Bashewam Primary & Junior School 1-8
2.75K subscribers
1.59K photos
122 videos
186 files
37 links
Bashewam School Grade 1-8
Download Telegram
Grade 5 & 7 Final Exam. Program.
የ6ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ መልስ መስጫ ወረቀት አጠቃቀም መመሪያ

👉 የተማሪዎች መለያ ቁጥር እና የትምህርት ዓይነት መለያ ቁጥር ለእያንዳንዳቸው በተቀመጠው ሳጥን ውስጥ ከላይ ወደ ታች መፃፍ አለበት፡፡

👉 በተፃፈው መለያ ቁጥር ፊት ለፊት የተፃፈውን ቁጥር የያዘውን አራት ማዕዘን ቅንፍ (Square Bracket) ብቻ ማጥቆር አለበት፡፡

👉 ተማሪዎች የመረጡትን መልስ ትይዩ በተሰጠው አራት ማዕዘን ቅንፍ (Square Bracket) ላይ በትክክል ማጥቆር አለባቸው፡፡

👉 ተማሪዎች ያጠቆሩትን መልስ መቀየር ቢፈልጉ መጀመሪያ ያጠቆሩትን የአራት ማዕዘን ቅንፍ (Square Bracket) በደንብ ማጥፋት አለባቸው፡፡

👉 በአንድ ረድፍ ከአንድ በላይ መልስ (የአራት ማዕዘን ቅንፍ/Square Bracket) ማጥቆር የተከለከለ ነው፡፡

👉 ለመፃፍ እና ለማጥቆር ከተፈቀደው ቦታ ውጭ ምንም አይነት ፅሁፍም ሆነ ጭረት ማድረግ የተከለከለ ነው

👉 መልስ በሚጠቆርበት ጊዜ እርሳሱ ከተሰጠው አራት ማዕዘን ቅንፍ (Square Bracket) መውጣት የለበትም። ከወጣም በማጥፊያ ማጥፋት ይጠበቅባችኋል።

👉 መልስ መስጫ ኮርነር ላይ ያሉትን አራት ጠርዞች መንካትም ፈጽሞ የተከለከለ ነው፡፡

👉 ተፈታኞች የመልስ መስጫ ወረቀታቸውን በንፅህና መያዝ አለባቸው ማለትም እንዳይቆሽሽ፣ እርጥበት  እንዳይነካው፤ እንዳይቀደድ እና እንዳይታጠፍ መጠንቀቅና ሙሉ ኃላፊነት መውሰድ አለባቸው፡፡

👉 በእስክሪብቶ መፃፍ አይፈቀድም። ስለዚህ እርሳስ፣ ላጲስ እና መቅረጫ አይለያችሁ

👉 ፈተና ጨረስኩ ብሎ አላስፈላጊ የሆነ ነገር፤ ስዕል ወይም ሌላ ከጀርባም ይሁን ከፊት አይፃፍበትም።

👉 በጣም የተቀረፀ ሹል እርሳስ በመንጠቀም ወቅት ወረቀቱ እንዳይቀደድ መጠንቀቅ አለብን።
8
የተፈታኞች መብትና ግዴታ

ማንኛውም ተፈታኝ የፈተና ደንብና ሥርዓት  አከባበር እንዲሁም የመልስ ወረቀት አጠቋቆርና   ተዛማጅ ሁኔታዎችን አስመልክቶ በሚሰጡ ገለፃዎች(Orientation)ላይ የመሣተፍ ግዴታ አለበት።

⭐️ተፈታኙ በገለፃው ላይ ባለመሳተፉ ምክንያት በፈተና አሰጣጥ ዙሪያ ለሚያጋጥመው ችግር ኃላፊነቱን ይወስዳል።

ማንኛውም ተፈታኝ የፈተና ጥያቄዎቹን መስራት ከመጀመሩ በፊት በፈተና የመልስ መስጫ ወረቀት ላይ የግል መለያ መረጃዎችን በሙሉ ግልፅ በሆነ ሁኔታ በቅደም ተከተል ጽፍ ማጥቆር ይኖርበታል (በተለይ የመለያ ቁጥር እና የትምህርት አይነት ኮድ)።

ማንኛውም ተፈታኝ የራሱን ችሎታና ዕውቀት ተጠቅሞ መስራት ይጠበቅበታል::

ማንኛውም ተፈታኝ ሞባይል፣ ካልኩሌተርና የመሳሰሉ ማንኛውንም ዓይነት  የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን ይዞ ወደ ፈተና ክፍል መግባት በጥብቅ የተከለከለ ነው ።

⭐️እያንዳንዱ ተፈታኝ ይህንን አውቆ በቅድሚያ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግ አለበት ።

ይህንን ባለማድረጉ ምክንያት በፈተና አሰጣጥ ዙሪያ ለሚያጋጥመው ችግር ተፈታኙ  ራሱ ኃላፊነቱን ይወስዳል።

⭐️ማንኛውም ተፈታኝ በመፈተን ላይ እያለ ፈተናውን እንዳይሠራ የሚያውኩ ሁኔታዎች ቢያጋጥመው በፈታኙ ሲፈቀደለት ችግሩን በመግለጽ አስፈላጊውን እርዳታ ማግኘት ይችላል ይሁንና በማንኛውም ምክንያት ለባከነ ጊዜ ተጨማሪ ሰዓት አይፈቀድም

⭐️ማንኛውም ተፈታኝ ፈተናው ከሚጀመርበት ጊዜ ተኩል ሰዓት /30 ደቂቃ/ ቀደም ብለው ከመፈታኛው ቦታ በመገኘት መቀመጫቸውን መያዝ አለባቸው።

ፈተናው ከተጀመረ ከ15 ደቂቃ በኋላ የሚመጣ ተፈታኝ ወደ ፈተናው አዳራሽ መግባት አይፈቀድለትም።

⭐️ማንኛውም ተፈታኝ ፈተናው ተጀምሮ 45 ደቂቃ ሳይሞላ ፈተናውን ሠርቶ ቢያጠናቅቅም እንዲወጣ አይፈቀድለትም።

⭐️ይሁን እንጂ ፈተናው ከተጀመረ ከ45 ደቂቃ በኋላ ከፈተና አዳራሹ ለመውጣት   እንዲፈቀድለት ሲጠይቅ የመልስ ወረቀቱን ለፈታኙ አስረክቦ በጸጥታ እንዲወጣ ይፈቀድለታል።

ፈተናው ሊጠናቀቅ ከ10 ደቂቃ ያነሰ ጊዜ ሲቀረው የሚጨርስ ተፈታኝ የሁሉም ተፈታኞች የመልስ ወረቀቶች እስኪሰበሰቡና ለፈተናው የተፈቀደው የጊዜ ገደብ አብቅቶ እስኪደወል ድረስ በቦታው ተቀምጦ እንዲቆይ ይደረጋል።

ፈተናው በሚሰጥበት ጊዜ ማንኛውም ተፈታኝ ትክክለኛ ያልሆነ የተቀደደ ወይም የተበላሸ የፈተና ጥያቄ ጥራዝ ከገጠመው ወይም የተሰጠው የመልስ ወረቀት የተበላሸ ከሆነ ወይም በራሱ እጅ ቢበላሽበት እጁን አንስቶ በመጠየቅ ሲፈቀድለት ሊያስቀይር ይችላል።

ለተፈታኞች የተፈቀዱ

✍️እርሳስ
✍️የተማሪዎች የደንብ ልብስ (UNIFORM)
✍️ADMISSION CARD
✍️ላጲስ፣ መቅረጫና ማስመሪያ

ለተፈታኞች የተከለከሉ

🔠 ስልክ ይዞ መግባት አይቻልም
🔠ካልኩሌተር
🔠የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን
🔠ሰዓት
🔠በሀኪም ከታዘዘ ውጪ የሆኑ መነጽሮች
🔠የሚነበቡ ጽሁፎች በሙሉ

የፈተና ኦረንቴሽን ቀን
     በ9/10/2017 ዓ.ም እስከ 5:00 ሰዓት
ፈተናው የሚሰጥበት ጊዜ ሰኔ 10,11እና 12  /2017 ዓ.ም
10😱4
Forwarded from Asamere Lema
Forwarded from Asamere Lema
ማሳሰቢያ:-
ዉድ ተማሪዎች ት/ቤቱ ሰርቪስ ያዘጋጃ ሰልሆነ እንዳያመልጣችሁ ሁሉም ተፈታኝ ተማሪዎች ከ2:00 በፊት ባሽዋም ት/ቤት መድረስ ይጠበቅባችኋል።
✍️ በቀን 10 እና 11 ሙሉ ቀን እስከ 9:00 ሰዓት የሚቆይ ስለሆነ ምሳ ይዞ መምጣት ይጠበቅባችኅል::ሐሙስ ሰኔ12 ግን 4:30 ሰዓት ላይ የፈተናው መጠናቀቂያ ይሆናል::
  በፈተና ቀናት ጠዋት በሰዓቱ መገኘት, የት/ቤቱን ዩኒፎርም መልበስ፣እርሳስ ፣ላጲስ እና አድሚሽን ካርድ መያዝ ከሁሉም ተማሪዎች በእጅጉ የሚጠበቅ ግዴታ ስለሆነ ዉድ- ወላጆች:- ተማሪዎች ከቤት ሲወጡ የማስታወስና የማረጋገጥ ሥራ እንድትሰሩ እናሳስባለን።
  🏆 ❤️  የምንወዳችሁ እና የምናከብራችሁ ዉድ የ 6ኛ ከፍል ተማሪዎቻችን መልካም ጊዜ ነበረን...🙏❤️🏆
❤️🏆መልካም የፈተና ጊዜ ይሁንላችሁ
!❤️🏆🏆🏆
                                 ት/ቤቱ
🏆 ❤️  We had a great time with our beloved and respected 6th grade students 🙏❤️🏆
❤️🏆Have a great exam season!❤️🏆🏆🏆

 
16👍9
ለ6ኛ ክፍል የተማሪ ወላጆች በሙሉ::
✍️ሐሙስ ሰኔ 12/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት ላይ የ6ኛ ክፍል የሚኒስትሪ ፈተና ይጠናቀቃል:: ስለሆነም እንዳጠናቀቁ ወደ ቤት የሚለቀቁ ስለሆነ ዉድ-ወላጆች ይህን አውቃችሁ እንድትረከቧችዉና ክትትል እንድታደርጉ እያሳወቅን አስከ 6:00 ሰዓት ቆይታችሁ በሰርቨስ ለመሄድ የምትፈለጉ ተማሪዎች ካላችሁ ጠብቃችሁ መሄድ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን::

                                 ት/ቤቱ
Forwarded from Asamere Lema
👍41
Forwarded from Asamere Lema
3
Forwarded from Asamere Lema
👍72
Forwarded from Asamere Lema
ላለፉት ሦስት ቀናት ሲሰጥ የቆየዉ የ2017 ዓ.ም የ 6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በዛሬው ዕለት ሰኔ 12/2017 ዓ.ም በሰላም ተጠናቀቀ።
ተማሪዎች ዝግጁ ሆነው በሰዓት እንዲደርሱ ክትትል ላደረጋችሁ ዉድ ወላጆች ፣ከዝግጅት ምዕራፍ ጀምሮ ተማሪዎቹን ለፈተና ለማብቃት ንቁ ተሳትፎና የላቀ ሚና ላበረከታችሁ ዉድ-መ/ራን፣ ርዕሳነ መምህራን፣ የአስተዳደር ሰራተኞች፣ በፈተና ወቅት የተቀላጠፈ የትራንስፖር አግልግሎት ለሰጣችሁ ሾፌሮች በትምህርት ቤቱ ስም እጅግ በጣም ከልብ እናመሰግናለን!!!
          መልካም ውጤት ለተማሪዎቻችን!!!
                              ት/ቤቱ
👍95
Congratulations to All 8th grade students who have been promoted to the next grade with high scores. You can check your results using the link above.
👍24🔥4
Forwarded from Asamere Lema
1
Forwarded from Asamere Lema
🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺
🌺እስኪ እንኳን ደስ አላችሁ እንባባል!!!
2️⃣0️⃣1️⃣7 ዓ.ም ከተማ አቀፍ የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ተማሪዎቻችን በከፍተኛ ዉጤት ወደ 9ኛ ክፍል ያልፉ ሲሆን የግቢያችን ከፍተኛው ዉጤት 99.6%ሆኖ ተመዝግቧል:
:
🌺🌹እንኳን ደስ አላችሁ!!!🌺🍒
🅒︎🅞︎🅝︎🅖︎🅡︎🅐︎🅣︎🅤︎🅛︎🅐︎🅣︎🅘︎🅞︎🅝︎
🌺🌹🌺🍒
👍18🏆9
Forwarded from Asamere Lema
👍12😁4
Forwarded from Getu Mulugeta
👏34🏆20