Bashewam Primary & Junior School 1-8
2.75K subscribers
1.59K photos
122 videos
186 files
37 links
Bashewam School Grade 1-8
Download Telegram
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዩች በመሉ እንኳን ለ1447ኛ ኢዳል ፈጥር በዓል በሠላም አደረሣችሁ ።
በዓሉ የሰላም,የፍቅር እና የመተሳሰብ ይሁንላችሁ

መልካም በዓል
!!!
21
Forwarded from Getu Mulugeta
የ8ኛ ክፍል የክልል አቀፍ ፈተና የ2015፣2016፣ እና 2017 ጥያቀዎችን በዚህ መለማመድ ይችላሉ 👆
4👍4
Forwarded from ኢትዮ ትምህርት ነክ መረጃዎችEthio Educational information 
#​የ2018 የብሔራዊ ፈተና ዝግጅት "ካርታ" ይፋ ሆኗል! 📍

​ለተማሪዎች ትልቅ የምስራች! የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የ2018 የ12ኛ ክፍል ፈተና በምን መልኩ እንደሚዘጋጅ ይፋዊ መግለጫ አውጥቷል።
ራሳችሁን አሁኑኑ ለማዘጋጀት ይህንን መረጃ በሚገባ ተረዱት!


📚 ፈተናው የሚካተቱባቸው የትምህርት ዓይነቶች
🔬 ለተፈጥሮ ሳይንስ (Natural Science):
​እንግሊዘኛ፣ ሒሳብ፣ ስኮላስቲክ አፕቲትዩድ (Aptitude)፣ ባዮሎጂ፣ ኬሚስትሪ እና ፊዚክስ።

🌍 ለማህበራዊ ሳይንስ (Social Science):
​እንግሊዘኛ፣ ሒሳብ፣ ስኮላስቲክ አፕቲትዩድ (Aptitude)፣ ታሪክ፣ ጂኦግራፊ እና ኢኮኖሚክስ።

🔍 ፈተናው ከየትኛው ክፍል ይወጣል? (አዲሱ መመሪያ)
​በጣም ሊታወቅ የሚገባው ነጥብ እዚህ ጋር ነው! ፈተናው
👉 ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያሉትን ሁሉንም ምዕራፎች ይሸፍናል፦
👉​9ኛ ክፍል፦ የድሮውና የአዲሱ ስርዓተ ትምህርት የጋራ ይዘቶች (Common Contents) ላይ ያተኩራል።

👉​ከ10ኛ - 12ኛ ክፍል፦ ሙሉ በሙሉ በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት ላይ የተመሠረተ ይሆናል።

​ልዩ ማሳሰቢያ ለኢኮኖሚክስ፦ በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት መሠረት ከ10ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ብቻ ይወጣል።

💡 የስኬት ቁልፉ ምንድነው?
👉​አሁኑኑ ይጀምሩ፦ ከ9ኛ ክፍል ጀምሮ ያሉትን የጋራ ይዘቶች መከለስ አይርሱ።
👉​አዲሱን ስርዓተ ትምህርት ይላመዱ፦ አብዛኛው የፈተና ይዘት በአዲሱ መፅሐፍ ላይ የተመሰረተ ነው።
👉​ታማኝነት ያሸንፋል፦ የፈተና ስርቆትንና ኩረጃን በጋራ በመከላከል የለፋችሁበትን ውጤት ተቀዳጁ! 💪

🔔 ይህ መረጃ ለጓደኞችዎ እንዲደርስ "Share" ያድርጉት! አንድ ላይ ሆነን ለተሻለ ውጤት እንዘጋጅ! 🎓
#Ethiopia #Grade12 #NationalExam #Education #2018E.C #Success #Students #ኢትዮጵያ
10👍1
Forwarded from ኢትዮ ትምህርት ነክ መረጃዎችEthio Educational information 
የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የትምህርት ዓይነቶችና የክፍል ደረጃዎች ይፋ ሆኑ

# የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት በ2018 ትምህርት ዘመን 12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የሚዘጋጅባቸውን የትምህርት ዓይነቶችና የክፍል ደረጃዎችን ይፋ አድርጓል።

#በዚሁ መሠረት ፈተና የሚሰጥባቸው የትምህርት አይነቶች በተፈጥሮ ሳይንስ እንግሊዝኛ፣ ሒሳብ፣ ስኮላስቲክ አፕቲትዩድ፣ ባዮሎጂ፣ ኬሚስትሪና ፊዝክስ መሆናቸውን ገልጿል፡፡

በማህበራዊ ሳይንስ ደግሞ እንግሊዝኛ፣ ሒሳብ፣ ስኮላስቲክ አፕቲትዩድ፣ ታሪክ፣ ጂኦግራፊና ኢኮኖሚክስ ናቸው።

ፈተናው በየትምህርት ዓይነቱ ከ9ኛ ክፍል እስከ 12ኛ ክፍል ያሉትን ሁሉንም ምዕራፎች የሚሸፍን ይሆናል።

የዝግጅት አግባቡም 9ኛ ክፍል ላይ የቀድሞውና የአዲሱ ስርዓተ ትምህርቶች የጋራ ይዘት ላይ ያተኩራል።

ከ10ኛ እስከ 12ኛ ከፍል ያለው በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት ላይ የተመሠረተ ይሆናል።

የኢኮኖሚክስ የትምህርት ዓይነት በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት መሠረት ሆኖ ከ10ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያለውን የሚሸፍን መሆኑም ነው የተገለጸው፡፡

ለተጨማሪ መረጃዎች
https://t.me/moedu123
4🔥1
👉በቀን 25/07/2018ዓ.ም የወርሃዊ የስራ አፈፃፀም ግምገማ የመማር ማስተማር ሂደትን, የተማሪዎች ዉጤት ትንተና,የተማሪዎች ስነ-ምግባር, የተጕዳኝ ትምህርት እንቅስቃሴን በተመለከተ የስራ አፈፃፀም ግምገማ እና በቴክኖሎጂ የታገዘ የመማር ማስተማር ቅድመ ዝግጅትና የተማሪዎች ዉጤት አያያዝ ላይ የእዉቀት ሽግግር ተካሄደ::

👉በእለቱ ካላችዉ ምርጥ ተሞክሮ በመነሳት የእዉቀት ሽግግር ላቀረቡልን👉መ /ር ጌቱ ሙሉጌታ👉የተማሪዎች ዉጤት ትንተና ሪፖርት ላቀረቡልን 👉ም/ር/መ/ር አቶ መስፍን ለገሰ, 👉ንቁ ተሳትፎ ላደረጋችሁ 👉መ/ራን እና የት/ቤት አመራር በት/ቤቱ ስም ከልብ እናመሰግናለን::
5
Forwarded from Mesfin Legesse
2
Forwarded from Mesfin Legesse
1👍1
Forwarded from Mesfin Legesse
Forwarded from Mesfin Legesse
1