Bashewam Primary & Junior School 1-8
2.75K subscribers
1.59K photos
122 videos
186 files
37 links
Bashewam School Grade 1-8
Download Telegram
. በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው በአዲስ መልክ የተደራጀ እና ስታደርዱን የጠበቀ ቤተ- መፀሃፍት አገልግሎት መስጠት ጀመረ

.በቅርብ ቀን ደግሞ ቤተ-ሙከራዉን ይጠብቁ!!!  እስከዛው በነባሩ ቤተ-ሙከራ ተማሪዎች በንድፈ ሃሳብ የተማሩትን በተግባር ሲማሩ በከፊል!
5
4
የተማሪዎች የሥነ ምግባር ረቂቅ መመሪያ በውስጡ ምን ምን አካቷል ?

➡️ " Crazy day ፣ olds day ፣ Valentine day " እና ሌሎችም አላስፈላጊ የሆኑ ባህልን የማይገልፁ ድርጊቶችን ማክበር ይከለክላል።

መመሪያው በመንግስት ፣ መንግስታዊ ባልሆኑ ፣ የግል ፣ በኃይማኖት ተቋማት የሚተዳደሩ ትምህርት ቤቶችና ከኢትዮጵያ ውጪ ባሉ ኮሚዩኒቲ ትምህርት ቤት በሚማሩ ተማሪዎች ላይ ተፈፃሚ ይሆናል።

በመመሪያው የተማሪዎች መብትና ግዴታዎች ሲቀመጡ በተማሪዎች ግዴታ ስር ፀጉርን በአግባቡ መሰራት/ማሳጠር፣ ከተፈጥሯዊ ጸጉራቸው ውጪ እንዳይጠቀሙ ተቀምጧል።

የሴቶቾ የትምህርት ቤት የደንብ ልብስ ቀሚስ ቁመት ከባት በታች መሆን ያለበት ሲሆን ከአካባቢው ባህል ጋር የማይቃረን ልብስ መልበስ የሚለውም ተካቷል።

በመመሪያው ከተከለከሉ ተግባራት መካከል ሲጋራ ማጨስ፣ አልኮል መጠጣት፣ ጫት መቃም፣ ዕፆችን መጠቀም/ማዘዋወር እንደዚሁም ሞባይልና የሙዚቃ ማዳመጫዎችን ወደ ትምህርት ቤት ይዞ መምጣት ይገኙበታል።

በትምህርት ቤት ግቢ ውስጥ ኃይማኖታዊ አምልኮ ስርዓትና የፖለቲካ እንቅስቃሴዎችን ማከናወንም በመመሪያው ተከልክሏል።

በመመሪያው ሀገራዊ እሴት ያልሆኑ መጤ ነገሮችን በሰውነት ላይ መነቀስ ሲከለከል፤ ሴት ተማሪዎች የጥፍር፣ የፀጉርና የከንፈር ቀለም ከመቀባትና ከመኳኳል እንደዚሁም አላስፈላጊ ጌጥ ከማድረግ ይከለክላል።

በተጨማሪም በረቂቁ  በትምህርት ቤት ውስጥ አላስፈላጊ የሆኑ የኢትዮጵያዊነት ባህልን የማይገልፁ ያላቸውን ድርጊቶች ፦
• Crazy Day,
• Gentle Day,
• Olds Day,
• Baby Day,
• Fruit Day,
• Tomato Day,
• Valentine Day,
• April the full,
• Color Day,
• Pyjama Day…etc መፈጸም፤ እና ሌሎችም አላስፈላጊ የሆኑ ባህልን የማይገልፁ ድርጊቶችን ማክበር እንደማይቻል ተገልጿል።

የተከለከሉ ተግባራትን በሚፈፅመት ላይ የተለያያ የእርምት እርምጃዎች ሲቀመጡ ቀላል እርምጃ ሊያስወስዱ በሚችሉ ጥፋቶች ስር ከፀጉር ጋር የተያያዙ እና ሌሎች ቀላል ጥፋቶች ተካተዋል።

የትምህርት ቤት ፕላዝማና ኮምፒውተር ለሌላ አላማ መጠቀም፣ በአጥር መዝልና መሽሎክ፣ ከላይ የተጠቀሱ አላስፈላጊ ባህሎችን ማክበር፣ አሉታዊ ምልክቶችን መነቀስ፣ ድብድብ እንደዚሁም ኃይማኖታዊ ስርዓት መፈፀምና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ማድረግ በከባድ ጥፋት ውስጥ ተካተዋል።

የቅጣት እርከኑ እንደ ተማሪዎች የትምህርት ደረጃና ጥፋቱ ሲለያይ ለከባድ የስነ ምግባር ግድፈት በመደበኛ ህግ መሰረት የህግ ተጠያቂነት ይኖራል።

መመሪያው የዲሲፕሊን ክስ አመሰራረት፣ የዲስፕሊን ኮሚቴ ስብጥር እንደዚሁም ተግባርና ኃላፊነትን በዝርዝር አስቀምጧል።

ከዚህ ባለፈ ፦
• ትምባሆ (ሲጋራ፣ ሺሻ)
• ጫት
• አልኮል
• የናርኮቲክ እና ሳይኮትሮፒክ ዝርያ ያላቸው አደገኛ ህገ ወጥ መድኃኒቶችና ሱስ አስያዥ ዕፆች በትምህርት ቤቶችና አካባቢ መገኘት፣ መጠቀም፣ መሸጥ፣ ማብቀል፣ ማምረት ወይም መለወጥ የተከለከለ እንደሆነ መመሪያው ላይ ተቀምጧል።

እንዲሁም ፦
• የአልኮል መሸጫና ማከፋፈያ ቤቶች
• የሲጋራ መሸጫ ሱቆች
• ሺሻ ቤቶች
• ጫት መሸጫና መቃሚያ ቤቶች
• ጭፈራ ቤቶች
• ቁማር ቤቶች
• የእንግዳ ማረፊያ ቤቶች
• የሰውነት መታሻ (ማሳጅ) ቤቶች
• የፊልም ማጫዎቻ ቤቶች
• ፕሌይ ስቴሽን ቤቶች
• ዲ.ኤስ.ቲቪ ቤቶች
• ከረንቡላ ፑል
•  ጆተኒ
• ቢንጎ እና የስፖርት ቁማር መጫወቻ ቤቶችም እገዳ ተጥሎባቸዋል።

በተጨማሪም መመሪያው በየደረጃው ያሉ የባለድርሻ አካላትን ተግባርያ ኃላፊነትም ዘርዝሮ ሲያስቀምጥ ማንኛውም ትምህርት ቤት ያለ መሸኛ ተማሪዎችን ተቀብሎ መመዝገብንም ከልክሏል።

ትምህርት ሚኒስቴር በመመሪያው ላይ ምክረ ሃሳብ ያላቸው ሰዎች በ  https://forms.gle/R72ai6EiMnzZtGsC6 እንዲያቀርቡ ጠይቋል።
24👍5
ባሸዋም ትምህርት ቤት ከ1ኛ - 4ኛ ክፍል የፈተና መረሐ ግብር
👍8🤨3
የ2018ዓም የመጀመሪያው ዙር የጥያቄና መልስ ውድድር በ3ኛ እና በ4ኛ ክፍል ተማሪዎች መካከል ተካሔዷል።

ባሸዋም ትምህርት ቤት ፡ ትውልድ እንቀርፃለን፡ ሁሌም ለለውጥ ዝግጁ ነን
3
1
8