Bashewam Primary & Junior School 1-8
2.75K subscribers
1.59K photos
122 videos
186 files
37 links
Bashewam School Grade 1-8
Download Telegram
ማስታወቂያ
ለ6ኛ ክፍል ተማሪዎች በሙሉ::
👉የ6ኛ ክፍል ተማሪዎች ነገ ረቡእ በቀን 03/10/2018ዓ.ም ሙሉ ቀን እስከ 9:00 ሰዓት የፈተና ግብረመልስ ወረቀት እና በት/ቤት ደረጃ ኦረንቴሽን የሚሰጥ ስለሆነ ሁላችሁም እንድትገኙ በድጋሜ እናሳስባለን::

👉ማሳሰቢያ:-በተለያዩ ምክንያት ክሊራንስ ያላጠናቀቃችሁ እና ኦርጂናል Admission Card ያልወሰዳችሁ የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች እስከ ቀን 03/10/2018 ዓ. ም በአካል በመቅረብ አጠናቃችሁ እንድትወስዱ በጥብቅ እናሳስባለን::
🫡1
👉ዛሬ በቀን 02/10/2018 ዓ. ም በት/ቤት ደርጃ ለ8ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ተፈኝ ተማርዎች ስለትምህርት ቱሩፋቶች, ስለ ስነ-ልቦና ዝግጅት,በራስ የመተማመን ሞራል ማነሳሳት እና በፈትና ወቅት መተግበር ስላለበት የፈተና ህግና ደንብ መመሪያ ዙሪያ ገለፃ(orientation)ተሰጥቷል::❤️
4
Forwarded from Mesfin Legesse
👏1🥴1
Forwarded from Mesfin Legesse
🔥1
Forwarded from Mesfin Legesse
2
Forwarded from Mesfin Legesse
4
Forwarded from Mesfin Legesse
4
👉ምክር ለተፈታኞች❤️

👉ተፈታኝ ተማሪዎች እንኳን በጉጉት ስትጠብቁት ለነበረው ፈተና  በሰላም አደረሳችሁ። ይህ ለእናንተ ወሳኝ ጊዜ ነው። እስካሁን ትምህርታችሁን እያጠናችሁ ቆይታችኋል። መልካም ነው። ነገር ግን በፈተና ወቅት የምታከናውኗቸው ተግባራትም የጥናታችሁን ያህል ውጤታችሁ ላይ ተጽዕኖ አላቸው። ስለዚህ በዚህ ወቅት ምን ማድረግ እንዳለባችሁና ምን ማድረግ እንደሌለባችሁ ጠንቅቃችሁ ማወቅ ይጠበቅባችኋል። ለዚህም ይረዳችሁ ዘንድ የሚከተሉትን ምክሮችን ከወዲሁ ተረድታችሁ ለመተግበር ዝግጁ ሁኑ!

👉 በዋዜማው ስልክ መዝጋትና ከሚረብሹ ነገሮች ራስን ማራቅ ያስፈልጋል። ስልካችሁን መዝጋት ሀሳባችሁን ሊሰርቁ ከሚችሉ ማህበራዊ ሚዲያዎች መራቅ ይገባችኋል። በዚህ ወቅት ትኩረታችሁን ፈተናችሁ ላይ ብቻ አድርጉ፤

👉 በቂ እንቅልፍ ተኙ። በፈተና ዋዜማ ለማንበብ ብላችሁ በፍጹም አታምሹ። ባጭሩ በዚህ ቀን ተጨማሪ ሰዓት ከማንበብ ይልቅ ተጨማሪ ሰዓት መተኛት የተሻለ ዉጤት አለው። በቂ እንቅልፍ አለመተኛት በፈተና ወቅት ለድብርትና ለራስ ምታት ሊዳርግና ሥራችሁን ሊያበላሽ ይችላል። ጥሩ እንቅልፍ ለመተኛት ከባድ ምግቦችን አለመመገብ፤ ብዙ ቡና አለመጠጣት፤ እና ሌሎች አነቃቂ ነገሮችን አለመውሰድ ይመከራል፤

👉ጠዋት ማልዶ መነሳት: በጊዜ ተነስቶ መዘጋጀት ከመቻኮል ጋር ተያይዞ ከሚመጣ መታወክ ያድናል። በተጨማርም ወደፈተናው አዳራሽ በጊዜ ለመድረስ ያስችላል፤

👉ቁርስ በአግባቡ መብላት: በፈተና ወቅት ቁርስ አለመብላት አእምሮአችን የሚፈልገውን ያህል ኃይል እንዳያገኝ ስለሚያደርግ ለማሰብ አቅም እንዲያንስ ያደርጋል። ስለዚህ ቀለል ያሉ ምግቦችን ተመግባችሁ መሄድ ይኖርባችኋል። ከባድ ምግቦችን መመገብ ደግሞ አእምሮአችን ምግብ የመፍጨት ሥራ ላይ ብቻ እንዲወጠር ስለሚያደርግ ድካምና እንቅልፍ ያመጣል፤

👉 ወደ መፈተኛ ቦታው ፈተናው ከሚጀምርበት ሰዓት በፊት ቀድሞ መድረስ ያስፈልጋል። ይህም ለመረጋጋት ከፍተኛ አስተዋጽዖ አለው፤

👉ከቤት ስትወጡ የፅህፈት መሳሪያዎቻችሁንና የመታወቅያ ካርዳችሁን መያዛችሁን እርግጠኛ ሁኑ። ይህም ከመንገድ ከመመለስና ከማርፈድ ያድናችኋል። ትርፍ እርሳሶችን እና የእርሳስ መቅረጫዎች መያዝ በጣም አስፈላጊ ነው፤

👉ወደ ፈተና አዳራሽ ከመግባት በፊት ወደ መፀዳጃ ቤት መሄድ መልካም ነው። ምናልባት የፈተናው ሰዓት ረዥም ቢሆንና ሽንት ቢይዛችሁ መጨናነቅን ያመጣል። አቋርጣችሁ መውጣት ላይፈቀድላችሁ ይችላል፤

👉የመልስ መስጫ ወረቀቱ ላይ ስማችሁን በአግባቡ መጻፋችሁን እርግጠኛ ሁኑ። አንድ ፊደል እንኳን ብትሳሳቱ ኋላ የት/ት ማስረጃችሁ ላይ ስለሚቀመጥ ለማስቀየር ዋጋ ያስከፍላል፤

👉መመሪያዎችን (instructions) በአግባቡ ማንበብና መተግበር ያስፈልጋል። በእያንዳዱ ፈተና ወረቀት ላይ ወይም የፈተናው ክፍሎች ላይ የሚሰጡትን መመሪያዎች በአግባቡ ማንበብና መተግበር ይኖርባችኋል፤

👉አትደንግጡ! በደንብ ተንፍሱ! ብዙ ኦክስጂን ወደ ውስጣችን ማስገባት ብዙ ምግብ እንዲቀጣጠልና ኃይል እንዲመረት ስለሚያደርግ ጉልበትና ድፍረት ይጨምርላችኋል፤

👉  አንዱ ጥያቄ ከከበዳችሁ ዝለሉት፤ አንድ ጥያቄ ላይ ተጠምዳችሁ ብዙ ጊዜ የምታጠፉ ከሆነ ቀጥለው ለሚጠብቋችሁ ጥያቄዎች ጊዜ ሊያጥራችሁ ይችላል። ስትዘሉት ግን የጥያቄ ወረቀቱ ላይ ምልክት ማድረጋችሁን እንዲሁም መልስ መስጫ ወረቀቱ ላይ ከተሰጡት አማራጮች አንዱን መልስ በግምት ማጥቆራችሁን አትርሱ። አጥቁሮ ማለፍ ምናልባት በኋላ የተሰጠው ጊዜ ቢያልቅና ወደ ጥያቄው መመለስ ቢያቅታችሁ መልስ መስጫ ቦታው ባዶ ሆኖ እንዳይቀር ያደርጋል፤

👉ቶሎ ለመውጣት አትቸኩሉ፤ ምንም አይጠቅማችሁም፤ ሰዓታችሁን አሟጥጣችሁ መጠቀማችሁን፤ ሁሉንም ጥያቄዎች በአግባቡ መመለሳችሁንና ማጥቆራችሁን አረጋግጡ። ጊዜ ቢተርፋችሁ ጥያቄዎቹን ለመከለስ ተጠቀሙበት፤

👉ያልገባችሁ ማንኛውንም ነገር ሲኖር ፈታኞችን ለመጠየቅ አትፍሩ (ከመልስ በስተቀር😉)፤

👉ልክ የፈተና ወረቀቱን ከመለሳችሁበት ጊዜ ጀምሮ የዚያ ትምህርት (subject) ነገር ማክተሙን በመገንዘብ ለቀጣዩ ፈተና እራስን ማዘጋጀት ይገባል። እንጂ፤ ስላለፈው ፈተና እያሰላልሰሉ መጨነቅ ለቀጣዩ ፈተና በምታደርጉት ዝግጅት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ያሳድራል።

🙏 ❤️መልካም የቅድመ ዝግጅት ጊዜ ይሁንላችሁ !!!❤️🙏👍
23👨‍💻2
👉Grade 6th Exam Orientation❤️
👌1
Forwarded from Mesfin Legesse
Forwarded from Mesfin Legesse
2