BDU-Central Students Union
5.17K subscribers
473 photos
12 videos
237 files
301 links
ይህ የባሕር ዳር ዩኒቨርስቲ የተማሪዎች ኅብረት መረጃ ማሰራጫ አውታር ነው።

Students' Union of Bahir Dar University main stream media channel.

Join to get #Latest_and_Reliable:-
#Information
#News
#Projects
#Opportunities
#Scholarships
#Trainings
#Insights

https://t.me/bducsu
Download Telegram
📢 Announcement
Safaricom Ethiopia, in collaboration with Bahir Dar University, has brought a great opportunity for the students of our university.
Through this program, students will have the chance to:
Learn online courses for free
Receive free data to support their learning
Gain valuable digital skills training
📌 Registration Requirements
Must be 5 Million Coders certified
Must have a Safaricom SIM card
Must complete SSS Training
Therefore, all students of our university are encouraged to fulfill the required information and take advantage of this opportunity.
📝 Registration Link
https://docs.google.com/forms/d/1fCbgCXwiCaECZPL4lgulci6_FTsOT4Fwl-ClRaIVwI8/edit
👉 Don’t miss this opportunity — Register now!
2
📢 ማስታወቂያ
Safaricom Ethiopia ከ Bahir Dar University ጋር በመተባበር ለዩኒቨርሲቲያችን ተማሪዎች ትልቅ የትምህርት እና የዲጂታል ክህሎት እድል አቅርቧል።
በዚህ ፕሮግራም ውስጥ ተማሪዎች፦
Online ኮርሶችን በነፃ መማር
ለመማር የሚያግዝ ነፃ ዳታ
የዲጂታል ክህሎት ስልጠና ያገኛሉ።
📌 የመመዝገቢያ መስፈርቶች
የ 5 Million Coders ሰርቲፊኬት
የ Safaricom ሲም ካርድ
SSS Training መውሰድ
ስለዚህ ሁሉም የዩኒቨርሲቲያችን ተማሪዎች አስፈላጊውን መረጃ በማሟላት የዚህን እድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ እናሳስባለን።
📝 የመመዝገቢያ ሊንክ
https://docs.google.com/forms/d/1fCbgCXwiCaECZPL4lgulci6_FTsOT4Fwl-ClRaIVwI8/edit
4
BDU-Central Students Union pinned «📢 ማስታወቂያ Safaricom Ethiopia ከ Bahir Dar University ጋር በመተባበር ለዩኒቨርሲቲያችን ተማሪዎች ትልቅ የትምህርት እና የዲጂታል ክህሎት እድል አቅርቧል። በዚህ ፕሮግራም ውስጥ ተማሪዎች፦ Online ኮርሶችን በነፃ መማር ለመማር የሚያግዝ ነፃ ዳታ የዲጂታል ክህሎት ስልጠና ያገኛሉ። 📌 የመመዝገቢያ መስፈርቶች የ 5 Million Coders ሰርቲፊኬት የ Safaricom…»
5👍3
BDU-Central Students Union
Photo
Due to technical reasons the previous call for this training doesn't work and we are forced to reannounce the call once again by cancelling the previous one.
Call for Applications for the “Youth Entrepreneurship Training” program organized by BDU-EDIC in collaboration with the Entrepreneurship Development Institute (EDI). The training aims to enhance students’ entrepreneurial mindset, innovation capacity, and practical business development skills.
In this regard, we kindly request your support in communicating and disseminating the attached poster to students at different campuses.
Key Information about Training:
·        Target Group: Active 3rd year and above Bahir Dar University students
·        Training Duration: 3 days (April 3–5, 2026)
·        Training Venues:
o   Group 1 & 2: BiT Campus
o   Group 3 & 4: CoBE Campus
o   Group 5 & 6: Peda Campus
·        Application Deadline: March 20, 2026.

Students can apply by sending an email to startup@bdu.edu.et indicating  their name, phone No., College/Faculty..., Year of study and training venue preferences (Indicated above or on the attached poster).
11👎4👍1
📢 አስቸኳይ ማስታወቂያ
Safaricom Ethiopia ከ Bahir Dar University ጋር በመተባበር ለዩኒቨርሲቲያችን ተማሪዎች ትልቅ የዲጂታል ክህሎት እና የትምህርት እድል አቅርቧል። በዚህ ፕሮግራም ተማሪዎች የOnline ኮርሶችን በነፃ መማር፣ ለመማር የሚያግዝ ነፃ ዳታ እና የዲጂታል ክህሎት ስልጠና ያገኛሉ።
📌 የመመዝገቢያ መስፈርቶች
• የ 5 Million Coders ሰርቲፊኬት
• የ Safaricom ሲም ካርድ
• SSS Training መውሰድ
⚠️ አስፈላጊ ማስታወሻ
ለፕሮግራሙ የተዘጋጀው ቦታ ውስን ስለሆነ እስካሁን ያልተመዘገቡ ተማሪዎች ዛሬውኑ በፍጥነት እንዲመዘገቡ እንጠይቃለን። ዕድሉ በቅድሚያ ለሚመዘገቡ ተማሪዎች ይሰጣል።
📝 የመመዝገቢያ ሊንክ
https://docs.google.com/forms/d/1fCbgCXwiCaECZPL4lgulci6_FTsOT4Fwl-ClRaIVwI8/edit
— Bahir Dar University Students' Union head office
👎1110🖕2
🎭 ከአንጋፋው አርቲስት ጌትነት እንየው ጋር፦

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የሲኒማና ቴአትር ጥበባት ትምህርት ክፍል የአገራችንን የጥበብ ባለውለታ አንጋፋው አርቲስት ጌትነት እንየውን በመጋበዝ ልዩ ምሁራዊ መድረክ አዘጋጅቶላችኋል።

በኢትዮጵያ የቴአትር እና የሥነ-ጽሑፍ ጉዞ ላይ ትኩረቱን የሚያደርገው ይህ መድረክ፣ ለጥበብ አፍቃሪያንና ለዘርፉ ተማሪዎች የማይታለፍ አጋጣሚ ነው።

🗓 ቀን፦ መጋቢት 09/2018 ዓ.ም
🕒 ሰዓት፦ ከሰዓት በኋላ 8:00 (2:00 PM)
📍 ቦታ፦ ፔዳ ካምፓስ፣ በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ኦዲቶሪየም አዳራሽ

ተጋባዦች፦
የዩኒቨርሲቲው ፋኩልቲ ተማሪዎችና መምህራን
የጥበብ ባለሙያዎች
ማንኛውም የሥነ-ጽሑፍና የቴአትር አፍቃሪ ሁሉ በዚህ ፕሮግራም ላይ እንዲገኙ በአክብሮት ተጋብዘዋል።

ኑ፣ ስለ ጥበብ እንወያይ!
የኢትዮጵያን የሥነ-ጽሑፍና ቴአትር ታሪክ ካለፉበት አንደበት እንስማ።

#BahirDarUniversity #BDU #GetnetEnyew #EthiopianLiterature #EthiopianTheatre #ArtAndCulture #ባህርዳርዩኒቨርሲቲ #ጌትነትእንየው
4
እንኳን ለኢድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!
ውድ የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የእስልምና እምነት ተከታይ ተማሪዎቻችንና መላው የዩኒቨርሲቲያችን ተማሪዎች በሙሉ እንኳን ለታላቁ የኢድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያልን በዓሉ የሰላም የደስታና የፍቅር እንዲሆንላችሁ የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት ልባዊ ምኞቱን ይገልጻል።
ኢድ ሙባረክ!!
መልካም በዓል!
👍2410
👍11👎72🥰1
የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት ከባህር ዳር
ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት ጽሕፈት ቤት


ባህር ዳር (መጋቢት 2018) —

በመጀመሪያ፣ የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት ጽሕፈት ቤት ለጤና ሳይንስ ኮሌጅ ተማሪዎች፣ ለተመራቂዎችና ለቤተሰቦቻቸው በሙሉ እንኳን ለታላቁ የምረቃ በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያለ ልባዊ መልካም ምኞቱን ይገልጻል። ዛሬ የምታከብሩት ድል የዓመታት የልፋታችሁና የጥንካሬያችሁ ውጤት በመሆኑ ኩራታችን ላቅ ያለ ነው።

ይህ የምረቃ መርሃ-ግብር ከመደበኛው የትምህርት ስኬት ባለፈ፣ የተማሪዎች ህብረት አመራሮች በአካዳሚክ ዘርፍም ጭምር ያላቸውን ቁርጠኝነትና ብቃት በተግባር ያስመሰከሩበት ልዩ አጋጣሚ ሆኖ ውሏል።

በዚህ በዓል ላይ የተገኙት የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት ፕሬዝዳንት አማረ ደጉ፣ በምረቃው ላይ የላቀ ውጤት ላስመዘገቡት አራት የተማሪዎች ህብረት ተወካዮች ያላቸውን ኩራት ገልጸዋል።

እነዚህ ተወካዮች፦

1️⃣አንተነህ ኑርልኝ

2️⃣ስለአባት ፈንታ

3️⃣ታምራት ታደለ

4️⃣ጥጋቡ ጫኔ
የተጣለባቸውን ከፍተኛ የተማሪዎች አገልግሎት ሃላፊነት እየተወጡ፣ በተመሳሳይ ሰዓት በትምህርታቸው እጅግ ከፍተኛ ውጤትና ማዕረግ (Great Distinction) ማስመዝገባቸውን ፕሬዝዳንቱ በደስታ ተናግረዋል።

"ዛሬ የተመረቁት የህብረታችን ተወካዮች፣ የተማሪዎች ህብረት በአገልግሎት ብቻ ሳይሆን በአካዳሚክ ደረጃም ቢሆን የተሻለና አርአያነት ያለው ስራ እንደሚሰራ ህያው ምስክሮች ናቸው፤" ሲሉ ፕሬዝዳንት አማረ ደጉ ገልጸዋል።

ፕሬዝዳንቱ አክለውም፣ እነዚህ ወጣቶች "አመራርነት በትምህርት ላይ ጫና ይፈጥራል" የሚለውን የተሳሳተ አመለካከት በመስበር ለሌሎች ተማሪዎች ትልቅ ተምሳሌት መሆናቸውን ጠቁመዋል።

በመጨረሻም፣ የተማሪዎች ህብረቱ ይህንን ድርብ ድል በማክበር ለተመራቂዎቹና ለቤተሰቦቻቸው መልካም ምኞቱን የገለጸ ሲሆን፣ በቀጣይም ህብረቱ በአካዳሚክና በአገልግሎት ዘርፍ ያለውን ጠንካራ ተሳትፎ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጧል።

ዘጋቢ፦ ቃለአብ ሰሙንጉስ
የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት የህዝብ ግንኙነት ስራ አስፈጻሚ
10🔥3👎1
👏15
የዘንዘልማ ግቢ ተማሪዎች ህብረት ስራ አስፈፃሚዎች በበጎ አድራጎት ስራ አርአያነታቸውን አሳዩ!!!

(ባህር ዳር፤ መጋቢት 21/2018 ዓ.ም)

በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የግብርና እና. አካባቢ ሳይንስ ኮሌጅ (ዘንዘልማ ግቢ) የተማሪዎች ህብረት ስራ አስፈፃሚዎች፣ ከተሰጣቸው መደበኛ የተማሪዎች ወኪልነት ስራ ባሻገር፣ በትናንትናው እለት በመስተንግዶ አገልግሎት ላይ በመሳተፍ ደማቅ የበጎ አድራጎት ስራ ማከናወናቸውን የተማሪ ህብረቱ የህዝብ ግንኙነት ዘርፍ አስታውቋል።

ቅዳሜ መጋቢት 19 ቀን 2018 ዓ.ም በተከናወነው በዚህ መርሃ-ግብር፣ የህብረቱ አመራሮች በግቢው የተማሪዎች ካፌ በመገኘት የምግብ መስተንግዶ ስራዎችን በማገዝ እናቶቻቸውንና እህት ወንድሞቻቸውን አግልግለዋል። ይህ ተግባር በግቢው ተማሪዎች ዘንድ ከፍተኛ አድናቆትን ያተረፈ ሲሆን፣ ተማሪዎችም "ይህ የአመራርነት ጥበብ እና የአንድነት መገለጫ ነው" ሲሉ ምስክረት ሰጥተዋል።

የመስተንግዶ ሰራተኞች በበኩላቸው፣ የህብረቱ ስራ አስፈፃሚዎች በራሳቸው ተነሳሽነት ወደ ስራው መሰማራታቸው ለስራ ያላቸውን ክብርና ለሰራተኛው ያለቸውን አጋርነት የሚያሳይ መሆኑን ገልጸዋል።

የዘንዘልማ ግቢ ተማሪዎች ህብረት ፕሬዝዳንት ተማሪ ፈንታሁን በጉዳዩ ላይ በሰጠው መግለጫ፣ ህብረቱ ከተማሪዎች አገልግሎት በተጨማሪ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣትና ለሌሎች ተማሪዎች አርአያ ለመሆን በቆራጥነት እንደሚሰራ አስታውቋል። ፕሬዝዳንቱም አክሎም፣ "በጎነት የጥንካሬያችን መሰረት ነው" በማለት መላው የዘንዘልማ ግቢ ተማሪዎች መሰል የበጎ አድራጎት ስራዎች ላይ እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርቧል።

የዩኒቨርሲቲው የተማሪ ህብረት የህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ይህን መሰል በጎ ተግባራት በሌሎች ካምፓሶችም ተጠናክረው እንዲቀጥሉ መልዕክቱን ያስተላልፋል።

"የእውቀት ባሕር ከጥበብ ማማ!"

ዘጋቢ፦ ቃለአብ ሰሙንጉስ
የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት የህዝብ ግንኙነት ስራ አስፈጻሚ
7👏7