Bashewam Primary & Junior School 1-8
2.75K subscribers
1.59K photos
122 videos
186 files
37 links
Bashewam School Grade 1-8
Download Telegram
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታይ ለሆናችሁ የትምህርት ቤታችን መምህራን፣ሰራተኞች፣ተማሪዎች እና ወላጆች በሙሉ እንኳን ለ1446ኛው የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!

ዒድ ሙባረክ !

ባሸዋም ት/ቤት

ትውልድ እንቀርፃለን፡
ሁሌም ለለውጥ ዝግጁ ነን!
4
Forwarded from Asamere Lema
2
Forwarded from Asamere Lema
.ሰኞ ሰኔ 02/2017 ዓ. ም በብስራት ት /ቤት በፈታኝ አካላት Orientation የሚሰጥ ስልሆነ አንድላይ በጋራ ለመሄድ እንዲመች ሁላችሁም ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት ላይ በት/ቤታችን ቅጥር-ግቢ (ባሽዋም) እንድትገኙ በጥብቅ እያሳሰብን ዉድ ወላጆች አስፍላጊዉን ክትትልና ቁጥጥር እንድታደርጉ እናሳዉቃለን::
                                    ት/ቤቱ
2
የተፈታኞች መብትና ግዴታ

ማንኛውም ተፈታኝ የፈተና ደንብና ሥርዓት  አከባበር እንዲሁም የመልስ ወረቀት አጠቋቆርና   ተዛማጅ ሁኔታዎችን አስመልክቶ በሚሰጡ ገለፃዎች(Orientation)ላይ የመሣተፍ ግዴታ አለበት።

⭐️ተፈታኙ በገለፃው ላይ ባለመሳተፉ ምክንያት በፈተና አሰጣጥ ዙሪያ ለሚያጋጥመው ችግር ኃላፊነቱን ይወስዳል።

ማንኛውም ተፈታኝ የፈተና ጥያቄዎቹን መስራት ከመጀመሩ በፊት በፈተና የመልስ መስጫ ወረቀት ላይ የግል መለያ መረጃዎችን በሙሉ ግልፅ በሆነ ሁኔታ በቅደም ተከተል ጽፍ ማጥቆር ይኖርበታል (በተለይ የመለያ ቁጥር እና የትምህርት አይነት ኮድ)።

ማንኛውም ተፈታኝ የራሱን ችሎታና ዕውቀት ተጠቅሞ መስራት ይጠበቅበታል::

ማንኛውም ተፈታኝ ሞባይል፣ ካልኩሌተርና የመሳሰሉ ማንኛውንም ዓይነት  የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን ይዞ ወደ ፈተና ክፍል መግባት በጥብቅ የተከለከለ ነው ።

⭐️እያንዳንዱ ተፈታኝ ይህንን አውቆ በቅድሚያ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግ አለበት ።

ይህንን ባለማድረጉ ምክንያት በፈተና አሰጣጥ ዙሪያ ለሚያጋጥመው ችግር ተፈታኙ  ራሱ ኃላፊነቱን ይወስዳል።

⭐️ማንኛውም ተፈታኝ በመፈተን ላይ እያለ ፈተናውን እንዳይሠራ የሚያውኩ ሁኔታዎች ቢያጋጥመው በፈታኙ ሲፈቀደለት ችግሩን በመግለጽ አስፈላጊውን እርዳታ ማግኘት ይችላል ይሁንና በማንኛውም ምክንያት ለባከነ ጊዜ ተጨማሪ ሰዓት አይፈቀድም

⭐️ማንኛውም ተፈታኝ ፈተናው ከሚጀመርበት ጊዜ ተኩል ሰዓት /30 ደቂቃ/ ቀደም ብለው ከመፈታኛው ቦታ በመገኘት መቀመጫቸውን መያዝ አለባቸው።

ፈተናው ከተጀመረ ከ15 ደቂቃ በኋላ የሚመጣ ተፈታኝ ወደ ፈተናው አዳራሽ መግባት አይፈቀድለትም።

⭐️ማንኛውም ተፈታኝ ፈተናው ተጀምሮ 45 ደቂቃ ሳይሞላ ፈተናውን ሠርቶ ቢያጠናቅቅም እንዲወጣ አይፈቀድለትም።

⭐️ይሁን እንጂ ፈተናው ከተጀመረ ከ45 ደቂቃ በኋላ ከፈተና አዳራሹ ለመውጣት   እንዲፈቀድለት ሲጠይቅ የመልስ ወረቀቱን ለፈታኙ አስረክቦ በጸጥታ እንዲወጣ ይፈቀድለታል።

ፈተናው ሊጠናቀቅ ከ10 ደቂቃ ያነሰ ጊዜ ሲቀረው የሚጨርስ ተፈታኝ የሁሉም ተፈታኞች የመልስ ወረቀቶች እስኪሰበሰቡና ለፈተናው የተፈቀደው የጊዜ ገደብ አብቅቶ እስኪደወል ድረስ በቦታው ተቀምጦ እንዲቆይ ይደረጋል።

ፈተናው በሚሰጥበት ጊዜ ማንኛውም ተፈታኝ ትክክለኛ ያልሆነ የተቀደደ ወይም የተበላሸ የፈተና ጥያቄ ጥራዝ ከገጠመው ወይም የተሰጠው የመልስ ወረቀት የተበላሸ ከሆነ ወይም በራሱ እጅ ቢበላሽበት እጁን አንስቶ በመጠየቅ ሲፈቀድለት ሊያስቀይር ይችላል።

ለተፈታኞች የተፈቀዱ

✍️እርሳስ
✍️የቀን ተማሪዎች የደንብ ልብስ (UNIFORM)
✍️ADMISSION CARD
✍️ላጲስ፣ መቅረጫና ማስመሪያ

ለተፈታኞች የተከለከሉ

🔠 ስልክ ይዞ መግባት አይቻልም
🔠ካልኩሌተር
🔠የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን
🔠ሰዓት
🔠በሀኪም ከታዘዘ ውጪ የሆኑ መነጽሮች
🔠የሚነበቡ ጽሁፎች በሙሉ

የፈተና ኦረንቴሽን ቀን ክፍል
በ2/10/2017 ዓ.ም
ፈተናው የሚሰጥበት ጊዜ ሰኔ 3 እና
4 /2017 ዓ.ም

                                  
7🥱3
G-8 Answer Sheet-Sample
8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና መስጫ ጊዜ ሰሌዳ
4👨‍💻1
ለ8ኛ ክፍል የተማሪ ወላጆች በሙሉ::
በቅድሚያ ለተማሪዎቻችን እንኳን በሰላም እና በጤና ለ8ኛ ክፍል ሚንስትሪ ፈተና አደረሳችሁ እያልን ከታች ባለው የከተማ አቀፍ የሚስትሪ ፈተና መስጫ የጊዜ ሰሌዳ መሰረት 
✍️ማክሰኞ ሰኔ 03/217ዓ.ም የሚጀምረዉ ፈተና  10:00 ሰዓት ላይ የሚጠናቀቅ ሲሆን
✍️ረቡዕ ሰኔ 4/2017 ዓ.ም 5:00 ሰዓት ላይ  ይጠናቀቃል:: ስለሆነም እንዳጠናቀቁ ወደ ቤት የሚለቀቁ ስለሆነ ዉድ-ወላጆች ይህን አውቃችሁ እንድትረከቧችዉና ክትትል እንድታደርጉ እናሳውቃለን::

ማሳሰቢያ:-
ሁሉም ተማሪዎች አንድ ላይ በጋራ ለመሄድ እንዲመች ከ1:30 በፊት ባሽዋም ት/ቤት መድረስ ይጠበቅባችኋል።
  በፈተና ቀናት የት/ቤቱን ዩኒፎርም መልበስ፣እርሳስ ፣ላጲስ እና አድሚሽን ካርድ መያዝ ከሁሉም ተማሪዎች በእጅጉ የሚጠበቅ ግዴታ ስለሆነ ወላጆች ተማሪዎች ከቤት ሲወጡ የማስታወስና የማረጋገጥ ሥራ እንድትሰሩ ይሁን ።
     ለተማሪዎቻችን መልካም የፈተና ጊዜ ይሁንላችሁ !
                                 ት/ቤቱ



 
11🥰1
የትምህርት ቤታችን የልዩ ፕሮግራም Special Day Program የመጨረሻውን ምዕራፍ ባማረና በደመቀ መልኩ ተከብሯል።
3👏2