Bashewam Primary & Junior School 1-8
2.75K subscribers
1.59K photos
122 videos
186 files
37 links
Bashewam School Grade 1-8
Download Telegram
ለባሸዋም ትምህርት ቤት ወላጆችና ህጋዊ አሳዳጊዎች በሙሉ ፡

ውድ ወላጆች ፡ ከመንግስት በወረደው አቅጣጫ መሰረት ከሰኞ ግንቦት 24/2018 እስከ ረቡዕ ግንቦት 26/2018ዓም ድረስ ትምህርት የማይኖር መሆኑን እያሳወቅን፡ ከሀሙስ ግንቦት 27/2018ዓም ጀምሮ መደበኛ ትምህርት የሚቀጥል  እና የ6ኛ ና 8ኛ ክፍል የሞዴል ፈተና ግንቦት 27/2018ዓም የሚጀምር መሆኑን እናሳውቃለን።
👍63
BEPS. Bashewam Primary & Junior School 1-8:
ለባሸዋም ትምህርት ቤት ወላጆችና ህጋዊ አሳዳጊዎች በሙሉ ፡

ውድ ወላጆች ፡ ከመንግስት በወረደው አቅጣጫ መሰረት ከሰኞ  ግንቦት 24/2018 እስከ ረቡዕ ግንቦት 26/2018ዓም ድረስ ትምህርት የማይኖር መሆኑን እያሳወቅን፡ ከሀሙስ ግንቦት 27/2018ዓም ጀምሮ መደበኛ ትምህርት የሚቀጥል  እና የ6ኛ ና 8ኛ ክፍል የሞዴል ፈተና ግንቦት 27/2018ዓም የሚጀምር መሆኑን እናሳውቃለን።

ማሳሰቢያ
:-ነገ የቅዳሜ በቀን 22/09/2018ዓ.ም ማጠናከሪያ ትምህርት (Tutorial class) የሚሰጥ ስለሆነ ሁላችሁም አንድትገኙ እናሳስባለን::                                        ግንቦት 21/2018ዓም
12👍5
ማሳሰቢያ:-ክፍያን በተመለከተ ክሊራንስ ያላጠናቀቃችሁ አንዳንድ ተማሪዎች 👉ከፈተና በፊት ክሊራንሰ አጠናቆ በእጅ መያዝ እጅግ ወሳኝ ስለሆነ ነገ ረቡእ በቀን 26/09/2018ዓ. ም የፋይናስ ክፍል እስከ 6:30 ክፍት ስለሆነ በአካል በመቅረብ እንድታጠናቅቁ እናሳዉቃለን::
👎5👍2
👉ማሳሰቢያ:-ለ6ኛ እና ለ8ኛ ክፍል የተማሪ ወላጆች በሙሉ::
    ከላይ በወጣው  የሞዴል ፈተና መስጫ የጊዜ ሰሌዳ መሰረት👉 የ6ኛ ክፍል ተማሪዎች ከግንቦት 27- ሰኔ 01/2018ዓ. ም ሦስቱንም ቀን ጠዋት እና ከሰዓት ፈተና ያላችሁ ስልሆነ እስከ 9:00 ሰዓት ከግቢ ሳይውጡ የሚቆዩ መሆኑን እየገለፅን  👉ለ8ኛ ከፍል ተማሪዎች አርብ ግንቦት 28/2018ዓ. ም  ከጠዋቱ 5:00 ሰዓት ላይ ፈተናው እንዳተጠናቀቀ ወደ ቤት የሚለቀቁ ስለሆነ ዉድ-ወላጆች ይህን አውቃችሁ እንድትረከቧችዉና ክትትል እንድታደርጉ እያሳሰብን በሰርቪስ መሄድ የምትፍልጉ ተማሪዎች ካላችሁ ግቢ ዉስጥ ቆይታችሁ 9:00 ሰዓት ላይ መሄድ የምትችሉ መሆኑን እናሳዉቃለን::
8👍3
ማስታወቂያ
ለ6ኛ እና ለ8ኛ ክፍል ተማሪ በሙሉ::
👉የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች ማክሰኞ በቀን 02/10/2018ዓ. ም እስከ 9:00 ሰዓት የፈተና ግብረመልስ ወረቀት እና በት/ቤት ደረጃ ኦረንቴሽን የሚሰጥ ስለሆነ ሁላችሁም እንድትገኙ እያሳሰብን:-
👉የ6ኛ ክፍል ተማሪዎች ነገ ሰኞ በቀን 01/10/2018ዓ.ም ፈተና ካጠናቀቃችሁ በኃላ የፈተና ግብረመልስ ወረቀት እና በት/ቤት ደረጃ ኦረንቴሽን የሚሰጠዉ ረቡእ በቀን 03/10/2018ዓ. ም ስለሆነ ሁላችሁም በተጠቀሰዉ ቀን እንድትገኙ ከወዲሁ እናሳዉቃለን::

👉ማሳሰቢያ:-በተለያዩ ምክንያት ክሊራንስ ያላጠናቀቃችሁ እና ኦርጂናል Admission Card ያልወሰዳችሁ የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች እስከ ቀን 03/10/2018 ዓ. ም በአካል በመቅረብ አጠናቃችሁ እንድትወስዱ በጥብቅ እናሳስባለን::
6👍2
የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ መልስ መስጫ ወረቀት አጠቃቀም መመሪያ ለተማሪዎች

➊ የተማሪዎች መለያ ቁጥር እና የትምህርት ዓይነት መለያ ቁጥር ለእያንዳንዳቸው በተቀመጠው ሳጥን ውስጥ ከላይ ወደ ታች መፃፍ አለበት፡፡

❷ በተፃፈው መለያ ቁጥር ፊት ለፊት የተፃፈውን ቁጥር የያዘውን ክብ ብቻ መጠቆር አለበት፡፡

➌ ተማሪዎች የመረጡትን መልስ ትይዩ በተሰጠው ክብ ላይ በትክክል ማጥቆር አለባቸው፡፡

❹ ተማሪዎች ያጠቆሩትን መልስ መቀየር ቢፈልጉ መጀመሪያ ያጠቆሩትን ክብ በደንብ ማጥፋት አለባቸው፡፡

❺ በአንድ ረድፍ ከአንድ በላይ ክብ ማጥቆር የተከለከለ ነው፡፡

❻ ለመፃፍ እና ለማጥቆር ከተፈቀደው ቦታ ውጭ ምንም አይነት ፅሁፍም ሆነ ጭረት ማድረግ የተከለከለ ነው፡፡

❼ ለመፃፍ ከተፈቀደው ቦታ ውጭ ተፅፎ ወይም ትንሽ ጭረት እና ነጥብ ከተገኘ የመልስ መስጫ ወረቀቱ ሙሉ  በሙሉ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡

❽ መልስ በሚጠቆርበት ጊዜ እርሳሱ ከተሰጠው የክብ ሳጥን መውጣት የለበትም። ከወጣም በማጥፊያ (Eraser/Rubber) ማጥፋት ይጠበቅባችኋል።

❾ መልስ መስጫ ኮርነር ላይ ያሉትን አራት ጠርዞች መንካትም ፈጽሞ የተከለከለ ነው፡፡

➓ ተፈታኞች የመልስ መስጫ ወረቀታቸውን በንፅህና መያዝ አለባቸው ማለትም እንዳይቆሽሽ፣ እርጥበት  እንዳይነካው፤ እንዳይቀደድ እና እንዳይታጠፍ መጠንቀቅና ሙሉ ኃላፊነት መውሰድ አለባቸው፡፡
⓫ በእስክሪብቶ መፃፍ አይፈቀድም። ስለዚህ እርሳስ፣ ላጲስ እና መቅረጫ አይለያችሁ

⓬ ፈተና ጨረስኩ ብሎ አላስፈላጊ የሆነ ነገር፤ ስዕል ወይም ሌላ ከጀርባም ይሁን ከፊት አይፃፍበትም።

⓭ በጣም የተቀረፀ ሹል እርሳስ በምንጠቀም ወቅት ወረቀቱ እንዳይቀደድ መጠንቀቅ አለብን።
10👍2