹ምን ይሆን?››እዛው ቀደሽ እይው የሚል ስሜት ተፈታትኗት ነበረ ..እንደምንም ነው የተቆጣጠረችው፡፡‹‹አመሰግናለው ብላለች ይበሉልኝ ፕሮፌሰር.እና ደግሞ እርሷ ስለመጡ ትልቅ ክብር ተሰምቶኛል…ፕሮፌሰር ››
‹‹እሱን ነገ እራስሽ ስታገኚው ታመሰግኚዋለሽ .አሁን ወደእንግዶችሽ.ተመለሸ ››
ሲፈን‹‹እሺ››አለችና ወደመቀመጫዋ ተመሰለች፡፡ፕሮግራሙ ተጀመረ ..ከቁመቷ ብዙም የማይተናነስ በስሟ ተጌጧ የተሰራ ባለደረጃ ኬከ ተቆረሰ… የተለኮሱት ሻማዎች ጠፉ….ደማቅ ባለብዙ ቀለም ርችቶች ተንጣጡ…ሁሉም ያመጣውን ውድና ልዩ ስጦታዎች በየተራ ለባለልደቷ አበረከቱላት…የተጠሩት እድምተኞች ለአይን እስኪታክት ድረስ ከተደረደሩት የቢፌ ምግብ ያሰኛቸውን አይነትና የሚችሉትን ያህል እያነሱ ተመገብ የመረጡትን መጠጥም እያስቀዱ መጠጣት ቀጠሉ
እንድ ሰዓት ሲሆን አባትዬው በዝግታ ከተቀመጡበት ተነስተው ድምፃቸውን አሞሹ… ሁለት ሶሰት ሆነው እዚህም እዛም ግሩፕ ወሬ ይዘው የነበሩት የባለልደቷ ታዳሚዎች ሁሉ ሀሳባቸውን ሰብስበው በጸጥታ ማዳመጥ ጀመሩ፡፡
አዛውንቱ አባቷ በሚቆራረጥ ሻካራ ድምፅ ንግግራቸውን ቀጡሉ
‹‹ልጄ የእኔ መላዐክ…እኔ አባትሽ እንዲህ አይነት ሀያ አምስት የሚሆኑ ልዩ ቀናትን እንዳከብርና አንቺን ለሰጠን አምላክ ምስጋና እያቀረብኩ እንድደሰት ስላደረግሺኘ አመሰግናለው…ይሄ ልደትሽ በእዚህ ቤት የመጨረሻው እንደሆነ ሳውጅ ሀዘን እየተሰማኝ ነው፡፡››
‹‹እንዴ አባ ለምን… .መደገሱ ሰለቸህ እንዴ?››ከንፈረሯን በኩርፊያ ወደፊት አስረዝማ ተነጫነጨች፡፡
‹‹አይደለም የእኔ መላአክ…ከአሁን ወዲህ የአንቺን ልደት የመደገሱም ሆነ የማክበሩ ሃላፊነት የባለቤትሽ ስለሆነ ከሀያስድስተኛ የልደት በአልሽ ጀምሮ የሚከበረው በገዛ ቤትሽ ባለቤትሽ ባለበት ነው፡፡የዛን ጊዜ እኔና እናትሽ ደጋሾች ሳንሆን ተጋባዝች ነው የምንሆነው፡፡››አዎ ትክክል ብለዋል ጋሼ...ትክክል ነው ቤቱ ተንጫጫ…ሲፈን አቀረቀረች …ሄኖክ ባለበት በደስታና በጉጉቱ ተቁነጠነጠ
በሉ …ሁላችሁም ስለመጣችሁ እግዚር ይስጥልኛ ….ተደሰቱ .ሽማግሌ ከዚህ በላይ ለመቆየት አቅም ስለማይኖረው ፍቀዱልኝና ልለያችሁ፡፡››
‹‹ይሂዱ ጋሼ ይሂዱ እናመሰግናለን፡፡››እቤቱ በአንድ ድምፅ ፍቃድ ሰጣቸው፡፡ሲፈን አባትየውን ጉንጭ በምስጋና ስማ ወደክፍላቸው ከሸኘቻቸው ቡኃላ ወደታዳሚው በመመለስ ለሁሉም እንዲሰማ ድፆን ከፍ አድርጋ መናገረ ጀመረች
‹‹እንግዲህ ሁሌ እንደሚደረገው እዚህ ያለውን የልደት ዝግጅት ተጠናቋል.. ሁላችንም እንዳለን ሳንበታተን መዝናናት ጭፈራ ወደተዘጋጀበት ሰፍራ ተያይዘን እንድንሄድ በክብር እጠይቃለው…አይዞችሁ እሩቅ አይደለም…፡፡
አርባ ምናምን ከነበሩት ታዳሚሆች መካከል ትላልቅ አዛውንቶችና የተወሰኑ ሚቸኩሉ ሰዎች ይቅርታ እየጠየቁ ከዛው ተስናብተው ወደቤታቸው በመሄድ 23 ብቻ ተያይዘው ለጭፈራ ባንድ ተዘጋጅቶ ወደሚጠብቃቸው ሆቴል ተጓዙ፡፡ከ23ቱ ሰዎች መካከል ይመጣሉ ብላ ያልጠበቀቻቸው ሁለት ሰዎች ተገኝተዋል፡፡ የመጀመሪያው ፕሮፌሰሯ የቢላል እናት ነች፡፡ያ በመሆኑ በጣ ተደስታለች፡፡ሌላው ደግሞ አቶ ወልደገብርአል ናቸው ..ቢሮዋ ድረስ ሄደው አሜሪካ ያለውን ልጃቸውን እንድታገባው የጠየቆት….የእሷቸው መገኘት ምቾት አልሰጣትም..‹‹ነገር ፍለጋ ካልሆነ በስተቀር በስልሳ ምናምን አመታቸው ቡጊ ቡጊ ሊጨፍሩ ነው እንዴ?››ስትል በውስጧ አጉረመረመች…እርግጥ ሌላው አግቢኝ ብሎ የጠየቃት ይበልጣል የተባለው የአባቷ ወዳጅም ከ23 መካከል ይገኛል...የእሱ ያልገረማት በመጀመሪ የ40 አመት ጎልማሳ ስለሆነ ሲሆን ሌላው ጭፈራና ዳንኪራ ባለበት እሱን አለማግኘት የማይታሰብና በጨፋሪነቱ ሀገር
2👍1
ያወቀው የድሮ አራዳ በመሆኑ ነው፡፡ቀድሞውንም ይሄ ሰውዬ የመጀመሪያው የልደት ፕሮግራም ላይ ከተገኘ ሁለተኛውንም እንደማይቀር እርግጠኛ ነበረች፡፡
እንደውሀ የሚረጨው መጠጥ መድረክ፤ የሞሉት ደናሾች ፤በየተራ ማይኩን ሚጨብጡት ግማሸ ደርዘን የሚሆኑ ወንድና ሴት ድምፃዊያኖች ፕሮግራሙን ልዩ አድረገውታል፡፡ሲፈን ውልቅልቅ እስክትል ድረስ ነው የደነሰችው..እያንደንዱ ሰው ከእሷ ጋር አብሮ ለመደነስ ስለመሚጠየቋት ሁሉንም ላለመሳቀየም ስትል በየዘፈኑ እየተነሳች መውረግረግ ግዴታም ጭምር ስለሆነባት ድክምክም ብላለች፡፡
ሶስት ሰዓት ላይ አንዱ ዘፈኝ ስራውን አቅርቦ በመጨረስ ከመድረክ ወርዶ ሌለኛው እስኪተካው ባለው ክፍተት ይበልጣል ተንደርድሮ ወደመድረክ ወጣና ማይኩን ጨበጠ…
‹‹.አንዴ አንዴ…››ድምፅን ከፍ አድርጎ ተናገረ…. ሁሉም ወሬቸውንም ሆነ እንቅስቃሴያቸውን አቁመው በፅሞና ለማዳመጥ ዝግጁ ሆኑ...
ዛሬ በአለም ላይ እጅግ ውብ እና ቆንጆ የሆነችን ልጅ ልደት እያከበርን በመሆናችን እንኳን ደስ ያለን…እኔም በጣም ደስ ብሎኛል፡፡››.ሁሉም በጭብጨባ ንግግሩን አደመቁለት….ሲፈን ምኑም አላማራትም……ሄኖክን ስታየው አንዴ መድረክ ላይ ሆኖ ሚዘላብደውና አንዴ ደግሞ እሷን እያየ ይቁለጨለጫል….ሽማግሌው ወልደገብርኤል እንደጎረምሳ ለመደባደብ በሚመስል ስሜት አይኗቻቸውን አጉረጥርጠው የኮታቸውን እጄጌ ወደላይ እየሰበሰብ ነበር
ይበልጣል ማይኩን በእጁ እንደጨበጠ እያወራ መድረኩን ለቆ ወረደ …‹‹አንቺ በእውነት ልዩና ማራኪ ሴት ነሽ..ወላጆችሽ ብቻ ሳይሆኑ ሀገርሽም ትኮራብሻለች…
ወደ እሷ በጣም እየተጠጋ ነው፡፡
‹‹….እኔ ደግሞ ከወላጆችሽም ሆነ ከአገርሽ በላይ እኮራብሻለው..በጣም አፈቅርሻለው….እባክሽ ባለቤቴ ትሆኚያለሽ?፡፡››ማይኩን ወለሉ ላይ አስቀመጠና ቀለበቱን ከማስቀመጫው አውጥቶ ወደእሷ ቀሰረ…
በድንጋጤ በርግጋ ከተቀመጠችበት ተነሳች...አይኖቾ ፈጠዋል….ከመናደዷ ብዛት ያን ሁሉ ሰዓት ስትደንስ ያላላባት አሁን ያልባት ጀመር፡፡በሆቴሉ ያሉ ሰዎች ሁሉ ምን ሊፈጠር ነው በሚል ጉጉት ትንፋሻቸውን ውጠው ሁኔታውን እየተከታተሉ ነው፡ሄኖክ ግን ኮሮና ይዞት የመጨረሻው የጣር ደረጃ ላይ እንዳለ ሰው መተንፈስ ሁሉ አቅቶት እየቃተተ ነው፡፡.ኪሱ ውስጥ እሱም ተመሰሳዩን ሊያደርግ ያዘጋጀውን ቀለበት በማፍትልተል የሚያደርገው ጠፍቶት ባለበት ደንዝዞ ቆሟል….ፕሮፌሰሯም ያልጠበቀችው ነገር ነው የሆነባት...ሁኔታውን እንዳየች ወዲያው ልጇ ለዚህ ሁኔታ የሚሰጠው መልስ ምን አይነት እንደሆነ መገመት ባለመቻሏ ብርክ ይዞታል፡፡
ሲፈን ትግስቷን አጣችና በሚርገበገበ ድምፅ መናገር ጀመረች‹‹አንተ ትልቅ እና የሰለጠንክ ሰው አይደለህም እንዴ…?በይሉኝታ እሺ ትለኛለች ብለህ እንዴት ነው ያሰብከው?፡፡እንዲህ ለመንበርክ እኮ ቀድመህ እኔ ላንተ ያለኝ ስሜት ላይ እርግጠኛ መሆን አለብህ…?ለዛውም እንደምታፈቅረኝና ልታገባኝ እንደምትፈልግ የጠየቅከኝ ጊዜ እኮ አክብሬህ በጨዋ ደንብ እንደማላፈቅርህና መቼም እንደማይሆን ነገሬህ ነበር..አሁን ተነስና ከዚህ ሆቴል ውጣልኝ….››.
በዛ ቅፅበት አቶ ወልደገብርኤል ከነበሩበት እየተንደረደሩ መጥተው አንገቱን አነቁትና በዛ ግዙፍ ሰውነታቸው ወደላይ በማንጠልጠል አርገፈገፉት ..‹‹ዝም በይው ይሄን ቅሌታም እኔ ነኝ ልኩን ማስገባው..››እያሉ አንጠልጥላው እየገፈታተሩ ይዘውት ከሆቴል ወጡ…
ሲፈን እንደምንም እሯሷን አረጋጋችና መሬት የወደቀውን ማይክ አንስታ ለሁሉም እንዲሰማ አድርጋ መናገር ጀመረች
‹‹ወዳጆቼ ለተፈጠረው ነገር ይቅርታ….ይሄ ሰውዬ ከዚህ በፊት እንደሚሚፊቅረኝ እና ሊያገባኝም እንደሚፈልግ ጠይቆኝ ፍቅረኛ እንዳለኝና ላገባው እንደማልችል በጨዋ ደንብ ነገሬው ነበር….እሱም የተረዳኝ ነበር የመሰለኝ..ዛሬ በልደቴ ላይም የተገኘው የአባቴ ወዳጅ ስለሆነ እና ከዚህ በፊትም ይገኝ ስለነበረ ዛሬም ተመሳሳዩን እንዳደረገ ነበር ያሰብኩት፡፡፡ ለማንኛውም ለተፈጠረው ያለመግባባት ሁላችሁንም ይቅርታ እጠይቃለው…..እግረመንገዴን ፍቅረኛዬ እዚህ በመካከለችን ስላለ ለሁላችሁም ላስተዋውቃችሁ…ሄኖኬ. አንዴ ከመቀመጫህ ብትነሳና ወደእዚህ ብትመጣ.
ያልጠበቀውን ነገር ስለተናገረች ቅድም ከደነገጠው በላይ ደንግጦ ከተቀመጠበት ተነተነሳ ወደእሷ መራመድ ጀመረ..ቤቱ በጭብጨባ ደመቀ..ስሯ ደረሰና በጭብጨባው ተበረታቶ ማይኩን ከእጇ ተቀበላት.
‹‹ሰዎች እንደምታዩት በጣም ደንግጪያለው…ሳልሰማ እለተምፅአት የታወጀ ነው የመሰለኝ..ሽጉጥ አልያዝኩም እንጂ ይዤ ቢሆን በዛች ቅፅበት ላጣት እንደሆነ በገመትኩ ጊዜ ወይ ሰውዬውን አልያም እራሴን ማጥፋቴ አይቀርም ነበር…ለማንኛውም አሁን አስፈሪ የነበረው አጭር ቅዥት አልፎል…ሲፈንዬ በመጨረሻዋ አስትንፋሴ እንደማፈቅርሽ ያወቅኩት ሰውዬው አግቢኝ ብሎ ጉልበትሽ ስር ሲንበረክ ነው፡፡ካንቺ ማብራሪያውን እስክሰማ ድረስ ልቤ መፈራረስ ጀምራ ነበር..››ንግግሩን ጋብ አረገና ተንበረከከ እጁን ወደኮት ኪሱ ከተና ቀለበቱን አወጣ….ሙሉ ቤቱ በሌላ ሰርፕራይዝ ተተረማመሰ
.‹‹.ታገቢኛለሽ.እባክሽ እምቢታሽን መቋቋም አልችልም››
ሲፈን ቅብዝርዥዥ አለባት..ነገሮች ሳታስበው ከቁጥጥሯ ውጭ ወጥተዋል…አሁን ወደኃላ መመለስ የምትችልበት ሁኔታ ላይ አይደለለም ያለችው …በመደንዝ ውስጥ እንዳለች እጣቷን ወደእሱ ዘረጋቸ...በደስታ እጣቷ ላይ የአልማዝ ፈርጥ ያለበትን አብረቅራቂ ቀለበት አጠለቀላት፡፡ ሆቴሉ በፌጨትና በጭብጨባ ተናጋ…አቶ ሃይለሚካኤል .ሰውዬውና አርቀው ወርውረው በጀግንነት ተኮፍሰው ወደሆቴል ሲመለሱ ያልተበቁት መተረማመስ ስለተበቃቸው ምን ተፈጠረ ብለው ሰውን እየገፈታተሩ ወደፊት ሲቀርብ ሲፈን ሌላ ቀለበት እጣቷ ላይ አጥልቃ በደስታ እየፈገገች ጣቶን ወደላይ ቀስራ ለታዳሚው ሁሉ ስታሳይ …ከጎኗ ያለ አንድ ሸበላ ወጣት አቅፎ ደረቱ ላይ ለጥፎ ሲስማት ተመለከቱ …እንዳመጣቸው ሰውን እየገፈታተሩ መልሰው ወጡ
‹‹አንቺ ሸርሙጣ ባልሰራልሽ እኔ የአባቴ ልጅ አይደለውም…ገንዘብሽን እንጂ እንቺን ማን የፈለገሽ መሰለሽ…? አንቺማ ያው እንደማንኛውም ሴት ሴት ነሽ….ሁለት ስንጥቅ አልያዝሽ›› እያጉረመረሙ መኪናቸውን ወደአቆሙበት ሄዱ… ከፍተው ገቡና ሽጉጣቸውን ካስቀመጡበት በማንሳት ጎናቸው ሽጠው ወደሆቴሉ በራፍ በመሄድ ሰወር ያለቦታ ፈልገው በመቀመጥ እድፍጠው ከእድምተኞች መካከል የሚፈልጉት ሰው እስኪወጣ መጠበቅ ጀመሩ
ሆቴሉ በሌላ ፌሽታና ደስታ ተሞልቷል…ሲፈንና ሄኖክን ሁሉም በየተራ እየመጣ እንኳን ደስ ያላችሁ እያላቸው ይሄድ ጀመረ….ፕሮፌሰሯም ወደሲፈን ጆሮ ተጠግታ ‹‹ በጣም ደስ ብሎኛል፡፡ደስተኛ ትዳር እንዲሆንልሽ ምኞቴ ነው፡፡ግን ደግሞ ቢላልን በተመከተ ሰሞኑን ተገናኝተን ማውራት አለብን››አለቻት
‹‹አመሰግናለው ፕሮፌሰር .ይገባኛል..ደውላለው››ብላ አሰናበተቻት፡፡ፕሮግራሙ ተጠናቀ ሁሉም ተራ በተራ እየተሰናበተ ወጣ፡፡በስተመጨረሻ ሲፈንና ሄኖክም ተያይዘው ሆቴሉን ለቀው ለመውጣት መራመድ ጀመሩ ‹‹...ወደቤትሽ ነው የምትሄጂው?››
‹‹አይ ወደ እናባዬ ቤት ነው የምሄደው››
2
‹‹አምሰት ሰዓት ሆኗል እኮ?››
‹‹አውቃለው ግን በጥዋት ቁርስ ከወላጆቼ ጋር መብላት አለብኝ›አለችው፡፡ እውነታው ግን ቢላል ምን እንደላከላት ለማወቅ ነው፡፡እርግጥ የተሰጧትን ስጦታዎች ሁሉ ከፍታ እያየች መደሰት ከልጅነቷ ጀምሮ ያዳበረችው ልምድ ነወ..የዛሬው ውስጥ ግን የተለየ ስጦታ ከተለየ ሰው ተሰጥቶት እዛው ጥላ ስለመጣች ነው አጥብቃ መሄድ የፈለገችው፡፡
ሄኖክ የጠየቃት የምሄደው ወደቤቴ ነው ካለችው ወይ አስከትላው እንዲትሄድ ወይም ደግሞ ሌላ ቦታ አብረው እንዲያድሩ ሊተይቃት ፈልጎ ነው፡፡ቀለበት ባሰረላት በዚህ ቅዱስ ቀን ከእሷ ተለይቶ ማደር ፈፅሞ አልፈለገም ነበር....ቢሆንም .ክርክር ውስጥ ገብቶ ይሄንን የመሰለ የተቀደሰ ስሜት ማደፍረስ እንደሌለበት ስለተረዳ ስሜቱን እንደምንም በውስጡ ጨቁኖ አስቀረው…አዎ ዛሬ ያልጠበቀውን ታላቅ ድል ነው ያተጎናፀፈው ፡፡ በቅርብ ሊያገባ ነው፡፡እሺ ብላ ቀለበት በጣቷ ላይ አጥልቃለች…ለዛውም በመአት ምስክሮች ፊት ፡፡

ይቀጥላል.....
5
😘ነፍስ ስታፈቅር😘

🔥ክፍል 33

///
ሲፈን ሄኖክን ተሰናብታ ቀጥታ ወደቤቷ ነው ያመራችው፡፡ሰዓቱ 5 ሰዓት ቢያልፍም ቀኑ የእሷ ስለሆነ ምንም አልተሳቀቀችም ….ዘበኛው ከፈተላትና መኪናዋን ወደውስጥ አስገብታ አቆመች፡፡ .ወላጆቾ በየክፍላቸው ገብተው የተኙ ቢሆንም ሰራተኞች ግን አሁንም በድግሱ ምክንያት የተዝረከረከውን ቤት በማስተካከልና በማፅዳት ላይ ስለሆኑ አልተኙም ነበር፡፡
ቀጥታ ወደራሷ ክፍል ነው ያመራችው፡፡ይሄ ክፍል የራሷን ቤት ገዝታ ከወጣች አመታ ያለፉት ቢሆንም አሁንም ግን እንዳለ ነው፡፡በሳምንት አንድ ወይም ሁለት ቀን መጥታ ትተኛበታለች፡፡ከአባቷ እቅፍና ከእናቷ ጠረን እኩል ነው የሚናፍቃት፡፡ይሄ መኝታ ከፍሏ የዕድሜዋን 90 ፐርሰንት ያሳለፈችበት ታሪካዊ ስፍራ ነው፡፡የልጅነቷን ጊዜ በደስታ ያስዋቡላት አሻንጉሊቶቾና መጫወቻዎቾ የተደረደሩበት….የጡቶቾ ማጎጥጎጥ እንደብረት ጠጥጥሮ ነገሯች ድንገት ሲነኳት አሞት እንባዋን እርግፍ እርግፍ አድርጋ ያለቀሰችበት…. ከዛም አልፎ ለአቅመሄዋን የመድረሶን ብስረት የሚያረጋግጠውን የወርአባዋን ያየችበትና በዛም ድንጋጤው ቤት ውስጥ በወቅቱ የነበሩ ሰዎች ሁሉ በድንጋጤ ወደክፍሏ እስኪንጋጉ ድረስ ከጣሪያ በላይ የጮኸችበት….. በሞባይሏ ከወንዶች ጋር በሽክሹክታ ብዙ ብዙ የፍቅርና ወሬዋችን ጆሮዋ እስኪግል ያወራችበት፡፡…በፌስ ብክ ከተዋወቀችውና በወቅቱ ልቧ እስኪጠፋ ድረስ ያፈቀረችው ከመሰላት ፈረንሳዊ ወጣት ጋር ፎን ሴክስ ደጋግማ የከወነችበት ፡፡…ልቅ የሆኑ ፊልሞችን በማየት ልቅነትን የተለማመደችበት ብዙ ቡዙ ታሪክ የሰራችበት የዘመናት ግዛቷ ነው፡፡ለመጀመሪያ ጊዜ ከንፈሮን የተሳመችበትም ድንግልናዋን ያጣችውም በዚህችው ክፍል ውስጥ ነው፡፡
ለማማያ ያህል ከንፈሮን ስትሳም
ትዝ ይላታል ገና የ15 ዓመት ልደቷን ካከበረች ከጥቂት ወራት ቡኃላ ነበር፡፡ኤርሚያስ የሚባል የ19 ዓመት የአጎቷ ልጅ ክረምት እነሱ ጋር ለማሳለፍ ከክፍለሀገር ይመጣል፡፡ኤርሚያስ ለስላሳ ቅልስልስ ያለ ባህሪ ያለው የሚያምር ንቁ ወጣት ነው፡፡እና ኤርሚያስን ከተማውን ማስጎብኘት፤ ..በየሲኒማ ቤቱ ይዞ መዞር ፤ ካፌና ኬክ ቤት ወስዶ መጋበዝ የእሷ ቋሚ ኃላፊነት ነበር፡፡መጀመሪያ ሰሞን ምንም እንኳን የምትወደው የአጎቷ ልጅ ቢሆንም እሱን አሰከትሎ በየቦታው መንከርፈፍ በጣም አተካችና ደባሪ ሆኖባት ነበር፡፡ግን ያው አሱንም ሆነ አባቷን ላለማስከፋት እንደምንም ስሜቷን ተቋጣጥራ አብራው ስትውል ሰታድር ሁኔታዎች ብዙም ሳይቆዩ ተቀየሩ፡፡
ኤርሚያስ በጣም የሚወደድና አብረውት ለዘላለም ውለው ቢያድሩ የማይሰለች ጣፈጭ ልጅ ሆኖ አገኘችው፡፡እናም አንድ ወር እነሱ ጋር ሲቆይ አንድ ሳምንትም የቆየ አልመሰላትም ነበር፡፡ያው ጊዜ መሽከርከሩና ኡደቱን ጠብቆ መንጎዱ አይቀርምና ኤርሚያስ ወደወላጆቹ ጋር የመሄጂያው ጊዜ ደረሰ..ለመሄድ አንድ ቀን ሲቀረው አስባበትና አልማ የራሷ የሆነ የመሸኛ ዝግጅት አሰናዳች፡፡ማንም ሳያያት የራሷን መኝታ ቤት ወለል በቀይ ፅጌረዳ አበባ ዝንጣፊ አለበሰችው፡፡መብራቱን አጠፋችና በአራቱ የክፍሉ ኮርነር አራት ትላልቅ ሻማዎች ለኩሳ በላያቸው ላይ የተለያዩ ከለር ያላቸው ክብ ወረቀቶች አድርጋባት እቤቱ እንዲያሸበርቅ አደረገች…ክፍሏ ያለውን ጠረጳዛ መሉ በፍራፍሬ እና በቸኮሌቶች ማላችው፤ከዛም ለአባቷ ከወዳጆቻቸው በተለያየ ግቢ በስጦታ መጥተውላቸው ከተከማቹ መአት ወይኖች መካከል ምርጥ ሚባለውን የፈረንሳይ ወይን ደብቃ አምጥታ ክፍሏ አኖረች፡፡ከዛ እራሷን አረጋግታ ከኤርሚያስ ጋር ከመላ ቤተሰቡ ጋ ሆነው በሳሎን የመሸኛ እራት በልተው ተጨውተው ከተሰነባበቱ ቡኃላ ወደመኝታ ክፍሎ ይዛው ሄደች፡፡
በራፍ ላይ ሲደርሱ ‹‹አይንህን ጨፍን›› አለችው
‹‹ለምን?››
‹‹ምን ቸገረህ ጨፍን አልኩህ ጨፍን..ቆይ እንደውም..››አለችና ከጀርባው ዞራ በሁለት እጆቾ አይኑን ጠርቅማ ሸፈነችውና በራፉን እንዲከፈት ገፋችው…ከገቡ ቡኃላ በእግሯ መልሳ በራፉን ዘጋችና መሀከል ወለል ድረስ ከወሰደችው ቡኃላ ቀስ ብላ ለቀቀችው፡፡
‹‹ኤርሚያስ ለደቂቃዎች የክፍሉን ዙሪያ ገባ ካየ ቡኃላ ለደቂቃዎች ረጅም ሳቅ መሳቅ ጀመረ…እሷ ደነገጠች፡፡የጠበቀችው እንደዚያ አይነት ግብረመልስ አልነበረም….በድንጋጤ አፍን ከፍቶ በአድናቆት ወደእሷ ቀርቦ …እሷንም ወደራሱ ጎትቶ አቅፎ ቢያንስ ግንባሯን እንደሚስማት ጠብቃ ነበር….እሱ ግን ሆድኑ በእጆቹ ይዞ በሳቅ ይንፈራፈር ጀመር፡፡
‹‹ምንድነው የመያስቅህ?››
‹‹ለምን አልስቅም …?ተቃልጂያለሽ እንዴ…?እኔ ስሔድልሽ እንዴት አድርገሽ ያፈቀርሺውን ጎረምሳ እንደምታማልይው እየተለማመድሺብኝ እያየው ለምን አልስቅ?››
‹‹አንተ ምን አይነቱ ውለታቢስ ሰው ግን…?ለአንተ ለወንድሜ የሽኝት ዝግጅት እንዲህ ለፍቼ ባዘጋጅ እንዲህ አመድ አፋሽ ታደርገኛለህ?››
‹‹እንደዛ እኮ አይደለም የእኔ ጣፋጭ እህት..ነገሩ አልተገናኝቶም ስለሆነብኝ ነው…ወይም እንዲህ ሮማንቲክ ዝግጅት ማዘጋጀትሽ ካልቀረ ያቺ በቀደም ያስተዋወቅሺኝን ራሄል የተባለችውን ጎደኛሽን ጠርተሸልኝ..በዛ ሰበር ቅንጥስ በሚሉ እግሮቾ በዚህ አበባ ላይ ስትራመድ እያየው ነፍሴን ባስደስት ...እናም ከነዛ ምርጥ ቸኮሌቶች መካከል አንዱን አፎ ውስጥ ከትቼ ቸኮሌቱን ብገምጥ እግረመንገዴንም እነዛን ክሬም የሚንጠባብባቸው የሚመስለሉ ከነፈሮቾን ብመጥላት…….
‹‹ጨረስክ…አባዬ ይሙት ብሽቅ ነህ...እኔ ነኝ ባለጌው… በል ደህና አደር..››አለችና ከተቀመጠችበት ተነሰችና አልጋዋ ላይ ወጥታ ብርድልብሱን ገልጣ ከውስጥ ገብታ በመጠቅል ተኛች፡
‹‹የእኔ አኩራፊ ..ዛሬማ ይሄን ሁሉ ድግስ ሜዳ ላይ በትኖ እንዲ በቀላል መተኛት የለም…ሻወር ወስጄ እስክመጣ ኩርፊያሽን አባረሽ ባትጠብቂኝ ነግሬሻለው ጭንሽ ውስጥ ገብቼ በቁንጥጨ ነው የማነሳልሽ›› ብሏት ልብሱን አዋለቀና ወደሻወር ቤት ገባ
ሲፈን ግን የቅርብ ሰው እንደሞተበትና ከደቂቃ በፊት እንደተረዳ ሰው ስቅስቅ ብላ በእንባ እየታጠበች ማልቀስ ጀመረች….ይህ ለቅሶ ቀኑን ሙሉ የእሱን ነገ መሄድ ባሰበች ቁጥር ልፍሰስ አልፍስ እያለ ሲተናነቃት የቆየና በመከራ ገድባው የቆየችው ስሜት ነበር...አሁን ግን እሱ ያልጠበቀችውን ነገር አድርጎ ሲያበሳጫት የተገደበ አንባዋን እንድትዘረግፈው መንገድ ከፈተላት፡፡
ከ10 ደቂቃ ቡኃላ ሰውነቱን ታጠቦና ቢጃማ ቀይሮ ሲመጣ ጥሏት ሲሄድ እንደነበረችው በብርድልብስ እራሷን ጠቅላለ ነበር ያገኛት..
‹‹እንቺ …!!!››እስከ አሁን ዘሎ አልጋ ላይ ወጣና ብርድልብሱን ገፈፋት
‹‹ተወኝ በክህ ልተኛበት››አመነጫጨቀችው
ሊሰማት አልፈለገም‹‹ልተኛ .አስጠንቅቄሽ ነበር እኮ….ጋሼ ቆንጥጦሽ አያውቅም አይደል…?.እጆቹን ወደ ጭኖቾ ማካከል ላከ…
‹‹ተወኝ ብየሀለው.. ተውኝ… .በጣም ፈራለው .››
አልተዋትም፡፡ ወደላይ በተሰበሰበው ቀሚሷ እጁን አስገብቶ ከፓንቶ ወረድ ብሎ የሚገኘውን ልስልስ የጭኗን ቆዳ በሁለት ጣቾቹ መካከል አስገብቶ ግን ደግሞ እንዳያማት እየተጠነቀቀ በስሱ ያፍተለትላት ጀመር..
‹‹በማርያም..ልጮህ ነው….እ ጮህኩ››
6
‹‹ሁለተኛ ታኮርፊያለሽ .››
‹‹አላኮርፍም .ሁለተኛ .በናትህ ኤርምዬ…›
ህመሙ ሳይሆን ከእጆቹ የሚረጩት ሙቀት ነው እያሰቃያት ያለው…ዘላ ተጠመጠመችበት...እራሷን መቆጣጠር አቃታትና ሽንተዋን ጭርቅ.ጭርቅ..አደረገች.
‹‹አንቺ…›› ተስፈንጥሮ ከአልጋው ወረደ
‹‹እሷም በተቃራው አቅጣጫ ወረደች.‹‹...ምን አይነት ብሽቅ ነህ ..ተወኝ ማለት አትሰማም እንዴ?‹‹
ጎንበስ ብላ ፓንቷን አወለቀችና አፍንጫው ላይ ወረወረችበት…
አባበላትና ከደቂቃዎች ቡኃላ ሀለቱም እርቅ አውርደው እሷ ቀድሞ አስባው በነበረው መሰረት ተረጋግተው ክፍራፍሬው እየበሉ ከቸኮሌቱን እየቆረሱ ማውራትና መጫወት ጀመሩ… ከዛ ቡኃላ ወደወይኑ ተሸጋግረው ጎን ለጎን አንድ ሌለኛቸው ላይ ተደግፈው መጎንጨት ጀመሩ ...እንግዲህ ያን ቀን ነበር የገዛ አጎቷን ልጅ ከንፈረ የሰማችው… ቀድሞ ማን መሳም እንደጀመረ እእከዛሬም ስታስበው መልሱን አታውቅም ግን በዕድሜ ዘመኗን ሙሉ ጣዕሙ ከከንፈሮ የማይጠፋ አይነት ተአምራዊ መሳሳም ነበር በዛ ለሊት የተሳሳመችው፡፡
የድንግልናዋም በ16 ዓመቷ ከሌላ ጎረምሳ ጋር እዚሁ ክፍል ነው የከወነችው..፡፡
እናም ለሲፈን ሀገር ሲበል ሁል ጊዜ ትዝ ምትላት ይህች ያሸበረቀችና የማረች የእድሜ ልክ መኝታ ክፏሏ ነች፡፡ከዚህች ክፍሏ ጋር የተያያዙ እኚህ ሁሉ ትዝታዎች ለምን በዚህ ደቂቃ በአዕምሮዋ እንደተግተለተሉ አልገባትም…
//
ከሀሳቧ ስትባንን በመጀመሪያ የለበሰችውን ልብስ በቁሟ አወላልቃ ጣለችና ቁምሳጥኑን ከፋፍታ ቀለል ያለ ቢጃማ ለበሰች፡፡ከዛ ወደአልጋ ሄደችና የተቆለሉትን ስጦታዎች ገፋ በማድረግ ሙሉ በሙሉ አልጋው ላይ ወጥታ ተቀመጠች፡፡
ሁሉንም ለማየት ጓጉታለች
‹‹….ምንድነው ግን የሚያጎጎኝ?›› ስትል እራሷን በትዝብት ጠየቀች ..ምከንያቱም እሷ መግዛት የማትችለውን ገዝቶ ሊሰጣት የሚችል ሰው እንደሌለ ታውቃለች፡፡
‹‹ያው ግን ስጦታ እኮ ሰዎች ስለእኛ ያላቸውን በጎ አመለካከት በራሳቸው አቅምና ፍላጎት ልክ የሚገልፁበት መንገድ ስለሆነ ትርጉሙ ከሰጡት እቃ ዋጋ አንፃር ሳይሆን በፍቅር ሚዛን ነው የሚመዘነው›ስትል ለራሷ መልስ ሰጠች ....እናም በመጀመሪያ ከሁሉም ስጦታዎች በጣም ትንሽ ሆኖ የሚታየውን የቢላልን ስጦታ ከመሀከል ጎልጉላ አወጣችና ለመክፈት ተዘጋጀች፡፡
ወደኃላ…ከ1 ሰአት በፊት
ሲፈንና ሄኖክ እጅ ለእጅ ተያይዘው በሳቅና በፈገግታ የታጀበ ወሬ እያወሩ ከሆቴል ሲወጡ አቶ ወልደገብርኤል ሽጉጡን ጎኑ እንደሻጠ በራፍ አካባቢ ሲጠብቃቸው ነበር..እንዳያቸው ተስፈንጥሮ ይበልጥ ወደኃላው ሸሸና ጨለማ ውስጥ ገባና ከኃላ የሸጎጠውን ሽጉት አውጥቶ አቀባበለ እና በተጠንቀቅ ሆኖ ይከታተላቸው ጀመር..ሁለቱም እንደተያያዙ መኪናቸውን ወደአቆሙበት ስፍራ ሄዱ… እነእሱም ሆኑ ሌሎች ሰዎች እንዳያዩት እየተጠነቀ ተከተላቸው…..የእሷ መኪና ተጠግተው ማውራታቸውን ቀጠሉ..ወልደገብርዔል ሽጉጡን በእሱ ትክክል አነጣጠረ…ቃታውን ልሳብ ወይስ የተሸለ እይታ እስካገኝ ልጠብቅ እያለ ከራሱ ጋር ሙግት በገጠመበት ቅፅበት ድንገት ሁለቱም ካበት ተንቀሳቀሱና በየመኪናቸው ገብተው በተቃኒ መስመር ጉዞ ጀመሩ.
ወልደገብርኤል ጊዜ ሳያጠፋ ተንደርድሮ ወደራሱ መኪና ገባና ሄኖክ በሄደበት አቅጣጨ መኪናውን አዙሮ ተፈተለከ..አስር ሜትር ያህል ከቀረበው ቡኃላ ፍጥነቱን መጥኖ አልሞ ለመተኮስ የሚያስችል ምቹ ጊዜ እስኪገጥመው ድረስ ይከተለው ጀመር
..//
አሁን
///
ሲፈን አልጋዋ ላይ ተመቻችታ ተቀምጣ በእጇ ቢላል የላከላትን ስጦታ ለመክፈት እየተዘጋጀች ነው..ልቧ እንደከበሮ ድው ድው እያለ ቢያስቸግራትም ቀስ ብላ ከፈተችው ..ውስጡ በኤ-4 መጠን ያሉ ሁለት ወረቀቶቸች ተጣጥፈው አገኘች፡፡አንደኛውን ገለጠች.. ስዕል ነው፡፡አስተውላ አየችው.. ..በጣም አስደንጋጭና ያልጠበቀችው አይነት ስጦታ ነው፡፡ያስደነገጣት ስጦታው ስእል መሆኑ አይደለም…መቼስ ወርቅ ይሰጠኛል ብላ እንደማታሰብ ማንም ያውቃል፡፡ እንደውም ቀድሞውንም የተለመዱትን ደብዳቤዎቹን ነበር የጠበቀችው …ስዕል መሆኑ እንደውም አስደሳችና የተለየ ስጦታ መሆን ነበረበት፡፡ ይሁን እንጂ የስዕሉ አይነት አስደንጋጩ ነበር
ስዕሉን ወደጎን አስቀመጠችና ሁለተኛውን ሉክ ገለጠች …ፅሁፍ ነው፡፡ልክ እንደተለመደው ጥርት ባለ የእጅ ፅሁፍ የተፃፈ… .ማንበብ ጀመረች፡፡
…ግብዙ የሰው ልጅ ልደቱን ለምን ብሎ እንደሚያከብር ሊገባኝ አይችልም፡፡ከነበረበት ሁለንተናዊ ኣለም ተነጥሎ ወደ እዚህች ምድር ሰው ተብሎ በመምጣቱ መመፃደቁ ነው?፡፡እሺ ሰው ሆኖ በዚህ ምድር መፈጠር ምኑ ላይ ነው አስደሳችነቱ? ጉንዳኖችም የዚህች ምድር ኑዋሪዎች ናቸው፣….ውሻና ድመትም እንደዛው…ለማንኛውም እንኳን ተወለድሽ ብዬ መልካ ምኞት ልመኝልሽ አልችልም፡፡እንደማስበው እሰከዛሬ እስከ ሀያአምስት አመትሽ ድረስ በፈንጥዝያ ልደትሽን ማክበር ካላቆረጥሽ ገና በዚች ምድር ላይ የመኖር ጉጉትሽ የጋለና በከፍተኛ ፍላጎት የተሞላ መሆኑን ነው የሚያመለክተው፡፡
ይሄ ለልደትሽ ከእኔ የሚበረከት ስጦታ እንዳልሆነ ልነግርሽ እፈልጋለው…እናቴ ልደቷ ላይ መገኘት ባትችል እንኳን የሆነ ስጦታ ላክላት ብላ ስታጨናንቀኝ ይሄንን ጭንቄቴን ላኩልሽ….እንደዚህ እንደላኩልሽአይነት ከደርዘን በላይ ተመሳሳይ አይነትስዕሎች ስስለው..ስዕሉን የሳልኩት አስቤበት ወይም ፈልጌው ሳይሆን ከቁጥጥሬ ውጭ በሆነ ኃይል ተገፋፍቼ ነው፡፡እናም በህልሜም ደግሞ ደጋግመ እያየውት ነው..ለምን አንደሆነ ምከንያቱን ፈፅሞ ባላውቅም እኔ አንቺን አንቄ ስገድልሽ..እና ደግሞ የዚህ የላኩልሽ ስዕል ተከታይም አለ…ከገደልኩሽ ቡኃላ እራሴን በገመድ አንጠልጥዬ ስገድል……..እርግጥ ትንቢቱ አንቺን አስደንግጦሽ አና አስበርግጎሽ ሊሆን ይችላል…እኔን ግን በጣም ነበር ያስደሰተኝ… ይታይሽ ይሄ አጋጣሚ እራሳችንን ከዚህ በስባሽና ቀርፋፋ ስጋ አላቀን ነፍሳችንን ነፃ የምናወጣበት ብቸኛው መንገድ እኮ ነው፡፡ሞት እኮ ነፍሳችንን ከስጋ እስረኝነት ነፃ የምናወጣበት ብቸኛው መንገድ ነው፡፡ስለሆነም በቀላሉ የሁለታችንም ነፍስ ከስጋ እስረኝነት ተላቆ ነፃ ከሆነን ይታይሽ በዚህ ምድር ግራቢቱ ተፃኖ ተቀፍድዶ ከመንቀርፈፍ ተላቆ ሰማየሰማያትን ሰንጥቆ አብሮ ለመንሻራሸር እድል ማግኘት ማለት ነው….በከዋክብት ገላ ላይ ተቃቅፎ የፍቅር ዳንስ ለመደነስ ችሎታውን መጎናፀፍ ማለት ነው፡፡በጨረቃ ጭን ላይ ቁጭ ብሎ ፀሀይን በሀሴት እየሞቁ መሽከርከር መቻል ማለት ነው፡፡
ግን ሳስበው አንቺ ለዛ ዝገጁ አይደለሽም፡፡ዛሬም ከዚህ ምድር ሱሰ አለተገላገልሽ……በዚህ ምድር ላይ የመቆየት ፍላጎትሽ ገና እንደተንቀለቀለ ነው .እና ያለፍላጎትሽ እንዳልገድልሽ ፈርቼዋለው. ……ስለሆነም ከዛሬ ጀምረ አንቼን በምንም አይነት አጋጣሚ ላላገኝሽ ወስኜያለው..እንቺ ከተቻለሽ ከዚህ ሰፈር በአፋጣኝ ለቀሽ ከእኔ ራቂ……በአጋጣሚ መንገድ ላይ በሩቅ ብታይኝ እንኳን አደራሽን ልታገኚኝ እዳትሞክሪ…….እንዲህ ደጋግሜ ከቁጥጥሬ ውጭ በስዕል የምስላቸው ነገሮች ትንቢት ናቸው……ሳይፈፀሙ ቀርተወ አያውቁም….ትናፍቂኛለሽ……አፈቅርሻለው
4👍1
አንብባ ጨረሰች..ሌላ መደንዝ
//
አንዳንድ ቀኖች ምን ያህል መአት ቀናቶች በውስጣቸው አምቀው ይዘዋል……እንዲያ ካልሆነ ይሄ ሁሉ መአት ገጠመኝና ህይወቷን ከመሰረቱ የሚገለባብጡ ነገሮች ቀስ በቀስ…..በወራትና በአመት የጊዜ ርዝመት መፈጸም ሲገባቸው እንዴት በአንድ ቀን ይህ ሁሉ ውጥንቅጥ ሊከወን ቻለ…?..ቢላል ገና ከአሁኑ በጣም ናፈቃት…..ከመኝታዋ ተነስታ መኪናዋን በማስነሳት በራ እሱ ወዳለበት ሄዳ ልታገኘውና የሚያወራው ነገር ሁሉ ዝም ብሎ አእምሮ የፈጠረው ፍራቻ እንደሆነና ምንም እንዳይጨነቅ ልትነግረውና ልታረጋጋው ፈለገች፡፡ ….ግን ስድስት ሰዓት አልፎል በዚህ እኩለ ለሊት እሷ መሄድ ብትችል እንኳን እንዴት ብላ የሰው ቤት ታንኳኳለች….?ለድርጊቷስ ምን አይነት ምክንያት ትሰጣለች…..?ባይሆን አይኔን በጨው ታጥቤ ፕሮፌሰሮ ጋር ልደውልና እንዴት እደሆነ ልጠይቃት ብላ አልጋዋን ለቃ ወረደችና ባርሳዋውን ከፍታ ሞባይሏና አወጣች….ስልኳ ሳይለንት ላይ ነበር ….. ገና በግዚ እየደወሉ መልካም ልዳት የሚሏት ሰዎች ስለበዙና ስላጨናነቋት ነበር ሳይለንት ላይ አድርጋ በዛው የረሳችው……፡፡
‹ 33 ሚስኮልና ከአስር በላይ መልዕክት አላት…..ከሚስኮሉ መካከል ከ25 በላይ አሁን በቅርብ ሰዓት ከሄኖክ ከአባቱና ከእህቱ በተከታታይ የተሞከረ ነው፡፡
‹‹…..ወይኔ ምን መአት ነው የተከሰተው…..?›› በቋመችበት ብርክ ያዛት …መልዕክቱን ከፈተች.. ..አብዛኛው ከተለያዩ ሰዎች የተላኩ የመልካም ልደት ምኞት መልዕክተች ናቸው….እንዱ ግን ከሄኖክ እህት የተላከ ነው…..ከፈተችው
‹‹እህቴ ተኝተሸ ነው እንዴ ስልክሽ አይነሳም…ችግር ተከስቶል …..ሄኖክ ካንቺ ጋር ቆይቶ ወደቤት ሲመለስ የሆነ ሰው ሊገድለው ሞክሮ ነበር…….ማለት ሽጉጥ ተኩሶ መቶት አሁን ቤተዛታ ሆስፒታል ነው ያለነው…….››
ጭው አለባት…የተቀመጠችበት አልጋ ከላይ ወደታች ሲገለባበጥ ይታያታል..

ይቀጥላል
5
😘ነፍስ ሲያፈቅር😘

🔥ክፍል 34
.
.
///
ሄኖክ መኝታ ቤቱ እጆቹ ትከሻው አካባቢ በፋሻ ተጠቅልሎ ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ተኝቷል፡፡ዛሬ አደጋው ከተፈጠረ ሶስተኛ ቀኑ ሲሆን ከሆስፒታል ወጥተ እቤት የገባው ግን ከሁለት ሰዓት በፊት ነው፡፡አደጋው እንደደረሰ ሰውነቱ ሙሉ በደም ታጥቧና እሱም እራሱን ስቶ ስለተገኘ ሁሉም ነገር በጣም አስደንጋጭ ይመስል ነበረ፡፡ ቢሆንም ቡኃላ ሆስፒታል ተወስዶ ደም ከወረሰው ልብሱ እሱን አላቀው በእርጋታ ሲመረምሩትና ቡኃላም ቀዶ ጥገና ሲያደርጉለት ትከሻውን ነድላ የገባቸው ጥይት በስጋው ውስጥ ሰምጣ ከመግባት ውጭ ምንም ያደቀቀችው አጥንት ሆነ የበጣጠሰችው ስር ስለልነበር. በቀላሉ እንዲያገግምና ወደቤቱ እንዲመለስ ምክንያት ሆኖል፡፡
ሲፈንም ባለፉት ሶስት ቀናት ስራም ካለመግባቷም በተጨማሪ በመሀል አንድ ቀን ለተወሰነ ሰዓት ልብሷን ለመቀየር ወደቤቷ ደርሳ ከመምጣቷ በስተቀር ከሄኖክ ሳትለይ እሱን በማስታመም እና በመንከባከብ ነው ያሳለፈችው፡፡
የቢላልን ሁኔታ እንኳን በስልክ ነው እናቱ ጋር ደውላ እየጠየቀች ያለቸው፡፡እናትዬውም ደህና እንደሆነና በተረጋጋ ስሜት ላይ እንዳለ ነው ደጋግማ የነገረቻት፡፡ እንደዛም በመሆኑ ቢያንስ እሱን በተመለከተ መረጋጋት እንዲሰማት አገዞታል፡፡
የወልደገብርኤል ሁኔታ በተመለከተ ደግሞ ወንጀሉን የሰራበት ቦታ የትራፊክ ካሜራ ያለበት በመሆኑ ብዙም ፖሊሶችን ሳያለፋ በበቂ መረጃ ነበር ወንጀለኛው እሱ መሆንን ማረጋገጥ የተቻለው፡፡ከዛም ፖሊሶች ከተወሸቀበት አሳደው በመያዝ ዘብጥያ ለማውረድ አንድ ቀን ከግማሽ ብቻ ነበር የወሰደባቸው፡፡
ሌላው አሳሳቢ ሆኖ የከረመው የሚዲያ ጉዳይ ነበር፡፡ሀኔታውም ከእሷ ታዋቂነት ጋር ተያይዞ በተለያዩ የግል ጋዜጦችና ኤፍ.ኤም የሬዲዬ ጣቢያዎች ላይ ተኩስ ዜና ሆኖ ሲቀባበሉት ነው የሰነበቱት.፡፡እሷ እንኳን ይህን ጉዳይ ስራዬ ብላ እየተከታተለችው ባይሆንም የተለያዩ የቅርብሽ ነን የሚሉ ሰዎች ግን እየደወሉም አንዳንዶቹ በአካልም ጭምር ያለችበት ድረስ በአካል እየተገኙ የተባለውን እና የተፃፈውን ያቀብሎት ነበር፡፡
አደጋውን ተከትሎ ጋዜጠኞቹ የተኳሹን ማንነት ከእሷ ጋር የሚያይዘውን የኃላ ታሪክ ጭምር…የፍቅረኛዋና ማንነት .በእለቱ ልደቷ ላይ የተፈጠረውና ትዕይንት በአጠቃላይ እየበረበሩና የራሳቸውን ቅመም እየጨመሩበት የተግለበለበ ገበያ ለማግኘት እየተጠቀሙበት ነው፡፡
ለምሳሌ አንዱ ጋዜጣ‹‹ቢሊዬነሯ ሲፈን ቀለበት ባሰረችበት ምሽት ከልጄ ሌላ ሌላ ሰው ማግባት የለብሽም ብሎ የተቆጣ አዛውንት ቀለበት ያሰረላትን ግለሰብ አስቧ እና አልሞ መውጫ መግቢያውን በመከታተል በሽጉጥ ተኩሷ መቶታል፡፡ መልከመልካሙ ፍቅረኛዋም በአሁኑ ሰዓት በህይወትና በሞት መካከል እየቃተተ ቤተዛታ ሆስፒታል በከፍተኛ ክትትል ስር እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሎል፡፡››ይላል፡፡
///
ቢሊዬነሯ ወጣት ቀለበት አሰረች…ፍረኛዋ ግን በጥይት ተመቶ ሳይሞት እንዳልቀረ ጭምጭምታዎች እየወጡ ነው…
//
ጉዳዩ የፍቅር ወይስ የገንዘብ?
ቢሊዬነሮን ለማግባት ሶሰት ሰዎች ፍልሜያ ውስጥ ገብተዋል፡፡በልደት በአሏ ላይ ሁለቱ ሰዎች በየተራ እንድታገባቸው ጉልበቷ ስር ተንበርክከው ቀለበ ቢማፀኖትም ከሁለት አንደኛውን መርጣ እሺ ያለችው ሲሆን ዝግጅቱ ላይ የነበሩት የሶስተኛው አፍቃሪዋ አባት ግን አድፍጠው እሺ የተባለውን እድለኛ ላይ ተኩሰው ሊገድሉት ሞክረዋል፡፡አሁን ይሙት ወይስ በዊልቸር የሚሄድ አካለ ጎዶሎ ሆኖ ይትረፍ ገና አልለየለትም
//
እኚን እና መሰል ጆሮ የሚያጮሁ ዜናዎች ናቸው የተሰራጩት..በዛም ምክንያት ሰለጉዳዩ ያልሰማ ወዳጀ ዘመድ የለም....
///
ከሰላሳ ደቂቃ በፊት እናትዬው ደውለው በአስቸኮይ አባትሽ ይፈልግሻል ብለው ነግረዋት ነበር፡፡እናም በዛ ምክንያት ሄኖክ ከመኝታው እስኪነቃ ድረስ በፍጥነት ደርሳ ለመመለስ ስለፈለገች ወደእዛው እየሄደች ነው፡፡ፈርታለች ‹‹አባቴ በጣም አዝኖብኝ ይሆናል ያስጠራኝ››አለች፡፡
እውነቷን ነው ጨንቋታል….አቶ ወልደገብርኤል ማለት ከሰላሳ አመት በላይ ከአባትዬው ጋር አብረው የሰሩና አብረው የኖሩ ጥብቅ ሚስጥሮችንም የተጋሩ የረጅም ጊዜ ወዳጆች ናቸው….እንዲህ በሷ ጉዳይ ወንጀል ሰርተው ዘብጥያ ሲወረወሩ የማይታመን ነገር ነው የሚሆንባቸው…‹‹ታዲያ እኔ ምን ላድርግ…?ይሄ እንዲፈጠር ፈፅም አልፈልግም ነበር…ዋናው ተጎጂ እኔም ነኝ..በእኔ ምክንያት ሚስኪን ሰው ገና በወጣትነቱ ሞቶ ነበር…በዛ ላይ ስሜ በየሚዲያዎች ማጣፈጫ ሆኖል›› እራሷን ለማፅናናት ሞከረች..
ግና አንድ በእርግጠኝነት የምታውቀው ሀቅ ቢኖር ለአባቷ እኚን የተከሰቱ ነገሮችን እውነታ አስረድቶ ለማሳመን በጣም አስቸጋሪ እንደሚሆነባት ነው ፡፡ወልደገብርኤል ሁል ጊዜ አጋጣሚውን ባገኘ ቁጥር ‹‹ልጅህና ልጄ እኮ ይዋዳሉ›› እና የመሳሰሉት ወሬዎችን ሲለሚያወራላቸው አባቷ እውነትም ከልጁ ጋር የፍቅር ግንኙነት እንዳላትና አሁን እሱን ከድታ ሌላ ሰው ቀለበት ሲያስርላት በማየቱ አባትዬው በዛ ብስጭት ችግር ውስጥ እንደገባ በማመን እሷን ክብር እንደሌላት ልጅ ቆጥሮ በአንድ ብቸኛ ልጁ በዚህ ዕድሜው ጉዳተኛ ልቡ ቢሰበር …. እኚህንና መሰል ስጨናቂና ሀሳችን እያብሰለሰለች ደረሰች፡፡
መኪናውን አቁማ ልክ መጥሪያ ደረሶት ለመጀመሪያ ጊዜ ፍርድ ቤት ቅረብ እንደተባለ ግለሰብ አርምጃዋን እየቆጠረች ወደ ሳሎን ስትገባ ክፍሉ ባዶ ነው፡፡ፀጥ ረጭ ብሎል
‹‹.ይሄ ጥሩ ምልክት አይደለም››አለች..ቀስ ብላ ሳሎን ሰንጥቃ አለፈችና ወደ አባትየው መኝታ ቤት አመራች….ፈራ ተባ እያለች አንኳኳች
‹‹ማነው ?ይግቡ›
ቀስ ብላ በራፉን ገፋ አደረገችና አንገቷን ወደውስጥ አሰገገች
አባትየው እንዳዮት አይናቸውን አጉረጥርጠው ከተጋደሙበት በመነሳት ቁጭ አሉ.
.ተንደርድራ በመሄድ ጉልበታቸታው ላይ ተደፋችና
‹‹አባዬ እባክህ አትበሳጭብኝ…ስወድህ…ሁሉን ነገር አስረዳሀለው›
‹‹አንቺ ቀጣፊ ዞር በይ…›
‹‹እባክህ አባዬ እንዳዛ አታድርግ››
‹‹ለምን አላደርግም..?ይሄንን የመሰለ ሸበላ ፍቅረኛ እያለሽ ነው እስከዛሬ ሸሽገሽው በጉጉት ስታሰቃይኝ የኖርሽው?››
‹‹ምን እያልክ ነው አባዬ?››
‹‹ነይ ተነሽ እቀፊኝ…ቀለበት ማሰርሽን ከሰማው ቡኃላ አስር አመት በዕድሜዬ ላይ እንደተመረቀልኝ ነው እየተሰማኝ ያለው…በሽታዬ ሁሉ ተጠራርጎ ጥሎኝ ሄዷል››
‹አባዬ የተበሳጨህብኝ መስሎኝ ነበር እኮ..?.››
‹‹እሱማ ተበሳጭቼብሻለው››
‹‹በጋሼ ወልደገብርኤል ምክንያት..››
‹‹ስሙን አትጥሪብኝ …ይሄ ቅሌታም ስግብግብ…..ሰው መሰለሽ…..ፖሊስ እጅ ከመግባቱ በፊት እጄ ቢገባ እኔ እራሴ ነበርኩ ግንባሩን በሽጉጥ ማፈርስለት…እሱንማ መቼም ይቅር አልለውም….ይሄን የመሰለ ደስታዬን ለገንዘብ ሲል ነጥቆኝ ነበር እኮ››
‹‹እና በሱ ምክንያት ካልሆነ በምን ምክንያት ነው የተበሳጨህብኝ?፡፡››
‹‹ፍቅረኛ እያለሽ እንደሌለሽ ስትቀጥፊ መኖርሽ ነዋ….››
ደስ አላት… ያልጠበቀችው ነገር ስለገጠማት ተተረማምሶና ደፍርሶ የነበረው ስሜቷ ሁሉ በደቂቃዎች ውስጥ ረጋ.
‹‹አባዬ እክስሀለው›


ይቀጥላል....
8
😘ነፍስ ስታፈቅር😘

🔥ክፍል 35
.
.
‹‹አዎ በትክክልም መካስ አለብሽ…ፍቅረኛሽን በደንብ አስታሚና ቶሎ እንዲድን አድርገሽ በፍጥነት በሁለት ወይም በሶስት ወራት ውስጥ ድል ባለ ድግስ አግቢና ይብልጥ አስደስቺኝ …››
‹‹እሞክራለው አባዬ…››
‹‹እሞክራለው ሳይሆን አደርገዋለው በይ››
‹‹እሺ እንዳልክ አባዬ .አደርገዋለው››እንዳስደሰቷት አስደሰተቻቸው ተሰናብታቸው ወጣች ፡፡እናትዬው እቤት ስላልነበሩ ከቤቱ ሌላ ያናገረችው ሰው አልነበረም፡፡
መጀመሪያ ተመልሳ ወደሄኖክ ጋር ለመሄድ ነበር ያሰበችው…ሳታስበው ግን የመኪናዋን መሪ ወደ ቤቷ አቅጣጫ አዞረች፡፡ደርሳ ክላክስ ስታደርግ ተዘራ በፍጥነት ከፈተላት
ከመኪናው ስትወርድ ተንደርድሮ ፊቷ በመገተር‹‹አንዴ እትዬ ሰላም ነሽ..?እንዴት ነሽ?›ሲል ጠየቃት፡፡
‹‹ሰላም ነኝ.፡ሰፈሩስ …?ሁሉ ነገር አማን ነው?››
‹‹አረ ሰላም ነው…እሷቸው ተሻላቸው?››የሄኖክን ጤንነት ነው እየጠየቃት ያለው፡፡በአካልም ሰላማያውቀው አንተ ማለት ከብዶት ነው፡፡
አሷም እየሳቀች‹‹ሰላም ናቸው ተሸሏቸዋል››አለችውና ወደውስጥ ገባች፡፡.ወደክፍሎ ሄዳ በፍጥነት ሻወር ወስዳ ልብሷን ቀይራ በሀያ ደቂቃዎች ውስጥ መልሳ ወጣች..መኪናዋን አስነስታ ግቢውን ለቃ ልትወጣ ስትል ተዘራ አንድ ቢጫ ፔስታል ይዞ ወደእሷ ተጠጋና‹‹ እትዬ››አሏት
‹‹አቤት ተዘራ››
‹‹ሰውዬሽ ትናንት ማታ አካባቢ መጥቶ ነበር››
‹‹ሰውዬዬ ማነው?››
‹‹‹እንዴ እትዬ እንዲህ በቶሎ እረሳሽው እንዴ...?ቢላሉ ነዋ››
‹‹ወይ መጥቶ ነበር…ሰላም ነው…?አሁን እሱ ጋር ልሄድ ነበር…ምን አለ?››መአት ጥያቄ ደረደረችለት፡፡
‹‹አይ ምንም አላለም….በራፉን አንኳኳና ስከፍትለት ይሄንን ፔስታል በእጄ አስጨብጦኝ ምንም ሳይለኝ በመጣበት እግሩ ተመልሶ ሄደ
‹‹አምጣው እስቲ… ምንድነው ውስጡ ያለው?››
‹‹አላውቅም እትይ እንቺው እይው››
‹‹ተቀበለችና ከፍታ ስታየው ስድስት የሚሆኑ ጋዜጦችና ሁለት መፅሄቶች ናቸው በውስጡ ያሉት ፡፡ሁሉንም አውጥታ ታፋዋ ላይ ዘረገፈችና እያገላበጠች አየቻቸው …ሁሉም ስለእሷ ቀለበት ማሰርና ስለፍቅረኛዋ አደጋ ወዘተ የሚተርኩ ናቸው …ሁሉንም ከነፔስታሉ አንድ ላይ ጨምድዳ በመኪናው መስኮት በማሻገር እግሩ ስር ወረወረችና መኪናዋን ለማስፈንጠር ዝግጁ ሆነች
‹‹ ቶሎ በል በራፉን ክፈትልኝ ..ፍጠን››
ድንገት ጮኸችበት…ተዘራም ድንገት ምን እንደቀየራት ምንም ሳይከሰትለት ተንደርድሮ ሄደና በፍጥነት ከፈተላት.. መኪናዋን ወደነቢላል ቤት አስፈነጠረችው …ለመድረስ ስድስት ደቂቃ ነው የፈጀባት፡፡ቡዙም ስለማትቆይ መኪናዋን ወደውስጥ ማስገባት አልፈለገችም....ገብታ አይኑን አይታው ብቻ ለመውጣት ነው አመጣጧ ፡፡በራፉን አስጠገግታ አመቻችታ አቆመችና ወረደች፡መጥሪያውን በፍጥነት ደጋግማ ተጫነች..ተከፈተላት፡፡
ግቢም ሳትበል ትንደርድራ ገባች..ፕሮፌሰሯ ግን ሳሎን በራፍ ላይ ተጋርዳ ጠበቀቻት፡፡
‹‹እንዴት ኖት ፕሮፈሰር?››
‹‹ደህና ነኝ ….አንቺ ሰላም ነሽ…?ከምጣትሽ በፊት እኮ ብትደውይልኝ ጥሩ ነበር ››ቅሬታ ባዘለ ንግግር፡፡
ሲፈን ደነገጠች ..ያልጠበቀችው አቀባበል ነው ያጋጠማት፡፡
‹‹ምነው? መምጣት አልነበረብኝም እንዴ?››
‹አይ ባልሆነ መንገድ አትረጂኝ ግን..ነገሮች እዚህ ጥሩ አይደሉም..በጣም ተመሰቃቅለዋል፡፡››
‹‹ቢላል ምን ሆነ?››
‹‹ከትናንት ማታ ጀምሮ እራሱን በሰንሰለት አስሮ ክፍሉን በላዩ ላይ ቆልፎል ..የሰንሰለቱን ቁልፈ የማይገኝበት ቦታ እንድትጥለው.ለሰራተኛ ሰጥቶት ነበር.ደብቃ ሰጥታኝ አስቀምጬዋለው››
‹‹እንዴ ምን ተፈጠረ.?ደጋግሜ እኮ ደውዬ ሰላም ነው ነበር ያሉኝ›
‹‹አንቺ ለራስሽ አስጨናቂ ችግር ላይ ነበር ያለሽው ሌላ ሀሳብ ልጨምርብሽ አልፈለኩም››
‹‹አሁን ላየው አልችልም››
ይቅርብሽ..ድምፅሺን ከሰማ ይበልጥ ይረበሻል.. ››
እራሷን መቆጣጠር አቃታትና ገፈታትራቸው ወደውስጥ ገባች …ሳሎኑን ሰንጥቃ በማለፍ ወደእሱ ክፍል አመራች...ከኃላ እየተከተሎት መሆኑን ታውቆታል… ደረሰች፡፡ክፍሉ እንደተዘጋ ነው፡፡ጠንከር ያለ ድምፅ ከውስጥ ይሰማታል ...ጆሮዋን በራፍ ላይ ለጠፈች፡፡ቢላል የሚያወራው በትክክል እየተሰማት ነው፡፡
‹‹አልገድላትም….ሲፈንን አልገድላትም…እኔ ሲፈንን መግደል የለብኝም…አዎ እሷ በእኔ እጅ መሞት የለባትም…አዎ ታግባ…..ሌላ ሰው ታግባ….ብትተወኝም አልገድላትም…ሲፈን አልገድላትም…አይ አይ ገድላታለው….ገድያት መሞት አለብኝ……››ያለማቋረት ይለፈልፋል፡፡
ለምን ወደውስጥ እንዳትገባ እንደፈለጉ አሁን ተገለፀላት….ሰውነቷን ብርክ ስለያዛት ሸርተት ብላ እዛው በራፍ ስር ቁጭ አለች….ፕሮፌሰሯም በዝግታ መጣችና ከጎኗ ተቀመጠችና አቀፈቻት፡፡


ይቀጥላል...
5👍1
😘ነፍስ ስታፈቅር😘

🔥ክፍል 36
.
.
///
ሄኖክ ተኝቷል፡፡፡አሁን አደጋው ከደረሰ አንድ ሳምንት ያለፈ ሲሆን በጤናው ላይም ከፍተኛ መሻሻል ስለታየ ከጥቂት ቀናት ቡኃላ ወጣ ወጣ ማለት እንደሚጀምር ሁኔታው በደንብ ያስታውቃል፡፡:በዚህም ምክንያት ቤተሰብ ሁሉ ደስተኛ ሆኗል፡፡፡ለማገገም እንዲረዱት ሲባል የሚወስዳቸው መድሀኒቶች ተፅዕኖ ሳይሆን አይቀርም ለረጅም ጊዜ እንቅልፍ በመተኛት ነው የሚያሳልፈው..እና አሁንም ከ30 ደቂቃ በፈት ነበር እንቅቅፍ የወሰደው..ሲፈንም ከገኑ ተጋድማ መፅሀፍ እያነበበች ነው..በራፉ በስሱ ተንኳኳ
ሄኖክን እንዳትቀሰቅሰወው እየተጠነቀች በዝግታ ከአልጋዋ ወረደችና በራፉን ሄዳ ከፈተች…የሄኖክ አባት ናቸው፡፡.ከነግዙፍ ግርማ ሞገሳቸው በራፍ አካባቢ ቆመው ያንን ነጭ ሪዛቸውን በቀኝ እጃቸው ወደታች ይልጋሉ፡
ባሏ ቤት እያለ ውሽማዋ እንዳመጣባት ሴት ደንግጣ‹ጋሼ…ሰላም ነው.?.ግቡ›አለች
‹‹ተኝቷል?›ጠየቁ
‹አዎ እንቅልፍ ወስዶታል››
‹አንቺን ነበር የፈለኩት››
‹‹ምነው በሰላም››
‹‹ተከተይኝ›አሉና ከእሷ መልስ ሳይጠብቁ ፊታቸውን አዙረው ታቦት እንደተሸከመ ካህን በአርምሞ እና በስክነት መራመድ ጀመሩ፡፡
እሷም ግራ ከመጋባት ውስጥ ሳትወጣ ከኃላ ተከተለቻቸው…ከእሷቸው መኝታ ቤት ጎን ካለ ተከፍቶ አይታው ከማታውቀው ክፍል ይዘዋት ገቡ፡ሰፊም ጠባብም ማይባል ዘመናዊና ልከኛ መኝታ ቤት ነው፡፡ሁሉ ነገር በስርዓት ፀድቶ እና ተስተካከሎ ነው የተቀመጠው.፡፡አልጋውም በልዩ ጥንቃቄ ያለምንም ዝንፈት ተነጥፎል፡፡ሲገቡ አይታ ወደውስጠ ዘልቃ ብትገባም ግን በጠቅላላ ሁኔታ አሁንም ግራ እንደተጋባች ነው፡እኚን ሰውዬ በሚገርም መሳቀቅ መፍራት ከጀመረች ሰነባብታለች፡፡‹‹ዛሬ ደግሞ ምን ዱብእዳ ሊጥሉብኝ ይሆን?››ስትል ውስጧን ጠየቀች….ግን መልሱን ማግኘት የምትችለው በትዕግስት ከመጠበቅ ብቻ እንደሆነ ስለተረዳች ለመታገስ ወሰነች፡፡
‹‹ይሄ ክፍል የእሷ ነበር.ከሞተች ቡኃላ እንደተዘጋ ነው፡፡እርግጥ አልፎ አልፎ ስትናፍቀኝ ገባና እቃዎቹን ዳስሼ..ጠረኗ ያለበት አልጋዋ ላይ ትንሽ አረፍ ብዬ ከመንፈሷ ጋር አወጋና እወጣለው..ከዛ ለተወሰኑ ወራቶች ሰላሜን አገኘለው፡፡››አሉ አልጋው ተርዝ ላይ በመቀመጥ እሷም ከጎናቸው እንድትቀመጥ በምልክት እየጋበዟት
ስለማን እያወሩ እንደሆነ ወዲያው ነው የገባት‹‹በጣም ነበር የሚያፈቅሯት?››ከጎናቸው በመቀመት ጠየቀቻቸው፡፡
‹‹ቃላት ከሚገልፁት በላይ››
‹‹እሷስ?››
‹‹አትጠላኝም››
‹‹አልገባኝም?››
‹‹ እኔ እሷን ከማፈቅራት እጥፍ በሆነ መጠን የምታፈቅረው ሌላ ሰው ነበር››
‹‹የእውነቶትን ነው?››በመደነቅ ተሞልታ ጠየቀች፡፡
‹‹አዎ እውነቴን ነው.፡፡ በጣም ነበር የሚፋቀሩት… ግን ሊጋቡ አይችሉም ነበር…ሁለቱ የአንድ አባት ልጆች ነበሩ…እህትና ወንድም ነበሩ…..ፍቅራቸውን አስቀጥለው ለፍሬ ማብቃት አልቻሉም ነበር››
‹‹እና እንዴት አደረጉ?››
‹‹እንዴት ብዬ እንደማስረዳሽ አላውቅም….?ነገሩ በጣም ውስብስብ ነው፡፡››
‹‹ካንቺ ጋር የሚያያይዘው ነገር አለ ካሉኝ የግድ ዝርዝር ታሪኩን ማወቅ አለብኝ››
‹‹ትክክል ነሽ…የራስን ያለፈ ታሪከ መናገር ማለት በታሪኩ ምክንያት በልብሽ ላይ ተከትቦ የቀረውን ጠባሳ ፈግፍጓ ማድማትና ስቃይሽ በፍጥንት እንዲያግም ምድረግ ነው….ቢሆንም የግድ ስለሆነ እነግርሻለው፡፡ እኔን ያገባችኝ ለሁለት ምክንያት ነበር...የመጀመሪያው እንደማፈቅራትና ያላችኝን ሁሉ ሳላቅማማ እንደማደርግላት እርግጠኛ ስለሆነች ነው››
‹‹ሁለተኛውስ?››
‹‹ሁለተኛውማ…››ረጅም የጭንቀት ትንፋሽ ወደውጭ ተነፈሱን ንግግራቸውን ቀጠሉ‹‹….ሁለተኛውን ምክንያት ባልናገር ምርጫዬ ነበር.. እስከዛሬ ከእሷ ጋር ካልሆነ በሰተቀር ከሌላ ከማንም ሰው ጋር አንስቼ አውርቼ አላውቅም..››
‹‹ጋሼ ያው እኔም ማለት እኮ እሷ እንደሆንኩ ደጋግመው ነግረውኛል..ምነው እውነት አይደለም እንዴ?››ሳታስበው በታሪኩ ውስጥ ጠልቃ ለመግባት የጋለ ጉጉት ውስጥ ገባች፡፡
‹‹አይ ትክክል ነው...ላንቺ መንገር ሳይሆን የከበደኝ ነገሩን እራሴው ማመን ስለማልፍግ ነው…ምን መሰለሽ ሁለተኛው ምክንያት አርግዛ ነበር…ከወንድሟ ነበር ያረገዘችው››
‹‹አርግዛ ነበር..? እና አስወረደችው?››
‹‹አይ አላስወረደችውም...ቶሎ አገባዋት.. የእኔ ልጅ ሆነ››ሌላ ያልጠበቀችውን ድብእዳ አንከባለው ወደእሷ ወረrወሩ፡፡
ሰውነቷን ሙሉ ነዘራት…‹‹እና ልጁስ? ማለቴ..?››
‹‹እንዳትነግሪው…››.
‹‹ለምን ?ለማን?.››ተወነባበደች፡፡
‹‹ልጁ ሄኖክ ነው.››አፈረጡት፡፡
‹‹ከዚህ በላይ መናገር አልችልም .››አሉን ከመቀመጫቸው ተነሱና ወደ ቁምሳጥኑ ተራመዱ፡፡ የስረኛውን መሳቢያ ከፍተው አንዲት የምትባረቀርቅ አነስተኛ ሳጥን አወጡና ተመልሰው ወደእሷ በመቅረብ እንድትቀበላቸው ሳጥን የያዘው እጃቸውን ዘርግተው ‹‹እንቺ ..ይህቺ ሳጥን ከእሱ ለእሷዋ በየጊዜው እየተፃፍ ስታጠራቅማቸውና በየጊዜው እያነበበችና መላልሳ እያየቻቸው የሀዘኖ እንጉርጉሮ ማድመቂያ ሙዚቃ አድርጋ ስትገለገልባቸው የነበሩ ደብዳቤዎችና ሌሎች እቃዎቾ ናቸው..እያቸው….እና እራስሽንም እዚህ ታሪክ ውስጥ መኖር አለመኖርሽን መርምሪበት…እኚ የሰጣውሽን ሁሉ መርምረሽ ካየሽ ቡኃላ እኔ ባልኩሽ መንገድ ምንም ስሜት ካልተሰማሽ ያው ከዛሬ ወዲህ በዚህ ጉዳይ ላይ ደግመን አናወራም ማለት ነው…ይህን በተመለከተ በወቅቱ ተነግረው ነበሩ ንግርቶች ስህተት ነበሩ፡፡ እኔም እነሱን አምኜ ለዘመናት እሷን ትመጣና ዳግመኛ አይኗን አያታለው ብዬ በጥበቃ ቆፍን ተቀፍድጄ በብቸኝነት ብርድ ስንቀጠቀጥ መኖሬ ሞኝነቴ የወለደው የህይወት ዘመን ኪሳራ ነበር ማለት ነው…ለማኛውም እስክትጨርሺ ግቢው ውሰጥ ዞር ዞር ብዬ አየር ልቀበል››
‹‹ጋሼ የምን ንግርት ነው?››
‹‹እሱን ሌላ ጊዜ በሰፊው አጫውትሸለን…ግን በግርድፉ አያታቸው የታወቁ ትንቢት ተናጋሪና መንፈሳዊ ሰው ነበሩ…እና እሱ ማለት የሄኖክን አባት እሷን በማግባቷ ምክንያት በብስጭት እራሱን ማጥፋቱን ተከትሎ አባትዬው አምርረው አዝነው ሲያዩ‹‹ .አትዘን ልጄ.. .ሴቷ ልጅህም በቅርብ ተከትላው ትሄዳለች…. …ግን ሁለቱም ጀምረው ያልጨረሱት ነገር ስላለ ….መልሰው እንደሚፈጠሩ እና አስኪገናኙና የተሳካ የፍቅር ጥምረት መመስረት እስከሚችሉ ይሄንን የመወለድና የሞት የህይወት ሽክርክሮሽ እንደማያቋርጡ ተናግረዋል…. ሰውየው በህይወት ሳሉ ከተናገሩት አንድም ያልተፈፀመ ትንቢት ስሌለ እኔን ጨምሮ መላ ቤተሰቡ አምነናቸዋል፡፡ቡኃላ ስንሰማ ለሄኖክ አባትም እራሱን እንደሚያጠፋ እና መልሶ ግን ሌላ ስጋ ለብሷ ከሌላ ሰው እንደሚወለድና እሷንም በተመሳሳይ ጉዞ ላይ ሰላች እንደሚያገኛት ነግረውት ነበር ይባላል፡››
‹‹እና ይሄ ማለት እኮ በቀጥታ እረሱን እንዲያጠፋ አበረታተውታል ማለት ይቻላል…እኜ ምን አይንት መንፈስ የተፀናወታቸው ደንዳና አያት ናቸው?ለመሆኑ ይሄንን ንግርት ነው ትንቢት እሷስ ታውቅ ነበር?;
‹‹አዎ ታውቅ ነበር…››
አይ ጋሼ የተረት አለም የመሰለ ታሪክ እኮ ነው እየነገሩኝ ያሉት…ሰውዬው በሁለቱም የልጅ ልጆቻቸው ያለጊዜ ሞት ተጠያቂ ናቸው..የልጆቹን ስነልቦና መጎዳት ተጠቅመው ስውር ግድያ ፈፅመውባቸዋል፡፡ ከላይ ከላዩ ስታይው ይመስላል..ሰውየውን አንቺ ስለማታውቂያቸው ብትጠራጠሪ አይገርመኝም..እንደኔ ግን ሲናገሩ ከአንደበታቸው እየሰማሽ በማስታወሻሽ ከፃፍሻቸው ከ50 በላይ ትንቢቶች መካከል በሰላሳ አመታት , ውስጥ ከ45 በላዩ ምንም ሳይዛነፉ እንዳሉት ሆነው ብታይና የቀሩትም በመከናወን ላይ መሆናቸውን ምልክት እያየሽ
6
ቢሆን ከመሀከሉ አንዱን ነጥለሽ የምትጠራጠሪበት አቅም ይኖርሻል?…ለምሳሌ ከመሞታቸው ከአመት በፊት እራሷቸው የሚመቱበትን ቀን ሰዓቱን ከነደቂቃው እኔ በአካል ባለውበት ተናግረው ነበር.የሆነው እንዳሉት ነበር..ለዛ ደግሞ ምስክር ነኝ..ባለቤቴ በሞተች ጊዜ እምረሬ እንዳላዝን በህይወት ሳለው ተመልሳ ባላሰብኩት ሁኔታ እቤቴ ድረስ መጥታ ዳግም እንደማገኛት ነግረውኛል..ለዛም ነው ሀያአምስት አመት ሙሉ ከቤቴ ብዙም ሳርቅ መስኮት አቅራቢያና በረንዳ ላይ ሳይተክተኝ በመቀመጥ ውጭ ውጭ እያየው ስጠብቃት ማለቴ ስጠብቅሽ የነበረው››ብለው ክፍሉን ለብቻዋ ትተውላት ወጡ፡፡
አየር ወደውስጧ በረጅሙ ሳበች .መልሳ ለቀችች…መልሳ ሳበችት..ከዛ ወደውጭ መልሳ ለቀቀችው.. ከነበረችበት ቅዣት መሳይ እውነታ ውስጥ ለመውጣት እያደረገችው ያለ ጥረትነው…የተረጋጋች ሲመስላት የተሰጣትን ሳጥኑን ቀስ ብላ ከፈተች….ውስጡ በፎቶዎችና በደብዳቤዎች ተሞልቷል.. ደብዳቤዎቹን ባሉበት ትታ ፎቶዎቹን አነሳችና ለማየት ተዘጋጀች…
ልቧ ትርትር አለባት…..የሆነ የሚቀስፍ አይነት ስሜት…ትንፋሽ ሚያቆራርጥ ...ከጀርባ ማጅራትን የሚጨመድድ አስጨናቂ ስሜት….ለምንድነውእንዲህ አይነት ስሜት የተሰማት? አታውቅም፡፡. ሁለት የአስራዎቹ መጨረሻ ላይ ያሉ ልጆች እርስ በርስ ተጣብቀው የተነሷቸው ፎቶዎችን ነው የምታየው፡፡ስትገምት የሄኖክ እናትና አባት ፎቶ ነው፡፡.በፍቅር እፍ ብለው ያበዱ አፍላ ወጣቶች ፎቶ…አናም ደግሞ የእህትና ወንድም ፎቶ…፡፡እሷን ምን አስደነገጣት..?የልጁን አይን የሆነ ቦታ ታውቀዋለች….፡፡የት ነው?.በጣም ቅርቧ የሆነ ግን ደግሞ የዘነጋችው ሰው አይኖች ናቸው፡፡
ሁለተኛውን ፎቶ ማየት ጀመረች..ጎረምሳው ለብቻውን የተነሳው ነው...የሆነ ጥቅጥቅ ያለ የባህርዛፍ ደን ውስጥ ከተራራ ላይ የሚንፎለፎል ፏፏቴ ያለበት ድንቅ መልካአ ምድር ያለበት ቦታ… ውሀውን በእጆቹ እየዘገነ የተነሳው ፎቶ ነው…
ሶስተኛው የቤተሰብ ፎቶ ነው .አባተና እናታቸውን ጨምሮ ሌሎች ሰዎች ባሉበት ሁለቱ ፍቅረኛሞች ጎን ለጎን ሆነው እጃቸው ተቆላልፎ እየተያ የተነሱት…
ምንድነው ነገሩ? የምታያቸው ፎቶዎች ሁሉ ዛሬ ለመጀመሪያ ቀን እንዳየቻቸው ሳይሆን ከአመታት በፊት አገላብጣ አስኪሰለቻት አይታ ያስቀመጠችውና ዛሬ ከረሳችበት ቦታ ፈልጋ በማውጣት ከአመታት ቡኃላ ከእንደገና አቧራውን እያራገፈች እያየችው ያለ የራሷ ታሪክ ነጋሪ ፎቶ መስሎ ነው እየተሰማት ያለው…
እስኪሰለቻት እያንዳንዱን ፎቶ እያገላበጠች አየች .አዝነው በመኮሳትር የተነሱት..ተደስተው በፈግግታ የተነሱት...በጋለ ፍቅር ላይ ሆነወ የተነሱት...በኩርፊያ ተገፋፍተው የተነሱት ..ከጓደኞቻቸው መካከል በመሰራረቅ እየተያዩ የተነሱት...ከቤተሰቦቻቸው ጋር አብረው የተነሱት. በጥምቀት ጭፈራ ላይ የተነሱት….በዘመድ ሰርግ ላይ የተነሱት….ፎቶው ቁጥር ስፍር የለውም….ግን ሳትጠግብ ለጊዜውም ቢሆን ማየቱን አቆረጠችና ሰብስባ አንድ ላይ አስቀመጠች…..ከዛ ወደ ደብዳቤው ለመግባት ተዘጋጀች…
አንድን ወረቀት ከውስጡ መዘዘችና ከፈተች.. አትኩራ አየችው..ፊደሎቹ ከወረቀቱ ላይ እየተነሱ በአየር ላይ ሲከረባባቱ እየታያት ነው..የቤቱ ኮርኒስም አብሮቸው እየተገለባበጠባት ነው…ከተቀመጠችበት የአልጋው ጠርዝ .ሸርተት አለችና ወደኃላዋ ወደቀች….እሷም ልክ እንደፊደሎቹ እየተገለባበጠች በደመና ሰረገላ ተጭና ወደ ሰማየ ሰማያት ነጎደች.. ከስንት ደቂቃ ቡኃላ እንደሆነ ባታውቅም ከሆነ ከማታውቀው ፕላኔት ላይ ስትንሳፈፍ ቆይታ እንደተመለሰች አይነት ስሜት ተሰማት …ቀስ በቀስ ዓይኖቾን ስትገልጥ በቀኟ ሽማግሌው በግራዋ ደግሞ የሄኖክ እህት ከበዋት በድንጋጤና በፍራቻ ግንባሯን እና ልቧን በቀዝቀዛ ውሀ በረጠበ ጨርቅ ሲያረሰርሱላት አገኘች
‹‹ምን ሆኜ ነው?››ለመጀመሪያ ጊዜ የጠየቀችው ጥያቄ ነበር፡
‹‹ሰላም ነሽ…?ትንሽ ደክሞሽ ነው?››ሽማግሌው ናቸው የመለሱላት
‹‹እህቴ አሁን ደህና ነሽ..?.ምን ይሰማሻል?››
‹‹ምንም አይሰማኝም.. ደህና ነኝ››
‹‹ምን ላምጣልሽ…? ምን ትፈልጊያለሽ?››
‹‹ተያት አታድክሚያት .አሁን እርፍት ታድርግበት…ተነሽ እንውጣላት.››ሽማግሌው ቀድመው ተነስተው ወደውጭ መራመድ ጀመሩ…ልጅቷም ተከተለቻቸው
‹‹አንዴ ላስቸግርሽ..ቦርሳየን ከሄኖክ ክፍል ፈልጌ ነበር››
‹‹አሁን አመጣልሻለው…››ብላ ወጣች….ወዲያው አምጥታ ሰጠቻትና ብቻዋን እንድትሆን በራፉን ዘግታላት ሄደች፡፡
እየፈራች በሚንቀጠቀጥ እጇ ቦርሳዋን ከፈተች…በቀደም የልደቷ ቀን ቢላል በአናቱ በኩል በስጦታ መልክ የላከላትን መልዕክት ነው ያወጣችው...ስዕሉን እዛው ተወችና ፅሁፉን አውጥታ ገለጠች .ቅድም ከየችው ደብዳቤ ጋር ጎን ለጎን አድርጋ አስተያየችው….የፈጣሪ ያለህ !!!እንዴት የሁለት የተለያዩ ሰዎች የእጅ ፅሁፍ በዚህ መጠን ሊመሳሰል ይችላል?፡፡የአያንደንደ ፊደል ቅርፅ…የፊደል አጠጣጣሉ…መጫረሻ ላይ የሚያሳርፋችው ፊርማዎች ሳይቀሩ ፍፅም የተመሳሰሉ ብቻ ሳይሆኑ አንድ አይነት ናቸው፡፡ምን አይነት አጋጣሚ ነው?፡፡
የቢላላን ደብዳቤ ወደቦርሳዋ መልሳ አስቀመጠችና ከሳጥኑ ከወጡት ደብዳቤዎች አንዱን መዛ ማንበብ ጀመረች፡፡
//
ግንቦት 2/1976
ሁለት ጡቶችሽ መንታ እንደ ተወለዱ በሱፍ አበባ መካክል እንደሚስማሩ እንደ ሚዳቆ ግልገሎች ናቸው፡፡
መግቢያው ከመፅሀፍ ቅዱስ ነው የወሰድኩት ..
ውዴ እክፍሌ ፊት ለፊት የተከልሻቸው አበቦች አድጋውና አብበው ዛሬ የተወሰኑት ከውስጣቸው መፈንዳት ጀምረዋል.. ሌሎቹ ደግሞ ከዛም አልፋው ባለቀለም አበባዎችና ማፍራት ላይ ናቸው፡፡አበቦቹ ባንቺ ጣቶች ተዳብሰው በፍቅር የተተከሉ የተፈጥሮ ፀጋዎች ስለሆኑ በማለዳ ተነሽቼ ከማደሪያዋ እየወጣች ባለችው ፀሀይ እየተደመምኩ ስራቸውን እኮተኩታላው…የእለት ምግባቸውን በተገቢው መጠን እና አይነት ያገኙ ዘንድ አፈር አስታቅፋቸዋለው…ከጥማቸው እስኪረኩ ድረስ ተራ በተራ የጠራና የጠለለ ንፅህ ውሀ አጠጣቸዋለው፡፡እናም በወጣው በገባው ቁጥር አጠገባቸው በርከክ ብዬ በሹክሹክታ ሳላዋራቸውና ለእንቺ ያለኝን የሚንበለብ ፍቅር ሳልነግራቸው አልፌ አላውቅም፡፡እና ደግሞ በፅሞና እንደሚሰሙኝ አውቀለው….፡፡
ከንፈሮቼ ተነቃንቀው አንቺን በተመለከተ ውዳሴ ማሰማት በሚጀምሩበት ቅፅበት ቅጠሎቻቸውን ማርገብገብ ይጀምራሉ፡፡ወዲያው ደግሞ የሚያደነዝዝ ገነታዊ ማዕዛቸውን ማህደራቸውን ከፍተው በመልቀቅ አካባቢውን ሲያውዱት እታዘበለው…..የተወሰኑት አበቦች ደግሞ ከመካከላቸው ልክ ትርኢት እንደሚያሳይ አስማተኛ ቀለማቸውን እያየዋቸው ይቀያይራሉ…እያለ ይቀጥላል
መጀመሪያውን ደብዳቤ አንብባ በመጨረስ ሀለተኛውን ከፈተች...በሌላ ቀን በተለየ ስሜት የተፃፈ ነው..፡፡ለሞቾ የሄኖክ እናት ከፍቅረኛዋ ከሀያ ምናምን አመት በፊት የተፃፈ ደብዳቤ….አሁን በዚህን ሰዓት ለእሷ አንደተፃፈ የልቧን ምት እያናረ….የደም ዝውውሯን እያፈጠነ ያለ ስሜት ቀሳፊ መልዕክት እንዴት ሆነ..?ማንበቧን ቀጠለች፡፡

ነሀሴ 25/ 1978 ዓ.ም
///
እንደማህተም በልብህ
እንዳማህተም በክንድህ አኑረኝ
4